Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.2K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
#ADVERTISEMENT

Ab Con General Waterproofing Works

የውሃ አቅርቦትዎን በከፍተኛ ደረጃ ለመጨመር በፋይበርግላስ የውሃ ማጠራቀሚያ ሴፕቲክ ታንክ ስርዓታት ይጠቀሙ !!!

◇ በፋይበርግላስ  የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ በጉድጓድ ዉስጥ ከሚመጣ የሽንት ቤት ፍሳሾች ሙሉ ለሙሉ የተከለለ ስለሚሆን ለዉሀ ብክለት  አስተማማኝ ነዉ ።
◇በፋይበርግላስ  የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ መበስበስ እና መሰነጣጠቅ የሚባል ነገር ፈፅሞ አይታሰብም።
◇በፋይበርግላስ የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ ለማፅዳት በቀላሉ የሚመች ሲሆን ፣ በዉሀ ዉስጥ በፍጥነት ለሚራባዉ አልጌ ደግሞ ፈፅሞ የማይመች ነዉ ።
◇በፋይበርግላስ  የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ ከመሬት በታች በጉድጎድ ዉስጥ ስለሚሰራ ቦታ ቆጣቢ ነዉ።
◇ለመዋኛ ገንዳ

◇ ለመኖሪያ ቤቶች ፣፤ሪል እስቴቶች ፤ድርጅቶች ፤ሆስፒታሎች፥ ሆቴሎች ፥ ኤምባሲዎች፥የእርሻ ቦታዎች ፥ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወዘተ የኛ ተጠቃሚዎች ናቸዉ።

🤳0913967277
     0968966602
❤3
👉CONSTRUCTION MANAGEMENT TECHNIQUES

💫Here are the key Construction Project Management Techniques, clearly structured and suitable for learning, or teaching,

1️⃣ Planning & Scheduling

✓ Work Breakdown Structure (WBS)

✓ Gantt Charts & Bar Charts

✓ Critical Path Method (CPM)

✓ Milestone Planning

📌 Ensures timely project delivery

2️⃣ Cost Management

✓ Detailed cost estimation

✓ Budget allocation

✓ Cash flow forecasting

✓ Cost variance analysis

📌 Controls overspending

3️⃣ Quality Management

✓ Quality Assurance (QA)

✓ Quality Control (QC)

✓ Material testing & inspections

✓ Standard compliance (codes & specs)

📌 Delivers durable and safe structures

4️⃣ Time Management

✓ Activity sequencing

✓ Resource leveling

✓ Progress tracking

✓ Delay analysis

📌 Avoids schedule overruns

5️⃣ Risk Management

✓ Risk identification

✓ Risk assessment & ranking

,✓ Mitigation planning

✓ Contingency reserves

📌 Minimizes project uncertainties

6️⃣ Resource Management

✓ Manpower planning

✓ Equipment allocation

✓ Material procurement planning

✓ Productivity monitoring

📌 Optimizes site efficiency

7️⃣ Communication Management

✓ Regular site meetings

✓ Progress reports

✓ Stakeholder coordination

✓ Documentation control

📌 Ensures clarity & teamwork

8️⃣ Safety Management

✓ Safety plans & toolbox talks

✓ PPE enforcement

✓ Site hazard analysis

✓ Accident reporting

📌 Protects workers and assets

9️⃣ Procurement Management

✓ Vendor selection

✓ Contract management

✓ Material delivery scheduling

✓ Inventory control

📌 Prevents work stoppages

🔟 Monitoring & Control

✓ Key Performance Indicators (KPIs)

✓ Earned Value Management (EVM)

✓ Site audits

✓ Corrective actions

📌 Keeps the project on track

@etconp
❤10👍5🥰1
የመውጫ ፈተና (Exist Exam) የሚሰጥበት ጊዜ ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑ ተገለጸ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መርሃ-ግብር መሰረት፣ የ2018 ትምህርት ዘመን አጋማሽ የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16 - 27 ቀን 2018 ዓ.ም ይሰጣል።

ይህንን የፈተና ፕሮግራም ተቋማት ለተማሪዎቻቸው እያሳወቁ ይገኛሉ።

Via tikvahethiopia

@etconp
❤4👍2
👉ቻይና በ10.5 ቢሊዮን ዶላር የምትገነባው ግዙፍ ካናል

ይህ በደቡብ ቻይና ጓንግዚ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ግዙፍ የውሃ መስመር (ካናል) እ.ኤ.አ. በ2026 ማብቂያ ላይ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፤

ቻይና ለዚህ ግዙፍ የፒንግሉ ካናል (Pinglu Canal) ግንባታ 10.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድባለች፤

ግንባታውም በአራት ዓመታት ውስጥ ተጠናቆ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፤


የፕሮጀክቱ ዋነኛ ዓላማ የቻይና ቁንጮ የኤክስፖርት መዳረሻ ከሆነችው ደቡብ ምስራቅ እስያ ጋር ያለውን የንግድ ትስስር ማጠናከር ነው፤

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የባህር በር ለሌላቸው የቻይና ደቡብ ምዕራብ ግዛቶች ቀጥተኛ የባህር ላይ መርከብ መስመር መዳረሻን የሚፈጥር ሲሆን፥ ይህም በቻይና የሀገር ውስጥ ክፍሎች እና በጎረቤት ሀገራት መካከል የሚደረገውን የሸቀጦች ትራንስፖርት ፈጣን እና ርካሽ ያደርገዋል፤


የጓንግዚ ዙዋንግ ራስ ገዝ ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን ናኒንግን ከቶንኪን ባሕረ ሰላጤ ጋር የሚያገናኘው ይህ የ134 ኪሎ ሜትር የውሃ መስመር፥ ቻይና ባለፉት መቶ ዘመናት የገነባችው የመጀመሪያው ትልቅ ካናል ነው።

Via South China Morning Post

@etconp
❤9👍2
👉"የ100 ሚሊዮን ዶላሩ የሜጋ ፕሮጀክት ጉዞ"

🚧የአርጀንቲናው ሪቨር ፕሌት ስታዲየም "ሞኑሜንታል" ወደ አዲስ ምዕራፍ እየመጣ ነው።

💫በአርጀንቲና እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ እንደ ሪቨር ፕሌት "ሞኑሜንታል" ስታዲየም ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ስፍራ የለም፤ አሁን ደግሞ ከታሪክ ማህደርነት ወደ ዓለም አቀፍ የምህንድስና ጥበብ ጎራ ዘው ብሎ ገብቷል፤

ይህ ስታዲየም የክለብ ግጥሚያዎች ብቻ ሳይሆን የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ታላላቅ ድሎችን የተቀዳጀበት ታሪካዊ መድረክ ነው፤


አሁን ግን ክለቡ ይፋ ባደረገው አዲስ የማስፋፊያ እቅድ፣ ስታዲየሙን ወደ 101,000 ተመልካቾች ከፍ ለማድረግ መወሰኑ ስታዲየሙን ከታሪካዊነቱ ባለፈ ወደ ዓለም አቀፍ የመሠረተ ልማት ግዙፍነት እንዲሸጋገር ያደርገዋል፤

ይህ ፕሮጀክት ስታዲየሙን በዓለም ላይ ከባርሴሎናው ካምፕ ኑ በመቀጠል በክለብ ደረጃ ሁለተኛው ግዙፍ ስታዲየም ያደርገዋል። ነገር ግን "ለኢንፍራኮን ሚዲያ" ዜና አንባቢዎች ትልቁ ዜና የመጠን መጨመሩ ብቻ ሳይሆን፣ የተጠቀመው እጅግ ውስብስብ የምህንድስና ጥበብ ነው።


ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚፈጀው ይህ ፕሮጀክት በዋናነት በሦስት የቴክኖሎጂ ምሰሶዎች ላይ ያተኩራል፦

የጣራው መዋቅር (Roof Engineering)


ፕሮጀክቱን የሚመራው የጀርመኑ SBP ድርጅት እንደ አሊያንዝ አሬና ያሉ ስራዎችን የሰራ ሲሆን፣ እዚህም "Lightweight Tension Structure" የተሰኘ ቴክኖሎጂን ይጠቀማል። ይህም ግዙፍ ዓምዶችን ከመጠቀም ይልቅ በብረት ኬብሎች እና በቀላል ክብደት ቁሶች በመታገዝ የተመልካቹን እይታ ሳይጋርዱ ስታዲየሙን መሸፈን ያስችላል።

የመቀመጫዎች አቀማመጥ (Civil Works)


ቀደም ሲል የነበረውን የሩጫ ትራክ በማጥፋት ተመልካቹ ወደ ሜዳው ጠጋ እንዲል (እስከ 12 ሜትር) ይደረጋል። ይህ ደግሞ አሁን ያለው የስታዲየም መሠረት ተጨማሪ 16,000 ተመልካቾችን እንዲሸከም "Foundation underpinning" የተሰኘ የመሠረት ማጠናከሪያ ስራን ይጠይቃል።

ዘመናዊ መሠረተ ልማት (Smart Stadium)


ግንባታው የWi-Fi 6 አውታረ መረብን እና ለኃይል ፍጆታ የሚረዱ የፀሐይ ብርሃን ኃይል ሰብሳቢዎችን (Solar panels) በማካተት ስታዲየሙን የቴክኖሎጂ ማዕከል ያደርገዋል።

ኢኮኖሚያዊ እና ስልታዊ ፋይዳ


ይህ ግንባታ በአርጀንቲና የመሠረተ ልማት ዘርፍ ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል። ፕሮጀክቱ በራሱ የሚቆም (Self-sustaining) ሲሆን፣ ክለቡ ግንባታውን ለማከናወን የወሰደውን ብድር የሚከፍለው ስታዲየሙ በሚያስተናግዳቸው ዓለም አቀፍ የስፖርት እና የሙዚቃ ኮንሰርቶች በሚገኝ ተጨማሪ ገቢ ነው።

በመጨረሻም፣ ይህ ማስፋፊያ ለ2030 ዓለም ዋንጫ ዝግጅት ትልቅ ግብዓት ነው። አርጀንቲና የዓለም ዋንጫውን ከፊል አስተናጋጅ ስለሆነች፣ ሞኑሜንታል የሀገሪቱን ገፅታ ለዓለም የሚያስተዋውቅበት ዋነኛ መስኮት ይሆናል።

በአጠቃላይ፣ የሪቨር ፕሌት አዲስ እቅድ ስፖርታዊ ፍላጎትን፣ የኢኮኖሚ ብልህነትን እና የምህንድስና ልቀትን በአንድ ላይ ያቆራኘ ታላቅ እርምጃ ነው።

#InfrastructureNews #CivilEngineering #StadiumRenovation #RiverPlate #SmartStadium

@etconp
❤7
👉ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና መሠጠት ጀመረ

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ተገጣጣሚ ቤቶችን ከሚገነባ የግል  ድርጅት ጋር በመተባበር ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና መሥጠት ጀምሯል።

የኢንስቲትዩቱ የሲቪል ፋካሊቲ ዲን ወ/ሮ ሰሎሜ ፋንታሁን በአገራችን ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ አጭር እድሜ ያለው ቢሆንም ሠፊ ፍላጎት እየተፈጠረ እንደሚገኝ ገልጸው ይህንን ፍላጎት ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ለማስቀጠል ያለመ ስልጠና መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ስልጠናው 16 ለሚሆኑ አስልጣኞች የተዘጋጀ ሲሆን ለሁለት ወር የሚቆይ በተግባር እና በንድፈሃሳብ የተደገፈ እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል።

ቤቶቹ በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ስታንዳርድ የተዘጋጀላቸው  መሆናቸውን  የተገለፀ ሲሆን የዘንድሮ ተመራቂዎች  የማህበረሰብ አገልግሎት የቤት ግንባታ ላይ የሚተገበር እንደሆነም ተገልጿል፤

መሠል ስልጠናዎች ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ለማስረጽ እና ለሥራ ፈጠራ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረውም በስልጠናው ላይ ተብራርቷል፡፡

ሥራና ክህሎት ሚኒስትር

@etconp
❤6👏6
👉የግንባታ ወጪን ለመቀነሰ የሚረዱ አማራጭ ዘዴዎች

💫ለህንፃ ግንባታ የሚያስፈልጉ እንደ ብረት፣ ሲሚንቶ፣ ብሎኬት፣ ጠጠር ያሉ ጥሬ ዕቃዎች ዋጋ እ.ኤ.አ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ከ1000 ፐርሰንት በበለጠ ዋጋ እየጨመረ የመሄዱ ጉዳይ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡

ለዚህ መንስኤ በዋነኝነት የሚጠቀሱት የማምረቻ፣ የሠራተኛ ጉልበት፣ የትራንፖርት ዋጋ መጨመር እና ተያያዥነት ያለው የዋጋ ግሽበት ናቸው፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ልዩ ባህሪ ደግሞ ጥሬ ዕቃዎችን በመግዛት እና በመደባለቅ፣ ጠንካራ ረጅም ዕድሜ የሚኖረው እና ውብ የሆኑ ህንፃዎችን መገንባት ነው፡፡

ከዚህ በመነሳት የኮንስትራክሽን ኤክስፐርቶች የጥሬ ዋጋ ንረትን በመቋቋም ወጪን ለመቀነስ ያስችላሉ ብለው በቀዳሚነት ያስቀመጧቸውን አሠራሮች መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ጠንካራ የዕቅድ ፕላን መዘርጋት

እንደ ማንኛውም የንግድ ዘርፍ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የመጨረሻ ልብ ማትረፍ ነው፡፡ ይህንን ትርፍ ለማግኘት ለግንባታው የሚያስፈልገውን በጀት እና ዝርዝር የግንባታ ሂደቶች የተመለከተ ጠንካር ያለ የዕቅድ ፕላን መቀየር ነው፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከሚያስችሉ ጠንካር ያሉ የዕቅድ ፕላኖች ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን ካለው  ነባራዊ ሁኔታ በመመርመር ቀደም ብሎ ማከማቸት በእያንዳንዱ የግንባታ ሂደት የሚያስፈልጉ ግብዕቶችን ቀደም ብሎ ማዘጋጀት ናቸው፡፡

2. መደበኛ የሆነ እና የሚደጋገም ዲዛይን

አንድ ህንፃ ከመሬት ተነስቶ እያደገ በሄደ ቁጥር፣ የሚይዛቸው የክፍል ገፅታዎች መደበኛ የሆነ ስፋት እና ገፅታ የተለበሱ እንደሆኑ ማድረግ ዋጋን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

ህንፃው ባደገ ቁጥር የውስጥ ገፅታ ዲዛይን የሚለዋወጥ ከሆነ፣ የጥሬ ቁስ ብክነት ያስከትላል፡፡ ለተለዋጭ ዲዛይን የሚሆን ሌላ ጥሩ ቁስ መግዛትን ይጠይቃል፡፡

እስከ ዘለቄታው ለግንባታ የሚያገለግሉ ቁሶችን ቀደም ብሎ ማከማቸት እንዳይቻል ያደርጋል፡፡ ለግንባታ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች በየጊዜው እንዲለዋወጡ ያደርጋል፡፡ የሥራ ፍጥነት እና ሂደትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ጋሬጣ ይፈጥራል፡፡

3.አማራጭ ቁሶችን መጠቀም

በህንፃ ግንባታ ህንፃው ለወደፊት የሚሰጠውን አገልግሎት ከግምት በማስገባት ረሳይክልድ የሆኑ ብረቶችን ከጂፕሰም እና ከጣውላ የሚዘጋጀ የውስጥ ማከፋፈያ ግርግዳዎችን መጠቀም፣ ተገጣማሚ ብሎኬቶች እና ግርግዳዎችን መጠቀም የህንፃው የግንባታ ዋጋ እንዲቀነስ ያደርጋሉ::

4. የግንባታ ባለሙያዎች ወጪን መቀነስ

የግንባታ ሂደትን በጊዜ ሰሌዳ ሸንሽኖ አስፈላጊውን ቁስ ቀደም ብሎ በማሟላት፣ ለግንባታው የሚያስፈልገውን ባለሙያ በጊዜው በመቅጠር ግንባታ የሚያስፈልግ የጉልበት (የሙያ) ክፍያ ወጪን በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ ይረዳል::

5. ጊዜ እና ገንዘብን መቆጠብ

ለግንባታ የሚያስፈልጉ እና ሥራን የሚያቀላጥፉ እንደ ሎደር፣ ኤክስካቫተር፣ ፓሌት (የብረት ምንጣፍ) የኮንክሪት ምንጣፍ ተሻካሚ፣ ተገጣጣሚ ብረቶችን፣ ግንባታው ሳይቋረጥ በሚፈለግበት ጊዜ ወዲያው የሚቀርቡበትን ቀደም ያለ ዝግጅት ማድረግ ለግንባታ የሚያስፈልግ ጊዜ በመቆጠብ፣ በፍጥነት ወደሚፈለገው ትርፋማ ጉዞ ለማምራት በተዛማጅነትም ወጪን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ብርሃን የሚያስገቡ መስታወቶችን እና የፀሀይ ብርሃንን ወደ ኤሌክትሪክ የሚለውጡ ግርግዳዎችን ማካተት፣ ህንፃው ከተጠናቀቀ በኃላ ዘላቂ የኃይል ፍጆታ (ገንዘብ) እንዲቆጠብ ያደርጋል
፡፡

⭐️የ YouTube ቻናላችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ SubScribe አረገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
❤16👍1
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት
                 ቁ.3 ቄራ

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤1🥰1
በ3.8 ቢሊዮን ብር በጀት የሚገነባው የቁንዲ - ጎሮዳሞሌ - ጅብሪል የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት አፈጻጸም 44.7 በመቶ ደረሰ

የሶማሌ እና የኦሮሚያ ክልሎችን በአስፋልት መንገድ የሚያስተሳስረውና 77.8 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የሎት 3 ቁንዲ - ጎሮዳሞሌ - ጅብሪል የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም 44.7 በመቶ ደረሰ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለግንባታው 3.8 ቢሊየን ብር በላይ የበጀለት ሲሆን፣ ግንባታውን በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት በፕሮጀክቱ ላይ የተለዋዋጭ መንገድ፣ የጠረጋ፣ የማፋሰሻ ቱቦ እና የፉካ ሥራዎች፣ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የካፒንግ እንዲሁም በርካታ የስትራክቸር ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ከቁንዲ ከተማ ተነስተው እስከ ጅብሪል ከተማ የሚዘልቀው ይህ መንገድ፣ በከተማ 19 ሜትር እንዲሁም በገጠር 8 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነው እየተገነባ የሚገኘው።

የግንባታ ሥራውን ኤምሲጂ ኮንስትራክሽን ኃ/የ/ማ እያከናወነው ሲሆን፣ የማማከር እና የቁጥጥር ስራው ደግሞ በኮር አማካሪ መሀንዲሶች አ.ማ እየተመራ ይገኛል።


ፕሮጀክቱ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ቀደም ሲል ከቁንዲ እስከ ጅብሪል ለመጓዝ ይወስድ የነበረውን የ8 ሰዓት ጉዞ ወደ 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በማሳጠር ለትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ትልቅ እረፍትን ይሰጣል።

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት አቋርጧቸው የሚሄዱ ከተሞችን፣ ወረዳዎችን እና ቀበሌዎችን በአስፋልት መንገድ ከማገናኘቱም በላይ፣ ለአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገት ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

የዚህ ፕሮጀክት አካል የሆኑት የጨረቲ - ሀገረመቆር (ክፍል 1) እና የሀገረመቆር - ቁንዲ (ክፍል 2) የመንገድ ግንባታዎች ቀደም ብለው ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው ይታወሳል።


@etconp
❤3
🧪 Admixture Compatibility: Key Lab Tests for Concrete Quality! 🧪

In concrete production, ensuring admixture compatibility with cement is crucial to avoid issues like rapid stiffening, slump loss, or strength reduction.
Here’s a quick guide to essential laboratory tests perfect for site engineers and quality supervisors.

Core Tests Explained
• Marsh Cone Test: Measures initial & final flow time of cement slurry to detect viscosity changes & set retardation.
• Mini Slump Test: Assesses workability & instability risks in fresh paste.
• Rheological Measurements: Tracks flow behavior, yield stress, & viscosity under varying dosages.
• ASTM Air Content: Ensures proper entrainment without excess.
• Strength Tests: Flexural strength (ASTM) evaluates early-age bending performance, while compressive strength (ASTM C39) measures 28-day load-bearing capacity.

Why It Matters:
Incompatibility (e.g., high C3A cements with certain WRAs) leads to hydration irregularities & poor durability—always trial mix first! Ethiopian standards align with ASTM C494 for admixtures.

Via Yonatan Tadesse, PMP®️

#ConcreteTech #Admixtures #ConstructionPro #CivilEngineering #QualityControl@ETCONp

@etconp
❤5