Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.2K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ADVERTISMENT

ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤5
👉አቢሲኒያ ባንክ የተነጠቀውን የመሬት ይዞታ ለማስመለስ አቤቱታ ማቅረቡን አስታወቀ

💫ከ 6ዐ በላይ ወለሎች ይኖሩታል የተባለለትን ግዙፍ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ለመገንባት የተረከበውን የመሬት ይዞታ የተነጠቀው አቢሲኒያ ባንክ፣ የተወሰደበት ዕርምጃ በልዩ ሁኔታ እንዲታይለት አቤቱታ ማቅረቡን ሪፖርተር ዘገበ፡፡

⏺እንደ ሪፖርተር ዘገባ ከሆነ፣ ባንኩ የዋና መሥሪያ ቤቱን ሕንፃ ለመግባት ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ተረክቦት የነበረውን 9,700 ካሬ ሜትር የመሬት ይዞታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነጥቆ ወደ መሬት ባንክ እንዲመለስ ካደረገ በኋላ፣ ለሌላ ልማት እንዲውል ማስተላለፉን ሰሞኑን በተካሄደው የባንኩ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገልጿል።

⏺ባንኩ የከተማ አስተዳደሩ የወሰደበት ዕርምጃ በልዩ ሁኔታ ታይቶ ይዞታው እንዲመለስለት ለተለያዩ የመንግሥት አካላት አቤቱታ አቅርቦ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ መሆኑን፣ የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መኮንን ማንያዘዋል ለጠቅላላ ጉባዔው አሳውቀዋል፡፡

በዚህ ቦታ ላይ ባንኩ የዋና መሥሪያ ቤቱን ሕንፃ ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግና ግንባታውን እንዲያከናውን ከተመረጠው ቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ጋር የኮንትራት ስምምነት አድርጎ እንደነበርም ይታወሳል፡፡


🚧በዚሁ ስምምነት መሠረት የቻይናው ኮንስትራክሽን ኩባንያ በተጠቀሰው ቦታ ላይ ግንባታውን ለመጀመር የሚያስችል የአፈር ማንሳትና የአፈር ደጋፊ (Sharing) ሥራዎች ጀምሮ እንደነበር አቶ መኮንን ማንያዘዋል ባቀረቡት ሪፖርት አስታውሰዋል፡፡

⏺የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቢሲኒያ ባንክ ሕንፃ ለመገንባት ተረክቦት የነበረውን ቦታ ወደ መሬት ባንክ ካስገባ በኋላ በአሁኑ ወቅት ለታክሲ ተርሚናል አገልግሎት አውሎታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቢሲኒያ ባንክ ያቀረበውን አቤቱታ ሰምቶ ይዞታውን ይመልስለት እንደሆነ ለማወቅ ሪፖርተር ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

አቢሲኒያ ባንክ በተነጠቀው በዚህ ይዞታ ላይ ለመገንባት አቅዶት የነበረው የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ 6ዐ ወለሎች እንደሚኖሩትና ይህም የሕንፃውን ርዝማኔ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ቀዳሚ ያደርገዋል ተብሎ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።


⏺በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በርዝመቱ ተጠቃሽ የሆነው ሕንፃ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስገነባው የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ሲሆን፣ ይህ ሕንፃ 209 ሜትር ርዝማኔ ያለው፣ አጠቃላይ 48 ወለሎቸ ያሉት ነው፡፡ አቢሲኒያ ባንክ ለመገንባት አቅዶ ሊገኘባ የነበረው ሕንፃ ግን 270 ሜትር ርዝማኔ ያለው ነበር፡፡

💫አቢሲኒያ ባንክ ይህንን ሕንፃ እንዲገነባለት ተዋውሎት የነበረው የቻይና ኮንትራክሽን ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ከገነባቻቸው ሕንፃዎች ውስጥ የአፍሪካ ኅብረትና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃዎች ይጠቀሳሉ።

Via Reporter

@etconp
❤14👍1
👉Today Tip Of Construction

🔥 The Silent Mistake That Weakens 80% of Columns on Site

💫Ever wondered why some concrete columns show honeycombs, cracks, or poor finishes—even when the mix design was perfect?

🚧The problem is not always the concrete… it’s how we place it.
Look at this 👇

🏷When concrete is poured from heights greater than 1.2m, segregation occurs. Aggregates detach, paste runs off, and the structure loses strength. That one mistake can silently compromise your project.

🚫 Wrong practice: Free-fall from height.

✅ Right practice: Use a hopper, tremie, or chute to control the flow and protect the mix.

@etconp
❤14👍1
👉የኢትዮጵያ የሪል እስቴት ገበያ እንዴት እየሄደ ነው?

💫የሪል እስቴት ገበያ በብዙ ጉዳዮች የሚቃኝ ሲሆን የሪል እስቴት ገበያ በዋነኛነት ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር ይያያዛል።

⏺ፈጣን እና ተከታታይነት እንቅስቃሴ ካለ የሪል እስቴት ገበያው ይጦዛል።

🚧የዱባይ አየር ሞቃት ነው ከዓመት ውስጥ ለብዙ ወራት የሚጨንቅ ነው በዚያ በረሃና የሚጨንቅ አየር ማን ይኖራል? ብዙ ሰው! ለምን? ሥራ አለኣ! ንግድ አለኣ!

💫ንግድና ሥራ ባይኖር ማንም ዱባይ ላይ አይቀመጥም። የዱባይ ገዥዎች ግን ነቄ አይደሉ? ከሌላው ዓለም ሰው እንዲመጣ አደረጉ። ለዚህ መሳቢያነት ታክሱን ዜሮ አደረጉ።

⏺በዚህ ምክንያት የዱባይ ገበያ ሁሌም እንደቆመ ነው። አይበርድም! የሪል እስቴት ገበያውም ያንን ተከትሎ እንደጎነ ነው። ደስ የሚለው የኛም ሀገር ሰዎች በዚያ የዱባይ ገበያ ላይ ተቋዳሽ ሆነዋል።
ረምዚን ሪል እስቴት እና ብሩክ ሪል እስቴትን ማየት ነው።

❇️እነ The First Group ገበያ ፍለጋ እዚህ ሲመጡ የኛዎቹም እዚያ ሄደው ገበያውን እየተሻሙ ነው። እንዲህ ነው ጨዋታ። በራስ ሜዳ ብቻ መጫወት ለብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድኑም አልበጀም።

⏺ንግድ ዝም ብሎ አይጦፍም። የተለኮሰ እሳት እንኳ ዝም ብሎ አይነድም። ነዳጅ ወይም ማገዶ እና አየር ይፈልጋል። ማራገብ ያስፈልጋል።

🏷የሀገራችን የሪል እስቴት ገበያ ኢኮኖሚውን ተከታይ ነው። የኢትዮጵያ ሪል እስቴት ገበያ እንዲጦፍ ኢኮኖሚው ሊነቃቃ ይገባል።

ሰላም እና የኢኮኖሚ መነቃቃት ያለባቸው የክልል ከተሞች ላይ የሪል እስቴት ገበያ መጦፉ የማይቀር ነው። ኢኮኖሚው የጦፈው የት ክልል ላይ ይመስላችኋል? መሃል ሜዳው ሲወጠር ወደ ክንፍ አተኩሩ! ይል ነበር የድሮ የኳስ አሰልጣኛችን።


📜ለመሆኑ ድሬ/አቡሴራ ላይ የሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ምን ላይ ደርሷል?

⏺አዲስ አበባ ላይ ብዙ ክፍት መሬት አለ። የአዲስ አበባ ዋጋ እየወረደ ነው። ቶሎ የሚነሳም አይመስልም። እዋይ! ቤታችን። ውሃ በላው!

ለማንኛውም ፈጣን የስትራተጂ ለውጥና ማስተካከያ ያስፈልጋል።

Via ኢንፍራኮን ሚዲያ


@etconp
❤9🥰1
👉በኢንዶኔዥያ በግንባታ ላይ እያለ የተደረመሰ ትምህርት ቤት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 54 ደረሰ

🚧በኢንዶኔዥያ ትምህርት ቤት መደርመስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 54 መድረሱን ባለሥልጣናቱ ገልፀዋል፣ የነፍስ አድን ሠራተኞች አሁንም ከ12 በላይ የጠፉ ሰዎችን ፍለጋ ላይ ይገኛሉ።

⚡️በምስራቅ ጃቫ በሚገኘው በአልኮዚኒ ኢስላሚክ አዳሪ ትምህርት ቤት ባለፈው ሳምንት ሰኞ በግንባታ ላይ እያለ የተደረመሰ ሲሆን በወቅቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ለጸሎት ተሰብስበው ነበር።

⏺የኢንዶኔዢያ የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ በዚህ አመት በሀገሪቱ የደረሰው አስከፊ አደጋ ነው ሲል ሰይሟል።

⏺በፍርስራሹ ውስጥ የሚገኙ 13 ተጎጂዎችን የማፈላለግ ስራውን የነፍስ አድን ሰራተኞች ለማጠናቀቅ በትግል ላይ ይገኛሉ፡

⏺አሁንም መርማሪዎች የህንጻዉን መደርመስ መንስኤ እያጣራ ነው።

⏺አንዳንድ ባለስልጣናት ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃው የተደረመሰበት ምክንያት መሠረቱ ያልተረጋጋ በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል።

🏷"በ2025 ከተከሰቱት አደጋዎች ውስጥ በተፈጥሮም ይሁን በሰዉ ሰራሽ ከተከሰቱት የአሁኑን ያህል የሞቱ ተጎጂዎች የሉም" ሲሉ የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ ምክትል የሆኑት ቡዲ ኢራዋን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

❇️ቢያንስ ሁለት ሰዎች ከፍርስራሹ በህይወት ቢወጡም በሆስፒታል ውስጥ ግን ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

@etcono
❤10😭3
👉መልካም የዓለም አቀፍ የኪነህንጻ ቀን

💫መስከረም 26 2018÷October 6 2025

📍ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ ቀናቹ ነው🙏

🚧በሙያው ገና በአገራችን ያልተተገበሩ ነገር ግን በተደጋጋሚ የሚዘለሉ አንኳር ጉዳዮች

1. የሙያ ፈተና።
2. የሙያ ፈቃድ (በፈተና እና በላይሰንሲንግ ብቻ የሚሰጥ)።
2. የትምህርት ቤቶች አክሬዲቴሽን።
3. ከግንባታ ወጪ በመቶኛ የሚታሰብ የባለሙያ ክፍያ።
4. ተገቢ ያልሆነ ሙያው የሚጠይቀውን ጉዳይ ወደአማካሪ የንግድ ድርጅቶች መውሰድ ጉዳይ።

⭐️ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች በተለያዩ የተራዘሙ ብዙ ባለድርሻ አካላቶች የተነሱ ቢሆንም አሁንም አፈጻጸማቸው ላይ መሰረታዊ ለውጥ አልመጣም።

⏺በመሆኑም አብዛኞቹ ጀማሪ ባለሙያዎች ሙያቸውን ለመለወጥ ይገደዳሉ።

⏺የቆዩትም አማካሪ ድርጅቶች አዲስ ተመራቂዎችን ወይም ተለማማጆችን ብቻ ይዘው ከወር ወር ደመወዝ እና የቤት ኪራይ ለመክፈል ይንገታገታሉ።

❇️የኢትዮጵያ አርኪቴክቶች በዓለም እንደሚደረገው ሁሉ ሙያን እና የፈተና መስፈርትን ያማከለ ፍቃድ፣ በተጨማሪም ለአገልግሎታቸው በህግ የተደነገገ ተገቢውን ክፍያ ሊቀበሉ ይገባል።

Via ethiopian Architecture And Urbanism

@etconp
❤11
#ADVERTISEMENT

🏭🏠TSEGAYE and YOHANNES J-Bolt & PLATE 🏚🏗 🌁🌆

🧿 OUR SERVICES ⤵️

🔲Plate

⚙️  J-Bolt

⚓Anchor Bolt

➽Tie Rod

Phone : 🤳0938494506 
              🤳 0951087077
              🤳 0929044037

👉አድራሻ፦  መርካቶ ምንአለሽ ተራ ከጭድ ተራ ከፍ ብሎ

https://t.me/tsegaye2016Jbolt
❤3
👉ትራምፕ በአንድ ቢሊዮን ዶላር በሳዑዲ የሚገነቡት ግዙፍ ሕንፃ

💫በለንደን አክሲዮን ገበያ የተመዘገበው Dar Global የተባለ ሪል ስቴት ኩባንያ በአንድ ቢሊዮን ዶላር ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ግዙፍ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ሊገነባ ነው።

🚧ለቅይጥ አገልግሎት የሚውለው "Trump Plaza Jeddah" የሚገነባው በሳዑዲ ሁለተኛ ዋና ከተማ በሆነችው ጅዳ ከተማ ውስጥ በንጉስ አብዱልአዚዝ ጎዳና ላይ መሆኑ ታውቋል።

❇️የሕንፃው ፕሮጀክት ውስጥ አፓርትመንት፣ ለሆቴል፣ ለቅንጡ ቢሮዎች እና ለመዝናኛ አገልግሎት የሚውሉ አረንጓዴ ሥፍራዎችም እንዳሉት ታውቋል።

⏺የሕንፃው ባለቤትም የፕሬዝዳንት ትራምፕ ቢዝነስን የሚመራው Trump Organisation እንደገለጸው፦ የሕንፃው መገንባት የኒውዮርክን ማንሃተን ጎዳናዎች ድባብን ጅዳ ውስጥ ለመፍጠር ያስችላል ብሏል።

⏺የፕሬዝዳንት ትራምፕ ቤተሰቦችን ቢዝነስ በመካከለኛው ምስራቅ እያሰፋው ይመጣል ከተባለው በጅዳ ከሚገነባው ግዙፍ ሕንፃ በተጨማሪ፣ Dar Global ሪል ስቴት ለትራምፕ ድርጅት በዱባይ እና በኳታር ተመሳሳይ የሪል ስቴት ግንባታዎችን እያካሄደ ነው።

@etconp
❤10👍1😱1
👉የኮንስትራክሽን ቁጥጥር መረጃ ሥርዓት ይፋ ሆነ

💫ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችል የኮንስትራክሽን ቁጥጥር መረጃ ሥርዓት ይፋ ሆኗል፡፡

⏺የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በቅርቡ ይፋ አድርጎ ወደ ተግባር የገባውን ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭ መሠረት አድርጎ ነው ሥርዓቱ የለማው።

⏺ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ የኮንስትራክሽን ቁጥጥር መረጃ ሥርዓት በዘርፉ የምንሰጠውን አገልግሎት በጥራት ለመስጠትና የቁጥጥር ስራዎችን ለማዘመን አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

⏺የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ሥርዓት እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።

⏺ሥርዓቱ በዋናነት በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኮንስትትራክሽን ባለስልጣንና በኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በጋራ መልማቱ ተመላክቷል።

⏺የኮንስትራክሽን ቁጥጥር መረጃ ሥርዓት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ያሉ ከ26 ሺህ የሚልቁ ተቋማትንና ተዋናዮችን ያቀፈ ሲሆን÷ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሚረዳ ተጠቁሟል፡፡

⏺የኮንስትራክሽን ዘርፉ በጂዲፒው ላይ ያለውን እስከ 20 በመቶ የደረሰ አበርክቶ ወደ 24 በመቶ ማሳደግ የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል።

Via FBC

@etconp
❤7👍2
👉The problem shown in the image is that the reinforcing steel (rebar) cage is not properly centered within the concrete column.

⏺This issue, known as an eccentric or shifted rebar cage, results in an inadequate concrete cover on one side of the column. 

🚧Problem: The rebar cage has shifted from its correct position, leading to a lack of sufficient concrete cover. This can compromise the structural integrity of the column. 

🏷Cause: The most common cause is the failure to use spacers or cover blocks to secure the rebar cage in place before pouring the concrete.

⏺Without these spacers, the rebar can move during the concrete pouring process. 

⭐️Solution: The correct solution is to use concrete spacers or cover blocks to maintain the required distance between the rebar and the formwork, ensuring the rebar remains centered and has the proper concrete cover on all sides.

⏺If the concrete has already been poured, the affected section of the column may need to be demolished and re-poured correctly. 

@etconp
❤12👍3👏2
👉Isolated Footing

💫The Most Common Foundation in Building Construction

1. In structural engineering, an isolated footing is provided to support a single column.
2. The load from the column is distributed safely to the soil below through this footing.
3. It is the most widely used type of shallow foundation for residential and commercial buildings.

⏺Flat / Pad Footing is Simple square/rectangular slab under a column.

⏺Sloped Footing is Economical design where concrete volume is reduced.

⏺In Stepped Footing it's thickness reduced step by step for heavy loads.

⏺In Circular Footing, it is Used where columns are circular or for architectural preference.

#isolatedfooting #civilengineering

@etconp
❤20👌1
👉Shear walls are one of the most critical structural elements in high-rise buildings, especially when it comes to resisting lateral forces such as wind and earthquakes.

💫Shear walls are the backbone of lateral stability in high-rise structures. They prevent excessive sway, protect against seismic and wind forces, and enhance both safety and efficiency of the building

@etconp
👏6
‎👉የመቐለ 70 እንደርታ ጥንታዊ ኪነ ህንፃ ጥበብ

📍መቐለ:ትግራይ:ኢትዮጵያ 👇

@etconp
🥰6❤2👍2🙏1
Ethio Construction Engineering
‎👉የመቐለ 70 እንደርታ ጥንታዊ ኪነ ህንፃ ጥበብ 📍መቐለ:ትግራይ:ኢትዮጵያ 👇 @etconp
‎👉ስነ-ህንጻ 70 እንደርታ ናይ መጽለሊ ጉዳይ ጥራሕ ኣይኾነይ÷ህያው ማህደር ናይ ምህንድስና ጥበብ፣ኸባብያዊ ምትዕጽጻፍይ ባህላዊ ምሳሌይ’ዩ።
‎
‎🧱ስትራክቸራል ኢንጅነሪንግ
‎ ኣእማን ብለይ ሞርታር ይንጸፍ፣ ኣብ ምትሕንፋጽ፣ ክብደትይ ምትእስሳር ጂኦሜትሪይ ልምርኮስ 'ዩ።
‎
‎🚧መንደቕ ኣብ ግዜ ምንቅጥቃጥ መሬት በምኽንያት ምንቅጥቃጥ ልፍጠር ንዝረት ክከላኸል የኽእል፣ እዚ ለለ ሓደጋ ምፍራስ ኣባይቲ/ህድሞታት-ኣዳራሻት ይቕንስ
‎
‎⏺መሰረታት ልኣባይቲ ልዕሊ ውሕጅይ ተስሓብቲ-ነብሳት የልዕልዎ፡ እዚለለ ምልክት ኽብርይ ቅድመ-ምክልኻልይ እዩ።
‎
🎲ስርዓታት ናሕሲ

⏺‎ቀሊል ፣ ልስርዓተ-ምትንፋስ ምቾት ልህብይ ሙቐት ልከላኸልይ እዩ።
⏺ብናይ ጽሕዲ ወይ ብኣሊዕ-ዓዲ ካብ ምድሪቤት ዓምድታት ልናሕሲ ልድገፍ ፡ መብዛሕትኡ ግዜ ብምሩጽ-ሓመድ ልተሰረሐ ጭቃ ፕላስተር ልዕሸግ።
⏺መንደቕ ብዝናብ ካብ ምፍራስ ይከላኸልይ ጽላል ለለዎ ድባብ ብምፍጣር ሀም መዝሓሊ መሳርሒ-ስርዓት ኾይኑ የገልግል።
‎
‎🌡️ ምትዕጽጻፍ ምስ ስነ-ምህዳር ኸባቢ
‎
‎⏺ምቁጽጻር ሙቐት፡ረጒድ መንደቕ እምኒ፡ሀም መቆጻጻሪ መጠን ሙቐት ኾይኑ የገልግል፡ኣብ ቀትሪ-መዓልቲ ሙቐት ይምጥጥ/ናብ ውሽጢ ገዛ ከይሓልፍ ይሕዝ፡ለይቲ ለለ ኣመጣጢኑ ይለቅቕ።
‎
⏺ጥቕሚ መሽኮታት፡-ኣብ ለይቲ/ቁሪ ግዜ ብኽነት ሙቐት ካብ ከይህልይይ ፍሰት ኣየር ውሽጢ ገዛ ኣብ ምቁጽጻርይ ይጠቅም።
‎
📍‎ምንጪ ጥረ-ኣቅሑት

❇️‎1-ኸባብያዊ እምኒ ፡ መብዛሕትኡ ግዜ ባዛልት ወይ ኖራ፡ ኣብ ኸባቢታት ገጸ-ምድሪ 70እንደርታ ልግነዩ።
‎
❇️‎2-ይ ምሩጽ-ሓመድ/ጭቃ ሀም ፕላስተር፦ምስ ኹነታት ኣየር-ፀባይ ወይ ምስ ኹነታት ወቅትታት ተዓጻጻፊ ናይ ምዃን ባህሪያት ለለዎ ጥራሕ ተይኾነስ ስርዓተ-ምትንፋስ ክሕሊ ተኽእሎ ምእንቲ ክህልዎ እቲ ጭቃ ምስ ሓሰር ልተሓዋወሰ እዩ።
‎
🏷ዕንጨይቲ ፡- ካብ ኣብ ቀረባ ልግነዩ ጽሕዲ(ብኣብዝሓ ጽሕዲ-ደስኣ) : ኣውሊዕ ብዘላቒ መንገዲ ልመጽእ ኾይኑ ፡ መብዛሕትኡ ግዜ ልወለዶታት ብቀፃሊ ዳግማይ ክጥቀመሉ ይኽእል ለ እዩ።

@etconp
❤5👏2
👉What is Formwork? Difference between Shuttering, Centering and Staging.

✅🏗️ Formwork:-

🔹Formwork is a temporary structure which is used as a mould to pour the concrete. Formwork may be the horizontal or vertical arrangement, made to keep concrete in position until it gains desired strength and shape.

✅ 🏗️ Shuttering:-

🔹 Shuttering is a part of form work. it is a vertical temporary which is used to bring concrete in desired shape. Vertical formwork is known as shuttering. Formwork for the column, retaining wall, footings, Side Beams are known as shuttering.

✅🏗️ Centering:-

🔹 Centering is a part of formwork. it is used to support the horizontal members like Slabs. Formwork for slabs and bottom of Beams known as Centre

✅🏗️ Staging:-

🔹 Staging is a Temporary structure which is used to support formwork either it may be for Centering or shuttering. Staging is done by using props, jacks, H frames, cup lock system, wooden bullies.

💫you can see in the picture, you will understand better

@etconp
❤19👍7
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉ለሀገራዊ የኮንስትራክሽን ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የከፈተው እና መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የግንባታ ቁጥጥር መረጃ ሶፍትዌር ስርአት (CRIS) እና የሳይበር ደህንነት አስተዳደር በወፍበረር ሲቃኝ🎥

📹266.3 Mb ስለሆነ ዋይፋይ ይጠቀሙ🙏

@etconp
❤3