Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.2K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ADVERTISMENT

ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤6
👉What are steel tension members?

🏷Explanation: Steel tension members are those structural elements that are subjected to direct axial tensile loads, which tend to elongate the members.

⏺A member in pure tension can be stressed up to and beyond the yield limit and does not buckle locally or overall. What's the difference between tension and compression?

✅Main Difference – Tension vs. Compression

⏺Tension and compression refer to forces that attempt to deform an object.

🎲The main difference between tension and compression is that tension refers to forces that attempt to elongate a body, whereas compression refers to forces that attempt to shorten the body.

✅What is net section rupture?
Net Section Rupture

⏺Deformations continue with increasing load until finally rupture (tension failure) of the member occurs when the entire net cross section of the member reaches the ultimate stress.

The design strength due to net section rupture for plates is given by.

🚧What is tensile rupture?

✅Tensile rupture is a strength based limit state similar to the tensile yielding limit state that we just considered.

⏺The concern at these locations is actual rupture so the applied forces are compared against the rupture strength in the region of reduced effective section.

✅What is slenderness ratio of a compression member?

⏺Explanation: The tendency of member to buckle is usually measured by its slenderness ratio. Slenderness ratio of member is ratio of effective length to appropriate radius of gyration (λ = kL/r)

@etconp
❤5👍3
👉ድፍርስ ውሃን እንዴት በባህላዊ መንገድ ማጣራት እንችላለን ?

💫የንፁ ውሃ አቅርቦት በሃገር ደራጃ 20% እንኳ በቅጡ ያልሞላን ፤ ከፊታችን ትልቅ የቤት ስራ የሚጠብቀን ፤ አሁን ከምንኖርበት በ20Km ራዲየስ ውስጥ ዛሬም እንኳን ሰው ከብት ሊጠጣው የማይገባውን ውሃ አገልግሎት ላይ የሚውል ... በቂ የከርሰ ምድርም ሆነ የላእላይ ምድር ውሃ ባለቤት ሆነን ግና የውሃ ፍላጎታችን ማሟላት ያልቻልን ምስኪን ህዝቦች ነን ።
.
ይህን ተንተርሰን መንግስት ላይም ሆነ የሚመለከተው አካል ላይ እጃችንን መቀሰር የፖለቲከኞች ስራ እንጂ የኛ ኢንጅነሮች ስራ አይደለም። እኛ ያለንን ሃብት እንዴት መጠቀም እንደምንችል መላዎችን መፍጠር እና በሌሎች ሃገራት ያሉ ቀላል ተሞክሮዎችን ወደ ሃገር ማምጣት ነው።
.
በዚህ ፅሁፍ በሜክሲኮ ገጠራማ አካባቢዎች የቁልቋል (Cactus ) ተክልን ተጠቅመው ድፍርስ ውሃን እንዴት እንደሚያጠሩ እናያለን። ይህ ዘዴ የደፈረሰን ውሃ እስከ 95% እንዲሁም ውሃው በባክቴርያ የተበከለ ከሆነ ባክቴርያውን እስከ 89% የማጥራት አቅም እንዳለው ተረጋግጧል።
.
- መጀመርያ የቁልቋል ተክልን እንቆርጥ እና ላዩ ላይ የሚገኙ እሾ ነገሮችን እናራግፍና በውሃ እናጥበዋለን

- ቁልቋሉን ለሁለት ሰንጥቀን በፀሐይ እንዲደርቅ እናሰጣዋለን

- የተሰጣው ቁልቋል በቂ ፀሐይ አጊኝቶ እንደደረቀ በመቆጫ ወይም በሌላ መፍጫ እንፈጨዋለን

- የተፈጨውን ቁልቋል ባጠራቀምነው የደፈረሰ ውሃ እንጨምራለን (ማጠራቀሚያው ባልዲ ቢሆን ይመረጣል )
- ለ አስራምስት ደቂቃ ያክል እናማስላለን
ከተማሰለ በኋላ እንዲሰክን ከ30 እስከ 45 ደቂቃ እንተወዋለን።

- ውሃው ከሰከነ በኋላ ከላይ እያጠለሉ መጠጣት ወይም ከላይ አጥልሎ ንፁሁን ውሃ በሌላ ማስቀመጫ መገልበጥ እና ለአገልግሎት መጠቀም
የውሃ ችግር ባለባቸው አከባቢዎች የምትገኙ ይህን ዘዴ እንድታስተዋውቁ እንመክራለን ።

🚧የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
❤20👍4🎉1
👉 INTERCON Construction Chemicals 

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Wall Putty, Prime Coat
● Concrete Repair Mortar
● Floor hardener, Epoxy
● Grout, Self-level mortar
● Quartz paint, Contextra
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Geotextiles and other construction chemicals and materials

☎️ Tel: 0961955555

🔹 Address 1: Signal road, around
Dinberwa Hospital

🔹 Addres 2: Wellosefer, Infront of
Dani Plaza
❤6👍1
👉TYPES OF BUILDINGS

▶️Depending upon the character of occupancy or the type of use, building can be classified into different categories as follows:

1. RESIDENTIAL BUILDINGS:

These buildings include one or two private dwellings, apartment houses (flats), hotels, dormitories etc.

2. EDUCATIONAL BUILDINGS:

These buildings include any building used for school, college or day care purposes involving assembly for instruction, education or recreation.

3. INSTITUTIONAL BUILDINGS:

These buildings include any building or part which is used for
medical treatment etc. Such as Hospitals, nursing homes,
orphanages, sanatoria, jails, prisons, mental hospitals etc.

4. ASSEMBLY BUILDINGS:

These buildings may include any building or part of a building
where a group of people gathers for recreation, amusement, social, religious or such types of purposes such as theaters, assembly halls, exhibition halls, restaurants, museum, club rooms, auditoria etc.

5. BUSINESS BUILDINGS:

These shall include any building or part of a building which is used for business transactions, keeping records of accounts, town halls, city halls, court houses etc.

6. MERCANTILE BUILDINGS:

These shall include those buildings which are used for soap,
market, stores, wholesale or retail.

7. INDUSTRIAL BUILDINGS:

This types of building mainly used for manufacturing purposes.
*Here products or materials of all kinds and properties are
fabricated, assembled or processed, for example, gas plants,
refineries, mills, dairies etc.

8. STORAGE BUILDINGS:

These buildings are generally used for the storage or sheltering of goods, wares, or merchandise like warehouses, cold storages, garages, stables, transit sheds etc.

9. HAZARDOUS BUILDINGS:

These buildings include any building which is used for storage, handling, manufacture or processing of highly combustible explosive materials or products which are liable to burn with extreme rapidly which may produce poisonous fumes, building which is used for storage, handling or manufacturing highly corrosive, toxic, acid or other liquids or chemicals producing flame, fumes explosive etc...

🏷For more information click this Link Below And Subscribe Our YouTube Channel👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤10
👉ለቢሾፍቱ ኤርፖርት ግንባታ በወር 16.5 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ እየቀረበ ነው ተባለ

🛩 ለቢሾፍቱ ኤርፖርት ግንባታ በወር የሚያስፈልገው የነዳጅ ድርሻ መጠን በልዩ ሁኔታ ተሰልቶ እየቀረበ መሆኑ ተገልጿል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ አጠገብ አቡሴራ በተባለ አካባቢ ለሚያስገነባው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ (ኤርፖርት) ግንባታ ፕሮጀክት፣ በወር የሚያስፈልገው የነዳጅ መጠን በልዩ ሁኔታ ተሰልቶ 16.5 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ እየቀረበ መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

🛩 የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ግንባታ መሠረት ድንጋይ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አማካይነት መቀመጡ ይታወሳል፡፡ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር)፣ የቢሾፍቱ ኤርፖርት ትልቅ አገራዊ ፕሮጀከት መሆኑንና ራሱን የቻለ የነዳጅ ድልድል ሥሌት እንደተሠራለት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

🛫 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለዚህ አገራዊ ሜጋ ፕሮጀክት ከ17 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ በወር ጥያቄ ማቅረቡን፣ ሆኖም አገሪቱ ከምታስገባው ነዳጅ ጋር በማመጣጠን 16.5 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ እየቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህ የድርሻ ሥሌትም በቀን ከሚቀርበው አንፃር በአማካይ ተሰልቶ የተፈቀደ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ለዚህም ሲባል የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች አስቀድመው ታንከር እንዲቀብሩ፣ ከኮንትራክተሮች ጋር ውል እንዲገቡ መደረጉን ጨምረው አስረድተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሦስት ኮንትራክተሮች በፕሮጀከቱ እየተሳተፉ መሆናቸውን፣ ለእያንዳንዳቸው ሰባት ትልልቅ ኩባንያዎች ነዳጅ እንዲያቀርቡ ውል መገባቱን ተናግረዋል፡፡ ትልልቆቹ ኩባንያዎች የተመረጡት ያላቸውን የሎጂስቲክስ አቅም መሠረት ተደርጎ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከሁለት ወይም ከሦስት ኩባንያዎች ጋር ብቻ የመሥራት ፍላጎት እንደነበረው፣ ነገር ግን በነዳጅ ሥርጭት ላይ ሊፈጠር የሚችል ችግርን ታሳቢ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በማስረዳት የአቅራቢዎች ቁጥር ከፍ እንዲል መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ወደ አገር ውስጥ ከሚገባው ነዳጅ 84 በመቶው በቀጥታ ለሕዝብ አገልግሎት እንደሚውልና ቀሪው ለትልልቅ ፕሮጀከቶች የሚመደብ መሆኑን ገልጸው፣ በአሁኑ ወቅት ለቢሾፍቱ ኤርፖርት እየቀረበ ያለው ነዳጅ በልዩ ሁኔታ መደልደሉንና ቀጥታ ተጠቃሚ የሆነውን ማኅበረሰብ ድርሻ እንዳይሻማ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ምን ያህል ነዳጅ እንደሚያስፈልገው ጥናት ተደርጎ መፈቀዱን የተናገሩት ደስታው (ዶ/ር)፣ የሥራ ሒደቱ ሲጠናከርና የተሸከርካሪዎች ብዛት ሲጨምር የሚቀርበው ድርሻ ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

🛫 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ካቀረበው ፍላጎት አንፃር በአሁኑ ወቅት እየቀረበ ያለው በቂ ነው ማለት አይቻልም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በአገር አቅም የሚቻለውን ያህል ለፕሮጀከቱ እየተሠራጨ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ፕሮጀከቱ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው አገራዊ ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሆኖም ከነዳጅ ጋር በተያያዘ ችግር ሥራው እንዲቆም እንደማይደረግ ግን ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡

ከአዲስ አበባ በደቡብ ምሥራቅ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ እየተገነባ ያለው ኤርፖርቱ፣ ከአሥር ዓመት በኋላ ሲጠናቀቅ እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን በዓመት የማስተናገድ አቅም እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ብቻ በዓመት 60 ሚሊየን መንገደኞችን ማስተናገድ እንደሚያስችል ተነግሯል፡፡

በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ባለፉት ዓመታት በተሠሩለት የማስፋፊያ ሥራዎች ምክንያት በእዚህ ዓመት 21 ሚሊዮን የሚጠጉ መንገደኞችን ያስተናግዳል ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቢሾፍቱን ኤርፖርት ግንባታን በፍጥነት መጀመር ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት ሲገልጹ፣ በየዓመቱ የመንገደኞች ቁጥር በሁለት ሚሊዮን የሚጨምር ከሆነ ከሁለትና ከሦስት ዓመታት በኋላ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተጨማሪ መንገደኞችን ማስተናገድ እንደማይችል አስታውቀው ነበር፡፡

‹‹ያንን ችግር ከወዲሁ ተገንዝበን ዛሬ ሥራ ካልጀመርን፣ የአፍሪካ ኩራት ታላቁ አየር መንገድ የሚለውን ስም ተጎናፅፈን ማቆየት እንቸገራለን፡፡ በዚህም ለነገ ዛሬ አስቀድሞ መሥራት በማስፈለጉ ይህ ውሳኔ ተወስኗል፤›› ብለዋል፡፡

🛫 የቢሾፍቱ ኤርፖርት አጠቃላይ ግንባታ ወጪ 12.5 ቢሊዮን ዶላር መገመቱን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሪፖርተር መግለጹ አይዘነጋም፡፡

@etconp
❤15
👉የስትራክቸር ዲዛይን ( Structural Design) – ትርጉም እና መግለጫ
ትርጉም (Definition)

🚧ሙሉ የስትራክቸር ዲዛይን ማለት አንድ ህንፃ ወይም መዋቅር በላዩ የሚጫኑ ሁሉንም ጭነቶች (loads) በደህና እንዲሸከም፣ እንዲቆም፣ እና ለረጅም ጊዜ በጥራት እንዲያገለግል የሚደረግ ሙሉ የምህንድስና እቅድ፣ ትንተና እና ዲዛይን ሂደት ነው።

ዓላማ: ስትራክቸሩ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ኢኮኖሚካል እና ጠንካራ እንዲሆን ማረጋገጥ።
የሙሉ የስትራክቸር ዲዛይን ዋና ደረጃዎች

1. የስትራክቸር እቅድ (Structural Planning)
ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ሲሆን የስትራክቸሩ አይነት እና አቀማመጥ ይወሰናል።
የሚካተቱት:
የስትራክቸር አይነት መምረጥ (RC, Steel, Timber)
የስትራክቸር አቀማመጥ መወሰን
የColumn፣ Beam፣ Slab እና Wall ቦታ መወሰን
የመጀመሪያ መጠን መወሰን
ዓላማ: ተስማሚ የስትራክቸር እቅድ ለመፍጠር።

2. ጭነት መለየት (Load Identification)
በስትራክቸሩ ላይ የሚጫኑ ሁሉንም ጭነቶች መወሰን።
የጭነት አይነቶች:
Dead load – የህንፃው ክብደት
Live load – ሰዎች፣ እቃዎች
Wind load – የነፋስ ጭነት
Earthquake load – የመሬት መንቀጥቀጥ ጭነት
ዓላማ: በስትራክቸሩ ላይ የሚጫኑ ኃይሎችን ለማወቅ።

3. የስትራክቸር ትንተና (Structural Analysis)
በስትራክቸር አካላት ውስጥ ያሉ ኃይሎችን ማስላት።
ያካትታል:
Reaction force
Bending moment
Shear force
Axial force
Deflection
ዓላማ: ስትራክቸሩ እንዴት እንደሚጎዳ ለማወቅ።

4. የአካላት ዲዛይን (Member Design)
እያንዳንዱ አካል ጭነቱን እንዲሸከም ይዲዛይናል።
አካላት:
Slab
Beam
Column
Foundation
የሚደረጉ:
መጠን መወሰን
Reinforcement ማስላት
ጥንካሬ ማረጋገጥ
ዓላማ: ደህንነት ማረጋገጥ።

5. የFoundation ዲዛይን (Foundation Design)
ጭነትን ወደ መሬት ማስተላለፍ።
አይነቶች:
Isolated footing
Combined footing
Raft foundation
ዓላማ: ጭነትን በደህና ወደ መሬት ማስተላለፍ።

6. ዝርዝር ስዕል ማዘጋጀት (Structural Detailing)
ለግንባታ የሚያገለግሉ ስዕሎችን ማዘጋጀት።
ያካትታል:
Reinforcement detail
Bar size and spacing
ዓላማ: ለግንባታ መመሪያ ማቅረብ።

7. የጥንካሬ እና የአገልግሎት ምርመራ (Stability and Serviceability Check)
ያካትታል:
Strength check
Deflection check
Crack check
ዓላማ: ስትራክቸሩ ደህና እንዲሰራ ማረጋገጥ።

8. የስትራክቸር ስዕል ማዘጋጀት (Preparation of Structural Drawings)
ያካትታል:
Layout drawing
Reinforcement drawing
Foundation drawing
ዓላማ: ለግንባታ መመሪያ መስጠት።

9. የዲዛይን ኮድ መከተል (Code Compliance)
የምህንድስና መመሪያዎችን መከተል
Safety factor መጠቀም
ዓላማ: ደህንነት ማረጋገጥ።

አጠቃላይ ሂደት (Summary Flow)

Structural Planning → Load Calculation → Structural Analysis → Member Design → Foundation Design → Detailing → Checking → Drawings

Via 𝑬𝒓. 𝑴𝒆𝒌𝒂𝒎𝒖 𝑴𝒐𝒉𝒂𝒎𝒎𝒆𝒅

🚧የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
❤21🔥4
የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት AI ላይ ትልቅ ተስፋ ጥለዋል

የኮንስትራክሽን ዘርፍ በሰው ኃይል እጥረት እና በውስብስብ የሥራ ሂደቶች እየተፈተነ ባለበት በዚህ ወቅት፣ብዙ ኩባንያዎች መፍትሄ ለማግኘት ወደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ፊታቸውን እያዞሩ ነው።

ዋና ዋና ነጥቦች፦

1. የሰው ኃይል እጥረት መፍትሄ፦

እንደ "Associated Builders and Contractors" መረጃ ከሆነ የኮንስትራክሽን ዘርፉ በአሁኑ ወቅት ወደ 349 ሺህ የሚጠጉ ሠራተኞች እጥረት አለበት። የ AI ወኪሎች ይህንን ክፍተት ለመሙላትና ሠራተኞች በሌሉበት ወይም በቂ ባልሆኑበት ቦታ ሥራዎችን ለማቀላጠፍ እየረዱ ነው።

2. የ AI ወኪሎች ሚና፦

እነዚህ የ AI ሶፍትዌሮች ተራ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ብቻ አይደሉም፤ ይልቁንም እንደ ሰው በራሳቸው ውሳኔ ሰጥተው ስራዎችን የሚያከናውኑ ናቸው። ለምሳሌ፦

🔹የግንባታ እቃዎችን በራሳቸው ማዘዝ እና ክትትል ማድረግ፤

🔹የፕሮጀክት የጊዜ ሰሌዳዎችን ማስተካከል፤

🔹በኢሜይል እና በሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች ከደንበኞችና ከአቅራቢዎች ጋር መነጋገር።

3. ውጤታማነትን መጨመር፦

AI ወኪሎች ሰራተኞች በቢሮ ውስጥ የሚያሳልፉትን አድካሚና ተደጋጋሚ ሥራዎች ስለሚረከቡ፣ የፕሮጀክት መሃንዲሶች ትኩረታቸውን በግንባታው ቦታ ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።

4. ተግዳሮቶች፦

ምንም እንኳን ቴክኖሎጂው ተስፋ ሰጪ ቢሆንም፣ የሳይበር ደህንነት ስጋቶች እና AI በራሱ የሚወስናቸው ውሳኔዎች ለሚፈጠር ስህተት "ተጠያቂው ማን ነው?" የሚሉ ጥያቄዎች አሁንም በዘርፉ ላይ ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛሉ።

የግንባታው ዘርፍ በባህላዊ አሠራር የሚታወቅ ቢሆንም፣ አሁን ግን የ AI ወኪሎችን በመጠቀም ሥራን ፈጣን፣ ርካሽ እና ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ ርምጃ እየወሰደ ይገኛል።



@etconp
❤9👍2
3160. The effective length of a fillet weld should not be less than
Anonymous Quiz
40%
(a) Two times the weld size
28%
(b) Four times the weld size
12%
(c) Six times the weld size
21%
(d) Weld size
👍4❤2
3161. When the bolts are subjected to reversal of stresses, the most suitable type of bolt is
Anonymous Quiz
11%
(a) Black bolt
12%
(b) Ordinary unfinished bolt
40%
(c) Turned and fitted bolt
37%
(d) High strength bolt
❤4👏2
For cohesive soil with increasing compactive effort the optimum moisture content ?
Anonymous Quiz
33%
Increase
43%
Decrease
18%
Remains constant
7%
Is zero
🙏7❤4
Q) To hydrate 500 kg cement fully water needed is ?
Anonymous Quiz
39%
100 kg
14%
110 kg
20%
115 kg
27%
120 kg
👍6
Q)The maximum numerical value of poisson' s ratio is ?
Anonymous Quiz
5%
0.0
43%
0.25
27%
0.50
25%
1.00
❤8
👉 INTERCON Construction Chemicals 

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Wall Putty, Prime Coat
● Concrete Repair Mortar
● Floor hardener, Epoxy
● Grout, Self-level mortar
● Quartz paint, Contextra
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Geotextiles and other construction chemicals and materials

☎️ Tel: 0961955555

🔹 Address 1: Signal road, around
Dinberwa Hospital

🔹 Addres 2: Wellosefer, Infront of
Dani Plaza
❤4👏1
👉ኢትዮጵያዊው መሀንዲስ ከዘንድሮ የአለማችን ምርጥ 15 የህንፃ ዲዛይነሮች አንዱ ሆነው ተመረጡ፡፡

💫አርክ ዴይሊ በየአመቱ በአለማችን ውስጥ የተገነቡ ህንፃዎችን በማወዳደር ሽልማት ይሰጣል፡፡

ይህ ተቋም ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ ባዘጋጀው በዚህ ውድድር ከሺህ በላይ ፕሮጀክቶች ለውድድር ቀርበዋል፡፡

በኦንላይን በተከናወነው ምርጫ ላይ ከ100 በላይ አገራት ወደ200 ሺህ ያህል ሰዎች ድምፃቸውን ሰጥተዋል፡፡

ተቋሙ የውድድሩን ውጤት ዛሬ ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህ መሰረት ከ15ቱ የአመቱ ምርጥ የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል ኢትዮጵያዊው የምህንድስና ድርጅት አንዱ ሆኗል፡፡

15ቱ ፕሮጀክቶች የተመረጡት በየዘርፉ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ሲሆን ይህ ድርጅት ‹‹ቤስት አፕላይድ ፕሮዳክት›› በሚለው ዘርፍ አንደኛ ደረጃን ማግኘቱም ታውቋል፡፡

ለዚህ ሽልማት የበቃው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሰለባዎች መታሰቢያ የተሰራው ዲዛይን ነው፡፡

ኢቲ 302 መታሰቢያ በሚል የተሰራውን ይህንን ዲዛይን ያዘጋጀው አለበል ደስታ አርክቴክቶችና መሀንዲሶች የተሰኘው ድርጅት ነው፡፡

አርክ ዴይሊ ይህ ፕሮጀክት አሸናፊ የሆነበትን ምክንያት ሲገልፅ ‹‹የኢቲ 302 መታሰቢያ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ 157 ሰዎች ትርጉም ያለው ክብር የሚሰጥና የበረራውን የመጨረሻ ሰአታት የሚተርክ ዲዛይን ነው›› ብሏል፡፡

Via ዘ ሐበሻ

@etconp
❤8👍3🔥1