Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Rebar corrosion occurs when chloride ions migrate to concrete material like steel bars. It is a type of corrosion that occurs in most highway bridges. These structures are usually constructed with rebar that is reinforced by steel throughout the support structures.

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
❤3
Steel water tank design

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
❤5👍1👌1
👉ዛሬ ደሞ ለ ሰርቨይንግ ሚጠቅማቹ ስለ Angle እና Direction ጠቃሚ መረጃ ልናጋራቹ ወደናል

▶️Northing = ማለት Y-Coordinate ማለት ነው – ከ (0,0) ወደ Y direction ምን ያህል እንደሚሄድ የሚያሳይ ነጥብ

▶️Easting = X Coordinate

▶️Azimuth angle = Clockwise አቅጣጫ ከ North ስንለካ የምናገኘው አንግል

▶️Bearing = acute angle ሲሆን clockwise ወይም counter clockwise ከ North ወይም South ስንለካ የምናገኘው

🚧ከዚህ ሌላ ህንፃዎች ላይ ከ angle እና direction አለማወቅ ወይም ግዴለሽነት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡

📜ለምሳሌ ለፀሀይ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ላይ ትልልቅ መስታወቶችን / መስኮቶችን ማድረግ፣ ዲዛይን ሲደረጉ ከታሰበላቸው አቅጣጫ ውጪ
የዞሩ ህንፃዎች መገንባት (በስህተት ፊታቸውን ወደ መንደር ጀርባቸውን ወደ መንገድ ያዞሩ ሞሎች፣ መኖሪያ ቤቶች ወዘተዎች እንዳሉ ሁላችንም እናውቃለን) ፣ ያልሆነ ቦታ ላይ ግንባታ በመጀመር ህንፃን ያልሆነ ቦታ ላይ ማሳረፍ ወይም የሰው ይዞታ ውስጥ እስከመግባት ፣ ስራው ከተጀመረ በኋላ አቅጣጫው ልክ እንዳልሆነ ሲያውቁ ፓዶችን እያነሱ ቦታ ማቀያየር ካልተቻለም እንደዛው የዞረ ፎቅ ገንብቶ መጨረስ …… ሁሉም ከአቅጣጫ አለማወቅ የተነሳ የሚፈጠሩ ችግሮች ናቸው፡፡

✨North, East, South, West አለማወቅ የሚያሳዝን ነገር ነው። አልተማሩም የምንላቸው አባቶቻችን እናቶቻችንን ሲቀጥሩ
‹‹በስተምዕራብ በኩል ያለው ዛፍ ስር ጠብቂኝ›› ሲሉ እናቶቻችንም ‹‹የከሰዓቱ ፀሀይ እንዳያስቸግረን በስተሰሜን በኩል ያለው ዛፍ ይሻለናል›› እያሉ ሃሳብ ያቀርቡ ነበር::

እኛ ፊደል ቀመሶች ግን ለስራ ደቡብ ክልል ተልከን ሰሜን ምስራቅ ክልል እንገኛለን፡፡😁

🌟ለማንኛውም አቅጣጫን ለማወቅ 3 መንገዶች አሉ፡፡

⏺አንደኛ ኮምፓስ መግዛት ወይም ስልክህ ላይ የኮምፓስ አፕሊኬሽኖችን መጫን፡፡

⏺ሁለተኛ ጠዋትና ማታ የፀሀይ መግቢያና መውጪያ ቦታዎችን እያዩ አዕምሮአችን አቅጣጫዎቹን ሴቭ እንዲያደርግ መጣር፡፡

⏺ሶስተኛው ደሞ ኮምፓስ ከሌለንና ፀሀይ እስክትገባ የምንጠብቅበትም ሰዓት ከሌለን ዞር ዞር በማለት ዲሽ መፈለግ… ናይልሳት የተሰራ ዲሽ ጀርባ በመሆን LNB የምትይዘዋ ዘንግ ቀጥታ የምታሳየው 7 ዲግሪ West ነው፡፡

📡ስለዚህ ከዲሹ አቅጣጫ በመነሳት ሌሎቹንም አቅጣጫዎች ማወቅ ትችላለህ፡፡

✌ደሞ ዲሽ አገኘው ብለህ በአረብ ሳት አቅጣጫ ተመርተህ ወደ ሰማይ የዞረ ፎቅ እንዳትሰራ😀 “ናይልሳት ነው seven degree West😉

📌ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።

📍Join for more updates New Work Vacancy anf Tender via the link below

t.me/ETCONpWORK
👍14❤2
A mountain carving themed on the Cizhou kiln is unveiled at Fengfeng mining area in Handan, North China's Hebei province, May 5, 2023. The kilometer long mountain carving features the unique history of the Cizhou kiln and the 72 firing procedures of porcelains at Cizhou kiln.

#chinaculture #culturheritage #archeology #ancientchina

@etconp
👏4👍2
የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማን በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ

የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማን በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ማዘጋጃ ቤት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት አዲስ ባወጣው የከተሞች የተቀናጀ ፕላን፤ የደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማ በሦስት ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በአስር ወረዳዎች እንድትደራጅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድርግ በተሰራው ሥራ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 46 አዲስ ፕሮጀክቶች እና 26 ነባር በድምሩ 72 ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሚገኙ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ኀላፊ ገብሬ ዳቢ ተናግረዋል፡፡

እነዚህም የመንገድ፣ የኮብል ስቶን ንጣፍ ፣የጋር መኖሪያ ቤቶች፣ቤተ መጻሕፍት እንዲሁም የውሀ ፕሮጀክቶች እንደሚገኙባቸው ተናግረዋል፡፡

አብዛኞቹ ሥራዎች በዚህ ዓመት ተጠናቀው አገልግሎት እንደሚጀምሩ የገለጹት ኀላፊው፤ ፕሮጀክቶቹ በመንግሥት በጀት፣ባለ ሀብቶች በሚያደርጉት ልገሳ እንዲሁም በኅብረተሰቡ ተሳትፎ እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተሰሩ እንደሚገኙም በመጠቆም፤ ከተጠናቀቁ በሁዋላ ከተማዋን ለኑሮ ምቹ እና ማራኪ ማድረግ፣ ለሥራ አጦች የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የሕብረተሠብን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል እንዲሁም የነዋሪውን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

ለፕሮጀክቶቹ ተሰጥቶ እየተሠራ ያለው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ወደፊት ከተማዋን በምሥራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

Via አዲስ ማለዳ

@etconp
👍8❤6🤔1
👉በጅማ ከተማ እየተሰራ የሚገኘው ፓርክ

🌟በኦሮሚያ ክልል የጅማ ከተማ መስተዳደር በከተማው ፓርክ እየገነባ እንደሆነ አስታወቀ ፓርኩ በውስጡ የሚይዘው Artificial lake, walk way, children playground, water fountain, water pond, cafe, shops በውስጡ እንደሚያካትት ተገልፇል።

@etconp
🙏10👍1
የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ህንፃ እና የሲኒማ ኮምፕሌክስ 4B+G+8 ግንባታዎችን ቀሪ ስራዎች ለማከናወን የሚያስችል አዲስ ውለታ የመፈራረም ስነስርዓት ተካሂዷል፡፡

ቀድሞ ግንባታውን ያከናውን የነበረው ስራ ተቋራጭ እቴቴ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶቹ በተለያየ አፈፃፀም ደረጃ ላይ እያሉ አቋርጦ በመውጣቱ ምክንያት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መነሻ ሆነው የቆዩት የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ እንዲሁም የሲኒማ ኮምፕሌክስ ግንባታዎች አዲስ ውለታ የመፈራረም ስነስርዓት ተከናውኗል፡፡

ጉዳያቸው በፍርድቤት በመያዙ እንዲሁም በጨረታ ሂደቶች ምክንያት ለ16 ወራት ገደማ ተቋርጠው የቆዩት እነዚህ ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጨረታውን ካሸነፈው ባማኮን ኢንጂነሪንግ ጋር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ውለታ የማሰር ስነ-ስርዓት አካሂዷል፡፡

የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ህንፃን ከ833 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም የሲኒማ ኮምፕሌክስ ቀሪ ስራዎች ከ954 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የፕሮጀክት ውል መጠን ጨረታውን ያሸነፈው ባማኮን ኢንጂነሪንግ ስራዎቹን አጠናቆ ለማስረከብ የ6 ወራት ዕድሜ የተሰጠው ሲሆን ከፕሮጀክቱ አንገብጋቢነት አንፃር የሚሰጠው ቅድመ ክፍያ በጥምር ሂሳብ / Joint Account / የሚተዳደር ሆኖ ለግብዓት ግዢ ብቻ የሚውል መሆኑን ከስራ ተቋራጭ ጋር መግባባት ላይ እንደተደረሰና ይህም ወደፊት ሊከሰት ከሚችል የግብዓት ዋጋ ንረት እንደሚታደግ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም በስነስርዓቱ ላይ እንዳሉት ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ቢሮው ቢሮው በቁርጠኝነት እንደሚሰራ  አበክረው በማንሳት ለውጥኑ ስኬታማነት ሁሉንም አካላት በማስተባበር አስቻይና ሁሉን ዓቀፍ መደላድሎች እንዲፈጠሩ ቢሮው ከዛሬዋ ዕለት ጀምሮ እንቅስቃሴ ማድረጉን እንደሚጀምር አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

ኃላፊዋ አክለውም ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት ቢሮው ቴክኒካል ድጋፍ ከማድረግም በዘለለ በልዩ ሁኔታ ሳምንታዊ የፕሮጀክት ግምገማ መርኃ-ግብር እንደሚኖር ማሳሰባቸውን
ከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@etconp
👍7❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟ንድፍ ደረጃ

🚧የማብሰያ ምግብ ቤት እርምቶች

📽ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል በማብሰያ ክፍል ያሉትን እርምት የሚያስፈልጉ ዝርዝሮችን ይጠቁማል፡፡

📌Kichen cabinet Dimensions

Via DeZone

@etconp
❤6👍6
📌ትብብርን ስለመጠየቅ ይመለከታል

✋ጤና ይስጥልኝ ፤ ፉአድ ረሺድ እባላለው የ ኮንስትራክሽን ባለሙያ ነኝ በአሁን ወቅት በ Leadership and Management " ማስተርሴን ለማጠናቀቅ የመመረቂያ ጥናት በመስራት ላይ እገኛለሁ ጥናቱ በደረጃ-1 ኮንትራክተሮች ላይ የሚያተኩር ነው እናም ለዚህም ይረዳኝ ዘንድ የዚህ ቻናል ቤተሰብ ይህ ከታች ያለው ፎርም እንድትሞሉልኝ በአክብሮት እጠይቃለው ፤ በቅድሚያ ለምታደርጉልኝ ትብብር እጅግ በጣም አመሰግናለው።

ሊንኩ ከዚህ በታች የተቀመጠው ነው
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdX0KJCSqQ9vRCYTykDeO8D6mRt7-vnxun_JM5-VvwcVFoRgg/viewform?usp=sf_link
👍10
👉ንፋስ፣ ኪነህንጻ እና ስነከተማ

✨ልሙጥ የመስታወት ገጽታን በመተው፣ ወጣ ገባ ያለን የህንጻ ገጽታን፣ በረንዳን፣ ዛፎችን እንዲሁም ሌሎች የስነከተማ ቁሶችን በመጠቀም ንፋስን እና አዲስ አየር በህንጻዎች ዙርያ እንዲነፍሱ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

Via 07sketches

@etconp
👍9🙏3
በሶማሌ ክልል ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ሊገነባ ነው

በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን ጉራዳሞሌ ወረዳ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት እንደሚገነባ ተገለጸ።

ፕሮጀክቱ ከ49 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተጠቁሟል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የፕሮጀክት ኮንትራት ውል ዛሬ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌው ናቸው።

ፕሮጀክቱ ለድርቅ ተጋላጭ በሆነ አካባቢ የሚገነባ በመሆኑ በተቀመጠው የግንባታ ጊዜ ወቅቱን ጠብቆ በጥራት እንዲከናወን ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌው በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በተገባው ውል መሰረት ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ ወጪ የሚሸፈነው ከዓለም ባንክ የአንድ ቋት የመጠጥ ውሃ፣ሳኒቴሽንና የሃይጂን (One WaSH) ፕሮግራም ብድር እንደሆነ ተጠቁሟል።

የባለብዙ መንደር የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ይችላል የተባለው የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ከ49ሺ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የውል ስምምነቱ አጠቃላይ የሲቪል ግንባታና አሌክትሮሜካኒካል ስራዎችን እንዲሁም የመስመር ዝርጋታን እንደሚያካትት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@etconp
👌5👍1