Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.28K photos
359 videos
1.99K files
3.34K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉ስለ ኦፒሲ እና ፒፒሲ የ ሲሚንቶ ኣይነቶች ትንሽ እንንገራቹ @COTMp
.
⏩OPC— Ordinary Portland cement
⏩PPC —Portland pozzollana cement

➡በሀገራችን ኢትዮጲያ በስፋት ህንፃ እና መሰረተ ልማት ግንባታ
ላይ በስፋት እየተጠቀምንባቸው የምንገኝባቸው የሲሚንቶ አይነቶች ናቸው።
የሁለቱንም የሲሚንቶ አይነቶች ጥቅም አንድነት እና ልዩነት ከዚህ በታች አጠር አድርገን እናቀርባለን።
▶ኦፒሲ/OPC/ በምጣነ ስርገት( Permeability) ከ ፒፒሲ/ PPC/ ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ ነው።
ውሃ ዘልነት /Heat of Hydration/ የኦፐሲ ከፍተኛ በመሆኑ ከፒፒሲ በተሻለ መልኩ ቶሎ የሚፈለገውን ጥረንካሬ ቀድሞ ያገኛል። በተቃራኒው ደግሞ ፒፒሲ heat of hydration ቀርፋፋ በመሆኑ ለመርጋት/curing period/ ተጨማሪ ቀናት ይወስዳል
ማለት ነው።
👉በጥንካሬ ደረጃ /Grade of Strength / ኦፒሲ 42.5R grade cement ሲሆን ፒፒሲ ደግሞ 32.5R Grade Cement ነው።
➡Note: Number represent compressive strength of
cement in MPa.
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉ስለ መሰንጠቅ (cracking ) @COTMp ...
.
⏩ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች መሰንጠቅ በMix design ትክክል አለመሆን ብቻ የሚመጣ ይመስላቸዋል ነገር ግን ለመሰንጠቅ (cracking ) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎችን ከዚህ በታች እንዲህ ዳስሰናል👇 ⚡መልካም ንባብ!
.
[፩] - አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ
.
*አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ መሰንጠቅ (cracking ) ይፈጠራል ስለዚህ የምንጠቀማቸውን ለኮንክሪት ግብዓት የሚሆኑ ቁሶችን (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ኮረኮንች) ጥራት መፈተሽ አለብን ኮንክሪቱ የብረት መዋቅር (reinforcement ) ያለው ከሆነ የብረቱን ጥራት መገምገም አለብን።
.
[፪] - መኮማተር (Shrinkage )
.
*ኮንክሪቱን በምንደባልቅበት እና ውሃ በምናጠጣበት ግዜ (Curing ) ተገቢውን ጥንቃቄ ካልወሰድን መኮማተር (shrinkage) መሰንጠቅን(cracking) ያስከትላል ።
መኮማተር (shrinkage) ለትልቅ የኮንክሪት ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው አስፈላጊውን የውሃ-ሲሚንቶ መመዛዘን (water cement ratio) ካልተጠቀምን በመኮማተር አማካኝነት መሰንጠቅ ሊፈጠር ይችላል ።
.
[፫] - ጥራት ያለው Aggregate የማንጠቀም ከሆነ
.
*Aggregate የኮንክሪትን አጠቃላይ ጥንካሬ ይወስንልናል ጥራቱ ጥሩ ያልሆነ Aggregate የምንጠቀም ከሆነ ከሲሚንቶ ጋር ተፈላጊውን ጥምረት (bond) ስለማይፈጥር ግንባታችን ሊሰነጠቅ ይችላል።
.
[፬] - መዋቅራችን ከአቅም በላይ የሆነ ክብደት ሲያስተናግድ
.
*ግንባታው / መዋቅሩ ተገቢውን ጥንካሬ ሳያገኝ በፊት ለትልቅ ክብደት የሚጋለጥ ከሆነ መሰንጠቅ ይከሰታል። በተጨማሪም መቀሰቻዎችን እና ቅስቱን (formwork ) ያለጊዜው የሚነሳ ከሆነም ግንባታችንን ለስንጣቆ ያጋልጠዋል።
.
[፭] - በትክክል ውሃ እንዲጠጣ የማይደረግ ከሆነ (improper curing )
.
*ይህ በአገራችን ከሚስተዋሉ ለመሰንጠቅ ከሚዳርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው - ውሃ በትክክል አለማጠጣት።
ኮንክሪት እንደተገነባ በተገቢው ጊዜ እና መጠን ውሃ ሊጠጣት አለበት ።
«ወንድና ሲሚንቶ ካልጠጣ ይሰነጠቃል» አይደል ሚሉት ሰካራም ወንዶች😂
.
[፮] - የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) አለመመጣጠን
.
*በጣም ትልቅ የሆነ የብረት መዋቅርን Mix ratio ትንሽ በሆነ ኮንክሪት የሙሌት ስራ ስንሰራ በብረቱ እና በኮንክሪቱ መካከል ያለ የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) non linear ይሆናል ይህ ደግሞ መሰንጠቅን ያስከትላል።
.
[፯] - በሳይት ላይ የሙሌት (casting ) ስራ ሲሰራ ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ለስራው ተገቢ የሆነ ባለሞያ (የቀን ሰራተኛን ጨምሮ) ካልተመደበ መሰንጠቅ (cracking) በሚሰራው ኮንክሪት ላይ መፈጠሩ አይቀርም።
.
ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below; እናመሰግናለን
t.me/COTMp
👆👆👆👆👆
❤1
Take a look at this picture it will give you tip about beam
👉ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን❤️
.
🙏ውብ ምሽት ተመኘን🙏
፡
⚡ቻናላችን Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ። እናመሰግናለን!
Chongqing, China 🇨🇳
Highway
Amazing
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉ዛሬ ደሞ ትንሽ ስለ ግድብ እንንገራቹ @COTMp
.
▶ግድብ (Dam) ማለት ግዙፍ አካል ሲሆን የውንዝን ሸለቆ ላይ ተገንብቶ የውሃን ተፋሰስ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚገታ ነው።
*ይህ መግታት (blockage) በውሃ ተፋሰስ ላይ መታቆርን (reservoir) ይፍጥራል ይህም ወሃውን ለተፈለገው አገልግሎት እንዲውል ቀላል ያደርገዋል።
ይህ አጋጅ ገዝፈ አካል ወይም ግድብ ከተለያዩ ቁሶች ይሰራል ፦ ኮንክሪት፣ የድንጋይና አፈር
መደምደም (compaction) ወዘተ...
.
➡ግድብ በዋነኛነት ለነዚህ አገልግሎቶች ይገነባል፦👇
.
1- ጎርፍን ለመቆጣጠር (for flood control)
.
2- ለውሃ አቅርቦት እና የመስኖ ስራ (for water supply and
irrigation)
.
3- የኤሌትሪክ ሃይልን ለማመንጨት (for electric power generation)
.
4- የአንድን ወንዝ ፍሰት ለመመጠን እና ለመቆጣጠር - (for regulation or balancing of a river flow)
.
⚡ አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉 ከ ታሪክ ማህደር በ Building Codes ዙርያ @COTMp
.
Building Codes - የሚገነቡ ህንፃዎች ማሟላት የሚገባቸውን
እስታንዳርዶች የያዘ የህጎች ስብስብ ነው፡፡ ህንፃዎች የግንባታ
ፍቃድን ለማግኘት Building Code መከተል አለባቸው፡፡
የእስታንዳርዶቹ አስፈላጊነትም - ሴፍቲ ፤ ጤና እና ጠቅላላ
የህንፃውን ደህንነት ( Structural , Mechanical , Sanitary , Fire resistance. Earth quake, Flood , Water Supply, Light, Ventilation, ወዘተ ) ለማረጋገጥ ነው ……. ኣለማችን ላይ EBCS,Eurocode , IS, BS, ወዘተ የምንላቸው የህንጻ ኮዶች ኣሉ፡፡ የኛ ደሞ EBCS(Ethioian building code of standards) ይባለል።
.
.
ከላይ የምትመለከቱት ህንፃ በሃገረ ሩሲያ - ሙሉ ለሙሉ
ከእንጨት ተገንበቶ የነበረ ረጅም ህንፃ ሲሆን Fire resistance
standard ባለሟሟላቱ የአካባቢው ባለስልጣናት አፍርሰውታል፡፡
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉ስለ TRUSS ... @COTMp
.
*Truss የምንለው Axial Load (compressive & tensile force) ብቻ የሚሸከሙ መዋቅሮች ናቸው፡፡
የትረስ ሜምበሮች የሚገናኙት በፒን ኮኔክሽን ማለትም (በአብዛኛው በብየዳና በብሎን ) ነው የሚገናኙት፡፡
*ሁለት አይነት ትረሶች አሉ Plain (2D) and Space truss (3D
ለምሳሌ የቴሌ ታወሮች )፡፡ *ትረሶችን ለህንፃና ለድልድዮች
ተመራጭ የሆኑበት ምክንያት ጠንካራና ክብደታቸው ቀላል ስለሆነ ነው፡፡ እናም ዛሬ ስለትረስ ልናወራ የቻልንበት ዋነኛ ምክንያት ብዙ ሳይቶች ላይ የግንባታ ግድፈት ስለምናይ አንዳንድ ነገር ለመጠቆም ያህል ነው::
ምንድነው ነገሩ ትረሶች ሲፈጠሩ Axial Load ብቻ እንዲሸከሙ ነው ሺርና ሞመንት መሸከም አይችሉም - Axial ፎርስም የሚሸከሙት የሚመጣውን ሎድ ቀጥታ መገናኛቸው ወይም joint ላይ ሲጫንባቸው ብቻ ነው:: ይህም ከጆይቱ ነው ወደ ሜምበሮች ሄዶ ከዛ ነው ወደ ኮለን ወይም ቢም የሚሄደው - ሳይት ላይ ግን ፐርሊኑን መሃል ሜምበሮቹ ላይ ሲበይዱት ይታያል - joint ላይ ነው መበየድ ወይም መታሰር ያለበት - ሳይት ላይ የሚደረገው ከሳይንስ ውጪ ነው ሃይለኛ ንፋስ ወይም ዝናብ ያለባቸው አካባቢዎች ይህ ነገር አሳሳቢ እና ኣደጋም ሊያደርስ ይችላል፡፡
Share Share Share
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉ስለ Road structure components @COTMp
.
*Super Elevation = የመንገድ Curve ላይ መኪናን ከመንገዱ
ውጪ የሚጎትትን Centrifugal Force ለመቋቋም የአስፓልቱ
ከርቭ ዙሪያውን ከፍ ተደርጎ ይሰራል - ለሹፌሩም ምቾትን ይሰጣል እንዲሁም በሚታጠፍበት ግዜ ኣደጋን ይቀንሳል፡፡
.
*Pavement Crown = ለፍሳሽ ተብሎ የአስፓልቱ መሃል ከዳርኞቹ ይልቅ ከፍ ተደርጎ ይሰራል የሚሰራ ኮምፐነንት ነው። ሌሎችም components ከላይ በ ፒክቸሩ እንደምታዩት ዲፋይን ተደርገዋል
.
ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
Flat slab with drop panel
▶️ለ ውድ የ ቻናላችን ቤተሰቦች😍
፡
👉እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለ ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ።🙏
.
⚡ቻናላችን Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ። እናመሰግናለን!
👉ውድ የቻናላችን ተከታታዮች
፡
▶️ዛሬ እናንተን አሳታፊ እና ተሸላሚ የሚያደርግ ጥያቄ ይዘን ቀርበናል
፡
▶️ይህ ከላይ የምትመለከቱት የየትኛው የአዲስ አበባ ህንፃ (Interior) ነው?
፡
▶️ትክክለኛ መልስ በፍጥነት ለመለሱ 3 ሰዎች የ25 👌 50 👌 ፡እና 👌 የ 100 ሜጋ ባይት የገና ስጦታ ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡
፡
▶️ @Philemona7 በሚለው ሊንክ በመጫን መልሱን inbox ያድርጉልን፡፡ ▶️ መልሱን ስትልኩ አብራችሁ ስም እና ስልክ ቁጥር ላኩልን፡፡
Ethio Construction Engineering
👉ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ፡ ▶️ዛሬ እናንተን አሳታፊ እና ተሸላሚ የሚያደርግ ጥያቄ ይዘን ቀርበናል ፡ ▶️ይህ ከላይ የምትመለከቱት የየትኛው የአዲስ አበባ ህንፃ (Interior) ነው? ፡ ▶️ትክክለኛ መልስ በፍጥነት ለመለሱ 3 ሰዎች የ25 👌 50 👌 ፡እና 👌 የ 100 ሜጋ ባይት የገና ስጦታ ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡ ፡ ▶️ @Philemona7 በሚለው ሊንክ በመጫን መልሱን inbox ያድርጉልን፡፡ ▶️…
👉የተሸላሚዎች ስም ዝርዝር 👇 ስልክ ቁጥራቹ ላኩልን
1. @Abuderdae
2. @ATLAS2025
3. TOYB
.
👏👏👏👏👏
▶️በጣም ብዙ ሰው ትክክለኛው መልስ ኣግኝትቶታል ነገር ግን ፈጥነው የመለሱት 3ቱ ናቸው፡፡ ለሁላችሁም የተሳተፋቹ ከልብ እናመሰግናለን፡፡🙏
.
🇪🇹 የጥያቄው መልስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት የተገነባው በ1965 ዐ.ም የሚገኘው ከብሔራዊ ትያትር ፊት ለፊት 🇪🇹
፡
▶️መልካም በዓል❤️
▶️እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ፡፡😍
.
⚡አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።እንወዳችዋለን፡፡❤️
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉 የአፈርን የመሸከም አቅም (BEARING CAPACITY) እንዴት እንጨምር?? ላላችሁን...
.
* ሶስት አይነት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከያ ቴክኒኮች አሉ - mechanical, chemical & other stabilization techniques
.
A) ሜካኒካል ውስጥ :-
.
1. Compaction - አፈሩን ስንጠቀጥቀው density/ unit
weight ይጨምራል ያ ማለት ደግሞ አፈርን የመሸከም አቅም ጨመረ ማለት ነው::
.
2. Excavation and Replacement – expansive soil ከሆነ ወይም ሌላ አስቸጋሪ አፈር ከሆነ ይህን መጠቀም እንችላለን
.
3. Mixing of Different Soils - ሳይታችን ላይ ያለው አፈር
coarse ወይም fine ብቻ ከሆነ ወይም ደግሞ አፈሩ አንድ አይነት
ብቻ ፀባይ ካለው ከተለያዩ አፈሮች ጋር በመደባለቅ የተሻለ የአፈር
ፀባይ ማግኘት እንችላለን
.
B) ኬሚካል :-
.
1. Lime stabilization - ይህንን የምንጠቀመው በአብዛኛው
ለexpansive soil ነው፡፡ አፈሩን ከ Lime ጋር በመደባለቅ
plasticity መቀነስ እንችላለን፡፡ የlime መጠኑ ከሚያስፈልገው
በላይ ከበዛ ግን B.C. ይቀንሳል፡፡
.
2. Cement stabilization - ሲሚንቶን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት መንገድ ነው፡፡ concrete
pavement ስር መጠቀም እንችላለን በአብዛኛው ለአየር
መንገዶች ፤ ለአውራ ጎዳናዎች ፤ ግድቦችን ከሽርሸራ ለመከላከል
ወ.ዘ.ተ. መጠቀም እንችላለን፡፡
.
3. Asphalt stabilization - አስፓልትን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት ዘዴ ነው በተለይም ለcohesive
አፈሮች፡፡ አፈሩን water proof በማድረግና ውሃማነትን በመቀነስ
B. Cን መጨመር እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ይህንን ድብልቅ
ለመንገዶች እንደ base course መጠቀም እንችላለን፡፡
.
.
C) ሌሎች የአፈርን ባህሪ ማስተካከያ መንገዶች:-
.
1. Drainage - ፓይፖችን አፈር ውስጥ በመቅበር ወይም
ጉድጓዶችን በመጠቀም ground water የምንቆጣጠርበት ነው
.
2. Precompression - ግንባታ ከመጀመራችን በፊት አፈሩ ላይ
ሎድ በመጫን ኮምፓክት የምናደርግበት ዘዴ ነው
.
3. Dynamic Stabilization
.
ሀ) Blasting - ቦምብ ወደውስጥ በመቅበር በፍንዳታው አፈሩ ይጠቀጠቃል::
.
ለ) Compaction Piles - ፓይሎችን ወደውስጥ በማስገባት
አፈሩ ወደ ጎን እንዲሸሽና እንዲጠቀጠቅ ማድረግ ይቻላል፡፡
ፓይሉን ስናስወጣውም በተቦረቦረው ጉድጓድ ውስጥ የተሻለ አፈር በማስገባት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከል እንችላለን፡፡
.
4. Injection And Grouting - አፈሩን በሲሚንቶ ወይም
በተለያዩ chemical ውህዶች በpressure በመምታት ground
water ና settlement መቆጣጠር እንችላለን፡፡
.
የተሻለውን ዘዴ ለመምረጥ የአፈሩንና የአካባቢውን ሁኔታ ፤
ኢኮኖሚ ፤ ሴፍቲና የመሳሰሉትን ነገሮች ማጤን አለብን፡፡
.
👉FOR MORE UPDATED AMHARIC CONSTRUCTION INFO JOIN US HERE 👇
http://t.me/COTMp
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉 ከ ታሪክ ማህደር በ Building Codes ዙርያ @COTMp
.
Building Codes - የሚገነቡ ህንፃዎች ማሟላት የሚገባቸውን
እስታንዳርዶች የያዘ የህጎች ስብስብ ነው፡፡ ህንፃዎች የግንባታ
ፍቃድን ለማግኘት Building Code መከተል አለባቸው፡፡
የእስታንዳርዶቹ አስፈላጊነትም - ሴፍቲ ፤ ጤና እና ጠቅላላ
የህንፃውን ደህንነት ( Structural , Mechanical , Sanitary , Fire resistance. Earth quake, Flood , Water Supply, Light, Ventilation, ወዘተ ) ለማረጋገጥ ነው ……. ኣለማችን ላይ EBCS,Eurocode , IS, BS, ወዘተ የምንላቸው የህንጻ ኮዶች ኣሉ፡፡ የኛ ደሞ EBCS(Ethioian building code of standards) ይባለል።
.
.
ከላይ የምትመለከቱት ህንፃ በሃገረ ሩሲያ - ሙሉ ለሙሉ
ከእንጨት ተገንበቶ የነበረ ረጅም ህንፃ ሲሆን Fire resistance
standard ባለሟሟላቱ የአካባቢው ባለስልጣናት አፍርሰውታል፡፡
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉የቻይናው Three Gorges Dam አስገራሚ ቁጥሮች @COTMp
.
* የግድቡን መሰረት ለመስራት 80,000 ድማሚት ሲጠቀሙ ይህ
ማለት ከ20 የሂሮሺማ የኒውክሌር ጥቃቶች ጋር እኩል ነው፡፡
.
* የግድቡ Reservoir ርዝመት 660ኪ.ሜ ነው - ይህም ማለት
ከአ.አ ማይጨው እንደማለት ነው፡፡
.
*18200 MW ያመነጫል ይህም 7965mw ከሚያመነጨው
የጃፓኑ Kashiwazaki-Kariwa የዓለማችን ትልቁ የኒውክሌር
ማብሊያ 230 ፐርሰትን ይበልጣል፡፡ ከህዳሴ ግድብ ደሞ 300 ፐርሰት/ 3 እጥፍ ይበልጣል፡፡
.
*ግንባታው 30 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት ፈጅቷል - ይህም
ማለት 30 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት ተጠቅመን 1 ሜትር
ዲያሜትር ያለው ድፍን ኮንክሪት pipe ብንሰራ ዓለምን አንድ ዙር
መዞር ይችላል፡፡
.
*463,000 ቶን ብረት የተጠቀሙ ሲሆን - ይህን ያህል ቶን ብረት
ተጠቅመን 63 ኤፍል ታወሮችን መገንባት እንችላለን፡፡
.
*በአማካኝ 77.5 ሜትር width ሲኖረው ይህም ከማንኛውም
አቅጣጫ የሚመጡ የሚሳኤል ጥቃቶችን እንዲቋቋም
ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም ከግዝፈቱ የተነሳ የቀን እርዝመት
በማይክሮ ሰከንድ እንዲጨምር አድርጓል፡፡ ከታላቁ የቻይና ግንብ
ቀጥሎ ከስፔስ ላይ የሚታይ የቻይና ሁለተኛው የሲቪል
ኢንጂነሪንግ ውጤት ነው፡፡
.
*ግንባታው ከ630 ቢሊየን ብር በላይ ሲፈጅ በ 2012 ተጠናቆ ከ1 ዓመት ከ6 ወር በኋላ ሙሉ ወጪውን መልሷል፡፡
.
*ሀብታሟ ሀገር ሳውዲ አረቢያ ከነዳጅ ፣ ከእንፋሎት ወዘተ
55000MW ስታመነጭ ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በትንሹ
45000MW ከውሃ ብቻ ማመንጨት ትችላለች
* እስካሁን ባለው 4000MW አይሆንም የምናመነጨው፡፡
18200 MW የሚያመነጨው 630 ቢሊየን ብር ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የመለሰ ኢትዮጵያ 45000 MW ስታመነጭ ምን ያህል
ብር ማግኘት እንደምትችል አስቡት።
ለማንኛውም Hydraulic Engineering ይህን ያህል ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል፡፡
▶️ውቢትዋ ደሴ ከተማ ❤️
፡
👉የናንተ ከተማም ላኩልን
፡
🙏ወብ ምሽት ተመኘን😍
፡
⚡ቻናላችን Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ። እናመሰግናለን!