Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.28K photos
359 videos
1.99K files
3.35K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ethics handout.docx
28.4 KB
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

▶️TODAY GREAT TIP @ETCONp
:
👉ዛሬ ደሞ አንድ First year engineering ተማሪዎች የተመረጡ የ engineering mechanics እና የengineering profession lecture notes ፖስት አረገናል
፡
🅾አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
Roman Aqueduct Vs Modern Aqueduct
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠ መግለጫ!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፀረ-ፕላጃሪዝም ፖሊሲ ከየካቲት 22 ጀምሮ ሊተገብር መሆኑን በይፋ እየገለጸ በፖሊሲው መሰረት ከዚህ በኋላ ማንኛውም መመረቂያ ጽሁፍ በ URKUND ሶፍትዌር አማካኝነት ተመርምሮ ከፕላጃሪዝም ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥ ዲግሪ እንደማይሰጥ ያሳውቃል፡፡

ፕላጃሪዝም አንድ የምረቃ ፅሁፍ የሚያዘጋጅ ወይም የምርምር ስራ የሚሰራ ሰው ሌሎች ሰዎች የሰሩትን ስራ የራሱ እንደሆነ አድርጎ በመውሰድ የአካዳሚክ እና የምርምር ሕግጋትን በመጣስ የሚፈፅመው ሕገወጥ ተግባር ነው፡፡

የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
Via Elias meseret
Types of window
👉በኮንስትራክሽን ውል አሰሪው የተቋራጩን ክፍያ አዘግይቶ መክፈል ጉዳይ /Delay payment/
------------- ---------------
▶️የኮንስትራክሽ ውል መሰረታዊ ባህሪው ሲታይ በዋናነት አሰሪና ተቋራጭን በተዋዋይነት የሚይዝ ሲሆን ጉልህ የሆነው ግዴታቸው ሲታይ ደግሞ ተቋራጩ በውሉና ዲዛይኑ/ስፔስፊኬሽኑ መሰረት ግንባታውን የማከናወን ሀላፊነት የሚኖርበት ሲሆን ክፍያ የመክፈል ጉዳይ ደግሞ ለአሰሪው ዋናውና ትልቁ ግዴታው ነው፡፡የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610፣3019እና 3020 እንዲሁም 3244 ተገናዝቦ ሲታይ ይሄን ሁኔታ ያስገነዝባል፡፡
*የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ "ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ስለሚፈጽሙት ስራዎችና ስለዋጋው ካልተስማሙ በቀር የተቋራጭነት ውል አለ አይባልም" በሚል የተደነገገው በኮንስትራክሽን ውል ለተቋራጩ የሚከፈለው ክፍያ ጉዳይ የውሉ መሰረታዊ ነጥብ መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ ስለክፍያ አይነቶች የህጉን ጉዳይ ወደፊት በሌላ ጽሁፍ የምናየው ይሆናል፡፡
*አሰሪው ለተቋራጩ ክፍያ የመክፈሉን ሁኔታ ያለበቂ ምክንያት ማዘግየት አይችልም፡፡
*አማካሪ መሀንዲሱ በተለይ ከተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ በቀረበለት ጊዜ የማረጋገጥና የማጽደቁን ስራ በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማጠናቀቅ ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(d)
*አሰሪው መስሪያ ቤት ደግሞ በአማካሪ መሀንዲሱ የጸደቀ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(e)
*አማካሪ መሀንዲሱ በተቋራጩ የቀረበውን የክፍያ ጥያቄ በሰባት ቀናት ውስጥ የማረጋገጥና የማጽደቅ ስራ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
*በዚህ ረገድ የመመሪያው አንቀጽ አንቀጽ 28.5(f) ግልጽ ምላሽ አስቀምጧል፡፡
*ይሄውም ተቋራጩ በዚህ ምክንያት ከአሰሪው ላይ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ የጠየቀ እንደሆነ አማካሪ መሀንዲሱ ይህን ተጨማሪ ክፍያ የመሸፈን ግዴታ ይኖርበታል፡፡
*ሆኖም ግን አማካሪ መሀንዲሱ ለሚሰጠው አገልግሎት ከሚከፈለው ክፍያ በላይ የሆነ ክፍያ ለመክፈል ሀላፊነት አይኖርበትም፡፡
*በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636 የአማካሪ መሀንዲሱን የእውቀት ስራ ውል ግዴታ ይደነግጋል፡፡ይሄውም አማካሪው "የኪነ ጥበብን ደንቦች በማፍረስ ጥፋት ጥፋት ካላደረገ በቀር በአሰሪው በኩል ስራ ተቋራጩን ሀላፊነት አይነካውም" በሚል ተቀምጧል፡፡(2636(2)) እንደዚሁም አማካሪው ሳይሰራ ከመቅረቱ የተነሳ ወይም በአሰሪው ላይ ጉዳትን የሚያመጣ ስራ ያደረገ እንደሆነ አጥፊ ነው ለመባል እንደሚችል የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636(3) ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ አማካሪው ክፍያ የማረጋገጥ እና የማጽደቅ ስራውን በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ባለማከናወኑ አሰሪው ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍል በተቋራጩ የተጠየቀ እንደሆነ አማካሪው አጥፊ ነው ሊባል ያስችለዋል ማለት ነው፡፡
*አሰሪው በአማካሪው የጸደቀው የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14 ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
*አሰሪው ያለበቂ ምክንያት ክፍያ ያዘገየ እንደሆነ ለተቋራጩ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ ለመክፈል ሀላፊነት እንደሚኖርበት የፌዴራል የግዥ መመሪያ/Federal public procurement directive/ አንቀጽ 28.5(g) ይደነግጋል፡፡
*ተጨማሪ ክፍያ ሲባልስ ምንን ያጠቃልላል? የሚለው ሲታይ በዋናነት ወለድ የመክፈል ሀላፊነትን የሚመለከት ይሆናል፡፡በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3268 ተቋራጩ መክፈልን በማዘግየት የሚታሰበውን ወለድ እንዲያገኝ መብት ይሰጠዋል፡፡የወለዱ መጠንም በውል ያልተወሰነ የሆነ እንደሆነ በአንቀጽ 1751 መሰረት ህጋዊ ወለድ በአመት 9(ዘጠኝ) በመቶ ሆኖ የሚሰላ ይሆናል፡፡
*ሌላው እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነጥብ ተዋዋዮች በውላቸው ላይ ክፍያን ማዘግየት የሚኖረውን ውጤት አስመልክቶ የቅጣት ስምምነት/penality clause/ ያካተቱ ከሆነ የፍትሀብሄር ህጉ አንቀጽ 1889 እና ተከታዮቹ ድንጋጌ እውቅና ስለሚሰጠው እና በአንቀጽ 1731 መሰረት ውል በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ስለሚቆጠር ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡
*አንዳንድ ክልሎችም በዚህ ረገድ በግዥ መመሪያቸው ላይ ዝርዝር ውጤቱን ያስቀምጣሉ፡፡
*አሰሪው ክፍያ በወቅቱ ባለመፈጸሙ ምክንያት ከወለድ ባለፈ ሌላም ጉዳት የደረሰበት ተቋራጭስ ከጉዳቱ ጋር እኩል የሆነ ኪሳራ ሊከፈለው አይገባም ወይ? የሚል ጥያቄም ሊነሳ ይችላል፡፡ምክንያቱም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2091 እና 1790(2) ለደረሰው ጉዳት ሀላፊ መሆኑ በህግ የታወቀ ሰው የሚከፍለው የጉዳት ካሳ ሀላፊነቱን ያመጣው ጉዳይ በተበዳዩ ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን አለበት በሚል በግልጽ ይደነግጋል፡፡
▶️በአጠቃላይ አሰሪው በማናቸውም ምክንያት የተቋራጩን ክፍያ በሚያዘገይበት ጊዜ ተቋራጩን ለውድቀት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው፡፡ምክንያቱም በሀገራችን አብዛኛው ተቋራጭ ድርጅት የፋይናንሽያል ማኔጅመንት ስርአት የለውም፡፡ተቋራጮቻችን የገንዘብ አቅማቸውም ደካማ ነው፡፡አብዛኛው ተቋራጭ ለአንዱ ፕሮጀክት የሚወስደውን የቅድሚያ ክፍያ ሌላ ፕሮጀክት ላይ ይጠቀምበታል፡፡በዚህ ምክንያት አንድ ተቋራጭ ሲከስር ብዙ ሰራተኛ እንደሚበተን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ስለዚህ በአሰሪዎች በኩል ተቋራጮች የሰሩበትን ክፍያ በወቅቱ እና በተሰራው ስራ ልክ አንዲከፈላቸው ለማድረግ እና በህጉ የተቀመጠው የክፍያ የጊዜ ገደብ እንዲከበር ጠንከር ያለ አቋም ወስዶ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
፡
https://t.me/COTMp
የአዲስ አበባ ከተማ ልዩ መገለጫ ይሆናል የተባለው የመሶብ ታወር ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ተነግሯል!

የመሶብ ታወር ሥራ አስኪያጅ አቶ ፀጋዬ ተክሉ እንደተናገሩት ከዓመት በፊት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ይፋ የተደረገው የመሶብ ቅርጽ ያለው ታወር ግንባታው ከመጪዎቹ አራት ወራት በኋላ ይጀመራል።

እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለጻ ፕሮጀክቱ ሁለት ሕንፃዎችን የሚያካትት ነው። የመጀመሪያው በመሶብ ቅርፅ የሚሠራው ባለ 70 ወለል ሕንፃ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሙዳይ ምስል ቅርፅ የሚሠራውና ባለ 20 ወለል ሕንፃ ነው።

ግንባታው በአዲስ አበባ በተለምዶ ሜክሲኮ በሚባለው አካባቢ በሚገኘውና ገነት ሆቴል ያለበት ሥፍራ ላይ የሚከናወን መሆኑን የገለፁት አቶ ፀጋዬ ከፕሮጀክቱ የግንባታ ወጪ ከ40 እስከ 49 በመቶ የሚሆነው የሚሸፈነው ከውጪ ሀገራት በሽርክና ሊሠሩ ከሚችሉ አካላት ሲሆን እስከ 51 በመቶ የሚደርሰው ወጪ ደግሞ በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ተሳትፎ የሚሸፈን መሆኑን አስታውቀዋል።

Via ኢ.ፕ.ድ
👉ነገ ሙሉ የ G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS እንዴት መስራት እንደምንችል ቲቶርያል ቪድዮ ከነ ሌክቸር ኖቱ ለመልቀቅ አስበናል፡፡
፡
👉ዝግጁ ናቹ ... አጋርነታቹ አሳዩን🙏🙏🙏
👉ትላንት ማታ ቃል በገባንላቹ መሠረት ሙሉ የ G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS እንዴት መስራት እንደምንችል ቲቶርያል ቪድዮ ከነ ሌክቸር ኖቱ ይሀውላቹ፡፡
፡
🅾አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
SIMON part 1 (1).rar
569.6 MB
👉G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS @ETCONp
SIMON part 1 (2).rar
330.1 MB
👉G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS @ETCONp
SIMON part 1 (3).rar
301 MB
👉G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS @ETCONp
SIMON part 1 (4).rar
30.5 MB
👉G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS @ETCONp
SIMON part 1 (5).rar
318.4 MB
👉G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS @ETCONp
SIMON part 1 (6).rar
398.6 MB
👉G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS @ETCONp
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
፡
👉ትላንት ማታ ቃል በገባንላቹ መሠረት ሙሉ የ G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS እንዴት መስራት እንደምንችል ቲቶርያል ቪድዮ ከነ ሌክቸር ኖቱ ይሀውላቹ፡፡
፡
🅾አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
👉Types of Joints in Construction @ETCONp
.
▶️Construction Joints
▶️Expansion Joints
▶️Contraction Joints
.
👉Construction Joints
*At first, we cannot pour a larger quantity of concrete in a
single time. So at that time, a certain portion has poured as
per the recommended shuttering design and the remaining
portion will be poured after a certain period.
In that, the construction joints are using to connect the old
and fresh concrete and it is also called as cold joints.
:
👉Expansion Joints
*As we discussed, the construction materials are formed by
the different raw material. The concrete may shrink or
expand due to the weather condition.
*So the expansion joints gap are provided to accommodate
the movement happening by the expansion or shrinkages
and it is avoiding the disfiguration of the structure.
*Mostly the expansion joint gaps are providing in large
structure & bridge girder to spread eventual stress. The joint
gaps are filled by the expansion material like fibre, bitumen
or some other special material.
*Expansion joint might be provided in mid of each
span in bridges.
*The provision of expansion joints is when the
structure length exceeding 45m.
*The reinforcements should not be provided on the
expansion joint area.
*The expansion joint material will be different based on
the structure.
*The expansion joints are provided as per IS 3414.
:
👉Contraction Joints
*It is another type of joints which controls the cracks
happening due to shrinkages. The contraction joints are
placed as a groove where the crack may form in concrete.
If the shrinkage crack is formed in the concrete slab then
the contraction joints prevent spreading on the other area.
*Specification The width of the groove should not be less than 5mm.
*The contraction joint depth is 1/4th of the Concrete mean depth.
*It should be placed in the weakest zone of the slab.
Another name of contraction joint is Control Joint .
.
http://t.me/COTMp
👉ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት @COTMp
.
⏩የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በሳይት የሚተገበር የፍተሻ አይነት ሲሆን የኮንክሪትን የመስራት አቅም (Workability) እና ፅኑእነት (Consistency) ለመለካት ይጠቅማል
.
➡ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በየእያንዳንዱ የኮንክሪት ሙሌት
ስራውስጥ መተግበር አለበት ። ስላምፕ ቴስት በትንሽ ወጪ
ምንተገብረው የኮንክሪትን Workability ምንመዝንበት ተመራጭ መፈተሻ ነው በዚህ ምክንያት ከ1922 GC ጀምሮ እስካሁን አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።
.
➡የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፉ ነገሮች
(Factors which influence the concrete slump test)
.
1- ለ ኮንክሪቱ እንደግብአት የተጠቀምናቸው እቃዎች
ባህርይ...ለምሳሌ ስነውህድ (ኬሚስትሪ) ቅጥነት ፣ የቁሱ
መጠን እና ስርጭት (particle size and distribution) ፣
እርጥበት ፣ የሲሚንቶ ግብአት እና እርጥበት የመያዝ አቅም.
.
2- የኬሚካል አድሚክስቸር መጠን አይነት መስተጋብር...
.
3- የኮንክሪቱ አየር የመያዝ አቅም
.
4- ኮንክሪት ማቀላቀያ ማጓጓዣ ቁስ እና ዘዴ
.
5- የኮንክሪቱ temperature
.
6- በኮንክሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውሃ መጠን
.
7- ኮንክሪቱ ለፍተሻ የተወሰደበት ግዜ
.
➡Slump test ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች
.
Slump ለመስራት የሚያገለግል መሃሉ ክፍት የሆነ ኮን (cone) መሰል ቅርፅ ማውጫ ይህ ቅርፅ ማውጫ 30cm ርዝመት 20 cm የታችኛው ዲያሜትር 10cm የላይኛው ዲያሜትር ያለው ነው (mold) መለኪያ ማስመሪያ
ከብረት የተሰራ 16 mm dia. እና 60 cm ርዝመት ያለው መጠቅጠቂያ ብረት ያስፈልጉናል።
.
➡ስላምፕ ቴስትን የመከወኛ ቅደም ተከተል
.
*step-1 መጀመርያ የቅርፅ ማውጫ ኮን (mold ) ንፁ
መሆን አረጋግጥ ኮንክሪቱ በቀላሉ ከሞልድ እንዲላቀቅ ቅርፅ
ማውጫውን ዘይት መቀባት አለበት
.
*step-2 ቅርፅ ማውጫውን (mold ) ትልቅ ዲያሜትር
ባለው ጫፍ በኩል ወንፊት ባልሆነ ስሃን ላይ አቁመው
.
*Step 3- የቅርፅ ማውጫ (mold) በእኩል 4 layer በኮንክሪት ሙሉት
.
*Step 4- እያንዳንዱን የኮንክሪት ላየር 25 ግዜ
በመጠቅጠቂያ ብረት ምቱት (ጠቅጥቁት) የአጠቃጠቅ
ጉልበታችሁ እኩል መሆን አለበት
.
*Step 5- ኮኑ (mold) ከሞላ በኋላ ትንሽ ዲያ ባለው
ጫፍ ላይ ያል ትርፍ ኮንክሪትን አስወግዱት ጫፉንም ለስኑት
.
*Step 6- ቅስ በማለት የኮንክሪት ቅርፅ ማውጫውን
(mold) ከኮንክሪቱ አለያዩት
.
*Step 7- ቀጥሎም ኮንክሪቱ ከቅርፅ ማውጫ (mold)
ያለውን የርዝመት ልዩነት ለኩት
.
.
Note - እዚጋ ማሳሰብ ምፈልገው ነገር ይህን ቴስት ስታደርጉ ቦታው ከእርግብግቢት (Vibration) የፀዳ መሆን አለበት ያልተረጋጋ ቦታ ላይ ማድረግ የቴስቱን ውጤት
ያበላሸዋል...ሳምፕሉ ከተወሰደ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ቴስቱን
መከወን አለብን
.
.
➡ከኮንክሪት ስላምፕ ቴስት የምናገኛቸው የውጤት አይነቶች
.
*True Slump - ይህ ከፍተሻው ምናገኘው ብቸኛው ልኬት
ነው ቅርፅ ማውጫው ከኮንክሪቱ ከተለያየ በኋላ ያለው የኮንክሪቱ
ቁመት ከቅርፅ ማውጫው በንፃሬ የምናገኘው ልዩነት (ምስሉን
ይመልከቱ)
.
*Zero Slump - ዜሮ ስላምፕ ኮንክሪቱ አነስተኛ የውሃ-
ሲሚንቶ ratio ያለው መሆኑን ያሳያል ዜሮ ስላምፕ ያለው ኮንክሪት ለመንገድ ግንባታ አገልግቶት ላይ ይውላል...
.
*Collapsed Slump - ይህ ደግሞ ከዜሮ ስላምፕ በተለየ
የኮንክሪቱን የውሃ ሲሚንቶ ውህድ Ratio ትልቅ መሆን ያሳያል
ይህ ማለት የኮንክሪቱ የእርጥበት መጠን ከፍተኛ መሆኑን እና
High workability mix ያሳየናል።
.
*Shear Slump- ይህ ደግሞ የፍተሻው ውጤት ሙሉ
እንዳልሆነ ይነግረናል።
.
ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
t.me/COTMp
👆👆👆👆👆
👉ስለ ብሎኬት @COTMp
.
⏩Hollow Concret Block (HCB) ወይም የግድግዳ ብሎኬት/Wall HCB/ በመባል ይታወቃል።
*የብሎኬት ምርት ሲደረግ ጠቀሜታው ለሁለት ጉዳይ ነው
1. ሸክም መቌቌም የሚችል/Load Bearing/
2. ሸክም መቌቌም የማይችል /Non-Load Bearing/
*ይሄንን መሰረት ያደረገም የደረጃ ክፍፍል/Class/ ይኖራቸዋል።
*ሸክም መቌቌም የሚችሉት ብሎኬቶች "ክላስ ኤ እና ቢ" /
Class A and B/ በመባል ሲመደቡ ሸክም መቌቌም
የማይችሉት የብሎኬቶች ደግሞ "ክላስ ሲ" /Class C/ በመባል
ይመደባሉ።
➡ብሎኬት በተለምዶ በመጠናቸው ባለ10፣ ባለ15 እና ባለ 20 በመባል ይለያሉ::
ርዝመት x ስፋት x ቁመት/ Length x width x depth/
ማለትም Standard Dimenssion
*40x20x20cm
*40x15x20cm
*40x10x20cm
➡እያንዳንዱ ብሎኬት ሸክም የመቌቌም አቅማቸው
በሜጋ ፓስካል(Mpa) ይለካል ከዚህ በላይ 👆 በምስል አስደግፈናል።
*Note:
1 kilogram per square centimetre = 0.0981 mega pascal

*Class A=3.8mpa
*Class B=3.2mpa
*Class C=1.8mpa
.
⚡ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።