Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
What’s the difference between Young’s modulus of elasticity and modulus of rigidity?

Discuss @cotmp

@etconp
👉Construction Notes
.
✍How do columns and beams work?

🚧Column is a structural functional part of a building that transfers the weight of the building received from the beam directly into the foundation.
📌Column fails by buckling.

🚧While Beam is also a structural functional part of a building that receives weight from the slab and transfer the weight directly to the column.
📌Beam fails majorly by deflection

#Constructionnotes

@etconp
👉በኮንስትራክሽን ውል ስለ ንኡስ ተቋራጭነት(sub-contract)
.
📌ንኡስ ተቋራጭነት(sub contract) በፍትሀብሄር ህጉ አገላለጽ ከዋናው ተቋራጭ የተስማማ ሁለተኛ ተቋራጭ ይባላል፡፡
*ይሄውም ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በከፊል ለማስፈጸም ከአንድ ሶስተኛ ወገን ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ውል ሁኔታ ነው፡፡
*ስለዚህ ንኡስ ተቋራጭነት የግንባታ ስራ ተቋራጮች ከአሰሪው ጋር ሊገነቡት ግዴታ የገቡበትን የግንባታ ስራ በከፊል ለሌላ ተቋራጭ በውል በሚያሰሩበት ጊዜ የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡
*(የፍ/ህ/ቁ 3201(2)) በንኡስ ተቋራጭነት ውል ውስጥ ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ተቋራጮች ናቸው፡፡
📌የንኡስ ተቋራጭነት አይነቶች ስንት ናቸው?
*ንኡስ ተቋራጭነት ሁለት አይነት ነው፡፡
🚧በአሰሪው የሚታወቅ(Nominated sub-contracting) እና በአሰሪው የማይታወቅ(Non nominated sub-contracting) ተብሎ ይከፈላል::
*ከውጤት አንጻር ተመሳሳይ ቢሆኑም ንኡስ ተቋራጭነቱን አሰሪው የፈቀደውና ያወቀው የሆነ እንደሆነ ጉልህ የሆነው ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ከመዘግየት ቅጣት ነጻ ይሆናል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3206)
📌ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩበት ክፍያ ከማን መጠየቅ ይችላሉ?
*ንኡስ ተቋራጮች በሁለት አማራጭ መንገድ ከፍያ ሊያገኙ የሚችሉበት የህግ አግባብ አለ፡፡*አንደኛው ከዋናው ተቋራጭ ላይ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከአሰሪው client/ ክፍያ የሚያገኙበት ሁኔታ ነው፡፡
**ይሄውም ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩት ስራ በውላቸው መሰረት ከዋናው ተቋራጭ ክፍያ የመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 1755፣1756) ምክንያቱም ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ህግ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ1731)
*በተጨማሪም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3040 በአንድ የህንጻ ስራ ተቋራጭነት ውስጥ የሚሰሩ ስራ ተቋራጮች ወይም ሰራተኞች የሰሩበትን ስራ ዋጋ ለመከፈል ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሰሪው ለስራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን ባሰሪው ላይ በቀጥታ ገንዘባቸውን ለመጠየቅ መብት አላቸው በሚል ይደነግጋል፡፡
*እንዲሁም በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3295 ላይ በግልጽ እንደተደነገገው በአስተዳደር መስሪያ ቤት የታወቀ ከዋናው ተቋራጭ ውስጥ ሁለተኛ ተቋራጭ የሆነ ሰው ላከናወነው የግንባታ ስራ ዋጋውን በቀጥታ ከአሰሪው መስሪያ ቤት/client/ ለመቀበል ይችላል፡፡
*ይሄውም የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎችን የሚመለከት ሲሆን ለቀጥታ ለአከፋፈሉ በቅድመ ሁኔታነትም ንኡስ ተቋራጩ የሚሰራው የስራ አይነትና ዋጋውም በንኡስ ተቋራጭነት ውሉ ላይ በግልጽ የተመለከተ እንደሆነ እና ዋናው ተቋራጭም በቀጥታ ከአሰሪው ስለሚከፈልበት ሁኔታ ፈቃዱን የሰጠበት እንደሆነ ነው፡፡
*ስለዚህ ንኡስ ተቋራጮች እንደዚህ በልዩ ሁኔታ ከዋናው አሰሪ ላይም በቀጥታ ክፍያ ለመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡
📌ሌላው በአስተዳደር መስሪያ ቤት የኮንስትራክሽን ውሎች ውስጥ ንኡስ ተቋራጮች በማናቸውም አኳኋን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ለመቀበል እንደማይችሉ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3296 ይደነግጋል፡፡
*ስለዚህ ንኡስ ተቋራጮች ኖምኔትድ ሰብኮንትራክተር ቢሆኑም እንኳ ቅድሚያ ክፍያ መጠየቅ አይችሉም ማለት ነው፡፡*ይህ ማለት ግን በንኡስ ተቋራጭነት ውላቸው ከተስማሙ ከዋናው ተቋራጭ ግን ቅድሚያ ክፍያ ለመውሰድ የሚከለክላቸው አይሆንም የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡

✍በ ጉባዔ አሰፋ

#ConstructionLaw

@etconp
Ethio Construction Engineering
What’s the difference between Young’s modulus of elasticity and modulus of rigidity? Discuss @cotmp @etconp
Main Difference – Modulus of Elasticity vs. Modulus of Rigidity

➪ The main difference between modulus of elasticity and modulus of rigidity is that the modulus of elasticity describes how a material gets deformed when a force is applied at right angles to a surface of an object, causing the material to elongate or shorten while the modulus of rigidity describes how a material gets deformed when a force is applied parallel to a surface of an object, causing one of the surfaces to become shifted with respect to another surface of the same object.

What is the Modulus of Elasticity ?

Modulus of elasticity (Young modulus) is a number that describes the ratio of stress to strain in an object that is being deformed by a force that is perpendicular to a surface of an object.

➪ σ =
F
A
➪ E =
σ
ε
➪ σ = E x ε

Where ; E = Young’s modulus of
elasticity
F = applied force
A = surface tension area
σ = stress
ε = strain (deformation per unit
length)

What is the Modulus of Rigidity ?

Modulus of rigidity (shear modulus) is a number that gives the Shear stress  acting on a material per unit area. The deforming force acts parallel to a face of the object, causing one face to become displaced with respect to another face.

➪ σ =
F
A
➪ G =
σ
ε
➪ σ = G x ε

Where ; G = Young’s modulus of
Rigidity
F = applied force
A = surface tension area
σ = stress
ε = strain (deformation per unit
length)

Relationship between Modulus of Elasticity and Modulus of Rigidity

➪ G =
E
2( 1+ν)

➪ E = 2G( 1+ν)

Where ; ν = possion’s ratio

Based on this we will have quiz

በዚህ መሰረት quiz ይኖረናል

@etconp
👉በአዲስ አበባ በህንጻ ግንባታ ሰራተኞች ላይ በደረሰ አደጋ ጉዳት ደረሰ!

🚧በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ እየተገነባ ባለ ህንጻ ላይ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 18፤ 2012 ጠዋት ላይ በደረሰ አደጋ አንድ ሰው ሲሞት በ9 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።
.
🚧በህንጻው ግንባታ ላይ የተሰማሩ 55 ሰራተኞችንም ጉዳት ሳይደረስባቸው በህይወት መትረፋቸውንም አስታውቋል። በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚገኘው ይህ ህንጻ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) መገንባት የጀመረ ሲሆን ግንባታው ሲገባደድ ኤጀንሲውን ጨምሮ የሰላም ሚኒስቴር እና ሌሎች ተቋማትን በውስጡ ይይዛል ተብሎ የሚጠበቅ ነው።
.
🚧ዛሬ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ተኩል ገደማ በህንጻው ላይ የደረሰው አደጋ መንስኤ በውጭ ግድግዳ ላይ የተለጠፉ የሴራሚክ ልባሶች መንሸራተት ያስከተለው እንደሆነ አንድ የነፍስ አድን ሰራተኛ ተናግረዋል።
የሴራሚክ ልባሶቹ፤ በግንባታ ሰራተኛ መወጣጫዎች (ስካፎሊዲንግ) ላይ በማረፋቸው የመደርመስ አደጋ መከሰቱን እና ጉዳት መድረሱን አክለዋል። በመወጣጫ መደርመስ አደጋው ጽኑ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰራተኞች መካከል አንድ ግለሰብ ሆስፒታል ሲደርስ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አንድ ባለሙያ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ዘጠኝ የግንባታ ሰራተኞች በሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙም አስረድተዋል።

Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

#FirstSafety

@etconp
👉የ ኮንስትራክሽን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) ምን ማለት ነው?
.
📌ውሎችን ለሌላ መልቀቅ (Assignment) ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በሙሉ እንዲፈጽምለት ለአንድ ሶስተኛ ወገን ለሆነ ሲያስተላልፍ ነው፡፡ (የፍ/ህ/ቁ 3201(1)) *ይሄውም ከንኡስ ተቋራጭነት ጋር ሁኔታው አንድ አይነት ሲሆን በዋናነት ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ለሌላ ተቋራጭ(ለንኡስ ተቋራጩ) የሚያሰራው ሙሉውን የግንባታ ስራ ነው፡፡

*በዚህ ውል ውስጥ ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ተቋራጮች ናቸው፡፡
**ለምሳሌ "ሀ" የተባለ ተቋራጭ "ለ" ከተባለ አሰሪ ጋር የኮንስትራክሽን ውል ገባ እንበል፡፡የግንባታ ስራው ደግሞ ትምህርት ቤት ቢሆን እና ሁለት ብሎክ መማሪያ ህንጻ እና አንድ ሽንት ቤት ግንባታ ቢሆን እንበል፡፡
እንግዲህ ዋናው ተቋራጭ "ሀ" ከግንባታ ስራው ውስጥ አንዱን ብሎክ መማሪያ ክፍል "ሐ" ለተባለ ተቋራጭ በውል ሰጥቶ ቢያስገነባው በ "ሀ" እና "ሐ" መካከል የሚደረገው ውል የንኡስ ተቋራጭነት ውል ይባላል ማለት ነው፡፡
*በሌላ በኩል ምናልባት ዋናው ተቋራጭ "ሀ" ሁሉንም ግንባታ ማለትም ሁለት ብሎክ መማሪያ ህንጻ እና አንድ ሽንት ቤት "መ" ለተባለ ተቋራጭ በውል ሰጥቶ ቢያስገነባው በዋናው ተቋራጭ "ሀ" እና "መ" በተባለው ተቋራጭ መካከል የተደረገው ውል በንኡስ ተቋራጭነት ሳይሆን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) በሚለው የህግ ክፍል የሚጠቃለል ይሆናል ማለት ነወ፡፡
.
📌ጀኔራል ኮንዲሽኖች ንኡስ ተቋራጭነትን በምን ሁኔታ ያስቀምጡታል?

🚧ፒፒኤ 2011 ስለ ንኡስ ተቋራጭነት አስመልክቶ በክሎስ 14 ላይ አስቀምጧል፡፡
*በዚህም የንኡስ ተቋራጭነት ውሉ በጽሁፍ መሆን እንዳለበት እና ይሄውም የቫሊዲቲ መስፈርት ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡
*ንኡስ ተቋራጮች በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ያልታወቁ( Non nominated) የሆኑ እንደሆነ ዋናው ተቋራጭ ሌሎች ንኡስ ተቋራጮችን የግንባታ ስራ ለማሰራት የአሰሪውን የጽሁፍ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል በሚል ያስቀምጣል፡፡
*የንኡስ ተቋራጭነት ውሉም ከዋናው ውል ጋር የተጣጣመ እና በዋናው ውል ጭምር የሚገዛ እንደሚሆን ክሎስ 14.3 ላይ ተቀምጧል፡፡
*ዋናው ተቋራጭ የአሰሪው መስሪያ ቤት ሳይፈቅድለት የንኡስ ተቋራጭነት ውል የገባ እንደሆነ አሰሪው ፎርማል ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልገው ውልን ማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 14.8 ያስቀምጣል፡፡
*ሌላው ንኡስ ተቋራጩ የግንባታ ስራ ለማከናወን ብቃት የሚያንሰው እንደሆነ አሰሪው መስሪያ ቤት ወይም መሀንዲሱ ዋናውን ተቋራጭ ሌላ ብቃት ያለው ንኡስ ተቋራጭ እንዲያመጣ ወይም ስራውን በራሱ እንዲያከናውን ሊጠይቀው እንደሚችል ክሎስ 14.9 ይገልጻል፡፡

🚧ፊዲክ ሬድ ቡክ 1999-በዚህ ጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ 4.4 ላይ ዋናው ተቋራጭ ሙሉውን የግንባታ ስራ ለንኡስ ተቋራጭ መስጠት እንደማይችል ተቀምጧል፡፡
*እንዲሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ላይ በሌላ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር ንኡስ ተቋራጩ በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ስሙ የተጠቀሰ በሆነ ጊዜ በንኡስ ተቋራጭነት ለማሰራት የመሀንዲሱን ፈቃድ መጠየቅ አይጠበቅበትም፡፡
*ሆኖም የታሰበው ንኡስ ተቋራጭ አዲስ እና በዋናው ውል ስሙ ያልተጠቀሰ የሆነ እንደሆነ በቅድሚያ የመሀንዲሱን ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ ይሆናል፡፡
*ዋናው ተቋራጭ ለመሀንዲሱ በተለይ ንኡስ ተቋራጩ የሚሰራውን የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን/ኮመንስመንት ዴት/ ተብሎ የታሰበውን ጊዜ ከ28 ቀን ባላነሰ ጊዜ ማስታወቅ ሲኖርበት ንኡስ ተቋራጩ በትክክል በሳይት ላይ ስራ የጀመረበትንም ቀን ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

🚧Nominated subcontractors በሚመለከት በክሎስ 5.1 ላይ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡
*በዚህም መሰረት ኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተር የሚባለው በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተር መሆኑ የተገለጸ እንደሆነ ወይም ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ንኡስ ተቋራጭ መርጦለት እንዲያሰራው ያዘዘው የሆነ እንደሆነ ነው፡፡
.
🚧ለኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተሩ ክፍያ የሚፈጸምለት በንኡስ ተቋራጭነት ውሉ አግባብ በመሀንዲሱ በሚሰጥ የክፍያ ሰርተፍኬት መሰረት ሲሆን ክፍያውን የሚፈጽመውም ዋናው ተቋራጭ ስለመሆኑ ክሎስ 5.3 ላይ ተቀምጧል፡፡

✍በ ጉባዔ አሰፋ

#ConstructionLaw

@etconp
👉Construction notes
.
🚧Why is concrete strong in compression?
.
📌Concrete is a heterogeneous material which is made up of cement (15–20%), Sand (25–30%), Coarse Aggregate (55–60%) and air (2–4%).
.
📌Compressive strength of concrete is based on the least of the compressive strength of cement-sand mixture, coarse aggregate, and the bond between C/S mixture and coarse aggregate.
.
📌Usually all three of these are comparable in compressive strength and none of them are particularity weak in compression hence, compressive strength of concrete is quite high as compared to its strength in tension.
.
📌Moreover given the fact that coarse aggregate occupies largest volume in concrete, its has the largest effect on the compressive strength of concrete. Usually coarse aggregate is the strongest of the three components in concrete, unless it is a high strength concrete (fc’>8,000 psi) in which case failure can occur due to shearing of coarse aggregates.

#Constructionnotes

@etconp
Ethio Construction Engineering
Main Difference – Modulus of Elasticity vs. Modulus of Rigidity ➪ The main difference between modulus of elasticity and modulus of rigidity is that the modulus of elasticity describes how a material gets deformed when a force is applied at right angles to…
Given the modulus of elasticity (E) and the poission’s ratio (ν), calculate the shear modulus of elasticity (G), where

E = 207 X 10⁹ N/m² (steel)
ν = 0.28 (steel)

1. 108 x 10⁸ N/m²
2. 80.8 X 10⁹ N/m² ....
3. 108 x 10⁹ N/m²
4. 80.8 x 10⁸ N/m²

You can use the formula from the previous post 👆🏾👆🏾

@etconp
Ethio Construction Engineering via @like
Given the modulus of elasticity (E) and the poission’s ratio (ν), calculate the shear modulus of elasticity (G), where E = 207 X 10⁹ N/m² (steel) ν = 0.28 (steel) 1. 108 x 10⁸ N/m² 2. 80.8 X 10⁹ N/m² .... 3. 108 x 10⁹ N/m² 4. 80.8 x 10⁸ N/m² You…
Given the modulus of elasticity (E) and the poission’s ratio (ν), calculate the shear modulus of elasticity (G), where

E = 207 X 10⁹ N/m² (steel) ν = 0.28 (steel)
Anonymous Quiz
19%
108 x 10⁸ N/m²
46%
80.8 X 10⁹ N/m²
26%
108 x 10⁹ N/m²
9%
80.8 x 10⁸ N/m²
👉የአዲስ አበባ አዳዲስ ገፅታዎች!
.
🙏ውብ ምሽት ተመኘን🙏
.
✋Addis Ababa Ethiopia ❤️

@etconp
Facade section

@etconp
👉Construction notes
.
🚧What is the different between the one way slab and two way slab?
.
📌One Way Slab
.
▶️one way slab is supported by beams on 2 sides of longer span (rectangular).
.
📌Two Way Slab
.
▶️Two way slab is supported by beams on 4 sides of both span(square).
.
📌One way slab

▶️In one way slab L/B>2 .here length is more than breadth
.
▶️In one way slab the Main reinforcement should be provided on one direction.
.
▶️The One way slab is supported by two parallel beams or walls.
.
▶️In one way slab the Main bars Dia should be not less than 12 mm.
.
▶️In one way slab the Distribution bars Dia should be not less than 8 mm.

📌Two way slab

▶️In two way slab L/B<2 .here length and breadth are almost equal.

▶️In two way slab the Main reinforcement should be provided on both direction.

▶️The two way slab is supported by four parallel beams or walls.

▶️Main bars Dia should be not less than 12 mm.

▶️Distribution bars Dia should be not less than 8 mm.

▶️Reinforcement of slab depends on size of room / slab.

#Constructionnotes

@etconp
👉የመንግስት ኮንስትራክሽን ግንባታ ስራዎችን ያለጨረታ ስለማከናወን
.
#የመንግስት የኮንስትራክሽን ስራዎችን ያለጨረታ ለመረጠው ተቋራጭ እየሰጡ የማሰራት ሂደት በሀገራችን በተግባር እየተለመደ መጥቷል፡፡ይሄውም በማህበረሰቡ ዘንድ ግርታን እየፈጠረ ይገኛል፡፡ስለሆነም በጉዳዩ ላይ የህግ ማእቀፉን በመዳሰስ በእርግጥ መንግስት ይሄን ለማድረግ ፈቃጅ ህግ አለው ወይ? የሚለውን ነጥብ በዚህ ጽሁፍ ምላሽ ለመስጠት ተሞክሯል፡፡
#የግንባታ አገልግሎት ግዥን ጨምሮ ለመንግስት ግዥ ተፈጻሚ የሚሆነው የፌዴራል የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001 ነው፡፡የዚህ አዋጅ የተፈጻሚነት ወሰን በአንቀጽ 3 ላይ እንደተቀመጠው አዋጁ በፌዴራል ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ለአዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብም ወጥቶ በስራ ላይ ውሏል፡፡ክልሎች የየራሳቸው የግዥ እና ንብረት አስተዳደር የህግ ማእቀፍ አላቸው፡፡በዚህ ጽሁፍ ግን የፌዴራሉን የህግ ማእቀፍ ብቻ የምንዳስስ ይሆናል፡፡
#በአዋጁ አንቀጽ 3(2) ላይ በብሄራዊ ደህንነት እና በሀገር መከላከያ ምክንያት ግዥ በተለየ ዘዴ ሊፈጸም እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡ሆኖም ለአፈጻጸሙ ዝርዝር መመሪያ እንደሚወጣለት ይገልጻል፡፡አዋጁ በመንግስት ለመንግስት ግዥ ላይም ተፈጻሚ እንደማይሆን ተደንግጓል፡፡ስለዚህ እነዚህን ልዩ ሁኔታዎች በሚመለከት አዋጁ ተፈጻሚ ስለማይሆን ግዥው አዋጁ ካስቀመጠው የግዥ ዘዴ ውጭ እንዴት መፈጸም እንደሚገባው ዝርዝር መመሪያ ካለ መፈተሽ አስፈላጊ ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ የኮንስትራክሽን ስራ ከብሄራዊ ደህንነት እና ከሀገር መከላከያ አንጻር ታይቶ በልዩ የግዥ ዘዴ እንዲፈጸም የሚያስገድድበት ሁኔታ አለ ወይ?ብሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
#ሌላው በአዋጁ አንቀጽ 6 ላይ አለማቀፍ ግዴታወችን በሚመለከት የተደነገገውን መመልከት ያስፈልጋል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 6(1) ላይ "ይህ አዋጅ የፌዴራል መንግስት ከአንድ ወይም ከአንድ በላይ ከሆኑ መንግስታት ወይም ከአለማቀፍ ድርጅቶች ጋር ባደረገው ወይም በሚያደርገው ስምምነት ወይም ከስምምነቱ ከመነጨ ግዴታ ጋር የማይጣጣም ከሆነ በስምምነቱ የተመለከተው ይጸናል፡፡" በሚል ተደንግጓል፡፡ስለዚህ በስምምነቱ እና በግዥ አዋጁ መካከል አለመጣጣም አለ ወይስ የለም የሚለውን መጀመሪያ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡በስምምነቱ እና በግዥ አዋጁ መካከል አለመጣጣም ከሌለ የግዥ አዋጁ ሙሉ በሙሉ መተግበር አለበት ማለት ነው፡፡
#በዚህ በአዋጁ አንቀጽ 6(1) ድንጋጌ መሰረት በተለይ አለማቀፍ አበዳሪ አካላት ወይም እርዳታ ሰጭ አካላት ከመንግስት ጋር በሚያደርጉት ስምምነት ምናልባት በአዋጁ ከተቀመጠው የግልጽ ጨረታ ውድድር ውጭ የግንባታ ስራው በፈለጉት ተቋራጭ እንዲሰራ ተስማምተው ከሆነ ስምምነቱ መከበር ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ለምሳሌ የቻይና ባንክ ለአንድ የግንባታ ፕሮጀክት የብድር ወይም እርዳታ ገንዘብ ለመስጠት ቢፈቅድ እና ግንባታው ግን በአንድ የቻይና ድርጅት ያለጨረታ እንዲከናወን ቅድመ ሁኔታ ቢያስቀምጥ፣የኢትዮጵያ መንግስት ያለው አማራጭ ወይ ብድርና እርዳታውን መተው አለበለዚያ ደግሞ ቅድመ ሁኔታውን ተቀብሎ የብድርና እርዳታውን ስምምነት መፈራረምና በስምምነቱ መሰረት መፈጸም ነው፡፡እንግዲህ መንግስት ቅድመ ሁኔታውን ተቀብሎ ስምምነት ከተፈራረመ በስምምነቱ መሰረት ለመፈጸም የግዥ አዋጁን መጣስ ግድ ስለሚሆንበት እንደዚህ አይነቱን ሁኔታ በህግ ማእቀፍ እውቅና ለመስጠት የአዋጁ አንቀጽ 6(1) ፈቃጅ ሆኖ ተደንግጓል ማለት ነው፡፡
#የአለማቀፍ ባይላተራል ኤይድ ኢንስቲትዩሽን በሚባሉት (ለምሳሌ እንደ USAID) ሁለት አይነት የግዥ ዘዴ ይኖራል፡፡አንደኛው እራሱ እርዳታ ሰጭው ጨረታውን አከናውኖ እርዳታ የሚሰጥበት አግባብ ይኖራል፡፡ሌላኛው ደግሞ በእርዳታ ተቀባዩ ሀገር ጨረታው የሚከናወንበት አግባብ ነው፡፡ሆኖም በዚህ በሁለተኛው ሂደት እርዳታ ተቀባዩ ሀገር መከተል የሚገባው የግዥ ፖሊሲ ይኖራል፡፡
#በመልቲላተራል ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩሽን(ለምሳሌ እንደ World bank) ባሉት ላይ የግዥ ሂደት በተበዳሪ ሀገራት የሚከናወን ይሆናል፡፡በዚህም ባንኩ የውል አካል አይሆንም፡፡የአበዳሪውን ባንክ የግዥ ፖሊሲ መከተል ግን የግድ ይሆናል፡፡በአብዛኛው የባንኩ የግዥ ፖሊሲ በብድር ስምምነት ውስጥ የሚቀመጥ ጋይድላይን ላይ ይካተታል፡፡ባንኩ የሱፐርቫይዘርነት አስተዋጽኦ ብቻ ይኖረዋል፡፡እንግዲህ ባንኩ የጨረታ ሂደቱን ካልተስማማበት ብድሩ ይሰረዛል ማለት ነው፡፡በመሰረቱ በአለም ባንክ ፕሮክዩርመንት ሪጉሌሽን ላይ አለማቀፍ የጨረታ ውድድር(international competitive bidding) መርህ ነው፡፡ሆኖም ውስን ፋይዳ(minor value) ላላቸው ግዥዎች የሀገር ውስጥ የጨረታ ውድድር(local compitative bidding) የሚፈቀድበት አግባብ ይኖራል፡፡ሌላው የወርልድ ባንክ ፕሮክዩርመንት ሪጉሌሽን የዶመስቲክ ሩል የበላይ ይሆናል የሚለው መርህ ነው፡፡ይሄውም በግዥ አዋጅ አንቀጽ 6(2) ጭምር እውቅና ተሰጥቶታል፡፡
#እንግዲህ የአለማቀፍ ባይላተራል ኤይድ ኢንስቲትዩሽን ሆነ መልቲላተራል ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩሽን የሚተገብሩት የግዥ ዘዴ ከላይ እንደተመለከተው የጨረታ ውድድርን የሚጋብዝ ነው፡፡
#በተጨማሪም ልዩ ግዥን በተመለከተ በአዋጁ አንቀጽ 60 ላይ አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ከፍተኛ ግዥዎች የሚፈጽም አካል ሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ እንደሚቋቋም ተደንግጓል፡፡በዚህ በሚቋቋመው አካል የሚፈጸሙ የግዥ አይነቶችም በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚንስትር የሚወሰኑ ይሆናል፡፡እንግዲህ የኮንስትራክሽን ስራ አገልግሎት ግዥ በልዩ ግዥ የሚካተት ይሆናል ወይ? በሚል መጠየቅ ይቻላል፡፡ምላሹን ለማግኘት ደግሞ ልዩ ግዥ ፈጻሚ አካል ተቋቁሟል ወይ? በልዩ ግዥ የሚፈጸሙ የግዥ አይነቶች ዝርዝር በሚኒስትሩ ተወስኗል ወይ?የሚለውን ማንሳት ይጠይቃል፡፡ልዩ ግዥ ቢሆንስ ያለጨረታ ውድድር ሊከናወን ይችላል ወይ?የሚለውም ሌላው በዝርዝር ምላሽ ማግኘት የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ልዩ ግዥን በተመለከተ በፌዴራል ፐብሊክ ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ አንቀጽ 26 ላይ በዝርዝር ተመልክቷል፡፡በእርግጥ የኮንስትራክሽን ስራን በቀጥታ ያለጨረታ በተቋራጭ የማሰራት ሁኔታ በዚህ የህግ ማእቀፍ ውስጥ የተፈቀደ ሆኖ ይካተታል የሚል እሳቤ የለኝም፡፡
#እንግዲህ በግዥ አዋጁ አንቀጽ 33(1) ላይ እንደተመለከተው በመንግስት ግዥ አፈጻጸም ስድስት አይነት የግዥ ዘዴዎች ሲኖሩ ይሄውም ግልጽ ጨረታ፣በመወዳደሪያ ሀሳብ መጠየቂያ የሚፈጸም ግዥ፣በሁለት ደረጃ ጨረታ የሚፈጸም ግዥ፣ውስን ጨረታ፣በዋጋ ማቅረቢያ የሚፈጸም ግዥ፣ እና ከአንድ አቅራቢ የሚፈጸም ግዥ ያካትታል፡፡
#በመርህ ደረጃ በአዋጁ አንቀጽ 33(2) ላይ እንደተቀመጠው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ማናቸውም ግዥ በግልጽ የጨረታ ዘዴ መፈጸም አለባቸው፡፡ሆኖም በአዋጁ በተፈቀዱ ልዩ ሁኔታዎች ከግልጽ ጨረታ ውጭ ግዥ መፈጸም ይቻላል፡፡
#ሌላው ሊነሳ የሚችለው ነጥብ በግዥ አዋጁ አንቀጽ 51(1)(ረ) ላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች "በጣም አስቸኳይ ከመሆኑ የተነሳ ከባድ ችግር የሚፈጥርና በመስሪያ ቤቱ ስራ አፈጻጸም ላይ ጉዳትን የሚያስከትል በመሆኑ ምክንያት በመስሪያ ቤቱ የበላይ ሀላፊ የተፈቀደ ግዥ" በሚመለከት ከአንድ አቅራቢ ግዥ ሊፈጽሙ እንደሚችሉየተደነገገው ነው፡፡ምናልባትም መንግስት በተግባር የግንባታ ስራዎችን ለተመረጠ ተቋራጭ ያለጨረታ የሚያሰራበት አግባብ ይህ ድንጋጌ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡👇
#ስለዚህ በሀገራችን የኮንስትራክሽን ስራዎች ያለጨረታ ለተቋራጭ የሚሰጡ በየትኛው ፈቃጅ ህግ ነው? የሚለው ሲታይ ምናልባት በአዋጁ አንቀጽ 3(2)፣6(1)፣60፣እና 51(1)(ረ) የተመለከቱት ጠባብ ሁኔታወች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ሆኖም በሀገራችን በመንግስት አስተዳደራዊ ውሳኔ እየተሰራበት ያለው ያለጨረታ ለተቋራጭ ሰጥቶ ግንባታ የማከናወን ሂደት በእርግጥ በእነዚህ ፈቃጅ የህግ ሁኔታዎች የተፈቀደና የታቀፈ ነው ወይ? የሚለው በተግባር ዝርዝር ፍተሻ ይጠይቃል፡፡
#በመጨረሻም በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3147 ላይ የመንግስት አስተዳደር መስሪያ ቤቶች ውል ለማድረግ አሸናፊውን ድርጅት በጨረታ ስነስርአት ሊመርጡ እንደሚችሉ ተቀምጧል፡፡ስለዚሁም በህጉ ላይ የጨረታ ስነስርአት እንዲፈጸም በተደነገገ ጊዜ ውሎች በጨረታ ካልተሰጡ ፈራሽ ናቸው በሚል በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3147(2) ላይ ተደንግጓል፡፡
#በአጠቃላይ የመንግስት ግንባታ ስራዎችን ያለጨረታ ለሚፈለገው ተቋራጭ መስጠት በህግ ረገድ ጠባብ ፈቃጅ ሁኔታዎች ያሉት ነው፡፡ስለዚህ ሲተገበርም በጠባቡ ሊሆን ይገባል::

በጉባኤ አሰፋ የተዘጋጀ

@etconp
👉Construction notes
.
📌Why should construction joints in concrete slabs have slip dowels through the joint from one slab into the adjacent?
.
▶️Concrete, like all other materials, expand when heated and contract when cooled.

▶️Dowels are provided between concrete pavement slabs to transfer load from one slab to the next when the wheel of the vehicle moves over the joint. If these dowels are firmly fixed in both the slabs, it will not allow slabs to contract or expand when weather turns cold or hot.
▶️This will cause temperature stresses to develop in the slabs and concrete adjacent to the joint will crack.
.
▶️To allow for expansion and contraction of both the slabs while maintaining load transfer mechanism, dowels are provided which are fixed at one end and able to slide or move into a groove on the other end, along with provision of expansion joint in the slab.

#Constructionnotes

@etconp
👉የ ዛሬ መወያያ አጀንዳችን
.
▶️የጉዳት ካሳ(LD) ለመቅጣት የስራ ተቋራጮች ክፍያ ካስገቡት ቀን ይጀምራል ወይስ ፋይናንስ ገብቶ ክፍያው እስከሚፈጸምበት ቀን?
*ለምሳሌ ሰኔ 30 የውሉ ጊዜ የሚጠናቀቅ ቢሆን ኮንትራክተሩ ሰኔ 28 ክፍያ አስገባ አማካሪው ጋ 13 ቀን ቆይቶ ክፍያው ጸድቆ ለባለቤት ቢላክ ፣ ከአማካሪው እስከ ተላከው ቀን ነው? ወይስ የመጨረሻ ክፍያውን በ25ኛው ቀን ከፋይናንስ ቢቀበል ከዚያች የመጨረሻዋ ቀን ድረስ እስካለችው ነው?
*Undelivered Service (LD) ኮንትራክተር ሲቀጣ በየተኛ የዘገዩ ቀናቶች ነው?

📩በመወያያ ግሩፓዎ ላይ ማለትም @COTMp ገብተው ሃሳብ ስጡበት እና ተወያይተን እንማማር።
What is "stucco" ?

▫On it's most basic form stucco is a mixture of portland cement , sand and lime
Ratios of these products vary depending upon application.
▫ Generally stucco is field mixed product , although concentrated versions are available.
▫Proportions are clearly spelled out in ASTM C926, Standard Specification for Application of Portland Cement-Based Plaster. Scratch coats are mixed at 1 part cement to 2-1/4 to 4 parts sand, brown coats are mixed at 1 part cement to 3 to 5 parts sand, and finish coats are 1 part cement to 1-1/2 to 3 parts sand.


#finishing #coat
@etconp
👉Construction Notes
.
📌when casting beam it is not recommended to stop the casting at the mid-span, why?
*Where are they supposed to stop? What about the column?
.
▶️The Construction Engineer says:-
.
📌I believe that you are asking why it is not good to stop the casting of a reinforced concrete beam at mid-span.
.
▶️It’s primarily because that would create a “joint” in the beam at the point that the casting was stopped and re-started. This is not a real joint, of course, but it’s a weakness that is incorporated into the beam.
.
▶️Also, mid-span is precisely where one would expect the maximum bending moment, for normal loading conditions. For example, a simply-supported beam of length L and distributed load W uniformly distributed over the entire beam (W = wL) has a maximum bending moment M = WL/8 and it occurs at the center of the span.
.
▶️If I were casting such a reinforced concrete beam, I would cast it at least as long as the distance between the supporting columns.

#Constructionnotes

@etconp
👍1
👉Which is heavier, cement or sand?
.
📌To answer this let us understand specific gravity , the specific gravity of a material gives us how much more or less dense the material is than water.
.
📌Water has a specific gravity of 1.000 (near 4°C). If a material is more dense than water, then its specific gravity is greater than 1.
If it is less dense than water, then the specific gravity is less than 1.

📌Specific gravity of sand is 2.6 - 2.7 and that of cement is 3.14 - 3.15
i.e. for the same volume occupied by cement and sand , cement is “3.15/2.8 = 1.16 times”heavier than sand.

#ConstructionNotes

@etconp