Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Ethio Construction Engineering
Further on wall system በጣውላ የሚሰራ ግድግዳ በሀገራችን በ ጣውላ ቤት መስራት አልተለመደም። በ ጣውላ ቤት መስራት ቅዝቃዜ ያለበት ቦታ በጣም ተመራጭ ነው ምክንያቱም እንጨት ቅዝቃዜን አምቆ ይይዛል። የጣውላ ግድግዳ ሁለት አካተክፍላት አሉት ቋሚ ጣውላ (መደገፊያ) እና ቦርድ( ፕላይ ውድ ወይም ማንኛውም አይነት የጣውላ ቦርድ) ቦርዱ ግን ውጫት የ እየር ሁኔታን መቋቋም አለበት ለዚህም…
Floor system (ስርዓተ-ወለል)

ተንጠልጣይ ወለል(suspended slab) መዋቅራዊ የህንፃ አካል ሲሆን የተደለደለ እና ለጥ ያለ ወይም ለ ramp ተዳፋት( sloppy) ቦታ ይሰጠናል።

የግብዓት አንፃር

፩. በፌሮ እና በ አርማታ የሚሰራ
፪. በጣውላ ሚሰራ
፫. በ ብረት ብቻ ሚሰራ
፬. ተገጣጣሚ

ከድጋፍ አንፃር

፩. በመሬት የሚደገፍ
፪. ተንጠልጣይ

- በ አርማታ እና በፌሮ ሚሰራው በስፋት የተለመደ ነው በሀገራችን
- ጥልቀቱ እንደሚሸከመው ክብደት ይለያያል በሀገራችን ብዙ ጊዜ ጥልቀታቸው 15ሳንቲም የሆኑ ሶሌታዎችን እንጠቀማለን

ኢታብስ ላይ እኚ የ ሶሌታ ምርጫዎች ይመጣሉ አዲስ File ስትከፍቱ።

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Youtube:- https://youtube.com/@Etconp432

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👍13👏2❤1💯1
🏷በኢትዮጵያ ፈጣን የሆነ የከተሜነት ምጣኔ መኖሩንና አሁን ላይ በኢትዮጵያ ያሉ ከተሞች ብዛት ከ 2ሺህ 500 በላይ መሆናቸው ተገልጿል።

🚧በኢትዮጵያ ያሉ ከተሞች ከአጠቃላይ አገራዊ ምርት እድገቱ(ጂዲፒ) ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውን እያመነጩ እንደሚገኙም ተጠቁሟል።

🚧የኮንስትራክሽን ዘርፍ ደግሞ ከግብርና በመቀጠል ለዜጎች ከፍተኛ የስራ እድል እየተፈጠረበት ነው መሆኑ ተነግሯል።

🚧ይህ የተነገረው በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የአቅም ግንባታ ፕሮጀክት ትግበራ ሰነዶች ላይ ያተኮረ ውይይት በመዲናዋ በሚካሄድበት ወቅት ነው።

Via ኢዜአ

@etconp
👍8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍2
🏷የግንባታ ዲዛይን ከተሰራ በኋላ የሚመለከተው የመንግሥት ቢሮ ዲዛይኖቹን (All drawings, details and BOQ) አይቶ እስከማረጋገጥ (መርምሮ አስተያየት ከመስጠት እስከማጽቀድ) የሚወስድበት ጊዜ በመመሪያ የተደነገገ ሲሆን ከፍተኛው ውስብስብነት እና ግዝፈት ላላቸው ሕንጻዎች (ምድብ ሐ) የሚወስደው ጊዜ 21 ቀን ነው።

▶️አንድ የግንባታ ፍቃድ ከ21 ቀን በላይ የማጽደቂያ ጊዜ ሊራዘምበት አይገባም።

▶️የህንጻ መመሪያና ስታንዳርድ ቁጥር 3/2015 (4.8)

@etconp
👍6👌1🤣1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💫ፋና ቴሌቪዥን በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባለቤትነት እየተገነባ የሚገኘውን የኮልፌ ቀራኒዮ (ቤተል መንዲዳ) ሆስፒታል ግንባታ ሂደትን በተመለከተ ያሰናዳው ዘገባ

🌟የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥር 22/2015 ዓ/ም

@etconp
🏷ፍሊንት ስቶንስ አክሲዮን ማህበር ያስገነባቸው ቤቶች የፍርድ ቤት እግድ ተጣለባቸው።

🚧የመኖርያ ቤቶችን ሰርቶ ለመሸጥ የተቋቋመው ፍሊንት ስቶን አክስዮን ማህበር ፣ ቤት ለመግዛት ከተመዘገቡ ግለሰቦች ጋር በገባው ውዝግብ ሳቢያ በቦሌ ክፍለ ከተማ ያለው የአደይ በሻሌ ሳይት ላይ ያሉ ጅምር ግንባታ ቤቶች በፍርድ ቤት ታገዱ።

🚧ዋዜማ እንደተመለከተችው የአደይ በሻሌ ሳይት ላይ “ፍሊንት ስቶን አክስዮን ማህበር በ26 ወራት (በሁለት አመት ከሁለት ወር) ቤት ሰርቼ አስረክባቹሀለሁ ብሎን በሰባት አመትም አላስረከበንም” ያሉ በእነ ሚሊዮን ግርማ ከሳሽነት የተካተቱ 213 ግለሰቦች ፣ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት ያቀረቡትን ክስ ተከትሎ ነው እግዱ የተላለፈው።

🚧ከሳሾቹም አክስዮን ማህበሩ በውሉ መሰረት መሰረት ግዴታውን አልፈጸመም ፣ ስለዚህ በውላችን መሰረት ቤታችንን ሰርቶ ያስረክበን የሚል አቤቱታን ነው ያቀረቡት። 

🚧ጉዳዩ በፍርድ ቤት ውሳኔ እልባት እስኪያገኝ ድረስም ከሳሾች በቦሌ ክፍለ ከተማ ያለው የፍሊንት ስቶን አክስዮን ማህበር የአደይ በሻሌ ሳይት እግድ እንዲወጣበት ጠይቀዋል።

🚧የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎትም በ28/04/2015 አ.ም በዋለው ችሎት እግዱን አስተላልፏል። በዚህም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የቤት ቁጥር አዲስ የሆኑ ፣ በካርታ ቁጥር ቦሌ -10 /69/1/6/4319/100 የተመዘገቡ ጅምር የመኖርያ ቤቶች እንዳይሸጡ ፣ እንዳይለወጡ ፣ በማንኛውም ሁኔታ ወደ 3ኛ ሰው ሳይዞሩ ታገደው ባሉበት ሁኔታ እንዲቆዩ አዟል።

🚧ተከሳሽ ፍሊንት ስቶን አክስዮን ማህበር እግዱ ተገቢ አይደለም ወይንም ይነሳልኝ ካለ በጽሁፍ ከሚያስገባው ምላሽ ጋር እንዲያቀርብ የተገለጸ ሲሆን ክስ ለመስማት ለ23/05/2015 አ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል።

🚧ዋዜማ እንዳጣራችው ከሆነ ፍርድ ቤት ያገደው የአደይ በሻሌ የፍሊንት ስቶን አክስዮን ማህበር ሳይት ያላለቁ ባለ 12 ፎቅ አምስት ህንጻዎች ናቸው።

🚧ዋዜማ ባደረገችው ሌላ ማጣራትም ፍሊንት ስቶን አክስዮን ማህበር ቤት አጠናቆ ከማስረከብ ጋር በተያያዘ በሌሎች ሳይቶችም ከገዥዎች ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባ ሲሆን ፣ ተጨማሪ ሶስት ሳይቶች ላይ ያሉ ገዥዎች ወደ ህግ ለማምራት ሂደት ላይ መሆናቸውን ተገንዝበናል።

🚧ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ የፍሊንት ስቶንስ ስራ አሰኪያጅ አቶ ፀደቀ ይሁኔንና ድርጅታቸውን ብንጠይቅም እስካሁን ምላሻቸውን ማግኘት አልቻልንም።

Via ዋዜማ

@etconp
👍8❤1
📩How to calculate the length of circular stirrup for circular concrete structures?

🔑Answer

🌟The cutting length of circular stirrup.
= [2πr + (2× overlapping length ) – (2× hook bend length) ]
= [2πr +(2× 10d ) – ( 2*2d )]

👌E.g., The stirrup with diameter 8mm has been designed for a circular concrete column having a diameter of 50cm. If the concrete cover considered for column is 50 mm, calculate the length of a single stirrup length.

💫solution:

🌟Step1: First we need to calculate the radius of reinforcement installation
r = [ (1/2×dia column) –concrete cover – (1/2× dia. stirrup)]
= [ (1/2×0.5) –0.05– (1/2×0.08)]
= [ 0.25 –0.05– 0.04]
= 0.16 m

🌟step 2: Calculate length of stirrup
= [2πr + (2× overlapping length ) – (2× hook bend length) ]
= [2π*0.16 +(2× 10*0.08 ) – ( 2*2*0.08)]
= [1.005 +1.6–0.32]
= 2.29 m

@etconp
👍15
📩"የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሚያስገነባቸው ግንባታዎች ላይ ትዕዛዝ መሥጠት ይችላል ወይስ አይችልም? "

🏷“አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሚያስገነባቸው ግንባታዎች ላይ በግንባታ ሒደት ውስጥ ለተቋራጩ የስራ ትዕዛዞችን እየሰጠ፣ የስራዎቹን አካሄድ የመወሰንና ስራው በሚፈቅደው አይነት እንዲፈፀም የስራ ተቋራጩን የማዘዝ ሥልጣን ያለው ሲሆን፣ ተቋራጩ በበኩሉ በአሠሪው የመንግሥት መሥሪያ ቤት በተሰጡት ፕላኖች አይነቶችና የዋጋና የስራ ማስታወቂያ መሰረት ጠንቅቆ የግንባታ ሥራውን የመስራት ግዴታ እንዳለበት።”

💫በፍ/ብሔር ህግ ቁጥር 3252 ንዑስ አንቀጽ 1 እና ንዑስ አንቀጽ 2 በግልፅ ተደንግጓል።

🚧ከዚህ ጋር ተያይዞ የጨረታ ሰነዱ በሚወጣበት ጊዜ በግንባታ ዲዛይኑ ላይ ከተመለከተው ልኬት በታች ሆኖ በኋላ በዲዛይኑ መሰረት ለሚሰራ ግንባታ የሥራው ባለቤት በግንባታው ሥራ ውል ሰነዱ ላይ ከተመለከተው ክፍያ ውጪ በተጨማሪነት በባለቤቱ ፈቃድና ትዕዛዞች መሠረት ለተሠሩ ሥራዎች ክፍያ ለመክፈል የሚገደድ ሲሆን በህጉ አግባብ በባለቤቱ የተሰጡ ተጨማሪ የሥራ ትዕዛዞች የሥራ ውሉ አካል ተደረገው የሚወሰዱ ይሆናል።

🔑የፍ/ብ/ህ/ቁ.3244, 3225,(1)(2), 3152(1), 3266(1), 3263, 3265(3)

@etconp
👍11🍌1
🌟HELLO DEAR ETCONp MEMBERS

🏷I am Abisa Mezgebe, an MSc student at the University of Science and Technology Beijing.

🚧I would like to ask @ETCONp Family's to collect data On road construction sector engineers.

💫The collected information will be used for the academic research entitled “Assessment of Workers Safety Practice and Posterior Probabilities of accidents in Road Construction Projects in Ethiopia” which is to be conducted as partial fulfillment of my MSc in Safety Science and Engineering.

📩So Please Help me on the Below Link And Fill My Questioner's.

🙏THANK YOU👌

https://forms.gle/cAW41GgFZQMXXGV69
👍8
🏷የደብረ ብርሃን ዓለም አቀፍ ስታዲየም ወደ ግንባታ ሥራ እንዲገባ አስፈላጊው ጥረት ይደረጋል ተባለ።

🚧በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ ይገነባል ተብሎ ለበርካታ ዓመታት የዘገየው የደብረ ብርሃን ዓለም አቀፍ ስታዲየም ወደ ግንባታ ሥራ እንዲገባ አስፈላጊው ጥረት እንደሚደረግ ተገልጿል።

🚧የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ቡድን ከ15 ዓመት በፊት ግንባታው ይጀመራል ተብሎ ቢታሠብም ሲጓተት ዛሬ ላይ የደረሠውን  የደብረ ብርሃን ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተመልክቷል፡፡

🚧በዚሁ ወቅት 41 ሄክታር  መሬት ከከተማ አሥተዳደሩ ተከልሎ የተሰጠው የስታዲየሙ ግንባታ ለረዥም ዓመታት ሳይጀመር መቆየቱ ነው የተገለጸው፡፡

🚧አኹን ላይ ግንባታው ካርታና ፕላን ተዘጋጅቶለት እንዲሁም የዋጋ ግምት ወጥቶለት  ግንባታውን ለማስጀመር፤ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤትና ኮሚቴ በማቋቋም ገቢ በማሰባሰብ ወደ ሥራ ለማስገባት  በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ከተማ አሥተዳደሩ ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

🚧የደብረ ብርሃን ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ደረጃውን የጠበቀና  ለአካባቢው ማኅበረሰብ ብሎም ለሃገር ያለው ፋይዳ ጠቃሚ መሆኑን በመረዳት ሁሉም አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።

@etconp
👍6
🏷ከ100 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባ ኮሌጅ በወላይታ ዞን ተመርቋል።

🚧በዴሳ የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ላለፉት ሰባት ዓመታት ግንባታው ሲከናወን ቆይቶ ለምረቃ መብቃቱ ተገልጿል።

🚧ኮሌጁ ከ300 በላይ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዙር ተቀብሎ በቴክኒክና ሙያ ዘርፎች ማስልጠን ይጀምራል ተብሏል።

@etconp
👍6🤔2
🏷ከግንባታ ህጎች አንጻር እንዴት ያዩታል?
(ቅሬታ የተፈጠረበት እውነተኛ Case)

🚧አንድ የመንግሥት ተቋም ሕንፃ ለማስገንባት ከተቋራጩ ጋር ውል ተፈራረመ። ተቋራጩ ሥራውን ከጀመረ በኋላ በተሰጠው ዲዛይን (Drawing) መሰረት ልኬት እየፈጸመ የአሠሪው ተቋም አማካሪ መሐንዲስ (Engineer) እያጸደቀለት ቢሠራም በእውነተኛው ሥራው ላይ ያለው የተመዘገበው የሥራ መጠን (Actual Quantity of activities) በውል ሰነዱ ላይ ከተፈራረሙበት የሥራ መጠን (with the quantities specified in the BOQ of contract document) በ49 በመቶ (49%) ጭማሪ ተገኘበት።
በዚህ መካከል ተቋራጩ በእውነተኛው የሥራ መጠን ተባዝቶ ክፍያ እንዲፈጸምለት ጠየቀ።
አሰሪው መሥሪያ ቤት ተጨማሪ የመጣበትን ጉዳይ በውል ስምምነቱ ሰነድ ላይ ከተገለጸው በላይ ስለሆነ ክፍያ አልፈጽምም ብሎ የግንባታ ሂደቱ እንዲቆም ትዕዛዝ ሰጠ።

🚧ይህ የክፍያ ጉዳይ፦
1ኛ. ከግንባታ ህግ አንጻር ተገቢነት ያለው ማንኛው ወገን ነው?
2ኛ. ጥፋት ያለበት ባለድርሻ አካል ማነው? ምን አይነት ጥፋት?

📩መልሱን በዚሁ ገጽ እንለቃቀን።

💫ከዚያ በፊት ግን ሁላችንም ምላሽ በመስጠት ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪያችን ዕድገት እውቀት እየተጋራን አስተዋጽኦ ለማረግ ያክል ከታች ባለው የ መወያያ ግሩፕ በ መግባት ሀሳብ ስጡበት

https://t.me/ETCONp
👍18🍌3🎃2
🏷አዲስ አበባ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ የምስራቅ አፍሪካ ከተሞች አንዷ መሆኗ ተገለጸ

🚧ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ የሚታወቀው የእንግሊዙ ሸፊልድ ዩንቨርሲቲ አዲስ አበባ በፍጥነት በማደግና በመስፋፋት ላይ ካሉ የምስራቅ አፍሪካ ከተሞች አንዷ መሆኗን አስታውቋል፡፡

🚧ዩንቨርሲቲው የኢትዮጵያውያንን ርዕሰ መዲና አዲስ አበባን ጨምሮ የዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ እንዲሁም የሩዋንዳ ርዕሰ መዲና ኪጋሊ፤ በቀጠናው በፍጥነት በመቀየር ላይ ያሉ ከተሞች ናቸው ሲል ጠቁሟል፡፡

🚧የጥናቱ ተሳታፊ የሆኑት የከተማ ምጣኔ ሀብት ባለሙያ እና የሸፊልድ ዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር ቶም ጉድፌሎው ከ23 ዓመታት በፊት ሦስቱ ከተሞች በጣም ሗላቀር እና የዓለም ፖሊሲ አውጭዎችን ቀልብ የማይስቡ ነበሩ ብለዋል፡፡

🚧ይሁን እንጂ አሁን ላይ አገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትኩረት መሳብ የቻሉ እና ከተሜነት በፍጥነት እያደገ ያለባቸው ከተሞች ናቸው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

🚧የፋብሪካዎች መስፋፋት፣ የግል ዘርፉ ማደግ እንዲሁም የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ከተሞቸን ቀድሞ ከነበሩበት ገጽታ ተለይተው እንዲታዩ ያደረጉ መሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡

🚧በተጨማሪም የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ቻይና በአፍሪካ ለምታደርገው የመንገድ ግንባታ ኢንቨስትመንት የትኩረት ማዕከል መሆኑ ለከተሞች በፍጥነት ማደግ እና መስፋፋት ሌላ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

🚧ሦስቱ ከተሞች ከብዙ ጊዜ በኋላ በዘመናዊ የከተማ ንድፍ ስርዓት ለመመራት ዕቅድ ማስቀመጣቸውና አዲስ የከተማ ራዕይ መንደፋቸው እንደ አንድ የእድገት መለኪያም ተወስዷል፡፡

🚧በዓለም ላይ ከተሜነት በፍጥነት እያደገ እና እየተስፋፋ ካለባቸው ቀጠናዎች አንዱ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

Via አዲስ ማለዳ

@etconp
👍8🤣2
🏷የአቃቂ ዞናል ስታዲየም የካፍ ስታንዳርድን እንዲያሟላ አድርጎ ለመስራት የሚያስችል የዲዛይን ክለሳ ተደረገ፡፡

🚧የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በባለቤትነት እያስገነባው የሚገኘው የአቃቂ ዞናል ስታዲየም የካፍ ስታንዳርድን በሚያሟላ መልኩ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ያስችላል የተባለለት የተከለሰ ዲዛይን በዛሬው ዕለት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአማካሪ ድርጅቱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

🚧በኔማድ የኪነ ህንጻ መሀንዲሶች ኃ/የተ/የግ.ማህበር የተዘጋጀው ይህ ዲዛይን ስታዲየሙ ዕውን በሚሆንበት ጊዜ  የካፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ሲጠናቀቅም በከተማችን ብቻም ሳይሆን በሀገር-ዓቀፍ ደረጃ በብቸኝነቱና በደረጃው ላቅ ያለ ስታዲየም ሆኖ ለስፖርት ማሕበረሰቡ  አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

🚧ከ25,000 በላይ የተመልካቾች እንዲሁም 140 ቪ.አይ.ፒ መቀመጫዎችን የመያዝ ዓቅም ያለው ይህ ስታዲየም ከዋናው የእግርኳስ መጫወቻ ሜዳ በተጨማሪ ሁለት የማሟሟቂያ ሜዳዎች እንዲሁም ሌላ የታዳጊዎች መጫወቻ  ሜዳ፣የመሮጫ ትራክ፣የአትሌቲክስ ስፖርት ማከናወኛ ስፍራ፣የቤት ውስጥ ውድድር የሚከናወንበት ቦታዎችን የሚያካትት ሲሆን ከነዚህም በተጨማሪ  መሰብሰቢያ አዳራሽ፣የመልበሻ ክፍሎች፣ካፍቴሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች እንደሚሟሉለት ዲዛይኑ በቀረበበት ወቅት መመልከት ተችሏል፡፡

@etconp
👍11🤣1
🏷አርባ ምንጭ ከተማ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ 10 ከተሞች አንዷ ትሆናለች ተባለ

🚧በአርባ ምንጭ ከተማ በቀጣይ ሶስት ወራት የአረንጓዴ አካባቢዎችን ጨምሮ የመዝናኛ ስፍራዎች እና በዋና ዋና አስፋልት መንገድ በግራና ቀኝ  የማልማት ስራ ተግባራዊ  ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

🚧ከእዚህ በተጨማሪ ከተማዋ ያላትን ተፈጥሯዊ ፀጋ ጥቅም ላይ በማዋል የቱሪስት መስህብ ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ አልሚዎች ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ማርቆስ ማቲዎስ ለብስራት ሬድ ተናግረዋል፡፡

🚧ይህንኑ እውን ለማድረግ ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን ያስታወቁት ከንቲባው ከተማዋን ጨምሮ በዙሪያዋ ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን መጠቀም የሚያስችል ስራ እንደተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

🚧በእዚህም ሂደት የአርባ ምንጭ ከተማን ውበት እና ፈጣን እድገት የሚያመላክቱ የመሰረተ ልማት ስራዎች ግንባታ በማፋጠን ከተማዋን በ2025 በአፍሪካ ከሚገኙ 10 ዋና ዋና ከተሞች አንዷ ለማድረግ ታቅዷል ሲሉ ከንቲባው በተጨማሪነት አንስተዋል፡፡

🚧መንግስትን ጨምሮ መዋለ ነዋያቸውን ፈሰስ በማድረግ ወደ እንቅስቃሴ የገቡ ባለሀብቶች ጋር በመቀናጀት ከተቀመጠው ጊዜ በቀደመ መልኩ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡

Via ናትናኤል ሀብታሙ

@etconp
❤8👍6👏1
🏷የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እያስገነባቸው ያሉ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀቶችን በቅርበት ለመከታተል የሚያስችለውን አዲስ አደረጃጀት በመፍጠር ወደ ስራ እንደገባ የሚታወስ ነው፡፡

🚧በአዲሱ የአደረጃጀት የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤቶቹ የመንገድ ፕሮጀክቶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የተቋቋሙ በመሆናቸው፤ ኘሮጀክቶቹን በቅርበት ለመከታተልና ለመደገፍ አስቻይ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡

🚧በዚህም ረገድ ከተቋቋሙት የኘሮጀክት ጽ/ቤቶች መካከልም የፍጥነት እና ልዩ ፕሮጀክቶች ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ስር የአዳማ አዋሽ ፣ የሞጆ-ሐዋሳ እና የኮይሻ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽ/ቤቶች ይገኛሉ፡፡

🌟የሞጆ-ሐዋሳ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ፅ/ቤት በአጠቃላይ 17,850,833,680.64 በሚሆን የገንዘብ መጠን 6 የመንገድ ፕሮጀክቶችን (በዲዛይንና በጨረታ ሂደት ላይ ያሉትን ሳያካትት) እያስተዳደረ ይገኛል፡፡

🌟በሌላ በኩል የአዳማ-አዋሽ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፅ/ቤት በአጠቃላይ 6,688,456,565.74  በሚሆን የገንዘብ መጠን 1 (በዲዛይንና በጨረታ ሂደት ላይ ያሉትን ሳያካትት) የመንገድ ኘሮጀክት እያስተዳደረ ይገኛል፡፡

💫በዚህም መሰረት  የሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፅ/ቤት እና የአዳማ-አዋሽ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፅ/ቤት  ያካተቷቸውን ፕሮጀክቶች መረጃ  እናስተዋውቃለን፡፡

💫ከታች የተጠቀሱትን ፕሮጀክቶች አስመልክቶ የአካባቢው ህብረተሰብ እና የመስተዳድር አካላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስተያየትና ጥያቄዎችን ለማቅረብ በአዳማ-አዋሽ እንዲሁም በሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካባቢ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽ/ቤት ማምራት እንደምትችሉ እየገለጽን ፣ እነዚህ ጽ/ቤቶች የታለመላቸውን ግብ እንዲመቱ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያሳስባል፡፡

🌟የአዳማ ኪ.ሜ60 የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክ አካባቢ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽ/ቤት መገኛ 📍አድራሻ፡- አዳማ ከተማ  ሞኤንኮ ፊትለፊት

🌟የሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽ/ቤት መገኛ
📍አድራሻ፡- ሻሸመኔ ከተማ  ሲሲሲሲ ካምኘ ውስጥ

@etconp
👍8
@ETCONp 2015 2nd Quarter Rate .Pdf.pdf
24.3 MB
🏷በ2015 ዓ.ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ይፋዊ ቀጥተኛ ዋጋ ተመን (2nd Quarter Construction Works of Direct Cost)

🔑በተለይ የዋጋ ተመን (BOQ - Priced bill of Quantities) ለምታወጡ የዲዛይን አማካሪዎች እና የፕሮጀክት መሐንዲሶች ይጠማችኋል።

💫በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም እንደመነሻ ሀሳብ ይጠቅማችኋል።

📍የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

@etconp
👍8🙏6
🎉📚 BIG NEWS! My new book is finally here! "Get Your Dream Job" is a practical guide that will help you achieve your professional goals. I'll be sharing tried and tested tips and strategies to help you find the right path towards your dream job! 💡

I'll be guiding you step by step through the preparation process, from CV writing to the interview, so you can be confident and ready for any kind of job opportunity. 📈

If you're looking for inspiration and motivation for your career, don't miss this chance! 💪 Take control of your future and order the book now! 📚

💥 Don't miss the opportunity to change your work life forever! 💥 Order now! Available on all Kindle marketplaces.

https://www.amazon.com/dp/B0BTK9B699

@etconp
👍6😱1