Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.2K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
🔹 Boundary Survey Plan – የProperty Boundary እና Coordinates።
🔹 Setting-Out Drawing – የCoordinates፣ Grid Lines፣ Benchmarks እና Construction Control Points መረጃ።
🔹 As-Surveyed Drawing – እንደተሰርቬይ የተመዘገበውን Existing Condition የሚያሳይ Drawing።
🔹 Survey Control Plan – የSurvey Control Points፣ Benchmarks እና Reference System ያሳያል።

8️⃣ Infrastructure Drawings
▶ Water Supply Network Drawing – የWater Supply Network አቀማመጥ።
▶ Irrigation Layout Drawing – የIrrigation System አቀማመጥ።
▶ Canal Profile Drawing – የCanal ቁመታዊ ፕሮፋይል።
▶ Canal Cross-Section Drawing – የCanal መስቀለኛ ክፍል።
▶ Dam General Arrangement Drawing – የDam አጠቃላይ አቀማመጥ።
▶ Spillway Drawing – የSpillway አቀማመጥና ዝርዝር።
▶ Intake Structure Drawing – የWater Intake Structure ዝርዝር።
▶ Bridge General Arrangement (GA) Drawing – የBridge አጠቃላይ አቀማመጥ።
▶ Bridge Structural Drawing – የDeck፣ Abutment፣ Pier፣ Foundation እና Reinforcement ዝርዝሮች።

9️⃣ Construction & Execution Drawings
🔹 Construction Drawing – ስራውን በSite ላይ ለመፈጸም የሚያገለግል Drawing።
🔹 Issued for Construction (IFC) Drawing – ተገምግሞና ተፈቅዶ ለConstruction በይፋ የተሰጠ Drawing።
🔹 Shop Drawing – በContractor፣ Subcontractor ወይም Supplier የሚዘጋጅ፣ አንድ Component እንዴት እንደሚመረት/እንደሚጫን በዝርዝር የሚያሳይ Drawing።
🔹 Fabrication Drawing – አንድ Component ለማምረት የሚያስፈልጉ ትክክለኛ Dimensions፣ Materials እና Details የሚያሳይ Drawing።
🔹 Installation/Erection Drawing – Components እንዴት እንደሚገጣጠሙና እንደሚተከሉ የሚያሳይ Drawing።

🔟 Coordination Drawings
🔹 Combined Services Drawing – Architectural፣ Structural፣ Electrical፣ Plumbing እና Mechanical Services በአንድ Drawing ላይ የሚያሳይ።
🔹 MEP Coordination Drawing – Mechanical፣ Electrical እና Plumbing Systems እርስ በርስ እንዳይጋጩ ለማስተባበር የሚያገለግል Drawing።
🔹 Clash Detection Drawing/Model – በተለያዩ Systems መካከል የሚፈጠሩ የPhysical Clash ችግሮችን ለመለየት የሚያገለግል።
🔹 Builder's Work Drawing – ለMEP Services የሚያስፈልጉ Openings፣ Sleeves፣ Penetrations እና Embedded Items የሚያሳይ Drawing።

1️⃣1️⃣ Tender & Contract Drawings
🔹 Tender/Bid Drawing – ተጫራቾች የስራውን ዋጋ ለማዘጋጀት ከTender Documents ጋር የሚሰጥ Drawing።
🔹 Design Drawing – እንዴት መገንባት እንዳለበት የሚያሳይ የDesign መረጃ።
🔹 Approved Drawing – በClient፣ Consultant ወይም በሚመለከተው Authority ተገምግሞ የጸደቀ Drawing።
🔹 Revision Drawing – በቀድሞ Drawing ላይ የተደረጉ ለውጦችን የያዘ አዲስ Revision።
🔹 As-Built Drawing – በConstruction መጨረሻ ላይ በተግባር እንደተገነባው የሚያሳይ የመጨረሻ Drawing።
🔹 Record Drawing – የተጠናቀቀውን Project ትክክለኛ ሁኔታ ለወደፊት Reference የሚመዘግብ Drawing።

🏛ምርጥ ቤዝመንት ያለው G+5 ህንፃ ማለትም አርክቴክቸራል፣ስትራክቸራል፣ኤሌክትሪካል እና ሳኒተሪ ያካተተ በ Auto Cad የተሰራ ዲዛይን ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a75638f22910_etconp

@etconp
❤8🙏3🥰2
👉የሳምንቱ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ዜናዎችና ቴክኖሎጂዎች 🏗️🌍

☄​ለዚህ ሳምንት ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን እና የሪል ስቴት ዘርፍ ትኩረትን የሳቡ ዋና ዋና ክስተቶች፣ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች እና የግንባታ ማሻሻያዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፦

​አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በግንባታ ደህንነት ቁጥጥር ላይ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ግንባር ቀደም የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች የደህንነት ካሜራዎችን ከ AI ቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት በግንባታ ቦታዎች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ የሚጠቁም ሥርዓት በስፋት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።

ቴክኖሎጂው ሠራተኞች የግንባታ እቃዎችን (ለምሳሌ ሄልሜት እና የደህንነት ማሰሪያዎችን) በትክክል ማጥለቃቸውን በራስ-ሰር በመከታተል የሥራ ላይ አደጋዎችን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ችሏል።

​የካርቦን ልቀት ቅነሳ በሲሚንቶ ማምረቻዎች
ዓለም አቀፍ የሲሚንቶ አምራቾች ማህበር ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሰረት፣ በግንባታ ግብአቶች ዘርፍ የሚወጣውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት በግማሽ ለመቀነስ የሚያስችሉ አዳዲስ 'ግሪን ሲሚንቶ' (Green Cement) አማራጮች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

በተለይ እንደ ቮልካን አሽ እና በኢንዱስትሪ ቆሻሻዎች ላይ የተመሰረቱ የሲሚንቶ ማምረቻ ቴክኖሎጂዎች በፈረንሳይ እና ጀርመን በስፋት ወደ ሥራ እየገቡ ናቸው።

​የትላልቅ ከተሞች የከርሰ ምድር መሠረተ ልማት እና አውቶሜትድ ቦይ ማዕቀፎች
በእስያ እያደጉ ባሉ መካከለኛ እና ታላላቅ ከተሞች፣ የትራፊክ መጨናነቅን እና የቧንቧ መስመር ጥገና ፈተናዎችን ለመቅረፍ ባለ ብዙ ደረጃ የከርሰ ምድር መሠረተ ልማት ኔትወርኮች እየተገነቡ ይገኛሉ።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ በሮቦቲክስ እና በዲጂታል መንታ (Digital Twin) ቴክኖሎጂዎች የሚታገዙ ሲሆን፣ የከተሞችን የረጅም ጊዜ ዘላቂነት እያረጋገጡ ይገኛሉ።

🚥​በቅድመ-ግንባታ

(Prefabrication) እና ሞጁላር ህንፃዎች ላይ የሚታየው ዕድገት በአሜሪካ እና በMiddle East (መካከለኛው ምስራቅ) የሪል ስቴት ገበያ የጊዜ እና የወጪ ቆጣቢነቱን ከፍ ለማድረግ በፋብሪካ ተጠናቀው የሚገጠሙ የሞጁላር ህንፃዎች ፍላጎት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ነው።

ይህ አሰራር የግንባታ ጊዜን እስከ 40 በመቶ መቀነስ እንደቻለ የዘርፉ ጥናቶች ያመለክታሉ።

🌟ለተጨማሪ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ የኮንስትራክሽን መረጃዎች ሌላኛው የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ETCONpWORK
❤8
👉የአስፋልት መንገዶች ለምን ይሰነጣጠቃሉ? 🛣️⚠️

በመንገድ ላይ እንደ አዞ ቆዳ የሚመስሉ ብዙ ትንንሽ ስንጥቆች አይተው ያውቃሉ? 😯

ይህ Alligator Cracking (Fatigue Cracking) የሚባል የመንገድ ንጣፍ መድከም ምልክት ነው። መንገዱ ለምን እንዲህ ይሆናል?

🔹 1. ከመጠን በላይ ጭነት 🚛
መንገዱ ከተሰላለት የበለጠ ከባድ መኪናዎች በተደጋጋሚ ሲያልፉበት፣ ንጣፉ በጊዜ ሂደት ይደክማል።

🔹 2. ደካማ የመንገድ መሠረት 🏗️
ከአስፋልቱ በታች ያለው መሠረት በቂ ካልተጠናከረ ወይም የመሸከም አቅሙ ዝቅተኛ ከሆነ፣ መንገዱ መስመጥና መሰነጣጠቅ ይጀምራል።

🔹 3. ውኃ 💧
ውኃ በስንጥቆች ወደ መንገዱ መሠረት ከገባ አፈሩን ሊያላላ ይችላል። በተለይም ጥሩ የውኃ ማስወገጃ ስርዓት ከሌለ ችግሩ ይባባሳል።

🔹 4. የአስፋልት እርጅናና የሙቀት ለውጥ ☀️🌧️
አስፋልት በጊዜ ሂደት ተለዋዋጭነቱን ያጣል። የሙቀት ለውጦችም ስንጥቆች እንዲፈጠሩና እንዲስፋፉ ሊያደርጉ ይችላሉ።

👉 ስለዚህ መንገድ መሥራት ብቻ አይበቃም ትክክለኛ የመንገድ መሠረት፣ ጥሩ የውኃ ማስወገጃ ስርዓት፣ የጭነት ቁጥጥር እና ወቅታዊ ጥገና ካለ የመንገዱን ዕድሜ ማራዘም ይቻላል🛣️

እርስዎ በአካባቢዎ እንዲህ ዓይነት የመንገድ ስንጥቅ አይተዋል? ምክንያቱ ምን ይመስልዎታል? 👇

​​🌐ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
❤17👏1
👉ባሁኑ ባለው ዋጋ የተሰራ፣ጨረታ ስትሞሉም የሚጠቅማቹ የመንገድ ስራ BOQ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6aa4f7a526f13_etconp
❤2🔥1
👉በቁፋሮ ስራ ወቅት የኦፕቲካል ሌቭል (Automatic Level) እና የኤክስካቬተር ቅንጅት! 🚜📐

🌟​በምስሉ ላይ እንደምታዩት የመንገድ ወይም የፍሳሽ መስመር ቁፋሮ (Excavation Work) በሚካሄድበት ወቅት በኤክስካቬተር የሚሰራውን ቁፋሮ በኦፕቲካል ሌቭል (Level Instrument) እየተቆጣጠርን እንገኛለን።

በዚህ ወቅት የሚደረግ የሌቭል ቁጥጥር ጥቅሞች፦

​1️⃣ ከመጠን በላይ ቁፋሮን መከላከል (Prevents Over-excavation)፦ የተወሰነውን ዲዛይን ጥልቀት (Design Depth) አልፎ ከመቆፈር የሚመጣን የአፈር እና የበጀት ብክነት ይከላከላል።

2️⃣ ትክክለኛ አጋደል መስጠት (Ensuring Proper Slope/Gradient)፦ የፍሳሽ ወይም የዝናብ ውኃ መስመሮች በትክክለኛው አጋደል እንዲፈሱ የከፍታና ዝቅታ መለካቱን በየደረጃው ይከታተላል።

3️⃣ አስፈላጊውን የመሰረት አፈር ደረጃ ማረጋገጥ (Subgrade Formation Level)፦ ለቀጣይ የጠጠር ንጣፍ (Sub-base/Base-course) ዝግጁ የሚሆነውን ደረጃ በትክክል ለማስቀመጥ ይረዳል።

​ጥራት ያለው ስራ የሚረጋገጠው በመሳሪያዎች ድጋፍና በጥንቃቄ በሚደረግ የሳይት ቁጥጥር ነው! 🤝

     ━━━━━━━━━━━━━━
​📌 ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን እና የሳምንቱን የኮንስትራክሽን ዜናዎች ለማግኘት ​የፌስቡክ ገፃችን ይጎብኙ👇

https://www.facebook.com/profile.php?id=61592085774934

@etconp
❤5👏2
👉Complete Guide to Reading Building Drawings

📐መፅሃፉ የህንፃን ድሮዊንግ በተግባር ለመረዳት እና ስለ ጠቅላላ አርክቴክቸር ሳይነስ የሚዳስስ ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውሩዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6aa7c4a30b34d_etconp
❤2👏2
​🏗️የኮንስትራክሽን ሴፍቲ

🌟የሕይወት እና የስኬት መሠረት
​በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ደህንነት (Construction Safety) አማራጭ የሌለው የሥራችን ልብ ነው።

🏛ግንባታዎች በታቀደላቸው ጊዜ፣ በበጀት እና በጥራት እንዲጠናቀቁ የሠራተኞቻችን ደህንነት ሁልጊዜም ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።

​⚠️ 3ቱ ዋና ዋና የኮንስትራክሽን አደጋ መከላከያ ምሰሶዎች

⬆️​የግል መከላከያ ዕቃዎች (PPE): ሄልሜት፣ የደህንነት ጫማ፣ መነጽር እና አንጸባራቂ ልብሶችን ሁልጊዜም በሥራ ቦታ ላይ በአግባቡ መጠቀም ግዴታ ነው።

🗂​የቁመት ሥራዎች ደህንነት: መሰላል እና ስካፎልዲንግ (Scaffolding) ከመጠቀምዎ በፊት ጽኑ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንዲሁም የደህንነት መጠበቂያ ገመድ (Safety Harness) መደረጉን ማረጋገጥ።

🗂​የአካባቢ ግንዛቤ: በሥራ ማዕከሉ ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ በመገንዘብ የደህንነት ምልክቶችን ማክበር እና ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ።

🔆​ማሳሰቢያ: ደህንነቱ የተጠበቀ የሥራ ቦታ የምርት ጥራትን ይጨምራል፤ የቤተሰብንም ሕይወት ከሀዘን ይታደጋል። "ደህንነት ቀዳሚው የሥራችን መለያ ነው!"

Via Ethio Con

@etconp
❤13👍1👏1🕊1
👉ምርጥ ቤዝመንት ያለው G+5 ህንፃ ማለትም አርክቴክቸራል፣ስትራክቸራል፣ኤሌክትሪካል እና ሳኒተሪ ያካተተ በ Auto Cad የተሰራ ዲዛይን ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a75638f22910_etconp
👌2🥰1
👉የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ወይም ካርታ አሰጣጥ ሒደት!

🌟የ“የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ወይም ካርታ አሰጣጥ” በኢትዮጵያ የሚመራው በመሬት ህግ እና በክልሎች መመሪያ መሠረት ነው።

🏛የአፈጻጸም ሂደቱ፦

1. የህግ መሠረት

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 40 መሬት የመንግስትና የህዝብ ንብረት መሆኑን ይወስናል።

ግለሰቦች የሚኖራቸው መብት = የመሬት ይዞታ (holding/use right) እንጂ የባለቤትነት መብት አይደለም።

የከተማ ቦታ የሊዝ አዋጅ 721/2004 (Urban Lands Lease Holding Proclamation No. 721/2011) ከተማ መሬት በሊዝ ስር እንደሚሰጥ ይወስናል።

የሊዝ ውል እና የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ አሰጣጥን ይደነግጋል።

የክልል መሬት አዋጅ

እያንዳንዱ ክልል የራሱ የከተማ መሬት አስተዳደር አዋጅ አለው።

የካርታ ስርዓት እና የመሬት መዝገብ በክልል ደረጃ ይተገበራል።

2. የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ (Title Deed) ምንድነው?

ግለሰብ ወይም ድርጅት በተወሰነ መሬት ላይ ያለውን የይዞታ መብት የሚያረጋግጥ ህጋዊ ሰነድ ነው።

.የቦታ መጠን
.የካርታ ቁጥር
.የቤት ቁጥር
.የመዝገብ ቁጥር

በከተሞች ውስጥ እንደ “ካርታ” ይጠራል።

3. የካርታ አሰጣጥ ሂደት (በአጠቃላይ)

1. ማመልከቻ

በከተማ መሬት አስተዳደር ቢሮ ማመልከቻ ማቅረብ

2. የመሬት መለኪያ (Survey)

.በቴክኒክ ባለሙያ መለኪያ ይደረጋል

.የካርታ ፕላን ይዘጋጃል

3. ምርመራ እና ማረጋገጫ

.የውል ሰነድ (ሊዝ ውል)

.ግብር ክፍያ ማረጋገጫ

.የግንባታ ፍቃድ (ካለ)

4. መዝገብ ላይ መመዝገብ

በመሬት መዝገብ ስር ይመዘገባል።

5. የካርታ መስጠት

የተረጋገጠ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ይሰጣል።

4. አስፈላጊ ህጋዊ መርሆች

* መሬት የግል ንብረት አይደለም

*  የሚሰጠው የመጠቀም መብት (use right) ነው

*  ካርታ በመዝገብ ካልተመዘገበ ሙሉ ህጋዊ ኃይል አይኖረውም

*  ማጭበርበር ወይም የሐሰት ካርታ የወንጀል ተግባር ነው

5. የተለመዱ ክርክሮች

.ድንበር ክርክር

.የሊዝ ጊዜ መጨረሻ

.የካርታ መቀየር

.የሕጋዊ ውርስ

ክርክር ቢኖር በመጀመሪያ በአስተዳደር ደረጃ ይታያል፤ ከዚያ ወደ ፍርድ ቤት ሊደርስ ይችላል።

.ህጋዊ መሠረት ህገ-መንግስት + የሊዝ አዋጅ
.የሰነድ አሰጣጥ ምዝገባ + መለኪያ + ማረጋገጫ ናቸው።
     ━━━━━━━━━━━━━━
​📌 ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን እና የሳምንቱን የኮንስትራክሽን ዜናዎች ለማግኘት ​የፌስቡክ ገፃችን ይጎብኙ👇

https://www.facebook.com/profile.php?id=61592085774934

@etconp
❤9🥰1
📚ምርጥ የ አፓርታማ ዲዛይን eBook መፅሃፍ ከፈለጉ ከታች ባለዉ ሊንክ ያውርዱ👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a685bb89bd08_etconp
🔥3❤1👏1
​🇨🇳ቻይና ግዙፍ የንፋስ ተርባይኖችን በቀላሉ ለመገንባት የሚያስችለውን አዲስ "ራሱን አራማጅ ክሬን" (Self-Climbing Crane) ቴክኖሎጂ እያራመደች ነው!

​ቻይና እጅግ ግዙፍ የንፋስ ተርባይኖችን በትልልቅ ከፍታዎች ላይ ለመግጠም የሚያስችል አዲስ ትውልድ የራሱን አራማጅ ክሬን (Self-climbing crane) ቴክኖሎጂ እያራመደች ይገኛል።

• ​የአሰራር ዘዴው፦ ይህ ስርአት የሃይድሮሊክ መካኒኮችን እና ሀይለኛ ክላምፖችን (Clamps) በመጠቀም ግንባታው ወደ ላይ ሲገፋ ከተርባይኑ ታወር ጋር እየተጣበቀ ደረጃ በደረጃ ወደ ላይ እንዲወጣ ያስችለዋል።

• ​ጠቀሜታው፦ ይህ የፈጠራ አካሄድ እጅግ ግዙፍ እና ግዙፍ ባህላዊ ክሬኖችን ፍላጎት በእጅጉ ይቀንሰዋል፤ እንዲሁም ረዣዥም የንፋስ ተርባይኖችን መግጠም የበለጠ ተግባራዊ እና ቀላል እንዲሆን ያደርገዋል።

• ​የወደፊት አቅጣጫ፦ የንፋስ ተርባይኖች እየተበራከቱ እና ቁመታቸውም እየጨመረ በሄደ ቁጥር እንደዚህ ያሉ ቴክኖሎጂዎች ለወደፊት የታደሱ የኢነርጂ (Renewable Energy) ፕሮጀክቶች ትልቅ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ።

​​🌐ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
❤8👏4🔥1
​📈የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች ዋጋ ግሽበት እና ዘላቂ የመፍትሔ አቅጣጫዎች

​በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚስተዋለው የሲሚንቶ፣ የብረት እና ሌሎች የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ መናር የፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ከፍተኛ ፈተና ውስጥ ከቶታል።

ግንባታዎች በታቀደላቸው ጊዜ እና በጀት እንዲጠናቀቁ ከዚህ በታች ያሉትን ነጥቦች መተግበር ተገቢ ነው።

​⚠️ 3ቱ ዋና ዋና ተጽዕኖዎች እና የመፍትሔ ምሰሶዎች

▪️​የግብዓት አቅርቦት እጥረት

በሲሚንቶ እና በብረት ምርቶች ላይ የሚታዩ ለዉጦች እና የዴፖ ክፍተቶች ፕሮጀክቶች እንዲዘገዩ ምክንያት ስለሚሆኑ፣ አገር በቀል አምራቾች አቅማቸውን ሙሉ በሙሉ እንዲጠቀሙ ድጋፍ ማድረግ።

▪️​ዘመናዊ የቁጠባ እና አማራጭ ቴክኖሎጂዎች

በባህላዊ የግንባታ υቃዎች ምትክ በአገር ውስጥ የሚገኙ አማራጭ የግንባታ ማቴሪያሎችን (ለምሳሌ ፕሪካስት ቴክኖሎጂዎችን) መጠቀም ወጪን በእጅጉ ይቀንሳል።

▪️​ውጤታማ የፕሮጀክት አስተዳደር

ኮንትራክተሮች እና ባለቤቶች የዋጋ ግሽበትን አስቀድሞ ያካተተ (Risk Management) የውል ማዕቀፍ በመዘርጋት ከወጪ ማሻቀብ ጋር የሚመጡ ኪሳራዎችን መቀነስ ይኖርባቸዋል።

​ማሳሰቢያ: የኮንስትራክሽን ሴክተሩ ሀገርን በመገንባት ሂደት ውስጥ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ የመንግስት እና የግል ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ትብብር ለኢንዱስትሪው ህልውና ወሳኝ ነው። "ጠንካራ መሰረት ለነገ ማህበረሰብ!"

Via Ethio Con

@etconp
❤4🔥1🥰1
👉ተቋራጭን ከሳይት ማባረር/Expel right/

ይህ መብት ያለው የትኛው አካል ነው? የሚለውን በተመለከተ ተቋራጭን ከግንባታ ሳይት/ከግንባታ ስፍራ ለማባረር መብት ያለው አሰሪው ነው፡፡

ስለዚህ መብቱ የግንባታው ባለቤት ወይም የአሰሪው ነው ስለዚህ ይህን መብት ተቋራጮች ሆኑ አሰሪ ያልሆነ ሌላ አካል ተግባራዊ ሊያደርገው አይችልም ማለት ነው፡፡

በየትኛው ህግ? ለሚለው ምላሹ በፍትሀብሄር ህጉ እና በጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት ነው፡፡በዝርዝር ሲታይ፡-

-በግንባታ ውሎች በተለይ ጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት መጠቀም የተለመደ ነው፡፡እነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች በራሳቸው ህግ አይደሉም፡፡
እዚህ ላይ አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች እንደ መመሪያ እና ህግ ስለሚቆጥሩት ይህ የግንዛቤ ክፍተት መታረም ይኖርበታል፡፡የግንባታ ውል ተዋዋዮች በስምምነታቸው እነዚህን ጀኔራል ኮንዲሽኖች የውሉ አካል ሲያደርጓቸው በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731 መሰረት በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ፡፡
እዚህ ላይ ሌላው ጉዳይ ስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ተብለው የሚቀመጡት ከጀኔራል ኮንዲሽኑ ድንጋጌዎች የተፈጻሚነት ቅድሚያ ይኖራቸዋል፡፡

ለምሳሌ ከነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ውስጥ የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/Standard condition of contract for the construction of civil work projects/ አንዱ ነው፡፡
ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን በከተማ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀ ሲሆን ይዘቱ በዋናነት ከFIDIC 1987 version የተወሰደ ነው፡፡
በአብዛኛው MoWUD 1994 ተብሎ ይጠራል፡፡
ሆኖም ዋናው ነጥብ ተዋዋዮች ጥቅም ላይ ያዋሉትና የውላቸው አካል ያደረጉት የትኛውን ጀኔራል ኮንዲሽን እንደሆነ መለየትና ማወቅ የግድ ይላል፡፡

-ከዚህ አንጻር MoWUD 1994 ክሎዝ 63 ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብትን አስመልክቶ በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡
በዚህ ድንጋጌ መሰረት በዋናነት አማካሪ መሀንዲሱ ለአሰሪው የተቋራጩን እንደውሉ ያለመፈጸም ሲያሳውቅ በተለይም ተቋራጩ ስራውን እንደተወው አማካሪው ሲያስታውቅ፣ተቋራጩ በአማካሪ መሀንዲሱ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ለ28ቀናት ስራውን ሳይጀምር ሲቀር፣በመሀንዲሱ ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ የግንባታ ቁሳቁሶችን በ28 ቀናት ውስጥ ከሳይት ያላስወጣ እንደሆነ፣በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ስራውን በውሉ አግባብ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ፣አማካሪ መሀንዲሱ እየከለከለው የስራውን ክፍል ለሌላ ተቋራጭ አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ወይም ተቋራጩ የከሰረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት ማባረር የሚችል ይሆናል፡፡

በዚህ ጊዜ ውሉ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡/Termination of contract/
-በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3288 አና ተከታዮቹ ላይ የተደነገገውም ተቋራጩ የውል ግዴታውን ባልፈጸመ ጊዜ የግንባታ ባለቤት ለሆነው ለአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ስራውን ከተቋራጩ ለመንጠቅ እና ውሉ ሳይቋረጥ ስራው በስራ መሪ ስር ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ መብት ይሰጠዋል፡፡እንዲሁም ውሉ ሊሰረዝ የሚችልበት ፈቃጅ የውል ቃል በግንባታ ውሉ ላይ ያለ እንደሆነ አሰሪው ቀሪውን ስራ ለሌላ ተቋራጭ በጨረታ ወይም በስምምነት በማሰራት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ይችላል፡፡/የፍ/ህ/ቁ 3291(1) በዚህም ምክንያት አሰሪው ለተጨማሪ ወጭ/Additional cost/ የተዳረገ እንደሆነ ከተቋራጩ ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 3291(2) በግልጽ መብት ይሰጠዋል፡፡
ሆኖም በውል ህግ ላይ አሰሪው የተቋራጩን ግዴታ በሚያከብድ ሁኔታ ቀሪውን ስራ ማከናወን እንደሌለበት የሚያስገነዝበውን ግዴታውንም ማክበር አለበት፡፡

በየትኛው የውል አይነት? ለሚለው በዋናነት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውሎችን በሚመለከት ሊተገበር የሚችል ነው፡፡
በግል የግንባታ ውሎች/private construction contract/ በተለይ ከፍ/ህ/ቁ 2610 እና ተከታዮቹ እንዲሁም ከፍ/ህ/ቁ 3019 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ውስጥ ተቋራጭን ስለማባበር አስመልክቶ ግልጽ ድንጋጌ አለመኖሩ ይህ መብት ለግለሰቦች ለመተግበር አስቸጋሪ የመሆኑን ሁኔታ ታሳቢ ተደርጐ በህግ አውጭው በማወቅ/ፐርፐዝሊ/ የተተወ ይመስላል፡፡ተዋዋዮች የግንባታ ውል ሲዋዋሉ ጀኔራል ኮንዲሽን ቢጠቀሙና በዚህም ስለተቋራጭ የማባረር መብት ድንጋጌ ቢኖረውስ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል?ይሄን እንዴት ይተገብረዋል የሚለው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ውሉ ግን ለተዋዋዮች ህግ ስለሚሆን በተቻለ መጠን ሊተገበር ይገባዋል የሚል እሳቤ አለኝ፡፡  

በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት? ለሚለው በዋናነት በ MoWUD 1994 ክሎዝ 63(2) ላይ እንደተቀመጠው በግንባታ ሳይት ላይ የተገኘ ቁሳቁስ በሙሉ በዝርዝር መመዝገብና ዋጋ ወጥቶለት መጠኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
በተቋራጩ የተሰራው ስራ መጠን/level of work done/ በትክክል መታወቅና በዝርዝር መመዝገብ አለበት፡፡ተቋራጩ ያለበት እዳ/ከወሰደው የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ ያልመለሰው ማለት ነው/ መታወቅ አለበት፡፡ለተቋራጩ የተከፈለው የስራ ክፍያ ሊታወቅ ይገባል፡፡
እነዚህን የሂሳብ ሁኔታዎች አመዛዝኖ እና ዋጋ አስቀምጦ ተቋራጩ የሚከፈለው ገንዘብ ካለ እንዲከፈለው ለአሰሪው የሚመልሰው ገንዘብ ካለም እንዲመልስ ሂሳብ የማስተሳሰብና ሪፖርት የማቅረብ ሀላፊነቱ የአማካሪ መሀንዲሱ ነው፡፡
በዚህ ረገድ አማካሪ መሀንዲሶች ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሪፖርት ስለማያቀርቡ የግንባታ ክርክሮች ያልተሸከፉ ይሆኑና ለፍርድ ቤቶች ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስቸገሪ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡

አሰሪው ይህን መብቱን ለመጠቀም ሀይል መጠቀም የሚችልበት ግልጽ ፈቃጅ ህግ ግን የለም፡፡

     ━━━━━━━━━━━━━━
​📌 ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን እና የሳምንቱን የኮንስትራክሽን ዜናዎች ለማግኘት ​የፌስቡክ ገፃችን ይጎብኙ👇

https://www.facebook.com/profile.php?id=61592085774934

@etconp
❤7🥰1
👉የኮንክሪት ስላብ ከተሞላ በኋላ Curing (ውኃ ማጠጣት) መቼ እና እንዴት መጀመር አለበት? 🏗️💧

በምስሉ ላይ እንደምታዩት፣ አዲስ የተሞላ የኮንክሪት ስላብ (Concrete Slab) ተገቢውን ጥንካሬ (Design Strength) እንዲያገኝ ውኃ ማጠጣት (Curing) ወሳኝ ደረጃ ነው።

💡 Curing መቼ መጀመር አለበት?

- የመጀመሪያው ደረጃ (Initial Curing)፦ ኮንክሪቱ መድረቅ እና ጠንካራ መሆን ሲጀምር — ማለትም ኮንክሪት ከተሞላ ከ6 እስከ 10 ሰዓታት በኋላ (Final Setting Time ላይ ሲደርስ) ወይም በሁለተኛው ቀን ጠዋት በቂ እርጥበት መስጠት መጀመር አለበት።

- የቆይታ ጊዜ (Duration)፦ የኮንክሪት ስላብ ቢያንስ ከ7 እስከ 14 ቀናት ተከታታይ ውኃ ማግኘት አለበት (Ordinary Portland Cement ከሆነ 7 ቀን፣ Rapid Hardening ወይም ሞቃታማ ቦታ ከሆነ እስከ 14 ቀን)።

💡 ውኃ የማጠጫ የተመደቡ ዘዴዎች፦

1️⃣ Ponding Method (ውኃ በግደብ መቋጠር)፦ በስላቡ ዙሪያ በጭቃ/በአሸዋ ግደብ በመስራት ውኃ እንዲቋጥር ማድረግ (ለስላብ በጣም ተመራጭ)።

2️⃣ Wet Covering (እርጥብ ጆንያ አልፎ አልፎ ማልበስ)፦ በጆንያ (Wet Gunny Bags) በመሸፈን አየር እንዳያደርቀው ማድረግ።

🚥Curing በሰዓቱ አለመጀመር የፕላስቲክ ሽሪንኬጅ ስንጥቅ (Plastic Shrinkage Cracks) እና የኮንክሪት ጥንካሬ መቀነስ ያስከትላል! 🤝

🌟የ ‎C-25 Concrete Cost Breakdown & Detailed Calculation ከነ Excel እና PDF Note ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a86960fc21e9_etconp
❤10🥰1
👉አስደሳች ዜና ለዚህ ቻናል ኮንትራክተሮች እና የማነኛውም ኮንስትራክሽን እና ኮንሰልታንት እንዲሁም የቢዝነስ ባለቤቶች

🌟ለድርጅታቹ እድገት እና ስራቹ በቀላሉ ማስተዳደር እንድትችሉ የሚያግዝ በ EXCEL የተገነባ ሲስተም ፋይል አዘጋጅተንላቹዋል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6aaa29dcad3b0_etconp
🙏3👏1
🛣️ Why Does a Road Need Different Layers?

⬇️A road is built in layers, and each layer has a specific purpose.

🗂Understanding these layers is essential for every civil engineer, contractor, and site professional.

🔹 Subgrade – The prepared natural soil that supports the entire pavement structure.
🔹 Sub-base – Provides additional support and helps improve drainage.
🔹 Base Course – A strong structural layer that distributes traffic loads.
🔹 Prime Coat – Helps bind the granular base with the asphalt layer.
🔹 Binder Course – Provides structural strength and supports the wearing surface.
🔹 Wearing Course – The top asphalt layer that directly receives traffic and provides a smooth riding surface.

📌 Remember:-The better the foundation, the longer the road can perform.

🌟Proper material selection, moisture control, layer thickness, and compaction are critical at every stage.

🏗️ Construction Knowledge | Practical Learning | Professional Growth

🚥ባሁን ዋጋ የተሰራ የመንገድ ስራ BOQ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6aa4f7a526f13_etconp
❤11🥰3
👉በመንገድ ግንባታ ላይ "Chainage (2+622)" ማለት ምን ማለት ነው? 🛣️

🔆​ብዙ ጊዜ በመንገድ ዳር መዋቅሮች (እንደ Pipe Culvert፣ Box Culvert እና Bridges) ላይ እንዲህ ያሉ ቁጥሮችን እንመለከታለን።

🚥በምስሉ ላይ የሚታየው "2+622" በምህንድስናው አለም ቼይኔጅ (Chainage / Stationing) ይባላል።

​💡 ትርጉሙ፦ይህ የፓይፕ ካልቨርት (Pipe Culvert) መዋቅር የመንገዱ መነሻ ነጥብ (Station 0+000) ከተባለው ቦታ 2 ኪሎሜትር ከ 622 ሜትር (2,622 ሜትር) ርቀት ላይ እንደሚገኝ ያሳያል።

🌟​የቼይኔጅ (Chainage) ዋና ጥቅሞች፦

1️⃣ ቦታን በቀላሉ ለመለየት (Location Identification)፦ በሳይት ላይ ያሉ መዋቅሮችን፣ ቁፋሮዎችን እና ጥገናዎችን በትክክል የት ቦታ ላይ እንደሆኑ ለመለየት።

2️⃣ ለቁጥጥር እና ለሪፖርት (Quality Control & Inspection)፦ ኢንጂነሮች እና ኢንስፔክተሮች ስራዎችን ለመቆጣጠር እና ለመመዝገብ።

3️⃣ የስራ መጠን ለመለካት (Payment & Quantity Estimation)፦ የተሰራውን ስራ ርቀት እና መጠን በትክክል ለመክፈልና ለመከታተል።

​ትክክለኛ ሰነድ እና መለኪያ — ለጥራት ያለው የመንገድ ስራ መሰረት ነው! 🤝

​📍 ለበለጠ የምህንድስና መረጃዎች ገጻችንን ይከተሉ።

​​🌐ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
❤12👍4
👉በማንኛውም የኮንስትራክሽን ሳይት ላይ፣ የአንድ ኮለም (column) ቱምቢው የተወሰነ ሲኖረው "5 ሚ.ሜ ብቻ እኮ ነው፤ ምንም አያመጣም በልስን ይስተካከላል" የሚለውን የተለመደ አባባል እንሰማለን።

ይህ የ "5 ሚ.ሜ ህግ" በብዙ ባለሙያዎች ዘንድ የተለመደ ነው። ነገር ግን ይህ 5 ሚ.ሜ ከየት መጣ? የህንፃ ኮዱስ በእርግጥ ምን ይላል? እስኪ አብረን እንየው....

በኮንስትራክሽን execution ወቅት በሳይት ላይ የሚፈጠሩ የአሰራር ጉድለቶችን (workmanship errors) ታሳቢ ለማድረግ፣ የEBCS code (EBCS EN 1992-1-1:2013) አንቀጽ 5.2 ለጂኦሜትሪክ መዛባት (geometric imperfection) በdesign stage ታሳቢ እንዲደረግ በግልፅ አስቀምጧል። እውነታው ሲመረመር የሳይቱ "5mm" ህግ የመጣው ከነዚህ የኮድ እሴቶች የመነጨ ነው::

🚥1. የቱምቢ ችግር (Verticality/Plumbness): ኮዱ አንቀጽ 5.2(5) ላይ መሰረታዊ የማጋደል መጠንን/inclination (1/200) በማለት ያስቀምጣል።
ይህ ማለት በየ 1 ሜትር ቁመት 5 ሚ.ሜ ማጋደል በdesign ወቅት ታሳቢ መደረግ አለበት ማለት ነው::
ለምሳሌ የተለመደውን 3 ሜትር ቁመት ያለው ኮለም ብንወስድ፣ Design ሲደረግ ታሳቢ የሚደረገው አጠቃላይ ማጋደል 15 ሚ.ሜ (3000/200) ነው።

በሳይት ላይ የምናገኘው "5mm" ከ 15mm ስለሚያንስ እጅግ በጣም ጥብቅ (Conservative) ሆኗል ማለት ነው so ተቀባይነት አለው ማለት ነው።

🚥2. የሊኛ ችግር (Horizontal Shifting/Eccentricity): ኮዱ አንቀጽ 5.2(7)(a) ላይ braced systems ላሉ ኮለሞች የኤክሴንትሪሲቲ መጠንን (Lo/400) በማለት ያስቀምጣል, lo ማለት የኮለሙ clear height ነው።
ለ 3 ሜትር (3000 ሚ.ሜ) ኮለም፣ የሚፈቀደው የHorizontal Shifting 7.5 ሚ.ሜ (3000/400) ነው።

እዚህም ጋር የሳይቱ የ 5 ሚ.ሜ ልማድ በdesign stage ከታሰበው የ 7.5 ሚ.ሜ ገደብ በታች በመሆኑ ስህተቱን በአስተማማኝ ሁኔታ (safely) ያስተናግደዋል።

እዚህ ጋር ልንገነዘበው የሚገባው ዋና ነጥብ፣ እነዚህ 1/200 እና Lo/400 አሃዞች የሳይት ላይ ስህተት መለኪያ ሳይሆኑ፣ ገና በዲዛይን ደረጃ (Design Stage) በስትራክቸራል መሃንዲሱ ስሌት ውስጥ የገቡ ታሳቢዎች መሆናቸውን እና ከቻልን zero error ካልቻልን ግን ለzero የቀረበ ሥራ እንድንሰራ ነው::

🗂መዛባቱ ትክክለኛውን የኮድ ገደብ (Actual Code Limits) ቢያልፍስ ምን ይፈጠራል??

🌟አንድ ኮለም ከላይ ከተጠቀሱት የኮድ ገደቦች ውጭ ሲያፈነግጥ፣ በኮለሙ ላይ የሚከተሉት ከባድ ስትራክቸራዊ ችግሮች ይፈጠራሉ እነሱንም እንደሚከተሉት አቀርብላችኋለሁ

🚥1. ያልታሰበ የጎንዮሽ ሞመንት መፈጠር (Unintended & Biaxial Bending): ኮለሙ ከሴንተር ላይኑ ሲያፈነግጥ ከላይ የሚመጣው ሸክም (axial load) በቀጥታ በኮሎሙ የክብደት ማዕከል (centroid) ላይ አያርፍም።
ይህ eccentricity በዲዛይን ወቅት ያልታሰበ ተጨማሪ ሞመንት (additional moment) በኮሎሙ ላይ ይፈጥራል(M=N*e)።
ኮሎሙ በሁለቱም አቅጣጫዎች (x እና y) ካጋደለ ደግሞ፣ ስትራክቸሩን ለበለጠ ጫና የሚያጋልጥ የሁለት አቅጣጫ ሞመንት (Biaxial Bending) ይፈጠራል ማለት ነው።

🚥2. የሁለተኛ ደረጃ እና የ P-Delta ተፅዕኖ (Second-Order & P-Delta Effects): መዛባቱ በጨመረ ቁጥር የኮሎሙ የጎንዮሽ ዝንበሌ (Deflection) ይጨምራል። ከላይ የሚያርፈው ሸክም በዚህ ያጋደለ ኮሎም ላይ ሲያርፍ፣ ሸክሙ እና Deflection ተባዝተው ተጨማሪ የሁለተኛ ደረጃ ሞመንት ይፈጥራሉ (P-Delta effect)።
ይህ ተፅዕኖ በተለይ ለቀጫጭን እና ረዣዥም ኮለሞች (slender columns) የኮሎሙን ሸክም የመሸከም አቅም በከፍተኛ ፍጥነት እንዲቀንስ ያደርገዋል።

🚥ሌላኛው የስትራክቸር መጎዳት እና የመሰበር አደጋ (Structural Distress & Failure): በመዛባቱ ምክንያት የተፈጠረው አጠቃላይ ሞመንት ኮለሙ design ከተደረገበት አቅም (design capacity) በላይ ሲሆን፣ በአንድ በኩል ያለው ኮንክሪት መሸርሸር እና መሰንጠቅ (concrete crushing/spalling) ይጀምራል።

▶️በሌላ በኩል ያለው ብረት (reinforcement) ከአቅም በላይ በመወጠር (yielding) ውሎ አድሮ ኮለሙ buckling failure ሊያጋጥመው ይችላል ማለት ነው።

▶️ይህን ከገደብ በላይ የሆነ መዛባት የሚያስከትለውን ከባድ የስትራክቸር አደጋ ከተረዳን "መቻቻል (tolerance) አለ" ብለን በስራችን ላይ ፈፅሞ መዘናጋት የለብንም።

⏺ይልቁንም በሳይት ላይ ስራዎችን ስንሰራም ሆነ ስናሰራ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና የጥራት ቁጥጥር በማድረግ፣ እንዲህ አይነት አደገኛ ሁኔታዎች እንዳይፈጠሩ የቻልነውን ሁሉ ማድረግ የሁላችንም የሙያ ግዴታ መሆኑን ላስታውሳቺሁ እወዳለሁ።

🏛የQuantity Surveying እና Building Construction Estimation ከ ሀ አስከ ፐ ችሎታዎን በተግባራዊ ምሳሌዎች የሚያሳድጉበት ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8dd294cbaa9_etconp
❤12🙏8🔥2🥰1