Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
🚧በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለሚሰማሩ ለውጭ አገር ዜጎች ሥራ ፈቃድ ለማውጣት የድጋፍ ደብዳቤ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለመወሰን መመሪያ ተዘጋጅቶ መጽደቁን የከተማና ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

@etconp
🚧ማሳሰቢያ

👉አንዳንዶቻችሁ የZoom App አጠቃቀሙን አስረዳን ብላችሁ በጠየቃችሁት መሠረት ከዚህ በታች ያሰፈርኩትን በመከተል እንድትረዱት። ጥያቄ ካላችሁ መጠየቅ አትርሱ።

@etconp

👇👇👇
👉በመጀመሪያ ከታች ያለው ሊንክ በመጠቀም zoom application ዳውንሎድ ያርጉ በመቀጠል ይመዝገቡ (register) user name and password.

⏺ከዛም ሎግ ኢን (login) ያርጉ በመጨረሻም ማክሰኞ እለት የምልከውን ሊንኩን በመጫን ሐሙስ ከምሽቱ 4:30 (15ደቂቃ ቀደም ብዬ እከፍታለሁ) ገብተው ተደላድለው ቁጭ ብለው ይከታተሉ።

🙏አመሰግናለሁ🙏

Download Center - Zoom
https://zoom.us/download
👐ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታቹ⁉️

🚧ዛሬ የቻናሉ አባል የሆነ ሰው ግዴታ ሚፈፅመው ተግባር ይኖራል እሱም ቻናሉን UNMUTE በማረግ ነው MUTE ያረጋቹ ሰዎች የቻናሉ የእይታ መጠን(view) ይቀንሳል እንዲሁም የ ምንለጥፋቸው ትምህርቶች አይደርሳቹም ስለዚህ MUTE የሆነባቹ ተከታዮቻችን ከታች ባለው UNMUTE በማረግ ይተባበሩን።

🔶Hello Guys How are you Please don't mute our channel it will affect the view of the channel and the posts will not reach to you!

@etconp
👍1
Conrete steel slab detail. Shear studs help the interaction between conrete slab and steel beams so that they work together. In cases where shear studs are not used, the load is transfered from the slab to the steel beams and higher capacity of the beam is required.

@etconp
Ethio Construction Engineering
🚧በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለሚሰማሩ ለውጭ አገር ዜጎች ሥራ ፈቃድ ለማውጣት የድጋፍ ደብዳቤ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለመወሰን መመሪያ ተዘጋጅቶ መጽደቁን የከተማና ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ @etconp
👉በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለሚሰማሩ ለውጭ አገር ዜጎች ሥራ ፈቃድ ለማውጣት የድጋፍ ደብዳቤ የሚሰጥበትን ሁኔታ የሚወሰን መመሪያ ቁጥር 29/2012 ጸደቀ::

🚧በከተማ ልማትና ኮንስትራክን ሚነስቴር የኮንስትራክሽን ዘርፍ ተወዳዳሪነት ማበልጸጊያ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱ ጀማል የመመርያው ዋና አላማ አስመልክተው እንደተናገሩት የውጭ ሀገር ዜጎችን ቀጥሮ በማሰራት በሂደትም እውቀትና ክህሎት ለተተኪ ኢትዮጵያዊያን በማስተላለፍ የቴክኖሎጅ ሽግግር እንዲፈጠር ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑ፤ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵዊያኖች የእውቀት እና የክህሎት ሽግግር እንዲያደርጉ፣ከዚህ በፊት በልማድ፣ እየተሰራ ያለውን የተዝረከረከ አሰራር በአሰረር በማረም ተገቢው ሰው ለተገቢው ስራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባበትና የስራ ስምሪት የሚያደርግበት ግልፅ አሰራር ለመዘርጋት ነው ብለዋል፡፡

🚧መመሪያው የኮንስትራክሽን ዘርፉን እንደ ምክንያት በመጠቀም የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎች በስፋት ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ከኮንስትራክሽን ሰራ ውጭ በሆኑ የስራ ዘርፎች የሚሰማሩ፣ በእንዲሁም መግባት የሌለበት ሰዎች ጨምር እየገቡ በተፈጠረውን የስራ እድል የመሻማት፣ ከዚህም ባሻገር የውጭ ምንዛሬ የማሸሽ ብሎም ለሙስና የተጋለጠ አሰራር በስፋት በመኖሩና የታሰበውን አለማ እያሳካ ባለመሆኑ በተደጋጋሚ የሚነሱ ቅሬታዎች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

🚧ይህን ችግር በዘለቄታዊነት ለመፍታት እንዲቻል ከባለድሻ አካላት መረጃ ማሰባሰብ ስራ በማከናወን፣ የተሰበሰበውን መረጃ በመተንተን ለመመሪያው ግብአት እንዲሆን በማድረግ ከባለድሻ አካላት ጋር በየደረጃው ውውይይት ከተደረገ በኃላ በሚመለከተው “በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለሚሰማሩ ለውጭ አገር ዜጎች ሥራ ፈቃድ ለማውጣት የድጋፍ ደብዳቤ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 29/2012” እንዲጸድቅ ተደርጓል ብለዋል፡፡

Via ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚነስቴር

@etconp
👉ይህ ህንፃ አዲስ አበባ ውስጥ ነው።

🚧ስለዚህ ህንፃ ያሎት ሀሳብ እና አስተያያት @COTMp Discussion ግሩፓቹ ላይ ፃፉልን።
.
➡️This Building Is in Addis Ababa If you Have any Comment On This Building Feel Free to write @COTMp

@etconp
👉ዛሬ ዕለተ ሰኞ ስለ ጨረታ እንወያይ...
.
1. ከሊስት ቢድ የተሻለ የጨረታ ዘዴ ምን አለ?

2.አማካሪዎች የጨረታ ዶክመንት ሲያዘጋጁ ኮፒ ፔስት ያደርጋሉ ይባላል?

3. አማካሪዎች የጨረታ ዶክመንት ሲያዘጋጁ በዲዛይን ያልተካተቱ ስራዎችን ይጨምራሉ።
*በዲዛይን ውስጥ ያለን ስራ ደሞ ይቀንሳሉ ይህ ደግሞ መንግስትና አሰሪ ተቋማትን ይጎዳል።
*እንደዚህ አይነት አሰራሮችን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?ተጠያቂ የምያደርጉ የህግ ማእቀፍ አለ? ካለስ ምን እርምጃ ተወሰደ ?
*የስራ ተቋራጮች በጨረታ ወቅት ዶክመንት አጣርተው ዋጋ ለመሙላት ምን ማድረግ አለባቸው? የስራ ተቋራጮች በዶክመንት ላይ ያሉ ችግሮችን ለይተው ጨረታን የማሰረዝ መብታቸው እስከ ምንድ ነው? *ብዙ ጊዜ ከጨረታ በሇላ ወደ ስራ ሲገቡ ችግሮችን ሲያነሱ ይታያል ።

4. በርካታ ኮንትራክተሮች ባሉበት ሀገር ውስን ጨረታ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለምን ይደረጋል ?
*በጨረታ ወቅት እንደ መስፈርት አመታዊ ተርን ኦቨር ከፍተኛ ነው ይህ ደሞ ተወዳዳሪዎችን ይቀንሳል! ይህ እንዴት ይሰራል ?

5.በጨረታ ወቅት ጨረታ ማፈን ምንድ ነው? ሚስጥር መጠበቅስ? የጥቅም ግጭት በጨረታ ወቅት እንዴት ይፈጠራል ?
.
✍ለመወያየት ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይፃፉልን👇
፡
http://t.me/COTMp
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
How to construct footing

Short video

Telegram:- @etconp
👉አዲስ አበባ የመጀመሪያውን የውሃ መውረጃ ማስተር ፕላን እየሰራች ነው!

🚧ለከተማዋ የሚሰራው የመጀመሪያው የውሃ መውረጃ (Drainage) ማስተር ፕላን በከተማዋ የሚታየውን የጎርፍ እክል በተቀናጀ እና ዘላቂ ሁኔታ ለመግታት ያስችላል ተብሏል፡፡

🚧የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሞገስ ጥበቡ ለካፒታል እንደተናገሩት ከተማዋ በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነውን ማስተር ፕላን እውን ለማድረግ የአለም ባንክ የ36 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

🚧የማስተር ፕላን ስራውንም ፓሌርሞ፣ ጣልያን መሰረቱን ያደረገው ሰሪንግ ኢንጂነሪያ ከኢትዮጵያ አጋሩ መታፈሪያ አማካሪ ኢንጂነሪንግ ጋር እያከናወነው ይገኛል፡፡

🚧የማስተር ፕላን ስራው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው የሚሉት የከተማው መንገዶች ባለስልጣን ኃላፊ፤ በተያዘው በጀት አመት ስራው ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡

🚧ማስተር ፕላኑ በቀዳሚነት የጎርፍ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችለንን አካሄድ ያመላክታል ያሉት አቶ ሞገስ ይህም የውሃ መውረጃዎችን በበቂ ሁኔታ ከማስተዳደር ባለፈ በጎርፍ አማካኝነት በመሰረተ ልማቶች ላይ እና በኢኮኖሚ ጥፋቶች ላይ የሚደርሱ ጫናዎችን ያስወግዳል ብለዋል፡፡

🚧በዋና ከተማዋ ቀላል የማይባሉ ቦታዎች ለጎርፍ ተጋላጭ ሆነዋል፡ ቀደም ሲል እያንዳንዱ መንገድ ዲዛይን ሲሰራ የውሃ መውረጃም ጥናት በተናጠል ይሰራ እንደነበር ይታወሳል በማስተር ፕላኑ ግን የሁሉም ዲዛይን ይቀናጃል ተብሏል፡፡

Via Capital

@etconp
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Ceramic tiling

@etconp
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያፈራውና አስደማሚ የግንባታ ሥራዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ቪዲዮዎችን የሚሠራው ‘THE B1M’ የዩቲዩብ ገጽ እ.ኤ.አ በ 2020 ከሚጠናቀቁ ግንባታዎች መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ከመጀመሪያዎቹ 20 ግዙፍ ግንባታዎች አንዱ እንደሆነ የሚያሳይ ዘገባ ሠርቷል!

🚧ዘገባው ለመመልከት ከዚህ ፅሁፍ አያይዘንላቹዋል።

📹23.4 MB USE WIFI

@etconp
👉What is a tension reinforced section and compression reinforced section

📸Refer The Below Two images to have a better visual understanding!

@etconp
🚧Tension reinforced section is when you have steel reinforcement (rebar) on the tension controlled region where the rebar is used to counteract the lack of tensile strength in concrete.

📌When reinforcement is only present in the tension zone, you have a singly reinforced beam.

@etconp
🚧rebar on the tension side only is not enough to resist the ultimate moment capacity of the beam, therefore, reinforcement in the compression region is needed.

📌When reinforcement is present in both zones (tension and compression), you have a doubly reinforced beam

@etconp
👉ስለ Professional ethics በ ኮንስትራክሽን ስራ ላይ
፡
▶️Professional ethics በጣም ወሳኝ ነገር ነዉ። ስራዎችን በሀላፊነት ስሜት መስራት ማለት ነዉ። ራስን ላለማራከስ ና ለራስ ክብር ከመስጠት ይነሳል። ሰዉ ምን ይለኛል ብቻ ሳይሆን የተሸከምነዉ ህሊና ቅለትና ክብደትም ማሳያ ጭምር ነዉ።
፡
▶️በርካታ መሀንድሶች Design ሲሰሩ ወተዉ ወርደዉ ሙያዉ እንደሚያዘዉ ትክክለኛ ዳታ በመሰብሰብ ከእንከኖች በተቻለ መጠን የፀዳ ሀገሪቷን ያላትን ዉስን ሀብት ከብክነት የሚጠብቅ ህ/ሰቡን ከመንገላታት የሚያድንና አሰሪ ተቋማትን ከህዝብ ወቀሳ የሚያተርፍ ራሱ ባለሙያዉን የሚያስመሰግን ብሎም ዘርፉን የሚያስከብር ስራ ይሰራሉ።
▶️በተቃራኒዉ ደግሞ ሳይሰሩ የደከማቸዉ አንዳንዴም ወደ ሳይት እንኳ ሳይሄዱ ቁጭ ብለዉ Data cook በማድረግ ሀገር የሚያወድሙ፣ የሙያ ብልግና የሚፈፅሙ የሙያዉ ጥላሸቶች አሉ።
▶️በመንግስት በኩል ከጥናትና ዲዛይን ጀምሮ እሰከ ተጠናቀቁ ግንባታዎች መልካም ያደረጉ ባለሙያዎችን ባግባቡ ለይቶ እዉቅና የመስጠት በዛዉ ልክ ደግሞ ያጠፉትን በይፋ መዉቀስና መቅጣት መጀመር መቻል አለበት።
፡
▶️በት/ት ተቋማት ዉስጥም የትምህርት አሰጣጥ ሁኔታዉን ማሻሻል የስፈልጋል። በስራ ላይ ስልጠና ክህሎትን ማሳደግ ያስፈልጋል። በየምህንድስና ዘርፉ የምርምርና የስልጠና ተቋም መክፈትና መስራት ያስፈልጋል።
፡
✉️ከሁሉ በፊት ግን ዉድ መሀንድሶች ካለንበት ዝቅጠት ለመዉጣት፣ ሀገራችንና ህዝባችን ከኛ የሚጠብቁትን ለመወጣት ሙያችን በሚያስገድደዉ ልክ ለመስራት ቆርጠን እንነሳ።

@etconp
Sileshi Stesema is inviting you to a scheduled Zoom Webinar.

Topic: BIM & Digital Transformation Webinar
"What is BIM"

Time: Aug 20, 2020 08:30 PM London.
ከምሽቱ ሰዓት ተኩል በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር

Join Zoom Meeting
https://us02web.zoom.us/j/86090203216?pwd=d3BSMlVLd2FDWVUweWJaZ2w5SnlNQT09

Meeting ID: 860 9020 3216
Passcode: 689342
One tap mobile

+442039017895,,86090203216#,,,,,,0#,,689342# United Kingdom
+441314601196,,86090203216#,,,,,,0#,,689342# United Kingdom

Dial by your location
+1 312 626 6799 US (Chicago)
+1 346 248 7799 US (Houston)
+1 669 900 6833 US (San Jose)
+1 929 205 6099 US (New York)
+1 253 215 8782 US (Tacoma)
+1 301 715 8592 US (Germantown)
Meeting ID: 860 9020 3216
Passcode: 689342
Find your local number: https://us02web.zoom.us/u/kX99f53R6

#BIM
@etconp
Methods adopted for purifying the public water supplies :-
i. screening
ii. plain sedimentation
iii. sedimentation aided with coagulation
iv. filtration
v. disinfection
vi. aeration
vii. softening
👉Screening: the removal bigger and visible objects, such as trees, branches, sticks, vegetations, fish, animal
life, etc. present in raw surface water source.
👉Plain sedimentation: the coarser suspended materials can be removed by letting the water settle in
sedimentation basins.
Chemical coagulation: the effectiveness of sedimentation may be increased by mixing with certain
chemicals with the water to form flocculent precipitate that carries the suspended particles to settle.
👉Filtration: the finer particles in suspension may then be removed by filtering the water through filters is
filtration.
👉Disinfection: The filtered water which may still contain pathogenic bacteria is then made bacteria-proof by
adding certain chemicals, such as chlorine; thus the process of killing of germs is termed as disinfection.
👉Aeration: for the safe of the resulting water that might not be attractive to the tongue of consumers.
Unpleasant taste and odour, and also oxygen deficiency can be removed by adding certain chemical
compounds, such as activated carbon or using ozone.
👉Softening: is addition of certain chemicals to bring the quality of water to the permissible limits of water
hardness
.
#waterengineering #watertreatment
@etconp
👉DESIGN PROCEDURES FOR A BUILDING FOUNDATION (STEP BY STEP)

1. DECIDE THE LOCATION OF COLUMNS & FOUNDATION AND TYPE OF LOADS ACTING ON THEM.(E.X DEAL LOAD,  LIVE LOAD OR WIND LOAD)

🚧On the building plan, the position of columns and load bearing walls should be marked, and any other induced loadings and bending moments.

🚧The loads should be classified into dead, imposed and wind loadings, giving the appropriate partial safety factors for these loads.

2. ESTIMATE ALLOWABLE BEARING PRESSURE OF SOIL USING GROUND INVESTIGATION REPORT.

🚧From a study of the site ground investigation (if available), the strength of the soil at various depths or strata below foundation level should be studied, to determine the safe bearing capacity at various levels.

🚧These values or presumed bearing values (from any standards or codes) in the absence of a site investigation are used to estimate the allowable bearing pressure.

3. DECIDE DEPTH OF FOUNDATION

🚧The invert level (underside) of the foundation is determined by either the minimum depth below ground level unaffected by temperature, moisture content variation or erosion this can be as low as 450 mm in granular soils but, depending on the site and ground conditions, can exceed 1 m or by the depth of basement, boiler house, service ducts or similar.

4. CALCULATE FOUNDATION AREA

🚧The foundation area required is determined from the characteristic (working) loads and estimated allowable pressure.

🚧This determines the preliminary design of the types or combination of types of foundation.

🚧The selection is usually based on economics, speed and buildability of construction.

5. DETERMINE VARIATION IN VERTICAL STRESSES

🚧The variation of vertical stress w.r.t depth is determined, to check for possible over-stressing of any underlying weak strata.

6. CALCULATE SETTLEMENT

🚧Settlement calculations should be carried out to check that the total and differential settlements are acceptable.

🚧If these are unacceptable then a revised allowable bearing pressure should be determined, and the foundation design amended to increase its area, or the foundations should be taken down to a deeper and stronger stratum.

7. COST CONTROL

🚧Before finalizing the choice of foundation type, the preliminary costing of alternative superstructure designs should be made, to determine the economics of increasing superstructure costs in order to reduce foundation costs.

8. CONSIDER TIME

🚧Alternative safe designs should be checked for economy, speed and simplicity of construction.

🚧Speed and economy can conflict in foundation construction an initial low cost solution may increase the construction period.

🚧Time is often of the essence for a client needing early return on capital investment.

🚧A fast-track programme for superstructure construction can be negated by slow foundation construction.

9. VARIATION IN GROUND CONDITION

🚧The design office should be prepared to amend the design, if excavation shows variation in ground conditions from those predicted from the site soil survey and investigation.

@etconp
❤2
👉የዓለማችን አምስቱ ውብ
ከተሞች

🚧በአሁኑ ወቀት በበርካታ የአለማችን በከተሞች ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

🚧እነዚህ ተግባራትም ከተሞችን ከብክለትና መሰል ችግሮች በመታደግ አረንጓዴ እና ጤናማ የሆኑ ከተሞችን ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ዋነኛ አላማ ያደረገ ነው፡፡

🚧እኛም በአረንጓዴ ልማት ስትራተጂ ውጤታማ ስራ የሰሩና ለሌሎች የአለማችን ከተሞች ተሞክሮ መሆን የቻሉ 5 ከተሞችን በደረጃ ልናስተዋውቃችሁ ወደናል::

📌በአለማችን የአረንጓዴ ልማት ዘርፍ ውጤታማ ስራ ከሰሩ ከተሞች መካከል በ5ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው በአሜሪካን ሀገር የምትገኘው ሳንፍራንሲስኮ ከተማ ናት ከተማዋ በዘርፉ ከሰራቻቸው ስራዎች መካከልም በሀገሪቱ ከሚገኙ ከተሞች በፅዳት፣ በአረንጓዴ ልማትና በኤሌትሪክ ሀይል የሚሰሩ የሀይል አማራጮችን በመጠቀም ተጠቃሽ ናቸው ይህም ጠንካራ ህግ ተፈፃሚ ከማድረግ ባሻገር ህብረተሰቡ ይህን ለመተግበር በአመለካከት የተለወጠ መሆኑ ነው ባጠቃላይ በከተማዋ 40 በመቶ የሚሆነው ክፍልም በአረንጓዴ ስፍራ የተሸፈነ ነው::

📌በአረንጓዴ ልማት ስትራተጂ በ4ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ በእስያ አህጉር የምትገኘው ሲንጋፖር ከተማ ናት ይህች ከተማ ሙሉ ለሙሉ በሚያስብል መልኩ መሰረታዊ የከተማ ልማት ጥያቄዎችን መፍታት የቻለች ከተማ ናት በከተሞቻቸው የሚሰሩ ስራዎች ለመጠበቅ ጠንካራ ህግ ከማርቀቅ ጎን ለጎን በአረንጓዴ ልማትና በአካባቢ ጥበቃ በተለይ ደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻን መልሶ አገልግሎት ላይ እንዲውል በማድረግ ረገድ ለሌሎች ከተሞች ተምሳሌት ሆነዋል፡፡
*በከተማዋ ወደ ሰላሳ የሚጠጉት አረንጓዴ የህዝብ ፓርኮችም ከተማዋ ለአረንጓዴ ልማት የሰጠችውን ትኩረት ማሳያዎች ሲሆኑ በከተማዋ ሰፋፊ ጥብቅ ደኖችም ይገኛሉ፡፡
*በቅርቡም ከተማዋ ተግባራዊ እድርጋ ውጤት ባስመዘገበችባቸው ስራዎች በዩኒስኮ የአለም ከተሞች ተምሳሌት በመሆን ያገኘችው ሽልማት ተጠቃሽ ነው፡፡

📌በ3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ የብራዚሏ ኩሪቲባ ከተማ ናት ይህች ከተማ ከአለማችን ከተሞች መካከል በአረንጓዴነቷ የሶስተኛ ደረጃን ይዛለች በከተማው ከሚወጣው ቆሻሻም 70 በሞቶውን ለመልሶ አገልግሎት ማዋል ችለዋል፡፡ *በርካታ ጥብቅ ደኖች በከተማዋ መኖራቸው እና ዘመናዊና ቀላል የአውቶብስ የትራንስፖርት ተግባራዊ ማድረጋቸው ከስኬቶቻቸው መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

📌በ2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ ደግሞ የፊንላዷ ሄልሲንኪ ናት ይህች ከተማ በአካባቢ ጥበቃና በ መሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ የሚታዩ ችግሮችን በአግባቡ በመቅረፍ ብሎም ለኪነ ህንፃ እና ሁለንተናዊ ለሆነ የከተማ ውበት ልዩ ትኩረት በመስጠት ውጤታማ ስራ ሰርተዋል በዚህም በአለማችን እጅግ በጣም ማራኪ ከሚባሉ ከተሞች ቀዳሚ ለመሆን ችለዋል ለዚህም እንደማሳያ የከተማዋ አብዛኛው ስፍራ በማራኪ አረንጉዴ ስፍራዎች ከመሸፈኑ ጎን ለጎን ከተማቸውን ማራኪ በሆነ የስነ ህንፃ ዲዛይን ዉብ ማድረግ በመቻላቸው ነው፡፡

📌በመጨረሻም በዘርፉ በ1ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ የዴንማርኳ ኮፐንሀገን ናት ይህች ከተማ ከአለማችን ከተሞች
በቀዳሚነት የካርቦን ልቀት በመቀነስ አረንጓዴ፣ ውብና ለኑሮ ተስማሚ ከተማ መቀለስ ችላለች፡፡ *በተጎናጸፉት ስኬትም በከተማ ልማት ዘርፍ አንከን አይወጣላቸውም እየተባሉ ይወደሳሉ፡፡
*ጥናቶች እንደሚጠቁሙትም ይህች ከተማ በአለማችንም እጅግ በጣም ደስተኛ ዜጎች ከሚኖሩባቸው ከተሞች መካከል በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ከተሞች ተርታ ተሰልፋለች፡፡

🚧እኛም ከነዚህ ከተሞች በርካታ ተሞክሮዎች መቅሰም ይኖርብናል እነዚህ ከተሞች ዛሬ የደረሱበት ስኬት ጠንካራ ህጎችን ማርቀቅና ተግባራዊ ማድረግ ወይም ደግሞ ከተሞቹ በመደቡት የገንዘብ አቅም እንዳይመስሎ በነዋሪዎቻቸው ዘንድ በአውንታዊና ቅን በሆነ አመለካከት የተቃኘ የአስተሳሰብ ልእልና መገንባት በመቻላቸው እንጂ፡፡

➡️በአረንጓዴ እና ዉብ ስፍራዎች የሚኖሩ ዜጎችም ደስተኛ ከመሆናቸውም ባሻገር አዳዲስ ሀሳቦችን በማፍለቅ የዜጎችን ህይወት መቀየር ይችላሉ፡፡

➡️በሀገራችን ከተሞችም በቅርቡ የተጀመሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች አሁን ባለው ተነሳሽነት ማስቀጠል ከቻልን በአለማችን ተጠቃሽ ከሆኑ አረንጓዴ እና ዉብ ከተሞች መካከል ከተሞቻችንን ለማስጠራት የሚያግደን ነገር አይኖርም።

🙏ቸር ይግጠመን።🙏

@etconp