Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሲሚንቶ ግብይትን ለመመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ መመሪያ ይፋ አደረገ!

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሲሚንቶ ግብይትን ለመመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ መመሪያ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ አዲስ መመሪያ ይፋ ያደረገው የሲሚንቶ ገበያው በአቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለውን አለመጣጣም እና ህገወጥነት ለማስተካከል፣በአሁኑ ወቅት ሥራ ላይ ያለው የሲሚንቶ የሥርጭት ሥርዓት አፈፃፀሙ በርካታ ክፍተቶች ያለበት በመሆኑ እና ከህብረተሰቡና በዘርፉ ስራ ላይ ካሉ ተዋንያኖች በተገኘው ግብዓት መነሻ በማድረግ መሆኑን አስታውቋል።

በመሆኑም ሚኒስቴሩ የሲሚንቶ ግብይትን ለመመቆጣጠር ካለፈው ዓመት ጀምሮ ስራ ላይ አውሎት የነበረውን የአሠራር መመሪያ ቁጥር 908/2014 በማሻሻል መመሪያ ቁጥር 940/2015 ስራ ላይ እንዲውል ይፋ ማደረጉን አስታውቋል።

መመሪያው ሲሚንቶን ከማምረት እስከ ማከፋፈል እና ይህን የሚያስፈፅሙ የመንግስት አካላት ሊከተሏቸው ስለሚገቡ የአሰራር ስርዓቶችን ያያዙ 13 አንቀፆችን ማካተቱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

አዲሱ መመሪያ ከፈለጉ በ @etconpbot ፃፉልን

@etconp
👍8🤯1👌1🤣1
@etconp_የሲሚንቶ_ግብይትን_ለመቆጣጠር_የወጣ_መመሪያ_pdf.pdf
280.7 KB
🚧የሲሚንቶ ግብይትን ለመቆጣጠር የወጣ መመሪያ ቁጥር 940_2015

@etconp
👌3👍1
🚧24 ሰአት የሚሰራበት አስገራሚ ፕሮጀክት።

🏠የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በተቋራጭነት የሚያከናውነው የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ዋና ቢሮ ግንባታ።

💫ሜክሲኮ፣አዲስ አበባ

@etconp
👍7❤4💔1
💫ትላንት ረቡዕ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ተመርቋል።

➡️ስለ ማዕከሉ ምን ይታወቃል ?

🚧ማዕከሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሌ ጋርመንት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሊዝ ነፃ ባቀረበው በ90 ሺሕ ሜትር ስኩዌር መሬት ስፋት ያለው መሬት ላይ የተገነባ ነው።

🚧የህንፃው ግንባታ ብቻ በ40 ሺሕ ሜትር ስኩዌር ላይ ያረፈ ነው፡፡

🚧የቻይና መንግሥት 80 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት የግንባታውን ሙሉ ወጪ ሸፍኗል።

🚧የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ 25 ወራትን  ፈጅቷል።

🚧ማዕከሉ የድንገተኛ አደጋ ኦፕሬሽን፣ የመረጃ፣ የላብራቶሪ፣ የስልጠና ፣ የኮንፈረንስ ማዕከል ፣ ቢሮዎች እና አፓርትመንቶች አሉት።

🚧የማዕከሉ ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ (አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ የማጠቃለያ ሥራዎች) እየተካሄደ ነው።

🚧ማዕከሉ በቅርቡ ሙሉ ስራው ተጠናቆ ወደ ሥራ ይገባል።

🚧በግንባታው ላይ ቻይናውያንና ኢትዮጵያውያን የህንፃ ባለሞያዎች እየተሳተፉበት ነው።

Via ENA

@etconp
👍7
አርክቴክቶች ወርሀዊ

"ላሊበላን የሚቀርጽ እምነት" በሚል በኢትዮዽያ ህንጻነዳፊዎች ማህበር በጥር 6 2015 የመድረክ ውይይት ተዘጋጅቷል። በውይይቱ አቶ ፋሲል ጊዮርጊስ ፣ አቶ ኪዳነማርያም ወልደጊዮርጊስ እና አቶ አገኘሁ አዳነ
የሚሳተፉ ሲሆን አቶ ማህደር ገብረመድህን ደግሞ ውይይቱን ይመሩታል።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
ቦታ። እንጦጦ የስነጥበብ ማዕከል
ሰአት ከ9-12 ሰአት
ከእስጢፋኖስ ቤተክርስትያን አካባቢ የሚነሳ ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል።
በተያያዘው የጉግል ማስፈንጠርያ ተጠቅመው ይመዝገቡ።

Meet our panelists for the coming session on "Documenting Architecture: 'LALIBELA-CARVING FAITH' Exhibition” at Entoto Fine Arts Center.

1. Fasil Giorghis
/Associate Professor, Chair holder of Conservation of Urban & Architectural Heritage at EiABC, AAU/
2. Kidanemariam WoldeGiorgis
/Sustainable Lalibela project manager/
3. Agegnehu Adane
/Director of Alle School of Fine Arts and Design, Addis Ababa/

Moderated by
Maheder Gebremedhin
/Principal Architect at Yema Architecture and director at The Urban Center/

Be sure to register at:
https://forms.gle/nexyfWpXZncXrUGU7

@etconp
👍6🍌1
🫴በጠየቃቹን መሰረት

🚧መያዥያ ገንዘብ (Retention money) እና
ቅደመ ክፍያ (ADVANCE PAYMENT) አብራሩልን ላላቹ

💫ቅደመ ክፍያ (ADVANCE PAYMENT)

➡በልዩ ሁኔታ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል ቅድሚያ ክፍያ/advance payment/ የሚፈቅድ ከሆነ ስራ ተቌራጩ ስራውን ለማሰጀመር ማሽነሪ እና የግንባታ ግብአት ለማስገባት በሚጠየቅ ግዜ የሚከፈል ክፍያ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል

▶️ቅድመ ክፍያው ስራ ተቋራጩን የሰራ ውሉን ተፈፃሚ የሚያደርግበትን የጠቅላላ ግምት ነው።
▶️በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል(Special condition of contract) የቅድሚያ ክፍያውን መጠን መግለፅ ሲኖርበት ነገር ግን ከጠቅላላ ፕሮጀክት ወጪ ሰላሳ (30%)ፐርሰንት መብለጥ የለበትም።
▶️ውል ተፈፅሞ ፕሮጀክት ሳይት ርክክብ ሳይደረግ ቅድሚያ ክፍያ አይሰጠውም።
▶️ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው ክፍያ ዋስትና ቦንድ ሊያቀርብ ይገባል።

💫መያዥያ ገንዘብ (Retention money)

➡️ስራ ተቋራጩ የተሰጠውን ስራውን ጨርሶ የስህተት ማስተካከያ ግዜ ድረስ/defect liability period / ሀላፊነት
ለመወጣቱ ማረጋገጫ እንዲሆን ከእያንዳንዱ የክፍያ ቅፅ የሚያዝ
ገንዘብ ነው።

▶ከክፍያ ቅፅ ምን ያህል ሊቆረጥበት እንደሚገባ ለፕሮጀክቱ በልዪ ሁኔታ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/በግልፅ ሊያስቀምጥ ይገባል።

▶ሆኖም ከ አስር ፐርሰንት (10%) የበለጠ መሆን አይችልም።

▶በሀገራችን አብዛኛውን ግዜ አምስት ፐርሰንት(5%) ብቻ የተለመደ ነው።

▶️ስራው እንደተጠናቀቀ ግማሹ ከመጨረሻ ክፍያ ጋር ቀሪው ደግሞ ከርክክብ በኋላ ስራው ላይ ስህተት ቢፈጠር በውሉ ላይ የማስተካከያ ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ ከመጨረሻ ርክክብ ጋር በአርባ አምስት (45) ቀናት ውስጥ ይለቀቅለታል።

@etconp
👍14❤1
ኢምፔሪያል አካባቢ የሚገኘው የመሸጋገሪያ ድልድይ ግንባታ በጥር ወር ይጠናቀቃል!

በአዲስ አበባ በኢምፔሪያል አካባቢ የሚገኘው የመሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ በጥር ወር ተጠናቅቆ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንደሚጀምር የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢያሱ ሰለሞን በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፣ ከወሰን ከመገናኛ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ ድልድይን ጨምሮ የግራ መስመር ግንባታው በቀጣዩ ወር ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። የመንገዱ ቀኝ መስመር ግንባታ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ላይ ይገኛል።

የማሳለጫ ድልድዩ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመት፤ 40 ሜትር የጎን ስፋት እና 3 ሜትር ቁመት ያለው መሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

የድልድዩ ግንባታ በቻይና ፈርስት ሃይ ዋይ ኢንጂነሪንግ የመንገድ ሥራ ተቋራጭ እየተከናወነ መሆኑንና የግንባታው ወጪም 800 ሚሊዮን ብር መሆኑን የገለጹት አቶ ኢያሱ፤ስታዲያ ኢንጂነሪንግ የተባለ ድርጅት የቁጥጥር ሥራውን እንደሚያከናውን አመልክተዋል።

Via EPA

@etconp
👍4
Ethio Construction Engineering
Southern Ethiopia cultural housing style ደቡብ ኢትዮጵያ የሚታወቁበት የቤት አሰራር ጎጆ ቤት ነው። የተለያዩ ኪነህንፃ ይዘት ያላቸው ግን በስያሜ ጎጆ ተብለብ ይጠራሉ። ከ ቦታ ቦታ የተለያየ አይነት ጎጆ አለ፣ ባህላቸውን ይገልፃል ያሉትን ጎጇቸው ያንፀባርቃሉ። ይህ አይነቱ ቤት እንዴት ይሰራ ይሆን? ፩. ምሶሶ የሚቆምበትን ቦት መለየት ምክንያቱም ጎጆ ቤት ክብ…
Further on wall system
በጣውላ የሚሰራ ግድግዳ

በሀገራችን በ ጣውላ ቤት መስራት አልተለመደም። በ ጣውላ ቤት መስራት ቅዝቃዜ ያለበት ቦታ በጣም ተመራጭ ነው ምክንያቱም እንጨት ቅዝቃዜን አምቆ ይይዛል።

የጣውላ ግድግዳ ሁለት አካተክፍላት አሉት ቋሚ ጣውላ (መደገፊያ) እና ቦርድ( ፕላይ ውድ ወይም ማንኛውም አይነት የጣውላ ቦርድ) ቦርዱ ግን ውጫት የ እየር ሁኔታን መቋቋም አለበት ለዚህም ነው siding የምንጠቀመው። siding ማለት የ ጣውላ ወይም የ vinyl እርከን የሚመስሉ የጣውላ ግድግዳ ውጫዊው አካል ላይ የሚረበረቡ ግድግዳ ላይ ዝናብ ቢያርፍበት flash አድርጎ ወደመሬት እንዲሄድ ያረጋል።

ሁለት አይነት framing መንገዶች አሉ በ ጣውላ አሰራር ምስሉ ላይ አንብቡ ግን ልዩነታቸው ballon framing የጣውላ frame structure ሲሆን platform ደግሞ load bearing structure ነው።

ጣውላ እሳንት የመቋቋም አቅሙ ደካማ ነው በ እሳት ይበላል ይህል ለመከላለከል chemical አለ ግን ከቃጠሎ ሙሉ በ ሙሉ አያመልጥም

ግድግዳ አሰራሩን በተመለከተ ጣውላ ድምፅ ያስተጋባል ስለዚህ sound insulation ያስፈልጋል ይህል ተማረግ ጥጥ ሚመስል ፎም ወይም በ ከረጢት አሸዋ ሞልቶ መውላት ይቻላል ከውስጠኛው እና ውጨኛው board / plywood መሀል።

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
Youtube :- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE
👍13
👉በኮንስትራክሽን ውል ጉዳይ የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ ምን ይላል?

🚧የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ በአሰሪው በሚመደብ አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና በተቋራጩ ተረጋግጦና ተማምነውበት የሚፈረም ሲሆን ለተቋራጩ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠንም በግልጽ ያስቀምጣል፡፡

▶️የክፍያ ምስክር ወረቀት ጋር ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪ አባሪ ተደርጐ ይያያዛል፡፡
▶️ቴክ ኦፍ ሽት የአሰሪው አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና የተቋራጩ መሀንዲስ በግንባታ ቦታ በአካል የሳይት ቪዚት በማካሄድ የተሰራውን ስራ መጠን እና አይነት ከለቀሙ በኋላ በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ከተመለከተው የእያንዳንዱ ስራ አይተም ዩኒት ሬት/ነጠላ ዋጋ አንጻር በዝርዝር በተናጠል በዋጋ የሚያስቀምጡበት የተሰራውን ስራ መጠን እና የገንዘብ መጠን ገላጭ ዝርዝር ሰነድ ነው፡፡

▶️ግራንድ ሳመሪ ደግሞ በዋናነት የግንባታወችን ዝርዝር/ብሎክ በማስቀመጥ የውሉን ዋጋ፣አስቀድሞ የተከናወነ ስራ መጠን፣አሁን የተከናወነ ስራ መጠን እና አጠቃላይ በተቋራጩ የተሰራውን የግንባታ ስራ መጠን ይጠቅሳል፡፡

▶️የክፍያ ሰርተፍኬት በአብዛኛው በአንድ ገጽ ተጠቃሎ የሚዘጋጅ ሲሆን በይዘት ደረጃ ግን ብዙ መረጃወችን አምቆ የያዘ ሰነድ ነው፡፡

▶️የክፍያ ሰርተፍኬት በተለይ ክፍያው የመጀመሪያ ዙር፣ሁለተኛ ዙር እያለ በሚታወቅበት መንገድ የሚዘጋጅ ሲሆን የመጨረሻ ዙር ክፍያ የሚባልም አለው፡፡

▶️የመጀመሪያ ዙር ክፍያ የሚፈጸመው በአብዛኛው ከቅድሚያ ክፍያ በኋላ ሲሆን ክፍያውም ለተሰራ ስራ የሚፈጸም ነው፡፡

▶️የመጨረሻ ዙር ክፍያ ደግሞ ግንባታው ተጠናቆ ጊዜአዊ ርክክብ/provisional acceptance/ ከተከናወነ በኋላ በህግ ከተቀመጡ ተቀናሾች በስተቀር ቀሪውን የስራ ክፍያ ጠቅልሎ አካቶ ወዲያውኑ በግንባታ ውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡

▶️የክፍያ ሰርተፍኬት የፕሮጀክቱን ስም፣ቦታ፣አሰሪውን፣ተቋራጩን፣አማካሪውን ይጠቅሳል፡፡
▶️ዋናውን የውል ገንዘብ መጠን፣ተቀጽላ ስራዎችን፣ቫሬሽንን እና የተከናወነውን የስራ መጠን ያመለክታል፡፡ውሉ የተደረገበትን ጊዜ እና ኮመንስመንት ዴት ይጠቁማል፡፡
▶️በተጨማሪም የቅድሚያ ክፍያ መጠን እና አድቫንስ ሪፔይ ያመለክታል በዚህም አስቀድሞ የነበሩ የክፍያ ቁጥሮችን ጭምር ይጠቁማል፡፡
▶️እንደዚሁም የሪቴንሽን መጠን እና የቅጣት መረጃንም የሚሰጥ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን ሁሉ መረጃ በያዘ የክፍያ ሰርተፍኬት ላይ አሰሪው/ተቆጣጣሪው/አማካሪው እና ተቋራጩ የሚፈራረሙበት ይሆናል፡፡  
▶️ስለዚህ የክፍያ ሰርተፍኬት ጸደቀ ማለት በሰርተፍኬቱ ላይ የተመለከተው ስራ ስለመሰራቱ እና ዋጋውንም ጭምር አሰሪውና ተቋራጩ አምነውበታል ማለት ነው፡፡
▶️እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የአሰሪው ዋና ግዴታ ለተቋራጩ በወቅቱ ክፍያ መፈጸም ነው፡፡
▶️የፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ ክሎስ 28.5 ላይ ስለኮንስትራክሽን ስራዎች ክፍያ እንዴት መፈጸም እንደሚገባው ይዘረዝራል፡፡
▶️በዚህ ረገድ በተለይ ክሎስ 28.5(a) ላይ የተቀመጠው እንደሚያስገነዝበው በኮንስትራክሽን ስራዎች ጉዳይ ክፍያ የሚፈጸመው በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠና የጸደቀ የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ እንዲቀርብ በማድረግ መሆኑን አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡
▶️እንግዲህ የክፍያ ጥያቄ የሚያቀርብ በመጀመሪያ ተቋራጩ እንደመሆኑ አማካሪው/ተቆጣጣሪው መሀንዲስ የሳይት ቪዚት በማካሄድ የክፍያ ጥያቄውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኋላ የክፍያ ሰርተፍኬቱን፣ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪውን ጨምሮ የሚያጸድቅና አረጋግጦ የሚፈርምበት እና በማህተምም የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡
▶️አማካሪው/ቶጣጣሪው በተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ እንደቀረበለት በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማረጋገጡን ስራ ማጠናቀቅ እንደሚገባው በዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(d) ላይ በአስገዳጅ ሁኔታ ተቀምጧል፡፡
▶️እንደዚሁም አሰሪው ደግሞ በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያውን መፈጸም እንደሚገባው በአስገዳጅ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡
▶️እንግዲህ ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በእጁ ይዞ እያለ እና አሰሪውም ደርሶት እያለ ሳይከፍለው ያዘገየበት እንደሆነ በግንባታ ውሉ እና የውል አካል በሚያደርጉት ጀኔራል ኮንዲሽን በተመለከተው አግባብ ተቋራጩ ኪሳራ ከአሰሪው ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል ዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(g) በግልጽ እና በአስገዳጅ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡
▶️ፒፒኤ 2011 ክሎስ 59 እንደዚሁ የኮንስትራክሽን ጉዳይ የስራ ክፍያ የሚፈጸመው በክፍያ ሰርተፍኬት አማካይነት ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡
▶️በአጠቃላይ ከላይ የተመለከተው የክፍያ ሰርተፍኬት ባህሪ እና የፒፒኤ ድንጋጌ የሚያስገነዝበው ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በአማካሪው/ተቆጣጣሪው እስከጸደቀለት ድረስ ያለምንም ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ ክፍያ ሊፈጸምለት እንደሚገባ ነው፡፡  አመሰግናለሁ

በ ጉባዔ ኣሰፋ

#ConstructionLaw

@etconp
👍25
Let’s discuss about MESOB tower

ምስሉ ላይ የተቀመጡ ጥያቄዎችን እንወያይበት በ discussion group @cotmp

እንደኔ እንደኔ ግን ይህ ህንፃ design stage’ኡን እንደጨረሰ contract ለሀገር ውስጥ ኮንትራክተሮች በ JOINT-VENTURE መስጠት እና quality የውጭ ሀገር consultantኦች ቁጥጥር ቢያረጉ

፩. የሀገር በቀል ኮንትራክተሮች ልምድ ይካብታል

፪. ኮንትራክተሮቻችን በ አለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በመሆን ነገ የውጭ ምንዛሪ ያስገኙልናል

፫. የውጭ ምንዛሬ እናተርፍበታለን

ይህን በተመለከተ መንግስት አስፈላጊውን equipment እንዲያሟሉ ለሀገር በቀል ተቋራጮች ከማመቻቸት በተጨማሪ ብድር ቢመቻች ባይ ነኝ በግሌ።

JORDANO’s point of view

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Youtube YouTube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
❤9👍8
‼️እሁድ እለት የሽልማት ጥያቄው ይጀምራል‼️

እሁድ ከቀኑ 11 ሰዐት ጥያቄውን እንለቅላችኋለን ከዛም ለተከታታይ 10 ቀን ይቆያል

We will start the giveaway questions on Sunday at 11LT then it will continue for 10 days straight

ስልካችሁ እንዲታይ ማትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩን ምንም ችግር የለም

If you don’t want your number to be shown in public DM use in a private message

እስከዛ ለጓደኞቻችሁ ይህን post አጋሩ
#share #ShareThisPost

Share this post to your friends so that they will be updated when it’s gonna start

አልሰማንም እንዳትሉ

ደህና እደሩ ቤተሰቦቻችን

Good night

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍11
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
@etconp payment certificate - Copy.xlsx
204.9 KB
Payment certificate

አብዛኞቻችሁ በጠየቃችሁን መሰረት payment certificate እንካችሁ ብለናል።

Payment certificate’ቱን ምታገኙት payment በሚል sheet ነው።

ለጓደኞቻችው በማጋራት አጋርነታችሁን አሳዩን 🙏።

Payment certificate

@etconp
👍19👏1