Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉China defies Japan and enters the Guinness Book of Records by building a 57 storey building in just 19 days.

🌟the power of Chinese engineering 🇨🇳👷

@etconp
👍17
ባለፉት 9 ወራት 194 ግንባታዎችን በማጠናቀቅ  ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ እንደተቻለ ተመላከተ፡፡

የቢሮው ዋነኛ ተግባር የሆነው የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታን በተመለከተ በቢሮ ደረጃ 24 እንዲሁም በክፍለከተማ 170 ግንባታዎችን ባለፉት 9 ወራት ማጠናቀቅ እንደተቻለ ቢሮው በ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የከተማዋን መሪ ፕላን መሰረት ያደረገ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ከመገንባት አንፃር በማዕከልና በክፍለከተማ ለ228 ፕሮጀክቶች ዲዛይን ማዘጋጀት ከመቻሉም ባሻገር ለ205 ፕሮጀክቶች የአዋጪነት ጥናት ስራ እንደተሰራ  ሪፖርቱ ያትታል፡፡

ተያይዞም በጊዜ ማዕቀፉ በቢሮው የተከናወኑ የምህንድስና ግዢ ስራዎችን በተመለከተ 184 የውል ሰነድ የማዘጋጀትና ውል የማዋዋል ተግባር እንደተከናወነና   9 የግልፅ እንዲሁም  7 የውስን ጨረታ ሰነዶች ማዘጋጀት እንደተቻለ በሪፖርቱ  ተጠቁሟል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዓቅም ከማሳደግ አንፃር በዘጠኝ ወራቱ ለ1,229 ስራ ተቋራጮች፣አማካሪዎችና ሞያተኞች  በ16 የስልጠና ርዕሶች ዙሪያ የዓቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት እንደተቻለና ከተለያዩ ተቋማት እንዲሁም ከቢሮው ዘርፍና ዳይሬክቶሬቶች ለመጡ 4,683 የግንባታ ግብዓት የዋጋ ተከላ ጥያቄዎች ምላሽ ከመስጠት ባሻገር 3 ጊዜ የግንባታ ግብዓት ላይ ወቅታዊ ጥናት በማድረግ መረጃው በወቅቱ ተደራሽ እንደተደረገ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የግብዓት ፍተሻ በማከናወን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ክትትልን ለማሻሻል ከሚሰሩ ስራዎች ውስጥ 6,695 አይተሞች በቤተሙከራ በመፈተሽ ውጤቱን ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ ስራ እንደተሰራ ሪፖርቱ ይገልፃል፡፡

ተያይዞም በጊዜ ማዕቀፉ በማዕከል ደረጃ 65 እንዲሁም በክፍለከተማ ደረጃ 319 በአጠቃላይ 384 በመንግስት በጀት የሚገነቡ ፕሮጀክቶች ላይ የክዋኔና ፋይናንሺያል ኦዲት ስራዎችን እንደተሰሩና  በዚህም በማዕከል 4.2 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም በክፍለከተማ 443,600.43 ብር የኦዲት ግኝት መገኘቱን ከቀረበው ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቢሮው ትኩረት እየሰጠው ከሚገኘው የስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በዘርፉ  ለ15,941 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በመፍጠር ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር ማሳካት እንደተቻለ የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም

@etconp
👍6❤2🙏2
220213_0819
My Recording
ሚያዝያ 21-22 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከ300 በላይ ከንቲባዎችና ርዕሳነ መስተዳሮች ተሳታፊ የሚሆኑበት ፎረም እንደሚጀመር ሰምተናል፡፡ ይህንን የሰማነው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በትላንትናው ዕለት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

በመግለጫቸው ላይም በ2013 ዓ.ም የተመሰረተው የከንቲባዎች ፎረምም ከተሞችን ለማነቃቃትና የውድድር መንፈስን በመፍጠር ለከተሞች የተሻለ ዕድገትን ለማምጣት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውና ሌሎችን ጉዳዮች በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው የከንቲባዎች ፎረም የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተም ከዛሬ ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ  ከ300 በላይ የሚሆኑ የሀገራችን ከንቲባዎች እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ወደ መዲናችን አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ የከንቲባዎች ፎረም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ጋር በመሆን በጋራ የሚያዘጋጁት መድረክ ነው፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም የከንቲባዎች ፎረም አስመልክቶ  የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታተሉት።

@etconp
👍7❤1🏆1
👉ቁጥሮች 28 ቢልዮን ዶላር❗️

ከ 3 ወር በፊት ለተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች በሰላም ስምምነቱ ዙርያ በመንግስት ገለፃ ተደርጎላቸው ነበር።

በገለፃው ላይ [በሰሜኑ ጦርነት] "በአነስተኛ ግምት 28... ቢልዮን ዶላር ጠፍቷል... 28 ቢልዮን ዶላር ምን እንሰራበት ነበር?" የሚል ንግግር ተካቷል።

እርግጥ ነው ከጠፋው ህይወት ይልቅ የባከነ ገንዘብ ብዙም አያሳስብም፣ ቀጣይ ትውልድም ቢሆን ሰርቶ ይመልሰዋል። ግን ደግሞ 28 ቢልዮን ዶላር ማለት:

⏺ቢያስ 5፣ ቢበዛ 6 የህዳሴ ግድብን የሚያክሉ ግዙፍ ግድቦችን ለመገንባት ያስችል ነበር፣

⏺ብዛታቸው ዘጠና አራት (94) የሆኑ ሌሎች የሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክን የሚያክሉ ፕሮጀክቶችን ይገነባ ነበር፣ 

⏺ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ130 በላይ አዳዲስ ኤርባስ A-350 ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ያስችል ነበር፣

⏺(በ2020 ግምት መሰረት) ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ እዳ ሙሉ ለሙሉ ከፍሎ 100 ሚልዮን ዶላር "ለሻይ" ይተርፍ ነበር። 

⏺ከሁሉም በላይ ደግሞ ከ17 ሚልዮን በላይ ዜጎቻችንን ከድህነት ወለል ለማውጣት የሚያስችሉ ትናንሽ የቢዝነስ እድሎችን መፍጠር ያስችል ነበር።

"ጽድቅ እና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም፣
ከጦርነት ሰላም ሳይሻል አይቀርም።"

ጦርነት ክፉ ነው። በደቡብም፣ በሰሜንም... በምስራቅም፣ በምዕራብም ሰላም ለሀገራችን 🇪🇹

Via Elias Meseret

@etconp
👍24😢6
ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን በተጀመረው ፍጥነት አጠናቆ ለነዋሪው ማስረከብ ይገባል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቦሌ ክ/ከተማ ቦሌ ቡልቡላ 20/80 እና 40/60 ነባር ሳይቶችን እና የየካ ክ/ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤቶች ላይ የመስክ ጉብኝት አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴው በቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም 20/80 ነባር ሳይቶች ለነዋሪዎች ተላልፈው የተወሰኑ ነዋሪዎች የገቡ ሲሆን አንዳንድ መጠናቀቅ ያለባቸው የተንጠባጠቡ ስራዎች ማለትም ሊፍት ገጠማ ፤ የሮቶ ከመስመር ጋር ያለማገናኘት እና ዋተር ፖምፕ አለመገጠም ፤ አንዳንድ ደረጃዎች የብረት ስራ አለመጠናቀቅ ሲሆኑ በአስቸኳይ መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ አሳስቧል።

ኢ/ር ቶማስ ደበሌ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር እየተሰሩ ያሉ የጋራ መኖሪያ ነባር ግንባታዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ያሉ ችግሮችን ተቋቁመው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሳይቱ የታዩትን ችግሮች በመለየት አመራሩ ተግቶና ጠንክሮ በመስራት እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ተጠናቀው ለነዋሪው መረከብ እንዳለባቸው የጋራ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ሌላው የየካ ክፍለ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤትን ጉብኝት ሲያደርጉ ቋሚ ኮሚቴው በኮንዶሚኒየም ፣በቀበሌና ንግድ ቤቶች ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎች አንስቷል። የጽ/ቤት ኃላፊውና የሚመለከታቸው አካላቶችም ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥተዋል ።

በክ/ከተማው ስር የሚገኙ 17,474 ቤቶች ወደ ሲስተም ገብተው የተመዘገቡ መሆናቸውንም ተመልክቷል።

በሌላ በኩል ቋሚ ኮሚቴው የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች የሚተላለፉበትን አሰራር የፈተሸ ሲሆን በልዩ ሁኔታ ከሚሰጣቸው ውጭ የተሻለ አሰራር ተከትሎ እንደሚሰራ ከተቋሙ ዳይሬክተር እና ከፋይሎች መረዳት ተችሏል ።

በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳሲ የተከበሩ ወ/ሮ ኒኢመታላህ ከበደ የቤቶች ፋይል ወደ ሲስተም መግባቱን እና በ13ተኛው ዙር የወጡ ቤቶች ተለይተው መያዛቸው እንደ ጠንካራ ጎን አንስተው ፤ ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን በተጀመረው ፍጥነት አጠናቆ ለነዋሪው ማስረከብ እንደሚገባና የነዋሪው ቅሬታ በአግባቡ መፈታት እንዳለበት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ባህላችንም መሻሻል እንደሚገባው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

Via AAHAB

@etconp
👍5
👉 ከ ታሪክ ማህደር በ Building Codes ዙርያ

🌟Building Codes - የሚገነቡ ህንፃዎች ማሟላት የሚገባቸውን እስታንዳርዶች የያዘ የህጎች ስብስብ ነው፡፡

⏺ህንፃዎች የግንባታ ፍቃድን ለማግኘት Building Code መከተል አለባቸው::

⏺የእስታንዳርዶቹ አስፈላጊነትም - ሴፍቲ ፤ ጤና እና ጠቅላላ የህንፃውን ደህንነት ( Structural , Mechanical , Sanitary , Fire resistance, Earth quake, Flood , Water Supply, Light, Ventilation, ወዘተ ) ለማረጋገጥ ነው::

▶️ለማችን ላይ EBCS,Eurocode , IS, BS, ወዘተ የምንላቸው የህንጻ ኮዶች ኣሉ፡፡

▶️የኛ ደሞ EBCS(Ethioian building code of standards) ይባለል።

🚧ከላይ የምትመለከቱት ህንፃ በሃገረ ሩሲያ ሙሉ ለሙሉ ከእንጨት ተገንበቶ የነበረ ረጅም ህንፃ ሲሆን Fire resistance standard ባለሟሟላቱ የአካባቢው ባለስልጣናት አፍርሰውታል፡፡

@etconp
👍6❤1
🌟 በመጀመሪያ ለምታደርጉልን ትብብር እያመሰገንን ለ msc ፕሮግራም ጥናታዊ ጽሁፍ የሚሆን መጠይቅ እንድትሞሉልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን ።

🌟 ADDIS ABABA SCIENCE AND TECHNOLOGY UNIVERSITY
COLLEGE OF ARCHITECTURE AND CIVIL ENGINEERING DEPARTMENT OF CIVIL ENGINEERING; CONSTRUCTION TECHNOLOGY AND MANAGEMENT

🏗 Questionnaire Survey for MSc Thesis on the title of; Assessment of challenges on sustainable construction practices in building construction projects in Addis Ababa.

https://docs.google.com/forms/d/1wpBgBvIx5Nze2gRqN-a1uiiSTFbGuqq_t25gRWv6gUk/edit
👍10
🙏 ትላንት ማታ ለተፈጠረው የተደጋገመ ማስታወቂያና አላስፈላጊ ጽሁፎች የ etconp ቤተስብን ይቅርታ እንጠይቃለን::

✨✨✨

📍ችግሩን አስተካክለነዋል ።

@etconp
🙏5👍1
👉ቅደመ ክፍያ

▶ADVANCE PAYMENT
.
➡በልዩ ሁኔታ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል ቅድሚያ ክፍያ/advance payment/ የሚፈቅድ ከሆነ ስራ ተቌራጩ ስራውን ለማሰጀመር ማሽነሪ እና የግንባታ ግብአት ለማስገባት በሚጠየቅ ግዜ የሚከፈል ክፍያ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል

1) ቅድመ ክፍያው ስራ ተቋራጩን የሰራ ውሉን ተፈፃሚ የሚያደርግበትን የጠቅላላ ግምት ነው።

2)በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል(Special condition of contract) የቅድሚያ ክፍያውን መጠን መግለፅ ሲኖርበት ነገር ግን ከጠቅላላ ፕሮጀክት ወጪ ሰላሳ (30%)ፐርሰንት መብለጥ የለበትም።

3) ውል ተፈፅሞ ፕሮጀክት ሳይት ርክክብ ሳይደረግ ቅድሚያ ክፍያ አይሰጠውም።

4) ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው ክፍያ ዋስትና ቦንድ ሊያቀርብ ይገባል።

@etconp
❤12👍7
DIFFRENECE OF WSM ANA LSM (5).PDF
183.1 KB
🌟 Working Stress Method (WSM) vs Limit State Method (LSM) in Structural Engineering.

🏗 Working Stress Method (WSM) and Limit State Method (LSM) are two common methods used in structural engineering for designing and analyzing structures. The Working Stress Method (WSM) is an older method that has been largely replaced by the Limit State Method (LSM) in most parts of the world.

🏗🏗🏗 This pdf will show you the diffrence b/n the method based on indian standard🏗🏗🏗

@Etconp
👍7❤4
👉የኮንስትራክሽን ውል
.
⚡በቁፋሮ ወቅት ሳይት ላይ ሊገኙ ስለሚችሉ አንዳንድ ነገሮች
ኮንስትራክሽን ኮንትራት ውል ምን ይላል???
⏩ ለምሳሌ: ወርቅ ወይም ሌላ መዐድን (ክምችቱ አነስተኛ የሆነ… ) ቢገኝ👆👆👆

@etconp
👍14
Fun story 😀

Nanjing university 🏫 made its WiFi password this, suppose you’re studying in this university and your friend from different campus came in and asked you what the password is ,what is gonna be your answer

አስናኝ ታሪክ 😆

ቻይና ናይንጂንግ ዩኒቨርስቲ የ ዋይፋይ ፖስወርዳቸውን ይሆን አረጉ እናንተ የዚህ ትምህርት ቤት ተማሪ ናችሁ እንበል ሚታቁት ሰው ከሌላ ቦታ መጥቶ ፖስወርድ ቢጠይቃችሁ መልሱ ምን ትሉት ይሆን

@etconp
🤣11👍4
👉USES OF CEMENT @COTMp
.
➡Cement is used widely for the construction of various structures. Some of them are listed below:
⏩Cement slurry is used for filling cracks in concrete structures.
⏩Cement mortar is used for masonry work, plastering and pointing.
⏩Cement concrete is used for the construction of various structures like buildings, bridges, water tanks, tunnels, docks, harhours etc.
⏩Cement is used to manufacture lamp posts, telephone posts, railway sleepers, piles etc.
⏩For manufacturing cement pipes, garden seats, dust bins, flower pots etc. cement is commonly used.
⏩It is useful for the construction of roads, footpaths, courts for various sports etc.

@etconp
👍9
🌟Happy International May day

@etconp
❤4
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፈቱ።

በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር በጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ዳርቻ የሚገኘው የሀላላ ካብ በ'ገበታ ለሀገር' ኮይሻ ኮሪደር ፕሮጀክት አካል በሆነው ሃላላ ኬላ ሪዞርት ውስጥ ተካቶ የለማ ድንቅ የቱሪስት መስህብ ስፍራ መሆኑን ተናግረዋል።

ሀላላ ኬላ ሪዞርት ከመዝናኛ ስፍራነቱ በተጨማሪ ታሪካዊና ባህላዊ ሙዚየሞችና የምርምር ማዕከላትን ያካተተ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የዳውሮ ዞን ለአይን የሚማርኩ መልከዓ ምድር፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች ባለቤት ስለመሆኑም አንስተዋል።

ኢትዮጵያውያን ለብዙ ስራዎች አእምሯችሁ እንዲከፈት የህዝብና አካባቢ ሰላም በእጅጉ በሚገኝበት የዳውሮ ዞን በመምጣት አዳዲስ ሀሳቦችን ለማፍለቅና ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት እንዲጎበኙም ጥሪ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሸትን በማለባበስ እውነት ማድረግ እንደማይቻልና ውሸትን ቀባብቶ እውነት ለማስመሰል መሞከር እንደ ሐላላ ኬላ ያሉ ፕሮጀክቶችን ለመፍጠር አያስችልም ሲሉም አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊት የብዙ ባህልና ቋንቋዎች መገኛ ሀገር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንን ብዘኃነት እንደራስ መቀበልን መለማመድ ያስፈልጋል ብለዋል።

እንደ ዋልታ ዘገባ፤ ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ ሀገር ናት የምንለው በባህልና ቋንቋ ብቻ ሳይሆን በተፈጥሮም እጅግ ማራኪ ሕብረ ብሔራዊ ቀለማትን በውስጧ የያዘች ሀገር መሆኗን መረዳት ያስፈልጋል፤ በዚህም አንዱ አካባቢ ከሌላው የተለየ የራሱ ተፈጥሯዊ ገፀ በረከቶችን የያዘ በመሆኑ በአግባቡ በማልማት መጠቀም እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በመጨረሻም የዳውሮ ማህበረሰብ የሐላላ ኬላ ሪዞርት እንደቀደሙ አባቶች ቅርስ በመጠበቅ ለትውልድ እንዲያሸጋግርና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን እንዲያረጋግጥ አሳስበዋል።

@etconp
👍7🤮4❤1👏1🎉1
🌟 በመጀመሪያ ለምታደርጉልን ትብብር እያመሰገንን ለ msc ፕሮግራም ጥናታዊ ጽሁፍ የሚሆን መጠይቅ እንድትሞሉልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን ።

🌟  ADDIS ABABA SCIENCE AND TECHNOLOGY UNIVERSITY
COLLEGE OF ARCHITECTURE AND CIVIL ENGINEERING DEPARTMENT OF CIVIL ENGINEERING; CONSTRUCTION TECHNOLOGY AND MANAGEMENT

🏗 Questionnaire Survey for MSc Thesis on the title of; Assessment of challenges on sustainable construction practices in building construction projects in Addis Ababa.

https://docs.google.com/forms/d/1wpBgBvIx5Nze2gRqN-a1uiiSTFbGuqq_t25gRWv6gUk/edit
❤5👍3🍌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📍ዛሬ የተመረቀው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የገበታ ለሀገር

📍ሐላላ ኬላ ሪዞርት ይህንን ይመስላል🔥

🎥በ ምስል ይመልከቱት✨

❤ውብ ምሽት ተመኘን🙏

@etconp
👍14❤4🤮4
👉ታሪክን የኋሊት

🌟ከጣልያን በፊት የተሰራ የአዲስ አበባ ካርታ፡፡

✨እኤአ 1909 ማለትም ከጣልያን መግባት 27 አመት ገደማ በፊት በፈረንሳይኛ የተዘጋጀ የአዲስ አበባ ካርታ ምስል ተያይዟል፡፡

✨በስተሰሜን በኩል የስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ የራስ ተፈሪ የነበረ መሆኑንና ሱ በስተምስራቅ ተቃራኒ ደግሞ የልጅ እያሱ ግቢ መሆኑን ያመላክተናል፡፡ የቀድሞው የልጅ እያሱ ግቢ የአሁኑ የጀርመን ባህል ማእከል ወይም ጎተ ኢንስቲትዩት መሆኑን እንረዳለን፡፡ የፒያሳው የአድዋ ጎዳና የራስ መኮንን መንገድ እንደሚባል፣ በደቡብ ያለው የባቡር ጣብያ የሚወስደው መንገድ ሩ ዴ ላጋር ወይንም የባቡር ጣብያ መንገድ እንደሚባልም እንመለከታለን፡፡ በካርታው በስተምስራቅ ደግሞ ዳግማዊ ምኒልክ በወንዞች ላይ ድልድይ እንዲሰሩ አስበው እና ከከተማ ውጭ መሆናቸውን ገምተው ለጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ሩስያ እንዲሁም እንግሊዝ ለኤምባሲዎች ሰፋፊ ቦታ መስጠታቸውን እንረዳለን፡፡
በደቡብ ምስራቅ የኡራኤል ቤተክርስትያን ፈንጠር ብሎ መገንባቱም ይታያል፡፡

በተከታታይ ከጣልያን በፊት፣ በጣልያን ግዜ፣ በ1960ዎቹ እንዲሁም ከዛን ወዲህ በደርግ ግዜ የተሰሩትን የአዲስ አበባ ካርታዎች በዚህ የቴሌግራም ጣብያ ማያያዛችን ይታወሳል፡፡

@etconp
👍7❤1
📌ትብብርን ሰለመጠየቅ

🌟 ለ BSc ፕሮግራም ጥናታዊ ጽሁፍ የሚሆን መጠይቅ እንድትሞሉልኝ ስል በትህትና እጠይቃለው።

🌟Hello there, i'm a student at AAU, EiABC and i am conducting a Bsc thesis research, i'm here to ask you a favor to post a link of google form to ETCONp Members 

Here is the link👇
https://forms.gle/HF8DvFWuHTzDLVgg6

🙏Thanks in advance🙏
❤2👍2🤮1🍌1
👉እስቲ ዛሬ ከ ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮች ጋ የተያያዘ እንዳስስ

​​🌟ብዙ ጊዜ ሶፍትዌር ስንገዛ crack የተደረጉ ናቸው። ይሄም የሆነው አንድም original የመግዛት አቅም ስለሌለን ሁለትም online ግብይት በኛ ሀገር ስላልተጀመረ ነው።

⇶crack
✏️ crack የተደረገ ማለት የ የሶፍትዌር አምራቾች የሚያወጡትን original ሶፍትዌሮች ሀከሮች ሀክ በማድረግ ያለ ክፍያ መጠቀም ማስቻላቸው ነው።

👽አንዳዴም ሀከሮች ለመልካም ነገር ይጠቅሙናል የሚባለው ለዚህ ነው። እነዚህን ሶፍትዌሮች ለመጫን ግን ብዙ ጊዜ ስንቸገር እንታያለን።

🔸ለዛሬም የተወሰኑ ነገሮችን ለማየት እንሞክራለን።
በመጀመሪያ ደረጃ ከ crack በተጨማሪም keygen እና patch የተሰኙ መንገዶች መተዋል። ከዚህ ሌላም ሊኖሩ ይችላሉ።
 
       ◉ step one_1↹

⇶Internet
⇒በመጀመሪያ ደረጃ internet ማጥፋታችንን ማረጋገጥ አለብን። ብዙ ጊዜ የሶፍትዌር ካምፓኒዎች originalityውን validate የሚያደርጉት በዚህ ስለሆነ ነው። ቀጥሎ አንቲ ቫይረስ ካለን disable ማድረግ አለብን አለበለዚያ crack ፋይላችንን ሊበላው ይችላል።

      ◉ step Two_2↹

⇶Run
⇒ሶፍትዌራችንን run አርገነው ከጫንን በኋላ launch/ መክፈት/ የለብንም መመሪያውም ላይም  tick ተደርጎ ከሆነ untick ማድረግ ይገባናል።


      ◉ step three_3↹

⇶Crack file
⇒በ crack መልክ የመጣ ሶፍትዌር ከሆነ crack ፋይል ውስጥ ያሉትን ፋይሎች copy አድርገን ሶፍትዌራችንን የጫንበትን location ከፍተን paste ማድረግ በዚ ሰአት ተመሳሳይ ነው overwrite ላርገው የሚል ምርጫ ሲመጣልን የስ/yes/ እንለዋለን።(ብዙ ጊዜ ሎኬሽኑ የሚገኘው local C/program file 86/ ውስጥ ነው አልያም የጫነው ሶፍትዌር icon ላይ right click በማድረግ open location የሚለውን መምረጥ።)

      ◉ step four_4↹

⇶Keygen
⇒ሶፍትዌራችን በዚህ መልክ ከሆነ ደሞ ሶፍትዌራችንን patch ማድረግ አለብን። patcher በመጠቀም ያገኘነውን key ሶፍትዌሩ ላይ መሙላት ። አንዳንዴ ደሞ በ ጽሁፍ መልክ ይመጣል በዚህ ሰአት ከፍተነው የምናገኘውን key copy አድርገነው ከዛ ሶፍትዌሩን run ስናደርገው የሚጠይቀን ቦታ ላይ እናስገባዋለን።

↹ ለምሳሌ office 2007 እና window xp በዚህ መልክ ነው የሚጫነው።
ነገር ግን keygen ከመጠቀማችን በፊት patching የሚያስፈልገው ከሆነ ቀጥሎ ያለውን step ይጠቀሙ።

      ◉ step five_5↹

⇶Patch
⇒በዚህ መልክ ሲመጣ ደሞ patch ፋይሉን Run as Administration በሚለው እንከፍተዋለን right click አድርገን።
▪️በዚህ ሰአት በ administrator account መግባታችንን ልብ ልንል ይገባል።

በላይ በገለጽናቸው መንገዶች ተጠቅመን activate ካደረግን በኋላ መስራቱን ቼክ አድርገን internet ከመክፈታችን በፊት firewall ውስጥ ገብተን የጫነው ሶፍትዌር access እንዳያደርግ block ብናደርግ ይመረጣል አለበለዚያ የተጭበረበረ መሆኑን ካወቀ መልሶ deactivate ሊያደርግብን ስለሚችል።

N.B ! ሶፍትዌር የያዘውን ፍላሽ ከመሰካታችን በፊት anti virus ሳችንን disable ማድረግ አለብን በተለይም እንደ smadav auto run የሆኑትን።

◉ ከዚህ ሌላ መንገዶች ሊኖሩ ይችላል ምክንያቱም በየቀኑ ሴኪሪያቲያቸውን እያጠናከሩ ስለሚመጡ በዛው መጠን crack ለማድረግ ፈታኝ እና ኮምሌክስ እየሆኑ ነው የሚመጡት ለዚህ ARCI GIS ጥሩ ማሳያ ነው።

Via Yirhe

@etconp
👍17