Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.2K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ብዝዎች እባካቹ ቅናሹ አራዝሙልን ባላቹት መሠረት ኦንላይን ስልጠናዎቻችን ምዝገባ ድጋሜ ጀምረናል

⛈ክረምት እውቀትዎ እና ሞያዎ ማዳበር ይፈልጋሉ?

💫እንግድያውስ የ ETABS እና QUANTITY SURVEYING ሙሉ ኦንላይን ኮርስ በ 25 % ቅናሽ ምዝገባ ጀምረናል እንዲሁም ሁለቱም ኮርሶች በአንድ ላይ ለሚወስዱ ከ እያንዳንዱ የ 40% ቅናሽ ይደረግላቹዋል🙏

📩ለመመዝገብ @Philemona7 ይፃፉልን ወይም ለበለጠ መረጃ በ 0925446661 ይደውሉልን❤️

@etconp
❤3👏2🥰1
👉በአዲስ መልክ ተዘጋጅተው በጸደቁ የኢትዮጵያ የህንፃ ኮድ ስታንዳርዶች  ላይ የባለድርሻ አካላት ምክክር ተካሄደ፡፡

🚧የግንባታ ደህንነት በአጋጣሚ የሚረጋገጥ ሳይሆን በስታንዳርድ እና በኮድ ይሁነኝ ተብሎ የሚከናወን ነው። የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. – የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን በአዲስ መልክ ተሻሽለውና ተዘጋጅተው የጸደቁ የኢትዮጵያ የህንፃ ኮድ ስታንዳርዶች ላይ ከመንግስት ተቋማት፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዘርፉ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፥ ከሙያ ማኅበራት፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ከግሉ ዘርፍ እና ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በከተማና መሠረተልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት የትምጌታ አስራት ዶ/ር መድረኩን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት የብሄራዊ ስታንዳርድ እና ኮድ ትግበራ የዘርፉ ግንባታ ዋና ምሶሶ አድርጐ ማየት እንደሚገባ ገልፀዋል።

የምክክር መድረኩ በሀገሪቱ የግንባታ ዘርፍ እየታዩ ያሉ ፈጣን ለውጦችን፣ የቴክኖሎጂ እድገቶችን፣ የከተሞች መስፋፋትን እና እየጨመረ የመጣውን የህንፃ ደህንነትና ጥራት ፍላጎት በማገናዘብ የተዘጋጁትን አዳዲስ እና የተሻሻሉ ኮዶች ለማስተዋወቅና ግብዓት ለመሰብሰብ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በፕሮጀክቱ 48 ኮድና ስታንዳርድ ተሻሽለው እና በአዲስ መልክ  ተዘጋጅተዋል። ኮዶቹ የመዋቅር ዲዛይን፣ የመሬት መንቀጥቀጥ መቋቋም፣ የጂኦቴክኒክ ዲዛይን፣ የውሃ አቅርቦትና ፍሳሽ ስርዓት፣ የኤሌክትሪክና የሜካኒካል ስርዓቶች፣ የእሳት፣ የሥራ ቦታ ጤናና ደህንነት፣ የህንፃ ፋሲሊቲ ማኔጅመንት እና የ(አሳንሰር) ቨርቲካል ትራንስፖርት ስርዓቶችን ጨምሮ የግንባታውን ዘርፍ በስፋት ይሸፍናሉ።

የኮድ ማሻሻያ ሥራው በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን መሪነት  እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና ቢውልት ኢንቫይሮመንት ኮሌጅ ፈጻሚነት የተከናወነ ሲሆን ከ128 በላይ ባለሙያዎች በዝግጅቱ ተሳትፈዋል።

የአማካሪው ቡድን አስተባባሪ የኢሳያስ ገ|ዮሃንስ (ዶ/ር) በአዲስ መልክ ተዘጋጅተው የጸደቁትን  ኮድና ስታንዳርድ በ5 በመክፍል ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ከተሳታፊዎች አስተያየቶችና የግልፅነት ጥያቄዎች ቀርበዋል።

የፀደቁት ኮድና ስታንዶች አስመልክቶ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተከታታይነት ያላቸው áˆľáˆáŒ áŠ“ እንደሚያስፈልግ፥ የፀደቁት ኮዶች በስራ ላይ ባለሙያው እንዲጠቀመው ተግባራዊ እንዲሆኑ ከፍተኛ ክትትልና ቅጣት አስፈላጊ መሆኑ፥ ዝርዝር የሆነ ጋይድ ላይን ቢዘጋጅ የሚሉ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን የተሻሻሉት ኮዶች የግንባታ ጥራትን፣ ደህንነትን፣ ዘላቂነትን እና የዘርፉን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸውም  ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።

እንዲሁም ኮዶቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆኑ የአቅም ግንባታ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መሠጠት ለዚህም እና የተቀናጀ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።

በተሰጡት አስተያየቶች ማብራሪያ የሠጡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ ዶ/ር ስልጠና በክሊፕ ተዘጋጅቶ ለተጠቃሚ በቀላሉ ለማድረስ እራሱን የቻለ እቅድ በመንደፍ በቀጣይ የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል።

የምክክር መድረኩ ተሻሽለው የጸደቁትን የኢትዮጵያ የህንፃ ኮድና  ስታንዳርዶች ወደ ተግባር ለማሸጋገር እና በግንባታው ዘርፍ የህግ ተገዢነትን፣ ጥራትን እና ደህንነትን ለማጠናከር ጠቃሚ መድረክ መሆኑ ተገልጻል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያ በኮድናስታንዳርድ ማሻሻያ ውስጥ አሻራቸውን ያሳረፉ ተቋማት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፥ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት እና በተለያየ ደረጃ ተሳታፊ ለነበሩ ባለሙያዎች የእውቅና  እና የምስጋና ስርተፊኬት ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ተበርክቶላቸዋል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን

@etconp
❤10👍10👏1
​🧠 ስትራተጂክ አመራር በኮንስትራክሽን ሳይት🚧

«በቦታህ መምህር፤ ያለቦታህ ተማሪ ሁን!»

🪧​ቃሉ በግንባታው ኢንደስትሪ ውስጥ ለምንገኝ መሪዎች፣ መሐንዲሶችና ኮንትራክተሮች የዕለት ተዕለት የሳይት ስራ ስኬታማነት ፍፁም ወሳኝ የሆነ መርህን ያስተምረናል።

​📐 1. «በቦታህ መምህር ሁን» (The Engineer's Authority)

• ​የንድፈ-ሐሳብ እና የዲዛይን የበላይነት፦ አንድ መሐንዲስ (Engineer) በቢሮ፣ በስትራቴጂክ ዕቅድ፣ በሕንፃ መዋቅር (Structural Design)፣ በኮንትራት አስተዳደር እና በኢንጂነሪንግ ሳይንስ ዙሪያ ሲሆን «መምህር» ነው.
• ​ውሳኔ ሰጪነት፦ የጥራት ቁጥጥርን፣ የደህንነት መስፈርቶችን እና የፕላን ትክክለኛነትን በሚመለከት ባለሙያው ሙያዊ እውቀቱን ተጠቅሞ ሳይቱን በልበ-ሙሉነትና በአስተማሪነት መምራት ይኖርበታል።

​🏗️ 2. «ያለቦታህ ተማሪ ሁን» (Learning from the Site Reality)

• ​የተግባር እና የልምድ ክብር፦ ጥቅሱ እንደሚያስተምረን፣ መሐንዲሱ ከቢሮ ወጥቶ ወደ ትክክለኛው የሳይት ግንባታ (Physical Site) ሲገባ፣ የዓመታት የተግባር ልምድ (Hands-on experience) ያላቸውን አንጋፋ ፎርመኖችንና (Foremen) ዋና ባለሙያዎችን ሲያገኝ «ተማሪ» መሆን መቻል አለበት።
• ​የ«ፕላን እና ሳይት» ልዩነትን ማስታረቅ (Plan vs. Site)፦

በወረቀት ላይ ያማረው ፕላን ሳይት ላይ በተግባር ሲደርስ ከከርሰ-ምድር፣ ከአየር ንብረት ወይም ከቁሳቁስ ባህሪ የተነሳ ያልታሰቡ ማነቆዎች ሊገጥሙት ይችላሉ።

በዚህ ሰዓት በትዕቢት ከመናገር ይልቅ፣ የፎርመኑን የተግባር ምክር ዝቅ ብሎ ማዳመጥና ከተግባሩ መማር የብልህ ስትራተጂክ መሪ መገለጫ ነው።

​🎯 የስትራተጂክ መሪ ትልቁ ጥበብ፦

​እውነተኛ ስትራተጂክ አመራር ያለው መሐንዲስ ወይም ኮንትራክተር፣ የፎርመኑን የተግባር ልምድ ከመሐንዲሱ የሳይንስ እውቀት ጋር በአክብሮትና በትህትና ማቀናጀት የሚችል ነው።

ይህ ሲሆን በሳይት ላይ አለመግባባቶች ይቀንሳሉ፣ የሥራ ፍጥነት ይጨምራል፣ የፕሮጀክት ጥራትም ይረጋገጣል!

​💬 ጥያቄ (Engagement Question)፦

​«'በቦታህ መምህር፤ ያለቦታህ ተማሪ ሁን።' በኮንስትራክሽን ሳይት ላይ በመሐንዲሶችና በፎርመኖች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች ዋነኛው መንስኤ መሐንዲሱ የንድፈ-ሐሳብ እውቀቱን ብቻ ይዞ የተግባር ባለሙያዎችን አለማዳመጡ፣ ወይም ፎርመኑ የሳይንስ ሕግጋትን ጥሶ በልምድ ብቻ መጓዙ ነው።

ለመሆኑ በእርስዎ የሥራ ልምድ በፕላን እና በሳይት መካከል ልዩነት ሲፈጠር ይህንን መርህ ተጠቅመው ያውቃሉ? መሐንዲስና ፎርመን ተደጋግፈው እንዲሰሩ ምን ዓይነት

'ስትራተጂክ አመራር' ያስፈልጋል? ሃሳብዎን ያጋሩን!»


@etconp
👏9❤7👍3
#ADVERTISEMENT

የጋብዮን ዋጋ

Galvanized Gabion
Daymend size 80/100
Wire thickness 2.5mm&3mm

👉 3×1×1=6,800
👉 2×1×1=4,600
👉 1×1×1=3,200

ስልክ 🤙
✅ 0949434363
✅ 0912955969
❤5👍1🎉1
👉የኢትዮጵያ የህንፃ ኮድ ስታንዳርዶች (EBCS)

👷‍♂️የኢትዮጵያ የህንፃ ኮድ ስታንዳርዶች (EBCS) በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የተዘጋጁ ሲሆን በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሕንፃዎችና የሲቪል ምህንድስና ሥራዎች ደህንነት፣ አገልግሎት ሰጪነት፣ ጤናማነት እና ጽናት እንዲኖራቸው የሚያስችሉ አጠቃላይ ደንቦች ናቸው።

እነዚህ ስታንዳርዶች የሕንፃዎችና መዋቅሮች ዕቅድ ዝግጅት፣ ዲዛይን፣ ግንባታ፣ አሠራር እና ጥገና የሚመለከቱ ዝቅተኛ መስፈርቶችን ይወስናሉ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያን አካባቢያዊ፣ ጂኦሎጂካዊ፣ የአየር ንብረት እና ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ያስገባሉ።

🏷ዋና ዋና የEBCS ተከታታይ ስታንዳርዶች

❇️EBCS-1፡ የዲዛይን መሠረቶች እና በመዋቅሮች ላይ የሚፈጸሙ ጫናዎች የመዋቅር ዲዛይን መሠረታዊ መርሆዎችን ያቀርባል፣ እነዚህም የመጨረሻ የአቅም ሁኔታ (Limit State Design)፣ የጭነት ጥምረቶች፣ የደህንነት መጠኖች (Safety Factors)፣ የሞተ ጭነት (Dead Load)፣ የተግባር ጭነት (Imposed Load)፣ የነፋስ ጭነት (Wind Load) እና ሌሎች የአካባቢ ተጽዕኖዎችን ያካትታል።

❇️EBCS-2፡ የሕንፃዎች ዲዛይን

የሕንፃ ዕቅድ፣ የቦታ ምርጫ፣ የአጠቃቀም ብቃት፣ ተደራሽነት እና ሥነ-ሕንፃዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ አጠቃላይ መስፈርቶችን ይገልጻል።

❇️EBCS-3 እስከ EBCS-6፡ የመዋቅር ቁሳቁስ ዲዛይን ስታንዳርዶች

🧷EBCS-3፡ የኮንክሪት መዋቅሮች
* EBCS-4፡ የብረት እና የተዋሃዱ (Composite) መዋቅሮች
*EBCS-5፡ የእንጨት መዋቅሮች
* EBCS-6፡ የግንበኝነት (Masonry) መዋቅሮች

🔗እነዚህ ስታንዳርዶች ለእያንዳንዱ ቁሳቁስ የዲዛይን ዘዴዎች፣ የቁሳቁስ መግለጫዎች፣ የዝርዝር ማብራሪያ መስፈርቶች እና የግንባታ ሂደቶችን ይዘረዝራሉ።

EBCS-7፡ የጂኦቴክኒክ ዲዛይን እና መሠረቶች

የቦታ ምርመራ፣ የአፈር ምደባ፣ የአፈር ተሸካሚ አቅም ግምገማ፣ የሰፈር ትንተና (Settlement Analysis)፣ የመሠረት ዲዛይን፣ የድጋፍ ግድግዳዎች (Retaining Structures) እና የመሬት ሥራዎችን ይመለከታል።

❇️EBCS-8፡ የርዕደ መሬት መቋቋም የሚችሉ መዋቅሮች ዲዛይን

የሴይስሚክ ዲዛይን መስፈርቶች፣ የሴይስሚክ ዞኖች ግምት፣ የመዋቅር ትንተና ሂደቶች እና ለርዕደ መሬት መቋቋም የሚያስፈልጉ ዝርዝር መስፈርቶችን ይዟል።

❇️EBCS-9፡ የሕንፃዎች የፕላምቢንግ አገልግሎቶች

የውሃ አቅርቦት ሥርዓቶች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የቆሻሻ ውሃ አወጋገድ፣ የዝናብ ውሃ ፍሳሽ፣ ሴፕቲክ ታንኮች፣ ሶክአዌይ ጉድጓዶች (Soakaway Pits) እና ተያያዥ የፕላምቢንግ ሥራዎችን ያካትታል።

❇️EBCS-10፡ የሕንፃዎች የኤሌክትሪክ ተከላዎች

የኤሌክትሪክ ሽቦ ሥርዓቶች፣ የመከላከያ መሣሪያዎች፣ አርቲንግ (Earthing/Grounding)፣ የኤሌክትሪክ ደህንነት እና በሕንፃዎች ውስጥ የኃይል ስርጭትን ይወስናል።

❇️EBCS-11 እስከ EBCS-13፡ የሕንፃ አገልግሎቶች

የሕንፃ ሜካኒካል አገልግሎቶች፣ የአየር ማናፈሻ (Ventilation) ሥርዓቶች፣ የአካባቢ ቁጥጥር ሥርዓቶች እና የእሳት መከላከያ መስፈርቶችን ይዳስሳል።

❇️EBCS-14፡ በህንፃ ግንባታ ውስጥ ጤና እና ደህንነት

🔖የሥራ ቦታ ጤና እና ደህንነት፣ የአደጋ መለያየት፣ የደህንነት ምልክቶች፣ የግል መከላከያ መሣሪያዎች (PPE) እና ደህንነቱ የተጠበቀ የግንባታ ሥራ ሂደቶችን ይወስናል።

⏺ከዓለም አቀፍ ስታንዳርዶች ጋር መጣጣም
⏺ኢትዮጵያ የህንፃ ስታንዳርዶቿን ከዓለም አቀፍ ዕውቅና ካላቸው ኮዶች ጋር በተለይም ከአውሮፓ ስታንዳርዶች (Eurocodes) እና ከISO ስታንዳርዶች ጋር በማጣጣም ላይ ትገኛለች። እነዚህ የተጣጣሙ ስታንዳርዶች ብዙ ጊዜ እንደ (ES EN) በመታተም የአገሪቱን የምህንድስና ሥራ ከዓለም አቀፍ ልምዶች ጋር ያስማማሉ።

🟡ይህ መጣጣም የሚያስገኘው ጥቅም፦

* የመዋቅር ደህንነትና አስተማማኝነት መሻሻል።
* በግንባታ ውስጥ የጥራት ማረጋገጫ መጠናከር።
* ከዓለም አቀፍ የምህንድስና እና የግንባታ ልምዶች ጋር የተሻለ ተኳሃኝነት መፍጠር።
* ለአካባቢያዊ እና ሴይስሚክ አደጋዎች የተሻለ መቋቋም መቻል።

🪧For farther information Please Subscribe Our Youtube Channel👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤13👏6
👉የሳምንቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዳሰሳ እና ወቅታዊ መረጃዎች

🔖​ሰላም የ ETCONp ቤተሰቦች የሳምንቱን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዋና ዋና ኩነቶች እና የዘርፉን እንቅስቃሴ የሚዳስስ አጭር ዘገባ ይዘን ቀርበናል።

​1. የጨረታ እና የፕሮጀክት ዝመናዎች

​በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚወጡ የኮንስትራክሽን ጨረታዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። በተለይም በመሠረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ እያገኙ መሆናቸውን ታዝበናል።

​አስፈላጊ ማሳሰቢያ: በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ባለሙያዎች እና ተቋራጮች፣ የጨረታ ሰነዶችን ከመሙላታቸው በፊት የቴክኒክ መስፈርቶችን እና የጊዜ ገደቦችን በጥንቃቄ እንዲያረጋግጡ እናሳስባለን።

​2. የግብዓት አቅርቦት እና ዋጋ ንረት

​የግንባታ ግብዓቶች (እንደ ብረት እና ሲሚንቶ ያሉ) አቅርቦት እና የዋጋ መዋዠቅ አሁንም ለዘርፉ ተግዳሮት ሆኖ ቀጥሏል።

​የባለሙያ ምክር: የግንባታ ፕሮጀክቶችዎን ሲያቅዱ፣ የግብዓት ዋጋ ለውጦችን ግምት ውስጥ ያስገባ የረጅም ጊዜ እቅድ መያዝ ፕሮጀክቶ በታቀደው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ይረዳል።

​3. የፖሊሲ እና የአሰራር ማሻሻያዎች

​የሕዝብ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን እያወጣ ያለው አዳዲስ መመሪያዎች፣ በጨረታ ሂደት ውስጥ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን የሚያሳዩ ናቸው።

​በቅርቡ በባለሥልጣኑ በኩል የተደረጉ የሪፎርም ስራዎች የግንባታ ተቋራጮች የአሰራር ልምዳቸውን ዘመናዊ እንዲያደርጉ ግብዣ የሚያቀርቡ ናቸው።

​4. የባለሙያዎች ምክር

​የኮንስትራክሽን ጥራትን ለመጠበቅ የቁጥጥር ስራዎች (Quality Control) መጠናከር ይገባቸዋል።

በግንባታ ቦታ ላይ የሚከናወኑ የዕለት ተዕለት ክትትሎች ለፕሮጀክት ስኬት ቁልፍ ናቸው።

@etconp
❤6🙏2
#ADVERTISEMENT

👉የ LINKEDIN ኣካውንትዎ በማከራየት ገንዘብ ይስሩ

💸ክፍያዎትን ባንክ ሆነ በባይናንስ መቀበል ይችላሉ።

🔖ቢያንስ 50 connections እና ኣካውንቱ ከተከፈተ 1 አመት የሞላው ከሆነ በ ወር 45 ዶላር እንከፍሎታለን💛

🚨Password በጭራሽ አይቀየርም።
🚨 በፈለጉበት ሰዓት አካውንቶን መልሰው መውሰድ ይችላሉ።

📩ከኛ ጋር መስራት የምትፈልጉ በ @Dagimsamuel ፃፉልን ወይም በ 0941078473 ደውሉልን🙏
❤2👌1
👉ጥብቅ ማስጠንቀቂያ⚡️

🏷የመሬት መንሸራተት ስጋት በሚኪ ሌላንድ ኮንዶሚኒየም🚨

💫በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የሚኪ ሌላንድ (ብርጭቆ) ኮንዶሚኒየም አካባቢ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት እና የመሬት ስንጥቅ ምክንያት ከፍተኛ የጂኦቴክኒካል እና የመዋቅር (Structural) ስጋት እየተፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።

🚧በአካባቢው የታየው የመሬት መቀመጥ (Settlement)፣ የአስፋልት መሰንጠቅ እና እስከ 3 ሜትር የሚደርስ የመሬት መውረድ በአካባቢው ያሉ ህንፃዎች፣ መንገዶች እና የመሠረተ ልማት ተቋማት ላይ ተጨማሪ ምርመራ እና አፋጣኝ የመከላከል ስራዎች እንዲካሄዱ ያስፈልጋል።

🧷እንደ ምህንድስና እይታ፣ በአካባቢው የጂኦቴክኒካል ጥናት፣ የSlope Stability Analysis፣ የውሃ ፍሰት ቁጥጥር (Drainage Improvement) እና አስፈላጊ የRetaining Structure ወይም የGround Stabilization ስራዎች በአፋጣኝ መተግበር ይገባል።

😱የሰው ህይወት እና ንብረት ደህንነት ከሁሉም በላይ በመሆኑ፣ የሚመለከታቸው አካላት በተቀናጀ መንገድ የምርመራ እና የማጠናከሪያ ስራዎችን እንዲያፋጥኑ ይጠበቃል።

#CivilEngineering #GeotechnicalEngineering #SlopeStability #StructuralSafety #AddisAbaba #CondominiumSafety

@etconp
❤8🙏5👍4
👉Flexible Pavement Layer System

1. Subgrade (Soil) – Natural ground that supports the entire pavement structure.

2. Geotextile Fabric – Separates soil and aggregates, improving stability and drainage.

3. Granular Sub-Base – Distributes loads and prevents excessive settlement.

4. Aggregate Base Course – Provides structural strength and load-bearing capacity.

5. Hot Mix Asphalt Binder Course – Intermediate asphalt layer that adds strength.

6. Hot Mix Asphalt Surface Course – Top riding surface, ensuring smoothness, safety, and durability.

Together, these layers distribute traffic loads safely to the underlying soil and increase pavement life.

#CivilEngineering #RoadConstruction #FlexiblePavement #HighwayEngineering #AsphaltPavement

@etconp
👍9❤6
👉በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለቀን ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ አስገዳጅ ሊሆን ነው❗️

ይህ መመሪያ በሰራተኛች ብቃት ማነስ ምክንያት በንብረት እና በግንባት ጥራት ላይ የሚደርስን ችግር ለመቀነስ ነው ተብሏል።


💫የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ዘርፍ እየታየ ያለውን የጥራትና የደህንነት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አዲስ መመሪያ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

❇️​ይህ አዲስ መመሪያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ዕለት ተዕለት የሚሰሩ የቀን ሠራተኞችንም የብቃት ደረጃ ማረጋገጥን ግዴታ የሚያደርግ ነው። ሚኒስቴሩ በዘርፉ የተሻለ ጥራትና ደህንነትን ለማስፈን እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል።

🏷​እንደ አዲሱ መመሪያ ዝርዝር ሁኔታ፡-

​📌​በየትኛውም የግንባታ ቦታ ላይ ለመስራት የሚፈልጉ ባለሙያዎች እና የቀን ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዝ ግዴታ ይሆናል።

​📌​ሕጋዊ የሰርተፊኬሽን ሥርዓት ያላሟላ እና ብቃቱ ያልተረጋገጠ ማንኛውም ባለሙያ ወይም ሠራተኛ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ እንዳይሳተፍ ሙሉ በሙሉ ይከለከላል።

​📌​መመሪያው ሙሉ በሙሉ ሕግ ሆኖ ወደ መሬት ወርዶ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ የተወሰኑ ዓመታት ሊወስድ ይችላል።

​📌 ​በአሁኑ ወቅት ግን የዚህ አሠራር የቅድመ ዝግጅት እና የሙከራ እንቅስቃሴዎች በይፋ መጀመራቸው ተገልጿል።

🪧​የዚህ አሠራር ዋና ዓላማ የግንባታ ሥራዎችን ጥራትና የሥራ ደህንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ማሻሻል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

@etconp
👍6❤1😭1
👉የሚኒስትሮች ምክር ቤት አዲስ የኮንስትራክሽን እና የከተማ ልማት ፖሊሲዎችን አጸደቀ

አዲስ አበባ — የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 57ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ የሀገሪቱን የግንባታ እና የከተማ ዕድገት መዋቅር በከፍተኛ ደረጃ ይቀይራሉ የተባሉ ሁለት ወሳኝ ረቂቅ ፖሊሲዎችን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።


ምክር ቤቱ በሰፊው ተወያይቶ ያፀደቃቸው እነዚህ ሰነዶች የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ረቂቅ ፖሊሲ እና የከተማ ልማት ረቂቅ ፖሊሲ ናቸው።

ሁለቱም ፖሊሲዎች ከዛሬው ዕለት ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውሉ ተወስኗል።

1. የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ፦ ወደ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ከፍተኛ ምርታማነት
ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ፣ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ዓመታት ሲተገበር የነበረው ነባሩ የኮንስትራክሽን ፖሊሲ በዘርፉ የተወሰኑ ለውጦችን ቢያስመዘግብም፣ አሁን ካለው የዓለም የቴክኖሎጂ ዕድገትና የፈጣን መሰረተ ልማት ፍላጎት አንጻር ሰፊ ክፍተቶች የነበሩበት መሆኑን አውስቷል።


አዲሱ ፖሊሲ እነዚህን ክፍተቶች በመሙላት ረገድ የሚከተሉትን ዋና ዋና ግቦች ያሳካል ተብሏል፤


◂▸ ምርታማነትንና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፦ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ዓለም አቀፋዊ ደረጃና ብቃት ማረጋገጥ።

◂▸ የሕግ ማዕቀፎችን ማጣጣም፦ በሥራ ላይ ያሉ አሰራሮችንና ሕጎችን በማዋሃድ ለግልና ለሕዝብ ኢንቨስትመንት ምቹ ማድረግ።

◂▸ አቅምን አሟጦ መጠቀም፦ የኢንዱስትሪውን የመልማት አቅም በመጠቀም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን የማድረግ ጉዞን ማፋጠን።

2. የከተማ ልማት ፖሊሲ፦ የከተማና ገጠር ትስስርን ማጠናከር


የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሁለተኛ አድርጎ ያፀደቀው፣ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት (ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ) በሥራ ላይ የቆየውን የከተማ ልማት ፖሊሲ በአዲስ መልክ የሚተካውን ሰነድ ነው።

ነባሩ ፖሊሲ በከተሞች የመሰረተ ልማት መስፋፋትና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ውጤቶች ቢያስመዘግብም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተሞች አካባቢ እየታዩ ያሉ አበረታች ለውጦችን ለማፅናትና ይበልጥ ለማጎልበት አዲስ ፖሊሲ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

የአዲሱ የከተማ ልማት ፖሊሲ ትኩረቶች፦


▸◂ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እና አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ማድረግ።

▸◂ ከተሞችን በኢኮኖሚ ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችሉ አሰራሮችን መዘርጋት።

▸◂ የከተማ-ገጠር እና የከተማ-ከተማ ትስስርን በበለጠ ማጠናከር።

◂▸ የማምረቻና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን በስፋት ማዳረስ።

ሁለቱም ፖሊሲዎች በምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ አስፈላጊ ግብዓቶች ከተካተቱባቸው በኋላ ከዛሬው ዕለት ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ በሥራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የምክር ቤቱ መግለጫ ያሳያል።


@etconp
👍3❤2
EBCS 1-Basis of Design & Actions on structures.pdf
11.2 MB
‎     
🚧የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
EBCS 2-Structural use of Concrete.pdf
19.3 MB
‎     
🚧የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
EBCS 3-Design of Steel Structures.pdf
14.2 MB
‎     
🚧የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
EBCS 4-Design of Composite steel & Concrete Structures.pdf
10.4 MB
‎     
🚧የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
EBCS 5-Utilization of Timber.pdf
20.1 MB
‎     
🚧የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
❤7🙏2👍1
EBCS 6-Masonry.pdf
15.3 MB
‎     
🚧የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
EBCS 7-Foundations.pdf
15 MB
‎     
🚧የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
EBCS 8-Design of Structures for Earthquake resistance.pdf
13.7 MB
‎     
🚧የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
🙏12❤7