Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.28K photos
359 videos
1.99K files
3.35K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
3D printing

@etconp
👉ይህ ከላይ የምትመለከቱት Seismic dampers በመባል ይጠራል ይህም በህንፃዎች ፣ድልድዮች እና በሌሎች ግንባታዎች ውስጥ ለሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያገለግል ነው::

🚧The Picture on The Above Is called Seismic dampers used in buildings, bridges or any other constructions to control earthquake induced vibrations on buildings.

@etconp
👉ታላቁ የ ህዳሴ ግድብ

🚧አሁን ላይ የሲቪል ሥራው 88 ነጥብ 8 በመቶ እንዲሁም የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራው 46 ነጥብ 5 በመቶ ደርሷል፡፡

🚧የኮርቻ ግድብ ሥራ ደግሞ 99 በመቶ መከናወኑን ጠቁመው በዩኒት ዘጠኝና አሥር የተርባይን ተከላ እየተካሄደ ነው፡፡

🚧በ2013 በጀት ዓመት የበጋ ወቅት ግድቡን ወደ 595 ሜትር ለማድረስ ይሰራል ተብሏል፡፡

🚧በ2013 የ11 ተርባይኖች ገጠማ እንደሚጠናቀቅና በክረምቱ ወቅት ደግሞ ግድቡ 13 ነጥብ 4 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንደሚይዝም ይጠበቃል፡፡

🚧እስካሁን ባለው ሂደት ለግድቡ 121 ነጥብ 8 የብር መውጣቱን ጠቁመው ግድቡን ለማጠናቅቅም የሚፈጀው አጠቃላይ ወጭ 160 ቢሊየን ብር ይሆናል።

@etconp
በቢም webinar ላይ ተሳታፊዎች ብዛት ያላችሁ ነበራችሁ። በምሽቱ ፕሮግራም ላይ ስለ ቢም (Building Information Modeling) ትንሽ ግንዛቤ ያገኛችሁ ይመስለኛል።

በዕለቱ Waiting Room ላቆይኋችሁ ይቅርታ እየጠየኩ ወደፊት ግን ምንም ሳትጠብቁ ቀጥታ እንድትገቡ ይደረጋል።

ይላችሁን አስተያየትም ማንኛውንም ጥያቄ በውስጥ መስመር ብትልኩልን።

በምሽት ፕሮግራም ላይ ያልተገኛችሁ ወይም በድጋሚ ማየት ለምትፈልጉ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ማየት ይቻላል።
https://youtu.be/i27WQLANMcE

ሐሙስ 3rd Sept. 2020 (ነሐሴ 28 ቀን 2012 ዓም) በተመሳሳይ ሰዓት ይቀጥላል።
#BIM
#DigitalTransformation
@etconp

እናመሰግናለን
ስለሺ ተሰማ
👉በኮንስትራክሽን ውል ስለ ግንባታ ስራ ርክክብ/Acceptance/

▶️በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክብ ያለ ሲሆን ይሄውም ግዚያዊ ርክክብ (provisional acceptance) እና የመጨረሻ ርክክብ(final acceptance) የሚያካትት ነው፡፡

▶️በዚህ ጽሁፍ በዋናነት በኮንስትራክሽን ውል ህግ እውቅና የተሰጣቸውን የርክክብ አይነቶች ምንነትና ተያያዥ ውጤታቸውን አስመልክቶ የህግ ድንጋጌዎችን እና አሁን ላይ በመንግስት ተቋማት እየተሰራበት ያለውን የፒፒኤ 2011 ጀኔራል ኮንዲሽን ድንጋጌዎችን ባካተተ ሁኔታ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡

🚧ግዚያዊ ርክክብ Provisional Acceptance/

⏺ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1) ይደነግጋል፡፡ *ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ የሚረከብበት ሂደት ነው ማለት ነው፡፡
*በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም የሚያረጋግጥ ነው፡፡
⏺ፒፒኤ 2011 ክሎስ 84.1 ላይ የስራ ምርመራ/verification and test/ በመሀንዲሱ ተቋራጭ ባለበት ሊደረግ እንደሚገባ በመርህ ደረጃ ተቀምጧል፡፡
*ሆኖም ግን ተቋራጩ ምርመራው ከሚካሄድበት እለት ከ30 ቀን በፊት በተገቢ ሁኔታ እንዲያውቀው ተደርጐ በምርመራው እለት ያልተገኘ እንደሆነ የስራ ምርመራው ተቋራጩ በሌለበት ሊካሄድ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡
⏺እንግዲህ መሀንዲሱ ስራውን ከመረመረ በኋላ ያላመነበትን የስራ ክፍል ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል፡፡
⏺በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን የሚረከበው ይሆናል ማለት ነው፡፡ስለዚሁም የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት ለተቋራጩ የሚሰጠው ይሆናል፡፡በመሰረቱ ተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንዲሰጠው መጠየቅ ያለበት ስራው ሊጠናቀቅ ይችላል ብሎ ከሚያስብበት ከ15 ቀን በፊት መሆን ይኖርበታል፡፡ከዚያም መሀንዲሱ ጥያቄው በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ የስራ ምርመራውን አጠናቆ ሰርተፍኬቱን መስጠት ወይም ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡መሀንዲሱ ሰርተፍኬቱን ሳይሰጥ ወይም ጥያቄውን ውድቅ ሳያደርግ 30 ቀኑ ያለፈ እንደሆነ ለተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንደተሰጠው ግምት እንደሚወሰድ ፒፒኤ ክሎስ 87 ያስቀምጣል፡፡
⏺ሌላው ተቋራጩ በስራው ላይ ያደረገው መሻሻል/መለወጥ ቢኖር እንኳ በዝምታ ግዜአዊ ርክክብ ከተደረገ መሻሻሉ ተቀባይነት እንዳገኘ የህግ ግምት እንደሚያስወስድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(2) ይደነግጋል፡፡እዚህ ላይ ተቋራጩ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት የመስራት ግዴታ ያለበት መሆኑ ይታዎቅ፡፡ ስለዚህ የህግ ግምቱ እሳቤ ተቋራጩ ከዲዛይኑ በመውጣት አሻሽሎ የሰራው ስራ ኖሮ በግዜአዊ ርክክብ ወቅት በዝምታ አሰሪው ካለፈው እንደተቀበለው ይቆጠራል ነው፡፡
⏺እንዲሁም ግዜአዊ ርክክብ መደረጉ የመድህንነት ጊዜው(warranty period) መጀመሩን እንደሚያመለክት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(3) ይደነግጋል።

🚧የመድህንነት ጊዜ(warranty period/Defects Liability period)

⏹የመድህንነት ጊዜ(warranty period) የሚባለው ከጊዜአዊ ርክክብ እስከ መጨረሻ ርክክብ ያለው ጊዜ ሲሆን አሰሪው ግንባታው በተቋራጩ በደህና ሁኔታ ስለመሰራቱ ለመመርመርና ለማረጋገጥ የሚያስችለው ጊዜ ነው፡፡የጊዜው ርዝማኔም በውላቸው ላይ የሚወሰን ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3277 ይደነግጋል፡፡ ሆኖም በውሉ ላይ የመድህንነት ጊዜው ርዝማኔ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ከጊዜአዊ ርክክብ ቀን ጀምሮ 365 ቀን ስለመሆኑ የፒፒኤ ክሎስ 88.7 ያስቀምጣል፡፡
⏹ተቋራጩ በዚሁ በመድህንነት ጊዜ በተለይ የተበላሹ ስራዎችን እንዲያድሳቸው በአሰሪው በታዘዘ ጊዜ የማስተካከል ግዴታ እንዳለበት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3278 ይደነግጋል፡፡ ለዚህም ለጥገና ወጭ ሲባል ከተቋራጩ ክፍያ ላይ ሪቴንሽን ገንዘብ(retention money or bond) 5% እየተቀነሰ በአሰሪው ይያዛል፡፡
⏹በመድህንነት ጊዜ ውስጥ የተለዩ ብልሽት ያለባቸው ስራዎችን እንዲያስተካክል ተቋራጩ ተጠይቆ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያላስተካከለ እንደሆነ አሰሪው የማስተካከያ ስራውን በተቋራጩ ወጭ በራሱ ወይም ሌላ ቀጥሮ ሊያሰራው ወይም ውሉን ሊያቋርጥ ስለመቻሉ ፒፒኤ ክሎስ 88.3 ለአሰሪው መብት ይሰጠዋል፡፡

🚧ከፊል ርክክብ/Partial Acceptance/
-በፒፒኤ ክሎስ 86 ላይ የግንባታ ስራው በከፊል እርክክብ የሚደረግበትንም አማራጭ ያስቀምጣል፡፡ይህ ማለት የተወሰነውን የስራ ክፍል(part of the work) ከአጠቃላይ ውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ በውል ላይ ከተቀመጠ ተቋራጩ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከአጠቃላይ የውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ ይገደዳል ማለት ነው፡፡በዚህም በአንድ ውል ውስጥ በተለያየ ጊዜ ጊዜአዊ ርክክብ ሊደረግ የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራል ማለት ነው።

🚧የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/
⏺የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/ በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት(definitively appropriate) ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡
⏺የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡ሆኖም ጊዜአዊ ርክክብ/ Provisional Acceptance/ በሚመለከት ግን በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት የሚያስገድድ ግልጽ ህግ የለም፡፡ስለዚህ ስራው ተጠናቆ አሰሪው ግንባታውን በእጁ ካስገባ ጊዜአዊ ርክክብ መደረጉን የሚያስገነዝብ ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ በጽሁፍ መደረጉ ይመከራል፡፡
⏺በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ ሀላፊነት አለበት፣መድህን ሆኖ ይቀጥላል፡፡በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ ለነበሩ ጉድለቶች(apparent defect) ግን ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡ሀላፊነቱ የሚመለከተው ግንባታው በውሉ የተመለከተውን የታለመለትን ጥቅም እንዳይሰጥ የሚያደርጉ ወይም አጠቃቀሙን በጣም ውድ የሚያደርጉና አክሳሪ የሚያደርጉ ጉድለቶችን ነው፡፡
⏺የመጨረሻ ርክክብ መደረጉ የተቋራጩን መሰረታዊ ግዴታ የሚያወርድለት ሲሆን ቀሪ ክፍያ ካለው እንዲከፈለው እና ዋስትና እንዲወርድለትና የዋስትና መያዣ ገንዘብ ካለም እንዲለቀቅለት ለተቋራጩ መብት የመስጠት ውጤት እንደሚኖረው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3281 ይደነግጋል፡፡
⏺ፒፒኤ ክሎስ 89 በተመሳሳይ ስለመጨረሻ ርክክብ የደነገገ ሲሆን የመጨረሻ ርክክብ ሰርተፍኬትም በመሀንዲሱ ለአሰሪውና ለተቋራጩ እንደሚሰጥ ያስቀምጣል፡፡

✍ጉባኤ አሰፋ ነበርኩኝ አመሰግናለሁ

#ConstructionLaw

@etconp
👉Building construction

🚧Principles of building planning

⏺1. Aspect : It is defined as the positioning of windows and doors in the external walls to take maximum advantage of natural gifts such as sunlight and wind or breeze.

⏺2. Prospect : Prospect means taking advantage of desirable views available from Windows, doors and balconies of features outside the building such as gardens, lake, sea, river etc.

⏺3. Orientation : Orientation means the placement of rooms with reference to the north direction.

⏺4. Privacy (Discuss @COTMp)

⏺5. Circulation : Circulation refers to movement from one place to other inside the building

⏺6. Grouping : This means planning room with same or similar functions together as a group.

⏺7. Roominess : A psychological feeling about bigness or smallness of space of a room is called roominess.

⏺8. Furniture requirements (Discuss @COTMp)

⏺9. Sanitation : Sanitation is concerned with light & ventilation. It includes proper planning for drainage arrangements.

⏺10. Elegance : It refers to the elevation of the building. The front elevation of the building must be aesthetically pleasing & elegant.

⏺11. Economy : Planning of building should be economical

⏺12. Access : The principle of access stresses the need for ease in moving from room to room.

⏺13. Architectural composition : This principle deals with the aesthetics or the beauty of the building. Architectural concepts such as unity, contrast, scale, proportion, mass composition are taken into account.

⏺14. Climate and it's affect : The climate of a place also affect the planning of a building.

#BuildingConstruction

@etconp
❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
The fixed support shown restricts translations or rotations in all directions. There are total of six support reactions in total.

Telegram:- @etconp
What is a dragline used for ?

1️⃣ for bulk excavation of loose souls

2️⃣ for digging trenches

3️⃣ for bulk excavation of clay

4️⃣ for demolishing buildings

#equipment

@etconp
Ethio Construction Engineering via @like
What is a dragline used for ? 1️⃣ for bulk excavation of loose souls 2️⃣ for digging trenches 3️⃣ for bulk excavation of clay 4️⃣ for demolishing buildings #equipment @etconp
👉Six main types of bridge

🚧1. Arch bridge counter load in its arch action An arch bridge is a bridge with abutments at each end shaped as a curved arch.

🚧2. truss bridge is a bridge whose load bearing superstructure is composed of a truss, a structure of connected elements usually forming triangular units.

🚧3. Beam bridges are the simplest structural forms for bridge spans supported by pier at each end. No moments are transferred throughout the support,

🚧4. suspension bridge is a type of bridge in which the deck is hung below suspension cables on vertical suspenders

🚧5. cable-stayed bridge has one or more towers (or pylons), from which cables support the bridge deck. A distinctive feature are the cables or stays, which run directly from the tower to the deck, normally forming a fan-like pattern or a series of parallel lines.

🚧6. cantilever bridge is a bridge built using cantilevers, structures that project horizontally into space, supported on only one end and join at the center.

#Bridge

@etconp
From table 5.8 of ES- EN 1992-1-2:2004
The REI marking identifies the fire-resistance rating of a structure. The REI marking consists of the following elements:

R = Load-bearing. The ability of a construction element to preserve its’ mechanical characteristics and the relevant load capacity during a normal fire.
E = Integrity. In other words, the structure’s ability to NOT allow the passage or production of gas or vapor to the area NOT exposed to the fire.
I = Thermal Insulation. To clarify, the ability of a structure to reduce within a temperature limit the transfer of heat to the unexposed (cold) side. The temperature limit is usually 140°C.

REI (followed by the number n, which indicates the classification). The constructive element must preserve for a determined amount of time n its’ mechanical resistance. @etconp
👉FACTORS AFFECT PROJECT MANAGER PERFORMANCE

🚧Cost Factors

*Increase in material *Inadequate labour
*Incorrect Planning Wrong *method of estimation *Financial control on site *Previous experience
*Lack of productivity standard
*Design changes
*Lack of coordination between designers &contractor
*High cost of machinery

🚧Time factors

*Delay due to material shortage Time taken to rectify
*defects Delay in payments
*Site preparation time
*Planned time
*Time to implement variation AInnovation and verage delay in claim

🚧Quality Factors

*Quality assessment system in organisation
*Conformance to specification Quality training
*Availability of experience persons
*Quality of equipments

🚧Productivity Factors

*Sequencing of work according to schedule
*Project complexity due to overlap
*Absenteeism rate throughout project
*Management-Labour Relationship

🚧Client Satisfaction

*Leadership skills
* Information coordination *Number of disputes
*Number of reworks

🚧Community Satisfaction Factors

*Quality of regular documents
*Neighbours and site *condition problems
*Compliance to regular documents
*Non compliance to regular documents

🚧Environment Factors

*Wastes in site
*Climatic conditions
*noise
*Air quality

🚧Health And Safety Factors

*Application of health safety factors on site
*Easiness to reach site *Accident rates
*Assurance rate

🚧Innovation and Learning Factors

*Coordination
*Learning from own experience
*Learning from others experience
*Training HR
*Reviews of failure and solve them.

@etconp
👉አዲስ አበባ የሚገኘው አደይ አበባ የ ስታዲየም ግንባታ ሂደት ይህንን ይመስላል።

🚧The picture on the Above is The Construction progress of the new Adey Abeba Stadium in Addis Abeba.

@etconp
🚧የጠ/ሚር ጽህፈት ቤት የእድሳት ስራ የሰራውና መሰረቱ ዱባይ የሆነው አሌክ (ALEC Engineering Contracting LLC) የተባለው ኩባንያ የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤትን በተመሳሳይ መልኩ ማደስ ጀምሯል።

🚧ለዚህም 1.8 ቢሊዮን ብር ወጪ ይደረጋል ሲል የዘገበው ፎርቹን ነው።

@etconp
👉What is bond stress of concrete?

🚧Bond stress is the result of the bonding between the concrete surface and the reinforcement steel. It varies depending upon the type of concrete and type of reinforcement used. If plane rounded steel is used as reinforcement then the bond stress will be less, if same concrete is used with HYSD steel as reinforcement then the bond stress is higher.
🚧In Simple terms it is like grip, more grip if surface is rough and less grip if surface is smooth and rounded.
🚧Bond stress is defined as the shear force per unit of Nominal surface area of a reinforcement bar acting parallel to the bar on the interface between the bars and surrounding concrete.
The bond between steel and concrete is mainly due to pure adhesive resistance, frictional resistance and mechanical resistance.
🚧The bond stress developed in concrete around the steel reinforcement is given by
➡️Design bond stress
🚧For deformed bars these values shall be increased 60%
🚧For bars in compression can be increased 25%
👉"በግንባታ ሂደት ውስጥ በአሰሪ ተቋማትና በስራ ተቋራጮች መካከል የኮንስትራክሽን አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ከፍርድ ቤት ውጭ የሆኑ መፍቻ መንገዶችን ተጠቅሞ ለችግሩ እልባት መስጠት አዋጭ መሆኑ ተገለፀ፡፡

🚧ይህ የተገለፀው የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለአመራሮችና ለምህንዲስና ባለሙያዎች ባዘጋጀው ስልጠና ላይ ነው፡፡

🚧ስልጠናውን በኔክሰስ ሆቴል የሰጡት የምህንድስና ውል ጉዳዮች የህግ አማካሪና ጠበቃ አቶ ዘውዱ ተፈራ እንደገለፁት በግንባታ ሂደት ውስጥ በአሰሪና በስራ ተቋራጭ መካከል አለመግባባት (Construction Dispute) ሲፈጠር በህግ የተሰጠ ስልጣን ካለ በድርድር፣ በሽምግልና ወይም በስምምነት መፍታት መቻል በፍርድ ቤት ሂደት የሚባክነውን ጊዜና ገንዘብን ያስቀራል፡፡"

#ConstructionDispute
#ConstructionLaw

@etconp
👉ሰላም ለ ሁላቹም በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ያለቹ የሞያ እና የቢዝነስ ማህበራት፣ የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበር፣የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር እና ሌሎች በመሆን በጋራ በከተማችን አዲስ አበባ የሚገነቡትን የእንጦጦ ፓርክ፣ሸገር ፓርክ እና አንድነት ፓርክ ለመጎብኘት በእቅድ ላይ እገኛለን።

🚧ስለዚህም መጎብኘት የምትፈልጉ ከታች ባስቀመጥንላቹ ሊንክ ገብታቹ ፎርሙን በመምላት እንድትመዘገብ ተጋብዛቹሃል።👇

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeR9Gvj6fAW5rEZFTTJQ_hBw-nKCRizQYccpHqlH7WLr9JyQg/viewform

@etconp
👉OFFICE OF THE BUILDING CONSTRUCTION PERFORMER COMMITTEE FOR DEBRE HAWI ST. YARED ANDENET MONASTERY

📌REQUEST FOR EXPRESSIONS OF INTEREST FOR MASTER PLANNING AND ARCHITECTURAL DESIGN PROJECT COMPLETION OF CHURCH AND CENTER FOR RELIGIOUS COMPLEX

1. The Office of the building construction performer committee for Debre Hawi St. Yared Andenet Monastery in collaboration with Association of Ethiopian Architects (AEA) invites all practicing Architects and Consulting Firms to participate in Architectural design competition for Master Planning and Architectural Design Project Competition of Church and Center for Religious Teaching Complex.

2. The Competition is a two-Stage Project Competition open for all Practicing Architects and consulting firms who are the member of AEA, through submittal of Expression of Interest (EOI)

3. Practicing Architects and consulting Firms will be shortlisted for competition’s participation based on their demonstration of response to this request.

4. Interested Practicing Architects and consulting Firms may obtain further information from Secretariat Office of the building construction performer committee for Debre Hawi St. Yared Andenet Monastery and inspect the EOI documents at the address given below at 7(a) from 9:00 A.M - 5:00 P.M (office hour).

5. A complete set of terms of reference (TOR) Documents in English can be purchased by interested Practicing Architects and consulting firms at the address below at 7(a) and upon submitting copies of their License and paying of a non-refundable fee of 500 Ethiopian Birr.
The method of payment will be Cash.

6. Request for EOI with relevant documents must be delivered to the address below at 7(b) at or before
5:30 P.M, September 07, 2020.Late entries are not accepted.

7. (a) Address documents will be issued from: Office of the building construction performer Committee for Debre Hawi St. Yared Andenet Monastery,Arada Sub-City,wereda -09, house no. 811 (Holy Trinty Cathedral Building, 3rd floor, Office No.05. Tel. 0902151111)

7. (b) Address bids will be delivered to: Office of the building construction performer Committee for Debre Hawi St. Yared Andenet Monastery,Arada Sub-City,wereda -09, house no. 811 (Holy Trinty Cathedral Building, 3rd floor, Office No.05, Mob+251902151111

8. Office of the building construction performer committee for Debre Hawi St. Yared Andenet Monastery reserves the right to accept or reject applications made pursuant to this request at its own discretion without assigning any reason thereof.

#Tender

@etconp
❤1
👉በህንድ ከባድ የህንጻ መደርመስ አደጋ ተከሰተ‼️

🚧አደጋዉ ትናንትና ከሰዓት የደረሰ ሲሆን በህንድ የፋይናንስ ከተማ ከሆነችዉ ሙምባይ አቅራቢያ ያጋጠመ ነዉ፡፡

🚧የተደረመሰዉ ህንጻ ባለ አምስት ወለል ሲሆን ማሃዳ በተባለዉ አዉራጃ ይገኛል፡፡

🚧በህንጻዉ ዉስጥ 200 ያህል ሰዎች እንደነበሩም ተነግሯል እስካሁን በተረጋገጠ መረጃ አንድ ግለሰብ ህይወቱ ሲያልፍ 30 ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል፡፡

🚧አደጋዉ እንዴት ሊያጋጥም እንደቻለ ማብራሪያ ባይሰጠውም በህንድ በተደጋጋሚ የህንጻ መደርመስ አደጋ እንደሚያጋጥም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

🚧በ 2017 ዓመት ምህረት ብቻ ብሄራዊ የወንጀል ቢሮ ባወጣዉ መረጃ መሰረት በህንድ 1,161 ህንጻዎች ተደርምሰዉ ከ1200 በላይ ሰዎችን ህይወት ነጥቋል፡፡

🚧ይህንኑ መሰል አደጋ በህንድ ዝናባማ ወቅት በሆነዉ ከሰኔ እስከ መስከረም ባሉት ወራት ያጋጥማል በተያዘዉ ዓመት ዝናብ ካስከተለዉ የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ በህንድ ከ800 በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

Via Dawit D

#FirstSafety

@etconp
👍1
👉Rahel Shawl, the Ethiopian Star Architect gave an interview to the daily "Addis Zemen" Enjoy it.

➡️‹‹ሕንፃዎችን ለመቶ ዓመት እንጂ ለአስርና ሃያ ዓመት ብለህ አትገነባም››- አርክቴክት ራሔል ሻውል አርክቴክት ራሔል ሻውል የተወለዱትና ያደጉት አዲስ አበባ ፒያሳ ነው። የአራዳ ልጅ ናቸው። ይሄ ትርጉም አለው ከሕብረተሰቡ ጋር ተግባብተህ ብዙ ነገር አውቀህ ታድጋለህ ከሕይወቴ አንዱ የምወደው አስተዳደጌን ነው ይላሉ በንጉሡ ጊዜ የፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት የጀነራል ሻውል ዘለቀ ልጅ ናቸው ደርግ አባታቸውን 8 ዓመት በእስር ቤት አቆይቷቸዋል አባታቸው በመታሰራቸው ምክንያት አምስቱንም ልጆች ያሳደጉት እናታቸው ናቸው የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ናዝሬት ስኩል ነው የተከታተሉት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕንፃ ኮሌጅ በመግባት በአርክቴክቸርና የከተማ ፕላኒንግ (አርበን ፕላኒንግ) ተመርቀዋል። በአርክቴክትነት( ኪነ ሕንፃ) የሥራ ዓለም ብዙ አሳልፈዋል የተለያዩ ዓለም አቀፍ አዋርዶች (ሽልማቶች) ተሸላሚም ናቸው በአርክቴክት ሙያ ለዓለም አቀፍ ሽልማት ሲቀርቡ አፍሪካን ወክለው የተመረጡ ሀገርን ያኮሩ ባለሙያ ናቸው።

ድሮ ኢትዮጵያ ብዙ ሴት አርክቴክቶች አልነበሯትም ትምህርት ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በነበሩበት ጊዜ ከ20 ወንዶች የአርክቴክት ተማሪዎች ሴት እሳቸው ብቻ ነበሩ ዛሬ ግን ብዙ የሴት አርክቴክቶች አሉን። በሀገራችን ስማቸው ጎልቶ የሚነሳ ታዋቂና ቀደምት የሴት አርክቴክት ናቸው በኢትዮጵያ አርክቴክት (ስነሕንፃ)፤ በሠሯቸው ሥራዎችና በዚህ ሙያ ያለውን የሴቶች ተሳትፎ፤ ከሙያው ጋር በተያያዘ ስላሉት ችግሮችና መፍትሔዎች ከአዲስ ዘመን ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለዛሬ ይዘን ቀርበናል።

አዲስ ዘመን፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ የመጀመሪያ ሥራዎትን የት ጀመሩ?

አርክቴክት ራሔል፡- የመጀመሪያ ሥራዬን ኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቸርች ኤንድ ቲዎሎጂ ኮሌጅ የሚባል የመጀመሪያ ፕሮጀክት ቢሮ ነበረ ወደአፍሪካ ሕብረት ሳር ቤት አካባቢ ያለ ነው ለሁለት ዓመት ተኩል እዚያ ነው የሠራሁት።

አዲስ ዘመን፡- ምን ምን ሥራዎችን ሠራችሁ ?

አርክቴክት ራሔል፡- ኮንሰፕት ዲዛይኑን (መነሻ ንድፉን) የቤተክርስትያኑንና ኮሌጁን የሠራው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያለን አስተማሪያችን ነበር ዲዛይን ዴቨሎፕመንት የሚባል አለ ድሮዊንጎችን እዚያው ደግሞ ፕሮጀክት ቢሮ ስለሆነ ዲዛይኑ እየተሠራ ግንባታውን ትቆጣጠራለህ ማለት ነው ሁለት ዓመት ተኩል እዚያ ላይ ስለ ሠራሁ ራሱን ያቻለ ትልቅ ትምህርት ሆነኝ በእኛ ጊዜ ትልቅ ፕሮጀክት ስለሆነ ዲዛይኑ በአዲስ አበባ ስታይል አርክቴክቸር በሚባል ነው የተሠራው የሕንፃው ዝርዝሩ፤ ውስጡ፤ ውጪው መሬቱን ዙሪያ አቀማመጡን አጥሩን ግንባታውን ሁሉንም ዲዛይን ሦስት ሆነን ነው የሠራነው አርክቴክቱ ማልከም ማግሬገር ይባላል ስኮትሽ ነው ቤተክርስትያኑ ቀጥሮን ከእሱ ጋር ነው የሠራ ነው ለእኔ ቀጥታ ከትምህርት ቤት ወጥቼ እዚያ መሥራቴ ትልቅ ዕድል ነበር ሙሉ በሙሉ ከዲዛይንና ኮንስትራክሽን ዝርዝር ከእዚያም ሱፕርቪዥን (ቁጥጥር) የሚለውን ነገር በጣም ነው የተማርኩበት።

አዲስ ዘመን፡- ቀጥለው በአርክቴክትነት የት ሠሩ ?

አርክቴክት ራሔል፡- ከዚህ ሥራ በኋላ የራሳችንን ቢሮ ከፈትን።

አዲስ ዘመን፤- ድርጅቱ ማን ይባላል ?

አርክቴክት ራሔል፡- ሦስት ሆነን ነበር የጀመርነው ከመጀመሪያው በኋላ ከመቀጠር ለምን የራሳችንን ሥራ አንሠራም ብለን ወሰንን እኔ ፣ ዮሴፍ በረደድና ሊያ ኤፍሬም ነበርን ትንሽ ቢሮ ይዘን ቪላዎች፤ ኤክስፓንሽኖች (ማስፋፋቶች)፤በዚህ ሥራዎችን ጀመርን የድርጅቱ ስም አባ አርክቴክት ይባላል 8 ዓመት ሠራን በ2014 (እኤአ) መስከረም ላይ ተለያየን ከዚያም የራሴን ቢሮ ራስ አርክቴክት በሚል ከፈትኩ ቢሮው ከተከፈተ መጪው መስከረም 16 ዓመት ይሆነዋል።

አዲስ ዘመን፡- ራስ አርክቴክት መጀመሪያ የት ሠራ?

አርክቴክት ራሔል፡- ከትንሹ ጀምረን 8 ዓመት አብረን ስንሠራ ብዙ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እየሠራን መጣን መጨረሻ ሽግግሩ ላይ ኔዘርላንድስ የሚባለው ፕሮጀክት ትልቅ ሥራ ስለነበር እኔ በኢትዮጵያ በኩል የፕሮጀክቱ ሊድ አርክቴክት(መሪ አርክቴክት) ነበርኩ ዳቾች ናቸው ዲዛይኑን የሠሩት በትብብር ነው የተሠራው።
አርክቴክቶች ገና ከውጭ ሲመጡ አባ አርክቴክት ሆኜ እተዋወቃቸዋለሁ ከዚያ በፊት ትላልቅ ፊስቱላ ሆስፒታሎችን በሙሉ እኛ ነን የሠራነው አዲስ አበባ አጉስታ ጋ ያለውን እሱ ፕሮጀክት ላይ ብዙ ዓመት ከዮሴፍ በረደድ ጋር አባ አርክቴክት ሆንን አብረን ሠርተናል ሦስተኛዋ ሊያ ኤፍሬም ሁለት ዓመት ብቻ ሠርታ አሜሪካ ገባች እኔና ዮሴፍ ነን የቀጠልነው።
በሕይወትህ ውስጥ የማእዘን ድንጋይ ተደርገው የሚወሰዱ ለውጦች ዕርምጃዎች አሉ በሙያህ የምታድግበት የመጀመሪያ የሠራነው ቤተክርስትያኑን ነው ከዚያ ፊስቱላ ሆስፒታሎቹን ሆስፒታሉ ፈንድ እየሰበሰበ ስለሆነ የምንሠራው እኛም በሙያው ብዙ አድገንብታል በክፍል በክፍል እየተደረገ ነው የተሠራው መካነ እየሱስ፤ቢንግሀም አካዳሚ ብዙ ሥራዎች ሠርተናል ከዮሴፍ በረደድ ጋር ከተለያየን በኋላ እኔም አንድ ሁለት ፕሮጀክቶች (አውት ሪቾች) ሀረር፤ መቀሌ ይሠራ ነበር እኔ ብቻዬን የሠራሁት መቱ ላይ ያለውን ነው ስንለያይ ቢሮ ስላለ እሱ ቀጠለ።

አዲስ ዘመን፡- ራስ አርክቴክት የሠራቸውን ሥራዎች ቢገልጹልን ?

አርክቴክት ራሔል፡- ራስ አርክቴክትን ከ16 ዓመት በፊት ስከፍት ምንድነው የሆነው ኔዘርላንድ ኤምባሲ የነበረውን ሥራ እኔ ነበርኩ የምመራው አብረህ ስትሠራ ፕሮጀክት እየተከፋፈልክ ስለሆነ እኔ እሱን ነበር የምቆጣጠረው ፕሮጀክቱ የአምስት ስድስት ዓመት ነበር ከዲዛይን ጀምሮ መሰረት ሲወጣ ግንባታ ሲጀመር ሁለት ዓመት ፈጀ በእኔ ሱፐር ቪዥን 2004 ላይ ግንባታው ተጠናቋል።
ከዚያ ወደ ራስ አርክቴክት ስገባ የሚቀሩ ሥራዎች ነበሩ ያው ፕሮጀክት አያልቅም እኔ ስወጣ ትንንሽ ሥራዎች ተሠርተው ተመርቀዋል እሱን ይዤ ነው ቤቴ እሠራ የነበረው በዚህ ሰዓት ላይ ሁለት ልጆች ወልጃለሁ ወጣ ገባ እያልኩ ነው የሠራሁት እንደ ሴትም ብትወስደው በጣም ትልቅ ፕሮጀክት ነው የመጀመሪያ ሥራ ራስ አርክቴክትን እንደጀመርኩ ትንሿ ልጄ ተወለደች በእጄ ላይ አንዳንድ ሥራዎች ስለነበሩ ቀጣይነትም ስለነበረው የግዴታ ላይሰንስ (የሥራ ፈቃድ) አስፈለገኝ፤ አወጣሁ በዚያ ነው የራሴ ድርጅት ራስ አርክቴክት የተጀመረው በራስ አርክቴክት ድርጅት ውስጥ የሠራነው ትልቁ ፕሮጀከት የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ነው።

አዲስ ዘመን፡- የኤምባሲውን ሕንፃ ዲዛይን አርስዎ ነዎት የሠሩት?

አርክቴክት ራሔል፡- ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲን ከሠራሁ በኋላ ብዙ ኤምባሲዎችን ሠርቼአለሁ የኤምባሲው ሥራ የኮላበሬሽን ሥራ ነው ኤምባሲው የግንባታ ሥራ ሲያስብ የሀገራቸው አርክቴክቶች መጥተው የሀገር ውስጥ አርክቴክቶችን ያወዳድራሉ ኔዘርላንድ ኤምባሲ ላይ ጥሩ የሥራ ውጤት ስለነበረኝ ወዲያውኑ ሰጡኝ።
ደቡብ አፍሪካዊ አርክቴክት ነበር ከእሱ ጋር ሆኜ ከዲዛይን ዴቨሎፕመንት ጀምሬ እየተመላለስኩ ሠራሁ እነሱም እየመጡ እዚህ ያለውን ዲዛይን ወደ አስር ኢንጂነሮች ነበሩ አብረን ሠራን በእነሱና በእኛ ግንባታው ሁለት ዓመት ፈጅቶ ተጠናቀቀ።

@etconp