👉ያማረ እና አስደሳች 127ኛ የ አድዋ ድል በዓል ይሁንላቹ!
"ጣሊያን በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ!"
⭐️የካቲት 23, 1888 ዓ.ም
❤Victory Of Adwa
@etconp

❤9👍4
👉ለ ውድ የ ቻናላችን ቤተሰቦች
🔖ለ ስራ ቅጥር እና የ ኮንስትራክሽን ጨረታዎች ምታገኙበት ቻናል ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉን።
https://t.me/ETCONpWORK

Telegram
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World
Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK
📩 @Philemona7

👉የ ጣልያን የ2023 የንድፍ ቀን።
⭐️የጣልያን የ2023 የንድፍ ቀንን ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በክሪኤቲቭ ሀብ በ ማርች 9 ቀን 2023 እኤአ ከጠዋቱ 4 ሰአት ተገኝተው ከታዋቂው Guilio Vinaccia ጋር እንዲያሳልፉ ተጋብዘዋል፡፡
🚧Italian Design Day 2023. The event will be held on March 9, at 10 am at the Creative Hub.
Via የጣልያን የባህል ማእከል

👍3
የጥቁር ገበያ የሲሚንቶ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተካሄደ ነው ተባለ።
⚡️በሲሚንቶ ምርት ላይ ያለአግብ ዋጋ በሚጨምሩ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡
⚡️ይሁን እንጂ በመዲናዋ ሲሚንቶ የለም በሚል ምክንያት አንድ ኩንታል ከ1 ሺህ 730 እስከ 1 ሺህ 850 ብር ዋጋ በጥቁር ገበያ በመሸጥ ነው የተባለ ሲሆን ቢሮው ከተቀመጠው ተመን በላይ ሲሸጡ በሚገኙ ነጋዴዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።

👍4🤮1💔1
👉ጎልድ ስታር አቬዬሽን በበኢትዮጵያ ሁለት የሄሊኮፕተር ማረፊያ ለመገንባት ጠየቀ።
⚡️መንግስት የኤርፖርት ግንባታ እና አስተዳደር በግል ባለሀብቶች እንዲያዝ መመሪያ ማዘጋጀቱን ተከትሎ ስምንት ኤርፖርቶች እና የሄሊኮፕተር ማረፊያዎች /heliport/ ለመገንባት ፍላጎት ያሳዩ አልሚዎች ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ማመልከቻ አስገብተዋል፡፡
⚡️ከነዚህም መካከል ሁለቱ በመካነ ሰላም እና ደብረታቦር የነበሩ ጥርጊያ የአየር ማረፊያዎችን /air strip/ መልሶ ለመገንባት የቀረቡ ማመልከቻዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡
⚡️ጎልድስታር አቪዬሽን የተሰኘዉ በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የተሰማራ የግል ኩባንያ በድሬዳዋ እና ሰበታ ከተሞች የሄሊኮፕተር ማረፊያዎች ለመገንባት ማመልከቱም ታውቋል፡፡
እስካሁን ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሲቪል አገልግሎት የሚዉል የሄሊኮፕተር ማረፊያ እንደሌለ ተነግሯል፡፡
Via ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ

👉Dynamic Tower
🚧Floor count: 80
🚧Cost: 1.2 billion USD
🚧Location: United Arab Emirates
🚧Developer: Dynamic Architecture
⭐️Architectural: 420 metres (1,378 ft)
💫Architect: David Fisher
@etconp
🚧Floor count: 80
🚧Cost: 1.2 billion USD
🚧Location: United Arab Emirates
🚧Developer: Dynamic Architecture
⭐️Architectural: 420 metres (1,378 ft)
💫Architect: David Fisher
@etconp
👍1
የአዲስ አበባ መምህራን የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ዕድል መመቻቸቱ ተገለጸ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚተዳደሩ የመንግሥት ትምህር ቤቶች መምህራን ያነሱትን የቤት ጥያቄ ተከትሎ፣ የከተማ አስተዳደሩ መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት መገንባት የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸቱ ተሰምቷል፡፡
በዚሁ መሰረት ቤት የሌላቸው እና በማኅበር ተደራጅተው ቤት መገንባት የሚፈልጉ መምህራን የቤት ምርጫ ፍላጎታቸውን እንዲያሳውቁ በየትምህርት ቤታቸው ፎርም ደርሷቸዋል፡፡በየትምህርት ቤቱ ለሚገኙ መምህራን የደረሰውን ፎርም አዲስ ማለዳ ተመልክታለች፡፡
መምህራኑ በደረሳቸው የቤት ፍላጎት ፎርም፤ ባለ አንድ፣ ባለ ኹለት እና ባለ ሦስት መኝታ ቤት እንደ ምርጫ ቀርቧል፡፡ በፎርሙ ላይም የቤቱ ዋጋ የተገለጸ ሲሆን፣ 60 ካሬ ስፋት ያለው ባለ አንድ መኝታ 900 ሺሕ ብር፣ 75 ካሬ ስፋት ያለው ባለ ኹለት መኝታ 1.12 ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም 105 ካሬ ስፋት ያለው ባለ ሦስት መኝታ ቤት 1.6 ሚሊዮን ብር ዋጋ ተቆርጦለታል፡፡
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ተዘጋጅቶ ለመምህራን የደረሰው የቤት ፍላጎት ማሳወቂያ ፎርም፣ በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ቁጠባ ያላቸው መምራንም የዕድሉ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ያመላክታል፡፡
በማኅበር ተደራጅተው ቤት መገንባት የሚፈልጉ መምህራን፣ የተወሰነ ፐርሰንት ቅድመ ክፍያ ከፍለው ቀሪውን ክፍያ ቤቱ ከተገነባ በኋላ ቤቱን እየኖሩበት ከደመወዛቸው ላይ በየወሩ የሚከፍሉበት ዕድል እንደ አማራጭ መያዙን አዲስ ማለዳ ሰምታለች፡፡ መምህራን ቤቱን ለመገንባት ቅድሚያ ሊከፍሉ ይችላል ተብሎ የተገመተው ቅድመ ክፍያ ከአጠቃይ ከቤቱ ዋጋ ከ10 እስከ 20 በመቶ ያህሉን ሳይሆን እንዳልቀረም ተጠቁሟል፡፡
Via አዲስ ማለዳ

👍15
በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ የሚገኙ አካላትን የአሰራር ሂደት በሚገባ መከታተል እና ቅጣት መጣል የሚያስችል አዲስ መመሪያ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ ዋለ።
እስካሁን ድረስ በስራ ላይ የነበረው የኮንስትራክሽን የቅጣት እና የክትትል መመሪያ የደህንነት ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት የማይችል እንደሆነ እና በዚህም ምክንያት ኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ የሚፈጸሙ የህግ ጥሰቶችን ተከትሎ የሚጣለዉ ቅጣት አነስተኛ እንዲሆን አድርጎትም ነበር ፡፡
በቅጣት አወሳሰንና አተገባበር ላይ የነበሩ ክፍተቶችን ለማስተካከል የቅጣት መመሪያው እንደ አዲስ መሻሻሉን በግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ኢንጂነር ከማል ጀማል ተናግረዋል፡፡
በስራ ላይ የነበረው መመሪያ በባለስልጣኑ ህግ መሰረት መስራት በማይችሉት ላይ አነስተኛ ቅጣት ሲጥል የነበረ እንደሆና በዚህም ምክንያት ተቋራጮችና አሰሪዎች ከህግ ውጪ እንዲሆኑ አድርጎ መቆየቱን አንስተዋል፡፡
አሁን ላይ እንደ አዲስ የተሻሻለዉ መመሪያ ከዚህ ቀደም ተግባራዊ ሲሆን የነበረውን ሂደት በመቀየር የክትትል እና የግምገማ ሂደቱ ይበልጥ ግልጽ የማድረግ አቅም አለው ብለዋል ዳሬክተሩ፡፡
ነባሩ መመሪያ አልሚውን ብቻ የሚቀጣ ሲሆን ይሄኛው መመሪያ አልሚውም፣ ኮንትራክተሩን እና አማካሪውን የጋር ተጠያቂነትን የሚጥልባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ሲተገበር የነበረው መመሪያ አነስተኛ የገንዘብ ቅጣት የሚጥል ሆኖ በመገኘቱና ህገወጥ ድርጊቶች በመበራከታቸዉ መመሪያ ቁጥር 3/2015 በሚል እንደ አዲስ መሻሻሉን ጠቅሰዋል፡፡
Via አዲስ አበበ ከተማ ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን

👍5
👉ቅዱስ ላሊበላ ቤተ ገብርኤል ቤተ መቅደስ መግቢያ ድልድይ እየተሠራ እንደሆነ ተገለጸ።
🚧የቤተ ገብርኤል ቤተ መቅደስ በቅዱስ ላሊበላ ከታነጹት 11 ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ ሲሆን የቤተ መቅደሱ መግቢያ ከቤተልሔሙ የጸሎት ቤት ፊት ለፊት በምሥራቅ በኩል ይገኛል። በሌላ በኩል ከቤተ አማኑኤል ቤተ መቅደስ በሚመጣ ተሻጋሪ ድልድይም መግባት የሚቻል ሲሆን ድልድዮቹ ከዛፍ ግንዶች ርብርብ እንደተሠሩ ርዝመታቸውም 10 ሜትር መሆኑ ይነገራል።
🚧በዛሬው ዕለት ወደ ቤተ ገብርኤል ቤተ መቅደስ መግቢያ ድልድይ በፈረንሣይ ላሊበላ ዲቨሎፕመንት ፕሮጀክት አማካኝነት እየተሠራ እንደሚገኝ የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ አስነብቧል፡፡

👍13💔2
👉ሓሪፍ ናይ ኮንስትራክሽን ቻናል ክንጥቁመኩም ካብ @ETCONp
⭐️ጠቓሚ ናይ ኮንስትራክሽን ፍለጠት ትቐስምሉ🔖
💵ናይ ኮንስትራክሽን ኣቑሑት ሸየጥትን ገዛእትን ዝራኸብሉ
📐ውቁባት ናይ መንበሪ ገዛ ዲዛይን ፕላን ትረኽብሉ🏠
📄ጠቕላላ ናይ ኮንስትራክሽን ሌክቸር ትምህርቲ ብ ኦንላይን ትመሃርሉ🗒
💻ናይ ኮንስትራክሽን ሶፍትዌራት ምስ ሴታኣፖም📀
📙 ኮንስትራክሽን መፅሓፍቲ ብ ቐሊሉ ትረኽብሉ📚
🎬ኮታስ ናይ ኮንስትራክሽን ትምህርቲ ብ ቪድዮታት ዝተሓገዘ ትምህርቲ ንምርካብ ተደልዮም 🎥
🌟አብ ታሕቲ ብዘሎ ሊንክ ናይቲ ቻናል ቤተሰብ ብምዃን ይተሓወሱና 👇
https://t.me/ETCONp

Ethio Construction Engineering
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!
📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT
For Ad:- https://telega.io/c/etconp

👍10
⭐️አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ (proposal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
A) ማውጫ (Table of contents)
ገፁ ከሦስት ከበለጠ ማውጫ ሊዘጋጅለት ይገበዋል፡፡ ማውጫ ሁሉንም ምዕራፎችና ንዑስ ምዕራፎች ያሉበትን ገፅ ባመላከተ መልኩ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
B) አጭር መግለጫ (Executive Summary)
ከግማሽ ገፅ ያልበለጠ ሆኖ ለያካትታቸው ሃሳቦች
☞ ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ያስገደደው ዋና ችግር
☞ፕሮጀክቱ የሚያመጣው ተፅዕኖ
☞ለችግሩ የተቀመጠ መፍተሄ
☞የፕሮጀክት አዋጭነት የሚያመላክት ግምገማ
☞ፕሮጀክቱ የሚያስገኘው ጥቅም
☞ፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠንና የሚወስደው ጊዜ መካተት አለባቸው፡፡
C) መግቢያ (Back Ground)
ከአንድ ገፅ ባልበለጠ መገለፅ ሲገባው የሚያካትታቸው ነጥቦች፡-
☞ ፕሮጀክቱ የሚፈታው ችግር ምን እንደሆነ
☞ ችግሩን ለምን መፍታት እንዳስፈለገው
☞ ስለፕሮጀክቱ አጠር ያለ ማብራሪያ የሚሉትን ይይዛል፡፡
D) ፕሮጀክቱ የሚመልሳቸው ችግሮች (Rationale)
ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ምክንያት የሆኑ ነገሮች ተሰርተው መገለፅ አለባቸው በተጨማሪም የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግብ ለአንባቢው ግልፅ በሆነ መንገድ መስፈር አለበት፡፡
E) የፕሮጀክቱ ዓላማ (project objective)
ፕሮጀክቱ ሊሰራበት የሚችሉ ዋናውንና ዝርዝር ዓላማዎች ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ሊያስገኘው ይችላል ተብሎ የታሰበውን ወጤት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡
F) የፕሮጀክቱመግለጫ (project Description):-
☞ የፕሮጀክቱ ስያሜና ዓላማ
☞ ጉዳዮን የሚያስረዳ ገለፃ
☞ የፕሮጀክቱ ቀጣይነት
☞ የፕሮጀክተ የሚተገበርበት ስልት
☞ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችና የፕሮጀክቱን የግዜ ሰሌዳ ከአስር ገፅ ባልበለጠ መገለፅ አለበት፡፡
G) የፕሮጀክቱ አመራርና አደረጃጀት (project management and organization):-
☞ ፕሮጀክቱን የሚመሩቱና የሚሳተፉ
☞ የባለሙያዎችን ኃላፊነትና ተግባር
☞ የፕሮጀክቱን ውስጣዊ አሰራር አደረጃጀት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም መግለፅ አለበት፡፡
H) የፕሮጀክቱ ያገባኛል ባዮችና ተጠቃሚዎች (stakeholders and Beneficiaries):-
☞ ተጠቃሚዎች (Beneficiaries) ማለት በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሚሆኑትን ይገልፃል፡፡
☞ ያገባኛል ባዮች (stakeholders):-
የመጀመሪያ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (Primary stake holders)፡-በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአሉታዊም ሆነ በአወንታዊ ተፅዕኖ የሚደርስባቸው ወይም በፕሮጀክቱ ላይ የሚያደርሱትን ያካትታል፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (secondary stake holders)፡- ለፕሮጀክቱ መሰራት የራሳቸው ድርሻና ተፅዕኖ ያላቸው ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ተቋማት ተለይተው መዘርዘር አለባቸው፡፡
I) የፕሮጀክቱ ትግበራ (project implementation):-
የፕሮጀክት ዕቅድ ማለት የሚሰሩት ስራዎች፤ ስራውን ለመስራት የሚያስፈልጉ የሀብት ድልድል፤ ስራው በማን፤ እንዴት፤ መቸና የት እንደሚፈፀም መገለፅ አለበት፡፡
J) ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋትና በጎ ጎኖች (Risk and Assumption):-
☞ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብሎ የሚታሰቡ ስጋቶች ይገለፁበታል፡፡
☞ ለፕሮጀክቱን ተፈፃሚነት የሚያፋጥኑ፤ የሚረዱ በጎ ጎን ያላቸው ነገሮች አብራርቶ በሰንጠረዥ መገለፅ አለበት፡፡

👍15❤2🥰1
የኮንስትራክሽን ማሽነሪ
✨✨✨✨✨✨✨
👉 ሚክሰር
👉 ቫይብሬተር
👉 ሊፍት
👉 ጀነሬተር የተለያዩ ማሽነሪ አካሪዬ እና ሻጮች ካላችሁ
@Etconpworks ላይ ማናገር ትችላችሁ
@etconpwork
✨✨✨✨✨✨✨
👉 ሚክሰር
👉 ቫይብሬተር
👉 ሊፍት
👉 ጀነሬተር የተለያዩ ማሽነሪ አካሪዬ እና ሻጮች ካላችሁ
@Etconpworks ላይ ማናገር ትችላችሁ
@etconpwork
👍1
👉የግንባታ፣የዕቃና አገልግሎቶች ግዥ product catalogue፣ የ Item definition እና በኢ-ጂፒ ሲስተም Specification የማዘጋጀት ጉዳይ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ ተገለፀ።
🚧በኢ-ጂፒ ሲስተም የግንባታ፣ የዕቃና አገልግሎት ግዥዎችን በቀላሉ ግብይት መፈፀም እንድንችል የፕሮዳክት ካታሎግ የማዘጋጀት፣ አይተሞችን ዲፋይን የማድረግ እና የእቃ መዘርዝር (Specification) ማዘጋጀት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ክቡር አቶ ወልደአብ ደምሴ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ገለፁ።
🚧በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲ ያዘጋጀው የኢ-ጂፒ ሲስተም የግንባታ፣የዕቃና አገልግሎቶች ግዥ Item Definition, Classification, Mapping and Specification of goods and services as per UNSPSC standard በማቅረብ በባለድረሻ አካላት ግምገማ ተደርጎበታል።
🚧በግምገማው ወቅት የተገኙት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ለኢ-ጂፒ ሲስተም የተዘጋጀው የግንባታ፣የዕቃና አገልግሎቶች ግዥ (Item Definition, Classification, Mapping and Specification of goods and services as per UNSPSC standard ) ስራን የሚያቀል ግዥን በቀላሉ መፈፀም የሚያስችል በመሆኑና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ በመሆኑ በሁላችንም የጋራ ጥረት ከግብ ልናጀርስ ይገባናል ብለዋል።
🚧በዩኒቨርስቲው በኩል የተሰራውን ስራ ያብራሩት ዶክተር ቀፀላ ሀይሉ ስራው አለም አቀፍ አሰራሮችን የተከተለና አለም አቀፍ ተሞከሮዎችን መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልፀው የUNSPSC የአሰራር ስርዓትን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።
🚧በሀገር ደረጃ ከIFMIS፣ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ አሰራሮችን መጋራቱን ገልፀዋል እንዲሁም ከ29ሺህ በላይ ቁሳቁሶች ካታሎግ የተዘጋጀላቸው መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።
Via መግንባ

👍7❤1
👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በሚገኙ ሕንጻዎች ላይ የንብረት ታክስ ለመጣል የሕንጻ ቆጠራ መጀመሩን ሪፖርተር ዘግቧል።
🚧በሕንጻ ቆጠራው፣ ግንባታቸው የተጠናቀቁና ገና ያልተጠናቀቁ ሕንጻዎች መካተታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
🚧ከሁለት ሳምንት በፊት አንድ ፎቅና ከዚያ ባላይ ባላቸው ሕንጻዎች ላይ የተጀመረው የመጀመሪያው ዙር የሕንጻ ቆጠራ፣ በሦስት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል የሕንጻ ቆጠራውን የሚያካሂደው፣ የአስተዳደሩ የሕንጻ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ሰጪ ባለሥልጣን እንደሆነ ዜና ምንጩ አመልክቷል።
🚧ባለሥልጣኑ፣ በሁለተኛው ዙር ቆጠራ ቪላዎችንና ሌሎች የመኖሪያ ቤቶችን የመቁጠር ዕቅድ እንዳለው ዜና ምንጩ ጨምሮ ዘግቧል።
Via ዋዜማ ራድዮ