Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.2K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
በሳይት ላይ የConcrete Vibrator Proper Usage & Inspection! 🧐🏗️

​በምስሉ ላይ እንደምናየው ኮንክሪት በሚፈስበት ወቅት የፖከር ቫይብሬተር (Poker Vibrator) አጠቃቀም የኮንክሪቱን ጥንካሬ እና ጥራት ለመወሰን እጅግ አስፈላጊ ነው።

​በኮንክሪት ንቅናቄ (Vibration) ወቅት ሊጠበቁ የሚገባቸው 3 ወሳኝ ህጎች፦

1. ​Vertical Insertion (በቀጥታ ቁልቁል መስደድ)፦ የቫይብሬተሩ ራስ (Needle) በኮንክሪት ውስጥ አግድም ሳይሆን በቀጥታ ቁልቁል (90^\circ) መግባት አለበት።

2. ​Duration (የጊዜ ገደብ)፦ ቫይብሬተሩ በአንድ ቦታ ላይ ከ 5 እስከ 15 ሰከንድ ብቻ መቆየት አለበት። የኮንክሪቱ ገጽታ ላይ የሲሜንቶ ወተት (Laitance) መታየት ሲጀምር ማውጣት ይገባል።

3. ​Avoid Horizontal Dragging፦ ቫይብሬተሩን በኮንክሪት ውስጥ አግድም እየጎተቱ ኮንክሪት ማንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው (Segregation ያስከትላል)።

​በእርስዎ ሳይት ላይ ቫይብሬተር ሲመታ በአንድ ነጥብ ላይ ለስንት ሰከንድ እንዲቆይ ታደርጋላችሁ? ሃሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን🙏

🚥​ተመሳሳይ ሙያዊ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የ YouTube ገጻችንን Subscribe ያድርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤17👍2
In general, the coefficient of thermal expansion
of concrete does not depend on which of the
following factors
Anonymous Quiz
15%
(a) Type of cement
25%
(b) Type of aggregate
16%
(c) The cement content
44%
(d) The quality of water
👍7❤6
𝐒𝐢𝐳𝐞 𝐨𝐟 𝐚 𝐫𝐢𝐠𝐡𝐭 𝐚𝐧𝐠𝐥𝐞𝐝 𝐟𝐢𝐥𝐥𝐞𝐭 𝐰𝐞𝐥𝐝 𝐢𝐬 𝐠𝐢𝐯𝐞𝐧 𝐛𝐲
Anonymous Quiz
26%
0.707 x throat thickness
33%
1.414 x throat thickness
23%
2.0 x throat thickness
19%
Throat thickness
❤8
A 1st class brick immersed in water for 24 hours, should not absorb water (by weight) more than
Anonymous Quiz
38%
10 %
35%
15 %
16%
20 %
11%
25 %
👏5❤3
2.በ EBCS የሳይት አሰራር መሰረት፣ ብላይንዲንግ ሳይደረግለት በቀጥታ አፈር ላይ ለሚሞላ የሰብ-ስትራክቸር ኮንክሪት (ለምሳሌ ፉቲንግ) የሚጠበቀው የኮንክሬት ከቨር (ስፔሰር) መጠን ስንት ነው?
Anonymous Quiz
13%
A) 15 ሚ.ሜ
15%
B) 25 ሚ.ሜ
55%
C) 50 ሚ.ሜ
17%
D) 75 ሚ.ሜ
🙏5❤2
👉የቤተ ክርስቲያን ሕንፃን ከመሠረታዊ የሕንፃ አካላት እስከ የተለያዩ ክፍሎችና የሕንፃ ቅርፆች በቀላልና በተደራጀ መልኩ ለመረዳት የተዘጋጀ ምርጥ የዲጂታል መጽሐፍ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8a873add2d7_etconp
👍2🙏2❤1
3.በብረት ለታጨቀ/congested ሺር ዋል (Shear wall) የሚሆን C-30 ኮንክሪት ስለምፕ ቴስት (Slump test) ስንሰራ፣ ኮንክሪቱ ወደ ታች ከመውረድ ይልቅ የላይኛው ክፍሉ ተቆርጦ ወደ ጎን ቢወድቅ (Shear slump)፣ የሳይት መሃንዲሱ ምን መረዳት አለበት?
Anonymous Quiz
9%
A) ኮንክሪቱ በጣም Workable እና ለታጨቀ ብረት ተስማሚ መሆኑን።
57%
B) ኮንክሪቱ Harsh መሆኑንና ምናልባትም በአሸዋ-ጠጠር ምጥጥን ችግር ቫይብሬት ሲደረግ Segregation ሊፈጠር እንደሚችል ያሳያል።
21%
C) የውሃ መጠኑ ስላነሰ ወዲያውኑ ውሃ መጨመር እንዳለበት።
13%
D) ስለምፑ ትክክል ነው ነገር ግን ጠንከር ያለ ቫይብሬተር (Vibrator) እንደሚያስፈልገው።
❤8
👉ለዚህ ጥያቄ ብዙዎቻቺሁ 50mm ብላቺሁ ነው መልስ የሰጣቺሁ እስኪ አብረን እንየው በ EBCS EN 1992-1-1:2013 መሰረት የፋውንዴሽን ከቨር በአፈሩ ወለል ዝግጅት ላይ ተመስርቶ በሁለት ይከፍላል (Section 4.4.1.3(4) ይመልከቱ)፦

1.lean ኮንክሪት (Blinding/Lean Concrete) ከተሞላ፦ ኮዱ እንደ "Prepared ground" (የተዘጋጀ መሬት) ይቆጥረዋል። ለዚህ ሁኔታ ኖሚናል ከቨሩ ቢያንስ k_1=40ሚ.ሜ መሆን አለበት ይላል።

2. Lean ኮንክሪት (Blinding/Lean Concrete) ሳይሞላ (Cast directly against soil)፦ ኮንክሪቱ በቀጥታ በአፈር ላይ (unprepared soil) የሚሞላ ከሆነ፣ ወለሉ ወጣ ገባ ስለሚሆን ስህተት (deviation) የመፈጠር እድሉ ከፍተኛ ነው።

ስለዚህ ኖሚናል ከቨሩ ቢያንስ k_2 =75ሚ.ሜ መሆን አለበት ይላል።

ለምን የ 75 ሚ.ሜ ኖሚናል ከቨር (Nominal Cover) አስፈለገ?
የኮዱ አንቀጽ (Section 4.4.1.3(2)) የኖሚናል ከቨርን ትርጉም ሲያብራራ፡ ኖሚናል ከቨር (C_(nom)) የሚባለው በድሮይንግ ላይ የምንጽፈው ሙሉ ከቨር ነው።

ይኸውም C_(nom)= C_(min)+ ∆C_(dev) (ዝቅተኛው ከቨር + በሳይት ስራ ሊፈጠር የሚችል የስህተት ልዩነት/Deviation) ድምር ነው።

Lean ኮንክሪት (Blinding) ሳይኖር 75 ሚ.ሜ ኖሚናል ከቨር የሚያስፈልግበት ዋናው ቴክኒካዊ ምክንያት በኮዱ አንቀጽ (Section 4.4.1.3(4)) ላይ እንደሚከተለው ተብራርቷል፦

"ኮንክሪቱ ወጣ ገባ በሆኑ ወለሎች (uneven surfaces) ላይ የሚሞላ ከሆነ፣ ለሚፈጠሩ ትላልቅ ስህተቶች (deviations) እድል ለመስጠት የኖሚናል ከቨር መጠን በአጠቃላይ መጨመር አለበት።"

🚥ይህንን ወደ ሳይት እውነታ ስንቀይረው፦

1⃣. የወለል ወጣ ገባነት፦አፈር በቀጥታ ሲቆፈር ወጣ ገባ ነው፤ ወጥ የሆነ 50 ሚ.ሜ ወይም 75 ሚ.ሜ ቀጥታ ልኬት ማግኘት አስቸጋሪ ነው።
2⃣. የብረቱ ክብደትና የመሰመጥ አደጋ፦lean ኮንክሪት (Blinding) የሌለው አፈር ከባዱ የፋውንዴሽን ብረት በእሱ ላይ ሲያርፍ ወይም ኮንክሪት ሲሞላ ሰራተኞች በእሱ ላይ ሲራመዱ፣ ብረቱን የደገፉት ስፔሰሮች ክብደቱን መቋቋም አቅቷቸው አፈሩ ውስጥ ይሰምጣሉ።

🌟ስለዚህ ለተጠየቀው ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ D. 75ሚ.ሜ ነው።

​💡 ተመሳሳይ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የፌስቡክ ገፃችን Follow ያድርጉ👇

https://www.facebook.com/profile.php?id=61592085774934

@​etconp
❤9🙏4
👉ኳንቲቲ ሰርቨይንግ በቀላሉ ለመረዳት እና ቴክ ኦፍ እንዲሁም Cost Breakdown ለማዘጋጀት የሚጠቅም እጅግ በጣም ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a71b78edc006_etconp
❤3🥰1
👉ለ 1 m² የልስን (Plastering) ስራ ምን ያህል ሲሚንቶ እና አሸዋ ያስፈልጋል?

🌟​በሳይት ደረጃ የቁሳቁስ ብክነትን (Material Wastage) ለመቀነስ እና ወጪን በትክክል ለማቀድ የልስን ስራ ስሜንቶ እና አሸዋ ስሌት ማወቅ ለሳይት ኢንጂነሮች እና ባለቤቶች ወሳኝ ነው።

🏛​ለ 1 m² ግንብ በ 12 mm ውፍረት እና በ 1:4 ሚክስሬሾ (1 ድርሻ ሲሚንቶ ፡ 4 ድርሻ አሸዋ) የሚከተለው መጠን ያስፈልጋል፦

​📌 የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፦

​🔹 ሲሚንቶ (Cement): ~8.2 kg ~6 m² ይበቃል)
​🔹 አሸዋ (Sand): ~0.023 m³

​💡 የሳይት ጥራት ቁጥጥር ምክሮች፦

1️⃣ የግንብ እርጥበት (Curing before plastering): ከልስን በፊት ብሎኬቱ በቂ እርጥበት ማግኘት አለበት፤ ካልሆነ ከልስኑ ውኃ በመምጠጥ ስንጥቅ (Shrinkage Cracks) ፈጥራል።

2️⃣ የሞርታር ቅልቅል ጊዜ (Setting Time): የተደባለቀው የሲሚንቶ እና አሸዋ ውህድ ከ30 እስከ 45 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ ስራ ላይ መዋል አለበት።

3️⃣ አንደኛ እና ሁለተኛ እጅ (Undercoat & Finish Coat): የውጭ ግንብ ከሆነ የረፈረፈው አሸዋ ማጣሪያ (Sieve) ማለፉን ማረጋገጥ።

💫​በእርስዎ ሳይት ላይ ለልስን ስራ 1:3 ወይስ 1:4 ሚክስሬሾ መጠቀምን ይመረጣሉ?

​💡ተመሳሳይ ሙያዊ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የ YouTube ገጻችንን Subscribe ያድርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤17👏2
‎👉ሙሉ የህንፃ ኤሌትሪክ ዲዛይን፣ መስመር ዝርጋታ እና የኤሌትሪክ ስራ የተግባር መማሪያ

⚡️‎በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ይህ ዲጂታል የህንፃ ኤሌትሪክ ስራን ከመሠረታዊ እውቀት እስከ ተግባራዊ የመስመር ዝርጋታ ድረስ በቀላልና በተደራጀ መንገድ ለመማር የሚያግዝ ምርጥ መፅሐፍ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇
‎
‎https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8bcb2fa3202_etconp
❤3🙏2
👉Types of Punching reinforcemt bar:

1.Cranked bars

Is also known as bent-up bars, are used in flat slabs to resist punching shear forces by providing inclined reinforcement around the column, similar to stirrups, to transfer shear stress from the slab to the concrete column more effectively. 

This improves the slab's structural integrity and shear capacity, preventing the concentrated loads from columns from causing shear failure and protecting against progressive collapse.  

Types of Punching reinforcment bar:

2.Shear Reinforcement (Stirrups/Dowel Bars/Shear Heads)

In flat slab design, punching shear at the slab–column connection is a critical failure mode.

Since the slab is thin and heavily stressed around columns, special reinforcement is often needed.

Here’s how shear reinforcement can be provided:

2.1. Stirrups (Closed Links / Vertical Hoops)

Concept: Vertical stirrups placed around the column in multiple perimeters.

Function: Intercept diagonal shear cracks and transfer shear safely.

Details:
Arranged in closed rectangular or circular hoops.

Placed within a critical perimeter around the column (usually at 0.5d to 1.5d from the column face).

2.2.Dowel Bars (Shear Dowel Reinforcement)

Concept: Vertical steel bars (dowels) anchored into the slab near the column face.

Function: Resist vertical shear and enhance punching resistance by direct load transfer.

Details:
Placed in concentric rings around the column.

Often welded to top and bottom anchorage bars or headed at ends for better anchorage.

Common in high-load slabs where stirrups are not practical.

2.3.Shear Heads (Steel Sections / Cruciform Beams)

Concept: Steel I-sections or cross-shaped steel profiles embedded in the slab around the column.

Function: Increase slab thickness locally, redistribute punching shear, and enhance capacity.

Details:
Usually four steel arms extending from the column in orthogonal directions.

Used in heavily loaded slabs (e.g., industrial buildings, parking structures).

Efficient when architectural requirements demand a flat soffit (no drop panels)

@etconp
❤6👍3
👉ብቃት ያለው ሲቪል ኢንጅነር ለመሆን የግድ ማወቅ ያለብዎት 10 ወሳኝ ነጥቦች:-

1️⃣ Drawing ማንበብና መረዳት

Architectural, Structural, Sanitary እና Electrical Drawings በትክክል ማንበብ መቻል።

2️⃣ Quantity Surveying (BOQ)

Quantity Take-off ማድረግ፣ BOQ ማዘጋጀት እና Cost Estimation ማወቅ።

3️⃣ Construction Materials

Cement, Concrete, Reinforcement, Blocks, Aggregates እና Waterproofing Materials ባህሪያቸውን መረዳት።

4️⃣ Site Management

ሰራተኞችን፣ ማሽኖችን እና የስራ ሂደትን በብቃት ማስተዳደር።

5️⃣ Concrete Technology

Mix Design፣ Slump Test፣ Cube Test እና Concrete Curing ማወቅ።

6️⃣ Surveying

Level፣ Total Station እና GPS መጠቀም እና Setting Out ማድረግ።

7️⃣ Contract Administration

Contract Documents፣ Variation Order፣ Payment Certificate እና Claims ማዘጋጀት መቻል።

8️⃣ Construction Software

AutoCAD፣ Civil 3D፣ ETABS፣ SAP2000፣ Excel እና MS Project መጠቀም።

9️⃣ Quality Control & Safety

የጥራት ቁጥጥር (QA/QC) እና የስራ ደህንነት (Safety) መስፈርቶችን ማወቅ።

🔟 Communication & Problem Solving

ከClient፣ Consultant እና Contractor ጋር በተገቢው ሁኔታ መግባባት እና የስራ ችግሮችን ፈጣን መፍታት።

✅ተጨማሪ ምክር: በኢትዮጵያ የConstruction Industry ውስጥ በጣም ተፈላጊ የሆኑ ክህሎቶች BOQ Preparation, Cost Estimation, Payment Certificate Preparation, AutoCAD እና Excel ናቸው።
እነዚህን በደንብ ካወቁ በቀላሉ ስራ ማግኘት ወይም የግል ኮንሰልታንሲ መጀመር ይችላሉ።

​💡 ተመሳሳይ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የፌስቡክ ገፃችን Follow ያድርጉ👇

https://www.facebook.com/profile.php?id=61592085774934

@​etconp
❤21👍5
‎👉ሙሉ የህንፃ ኤሌትሪክ ዲዛይን፣ መስመር ዝርጋታ እና የኤሌትሪክ ስራ የተግባር መማሪያ

⚡️‎በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ይህ ዲጂታል  የህንፃ ኤሌትሪክ ስራን ከመሠረታዊ እውቀት እስከ ተግባራዊ የመስመር ዝርጋታ ድረስ በቀላልና በተደራጀ መንገድ ለመማር የሚያግዝ ምርጥ መፅሐፍ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇
‎
‎https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8bcb2fa3202_etconp
👏2❤1
👉በ 28 ሰዓታት ውስጥ የተገነባው ባለ 10 ፎቅ ሕንፃ፦ የዘመናዊው የሞዱላር ግንባታ አብዮት!

​የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በየጊዜው ከምንገምተው በላይ ፈጣን እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እያስተዋወቀ ይገኛል።

ከዚህ በፊት ከዓመታት በላይ ሊፈጅ የሚችለውን የግንባታ ሂደት በሰዓታት ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ቻይናዊው "ብሮድ ግሩፕ" (Broad Group) ኩባንያ በተግባር አሳይቷል።

•  ​እንዴት ተቻለ? (የሞዱላር ግንባታ ቴክኖሎጂ)፦

◦ ​የሕንፃው አብዛኛዎቹ ክፍሎች እና መዋቅሮች አስቀድመው በፋብሪካ ውስጥ በከፍተኛ ጥራት ተዘጋጅተው (Prefabricated modules) በጭነት መኪናዎች ወደ ግንባታው ቦታ ይወሰዳሉ።
◦ ​ቦታው ላይ ሲደርሱም በክሬኖች (Cranes) አማካኝነት እንደ መጫወቻ ብሎኮች (Lego pieces) እየተደራረቡ እና በቦልቶች እየተጠበቁ፣ የኤሌክትሪክ እና የውሃ ዝርጋታዎች ተጠቃለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ ሕንፃ እንዲቆም ይደረጋል።
•  ​የዚህ ቴክኖሎጂ ዋና ዋና ጥቅሞች፦

◦ ​ እጅግ እጅግ ፈጣን አፈጻጸም፦ ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው እጅግ አጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ።
◦ ​ቀላል እና ጽኑ አቋም፦ በፋብሪካ የሚዘጋጁት የብረት ንጣፎች (Stainless steel modules) ከተለመዱት የኮንክሪት ሰሌዳዎች በበለጠ መልኩ ቀላል ግን እጅግ ጠንካራ በመሆናቸው ለተፈጥሮ አደጋዎች (እንደ ምድር መንቀጥቀጥ) የማይበገሩ እንዲሆኑ ተደርገው የተሰሩ ናቸው።
◦ ​የብክነት መቀነስ፦ በግንባታ ቦታ ላይ የሚከሰተውን የቁሳቁስ ብክነት እና  ውድድር  በእጅጉ ይቀንሳል።

@etconp
❤13😱3🔥2
🌙ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ እንኳን ለ1501 ኛው የነቢዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🕌

@etconp
❤6
👉የኮንክሪት ኮር ቴስት ምንድነው?

🌟ኮር ቴስት ተሞልቶ የተጠናቀቀና 28ቀን የሞላው ኮንክሪትን  compressive strength ውጤትን በተሻለ/በትክክለኛ መንገድ ለመለካት የሚደረገው ቴስት ነው ነው።

🚥በዚህ ሂደት፣

1.Destruct Core Samples: ከተጠናቀቀው የኮንክሪት አካል (ስላብ፣ ቢም፣ ኮሎን) ላይ በሞቦርቦር ኮንክሪት ቁርጥራጭ (core sample) በ core drill መሳሪያ በመጠቀም ይወጣል።

2. Testing: እነዚህ የኮር ናሙናዎችን በላቦራቶሪ በመጨረሻ ግፊት መንገድ በሚደረግ ሙከራ ይመርመራሉ።

⬆️ውጤቱም ኮንክሪቱ የተፈላጊውን ውጤት ማሟላት/አለማሟላት ይጠቁማል ይህውም ለምህንድስና ቡድኑ ለውሳኔ ይቀርባል።

🗂ኮር ቴስት መስራት አስፈላጊ የሚሆነው መቼ ነው?

1. የሀመር ቴስት (Rebound Hammer) ውጤት ጥሩ ባይሆን

2. በውል አንቀጾች አስገዳጅ ሲሆን

ኮር ቴስት ለምን የመጨረሻው አማራጭ ሆነ ?

ሁልጊዜ ትክክለኛ/ከሁሉም በተሻለ/ ውጤት ስለሚሰጠን።

​💡ተመሳሳይ ሙያዊ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የ YouTube ገጻችንን Subscribe ያድርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤10👍1🎉1