Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.2K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ዛሬ ምርጥ መፅሃፍ ይዘንላቹ መጥተናል

🏛Quantity Surveying & Specification📘

🌟የQuantity Surveying እና Building Construction Estimation ከ ሀ አስከ ፐ ችሎታዎን በተግባራዊ ምሳሌዎች የሚያሳድጉበት ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8dd294cbaa9_etconp
❤5🔥1
👉የኮለን ፎርምወርክ ቼክሊስት[Elements of good Column formwork finish]

1.ጥብቅ መሆኑን/Formwork rigidity/

የተዘጋጀው ፎርምወርክ የራሱን ክብደት፣የብረቱን ክብደት፣የርጥብ ኮንክሪቱን ክብደት፣ የኮንክሪት ሰራተኞች፣ የንፋስ ግፊት፣ የስራ መሳሪያዎችና ሌሎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጫናዎችን የሚቋቋም ሆኖ በቂ ጥንካሬ ኖሮት መሰራቱን ማረጋገጥ የመጀመሪያ ነው።

2.የፎርምወርክ ጥራት/Quality of formwork material/

ለፎርምወርክ ስራ ጥቅም ላይ የዋለው እቃ ያልተጣመመ፣ ያላበጠና ያልጎበጠ ፣ወጥነት ያለው ፣ያልተቀደደና ጥሩ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ያለው መሆኑን

3.አቀባዊ ሊኛ/ቱምቢ/Vertical alignment/

የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ልክ በሚገባ ወደላይ ቀጥ ማለቱን

4.አግድም ሊኛ/Horizontal alignment/

ኮለምኑ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ከሌሎች ኮለኖች አንጻር ያለው አቀማመጥ፣ ከታወቀ መነሻ በሚገባ ወጥነት ያለው መሆኑን

5.የኮለን ወርድና ስፋት ልክ/Design dimension/

የኮለኑ ወርድና ስፋት በዲዛይኑ መሰረት መሰራቱን ማረጋገጥ።

6.ከመነሻው ያለው ርቀት/Distance from reference/center to center/

አንዱ ኮለን ከሌላው ኮለን ርቆ የተቀመጠው በዲዛይኑ መሰረት መሆኑን

7.መሃል ገጠምነት/Eccentricity/

ተንጠልጣይ ወለል/Suspended floors/ በሚኖራቸው ግንባታዎች ላይ የላይኛው ወለል ኮለን ከታችኛው ወለል ኮለን ጋር ሴንተራቸው ፍፁም መሃል ገጠም/eccentric/ መሆኑን ማረጋገጥ

8.ከብረቱ ያለው ተገቢ ርቀት
/Design cover/

በፎርምወርኩና በብረቱ መሃል በልዩ ጡብ/Spacers/ መለየቱን ማረጋገጥ ሌላው በጣም አስፈላጊው ነጥብ ነው።

@etconp
❤17👍2
🕌Mosque Architecture & Construction

🌟ስለ መስጊድ አርክቴክቸር እና ግንባታ በተግባር ለመማር የሚረዳ 4 PDF Files ያሉት ZIP Package አዘጋጅተናል📚

📐 የሚያካትተው፦
✅ Mosque Architecture
✅ Concept & Geometry
✅ Space Planning
✅ Design Synthesis & Form
✅ የአርክቴክቸራል እና Structural Drawings የምሳሌ ፕሮጀክቶች
✅ ለመማርና ለፕሮጀክት ማጣቀሻ የሚሆኑ ዝርዝር ማብራሪያዎች ያለው ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8fbfb8b8611_etconp
❤5🥰1
👉የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ እና በኮንስትራክሽን ውል የስራ መጀመሪያ ቀን/Commencement date/.

በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ የስራ መጀመሪያ ቀን እና ውል የተደረገበት ቀን የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡

ይሄውም የሆነበት ውሉ በተደረገበት እለት የግንባታ ስራ ይጀመራል ተብሎ ስለማይታሰብ ነው፡፡

*በኮንስትራክሽን ውል የስራ መጀመሪያ ቀን/Commencement date/

በመርህ ደረጃ የውል የግንባታ ስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ነው፡፡ ስለዚህ የውሉ የግንባታ ጊዜ ተብሎ የሚጠቀሰውን ቀን ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ መቁጠር ስህተት ነው፡፡

ምክንያቱም የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ መካከል ከተፈረመ በኋላ የግንባታው ተጨባጭ ስራ በተለያየ ምክንያት ሊዘገይ ይችላል፡፡ለምሳሌ ግንባታው የሚከናወንበት ቦታ የይገባኛል ጭቅጭቅ ቢነሳበት ጭቅጭቁ እስኪፈታ ድረስ አሰሪው የግንባታውን ሳይት ለተቋራጩ ማስረከብ ያልቻለ እንደሆነ ግንባታው ችግሩ እስከሚፈታ ድረስ ሳይጀመር መቆየቱ የማይቀር ይሆናል፡፡

*ለተቋራጩ የሳይት ርክክብ/site handover/

ለግንባታ የተወሰነው ቦታ ከጥያቄ ነጻ ከሆነና አሰሪው ሙሉ ባለይዞታ ለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ፤ ውል ላዋዋለው ሥራ ተቋራጭ የሥራ ቦታውን ያስረክባል ወይም የሳይት ርክክብ ያደርጋሉ ማለት ነው፡፡

ይህ ከሆነ በኋላ አሰሪው ሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራውን የሚጀምርበትን ቀን
- በርክክብ ወቅት በቃለ ጉባዔ ይወስናል፡፡
- ወይም አስቀድሞ በውሉ ልዩ ሁኔታዎች(Special condition of contract) ላይ በተቀመጠው ቀን እንደሆነ ታውቆ በተባለው ቀን ሥራ ይጀመራለረ ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ሥራ ተቋራጩ ሳይት ሳይረከብ የግንባታው ጅማሬ ቀን ሊቆጠር አይችልም ማለት ነው፡፡
ሳይት ርክክብ ከተደረገ በኋላ እንደፕሮጀክቱ ዓይነት ወይም መጠን ስፋት የሞቢላይዜሽን ቀን ተጨምሮ ዋና የግንባታ ሥራ ማስጀመሪያው ቀን ይወሰናል፡፡ ስለዚህ ተቋራጩ የግንባታ ቁሳቁስ እና የሰው ሀይል ሞቢላይዝ እስከሚያደርግበት ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ የስራ መጀመሪያ ቀን ሊጀምርበት አይገባም፡፡

በዚህ ረገድ በተግባር አልፎ አልፎ ስህተት ሲሰራ ይስተዋላል፡፡ይሄውም አሰሪዎች አንዳንዴ የግንባታውን ጊዜ ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምረው በመቁጠር እና ተቋራጩን በቂ ምክንያት ካለህ የጊዜ ማራዘሚያ/Time extension/ ጠይቅ የሚሉበት የተሳሳተ ሁኔታና አጋጣሚ አለ፡፡

በዚህ ረገድ በሀገራችን እና በአለም ሀገራት እየተሰራባቸው ያሉ የዳበሩ የፊዲክ ጀኔራል ኮንዲሽኖች እና በሀገራችን ተጣጥመው የተቀረጹ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ምን ይዘት አላቸው የሚለውን እና የፍትሀብሄር ህግ ድንጋጌዎችን ደግሞ ቀጥለን እንዳስሳለን፡፡

1. FIDIC RED BOOK 1999

በፊዲክ ሬድ ቡክ 1999 ቨርሽን ክሎስ 8.1 ላይ ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ስራ እንዲጀምር ማስታወቅ እንዳለበት እና ከ7 ቀን ያላነሰ ጊዜ መስጠት እንደሚገባው ይጠቅሳል፡፡

እንደዚሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በልዩ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር የስራ መጀመሪያው ቀን/ Commencement date/ ተቋራጩ በጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ42 ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበት ተቀምጧል፡፡

በተጨማሪም ተቋራጩ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ወዲያውኑ እና ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡ተቋራጩ/contractor/ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ይቅርታ ሊያሰጥ የሚችል ምክንያት ሳይኖረው ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት በክሎስ ላይ የተቀመጠውን ግዴታውን ያልተወጣ እንደሆነ ደግሞ አሰሪው/client/ውሉን ለማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 15.2(c) ላይ ተቀምጧል

2. FIDIC 1987

በኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ፎር ወርክስ ኦፍ ሲቪል ኢንጅነረንግ ኮንስትራክሽን ፊዲክ 1987 ቨርሽን ክሎስ 41.1 ላይ ስለ ኮመንስመንት ዴት/የስራ መጀመሪያ ቀን ተቀምጧል፡፡ይዘቱም መሀንዲሱ የስራ መጀመሪያውን ቀን በጨረታ ሰነዱ አፔንዴክስ ላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት የሚገልጽ ነው፡፡ተቋራጩም የስራ መጀመሪያው ቀን በመሀንዲሱ ከተገለጸለት በኋላ ያለመዘግየት እና በተቻለ ፍጥነት የግንባታ ስራውን መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡

የግንባታ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቆጠር የሚጀምረውም ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ስለመሆኑ ክሎስ 43.1 ላይ ተቀምጧል፡፡

እንግዲህ ተቋራጩ በቂ ምክንያት ሳይኖረው በክሎስ 41.1 ላይ በተመለከተው አግባብ የግንባታ ስራውን ሳይጀምር የቀረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ለማቋረጥ እና ተቋራጩን ከሳይት ለማስወጣት መብት/expel right/ እንዳለው ክሎስ 63.1 ያስቀምጣል፡፡

3. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር  አቋም/MoWUD 1994

ይህ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ1994 ስራ ላይ አውሎት የነበረው የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/MoWUD 1994 በተለይ ከፊዲክ/FIDIC 1987 ቨርሽን የተወሰደ ሲሆን ስለኮመንስመንት ዴት በሁለቱም ጀኔራል ኮንዲሽኖች ላይ ተመሳሳይ ይዘት ባለው ሁኔታ ያስቀምጣሉ፡፡
ስለዚህ ማብራሪያውን መድገም አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም፡፡

4. የመንግስት ግዢዎች ኤጀንሲ/PPA 2011

በፒፒኤ 2011 ቨርሽን ክሎስ 71 ላይ የስራ መጀመሪያ ቀን በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ላይ ሊቀመጥ እንደሚችል ወይም ደግሞ በአስተዳደራዊ መንገድ በኢንጅኒየሩ በሚሰጥ ትእዛዝ ሊታወቅ እንደሚችል ይጠቅሳል፡፡

እንዲሁም በሌላ ሁኔታ በውሉ ላይ ካልተገለጸ በስተቀር ለተቋራጩ የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለጸ ቀን ጀምሮ ታስቦ ከ120 ቀናት ለማለፍ አይችልም፡፡

5-የፍትሀብሄር ህግ

የስራ ማከናወኛ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610 - 2637) በሚመለከት በውሉ ላይ የጊዜ ጉዳይ በግልጽ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ተቋራጩ ወዲያውኑ ስራ መጀመር እንደሚኖርበት በአንቀጽ 2619 ላይ ተደንግጓል፡፡የግንባታ ጊዜ በተገለጸባቸው ውሎች ደግሞ ስራ ተቋራጩ ስራውን ወዲያው ያልጀመረ እንደሆነ እና በጊዜ ገደቡ የግንባታ ስራውን ለመፈጸም የማይችል መሆኑ የታወቀ እንደሆነ አሰሪው ለተቋራጩ ስራውን የሚጀምርበትን ጊዜ ሊወስንለት እንደሚችል በአንቀጽ 2618 ላይ ተቀምጧል፡፡

ሌላው እነዚህ ደንቦች ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ስራ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3019-3040) በሚመለከተው የግል የስራ ተቋራጭነት ውል ላይ ጭምር ተፈጻሚነት እንደሚኖራቸው ከአንቀጽ 3019(2) ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡

የአስተዳደር መስሪያ ቤት የኮንስትራክሽን ውል ማለትም የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3244 እና ተከታዮቹ) በሚመለከት እያንዳንዱ ተዋዋይ ወገን ግዴታዎቹን በውሉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡

በውሉ ላይ ግልጽ የጊዜ ስምምነት የሌለ እንደሆነ ደግሞ ግዴታው በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ መፈጸም እንደሚኖርበት በአንቀጽ 3174 ላይ ተቀምጧል፡፡

ይህ ድንጋጌ ስለአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጠቅላላው የተደነገገ ሲሆን የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውልን በሚመለከተው ልዩ ክፍል ላይም በግልጽ ስለስራ ጊዜ ተደንግጓል፡፡

@etconp
❤11👍4
👉ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን ብዝዎች በጠየቃቹን መሰረት የ ETABS ቲቶርያል ቪድዮ በአማርኛ ቋንቋ ከ introduction ጀምሮ Analysis እና Design ኣካተን ምርጥ ቪድዮ ኣዘጋጅተንላቹዋል።

🫵እንሆ ዛሬ ክፍል 1 ይዘንላቹ መጥተናል👇

https://youtu.be/yB1KO_nYByc

@etconp
❤5🙏3🔥1
👉ዛሬ ምርጥ መፅሃፍ ይዘንላቹ መጥተናል

🏛Quantity Surveying & Specification📘

🌟የQuantity Surveying እና Building Construction Estimation ከ ሀ አስከ ፐ ችሎታዎን በተግባራዊ ምሳሌዎች የሚያሳድጉበት ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8dd294cbaa9_etconp
❤2👌2🔥1
📐 Stirrups BBS Calculation – Step by Step🏗️

🌟Learn how to calculate stirrup cutting length, quantity, and total steel weight for an RCC column.

📌 Column Size: 230 × 460 mm
📌 Stirrup Dia: 8 mm
📌 Spacing: 150 mm c/c
📌 No. of Stirrups: 34 Nos.
📌 Cutting Length: 1162 mm
📌 Total Weight: ≈ 15.60 kg

☄Full Cualculation and description is on the image.

🗂Save this post for your Civil Engineering & Site Work reference.

​💡ተመሳሳይ ሙያዊ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የ YouTube ገጻችንን Subscribe ያድርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤6
🏗️ Bid & Contract Document Package

🌟ለኢትዮጵያ የግንባታ Bid, Tender & Contract ዝግጅት የሚያግዝ ፕሮፌሽናል ፓኬጅ።

📦 4 Editable MS Word Documents
📁 One ZIP File

🇪🇹 ለኢትዮጵያ ግንባታ ፕሮጀክቶች

🏛ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a7fed4a173ec_etconp
❤2🙏2
👉ስለ አንድ ህንጻ አጠቃላይ ይዘቶች

🌟የአንድ ህንፃ ክፍል በዋናነት በሁለት ይከፈላል።

1.ታችኛው መዋቅር/Sub structure/: ከመሬት በታች የሚገኘው የህንጻ ግንባታ ክፍል ሲሆን

2.ላይኛው መዋቅር/Super structure/: ከመሬት በላይ የሚገኘው የህንጻ ግንባታ ክፍል ሲሆን

🗂አንድ ህንጻ የሚኖሩት መሰረታዊ ይዘቶች/Basic Components/

*መሰረት/Foundations/
ግድግዳዎች/Walls/
ወለሎች/Floors/
በርና መስኮቶች
*ደረጃዎች
ጣሪያዎች

*የተለያዩ አገልግሎት ላይ የሚው የማጠናቀቂያ ስራ ግብዓቶች

🚥አንድ ህንጻ የታሰበለትን የተሟላ አገልግሎት እንዲያስገኝ በዲዛይን ወቅት መታወስ ስለሚገባው መሰረታዊ ሁኔታዎች/Design and Performance requirements/

1.ህንጻው በቂ ጥንካሬና ፅኑነት ሊኖረው የሚገባ ሆኖ ዲዛይን መደረጉን/Strength and Stability/

2.የመለጠጥ ወይም የመኮማተር ርጋቴው ታሳቢ መደረጉ/Dimensional Stability/

3.የተጠቃሚውን ምቾት ያገናዘበ /Comfort and Convenience/

4.ርጥበትና የፍሳሽ ስርገትን የመከላከል ብቃት ሊኖረው የሚገባ መሆኑ/Resistance to Moisture Protection/

5.እሳት የመቋቋም ብቃት /Fire protection/

6.የሙቀት ክለላ/Heat thermal/ insulation

7.በቂ ብርሃንና አየር የሚያስገባ መሆኑ/light and Ventilation/

8.የድምፅ ክለላ/Sound Insulation/

9.ለረጅም ጊዜ ዘላቂ ስለመሆኑ/Durability/

10.ጥበቃ/ደህንነት/Security/

11.በብል በቀላሉ የማይጠቃ መሆኑ/Protection to Vermin and termites/

12.ወጭ ቆጣቢ መሆኑ/Building Economy/

​💡ተመሳሳይ ሙያዊ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የ YouTube ገጻችንን Subscribe ያድርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤9👍2🔥1🙏1
ETABS 21.1.0. etconp .rar
1018.6 MB
👉ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን ብዝዎች በጠየቃቹን መሰረት የ ETABS ቲቶርያል ቪድዮ በአማርኛ ቋንቋ ከ introduction ጀምሮ Analysis እና Design ኣካተን ምርጥ ቪድዮ ኣዘጋጅተን ዛሬ ክፍል 1 የለቀቅን ሲሆን👇

https://youtu.be/yB1KO_nYByc

የምንጠቀምበት ሶፍትዌር ደሞ ከዚህ ፅሁፍ አያይዘነዋል🙏

@etconp
🙏6❤4🥰3
👉አዲስ ባሁን የገበያ ዋጋ የተሰራ የህንፃ Cost BreakDown Analysis እና BOQ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊን ያውርዱ👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a7d4cdc7b3de_etconp
🥰2🙏1
👉በሳይት ላይ የፓድ ፋውንዴሽን (Pad Footing) የጥራት እና የመለኪያ ፍተሻ🏗️

☄​በምስሉ ላይ እንደምናየው የፓድ ፋውንዴሽን ቁፋሮ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ የሊን ኮንክሪት (Blinding Concrete) ከመፍሰሱ በፊት የፓዱ ስፋት፣ ጥልቀት እና የኮለሙ መካከለኛ ነጥብ (Centerline) ከፕሮፋይል ገመድ (Grid Line) ጋር እየተፈተሸ ይገኛል።

🚥​በ Pad Footing ቁፋሮ ወቅት ትኩረት የሚሹ 3 ዋና ዋና ነጥቦች፦

1. ​Soil Bearing Capacity (የአፈር የመሸከም አቅም)፦ ቁፋሮው በዲዛይኑ የተጠቆመው ጠንካራ የአፈር ንብርብር (Bearing Strata) ላይ መድረሱን ማረጋገጥ።

2. ​Excavation Dimensions (የቁፋሮ ስፋትና ጥልቀት)፦ የፓዱ ርዝመት፣ ወርድ እና ጥልቀት ከስትራክቸራል ስዕሉ ጋር ሙሉ በሙሉ መጣጣሙን መፈተሽ።

3. ​Centerline Alignment፦ የኮለሙ መካከለኛ ነጥብ ከፓዱ መካከለኛ ነጥብ ጋር መግጠሙን ማረጋገጥ፤ ይህም Eccentric Loading (ያልተጠበቀ ጭነት) እንዳይኖር ይከላከላል።

⬆️​በእርስዎ ሳይት ላይ የPad Footing ቁፋሮ ሲያካሂዱ አፈሩ ልቅ (Loose Soil) ቢሆን ምን አይነት መፍትሔ ይወስዳሉ?

​💡ተመሳሳይ ሙያዊ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የ YouTube ገጻችንን Subscribe ያድርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤9🙏3👍1👏1
👉የ ህንፃ ዲዛይን አዘጋጅታቹ ለማፅደቅ ዲዛይኑ መካተት ያለባቸው የአርክቴክቸራል፣ስትራክቸራል፣ሳኒተሪ እና ኤሌክትሪካል ቼክሊስቶች ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱ👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a76b89233390_etconp
❤1🙏1
👉Reasons for Bid Cancelation
/ጨረታ ስለመሰረዝ/

1. በቂ የተጫራች ቁጥር ማግነኘት ሳይቻል ሲቀር[ከ3 በታች ተሳታፊ]

2. የቀረበው የተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ከተያዘው ባጀት በላይ ሲሆን

3. የቀረቡት  የተጫራቾች ሰነድ አጥጋቢ ሳይሆን ሲገኝ

4. የሰነድ ግራቀኝ ማጣራት /ምርመራ / ወቅት የቀረቡት ሰነዶች ማጭበርበር ሲገኝባቸው

5. የጨረታ ሰነዱ ላይ ያልታዩ የውል ሁነቶች/conditions/ ሲገኙ

6. የጨረታ ሰነዱ ላይ የልዩ ሁኔታዎች ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ

@etconp
❤9
👉ኮንስትራክሽን ሳይት ላይ የሚጠቅሙ Template Format ዶክመንቶች ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱ👇

🌟ከ ፎርማቶቹ Site Diary,Site Book እና ሌሎች ተካቶባቹዋል

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a740ccd63237_etconp
👌2👍1
👉በሳይት ላይ የሚያጋጥም ከባድ መዋቅራዊ አደጋ፦ Column Buckling Failure⚠️🏗️

🌟​በምስሉ ላይ እንደምናየው የተጠናከረ ኮንክሪት አምድ (RC Column) ከባድ የቦታ መፈናቀል እና የመታጠፍ (Buckling) አደጋ አጋጥሞታል።

☄ይህ አይነቱ አደጋ ሙሉ ህንፃውን ለውድቀት (Catastrophic Collapse) ሊዳርግ የሚችል አደገኛ ሁኔታ ነው።

🏛​ለ Column Buckling መንስኤ የሚሆኑ 3 ዋና ዋና ነጥቦች፦

1. ​High Slenderness Ratio (የረጅም አምድ ሁኔታ)፦ የኮለሙ ርዝመት ከስፋቱ አንጻር አላስፈላጊ በሆነ ሁኔታ ረጅም ሲሆን (Slender Column) የመታጠፍ እድሉ ይጨምራል።

2. ​Inadequate Lateral Ties (የካንሰል ብረት አነስተኛነት/ርቀት)፦ የካንሰል ብረቶች ርቀት (Stirrup Spacing) ከተፈቀደው በላይ ሰፊ ሲሆን ዋናዎቹን የ ቁም ብረቶች (Main Longitudinal Rebars) አግዶ የመያዝ አቅማቸው ይቀንሳል።

3. ​Eccentric Loading & Poor Concrete Quality፦ ጭነቱ ከመካከለኛ መስመር (Centerline) ውጪ ማረፍ ወይም የኮንክሪት ጥራት ማነስ (Honeycombing)።

🚥​በእርስዎ ሳይት ላይ ረጅም ኮለሞችን (Slender Columns) ሲነድፉ ወይም ሲሰሩ Bucklingን ለመከላከል የሚያደርጉት ዋነኛ ጥንቃቄ ምንድን ነው? ሃሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን

​💡ተመሳሳይ ሙያዊ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የ YouTube ገጻችንን Subscribe ያድርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤8
👉ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን ብዝዎች በጠየቃቹን መሰረት የ ETABS ቲቶርያል ቪድዮ በአማርኛ ቋንቋ ከ introduction ጀምሮ Analysis እና Design ኣካተን ምርጥ ቪድዮ ኣዘጋጅተንላቹዋል።

🫵እንሆ ዛሬ ክፍል 2 ይዘንላቹ መጥተናል👇

https://youtu.be/nI-r7Tbcba4
❤2🙏2👍1
🕌ስለ መስጊድ አርክቴክቸር እና ግንባታ በተግባር ለመማር የሚረዳ 4 ምርጥ መፅሐፍ በአንድ ላይ አዘጋጅተናል📚

📐 የሚያካትተው፦
✅ Mosque Architecture
✅ Concept & Geometry
✅ Space Planning
✅ Design Synthesis & Form
✅ የአርክቴክቸራል እና Structural Drawings የምሳሌ ፕሮጀክቶች
✅ ለመማርና ለፕሮጀክት ማጣቀሻ የሚሆኑ ዝርዝር ማብራሪያዎች ያለው ነው🌙

💫እነዚህ መፍሐፍ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8fbfb8b8611_etconp
❤3
🧱 በሊንቴል ቢም (Lintel Beam) እና በበሮች/መስኮቶች አናት ግንባታ ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ ወሳኝ ጥንቃቄዎች!

​በምስሉ ላይ እንደሚታየው ከስር በቀይ ጡብ (Brick Plinth Work) ከተሰራ መሰረት በላይ የብሎኬት ግንብ (HCB Superstructure Wall) የተገነባ ሲሆን፤ በበሮች እና በመስኮቶች ክፍተት አናት ላይ የሊንቴል (Lintel Beam) ስራ ተከናውኗል።

​📌 በሳይት ደረጃ ለጥራት ቁጥጥር ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነጥቦች፦

​1️⃣ የሊንቴል ቢም ጥቅም (Purpose of Lintel Beam): ከበሩ ወይም መስኮቱ በላይ የሚገነባው ግንብ ክብደት በቀጥታ በፍሬሙ (Door/Window Frame) ላይ አርፎ ጉዳት እንዳያደርስ ክብደቱን ወደ ጎን ግንቦች ያስተላልፋል።

2️⃣ የማረፊያ ርዝመት (Bearing Length): ሊንቴል ቢም ከክፍተቱ (Opening) አልፎ በሁለቱም ጎን ባሉት ግንቦች ላይ አነስተኛው ከ15 እስከ 20 ሴ.ሜ (cm) ማረፍ/መደገፍ አለበት።

3️⃣ ተከታታይ የሊንቴል ባንድ (Continuous Lintel Band): በተለይ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ባላቸው አካባቢዎች ሊንቴሉ በነጠላ ክፍተቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በህንፃው ዙሪያ ሙሉ በሙሉ የታሰረ (Continuous Band) ሆኖ ቢሰራ የህንፃውን መዋቅራዊ ጥንካሬ በእጅጉ ይጨምራል።

4️⃣ የመሰረት እና የብሎኬት ስራ ትስስር: ከስር ያለው የቀይ ጡብ መሰረት እና የብሎኬት ግንቡ በትክክለኛ የሲሚንቶ ሞርታር ውህድ እና በሌቭል (Plumb/Level) መሰራቱን ማረጋገጥ።

​🌟አዳዲስ የስራ ቅጥሮች እና የኮንስትራክሽን ጨረታዎች ሲወጡ በቀላሉና በ ትኩሱ ለመመልከት ከታች ባለው ሊንካችን ይቀላቀሉን።

📌እንዲሁም ለወዳጆቻቹ SHARE ያርጉ👇

https://t.me/ETCONpWORK
https://t.me/ETCONpWORK
❤8👍1