Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.22K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
🏭🏠TSEGAYE and YOHANNES J-ቦልት & PLATE 🏚🏗 🌁🌆

🧿 የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ⤵️

🔲Plate at any Size & thickness.

⚙️  J-Bolt height and diameter    you want it.

🔩 anchor ⚓ bolt at any size

🏭🛖🌉scrap(ተረፈ-ምርት)🚧🪝

🔗 ቁርጥራጭ ፌ ሮካሎት መጥተን በኪሎ እንዳስፈላጊነቱ በሜትርም እንገዛለን።
Phone : 🤳0938494506 
              🤳 0951087077
              🤳 0929044037
እናመሰግናለን::
👉አድራሻ፦  መርካቶ ምንአለሽ ተራ ከጭድ ተራ ከፍ ብሎ

https://t.me/tsegaye2016Jbolt
❤2👍1
👉አለም አቀፍ ንድፍ ውድድር አሸናፊዎቹ ኑሀሚን እና ሳሙኤል።

💫የ አፍሪካ አርክቴክቶች ማህበር ለኪነህንጻ ለተማሪዎች "Emergency Response for Shelter Design For Displaced People in Africa" በሚል በአፍሪካ ለሚገኙ ተፈናቃይ ሰዎች መጠለያ  ያዘጋጀውን አለምአቀፍ የንድፍ ውድድር  የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አርክቴክቸር ትምህርት ክፍል አምስተኛ አመት ተማሪ የሆኑት ኑሀሚን ደሳለኝ እና ብርሀኑ ተክለማርያም ከምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪዎች አንደኛ በመውጣት አሸንፈዋል።

ከምስራቅ አፍሪካ ቀጣና አንደኛ የወጣ ንድፍ።
የንድፍ ርዕስ "መጠለያን እንደዘር"
"Shelter as a seed"
ER-02-NSA -1ST RUNNER UP - EAST REGION

‹‹አንድ ሰው ቤት መሥራት ሲያቅተው አሥር ሰዎች ግን  መንደር መሥራት ይችላሉ›› በሚለው ጥበባዊ  አባባል ተነሳስተን  የነደፍነው  የመጠለያ ንድፋችን ከመጠለያነት አልፎ፣ የበለፀገ ማኅበረሰብን ያጎለብታል ብለን እናስባለን።  ንድፋችንን የተፈናቀሉ ሰዎች አካባቢያቸውን በጋራ እንዲቀርጹ ወደሚያስችል  የባሕላዊ ገጽታ አሸጋግረነዋል።

እስቲ አስቡት : የነደፍነው አንድ ነጠላ ቤት ብቻ ሳይሆን ለዕድገት የሚሆንን ዘር ነው ያዘጋጀነው። ስደተኞች  በታወቁ የአካባቢ ቁሳቁሶች በመጠቀም እና በተፈጥሮ እውቀታቸው እየተመሩ የመጠለያቸው ግንባታ ንቁ ተሳታፊ ይሆናሉ።

ይህ ንድፍ  መጠለያ ብቻን  ሳይሆን ያቀፈው ግለሰቦች ማህበራዊ አስተዋፅዖ በማድረግ ወደሚከበሩበት፣ እና የጋራ ተግባር የሚያብብበት  ደማቅ የጋራ ተስፋ የሚሰጥ መልክዓ ምድር  መንደር ጭምር ነው።  ። 

የንድፋችን ፍሬ ነገር የሚከተለው ነው።   " በህዝቡ ትብብር የተገነባ ፣ በህዝቡ መንፈስ  የተቃኘ ፣  እና በብሩህ የወደፊት ተስፋ የሚያብብ የመንደር ዘር ነው።

ንድፍ ቡድን አባላት።
ኑሀሚን ደሳለኝ እና ብርሀኑ ተክለማርያም
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የአርክቴክቸር እና ከተማ ፕላን ትምህርት ክፍል።

የ ኢትዮጵያ አርክቴክቸር እና አርባኒዝም ለኑሀሚን እና ብርሀኑ የሚከተለውን ቃለመጠይቅ አድርጎ ነበር። *

ኢአአ። (ኢትዮጵያ አርክቴክቸርና አርባኒዝም) ስለውድድሩ ከየት ነው የሰማችሁት?

"ኑሀሚን እና ብርሀኑ"   ስለ ውድድሩ የሰማነው ከ Ethiopian architecture construction and urbanism ቴሌግራም ገጽ ላይ ነበር።

"ኢአአ"።  ስንት ቀን ፈጀባችሁ?

"ኑሀሚን  እና ብርሀኑ "  ። የፈጀብን ቀን ከ December 22 አሰከ February 23 ነበር

"ኢአአ"።  የስንተኛ አመት ተማሪዎች ናችሁ?
"ኑሀሚን  እና ብርሀኑ " ። 5 ተኛ አመት ተማሪዎች ነን

"ኢአአ"።  እንዴት ሁለታችሁ በግሩፕ ሰራችሁ?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ "። ሌላ አነስ ያሉ ታስኮችን አብረን ስንሰራ ስለነበር እናም ስለምንግባባ አብረን ውድድሩን ለመሞከር ወሰንን፣ በተጨማሪም የ software skill ላይ ጥሩ ስለሆንን

"ኢአአ"። ሌላ ከአርባምንጭ የተወዳደሩ ተማሪዎች አሉ?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ "። የተመዘገቡ ብዙ ተማሪዎች ነበሩ ውድድሩን እስከመጨረሻ የሄዱ ሌላ 3 ተማሪዎች ነበሩ (አናን ኤልያስ፣ በጸሎት ወንድይፍራው እና ሃይለኢየሱስ ሲሳይ) ይሄ እኛ የምናውቀው ነው።

"ኢአአ"። ሌላ በሀሳብ ያገዛችሁ ሰው አለ?
"ኑሀሚን  እና ብርሀኑ "  አርኪቴክት አዲሱ አዱኛ እና አርኪቴክት ኤሊያስ ጀማል በአጠቃላይ አባ አርኪቴክትስ። እንዲሁም አብሮን በአንድ ክፍል  የሚማረው  ጉቱ ደጉ በብዙ ሀሳብ ሲረዳን ነበር።

"ኢአአ"።  እንዴት አባ አርክቴክት ስ በሀሳብ አገዟችሁ?
"ኑሀሚን  እና ብርሀኑ" ። Internship እዛ ነበር የወጣነው።

"ኢአአ" ። ማሸነፋችሁን ስትሰሙ ምን ተሰማችሁ?
"ኑሀሚን እና ብርሀኑ"። ማሸነፋችን ስንሰማ የነበረው ደስታ ልዩ ነበር ምክንያቱም ከተወሰነ 100 በላይ ተወዳዳሪዎች ነበሩ እንዲሁም ብዙ የደከምንበት ስለነበር ነው።

"ኢአአ"  ከዚህ በፊት የዲዛይን ውድድር ተወዳድራችሁ ታቃላችሁ?
"ኑሀሚን  እና ብርሀኑ"። አዎ በ 120 HOURS it was National Art Museum for Andorra. in this competition we can not get in the finalist list and we are searching for other competition with free entry

"ኢአአ" ። ብርሀኑ ከአርክቴክቸር ምን ደስ ይልሀል?
የምታደንቀው ኢትዮጵያዊ አርክቴክት ማነው? አለምአቀፋዊስ?  የምታደንቀው አሁናዊ ህንጻስ?

"ብርሀኑ"። ከአርክቴክቸር እኔ የምወደው ሁሌም አዲስ ነገርን አገኝበታለሁ ሁሌም እየተማርኩበት ነው ምሄደው ሌላው ምንም ነገር እንደሚቻል ያስተማረኝ ነው።

ከኢትዮጵያ የማደንቃቸው አርክቴክቶች ብዙ ቢሆኑም አንድ ለመጥቀስ ያህል አርክቴክት አሃዱ አባይነህ፣ ከውጪ ደግሞ Bjarke Ingels.

የማደንቀው አሁናዊ ህንጻ ደግሞ የ አርክቴክት ዘለቀ በላይ ቦሌ ላይ የነደፈው ህንጻ Nile Source ህንጻ

"ኢአአ"  ኑሀሚን ከአርክቴክቸር ምን ደስ ይልሻል?
የምታደንቂው ኢትዮጵያዊ አርክቴክት ማነው? አለምአቀፋዊስ?  የምታደንቂው አሁናዊ ህንጻስ?

"ኑሀሚን" ። አርክቴክቸር ለኔ ነግሮችን በብዙ dimension እንዳይ አስችሎኛል፣ የተለያዩ skill እንዳዳብር  በብዙ ያደርገናል  ፣ ሌላው creative የሆነ mind እንዲኖረን ያደርጋል
ከኢትዮጵያ የማደንቀው  አርክቴክት አለበል ደስታ። ከውጪ ደግሞ Zaha Hadid።
የማደንቀው አሁናዊ ህንጻ ደግሞ በአለበል ደስታ የተነደፈው ለ ET 302 memorial ህንጻ።

"ኢአአ" ለሴት አርክቴክቸር ተማሪ የምታስተላልፊው መልዕክት አለ?

"ኑሀሚን"። የጀመራችሁበትን ምክንያት፣ የነበራችሁን ውስጣዊ መነሳሳት እና ፍላጎት ሁሌም አስታውሱ ምክንያቱም ካሰብንበት ለመድረስ ትልቅ ሀይል የሚሰጠን የጀመርንበት ምክንያት ነውና

" ኢአአ" አመሰግናለሁ።

"ኑሀሚን  እና ብርሀኑ" እኛም እናመሰግናለን።

(* ቃለ ምልልሱ በመጋቢት ወር መጨረሻ አካባቢ የተደረገ ነበር)

Via ethiopian architecture and urbanism

@etconp
❤20
👉FIDIC Contracts Explained… The Color Codes in 1 Minute!

💫FIDIC contracts are the global standard in construction projects, and each color serves a different purpose:

1️⃣ Red Book
• For traditional projects where the Employer designs and the Contractor builds.

2️⃣ Yellow Book
• For Design & Build projects where the Contractor handles both design and execution.

3️⃣ Silver Book
• For Turnkey projects, where the Contractor bears most of the risk.

4️⃣ Green Book
• For small, simple, and short-term projects.

Choosing the right FIDIC contract from the start saves time, effort, and reduces future disputes!

@etconp
❤21👏4🥰2🔥1
👉Understanding Bridge Load Mechanics

🏷Ever wondered what types of forces and loads a bridge endures daily?

🔸 Dead Load – The permanent weight of the bridge itself.
🔸 Live Load – Vehicles and pedestrians in motion.
🔸 Dynamic Load – Impact of moving traffic.
🔸 Thermal Load – Effects due to temperature changes.
🔸 Seismic Load – Earthquake-induced forces.
🔸 Hydraulic Load – Water pressure from below or the sides.
🔸 Herzamik Load – Subsoil pressure.
🔸 Compression Forces – Transfer of forces through the arch.

🚧Understanding these factors is essential for civil and structural engineers during the design, analysis, and maintenance of infrastructure.

👷 Whether you're a student, a practicing engineer, or just curious about structural mechanics — this is a great reminder of how much detail goes into ensuring the bridges we use every day are safe and sound.

@etconp
❤13👍1
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን


0904040477
0994941708
❤3
👉በግንባታ ሥፍራ ላይ ለሚገኙ የግንባታ ዕቃዎች (Materials on Site) የሚፈፀም ክፍያ ከ 50% ወደ 60% አደገ

💫አዲሱ የፌደራል ግዥ መመሪያ የሚከተሉትን ነጥቦች አካቷል።

⏺በግንባታ ሥፍራ ላይ ለሚገኙ የግንባታ ዕቃዎች (ማቴሪያሎች) ከዋጋቸው እስከ ስልሳ በመቶ (60%) የሚደርስ ክፍያ መፈፀም ይቻላል፡፡

⏺ሆኖም መንግስት መ/ቤቶች የተጠቀሰውን የስልሳ በመቶ (60%) ክፍያ ከመፈፀማቸው በፊት የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ አለባቸው፡፡

1⃣ በግንባታ ሥፍራ ላይ ለሚገኙ ዕቃዎች ክፍያ እንዲከፈለው የሚጠይቅ ማናቸውም ሥራ ተቋራጭ የሚያቀርባቸው ዕቃዎች የተገዙበትን ዋጋ የሚያመለክት ደረሰኝ ትክክለኛነት በመንግስት መ/ቤቱ እና በአማካሪው መረጋገጥ አለበት፡፡

2⃣ ክፍያ የተፈፀመበት በግንባታ ሥፍራ የሚገኝ የግንባታ ዕቃ ሥራ ላይ እንዲውል ሲደረግ የተፈፀመው ክፍያ ከሚቀጥለው ክፍያ መቀነስ አለበት፡፡

3⃣ በአንድ የግንባታ ሥፍራ የሚገኙ ዕቃዎችን ለሌላ የግንባታ ፕሮጀክት በግብአትነት መጠቀምም ሆነ ለሌላ የተለየ ዓላማ ማዋል አይቻልም።

4⃣ ሥራ ተቋራጩ በግንባታ ሥፍራ ላይ ለሚገኙ ዕቃዎች ክፍያ እንዲከፈለው ከሚያቀርበው ጥያቄ ጋር ዕቃዎቹ በክምችት ላይ እያሉ አደጋ ቢደርስባቸው፣ ቢሰረቁ፣ ወይም ለረዥም ጊዜ ሥራ ላይ ሳይውሉ በመቅረታቸው ቢበላሹ የጉዳቱን መጠን ለማካካስ እንዲቻል በግንባታ ሥራ መደበኛ የጨረታ ሠነድ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ድንጋጌ ላይ በተጠቀሰው አግባብ ኢንሹራንስ በመግባት ዕቃዎቹ ኢንሹራንስ የተገባላቸው መሆኑን የሚያመለክት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

@etconp
❤16👍3
👉Construction Tip of the Day:

💫What Is Formwork?


🔴 Formwork is the temporary mold into which concrete is poured and shaped until it hardens.

🛠 Types of Formwork:

⏺Timber formwork – easy to shape, affordable

⏺Steel formwork – reusable, durable, and gives a smooth finish

⏺Plastic formwork – lightweight and best for repetitive structures

✅ Why it’s important:

🟠 Defines the shape and size of concrete elements

🟠 Ensures safety during pouring

🟠 Affects the quality of surface finish

🟠Influences the speed and cost of the project

💡 Tip: Always oil the formwork before pouring to prevent sticking and ensure easy removal!

⚡️Strong formwork = Strong and accurate structure.

@etconp
❤17
👉ጣልያን የዓለማችን ረጅሙን ተንጠልጣይ ድልድይ ልትገነባ ነው

🚧የጣሊያን መንግስት የሲሲሊ ደሴትን ከዋናው የሀገሪቱ መሬት ጋር የሚያገናኘውን የዓለማችን ረጅሙን ተንጠልጣይ ድልድይ ለመገንባት የሚያስችል የ13.5 ቢሊዮን ዩሮ (15.6 ቢሊየን ዶላር) ፕሮጀክት አጽድቋል።

ከብዙ አስርት አመታት እቅድ እና ከባድ ውዝግብ በኋላ የድልድዩ ሥራ መፅደቁን የሀገሪቱ የትራንስፖርት እና የመሠረተ ልማት ሚኒስትር ማትዮ ሳልቪኒ አስታውቀዋል።

ድልድዩ 3.3 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ሲሆን፤ ይህም በዓለም ላይ ካሉት ረጅም ተንጠልጣይ ድልድዮች ቀዳሚ ያደርገዋል።

ድልድዩ የባቡር ሀዲዶች እና የተሽከርካሪ መስመሮች ይኖሩታል ተብሏል።

ተንጠልጣይ ድልድዩ 400 ሜትር (1,300 ጫማ) ከፍታ ባላቸው ሁለት ማማዎች መካከል ላይ የሚዘረጋ ሲሆን ከፍተኛ ንፋስ እና የመሬት መንቀጥቀጥን እንዲቋቋም ተደርጎ መነደፉ ተነግሯል።

ፕሮጀክቱ የሃገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ለማሳደግ እና በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥርም ነው የተገለጸው።

ይሁን እንጂ ፕሮጀክቱ ከ50 ዓመታት በፊት ከታቀደ ጀምሮ ብዙ ጊዜ በመዘግየቱ ብዙዎች መጠናቀቁን ጥያቄ ውስጥ ከተውታል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

@etconp
❤11👍2