Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.24K photos
359 videos
1.99K files
3.24K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ዘለቀ በላይ የኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስትያን የሚያሰራውን ባለ18 ወለል ህንጻ ነድፏል።

🚧ግንባታው መንግስታዊ ለሆነው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የመጀመርያው የአገር ውስጥ መንግስታዊ ያልሆነ አሰሪ የግንባታ ስራ መሆኑ ታውቋል።

⏺የሚፈጀው ጊዜ: 540  ቀናት
⏺የግንባታ ዋጋ ፡  803,970,655.48 ብር

🏷ዘለቀ በላይ እንደወትሮው ሁሉ በቅርጽ የበለጸገ፣የእይታ ማረፍያ የሆነ እና አነጋጋሪ የሚሆን ረጅም ህንጻ የነደፈ ሲሆን፣ ከጎኑ የቤተክርስቲያኒቱ ህንጻ የሆነው  የፍልውሀ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስትያን ህንጻ በጥር ወር መጨረሻ በ1953  (4th Feb 1961) በአጼ ኃይለስላሴ ተመርቆ የተከፈተ ከግማሽ ምእተ አመት በላይ የአዲስአበባን መሀልከተማ ውበት ሆኖ የቆየ የአምልኮ ህንጻ ሆኖ ቆይቷል።

⏺ዘለቀ በላይ ልህቀት ያላቸውን ህንጻዎች በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የተለያዩ ካምፓሶች ውስጥ የገነባ ሲሆን ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ በመዲናችን ውስጥ ለየት ባለ ፍልስፍና የተሞሉ በጥበብ የነደፋቸውን ህንጻዎች ለእይታ እያበቃ መሆኑ ይታወቃል።

⏺ዘለቀ በላይ በአዲስ አበባ እና በፊንላንድ የተማረ ህንጻ ነዳፊ ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአርክቴክቸር ዲፓርትመንት ውስጥ የንድፍ ትምህርትን  ለረጅም ግዜ አስተምሯል።

⭐️በኪነህንጻ ውስጥ ያሉ የጎንዮሽ እና አግድም መተላለፍያዎችን አግንኖ ከመንደፉም በላይ ለአጠቃላይ የኪነህንጻዎቹ ቅርጽ ልዕልና ሲባል መደበኛ የገጽታ ክፍተቶችን የማይጠቀም መሆኑን  እናስተውላለን።

💫በዚህም ምክንያት እይታዊ ቅኔን ያዘሉ፣ሚዛናቸውን ለመረዳት የሚያዳግቱ፣ጥያቄ ጫሪ እና አነጋጋሪ ህንጻዎችን በመንደፉ የታወቀ ስመጥር ኢትዮጵያዊ ህንጻ ነዳፊ ነው።

@etconp
❤24🔥2👍1
👉አዲስ አበባ ህንፃዎቿም፣ መኖሪያ ቤት አጥሮቿም ንግድ ቤቶቿም ተመሳሳይ ቀለም ተቀብተዋል፤ እየተቀቡም ነው፡፡

🚧ይህም ህንፃን ከህንፃ ለመለየት እንኳን አስቸጋሪ ሲያደርገው ይታያል። አሰራሩ ወደ ሌሎች ከተሞችም እየተዛመተ ነው፡፡

⏺ይህንን የቀለም ቅብ ጉዳይ እንዴት ይታያል ስንል የዘርፉ ባለሞያን ጠይቀናል፡፡

🏷ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ የቀለም ቅብ ሳይንስ ባለሞያ ናቸው። እሳቸውም ከሌሎች ያደጉ ሃገራት ልምድ አንፃር ከተማን አንድ ወጥ ቀለም መቀባት በሞያው አይመከርም ይላሉ።

⏺ባለሞያው በተለየ ምክንያት ከፍተኛ የፀሐይ ሙቀትና በረሃማ የአየር ንብረት ውስጥ ያሉ ከተሞችን የሙቀት መጠን ለመቀነስ ካልሆነ በቀር እንደ አዲስ አበባ ያሉ ከተሞችን ተመሳሳይ ቀለም ማልበስ ቀለም ከማህበረሰብ ጋር ያለውን የታሪክ፣ የስነ ልቦና እና የፍልስፍና መስተጋብር ሳይንሳዊ ትርጉም ይጣረሳል ይላሉ።

⏺በከተማ የቀለም ቅብ ሳይንስ (Urban color planning) ህግ ስርዓት ያልጠበቀ ዥንጉርጉር የከተማ ቀለም ቅብና በተቃራኒው ደግሞ የአንድ አይነት ወጥ የቀለም ቅብ አይፈቀድም የሚሉት ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ ሌሎች የክልል ከተሞች እንደ አዲስ አበባ ወጥ ቀለም ሳይሆን አከባቢያዊ የከተማ ቅብ ስርዓትን (zonal coloring system) እንዲጠቀሙ መክረዋል።

⏺ባለሞያው አከባባያዊ የከተማ ቀለም ቅብ ስርዓት፤ በአንዲት ከተማ ውስጥ ያሉ ሰፈሮችን ታሪክ፣ የማህበረሰብ ስነልቦናና ፍልስፍና ማስረዳት ይችላል ነው የሚሉት።

💫ሙሉ ዘገባውን በድምጽ ያድምጡ👇
https://www.mixcloud.com/ShegerFM/tgh5r/

Via Sheger Radio

@etconp
👍6❤4🔥2🥰1
👉የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ ኮሚቴ የሥራ አፈጻጸም ተገመገመ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ ኮሚቴ የሥራ አፈጻጸሙ የሁለቱም አካላት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተገምግሟል፡፡

የጋራ ኮሚቴው የጋራ መግባባትና ውሳኔ በሚስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጎ የመፍትሔ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

ኮሚቴው ያከናወናቸው ተግባራትም የአዲስ አበባ ከተማ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ እንደሆነ ነው የተገመገመው፡፡ በኮሪደር ልማቱ የታየው ትብብር እንደ አብነት በጥንካሬ ተግምግሟል፡፡

በይዞታ ማስተላለፍ እና በካሳ ክፍያ ረገድ ያሉ ችግሮችም የጋራ ኮሚቴው ለመፍታት ስምምት ላይ ደርሷል፡፡ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ይዞታ የሕዝብና የመንግስት ሀብት በመሆኑ በጋራ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ የጋራ ኮሚቴው አጽኖት ሰጥቶበታል፡፡

ልማትና የላቀ የሕዝብ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ የጋራ ውሳኔዎች በመወሰን የአዲስ አበባ ከተማን በጋራ ለማልማት ትኩረት እንደሚደረግ ነው የጋራ ኮሚቴው የገለጸው፡፡

በሁለቱ አካት ባለው የእርስበርስ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያም ሰፊ ግምገማ ከተደረገ በኋላ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

የጋራ ኮሚቴው፡- ጥምር የቴክኒካል ኮሚቴው ተጨማሪ ሥራ በሚጠይቁና ያልተፈቱ ችግሮችን ለይቶ እንዲያቀርብ አቅጣጫ በማስቀመጥ ግማገማውን አጠናቋል፡፡

@etconp
❤14👍1
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

♧ ሁሉን በአንድ ቦታ ለሁሉም ቅርብ

♧ ምስክራችን ስራችን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

♧ ይደውሉልን ያማክሩን

0904040477
0994941708
🔥2
Ethio Construction Engineering
👉SOIL STABILIZATION: 💫Soil stabilization is a technique of increasing or maintaining stability of soil mass. 🚧Methods of soil stabilization: 1. Mechanical stabilization: It is by suitable grading or by compaction. Mechanical stabilized construction needs…
👉STABILISATION OF SOIL WITH ADDITIVES:

💫Stabilisation of soil with some kind of additive is very common.

⏺The mode and degree of alternation necessary depend on the nature of the soil and its deficiencies.

⏺If additional strength is required in the case of cohesionless soil, a cementing or a binding agent may be added and if the soil is cohesive, the strength can be increased by making it moisture-resistant, altering the absorbed water films, increasing cohesion with a cement agent and adding internal friction.

🚧Compressibility of a clay soil can be reduced by cementing the grains with a rigid material or by altering the forces of the adsorbed water films on the clay minerals.

⏺Swelling and shrinkage may also be reduced by cementing, altering the water adsorbing capacity of the clay mineral and by making it moisture-resistant. Permeability of a cohesionless soil may be reduced by filling the voids with an impervious material or by preventing flocculation by altering the structure of the adsorbed water on the clay mineral; it may be increased by removing the fines or modifying the structure to an aggregated one. 

⏺A satisfactory additive for soil stabilisation must provide the desired qualities and, in addition, must meet the following requirements: Compactibility with the soil material, permanency, easy handling and processing, and low cost.

⏺Many additives have been employed but with varying degrees of success. No material has been found to meet all the requirements, and most of the materials are expensive.

@etconp
❤4
👉በ1.2 ቢሊዮን ብር የሚገነባው የቴፒ-ሚዛን የመንገድ ግንባታ በሚቀጥለው ዓመት ይጠናቀቃል

🚧በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግንባታው በመካሄድ ላይ የሚገኘው የቤንች ሸኮን እና የሸካ ዞኖችን የሚያገናኝ የቴፒ-ሚዛን 47.87 ኪሎ ሜትር አስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በቀጣዩ በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡

💫በእስካሁኑ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣የማፋሰሻ፣ የስትራክቸር፣የሰብ ቤዝ እና የቤዝ ኮርስ ንጣፍ እንዲሁም 25 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ንጣፍ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

⏺የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱን እያከናወነ የሚገኘው ቻይና ግዞባ ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (CGGC) የተባለ የቻይና የስራ ተቋራጭ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራው ደግሞ ፕሮሚነንት ኢንጂነሪንግ ሶሉሽንስ አማካሪ ድርጅት አማካኝነት በመካሄድ ላይ ነው።

⏺ለግንባታው ማስፈጸሚያ የሚውለውን 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በኢትዮጵያ መንግሠት የተሸፈነ ነው።

⏺አሁን ላይ የሥራ ተቋራጩ ከአጠቃላይ ሥራው 31.6 ኪሎ ሜትር ወይም 66 በመቶውን ያጠናቀቀ ሲሆን የፕሮጀክቱን ቀሪ ሥራዎችም በሚቀጥለው በጀት አመት ለማጠናቀቅ እየሠራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታውቋል፡፡

@etconp
👍7❤3
👉JOB VACANCY

🏷Miraj Abubaker General Contractor

🚧We Need👇

💫Architect

💫Office Engineer

@etconp
🥰2❤1🔥1👏1
👉የተሰበረ ወይም የተጋነነ የጨረታ ዋጋ (Unusually Low or Excessively High Bid Prices) በአዲሱ የግዥ መመሪያ

🚧የተሰበረ ወይም የተጋነነ የጨረታ ዋጋን (Unusually Low or Excessively High Bid Prices) በተመለከተ በአዲሱ የግዥ መመሪያ አንቀጽ 123 የሚከተሉትን ዝርዝር ነጥቦች ይዟል።

1. የዕቃ ግዥን በተመለከተ በተጫራቹ የቀረበው የጨረታ ዋጋ እንደቅደም ተከተላቸው ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በሚገኝ የዋጋ መረጃ፣ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የዋጋ መረጃ እንደሌለ ማረጋገጫ በሚሰጥበት ጊዜ እንደሁኔታው ከታወቀ አምራች፣ ይህም ካልሆነ ከመሥሪያ ቤቶች በሚቀርብለት ጥያቄ መነሻ ባለስልጣኑ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በማዕከል በሚከናወን የገበያ ዋጋ ጥናት መሰረት በሚገኘው የገበያ ዋጋ ጋር በአንጻራዊነት ሲታይ የቀረበው ዋጋ ከ10% (አስር በመቶ) የበለጠ ሲሆን እንደተጋነነ የጨረታ ዋጋ እንዲሁም የቀረበው ዋጋ ከ30% (ሰላሳበመቶ) ያነሰ ሲሆን እንደተሰበረ የጨረታ ዋጋ ይቆጠራል፡፡

2. የምክር እና ከምክር ውጭ የሆነ የአገልግሎት ግዥን በተመለከተ ከመሥሪያ ቤቶች በሚቀርብለት ጥያቄ መነሻ ባለስልጣኑ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በማዕከል በሚከናወን የገበያ ዋጋ ጥናት መሰረት በሚገኘ የገበያ ዋጋ ጋር በአንጻራዊነት ሲታይ የቀረበው ዋጋ ከ10% (አስር በመቶ) የበለጠ ሲሆን እንደተጋነነ የጨረታ ዋጋ እንዲሁም የቀረበው ዋጋ ከ20% (ሃያ በመቶ) ያነሰ ሲሆን እንደተሰበረ የጨረታ ዋጋ ይቆጠራል፡፡

3. የግንባታ ግዥን በተመለከተ በተጫራቹ የቀረበው የጨረታ ዋጋከምህንድስና ግምት ዋጋ ጋር በአንጻራዊነት ሲታይ የቀረበው ዋጋ ከ15% (አስራ አምስት በመቶ) የበለጠ ሲሆን እንደተጋነነ የጨረታ ዋጋ እንዲሁም በተጫራቹ የቀረበው የጨረታ ዋጋ ከምህንድስና ግምት ዋጋ ጋር በአንጻራዊነት ሲታይ የቀረበው ዋጋ ከ20% (ሃያ በመቶ) ያነሰ ሲሆን እንደተሰበረ የጨረታ ዋጋ ይቆጠራል፡፡

4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት ለማወዳደሪያነት የሚውለው የምህንድስና ግምታዊ ዋጋ በግዥ ፈፃሚ የመንግስት መ/ቤቱ የተዘጋጀ እና ለግንባታው ግብዓት የሚሆኑ ሁሉም ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በሚገኘው የዋጋ መረጃ፣ የስታትስቲክስ አገልግሎት የዋጋ መረጃ እንደሌለ ማረጋገጫ በሚሰጥበት ጊዜ እንደሁኔታው ከታወቀ አምራች፣ ይህም ካልሆነ ከመሥሪያ ቤቶች በሚቀርብለት ጥያቄ መነሻ ባለስልጣኑ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በማዕከል በሚከናወን የገበያ ዋጋ ጥናት መሰረት የተዘጋጀ እና ቢያንስ በሦስት ወራት ውስጥ ወቅታዊ የተደረገ መሆን አለበት፡፡

5. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1፣ 2 እና 3 መሰረት ከተጫራቹ የቀረበው ዋጋ የተጋነነ ሆኖ ሲገኝ የመንግሥት መ/ቤቱ በአዋጁ አንቀጽ 26 (1(መ)) መሰረት ውል ከመፈረሙ በፊት ጨረታውን ወይም የመጫረቻ ሰነድን በማናቸውም ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ውድቅ ማድረግ አለበት፡፡

6. የመንግስት መ/ቤቱ በዚህ መመሪያ እና በመደበኛ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሠረት ተጨማሪ ምርመራ ሳያከናውን የቀረበው የጨረታ ዋጋ የተሰበረ በመሆኑ ምክንያት ብቻ ተጫራቹን ከውድድሩ ውጭ ማድረግ የለበትም፡፡

7. የመንግስት መ/ቤቱ በቀረበው የጨረታ ዋጋ ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ እንዲያስችለው የተሰበረ የጨረታ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች ዝርዝር ማብራሪያ እና ተያያዥ ሰነዶች እንዲያቀርብ መጠየቅ አለበት፡፡

8. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት መ/ቤቱ የሚጠይቀው ማብራሪያ ሌሎች በመደበኛ የጨረታ ሰነዱ ከሚገለጹት ነጥቦች በተጨማሪ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ሊያካትት ይችላል፡፡

ሀ/ተጫራቹ ባቀረበው ዋጋ ጥራቱንና የመ/ቤቱን ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ ለማመጠናቀቅ የሚያስችለው
ለ/ሥራውን ማከናወን ወይም አቅርቦቱን መፈጸም የሚያስችለው የተለየ ዘዴ ያለው ስለመሆኑ፣
ሐ/ሥራውን ወይም አቅርቦቱን በዚህ ዋጋ ለመስራት ወይም ለመፈጸም የሚያስችለው የተለየ ምቹ ሁኔታ ወይም ሙያዊ መፍትሔዎች ያለው ስለመሆኑ፣እንዲሁም
መ/ ተጫራቹ ከዚህ ቀደም ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የገባቸውን ውሎች እና አፈጻጸም የሚያሳይ መግለጫ እና ሰነዶች፣

9) በአዋጁ፣ በዚህ መመሪያ እና በመደበኛ የጨረታ ሰነዱ ድንጋጌዎች መሰረት መ/ቤቱ በዚህ ረገድ የሚወስዳቸው
ውሳኔዎች እንደተጠበቁ ሆኖ መንግስት መ/ቤቱ ከተጫራቹ ማብራሪያ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ
ቀናት ጊዜ ውስጥ ከተጫራቹ የቀረበውን ሀሳብ ተቀባይነት ስለማግኘቱ ወይም ስላለማግኘቱ ውሳኔውን
ለተጫራቹ ማሳወቅ አለበት፡፡

10) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 9 መሰረት ከተጫራቹ የቀረበውን ኃሳብ የማይቀበለው ከሆነ የመንግሥት መ/ቤቱ በአዋጁ አንቀጽ 26 (1(መ)) መሰረት ውል ከመፈረሙ በፊት ጨረታውን ወይም የመጫረቻ ሰነድን በማናቸውም ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ውድቅ ማድረግ አለበት፡፡

@etconp
❤19👍7
👉የግንባታ ባለአሻራው አረፉ

💫ከ 1950 ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ በነበሩት አልቤርቶ ቫርኔሮ ማረፋቸው ተሰማ።

ከታሪካዊ ሥራዎቻቸው መካከል የአፍሪካ አዳራሽ (የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን)፣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ሂልተን ሆቴል፣ ሚሊኒየም አዳራሽ፣ የጅማ አባጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ማሻሻያ፣ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት፣ የአንድነት ፓርክ እና የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ሥራ ይገኙበታል።


ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ህልፈታቸውን አስመልክቶ፦ "ሥራቸው የሀገራችንን የግንባታ ከባቢ እና ታሪካዊነት ያላቸው ምልክቶችን ላቅ ባለ ደረጃ የቀረፀ ነው፤ የተሰማኝን ሀዘን ለመግለጽ እፈልጋለሁ" ብለዋል።

ጨምረውም፦ የሥራ ውርሳቸው በነዚህ ብሔራዊ ምልክቶች እና በሚወክሉት የእድገት ትእምርት ሲታወስ ይኖራል። ለነፍሳቸው ረፍትን፣ በረፍታቸው ላዘኑ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን ሲሉ ገልጸዋል።

@etconp
😭10❤7👍2
👉 INTERCON Construction Chemicals 

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Wall Putty, Prime Coat
● Concrete Repair Mortar
● Floor hardener, Epoxy
● Grout, Self-level mortar
● Quartz paint, Contextra
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Geotextiles and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555
Address: Signal, around signal mall
❤2👍2🔥1