Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.21K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ግንባታዎች ከመንገድ የሚኖራቸውን ርቀት (Setback) በተመለከተ የተሻሻለ ውሳኔ ተላልፏል

💫የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታዎች ከመንገድ የሚኖራቸውን ርቀት (Setback) እና ተያያዥ የግንባታ ፈቃድ መመሪያዎችን አስመልክቶ የተሻሻለ ያለውን ውሳኔ አስተላልፏል።

💥አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ህንፃዎች ከይዞታ ወሰን የሚኖራቸው ርቀት (Set Back Regulation) በተመለከተ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም ውሳኔ ማስተላለፋ ይታወቃል።

በመመሪያው ላይ ግልፅ ያልሆኑና በአሰራር ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጉዳዮችን በተመለከተ ደግሞ ካቢኔው ሰኔ 10/2016 ዓ.ም ባካሄደው ሶስተኛ ዓመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በመወያየት ማሻሻያ ተደርጎ ወደ ስራ ተገብቶ ነበር።

የተሻሻለው ውሳኔ ማስተለፍ ያስፈለገው የሴትባክ ህግ አፈፃፀም ሂደት ላይ የታዩ ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም በከተማዋ ውስጥ ከግንባታ ፈቃድ ጋር በተያያዘ ከአልሚዎችና ፕላን ፈፃሚ ተቋማት በኩል በተደጋጋሚ የሚቀርቡ በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ያስችል ዘንድ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመመሪያው ላይ ተመልክቷል።

"የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ በ5ኛ ዓመት በ1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተወያይቶ እንዲያፀድቅ የቀረበውን ራሱን ችሎ የሚለማ ቦታ ዝቅተኛው ስፋትና የፊት ለፊት ገፅታ ርዝመት ጥናት ካቢኔው ተወያይቶ ያሳለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንድታደርጉ" ሲል ይገልጻል።

በእዚህም መሰረት ከ 28/12/17 ዓም ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ፕላን እና ልማት ቢሮ የከተማዋ ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ፣ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፣ የመሬት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ እንዲሁም  ለሁሉም የክፍለ ከተማ የፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች የካቢኔውን ውሳኔ እንዲያስፈጽሙ መመሪያ አውርዷል።

@etconp
❤11👍1
#ADVERTISEMENT

🏭🏠TSEGAYE and YOHANNES J-Bolt & PLATE 🏚🏗 🌁🌆

🧿 OUR SERVICES ⤵️

🔲Plate

⚙️  J-Bolt

⚓Anchor Bolt

➽Tie Rod

Phone : 🤳0938494506 
              🤳 0951087077
              🤳 0929044037

👉አድራሻ፦  መርካቶ ምንአለሽ ተራ ከጭድ ተራ ከፍ ብሎ

https://t.me/tsegaye2016Jbolt
❤10
👉ዊ ቢውልድ (የቀድሞ ሳሊኒ ኢምፕሬጊሎ) ስለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምን አለ ?

" ፕሮጀክቱ ከሦስት መካከለኛ መጠን ካላቸው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ጋር የሚስተካከል ነው ! "

" ዊ ቢውልድ " በይፋዊ ኤክስ ገጹ ባስተላለፈው አጭር ጹሑፍ " የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሦስት መካከለኛ መጠን ካላቸው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ጋር የሚስተካከል ነው " ሲል ገልጾታል።

ኩባንያው ፦

" ታላቁ የህዳሴ ግድብ በአፍሪካ ትልቁ እና በዓለም ላይ ካሉ 10 ግዙፍ ግድቦች ተርታ አንዱ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የኃይል ስትራቴጂ ዋነኛ መሠረት ነው።

ፕሮጀክቱ በውስብስብ የግንባታ ጥበብ  የጥቁር አባይን ውሃ በመጠቀም 5,150 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም የፈጠረ ሲሆን ይህም ከሦስት መካከለኛ መጠን ካላቸው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ጋር የሚስተካከል ነው።

ሪከርድ ስለሰበረው ፕሮጀክት ቁጥሮችን ይመልከቱ [ቪዲዮው ከላይ ተያይዟል] " ሲል መልዕክቱን አጋርቷል።

" ዊ ቢውልድ " ማነው ?

ዊቢውልድ (የቀድሞው ሳሊኒ ኢምፕሬጊሎ) እ.ኤ.አ ከ1950ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ የውሃ ኃይል እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ግልገል ጊቤ አንድ፤ ግልገል ጊቤ ሁለት፤ ግልገል ጊቤ ሦስት ፕሮጀክቶችኝ ገንብቷል። የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ግድብ እንዲሁም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በዚሁ ኩባንያ ሥር ግንባታቸው የተከናወነ ነው።

#Ethiopia
#GERD 💪

Via Tikvah Magazine

@etconp
❤15
👉በአፍሪካ 10ሩ ምርጥ የአውሮፕላን ማረፊያዎች - 2025

💫1)- ኬፕ ታውን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ - ደቡብ አፍሪካ

💫2)- ኦአር ታምቦ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ – ጆሃንስበርግ፣ ደቡብ አፍሪካ

💫3)-ኪንግ ሻካ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ - ደርባን ፤ ደቡብ አፍሪካ

💫4)-ማርኬክ ሜናራ አውሮፕላን ማረፊያ - ሞሮኮ

💫5)-መሐመድ v ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ - ካዛብላንካ፤ ሞሮኮ

💫6)-አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ – ኢትዮጵያ

💫7)-ኪጋሊ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ - ሩዋንዳ

💫8)-Sir Seewoosagur Ramgoolam ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ – ሞሪሸስ

💫9)- ካይሮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ – ግብፅ

💫10)- ኢቫቶ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ – አንታናናሪቮ፣ ማዳጋስካር

ምንጭ፡ ስካይትራክስ

⚡️እንደ ካሜሩን፣ ናይጄሪያ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዚያና ጋና ያሉ አገራት በዝርዝሩ ውስጥ መካተት አልቻሉም፡፡

@etconp
❤18🎉1
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

♧ ሁሉን በአንድ ቦታ ለሁሉም ቅርብ

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤3👏3
👉በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እየተገነባ የሚገኘው የሰመራ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የሁለት ኪ.ሜ መንገድ ተጨማሪ መስመር የመሥራትና ደረጃ ማሳደግ፣ 4 የህዝብ ፓርኮች፣ ከ12 በላይ የውሃ ፋውንቴኖች፣ የሳይክልና የእግረኛ መንገዶች፣ ሙዚየም፣ አንስተኛ የመጫወቻ ሜዳ፣ የአፋርን ባህል ፣ አሴት፣ ቅርስ የሚያሳዩ የአርት ሥራዎች፣ የልጆች መጫወቻ እና ሌሎች የከተማ መሰረተ ልማት ግንባታዎችን ያካተተ ነው፡፡

@etconp
❤13👍2🎉1
#ስለታላቁ_የኢትዮጵያህዳሴ_ግድብ
አጠር ያለ ቴክኒካል መረጃ ልስጣችሁ

የኢትዮጲያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካዊያን ኩራትና አዲስ የብርሀን መንገድ የከፈተልን በአለም ላይ ትልቁን ግድብ ሰርተን በማጠናቀቃችን ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል።

ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ከአፍሪካ አንደኛ የሆነ የሀይል ማንጫ ሲሆን ከአለም በሀይል ማመንጨት 3ኛ ነው።

በአለም ከፍተኛ ውሀ የመያዝ አቅሙ እስከዛሬ በሀይል ማመንጨት አንደኛ የተባለው የቻይና three Gorgeous Dam በሁለት እጥፍ የሚበልጥ ከአስዋን ግድብ በሀይል ማመንጨት 2.5እጥፍ የሚበልጥ ግድብ ነው።

ይህ ግድብ ብሔራዊ ኩራታችን በታሪክ አጋጣሚ አንድ ያደረገን ኢትዮጲያዊያንና አፍሪካዊያንን ያስተደሰተ ያስደመመ ግድብ ነው።

#ታላቁ_ግድባችን_በግንባታ_ወቅት_የነበሩ_አምስት_መሠረታዊ_ተግዳሮቶች

#10ሚሊዮን ሜኩ ኮንክሪት እግዚኦ..

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከአለም  በግዝፈቱ በስፋቱ እና በውስብስብ የኢንጂነሪንግ ስራዎች ትልቅ ቢሆንም ግንባታውን ሊያደናቅፉ የሚችሉ በርካታ ቻለንጆች አጋጥመውታል።

ከነዚህ ተግዳሮቶች በመነሳት በርካታ ውስብብ የምህንድስና ጥበብ የተማርንባቸውና ለቀጣይ ትውልድ እና ወደፊት ለሚሰሩ ሜጋ ግንባታ ስራዎች የምንማርባቸው ተጨማሪ የምርምር ስራ የሚሰራበት ጥሩ አጋጣሚ የሆነ ታላቅ ግድብ ነው።

#የነበሩ_ቻለንጆች

1ኛ ከኢንጂነሪግ ቴክኒካል ስራዎች
👉74ቢሊዮን ሜኩ ( 1870km2 ) ስፋት ያለውን ውሀ ለመያዝ የሚያስችል ለዋናው ግድብና ለሌሎች ስትራክቸር ስራዎች ከ10ሚሊዮን ሜኩ ያላነሰ ኮንክሪት ሙሌት ስራ የተሰራ ከአለም በኮንክሪት ሙሌትና በተጠቀምነው የብረት መጠን ከቻይናው 3Gorgeous ቀጥሎ ነው።

የቻይናውን ግድብ ለመስራት 43ሚሊዮን ሜኩ ኮንክሪት  2.7ሚሊዮን ቶን ብረት ተጠቅመዋል

የኛው ግድብ 10ሚሊዮን ሜኩ ኮንክሪትና 175ሺ ቶን ብረት ተጠቅመናል።
ዝርዝሩን ነገ በስልክ ከገባሁ እነግርሃለሁ

በገንዘብ ደረጃ ሁለቱን ስናሰላ
#እንድታውቁት ከፍተኛ ስትሬንግዝ ያለው የኮንክሪት ወጭ በቀላሉ አሁን ባለው ዋጋ =15ሺ ብር ሲሆን =>
10ሚ *  15ሺ = 150ቢሊዮን ብር ሌላውን ተውትና እግዚኦ ከማለት ውጪ ምን ይባላልቢሆን

175ሺ ቶን ብረት ማለት አንድ ቶን 260ሺብር ቢሆን
=> 175ሺ ቶን x 260ሺብር
45.5ቢሊዮን ብር ወጪ ሆኗል


በሁለቱ አይተም ብቻ ወደ 200ቢሊዮን ብር ወጪ ሆኗል።
ሌላውን ሁሉ ትታችሁ ማለት ነው


👉ለግድቡ ስራ ማሳለጫ በርካታ ተያያዥ መሠረተ ልማቶች ለመገንባትና የውሀ መቀልበሻ ግድብ ስራ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግዢ የማሽኖቹ የሰራተኞቹ አረ ብዙ ብዙ

የስራ ቻለንጆች በአጭሩ

👉ተፈጥሮአዊ የመሬቱ አቀማመጥና ከመሬት በታች የተሰሩ በርካታ ውስብስብ ግንባታዎችና የመሬት ውስጥ ጥናት ስራ

👉የሀይል ማንጫ ውስብስብ  የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎችና የውስጥ ለውስጥ የዋሻ ግንባታ ስራ

2ኛ #የገንዘብና_የሎጀስትክ አቅርቦት እንዳይኖር አለም አቀፍ ተጽዕኖዎች

3ኛ #አከባቢዊ የተፈጥሮ ሁኔታዎች ለስራ ምቹ አለመሆን በርካታ ወገኖች ዋጋ መክፈል

4ኛ #አለም_አቀፍ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች መኖር

5ኛ #አለም_አቀፍ_ግዢዎች የኤሌክትሮሜካኒካልና ተያያዥ  የእቃ ግዢ እንዳይከናወን የነበሩ አለም አቀፍ ተጽእኖዎች

እነዚህን አምስት አደገኛ ቻለንጆች አለፈን ግንባታውን አጠናቀን አለምን አስደምመናል እኛም ተደስተናል።

👇👇👇

5ቱ ዝርዝር ጉዳዮች በጥልቀት የተወያየንበትን ሙሉ ፕሮግራም ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ሰብስክራይብ ሼር እያደረጋችሁ አድምጡ ።
ማንኛውም ጥያቄዎች ካላችሁ ጻፉልን መልስ እሰጣለሁ ።

መልካም አዲስ አመት

አክባሪያችሁ አቤሴሎም ነኝ
አመሠግናለሁ

https://youtu.be/0BWvynzIC2w?si=m5VdVfPN2oa1ca5a
❤28