Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉አለምአቀፍ የህንጻ ንድፍ ውድድር

➡️በሴኔጋል ለሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የንድፍ ውድድር ተዘጋጅተዋል ተማሪዎች፣ ህንጻነዳፊዎች፣ የንድፍ ባለሙያዎች በተጨማሪም ማንኛውም ለችግሩ መፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ የሚችል ሰው የተጋበዙ ሲሆን አሸናፊዎች የገንዘብና የአለምአቀፍ ኢንተርንሺፕ ልምምድ ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።

▶️ውድድሩን በነጠላም ሆነ በጋራ መሳተፍ ይቻላል።

🌟ውድድሩን ለመካፈልና መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ድረገጽ ይጎብኙ።

🔖www.kairalooro.com

🎁መልካም እድል🎉

👉2023’s Edition – Primary School in Africa

➡️We are glad to announce the opening of a new contest for a Primary School in Senegal, Africa.
*⃣The competition is open to students, architects and designers from around the world.

➡️Competition Awards:

*⃣1st prize: 5.000€ + Internship at Kengo Kuma in Japan + Construction.
*⃣2nd prize: 2.000€ + Internship at Benedetta Tagliabue EMBT Architects in Spain.
*⃣3rd prize: 1.000€ + Internship at SBGA - Blengini Ghirardelli in Italy.

➡️Others awards: 2 honourable mentions, 5 special mentions, 20 finalists, 20 Top 50.

➡️The registration will open on 13rd January 2023. Participation is open to architects, students, designers, engineers and anyone who wants to propose a solution to the theme. It is possible to participate in the competition individually or in teams.

*⃣We are looking for a new school model that can protect and foster the development of every child’s potential!

➡️All competition proceeds will be donated to support charity projects by Balouo Salo - Humanitarian Organization in Africa aimed to improve life condition if rural communities.

🌟To join the competition, visit our official website: www.kairalooro.com

@etconp
👍4🙏4
👉Ethiopian Association of Civil Engineers EACE invites you to participate in short training: Construction project management overview

🌟By Dr. Denamo Addissie

🏷Register online

https://forms.gle/DfHzG5LBtriEKrVbA

@etconp
👍7
👉የ20/80 እና 40/60 ባለዕድለኞች ውል እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀረበ።

➡️የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የ14ኛ ዙር 20/80 እና 3ኛ ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት እድለኞች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ከጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ባለእድለኛው ወይም ወኪሉ ቀርበው ውል መዋዋል እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል።

@etconp
🥰1
👉የህንጻ ግንባታ ላይ የሚታዩ ችግሮች/Defects in Building Construction/

➡️የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ለሚታዩ ችግሮች ዋና ዋና የመከሰቻ ምክንያቶች:
/Major Causes of defects in construction/

🌟1ኛ.ጥራታቸውን ያልጠበቁ የግንባታ ግብዓቶችን መጠቀም

*⃣ከአመራረት፣ ከአያያዝ ችግር ወይም የአገልግሎት ጊዜያቸው በማለፉ ምክንያት ጥራታቸው የጎደለ የግንባታ ግብዓቶችን መጠቀም በግንባታ ስራው ላይ የተለያዩ ከቀላል እስከ አደገኛ ችግር የሚያመጣ ይሆናል።

🌟2ኛ.ቸልተኝነት ወይም ደካማ የስራ ቁጥጥር

*⃣ሁሉም ነገር በተሟላበት ሁኔታ የተቆጣጣሪ ባለሞያዎች ለስራ ቁጥጥሩ ካላቸው ደካማ አቀራረብ የተነሳ በታችኛው የሰው ሃይል የተሰሩ ስህተቶችን በጊዜው ማረም ሳይቻል ቀርቶ በሂደት ችግሮቹ ስር ሰደው እስከ የከፋ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ይሆናል።

🌟3ኛ. ከባለሞያዎች የብቃት/ልምድ ማነስ ምክንያት ችግሮች ይከሰታሉ።

*⃣በተወሰነ መጠን ስልጠና ካላቸው ጀምሮ በከፍተኛ ደረጃ ስልጠና ያላቸው ባለሞያዎች ስራን የመረዳት አቅማቸው ደካማ ከመሆኑ ወይም ከሚሰሩት ስራ ጋር ተዛማጅ የሆነ በቂ የሆነ የስራ ልምድ የሌላቸው ሲሆንና ስራን በነሲብ/በግምት በመስራት ምክንያት ስህተቶች ሊከሰቱ ይችላሉ።

🌟4ኛ. ከዲዛይን ስህተት

*⃣ስህተት ያለበትን ዲዛይን አስቀድሞ በሚገባ ሳይታይና ጥያቄ ሳይቀርብበትና ማስተካከያ ሳይደረጋበት /Without Clarification and design Modification/ወደ ስራ ትግበራ መግባት ስራው ከጠናቀቀ በኋላ የእርምት ርምጃ መውሰድ ባብዛኛው አዳጋች ስለሚሆን በሂደት አደገኛ ችግር ያመጣል።

🌟5ኛ. ለስራ ምቹ ባልሆነ የአየር ጠባይ መስራት

*⃣አንድአንድ የግንባታ ስራዎችን ለማከናወን የተመቸ የአየር ጸባይን መጠበቅ ግድ የሚሆንበት አስተዳጅ ምክንያቶች አሉ።

▶️ለምሳሌ ዝናብ እየዘነበ የኮንክሪት ሙሊት ስራን ማከናወን በተለይ እንደ የወለል ስላብ ፣ደረጃና ራምፕ ያሉ horizontal structural members /በቀጣይ ክፍሎች የምንመለከታቸው/የተለያዩ የኮንክሪት ችግሮችን ያመጣሉ።

🌟6ኛ. ማጭበርበር

*⃣ላልተገባ ጥቅም ሲባል በባለሞያዎች፣በተቋራጮች፣ወይም በተቆጣጣሪ ባለሞያዎች አሻጥር ጥራታቸው የጎደለ የግንባታ ግብዓቶችን በመጠቀም፣ ወይም ከተቀመጠ የስራ ጥራት ደረጃ ልክ/Standard/ በታች  ስራው እንዲሰራ ማድረግ በቀጣይ ችግሮች እንዲከሰት የሚያደርግ ይሆናል።

▶️ለምሳሌ: ከደረጃ በታች የሆነ የሙሊት አፈርን ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል ስራ ላይ እንዲውል መፍቀድ ቀጣይ የህንጻው አጠቃላይ ደህንነት ላይ የሚያመጣውን ችግር መገመት አይከብድም።

🌟7ኛ. ከተፈቀደው በላይ የሚመጣ ጫና

*⃣ህንጻው ሊቋቋም ከሚችለው ጫና መጠን/Design loads/ በላይ ህንጻው ላይ የሚመጡ ተፈጥሮአዊ ወይም ሰው ሰራሽ ጫናዎች የህንጻው ደህንነት ላይ እስከ ከፋ ችግሮችን ሊያመጡ ይችላሉ።

@etconp
👍23
የክርስትና እምነት ተከታይ ለሆናቹ የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ❤️🙏

መልካም የገና በአል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን❤️
https://t.me/ETCONp
❤4👍4
👉ከ በዓል ማግስት እስቲ ትንሽ ደሞ እናስደምማቹ...

🏷የቻይናው Three Gorges Dam አስገራሚ ቁጥሮች...

➡️የግድቡን መሰረት ለመስራት 80,000 ድማሚት ሲጠቀሙ ይህ ማለት ከ20 የሂሮሺማ የኒውክሌር ጥቃቶች ጋር እኩል ነው፡፡

➡️የግድቡ Reservoir ርዝመት 660ኪ.ሜ ነው።
*⃣ይህም ማለት ከአ.አ እስከ ማይጨው እንደ ማለት ነው፡፡

➡️18200 MW ያመነጫል ይህም 7965mw ከሚያመነጨው የጃፓኑ Kashiwazaki-Kariwa የዓለማችን ትልቁ የኒውክሌር ማብሊያ 230 ፐርሰትን ይበልጣል፡፡
*⃣ከህዳሴ ግድብ ደሞ 300 ፐርሰት/ 3 እጥፍ ይበልጣል፡፡

➡️ግንባታው 30 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት ፈጅቷል - ይህም ማለት 30 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት ተጠቅመን 1 ሜትር ዲያሜትር ያለው ድፍን ኮንክሪት pipe ብንሰራ ዓለምን አንድ ዙር
መዞር ይችላል፡፡

➡️463,000 ቶን ብረት የተጠቀሙ ሲሆን ይህን ያህል ቶን ብረት ተጠቅመን 63 ኤፍል ታወሮችን መገንባት እንችላለን፡፡

➡️በአማካኝ 77.5 ሜትር width ሲኖረው ይህም ከማንኛውም አቅጣጫ የሚመጡ የሚሳኤል ጥቃቶችን እንዲቋቋም ያደርገዋል፡፡

*⃣በተጨማሪም ከግዝፈቱ የተነሳ የቀን እርዝመት በማይክሮ ሰከንድ እንዲጨምር አድርጓል፡፡

*⃣ከታላቁ የቻይና ግንብ ቀጥሎ ከስፔስ ላይ የሚታይ የቻይና ሁለተኛው የሲቪል ኢንጂነሪንግ ውጤት ነው፡፡

➡️ግንባታው ከ630 ቢሊየን ብር በላይ ሲፈጅ በ 2012 ተጠናቆ ከ1 ዓመት ከ6 ወር በኋላ ሙሉ ወጪውን መልሷል፡፡

➡️ሀብታሟ ሀገር ሳውዲ አረቢያ ከነዳጅ ፣ ከእንፋሎት ወዘተ 55000 MW ስታመነጭ ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በትንሹ 45000 MW ከውሃ ብቻ ማመንጨት ትችላለች።

*⃣እስካሁን ባለው 4000 MW አይሆንም የምናመነጨው 18200 MW የሚያመነጨው 630 ቢሊየን ብር ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የመለሰ ኢትዮጵያ 45000 MW ስታመነጭ ምን ያህል ብር ማግኘት እንደምትችል አስቡት።

🌟ለማንኛውም Hydraulic Engineering ይህን ያህል ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል፡፡

@etconp
👍37👌8
🎉ደግመን እናስደምማቹ...

👉የአለማችን የመጀመሪያው ከመሬት ጋር ያልተገናኘው ሰማይ ጠቀስ ህንጻ

➡️በወትሮው ልማድ ጠራነው እንጂ ለነገሩ መባል ያለበት ምድር ጠቀስ ህንጻ ነበር፡፡

➡️እስካሁን የአየር ላይ ጓሮ በቻይና፣ ተንሳፋፊ ከተማ በፓስፊክ ተሰርተው አይተን አድንቀናል፡፡

➡️ይህ የስነ-ህንጻ ጥበብ አሁን ደግሞ ከፍ ወዳለ ደረጃ ደርሷል፡፡

🌟መቀመጫቸውን በኒዮርክ ያደረጉ የስነ ህንጻ ጠበብቶች ከአስትሮይድ ላይ ተንጠልጥሎ ቁልቁል ወደ ምድር 50 ሺህ ኪሎሜትር ያክል የሚርቅ ምድር ጠቀስ ህንፃን ለመገንባት ዲዛይን አቅርበዋል፡፡

▶️ይህ ክላውድስ አርክቴክቸር በተሰኘው ኩባንያ ዲዛይን የተደረገው ህንጻ በአለማችን ረጅሙ ከመሆኑ በተጨማሪ ብቸኛው መሰረቱ ከላይ የሆነ የተንጠለጠለ ህንጻም ነው፡፡

▶️ኩባንያው ከዚህ በፊት የማርስ ላይ የበረዶ ቤቶችን ዲዛይን ሰርቶ ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡

▶️እንደ ኩባንያው መረጃ ከሆነ ዩኒቨርሳል ኦርቢታል ሰስፔንስ ሲስተም ሲሉ በጠሩት ዘዴ (UOSS) አማካኝነት ህንጻውን ለማንጠልጠል ታስቧል፡፡

▶️ለሀይል አቅርቦትም የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፎችን የሚጠቀም ሲሆን ለውሀ አቅርቦትም የዝናብ ውሃን መሰብሰብ በሚያስችል መልኩ እንደሚገነባ ተሰምቷል፡፡

▶️መጠሪያው አናሌማ ታወር የተሰኘው ይህ ልዩ ኪነ-ህንጻ ብዙ መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች ቢኖሩበትም የአለማችን ብዙ ሪከርዶችን የሚሰብር ልዩ ህንጻ  ይጠበቃል፡፡

@etconp
👍13👏2
@ETCONp 2015 2nd Quarter Rate .Pdf.pdf
24.3 MB
🌟የ2015 ዓ.ም 2ኛ ሩብ ዓመት የግንባታ ሥራዎች የቀጥተኛ ዋጋ (Direct Cost) ጥናት

🏷የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ታሕሳስ 30/2015 ዓ/ም

@etconp
👍5🙏2
👉በቅርቡ ይመረቃል🌟

➡️የኢትዮጵያ እና ቻይና የግንባታ ሙያተኞች አሻራ ያረፈበት የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና ጽሕፈት ቤት ህንፃ በቅርቡ ይመረቃል፡፡

➡️በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተገነባው የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና ጽሕፈት ቤት ህንፃ በ90 ሺሕ ሜትር ስኩዌር መሬት ስፋት ያረፈ ሲሆን የህንፃው ግንባታ ብቻ በ40 ሺሕ ሜትር ስኩዌር ላይ ያረፈ ነው፡፡

➡️ህንፃው የድንገተኛ ህክምና ክፍል፣ የመረጃ ማዕከል፣ ላቦራቶሪ፣ የስልጠናና የስብሰባ አዳራሾችን እና ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን የሚረዱ ማዕከላትን ያቀፈ መሆኑም ተገልጿል፡፡

@etconp
👍14
👉Construction Engineering Abbreviation Tips

➡️The common abbreviation used in Construction Industry

👷 A.A.S.H.T.O – American Association of state highway Transport Official.

👷 A.C.I – American Concrete Institute.


👷 A.R.E.A – American Railway Engineering Association.

👷 A.B – Anchor  Bolt Or Asbestos Board

👷 AC – Asphalt Concrete

👷 A.S.C – Allowable Stress of concrete.

👷 A.S.T.M – American society for testing materials

👷 AC – Asbestos Cement.

👷 AE – Assistant Engineer

👷 APM – Assistant Project Manager

👷 B.M – Benchmark

👷 B.M – Bending Moment.

👷 BLK – Block Work

👷 BOQ – Bill Of Quantities

👷 BRW – Brick Retaining Wall

👷 BWK – Brick Work

👷 B.O.F – Bottom Of Foundation

👷 BHK – Bedroom, Hall, Kitchen

👷 C.I.Pipe – Cast iron pipe.

👷 C.I.Sheet – Corrugated Iron sheet.

👷CL- Centre Line

👷CRW – Concrete Retaining Wall

👷 CBW – Concrete Block Wall

👷 CIP – Cast In Place

👷 CMU – Concrete Masonry Unit

👷 CJ – Construction Joint

👷 CC – Centre To Centre

👷 CC – Cement concrete.

👷 CE – Chief Engineer

👷 CP – Cement plaster.

👷 CPM – Critical path method.

👷 CS – Comparative statement.

👷 D – Diameter

👷 DL – Development Length

👷 Dia – Diameter

👷 DIM – Dimension

👷 D.L – Dead load.

👷 DPC – Damp proof course.

👷 DPR – Daily Progress Report

👷 DRG – Drawings

👷 DWLS – Dowels

👷 EJ – Expansion Joint

👷 E.L – Environmental load.

👷 EL – Existing Load

👷 EGL – Existing ground level.

👷 ELCB – Earth Leak Circuit Breaker

👷 F.M – Fineness Modulus.

👷 Ft – Foot Or Feet

👷 FL – Floor Level

👷 FGL – Formation ground level.

👷 FOC – Factor Of Safety

👷 GL – Ground Level

👷 GL – Ground level.

👷 GP – Ground plane.

👷 HFL – Highest Flood Level.

👷 HAC – High Alumina Cement

👷 HP – Horizontal plane.

👷 IOM – Inter Office Memo

👷 ISI – Indian standard institute.

👷 JE – Junior Engineer

👷 JST – Joist

👷 Kg  – Kilogram.

👷 L.L – Live load.

👷 LW – Light  Weight

👷 LWC – light Weight Concrete

👷 LC – Lime concrete.

👷 M – Meter

👷 MM – Millimeter.

👷 MB – Measurement book.

👷 MCB – Miniature Circuit Breaker

👷 MEP – Mechanical Electrical Plumbing

👷 MFL – Maximum Flood Level

👷 MRC – Material Receipt Challan

👷 MT – Metric Tonnes

👷 N – Newton

👷 NCF – Neat cement finishing.

👷 OPC – Ordinary Portland Cement

👷 OGL – Original ground level.

👷 OSR – Open Soace Reservation Area

👷 PC – Pile Cap

👷 PC – Precast Concrete

👷 PCC – Plain Cement Concrete

👷 PERT – Programme Evaluation and Review Technique.

👷 PL – Plinth level.

👷 PM – Project Manager

👷 PO – Purchase Order

👷 PPE – Personal Protective Equipment

👷 PPR – Poly Propylene Random.

👷 PVC – Poly vinyl choloride .

👷 PVC – Polyvinyl Chloride

👷 PSF – Pound Per Square Foot

👷 PSI – Pound Per Square Inch

👷 PWD – Permanent Works Engineer

👷 QC – Quality control

👷 QS – Quantity Surveyor

👷 RC – Reinforced Concrete

👷 R.B.W – Reinforced brick work.

👷 RBC – Reinforced Brick concrete.

👷 RCC – Reinforced Cement Concrete

👷 RMC – Ready Mixed Concrete concrete.

👷 RL – Reduced level.

👷 SCC – Self Compacting Concrete

👷 STP – Sewage Treatment Plant

👷 SRC – Sulphate Resisting Cement

👷 SWG – Standard wire gauge.

👷 TB – Tie Beam

👷 TBM – Tunnel Boring Machine

👷 TDS – Total Dissolved Solids

👷 TOB – Top Of Beam

👷 TMT – Thermo Mechanical Treatment

👷 TOC – Top Of Concrete

👷 TOW – Top Of Wall

👷 U.S.C – Ultimate stress of concrete.

👷 UPVC – Unplasticized Polyvinyl chloride.

👷 USD – Ultimate strength design.

👷 VP – Vertical plane.

👷 W.C – Water closet.

👷 WL – Working Level

👷 W.S.D – Working stress Design

👷 WO –  Work Order

@etconp
👍22🕊1
👉በኮንስትራክሽን ውል ስለ ግንባታ ስራ ርክክብ/Acceptance after completion/

➡️በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክብ ያለ ሲሆን ይሄውም ግዚያዊ ርክክብ(provisional acceptance) እና የመጨረሻ ርክክብ (final acceptance) የሚያካትት ነው፡፡

➡️በዚህ ጽሁፍ በዋናነት በኮንስትራክሽን ውል ህግ እውቅና የተሰጣቸውን የርክክብ አይነቶች ምንነትና ተያያዥ ውጤታቸውን አስመልክቶ የህግ ድንጋጌዎችን እና አሁን ላይ በመንግስት ተቋማት እየተሰራበት ያለውን የፒፒኤ 2011 ጀኔራል ኮንዲሽን ድንጋጌዎችን ባካተተ ሁኔታ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡

🚧ግዚያዊ ርክክብ/Provisional Acceptance/

*⃣ግዜያዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ስለ መሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1) ይደነግጋል፡፡

*⃣ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል፡፡

🌟ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ የሚረከብበት ሂደት ነው ማለት ነው እንዲሁም በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም የሚያረጋግጥ ነው፡፡

➡️ፒፒኤ 2011 ክሎስ 84.1 ላይ የስራ ምርመራ/verification and test/
በመሀንዲሱ ተቋራጭ ባለበት ሊደረግ እንደሚገባ በመርህ ደረጃ ተቀምጧል፡፡
ሆኖም ግን ተቋራጩ ምርመራው ከሚካሄድበት እለት ከ30 ቀን በፊት በተገቢ ሁኔታ እንዲያውቀው ተደርጐ በምርመራው እለት ያልተገኘ እንደሆነ የስራ ምርመራው ተቋራጩ በሌለበት ሊካሄድ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡

➡️እንግዲህ መሀንዲሱ ስራውን ከመረመረ በኋላ ያላመነበትን የስራ ክፍል ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል፡፡

➡️በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን የሚረከበው ይሆናል ማለት ነው፡፡
*⃣ስለዚሁም የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት ለተቋራጩ የሚሰጠው ይሆናል፡፡
*⃣በመሰረቱ ተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንዲሰጠው መጠየቅ ያለበት ስራው ሊጠናቀቅ ይችላል ብሎ ከሚያስብበት ከ15 ቀን በፊት መሆን ይኖርበታል ከዚያም መሀንዲሱ ጥያቄው በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ የስራ ምርመራውን አጠናቆ ሰርተፍኬቱን መስጠት ወይም ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
*⃣መሀንዲሱ ሰርተፍኬቱን ሳይሰጥ ወይም ጥያቄውን ውድቅ ሳያደርግ 30 ቀኑ ያለፈ እንደሆነ ለተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንደተሰጠው ግምት እንደሚወሰድ ፒፒኤ ክሎስ 87 ያስቀምጣል፡፡

*⃣ሌላው ተቋራጩ በስራው ላይ ያደረገው መሻሻል/መለወጥ ቢኖር እንኳ በዝምታ ግዜአዊ ርክክብ ከተደረገ መሻሻሉ ተቀባይነት እንዳገኘ የህግ ግምት እንደሚያስወስድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(2) ይደነግጋል፡፡እዚህ ላይ ተቋራጩ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት የመስራት ግዴታ ያለበት መሆኑ ይታዎቅ፡፡

*⃣ስለዚህ የህግ ግምቱ እሳቤ ተቋራጩ ከዲዛይኑ በመውጣት አሻሽሎ የሰራው ስራ ኖሮ በግዜአዊ ርክክብ ወቅት በዝምታ አሰሪው ካለፈው እንደተቀበለው ይቆጠራል ነው እንዲሁም ግዜአዊ ርክክብ መደረጉ የመድህንነት ጊዜው(warranty period) መጀመሩን እንደሚያመለክት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(3) ይደነግጋል፡፡

🌟የመድህንነት ጊዜ(warranty period/Defects Liability period)

▶️የመድህንነት ጊዜ(warranty period) የሚባለው ከጊዜአዊ ርክክብ እስከ መጨረሻ ርክክብ ያለው ጊዜ ሲሆን አሰሪው ግንባታው በተቋራጩ በደህና ሁኔታ ስለመሰራቱ ለመመርመርና ለማረጋገጥ የሚያስችለው ጊዜ ነው፡፡የጊዜው ርዝማኔም በውላቸው ላይ የሚወሰን ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3277 ይደነግጋል፡፡
ሆኖም በውሉ ላይ የመድህንነት ጊዜው ርዝማኔ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ከጊዜአዊ ርክክብ ቀን ጀምሮ 365 ቀን ስለመሆኑ የፒፒኤ ክሎስ 88.7 ያስቀምጣል፡፡

⏩ተቋራጩ በዚሁ በመድህንነት ጊዜ በተለይ የተበላሹ ስራዎችን እንዲያድሳቸው በአሰሪው በታዘዘ ጊዜ የማስተካከል ግዴታ እንዳለበት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3278 ይደነግጋል፡፡
ለዚህም ለጥገና ወጭ ሲባል ከተቋራጩ ክፍያ ላይ ሪቴንሽን ገንዘብ(retention money or bond) 5% እየተቀነሰ በአሰሪው ይያዛል፡፡

▶️በመድህንነት ጊዜ ውስጥ የተለዩ ተለዩ ብልብልሽት ስራዎችን እንዲያስተካክል ተቋራጩ ተጠይቆ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያላስተካከለ
እንደሆነ አሰሪው የማስተካከያ ስራውን በተቋራጩ ወጭ በራሱ ወይም ሌላ
ቀጥሮ ሊያሰራው ወይም ውሉን ሊያቋርጥ ስለመቻሉ ፒፒኤ ክሎስ 88.3 ለአሰሪው መብት ይሰጠዋል፡፡

➡️ከፊል ርክክብ/Partial Acceptance/

▶️በፒፒኤ ክሎስ 86 ላይ የግንባታ ስራው በከፊል እርክክብ የሚደረግበትንም አማራጭ ያስቀምጣል፡፡
*⃣ይህ ማለት የተወሰነውን የስራ ክፍል (part of the work) ከአጠቃላይ ውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ በውል ላይ ከተቀመጠ ተቋራጩ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከአጠቃላይ የውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ ይገደዳል ማለት ነው፡፡
*⃣በዚህም በአንድ ውል ውስጥ በተለያየ ጊዜ ጊዜአዊ ርክክብ ሊደረግ የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራል ማለት ነው፡፡

🚧የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/

➡️የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/ በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት (definitively appropriate) ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡

▶️የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡ሆኖም ጊዜአዊ ርክክብ/ Provisional Acceptance/ በሚመለከት ግን በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት የሚያስገድድ ግልጽ ህግ የለም፡፡
ስለዚህ ስራው ተጠናቆ አሰሪው ግንባታውን በእጁ ካስገባ ጊዜአዊ ርክክብ መደረጉን የሚያስገነዝብ
ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ በጽሁፍ መደረጉ ይመከራል፡፡

🌟በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ
በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ
ሀላፊነት አለበት፣መድህን ሆኖ ይቀጥላል፡፡

*⃣በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ
ለነበሩ ጉድለቶች(apparent defect) ግን ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡
ሀላፊነቱ የሚመለከተው ግንባታው በውሉ የተመለከተውን የታለመለትን ጥቅም እንዳይሰጥ የሚያደርጉ ወይም አጠቃቀሙን በጣም ውድ የሚያደርጉና አክሳሪ የሚያደርጉ ጉድለቶችን ነው፡፡

*⃣የመጨረሻ ርክክብ መደረጉ የተቋራጩን መሰረታዊ ግዴታ የሚያወርድለት ሲሆን ቀሪ ክፍያ ካለው እንዲከፈለው እና ዋስትና እንዲወርድለትና የዋስትና መያዣ ገንዘብ ካለም እንዲለቀቅለት ለተቋራጩ መብት የመስጠት ውጤት እንደሚኖረው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3281 ይደነግጋል፡፡

*⃣ፒፒኤ ክሎስ 89 በተመሳሳይ ስለመጨረሻ ርክክብ የደነገገ ሲሆን የመጨረሻ ርክክብ ሰርተፍኬትም በመሀንዲሱ ለአሰሪውና ለተቋራጩ እንደሚሰጥ ያስቀምጣል፡፡

@etconp
👍21❤1🥰1🎉1
የሽልማች ጥያቄ (Give away quizzes)

ሰሞኑን በ Facebook ገፃችን ለተከታታይ ለ 10 ቀን የሚዘልቅ አንዳንድ ጥያቄ ልንጠይቃችሁ እና ልንሸልማቹ አስበናል። የምንሸልመው 100 ብር የሞባይ ካርድ ነው ለተከታታይ 10 ቀን የሚዘልቅ ነው። ሁሉም ጥያቄዎች የሚለቀቁት በ Facebook ገፃችን ነው።

የ Facebook ገፃችንን የማታውቁ ሊንኩ 👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿

https://www.facebook.com/etconp/

መመሪያ /instruction

1. መልስ መመለስ ሚቻለው Facebook ገፃችን comment ላይ ብቻና ብቻ ነው (ለተጠየቀው ጥያቄ post ኮመንት ላይ)

- your answer is valid only if you answer on our Facebook page

Our Facebook page link:- https://www.facebook.com/etconp/

2. መልስ ከመለሳችሁ በኋላ እዛው ላይ ስልካችሁን አያይዙልን

- You should attach your phone number at the bottom of your answer so that we can reach you

3. ምንሸልመው የመጀመሪውን ትክክለኛ መላሽ ነው

- We reward the first person who gives us the correct answer.

4. በየ እለቱ የየእለቱን መላሽ የሸለምነውን screenshot እናጋራችኋለን

- We’re gonna share the screenshot of the reward daily

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍16🤡1
በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጥ መንገድ እየተወረሩ መሆናቸው ተገለጸ

ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ሽፈራው ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ታኅሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. የቀረበ ሲሆን፣ ሪፖርቱን ለመታደም ከመጡ ተቋማት ከቀረቡ አቤቱታዎች መካከል የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት ክፍት የሆኑ ቦታዎች ሕገወጥ ወረራን ይመለከታል፡፡ 

ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በግለሰቦች እየተወረሩ መሆኑን፣ በታችኛው ዕርከን የሚገኙ አመራሮች የግብር ደረሰኝ እየሰጧቸው ያላግባብ ቦታዎቹ እየተሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የቤቶች ልማት ቢሮ በዚህ ጉዳይ ሁለትና ሦስት ቦታዎች ላይ ችግር እንዳጋጠመው በመግለጽ፣ ለአረንጓዴ ልማት የሚውሉ ቦታዎች ላይ የባለቤትነት ጥያቄዎች መበራከታቸውን ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል፡፡

ቦታዎቹን በሕገወጥ መንገድ ወስደው በክረምት ወቅት ጤፍ የሚዘሩ ግለሰቦች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ የፍትሕ ቢሮው በጉዳዩ ላይ በቂ ትኩረት ማድረግ አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በበኩላቸው፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት ተብለው የተተው ቦታዎችን ከሕገወጦች መከላከል እንደሚገባ በመግለጽ፣ ቦታዎቹን በባለቤትነት እንዲያስተዳድሩት የተሰጣቸው ተቋማት ተገቢውን ማስረጃ በመያዝ ሕገወጥ ወረራውን መከላከል እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡

ለአረንጓዴ ልማት ከተተው ቦታዎች መካከል አንዱ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ፈይሳ፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጦች እንዳይያዙ የሚያስተዳድራቸው ተቋም ኃላፊነት እንደተሰጠው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሊኖረው ይገባል፡፡

በጋራ መኖሪያ ቤቶችና በማኅበር ቤቶች አካባቢ ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጦች ተወረዋል የሚሉ ክሶች እንደሚቀርቡ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

እነዚህን ቦታዎች አንዳንድ ጊዜ የሚያስተዳድሩ አካላት ማስረጃ እንደሌላቸውና በዚህም ሳቢያ የሚመጡ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ለአብነትም በአያት አካባቢ 10,000 ካሬ ሜትር ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በግለሰቦች መያዛቸውን አክለዋል፡፡

ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ለአረንጓዴ ልማት ክፍት የተደረጉ ቦታዎችን የሚያስተዳድረው አካል ይዞታው በሥሩ እንደሚገኝ የሚገልጽ ማስረጃ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፣ ማስረጃው በሌለበት ግን ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ እውነታው ሌላ ሆኖ በቂ ማስረጃ ባለመኖሩ፣ ፍርድ ቤቶች በተቃራኒው የሚፈርዱበት ሁኔታ አለ ብለዋል፡፡

Via Ethiopian Reporter

@etconp
👍9👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉Earthquake Resistance

@etconp
👍6
➡️የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራልን የማደስ ስራ በ18 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ውል መታሰሩ ተገለጸ።

▶️የእድሳት ስራው በ172 ሚሊየን ብር እንደሚከናወንም ተገልጿል።

▶️ከ1936 ጀምሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከ80 ዓመታት በላይ ማገልገሉ ነው የተገለፀው።

▶️የእድሳት ስራው በሁለት ተከፍሎ እንደሚሠራ የተገለፀ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር የህንፃ ቤተክርስቲያኑ የእድሳት ስራ እንደሚከናወን እና ይህም በ172 ሚሊየን ብር ለመስራት ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

▶️ሁለተኛው ዙር የእድሳት ስራ ጊቢውን እና አጠቃላይ የጊቢውን መልክዓምድር የማሳመር እና ውበቱን እንደጠበቀ እንዲቆይ የማድረግ ስራ መሆኑ ተገልጿል።

▶️በ3 ወር ውስጥ ጥናት በማካሄድ የካቴድራሉን የእድሳት ስራ ለመስራት ቢጀመርም የጥናት ስራው ብቻውን ወደ 2 አመት አከባቢ ፈጅቷል ነው የተባለው።

▶️በተቻለ አቅም የእድሳት ስራውን ባጠረ ጊዜ በጥንቃቄ ለማከናወን ሲባል የጥናት ጊዜው መርዘሙ ነው የተገለፀው።

▶️የሁለተኛውን ዙር የእድሳት ስራ ለመጀመርም ሰፊ ጥናት እየተደረገ መሆኑ እና የሚያስፈልገው የበጀት መጠንም እየተሰላ መሆኑ ተገልጿል።

▶️ይህ ቤተክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶሱ የሚመራ ቢሆንም ግን እንደ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ሁሉ በህዝብ ርዳታ እና ልገሳ የእድሳት ስራው እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ሊቀ ስልጣናት ቆሞስ አባ ሲራክ አድማሱ ናቸው።

▶️ቅዱስ ሲኖዶሱ እስካሁን 10 ሚሊየን ብር ገቢ ማድረጉን ገልፀው የመላው የእምነቱ ተከታይ ርብርብ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

Via Ethio Fm

@etconp
👍13🎃1
ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ለ105 የጎጆ ሮስካ የአገር ውስጥ ተመዝጋቢዎች ዕጣ አወጣ!

ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ትሬዲንግ ኃ/የተ የግል ማኅበር የመኖሪያ ቤት ግንባታ ለማከናወን አቅማቸው አናሳ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ያዘጋጀውን፤ የጎጆ ሮስካ የቤት ዕቁብ የአገር ውስጥ ሞዴል ዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ግራን‍‍‍ድ ኤልያና ሆቴል አከናውኗል።

በዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓቱ ላይ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች፣ የጎጆ ብሪጅ ሀውስ የቦርድ አባላት፣ የዳሽን ባንክ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም በርካታ የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ደንበኞች ተገኝተዋል።

በዕጣውም ኹለት ሳይቶች ማለትም በብሄረ ፅጌ አካባቢ እንዲሁም በአያት ሜቄዶንያ አካባቢ ባሉ ሳይቶች ሲሆኑ፤ በአጠቃላይ በሚገነቡ 118 ቤቶች ውስጥ በብሔረ ፅጌ አካባቢ 42 መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም 63 ቤቶች በድምሩ 105 ቤቶች ዕጣ ይፋ ተደርጓል።

Via አዲስ ማለዳ

@etconp
👍8
@ETCONp_ብቃት_ማረጋገጫና_ምዝገባ_መመሪያ_Pdf.pdf
50.8 MB
✍️በጠየቃቹን መሰረት

👉የኮንስትራክሽን ባለሙያ ፣ አማካሪ፣ የስራ ተቋራጭ ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ

@etconp
👍10
🚧የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን /contract signing date/

➡️የኮንስትራክሽን ውል ስምምነት /contract agreement በአሰሪ/ client እና በተቋራጭ/contractor መካከል የሚፈረምበት ቀን የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

➡️እዚህ ላይ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020 ድንጋጌ እና አንድ ውል ተቋቋመ ሊባል የሚችለው መቸ ነው? የሚለው ማለትም የውል አቀራረብ/offer እና አቀባበል/acceptance በሚመለከት በፍትሀብሄር ህጉ 1681 እና ተከታዮቹ የተደነገገው እና የውል ፎርም ጉዳይ ከግምት ውስጥ መግባት ጭምር አለበት፡፡

➡️የግል የኮንስትራክሽን ውል ጉዳዮችን በሚመለከተው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ አሰሪና ተቋራጭ ስለሚሰራው ስራ እና ስለዋጋው ካልተስማሙ በስተቀር የተቋራጭነት ውል አለ እንደማይባል ተደንግጓል፡፡

➡️ሌላው ከአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎችን በሚመለከት ስለውሎች በጠቅላላው የተደነገገው ጭምር ተፈጸሚነት እንዳለው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3131(1) ይደነግጋል፡፡

➡️የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጽሁፍ መደረግ እንዳለባቸው በፍትሀብሄር ህግ ስለውሎች በጠቅላላው በሚደነግገው ክፍል በአንቀጽ 1724 ላይ ተደንግጓል፡፡

➡️የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2005(1) ላይ እንደተደነገገው ደግሞ የጽሁፍ ሰነድ በላዩ ላይ የተጻፈውን ቀን በሚመለከት በተፈራራሚዎች መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ነው ይላል፡፡

▶️እንግዲህ ውል የተደረገበት ቀን በአሰሪና ተቋራጭ መካከል የውል ግንኙነት መቋቋሙን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡

▶️ውል ደግሞ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ በተዋዋዮች መካከል እንደህግ እንደሚቆጠር የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731(1) ይደነግጋል፡፡

➡️ሆኖም ግን ውሉ የተደረገበት ቀን የውሉ የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን ተደርጐ ሊወሰድ አይገባም፡፡

@etconp
👍15