Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉በአማራ ክልል የሪል ስቴት ልማት ፕሮጀክቶች የሚስተናገዱበት መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ

በአማራ ክልል በሪል ስቴት ልማት የሚሳተፉ ባለሀብቶች የመንግሥትን የቤት ልማት አቅጣጫን በመከተል በመኖሪያ ቤት ልማት ላይ ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግና ሕግን እና ስርዓትን ተከትለው የልማቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ የሪልስቴት ልማት የሚተዳደርበት እና የሚመራበት ሕግ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ የክልሉ ከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በተጨማሪም በሪልስቴት ፕሮጀክቶች መሳተፍ ለሚፈልጉ አካላት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ብሎም የከተማ ነዋሪዎች በራሳቸው የይዞታ ቦታ ላይ የከተማዉ የአካባቢ ልማት እቅድ የሚፈቅድ ከሆነ አፓርታማ በቅንጅት ወይም በተናጥል ለማልማት የሚፈልጉትን አካላትን ለማስተናገድ እና ቤት የሚያስተላልፉበትን አሰራር መዘርጋት በማስፈለጉ መመሪያው እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ነገር ግን ከሰሞኑ በአንዳንድ የአማራ ክልል ከተሞች ከሪል ስቴት ልማት ጋር በተያያዘ የሪል ስቴት ፕሮጀክቶች ተመልምለው ቦታ ሊያገኙ ነው በሚል የሚናፈሰው ወሬ ዉሸት በመሆኑ፣ በክልሉ የሪል ስቴት ልማት ፕሮጀክቶች የሚስተናገዱበት ስርዓት በመመሪያ ፀድቆ ሥራ ላይ እስኪውል ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው አሳስቧል፡፡

በከተሞች ልዩ ክልላዊ ወይንም አገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች ሆነው በምደባ እንዲተላለፉ ተመልምለው፣ ውሳኔ የተሰጣቸውና አዲስ የሚቀርቡ ፕሮጀክቶች ወደፊትም እንዲሰጥባቸው የሚቀርቡ የሪልስቴት ፕሮጀክቶችን ወጥና ስርአት ባለው መንገድ ለመምራት ይቻል ዘንድ ኹሉም ከተሞችና ዞን አስተዳደሮች መመሪያው ጸድቆ ስራ ላይ እስኪውል ድረስ ምንም አይነት የሪልስቴት ፕሮጀክት ወደ ቢሮው እንዳይልኩ አሳስቧል፡፡

Via Addis maleda

@etconp
👍7
ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የሚገነባው የህክምና መስጫ ተቋም

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በመንግስት በተመደበ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አዲሱ ገበያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ባለ አሥራ አምስት ወለል ሕንፃ ለማሠራት የሚያስችለውን እንቅስቃሴ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ህንፃው ለአዲስ አበባ የቃጠሎ፣ የድንገተኛ እና የአደጋ ሕክምና መስጫ ሆስፒታል /አቤት ሆስፒታል/ አገልግሎት የሚውል ሲሆን ሕንፃው ከሚይዛቸው ወለሎች መካከል አራቱ ከምድር በታች ሲሆኑ የቀሩት አሥራ አንዱ ደግሞ ከምድር በላይ ናቸው፡፡

ሕንፃው ሲጠናቀቅ ደረጃቸውን የጠበቁ 18 የቀዶ ሕክምናና 40 የማገገሚያ ክፍሎች፣ እንዲሁም ከ700 በላይ አልጋዎች ይኖሩታል፡፡ በተጨማሪም  ከምድር በታች ከሚገኙት ወለሎች መካከል ሁለቱ ለየት ያሉ አገልግሎቶች እንዲሰጡ ታስቦ ተዘጋጅተዋል፡፡

የሕንፃው መጨረሻ ፎቅ ላይ ለሄሊኮፕተር ማሳረፊያ የሚውል ቦታ ያለውና ለአስተዳደርና ለልዩ ልዩ ሥራዎች ማከናወኛ የሚውሉ  በርካታ ክፍሎች ያሏቸው ሁለት ብሎኮች ከሕንፃው ጋር ተያይዘው ዲዛይን ተደርገዋል ተብሏል፡፡

@etconp
👍15❤1
👉What is a cover block or spacer?

🌟Concrete Cover Blocks is also known as Spacers which is used to provide spacing at Slab, Column, Beam & foundation.

🚧Application is very simple
as place COVER BLOCK between Rebar (Reinforcement bar) and ground/wall.

🚧Spacers are used to provide specific height for your concrete reinforcement structure before pouring.

@etconp
❤5🏆1
👉For the construction of a house, among other factors, the following requirements must be satisfied:

1. A site on which to build the house,
2. Permission from local authorities to build the house,
3. Materials for building the house,
4. skilled laborers for the erection of the house,
5. Financial source and
6. Professionals, such as architects and engineers.

🚧As each one of these requires money, the financial aspect is therefore very important and the costs must always be considered during all the planning and building stages. However, this does not mean that it is always economical to save money or build cheaply. "The poorest often builds the dearest" is too often proven true.

https://telegram.me/ETCONpWORK
👍2
EiABC (Ethiopian Institute of Architecture, Building Construction and City development)

The chair of Appropriate Building Technology (#ABT) recently led a site visit for EiABC Architecture students to the HQ of the Horn of Africa Regional Environmental Center located inside Gulele Botanic Garden.
This LEED®Gold Green certified building is the first of its kind in Ethiopia and showcases impressive sustainable design features. The building is a net-zero structure constructed using locally sourced materials, such as Adobe and Glued Laminated Timber. The roof structures are made of round timber frames, and the building also boasts green roofs, which are eco-friendly and climate-conscious.

#architecture #sustainability
❤8👍2
👉የግንባታ ኦዲት (Construction Audit) ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

ከተለያዩ የፋይናንሽያልና የክዋኔ ኦዲት ዳይሬክቶሬቶች ለተወጣጡ የኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ከፍተኛ ኦዲተሮች በግንባታ ኦዲት (Construction Audit) ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው ከሚያዚያ 3-18 /2015 ዓ.ም በስራ አመራር ኢንስቲቲዩት በሁለት ዙር የተሰጠ ሲሆን በጥቅሉ ከከፍተኛ ኦዲተርነት እስከ የኦዲት ዳይሬክተር ያሉ 195 የሚሆኑ ሰልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡

ስልጠናው ለኦዲተሮች በግንባታ ግዥ ስርዓትና የውል አስተዳደር፣ በግንባታ ጥራት አጠባበቅ ሂደቶች እንዲሁም በግንባታ ኦዲት የስጋት ዳሰሳ ዙሪያ ግንዛቤን ያስጨበጠና በተሻለ አቅም ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የግንባታ ዘርፉ እጅግ እያደገና ውስብስብ እየሆነ እንደመምጣቱና ከፍተኛ በጀት የሚንቀሳቀስበት እንደመሆኑ ስልጠናው የተለያየ የልምድ ልውውጥ የተደረገበትና በዘርፉ ለሚደረግ የኦዲት ስራም ጠቃሚ ግብዓት የተገኘበት መሆኑን በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የገለጹት ሰልጣኞቹ በቀጣይም ተመሳሳይ ስልጠናዎችን የመስጠቱ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

መ/ቤቱ ለስልጠናዎችና ግንዛቤ ማስጨበጫዎች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በየጊዜው በተለያዩ ዘርፎችና ደረጃዎች ለሚገኙ የመ/ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለባለድርሻ አካላት ጭምር ተከታታይ የሆኑ ተገቢ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡

@etconp
👍3
👉ትምህርታዊ ንግግር

✨ፕሮፌሰር ማርኮ ዲ ኑንዚዮ
ቦታ ኢአይኤቢሲ፣ ስዊድን እልፍኝ (ስዊድሽ ፓቪልዮን) ሰአት ከቀትር በኋላ በ 11፡00 ሰዐት ሚያዝያ 25 2015

✨ፕሮፌሰር ማርኮ በእንግሊዝ አገር በሚገኘው የበርሚንግሀም ዩኒቨርስቲ መምህር ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ የኖረ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ማህበራዊ ህይወት ላይ በጥልቅ የጻፈ፣ እንዲሁም የተመራመረ ምሁር ነው፡፡

📍በሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓም በ EIABC “ከተማን ማወቅ” በሚል ር እስ ትምህርታዊ ንግግር ያቀርባል፡፡

🌟ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡

Via Chair of Basic Architecture and Design, EiABC

@etconp
👌5❤1👍1
Innovative structure combining the outrigger system with rigid SLB dissipators for slender tall buildings.
The outrigger systems is a structural systems used for skyscrapers that has gained popularity for the past 20 years. In this building the innovation is the combination of the stiff SLB devices in a serial spring configuration with the concrete outriggers. The advantages of this solution are many such as:
- The force in the SLB devices is precisely predetermined so the forces transferred between the outriggers and the structural column are limited and known.

@etconp
❤3👍2
Ethio Construction Engineering
Innovative structure combining the outrigger system with rigid SLB dissipators for slender tall buildings. The outrigger systems is a structural systems used for skyscrapers that has gained popularity for the past 20 years. In this building the innovation…
The SLB devices are stiff dissipators that in a configuration of springs in sere prevent losing rigidity
- The SLB devices dissipate energy through yielding, protecting the main structure from damage in strong earthquakes
For this particular building the addition of the outriggers equipped with SLBs reduced the main structural period from about T1=7s to T1=6s. This stiffness increment allowed to eliminate half the number of the perimeter columns which end up in about 20kg/m2 corrugated steel reinforcement ratio.

(Render and Architecture from Sordo Madaleno)

@econp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432
❤4👍1
👉China defies Japan and enters the Guinness Book of Records by building a 57 storey building in just 19 days.

🌟the power of Chinese engineering 🇨🇳👷

@etconp
👍17
ባለፉት 9 ወራት 194 ግንባታዎችን በማጠናቀቅ  ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ እንደተቻለ ተመላከተ፡፡

የቢሮው ዋነኛ ተግባር የሆነው የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታን በተመለከተ በቢሮ ደረጃ 24 እንዲሁም በክፍለከተማ 170 ግንባታዎችን ባለፉት 9 ወራት ማጠናቀቅ እንደተቻለ ቢሮው በ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የከተማዋን መሪ ፕላን መሰረት ያደረገ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ከመገንባት አንፃር በማዕከልና በክፍለከተማ ለ228 ፕሮጀክቶች ዲዛይን ማዘጋጀት ከመቻሉም ባሻገር ለ205 ፕሮጀክቶች የአዋጪነት ጥናት ስራ እንደተሰራ  ሪፖርቱ ያትታል፡፡

ተያይዞም በጊዜ ማዕቀፉ በቢሮው የተከናወኑ የምህንድስና ግዢ ስራዎችን በተመለከተ 184 የውል ሰነድ የማዘጋጀትና ውል የማዋዋል ተግባር እንደተከናወነና   9 የግልፅ እንዲሁም  7 የውስን ጨረታ ሰነዶች ማዘጋጀት እንደተቻለ በሪፖርቱ  ተጠቁሟል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዓቅም ከማሳደግ አንፃር በዘጠኝ ወራቱ ለ1,229 ስራ ተቋራጮች፣አማካሪዎችና ሞያተኞች  በ16 የስልጠና ርዕሶች ዙሪያ የዓቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት እንደተቻለና ከተለያዩ ተቋማት እንዲሁም ከቢሮው ዘርፍና ዳይሬክቶሬቶች ለመጡ 4,683 የግንባታ ግብዓት የዋጋ ተከላ ጥያቄዎች ምላሽ ከመስጠት ባሻገር 3 ጊዜ የግንባታ ግብዓት ላይ ወቅታዊ ጥናት በማድረግ መረጃው በወቅቱ ተደራሽ እንደተደረገ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የግብዓት ፍተሻ በማከናወን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ክትትልን ለማሻሻል ከሚሰሩ ስራዎች ውስጥ 6,695 አይተሞች በቤተሙከራ በመፈተሽ ውጤቱን ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ ስራ እንደተሰራ ሪፖርቱ ይገልፃል፡፡

ተያይዞም በጊዜ ማዕቀፉ በማዕከል ደረጃ 65 እንዲሁም በክፍለከተማ ደረጃ 319 በአጠቃላይ 384 በመንግስት በጀት የሚገነቡ ፕሮጀክቶች ላይ የክዋኔና ፋይናንሺያል ኦዲት ስራዎችን እንደተሰሩና  በዚህም በማዕከል 4.2 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም በክፍለከተማ 443,600.43 ብር የኦዲት ግኝት መገኘቱን ከቀረበው ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቢሮው ትኩረት እየሰጠው ከሚገኘው የስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በዘርፉ  ለ15,941 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በመፍጠር ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር ማሳካት እንደተቻለ የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም

@etconp
👍6❤2🙏2
220213_0819
My Recording
ሚያዝያ 21-22 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከ300 በላይ ከንቲባዎችና ርዕሳነ መስተዳሮች ተሳታፊ የሚሆኑበት ፎረም እንደሚጀመር ሰምተናል፡፡ ይህንን የሰማነው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በትላንትናው ዕለት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

በመግለጫቸው ላይም በ2013 ዓ.ም የተመሰረተው የከንቲባዎች ፎረምም ከተሞችን ለማነቃቃትና የውድድር መንፈስን በመፍጠር ለከተሞች የተሻለ ዕድገትን ለማምጣት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውና ሌሎችን ጉዳዮች በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው የከንቲባዎች ፎረም የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተም ከዛሬ ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ  ከ300 በላይ የሚሆኑ የሀገራችን ከንቲባዎች እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ወደ መዲናችን አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ የከንቲባዎች ፎረም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ጋር በመሆን በጋራ የሚያዘጋጁት መድረክ ነው፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም የከንቲባዎች ፎረም አስመልክቶ  የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታተሉት።

@etconp
👍7❤1🏆1
👉ቁጥሮች 28 ቢልዮን ዶላር❗️

ከ 3 ወር በፊት ለተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች በሰላም ስምምነቱ ዙርያ በመንግስት ገለፃ ተደርጎላቸው ነበር።

በገለፃው ላይ [በሰሜኑ ጦርነት] "በአነስተኛ ግምት 28... ቢልዮን ዶላር ጠፍቷል... 28 ቢልዮን ዶላር ምን እንሰራበት ነበር?" የሚል ንግግር ተካቷል።

እርግጥ ነው ከጠፋው ህይወት ይልቅ የባከነ ገንዘብ ብዙም አያሳስብም፣ ቀጣይ ትውልድም ቢሆን ሰርቶ ይመልሰዋል። ግን ደግሞ 28 ቢልዮን ዶላር ማለት:

⏺ቢያስ 5፣ ቢበዛ 6 የህዳሴ ግድብን የሚያክሉ ግዙፍ ግድቦችን ለመገንባት ያስችል ነበር፣

⏺ብዛታቸው ዘጠና አራት (94) የሆኑ ሌሎች የሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክን የሚያክሉ ፕሮጀክቶችን ይገነባ ነበር፣ 

⏺ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ130 በላይ አዳዲስ ኤርባስ A-350 ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ያስችል ነበር፣

⏺(በ2020 ግምት መሰረት) ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ እዳ ሙሉ ለሙሉ ከፍሎ 100 ሚልዮን ዶላር "ለሻይ" ይተርፍ ነበር። 

⏺ከሁሉም በላይ ደግሞ ከ17 ሚልዮን በላይ ዜጎቻችንን ከድህነት ወለል ለማውጣት የሚያስችሉ ትናንሽ የቢዝነስ እድሎችን መፍጠር ያስችል ነበር።

"ጽድቅ እና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም፣
ከጦርነት ሰላም ሳይሻል አይቀርም።"

ጦርነት ክፉ ነው። በደቡብም፣ በሰሜንም... በምስራቅም፣ በምዕራብም ሰላም ለሀገራችን 🇪🇹

Via Elias Meseret

@etconp
👍24😢6
ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን በተጀመረው ፍጥነት አጠናቆ ለነዋሪው ማስረከብ ይገባል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቦሌ ክ/ከተማ ቦሌ ቡልቡላ 20/80 እና 40/60 ነባር ሳይቶችን እና የየካ ክ/ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤቶች ላይ የመስክ ጉብኝት አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴው በቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም 20/80 ነባር ሳይቶች ለነዋሪዎች ተላልፈው የተወሰኑ ነዋሪዎች የገቡ ሲሆን አንዳንድ መጠናቀቅ ያለባቸው የተንጠባጠቡ ስራዎች ማለትም ሊፍት ገጠማ ፤ የሮቶ ከመስመር ጋር ያለማገናኘት እና ዋተር ፖምፕ አለመገጠም ፤ አንዳንድ ደረጃዎች የብረት ስራ አለመጠናቀቅ ሲሆኑ በአስቸኳይ መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ አሳስቧል።

ኢ/ር ቶማስ ደበሌ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር እየተሰሩ ያሉ የጋራ መኖሪያ ነባር ግንባታዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ያሉ ችግሮችን ተቋቁመው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሳይቱ የታዩትን ችግሮች በመለየት አመራሩ ተግቶና ጠንክሮ በመስራት እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ተጠናቀው ለነዋሪው መረከብ እንዳለባቸው የጋራ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ሌላው የየካ ክፍለ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤትን ጉብኝት ሲያደርጉ ቋሚ ኮሚቴው በኮንዶሚኒየም ፣በቀበሌና ንግድ ቤቶች ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎች አንስቷል። የጽ/ቤት ኃላፊውና የሚመለከታቸው አካላቶችም ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥተዋል ።

በክ/ከተማው ስር የሚገኙ 17,474 ቤቶች ወደ ሲስተም ገብተው የተመዘገቡ መሆናቸውንም ተመልክቷል።

በሌላ በኩል ቋሚ ኮሚቴው የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች የሚተላለፉበትን አሰራር የፈተሸ ሲሆን በልዩ ሁኔታ ከሚሰጣቸው ውጭ የተሻለ አሰራር ተከትሎ እንደሚሰራ ከተቋሙ ዳይሬክተር እና ከፋይሎች መረዳት ተችሏል ።

በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳሲ የተከበሩ ወ/ሮ ኒኢመታላህ ከበደ የቤቶች ፋይል ወደ ሲስተም መግባቱን እና በ13ተኛው ዙር የወጡ ቤቶች ተለይተው መያዛቸው እንደ ጠንካራ ጎን አንስተው ፤ ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን በተጀመረው ፍጥነት አጠናቆ ለነዋሪው ማስረከብ እንደሚገባና የነዋሪው ቅሬታ በአግባቡ መፈታት እንዳለበት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ባህላችንም መሻሻል እንደሚገባው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

Via AAHAB

@etconp
👍5