Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.21K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የዓለም ረጅሙ ቀጥተኛ መንገድ በሳውዲ አረቢያ

💫በረሃማ በሆነው የሳውዲ አረቢያ ምድር ላይ የሚገኘው እና 240 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ፣ በዓለም ላይ ረጅሙ ቀጥተኛ መንገድ በመሆን የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

🚧ይህ መንገድ የሀገሪቱን ሩቅ አካባቢዎች ለማገናኘት ተብሎ የተሰራ ሲሆን፣ የዘመናዊ የምህንድስና ድንቅ ስራ ተብሎ እየተጠራ ነው።

⏺ይሁን እንጂ መንገዱን መንከባከብና አገልግሎት መስጠት ቀላል አይደለም የተባለ ሲሆን እንደ አሸዋማ ንፋስ፣ ከፍተኛ የፀሐይ ሙቀት እና ለረጅም ጊዜ በሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ላይ የሚከሰት ድካም ያሉ በርካታ ተግዳሮቶች ያጋጥሙታል ተብሏል።

⏺የመንግስት የትራንስፖርት ባለስልጣናት እነዚህን ችግሮች ለመቋቋም የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርገዋል።

⏺ከእነዚህም መካከል አሽከርካሪዎች እንዳይደክሙ ለማገዝ የማንቂያ ንጣፎች (rumble strips)፣ ግልጽ የመንገድ ምልክቶች እና አሽከርካሪዎች አረፍ እንዲሉበት የተዘጋጁ ማረፊያ ጣቢያዎች ይገኙበታል ተብሏል።

⏺እነዚህ ጥረቶች መንገዱ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል ነው የተባለው።

⏺የዚህ መንገድ ያልተቋረጠ ርዝመትና አስቸጋሪ በሆነ የበረሃ አካባቢ መገኘቱ በአለም ላይ ልዩ የሚያደርገው ሲሆን፣ የሳውዲ አረቢያን የምህንድስና ብቃት የሚያሳይ ማሳያ ነው ተብሎ ተገልጿል።

@etconp
❤12👍1
👉በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚመሰረቱ ከተሞች ማስተር ፕላን የማዘጋጀት ሥራ መጀመሩ ተገለጸ

💫በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚመሰረቱ ከተሞች ማስተር ፕላን የማዘጋጀት እንዲሁም የአሶሳ ከተማን የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራ፤ 'ሲቲስ አሊያንስ' በተሰኘ ድርጅት አማካኝነት በይፋ መጀመሩን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ አስታውቋል።

ፕሮጀክቱን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ እና ሲቲስ አሊያንስ በጋራ ተግባራዊ እንደሚያደርጉት የክልሉ የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ደርበው ዘንቶ ለአሐዱ ተናግረዋል።

"ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ አምስት ከተሞች ላይ የሚከናወን ነው" ያሉም ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ሁለቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ ከተማ አሶሳ እና በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚመሰረት ከተማ መመረጡን አስታውቀዋል።

በዚህ መሠረት "ለአሶሳ ከተማ ለ30 ዓመታት የሚያገለግል የማስፋፊያ ፕላን እና በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ለሚመሰረቱ ከተሞች ደግሞ አዲስ ፕላን የማዘጋጀት ሥራ በይፋ ተጀምሯል" ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ እንደ ክልል ለጊዜው "አበንኮሮ" የተሰኘ አንድ ከተማ ብቻ ተመስርቶ ማዘጋጃ ቤት መቋቋሙንም ገልጸዋል፡፡

የሚመሰረቱት ከተሞች የቱሪዝም ከተሞች እንደሚሆኑ ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ ከተማው ዓለም አቀፍ ሆቴሎች እና ሪዞርቶችን እንደሚያካትት ገልጸዋል።

ወደፊት በአካባቢው ብዙ ከተሞች ይመሰርታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለጹም ሲሆን፤ አካባቢው የዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን ትኩረት መሳቡን ጠቁመዋል።

ቀደም ሲልም የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱ አልሚዎች እንዳሉ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ የሐይቁን መሃል በተመለከተ ከፌደራል መንግሥት ጋር በትኩረት የሚሰራ መሆኑ የተጠበቀ ቢሆንም ብዙ ደሴቶች በመኖራቸው ጥናት እንደሚፈልግ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የአሶሳ ከተማ ከሦስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ ማስተማር ፕላኑ ተሰርቶ ሥራ ላይ መዋሉን ጠቁመዋል።

"ነገር ግን ከተማዋ ከሕዳሴው ግድብ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ እንደመሆኗ መጠን በፍጥነት እያደገች ነው" ብለዋል።

ሆኖም ለ30 ዓመታት የሚያገለግል የማስፋፊያ ፕላን በማስፈለጉ በሲቲስ አሊያንስ ድርጅት አማካኝነት ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እንደሚደረግ አመላክተዋል።

Via አሐዱ ሬዲዮ

@etconp
❤21
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ዋዜማ—ጉባ

ህዳሴ:- የኢትዮጵያውያን አንድነት ሃውልት፣ የፅናት ምልክት፣ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ብስራት ነው!

የዚህን ዘመን  አድዋ በደሙ፣ በላቡ፣ እና በውሃው በአንድነት ሆኖ የከተበ ትውልድ አካል መሆን ያኮራል።

የኢትዮጵያ ከፍታ አይቀሬ ነው!

@etconp
❤19🔥1
ADVERTISMENT

ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤4
👉ለባከነ የግንባታ ጊዜ ''የጊዜ ጉዳት መቀጫ''/Liquidated damage/

💫በኮንስትራክሽን ውል ላይ የውሉ የግንባታ ስራ ተብሎ የተቀመጠውን በዲዛይኑ እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽኑ መሰረት በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሰርቶ ማጠናቀቅ የተቋራጩ ሀላፊነት ነው።

🚧ተቋራጩ የውሉን የግንባታ ስራ በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በወቅቱ ሰርቶ ያላጠናቀቀ እንደሆነ ከውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ/completion date/ በኋላ ግንባታው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ለእያንዳንዱ ቀን ተቋራጩ የግንባታ መዘግየት ምክንያት ለአሰሪው የጊዜ ጉዳት መቀጫ/Liquidated damage/ የመክፈል ሀላፊነት ይኖርበታል፡፡

🌟በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሲባል ምን ማለት ነው?

⏺አንዳንድ አሰሪዎች/client/ በግንዛቤ እጥረት በውሉ ላይ የተቀመጠው ተቋራጩና አሰሪው ለግናባታው ማጠናቀቂያ የተስማሙበትን የቀን ብዛት/የጊዜ እርዝማኔ/ መቆጠር የሚጀምረው ውሉ በግራ ቀኙ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ ይረዱታል፡፡ይሄ አረዳድ ስህተት ነው፡፡

📍በኮንስትራክሽን ውል ስለ ጊዜ አቆጣጠር በተለይ
-የግንባታ ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ፣
-ሞቢላይዜሽን ፔሬድ/mobilization period/፣
-የሳይት መረከቢያ ቀን/site handover/፣
-የስራ መጀመሪያ ቀን/commencement date/ እና
-የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ የሚሉትን መረዳት የግንባታ የጊዜ የጉዳት መቀጫ/Liquidated damage/ የሚለውን በአግባቡ ለማወቅ ይጠቅማል፡፡

⏺በመሰረቱ በውሉ የተቀመጠው የስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ተቋራጩ የግናባታውን ሳይት ከአሰሪው ከተረከበ በኋላ ነው፡፡ይሄውም ከሳይት ርክክብ በኋላ የስራ መጀመሪያ ቀን /commencement date/ በመሀንዲሱ የሚወሰን እና ለተቋራጩ የሚገለጽለት ይሆናል፡፡

⏺እንግዲህ በመሀንዲሱ ከሚወሰነው የስራ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ በውሉ ላይ የተቀመጠው ቀን ይቆጠርና የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቼ እንደሆነ ለማወቅ ያስችላል ማለት ነው፡፡

⏺እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነገር በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ ውል ሊደረግ የሚችልበት እድልም አለ፡፡/Partial completion/ ማለት ነው፡፡የቀን አቆጣጠሩ ከላይ እንደተብራራው የሚሰላ ይሆናል፡፡

⏺ስለሆነም የግንባታ መዘግየት ቅጣት የሚለው ጉዳይ የሚመጣው ተቋራጩ የውሉን የግንባታ ስራ በውሉ ስራ የማጠናቀቂያ ጊዜ /completion date/ ሳያጠናቅቅ የቀረ እንደሆነ ነው፡፡የገንዘብ ቅጣቱ የሚጣለው በተቋራጩ ላይ ነው፡፡ተቋራጩ ግንባታውን ላዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን በውሉ የተቀመጠውን የጊዜ ኪሳራ መቀጫየሚከፍል ይሆናል፡፡በነገራችን ላይ እየተቀጡ መስራት ለተቋራጩ መብትም ጭምር ነው፡፡ይህ ማለት አሰሪው የውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ ስላለቀ ውል አቋርጣለሁ ማለት አይችልም፡፡በውሉ ላይ የተቀመጠው የመዘግየት ቅጣት ጣሪያ መጠን ከሞላ በኋላ ግን አሰሪው ውል ማቋረጥ ይችላል፡፡ውል ከተቋረጠ በኋላ የመዘግየት ቅጣት የሚባል ነገርም የለም፡፡

❇️ሌላው ተቋራጩ ወደ መዘግየት ቅጣት እንዲገባ ከመደረጉ አስቀድሞ በአግባቡ መረጋገጥ ያለበት ነገር መሀንዲሱ ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ/Extension of Time / ፈቅዷል ወይስ አልፈቀደም የሚለው ነጥብ ነው፡፡ምክንያቱም ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ ተፈቅዶለት ከሆነ የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜውም አብሮ ስለሚራዘምና ቀኑ ስለሚቀየር ነው፡፡

⭐️የሀገራችንን የህግ ማእቀፍ በዚህ ረገድ ምን ይላል? የሚለውን ለመመለስ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1887 እስከ 1895 ድረስ የተደነገጉትን መዳሰስ ይጠይቃል፡፡

⏺በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1889 ላይ ተዋዋዮች በውላቸው ምናልባት አንደኛው ወገን እንደውሉ ግዴታውን ያልፈጸመ እንደሆነ ወይም አጓድሎ የፈጸመ እንደሆነ ወይም አዘግይቶ የፈጸመ እንደሆነ የሚከፍለውን የመቀጮ መጠን አስቀድመው በውላቸው ለመወሰን እንደሚችሉ በሚፈቅድ መልኩ ተደንግጓል፡፡

⏺እዚህ ላይ የውል ግዴታን አዘግይቶ መፈጸም ስለሚያስከትለው ቅጣት የሚዋዋሉት በተለይ የግንባታ ጊዜ የጉዳት መቀጫ/liquidated damage/ የሚመለከት ይሆናል፡፡

🎲የመዘግየት ቅጣት ስምምነት ባለ ጊዜ አሰሪው የውሉ ስራ እንዲፈጸምና የቅጣት ገንዘቡንም ለመቀበል መብት እንደሚኖረው የፍ/ህ/ቁ 1890(2) ይደነግጋል፡፡እንደዚሁም አሰሪው ኪሳራ ባይደርስበት እንኳ የመዘግየት ቅጣት ገንዘቡ ሊከፈለው እንደሚገባ የፍ/ህ/ቁ 1892(1) ይደነግጋል፡፡እንግዲህ ተቋራጩ ግንባታውን በወቅቱ ያላጠናቀቀው አሰሪውን ሆነ ብሎ ለመጉዳት አስቦ ጉልህ በሆነ ቸልተኝነት ወይም በከባድ ጥፋት መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ አሰሪው በውሉ ከተቀመጠው የቅጣት ገንዘብ በላይ በደረሰበት ትክክለኛ ጉዳት መጠን ልክ ከተቋራጩ ላይ ኪሳራ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 1892(2) ይደነግጋል፡፡

⏺ሌላው የመዘግየት ቅጣት መጠን በዳኞች ሊቀነስ የሚችልበት እድል ስለመኖሩ የፍ/ህ/ቁ 1893 ይደነግጋል፡፡ይሄውም ተቋራጩ ግዴታውን በከፊል የፈጸመ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ይህ ማለት ተቋራጩ ባከናወነው ስራ ሁሉ ቅጣት የሚጣልበት አይሆንም ማለት ነው፡፡

⏺በዚህ ረገድ በሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ አንቀጽ 47(1) ላይ ተቋራጩ ስራውን በውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ ካላጠናቀቀ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን የውሉን ዋጋ 1/1000 እንደሚከፍል እና ይሄውም አጠቃላይ መጠኑ ከውሉ ዋጋ ከ(10-20%)መብለጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ሆኖም ግን በከፊል ለተከናወነው ስራ መሀንዲሱ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በሰጠ ጊዜ የቅጣቱ መጠን የሚሰላው ባልተከናወነው ስራ መጠን ዋጋ ላይ በመመስረት ይሆናል ማለት ነው፡፡

📜በመጨረሻም የመዘግየት ቅጣት በኛ ሀገር ከላይ እንዳየነው እንደቅጣት የሚቆጠርና በህጉ ቅጣቱ እውቅና የሚሰጠው ሲሆን በኮመን ሎው የህግ ስርአት ግን ቅጣት አይደለም፡፡በኮመን ሎው የጊዜ የጉዳት መቀጫ በአሰሪው ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን የሚኖርበት ሲሆን የቅጣት አይነት ተመሳሳይ ባህሪ ካለው ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

⚡️ለተጨማሪ የግንባታ እና ጨረታዎች ከታች ባለው ሊንክ ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤25👍3
The Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) stands as a collective achievement of the Ethiopian people. Beyond its economic promise, it serves as a powerful reminder that national consensus can be a unifying symbol and a tool for cohesion. For this legacy to endure, however, it must be framed within a narrative that transcends individual ambition, narrow nationalism, and class divisions.

To fully realize its economic and symbolic value, Ethiopia must also put an end to war and restore peace. As long as multiple civil conflicts persist, national strategic projects such as the GERD will remain vulnerable and fall short of their potential. Wars not only deplete human and financial resources needed to further investment on the project, say for expansion of transmission lines, but also inflict severe environmental damage, undermining the very foundations of sustainable green energy development.

Congratulations to the people of Ethiopia!

Via Jawar Mohammed

@etconp
❤26
⭐️Congratulations to my Ethiopia on completing the Grand Renaissance Dam🚧

❇️Proud to be Ethiopian😇

🙏ኢትዮጵያዬ እንኳን ደስ አለሽ❤️

💫እንኳንም ልጆችሽ ሆንን ❤

@etconp
❤24👏2👍1😭1
👉Construction Tip of the Day:

💫What Is Formwork?


🔴 Formwork is the temporary mold into which concrete is poured and shaped until it hardens.

🛠 Types of Formwork:

⏺Timber formwork – easy to shape, affordable

⏺Steel formwork – reusable, durable, and gives a smooth finish

⏺Plastic formwork – lightweight and best for repetitive structures

✅ Why it’s important:

🟠 Defines the shape and size of concrete elements

🟠 Ensures safety during pouring

🟠 Affects the quality of surface finish

🟠Influences the speed and cost of the project

💡 Tip: Always oil the formwork before pouring to prevent sticking and ensure easy removal!

⚡️Strong formwork = Strong and accurate structure.

@etconp
❤14👍5
👉Types of Punching reinforcemt bar

💫1.Cranked bars

▶️Is also known as bent-up bars, are used in flat slabs to resist punching shear forces by providing inclined reinforcement around the column, similar to stirrups, to transfer shear stress from the slab to the concrete column more effectively. 

▶️This improves the slab's structural integrity and shear capacity, preventing the concentrated loads from columns from causing shear failure and protecting against progressive collapse.  

💫2.Shear Reinforcement (Stirrups/Dowel Bars/Shear Heads)

⏺In flat slab design, punching shear at the slab–column connection is a critical failure mode.
⏺Since the slab is thin and heavily stressed around columns, special reinforcement is often needed.

🏷Here’s how shear reinforcement can be provided:

🚧2.1. Stirrups (Closed Links / Vertical Hoops)

⏺Concept: Vertical stirrups placed around the column in multiple perimeters.

⏺Function: Intercept diagonal shear cracks and transfer shear safely.

⏺Details:Arranged in closed rectangular or circular hoops.

📍Placed within a critical perimeter around the column (usually at 0.5d to 1.5d from the column face).

🚧2.2.Dowel Bars (Shear Dowel Reinforcement)

⏺Concept: Vertical steel bars (dowels) anchored into the slab near the column face.

⏺Function: Resist vertical shear and enhance punching resistance by direct load transfer.

⏺Details:Placed in concentric rings around the column.

▶️Often welded to top and bottom anchorage bars or headed at ends for better anchorage.

▶️Common in high-load slabs where stirrups are not practical.

🚧2.3.Shear Heads (Steel Sections / Cruciform Beams)

⏺Concept: Steel I-sections or cross-shaped steel profiles embedded in the slab around the column.

⏺Function: Increase slab thickness locally, redistribute punching shear, and enhance capacity.

⏺Details:Usually four steel arms extending from the column in orthogonal directions.

📍Used in heavily loaded slabs (e.g., industrial buildings, parking structures).

❇️Efficient when architectural requirements demand a flat soffit (no drop panels)

...ይቀጥላል

@etconp
❤15👍1
እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2018 ዓ.ም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

2018 የሰላም የጤና ያሰብነው ምናሳካበት፣ሀገራችን ሰላም የምትሆንበት አመት ያርግልን🙏

መልካም አዲስ ዓመት❤

@etconp
❤13🙏2
መልካም አዲስ ዓመት❤

2018 ዓ/ም እንደ ሀገር የሰላም፣ የፍቅር ፣ የደስታ ፣ መልካም መልካሙን የምንሰማበት፣ በችግር ላይ ያሉ ወገኖቻችን መፍትሄ የሚያገኙበት፣ የወገኖቻችንን ሰቆቃ የማንሰማበት፣ ያለ ሰቀቀን ወጥተን የምንገባበት፣ በሰው ሰራሽ ችግሮች በጦርነት በግጭት እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋ ወገኖቻችን የማይረግፉበት ፣ የኑሮው ጫና የሚቀልበት፣ የእናቶች የአባቶች እምባ የማይፈስበት እንዲሆንልን ፈጣሪ ይርዳን🤲

ውድ ቤተሰቦቻችን አዲሱ ዓመት የስኬት ፣ ያሰባችሁት ሁሉ የሚሳካበት፣ እውነተኛ ደስታን የምታገኙበት፣ በሰላም እንደወጣችሁ በሰላም የምትገቡበት፣ በጎ በጎው ብቻ ወደናተ የሚመጣበት፣ ሰርታችሁ የምትለወጡበት፣ በሀገራችሁ ደስ የምትሰኙበት፣ የተስፋ ፣ የበረከት ዓመት ይሁንላችሁ😇

ፈጣሪ ረጅም እድሜን ከተሟላ ጤና ጋር ይስጣችሁ🙏

@etconp
❤13
👉ግንባታዎች ከመንገድ የሚኖራቸውን ርቀት (Setback) በተመለከተ የተሻሻለ ውሳኔ ተላልፏል

💫የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታዎች ከመንገድ የሚኖራቸውን ርቀት (Setback) እና ተያያዥ የግንባታ ፈቃድ መመሪያዎችን አስመልክቶ የተሻሻለ ያለውን ውሳኔ አስተላልፏል።

💥አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ህንፃዎች ከይዞታ ወሰን የሚኖራቸው ርቀት (Set Back Regulation) በተመለከተ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም ውሳኔ ማስተላለፋ ይታወቃል።

በመመሪያው ላይ ግልፅ ያልሆኑና በአሰራር ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጉዳዮችን በተመለከተ ደግሞ ካቢኔው ሰኔ 10/2016 ዓ.ም ባካሄደው ሶስተኛ ዓመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በመወያየት ማሻሻያ ተደርጎ ወደ ስራ ተገብቶ ነበር።

የተሻሻለው ውሳኔ ማስተለፍ ያስፈለገው የሴትባክ ህግ አፈፃፀም ሂደት ላይ የታዩ ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም በከተማዋ ውስጥ ከግንባታ ፈቃድ ጋር በተያያዘ ከአልሚዎችና ፕላን ፈፃሚ ተቋማት በኩል በተደጋጋሚ የሚቀርቡ በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ያስችል ዘንድ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመመሪያው ላይ ተመልክቷል።

"የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ በ5ኛ ዓመት በ1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተወያይቶ እንዲያፀድቅ የቀረበውን ራሱን ችሎ የሚለማ ቦታ ዝቅተኛው ስፋትና የፊት ለፊት ገፅታ ርዝመት ጥናት ካቢኔው ተወያይቶ ያሳለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንድታደርጉ" ሲል ይገልጻል።

በእዚህም መሰረት ከ 28/12/17 ዓም ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ፕላን እና ልማት ቢሮ የከተማዋ ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ፣ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፣ የመሬት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ እንዲሁም  ለሁሉም የክፍለ ከተማ የፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች የካቢኔውን ውሳኔ እንዲያስፈጽሙ መመሪያ አውርዷል።

@etconp
❤11👍1