Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.2K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
በ3.8 ቢሊዮን ብር በጀት የሚገነባው የቁንዲ - ጎሮዳሞሌ - ጅብሪል የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት አፈጻጸም 44.7 በመቶ ደረሰ

የሶማሌ እና የኦሮሚያ ክልሎችን በአስፋልት መንገድ የሚያስተሳስረውና 77.8 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የሎት 3 ቁንዲ - ጎሮዳሞሌ - ጅብሪል የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም 44.7 በመቶ ደረሰ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለግንባታው 3.8 ቢሊየን ብር በላይ የበጀለት ሲሆን፣ ግንባታውን በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት በፕሮጀክቱ ላይ የተለዋዋጭ መንገድ፣ የጠረጋ፣ የማፋሰሻ ቱቦ እና የፉካ ሥራዎች፣ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የካፒንግ እንዲሁም በርካታ የስትራክቸር ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ከቁንዲ ከተማ ተነስተው እስከ ጅብሪል ከተማ የሚዘልቀው ይህ መንገድ፣ በከተማ 19 ሜትር እንዲሁም በገጠር 8 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነው እየተገነባ የሚገኘው።

የግንባታ ሥራውን ኤምሲጂ ኮንስትራክሽን ኃ/የ/ማ እያከናወነው ሲሆን፣ የማማከር እና የቁጥጥር ስራው ደግሞ በኮር አማካሪ መሀንዲሶች አ.ማ እየተመራ ይገኛል።


ፕሮጀክቱ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ቀደም ሲል ከቁንዲ እስከ ጅብሪል ለመጓዝ ይወስድ የነበረውን የ8 ሰዓት ጉዞ ወደ 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በማሳጠር ለትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ትልቅ እረፍትን ይሰጣል።

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት አቋርጧቸው የሚሄዱ ከተሞችን፣ ወረዳዎችን እና ቀበሌዎችን በአስፋልት መንገድ ከማገናኘቱም በላይ፣ ለአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገት ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

የዚህ ፕሮጀክት አካል የሆኑት የጨረቲ - ሀገረመቆር (ክፍል 1) እና የሀገረመቆር - ቁንዲ (ክፍል 2) የመንገድ ግንባታዎች ቀደም ብለው ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው ይታወሳል።


@etconp
❤3
🧪 Admixture Compatibility: Key Lab Tests for Concrete Quality! 🧪

In concrete production, ensuring admixture compatibility with cement is crucial to avoid issues like rapid stiffening, slump loss, or strength reduction.
Here’s a quick guide to essential laboratory tests perfect for site engineers and quality supervisors.

Core Tests Explained
• Marsh Cone Test: Measures initial & final flow time of cement slurry to detect viscosity changes & set retardation.
• Mini Slump Test: Assesses workability & instability risks in fresh paste.
• Rheological Measurements: Tracks flow behavior, yield stress, & viscosity under varying dosages.
• ASTM Air Content: Ensures proper entrainment without excess.
• Strength Tests: Flexural strength (ASTM) evaluates early-age bending performance, while compressive strength (ASTM C39) measures 28-day load-bearing capacity.

Why It Matters:
Incompatibility (e.g., high C3A cements with certain WRAs) leads to hydration irregularities & poor durability—always trial mix first! Ethiopian standards align with ASTM C494 for admixtures.

Via Yonatan Tadesse, PMP®️

#ConcreteTech #Admixtures #ConstructionPro #CivilEngineering #QualityControl@ETCONp

@etconp
❤5
👉 INTERCON Construction Chemicals 

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Wall Putty, Prime Coat
● Concrete Repair Mortar
● Floor hardener, Epoxy
● Grout, Self-level mortar
● Quartz paint, Contextra
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Geotextiles and other construction chemicals and materials

☎️ Tel: 0961955555

🔹 Address 1: Signal road, around
Dinberwa Hospital

🔹 Addres 2: Wellosefer, Infront of
Dani Plaza
#ADVERTISEMENT

Ab Con General Waterproofing Works

የውሃ አቅርቦትዎን በከፍተኛ ደረጃ ለመጨመር በፋይበርግላስ የውሃ ማጠራቀሚያ ሴፕቲክ ታንክ ስርዓታት ይጠቀሙ !!!

◇ በፋይበርግላስ  የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ በጉድጓድ ዉስጥ ከሚመጣ የሽንት ቤት ፍሳሾች ሙሉ ለሙሉ የተከለለ ስለሚሆን ለዉሀ ብክለት  አስተማማኝ ነዉ ።
◇በፋይበርግላስ  የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ መበስበስ እና መሰነጣጠቅ የሚባል ነገር ፈፅሞ አይታሰብም።
◇በፋይበርግላስ የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ ለማፅዳት በቀላሉ የሚመች ሲሆን ፣ በዉሀ ዉስጥ በፍጥነት ለሚራባዉ አልጌ ደግሞ ፈፅሞ የማይመች ነዉ ።
◇በፋይበርግላስ  የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ ከመሬት በታች በጉድጎድ ዉስጥ ስለሚሰራ ቦታ ቆጣቢ ነዉ።
◇ለመዋኛ ገንዳ

◇ ለመኖሪያ ቤቶች ፣፤ሪል እስቴቶች ፤ድርጅቶች ፤ሆስፒታሎች፥ ሆቴሎች ፥ ኤምባሲዎች፥የእርሻ ቦታዎች ፥ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወዘተ የኛ ተጠቃሚዎች ናቸዉ።

🤳0913967277
     0968966602
❤1
👉ከውል የማፈንገጥ ሂደት የሚያስከትላቸው ችግሮችና፣ የመፍትሄ ስርዓቶች/Damage, Breach of Contract and Remedies/

💫1.ከውል ማፈንደጥ ስንል ምን ማለት ነው?

🚧በመካከላቸው ህጋዊ የውል ስምምነት ካደረጉ ተዋዋይ አካላት መካከል አንደኛው ወገን በውሉ የተቀመጡ መሠረታዊ  ግዴታዎችን ሆነ ብሎ በማወቅ ወይም ባለማወቅ ያለምንም የህግ ድጋፍ ወይም ማብራሪያ በሌለው ምክንያት አለመፈጸም ወይም በውል በተቀመጡ የውል ሁኔታዎች መሠረት መስራት አለመቻልን ከውል ማፈንገጥ
/breach of contract/ ይባላል፡፡

🚧ይህ ከውል የማፈንገጥ ሁኔታ በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖቸ መካከል ግጭት እንዲነሳ የሚያደርግ ነው፡፡እነዚህን ከውል በማፈንገጥ ምክንያት የሚነሱ ግጭቶች በፍርድ ቤት የመፍታት ሂደት ብዙ ገንዘብ የሚጠይቅና ጊዜ አባካኝ ከመሆኑም ባሻገር ጉዳዩ እስኪቋጭ አዕምሮን ዕረፍት ሊነሳ የሚችልና የሚያስጨንቅ ነው፡፡

💫2.ከውል በማፈንገጥ የተጎጂው አማራጭ መብቶች

🚧በአንድ ተዋዋይ ወገን ከውል ማፈንገጥ ምክንያት ውል ያልተፈጸመለት ወገን ራሱን ለመጠበቅ የሚከተሉትን አማራጭ መንገዶች ሊጠቀም ይችላል፡፡
(ፍትሐ ብሄር ሕግ ቁጥር 1771)

-ለደረሰበት ጉዳት ተመጣጣኝ የጉዳት መቀጮ (ፍብሕቁ 1771(2)

-ውል አስገድዶ ማስፈጸም (ፍብሕቁ 1771(1)

-ውል እንዲፈርስለት መጠየቅ (ፍብሕቁ 1771(1)

💫3.የጉዳት መቀጮ (ፍትሐ ብሄር ሕግ ቁጠር 2360)

🚧የጉዳት መቀጮ ተጎጂው በድርጊቱ የደረሰበትን የጥቅም መቅረት ወይም መቀነስ ለማመዛዘንና ለጉዳቱ መነሻ የሆነው ተግባር ባይፈጸም ኖሮ ተጎጂ ያገኝ የነበረውን ኢኮኖሚያዊ አቋም ለመጠበቅ በታቀደ ዓላማ የሚተገበር አሰራር ነው፡፡ከውል ማፍረስ ጋር ተያይዞ የሚታየው የጉዳት መቀጮ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ካለው ተነጻጻሪ ግዴታ አኳያ የአንደኛው ወገን ግዴታውን አለማክበር በሌላው ተዋዋይ ወገን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ከሚያመጣው አሉታዊ ውጤት አንጻር ነው፡፡ይህ ከውል አፈንጋጩ ግዴታውን በተፈለገው ጊዜና በሚፈለገው አኳኆን አለመፈጸም ለተጎጂው ተመጣጣኝ የሆነ የጉዳት መቀጮ የመጠየቅ መብት ያስፈልገዋል፡፡

🚧ምንጊዜም ቢሆን የተጎጂ ኪሳራ ውሉ በተፈለገው ጊዜና አኳኋን ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ተጎጂው ሊያገኝ ይችል የነበረው ጥቅም የሚያሟላና የሚያካክስ ሊሆን ይገባዋል፡፡

⏺ከውል በማፈንገጥ ምክንንት የሚነሱ ግጭቶችን ለማርጋት የሚኬድባቸው የተለያዩ ዓይነት የመፍትሄ ስርዓቶች አሉ፡፡

⏺ከውል በማፈንገጥ ምክንያት የሚነሳ ቅሬታ የህግ ተቀባይነት ሲያገኝ፣ በህግ ኪሳራን የማስመለስ ሂደቱ ለሚደርሰው ጉዳት ካሳ የማስከፈል ሂደቱ ከዚህ ቀጥሎ በተቀመጡ መንገዶች መሠረት ይሆናል፡፡    
                                                                   
🌟እነዚህም ፡- 

i. የተመጣጣኝ ካሳ የኪሳራ መቀጮ/Compensatory Damages/

▶️በተመጣጣኝ ካሳ የኪሳራን መቀጫ፣ ከውል ያፈነገጠው ወገን ለተጎጂው የሚከፍለው መቀጫ የደረሰው ኪሳራ መጠን ተለክቶ ለደረሰው ኪሳራው ልከኛ የሆነ ካሳ በመክፈል የሚደረግ የመቀጫ ዓይነት ነው፡፡

▶️በዚህ ሂደት የሚደረግ የኪሳራ ወይም የጉዳት መቀጮ በተለካው ጉዳት ልክ ስለሚፈጸም ልከኛ መቀጮ/   actual damages/ ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡

ii. በአስተማሪ የቅጣት ርምጃ የሚደረገረግ የጉዳት መቀጮ/Punitive Damages/

▶️ከተመጣጣኝ ካሳ የጉዳት መቀጮ በተለየ ከውል ያፈነገጠው ወገን ጥፋቱን እንዲያርምና እንዳይደግም ማስተማሪያ እንዲሆነው፣ ለሌሎችም ውጫዊ አካላት ጭምር ምሳሌ እንዲሆን ተብሎ የሚሰጠው ወይም የሚጣል  የቅጣት ወይም የጉዳት መቀጮ ዓይነት ነው፡፡

▶️አስተማሪ የቅጣት ርምጃ በተመጣጣን ካሳ የጉዳት መቀጮ ላይ ተጨማሪ ሆኖ ሊሰጥ ይችላል፡፡

▶️ይህ ዓይነቱ የጉዳት መቀጮ አልፎ አልፎ ከተመጣጣኝ ካሳ  ጉዳት መቀጮ ውጪ ለብቻው ሊፈጸም ይችላል፡፡

iii. የጊዜ ጉዳት መቀጮ(Liquidated damages/Damage from late completion)

▶️ይህ ዓይነቱ የጉዳት መቀጮ የሚተገበረው ከተዋዋይ ወገኖች አንደኛው ሥራውን በውሉ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለመፈጸም ሳይችል ሲቀር ወይም ስራውን በማዘግየት ከውል ያፈነገጠ እንደሆነ ነው፡፡

iv. አነስተኛ መጠን የጉዳት መቀጮ (Nominal damages)

▶️ከተዋዋይ ወገኖች በአንዱ የተፈጠረው ከውል የማፈንገጥ ሂደት የደረሰው ጉዳት ለታለፍ የሚችልና ውል በተጣሰበት ወገን ላይ የሚያደርሰው ኪሳራ ይህ ነው የማይባል ወይም የሚታለፍ (insignificant) እና በምክር ወይም በማስጠንቀቀቂያ የሚታለፍ ሲሆን ይህ ዓይነቱ የጉዳት መቀጮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

⭐️የ YouTube ቻናላችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ SubScribe አረገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤8
ጨረታ

አዲስ ዘመን ጥር 21 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍3
ጨረታ

አዲስ ዘመን ጥር 22 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤3👏2
ጨረታ

አዲስ ዘመን ጥር 22 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤3👍3
ጨረታ

አዲስ ዘመን ጥር 22 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👏2
ጨረታ

ሪፖርተር ጥር 20 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍2
ጨረታ

ሪፖርተር ጥር 20 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2
ጨረታ

አዲስ ዘመን ጥር 19 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍1
ጨረታ

አዲስ ዘመን ጥር 19 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤1👏1