Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የ ኮንስትራክሽን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) ምን ማለት ነው?

📌ውሎችን ለሌላ መልቀቅ (Assignment) ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በሙሉ እንዲፈጽምለት ለአንድ ሶስተኛ ወገን ለሆነ ሲያስተላልፍ ነው፡፡ (የፍ/ህ/ቁ 3201(1)) *ይሄውም ከንኡስ ተቋራጭነት ጋር ሁኔታው አንድ አይነት ሲሆን በዋናነት ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ለሌላ ተቋራጭ(ለንኡስ ተቋራጩ) የሚያሰራው ሙሉውን የግንባታ ስራ ነው፡፡

*በዚህ ውል ውስጥ ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ተቋራጮች ናቸው፡፡

**ለምሳሌ "ሀ" የተባለ ተቋራጭ "ለ" ከተባለ አሰሪ ጋር የኮንስትራክሽን ውል ገባ እንበል፡፡የግንባታ ስራው ደግሞ ትምህርት ቤት ቢሆን እና ሁለት ብሎክ መማሪያ ህንጻ እና አንድ ሽንት ቤት ግንባታ ቢሆን እንበል፡፡

እንግዲህ ዋናው ተቋራጭ "ሀ" ከግንባታ ስራው ውስጥ አንዱን ብሎክ መማሪያ ክፍል "ሐ" ለተባለ ተቋራጭ በውል ሰጥቶ ቢያስገነባው በ "ሀ" እና "ሐ" መካከል የሚደረገው ውል የንኡስ ተቋራጭነት ውል ይባላል ማለት ነው፡፡

*በሌላ በኩል ምናልባት ዋናው ተቋራጭ "ሀ" ሁሉንም ግንባታ ማለትም ሁለት ብሎክ መማሪያ ህንጻ እና አንድ ሽንት ቤት "መ" ለተባለ ተቋራጭ በውል ሰጥቶ ቢያስገነባው በዋናው ተቋራጭ "ሀ" እና "መ" በተባለው ተቋራጭ መካከል የተደረገው ውል በንኡስ ተቋራጭነት ሳይሆን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) በሚለው የህግ ክፍል የሚጠቃለል ይሆናል ማለት ነወ፡፡
.
📌ጀኔራል ኮንዲሽኖች ንኡስ ተቋራጭነትን በምን ሁኔታ ያስቀምጡታል?

ፒፒኤ 2011 ስለ ንኡስ ተቋራጭነት አስመልክቶ በክሎስ 14 ላይ አስቀምጧል፡፡

*በዚህም የንኡስ ተቋራጭነት ውሉ በጽሁፍ መሆን እንዳለበት እና ይሄውም የቫሊዲቲ መስፈርት ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡

*ንኡስ ተቋራጮች በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ያልታወቁ( Non nominated) የሆኑ እንደሆነ ዋናው ተቋራጭ ሌሎች ንኡስ ተቋራጮችን የግንባታ ስራ ለማሰራት የአሰሪውን የጽሁፍ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል በሚል ያስቀምጣል፡፡

*የንኡስ ተቋራጭነት ውሉም ከዋናው ውል ጋር የተጣጣመ እና በዋናው ውል ጭምር የሚገዛ እንደሚሆን ክሎስ 14.3 ላይ ተቀምጧል፡፡

*ዋናው ተቋራጭ የአሰሪው መስሪያ ቤት ሳይፈቅድለት የንኡስ ተቋራጭነት ውል የገባ እንደሆነ አሰሪው ፎርማል ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልገው ውልን ማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 14.8 ያስቀምጣል፡፡

*ሌላው ንኡስ ተቋራጩ የግንባታ ስራ ለማከናወን ብቃት የሚያንሰው እንደሆነ አሰሪው መስሪያ ቤት ወይም መሀንዲሱ ዋናውን ተቋራጭ ሌላ ብቃት ያለው ንኡስ ተቋራጭ እንዲያመጣ ወይም ስራውን በራሱ እንዲያከናውን ሊጠይቀው እንደሚችል ክሎስ 14.9 ይገልጻል፡፡

ፊዲክ ሬድ ቡክ 1999-በዚህ ጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ 4.4 ላይ ዋናው ተቋራጭ ሙሉውን የግንባታ ስራ ለንኡስ ተቋራጭ መስጠት እንደማይችል ተቀምጧል፡፡

*እንዲሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ላይ በሌላ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር ንኡስ ተቋራጩ በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ስሙ የተጠቀሰ በሆነ ጊዜ በንኡስ ተቋራጭነት ለማሰራት የመሀንዲሱን ፈቃድ መጠየቅ አይጠበቅበትም፡፡

*ሆኖም የታሰበው ንኡስ ተቋራጭ አዲስ እና በዋናው ውል ስሙ ያልተጠቀሰ የሆነ እንደሆነ በቅድሚያ የመሀንዲሱን ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ ይሆናል፡፡

*ዋናው ተቋራጭ ለመሀንዲሱ በተለይ ንኡስ ተቋራጩ የሚሰራውን የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን/ኮመንስመንት ዴት/ ተብሎ የታሰበውን ጊዜ ከ28 ቀን ባላነሰ ጊዜ ማስታወቅ ሲኖርበት ንኡስ ተቋራጩ በትክክል በሳይት ላይ ስራ የጀመረበትንም ቀን ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

Nominated subcontractors በሚመለከት በክሎስ 5.1 ላይ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡

*በዚህም መሰረት ኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተር የሚባለው በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተር መሆኑ የተገለጸ እንደሆነ ወይም ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ንኡስ ተቋራጭ መርጦለት እንዲያሰራው ያዘዘው የሆነ እንደሆነ ነው፡፡
.
ለኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተሩ ክፍያ የሚፈጸምለት በንኡስ ተቋራጭነት ውሉ አግባብ በመሀንዲሱ በሚሰጥ የክፍያ ሰርተፍኬት መሰረት ሲሆን ክፍያውን የሚፈጽመውም ዋናው ተቋራጭ ስለመሆኑ ክሎስ 5.3 ላይ ተቀምጧል፡፡

Via ጉባዔ አሰፋ

#ConstructionLaw

@etconp
👍22❤2
By :- Tarekegne Lemma

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
❤4🙏2👍1👌1
Maximum slope and maximum vertical deflection for various loading conditions on beams:

+ Cantilever beam with point loading at the free end:
Maximum Slope: The slope is highest at the fixed end of the beam and is directly proportional to the point load applied.
Maximum Vertical Deflection: The maximum deflection occurs at the fixed end of the beam and is influenced by the magnitude of the point load.

+ Cantilever beam with a moment at the free end:
Maximum Slope: The slope is maximum at the fixed end and is directly proportional to the applied moment.
Maximum Vertical Deflection: The maximum deflection occurs at the fixed end and is influenced by the magnitude of the applied moment.

PART 1

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
❤3👍1
Ethio Construction Engineering
Maximum slope and maximum vertical deflection for various loading conditions on beams: + Cantilever beam with point loading at the free end: Maximum Slope: The slope is highest at the fixed end of the beam and is directly proportional to the point load applied.…
PART II

+ Cantilever beam with a uniform distributed load over the full span:
Maximum Slope: The slope is highest at the fixed end and is influenced by the magnitude of the distributed load.
Maximum Vertical Deflection: The maximum deflection occurs at the free end of the beam and is influenced by the magnitude of the distributed load.

+ Simply supported beam with a force at midspan:
Maximum Slope: The slope is highest at the midspan and is directly proportional to the magnitude of the applied force.
Maximum Vertical Deflection: The maximum deflection occurs at the midspan and is influenced by the magnitude of the applied force.

+ Simply supported beam with a force at a point other than midspan:
Maximum Slope: The slope varies depending on the location of the applied force and beam properties.
Maximum Vertical Deflection: The maximum deflection varies based on the location of the applied force and beam properties.

+ Simply supported beam with a uniformly distributed load over the full span:
Maximum Slope: The slope is highest at the midspan and is influenced by the magnitude of the distributed load.
Maximum Vertical Deflection: The maximum deflection occurs at the midspan and is influenced by the magnitude of the distributed load.

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
❤3
Ethio Construction Engineering
PART II + Cantilever beam with a uniform distributed load over the full span: Maximum Slope: The slope is highest at the fixed end and is influenced by the magnitude of the distributed load. Maximum Vertical Deflection: The maximum deflection occurs at the…
PART III

+ Simply supported beam with a moment at one support:
Maximum Slope: The slope is highest at the location of the applied moment and depends on the magnitude of the moment and beam properties.
Maximum Vertical Deflection: The maximum deflection occurs at the location of the applied moment and is influenced by the magnitude of the moment and beam properties.

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
❤3
በ twitter ብቅ ብለናል

Link:- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg

ብዙ ነገር በዚህ ገፅ እናጋራችኋለን

- አጫጭር ፅሁፎችን እንለቅበታለን
- poll ለ ጥናታዊ ፅሁፍ( Research) እንለቅበታለን
- space ላይ ውይይት እናረጋለን በቀጥታ የድምፅ ግንኙነት

@etconp

ተቀላቀሉን ሽልማት ይኖራል ተቀላቅላችሁ screenshot follow ያረጋችሁበትን comment ላይ ካስቀመጣችሁ።
👍4👏2
የሕንፃ አዋጅ

የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 መሰረት የአዋጁን ድንጋጌዎች በመተላለፍ የግንባታ ሥራ ፈቃድን በሚሰጡ የመንግሥት ኃላፊዎች እና ይህንኑ እንዲያከናውኑ ሃላፊነት በተሰጣቸው ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች፣ በተመዘገቡ ባለሙያዎች ወይም ሥራ ተቋራጮች፣ እንዲሁም በግንባታ ባለቤቶች የሚፈፀሙ ጥፋቶች እንደሁኔታው ከ6 ወር ጀምሮ እስከ 15 አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ500 (አምስት መቶ) ብር እስከ 50000 (ሀምሳ ሺ) ብር የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም በ1996 የወጣው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 501 የህንጻ ሾል ደንቦችን መጣስ በሚል ርእስ ሾር ማንም ሰው ማንኛውንም አይነት የህንጻ ሾል ወይም የህንጻ ማፍረስ ሾል ሲቆጣጠር፣ ሲመል ወይም ሲፈጽም በህግ የተደነገገውን ወይም በህንጻ ሾል ሙያ ወይም ልምድ የሚሰራባቸውን የጥንቃቄ ደንቦችን አስቦ በመጣስ የህዝብን ደህንነት ወይም የሰዎችን ሕይወት፣ ጤንነት ወይም አካል ወይም የሌላውን ሰው ንብረት አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ ከ3 ወር በማያንስ ቀላል እስራት እና በመቀጮ የሚቀጣ ሲሆን ወንጀሉ የተፈጸመው በቸልተኝነት እንደ ሆነ  ከ1 አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና በመቀጮ እንደሚያስቀጣ ያመለክታል፡፡

በአጠቃላይ ማንኛውም የሕንፃ ግንባታ ሥራ በሚከናወንበት ወቅት ጉዳት እንዳያደርስ የግንባታ ሥፍራውን ተቀባይነት ባላቸው ቁሶች መከለል፣ በቁፋሮ ወቅት ከመሬት በታች ሊኖሩ የሚችሉ የመሠረተ ልማት መሥመሮች እንዳይጎዱ፣ በአካባቢው የትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል፣ ተቀጣጣይነት ያላቸውን የግንባታ ቁሳቁሶች በአያያዝ ጉድለት ለእሳት አደጋ እንዳይጋለጡ በማድረግ፣ በግንባታ ሥራ ላይ ለተሠማሩ ሠራተኞችና ጐብኚዎች የደህንነት መጠበቂያዎችን በማሟላት፣ ለግንባታ የሚውሉ የኬሚካል ውጤቶች በአጠቃቀም ወቅት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ እና ብናኝ ጭስና አንጸባራቂ ጨረር የመሳሰሉ አዋኪ ነገሮች አካባቢውን እንዳይረብሹ ተገቢው ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት በህጉ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

#ConstructionLaw

@etconp
👍8❤1🙏1
በኮንስትራክሽን ውል የግንባታ መዘግየት ቅጣት/Liquidated damage/
====================
#በኮንስትራክሽን ውል ላይ የውሉ የግንባታ ስራ ተብሎ የተቀመጠውን በዲዛይኑ እና ዝርዝር ስቴስፊኬሽኑ መሰረት በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሰርቶ ማጠናቀቅ የተቋራጩ ሀላፊነት ነው፡፡

#ተቋራጩ የውሉን የግናባታ ስራ በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በወቅቱ ሰርቶ ያላጠናቀቀ እንደሆነ ከውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ/completion date/ በኋላ ግንባታው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ለእያንዳንዱ ቀን ተቋራጩ የግንባታ መዘግየት ቅጣት/Liquidated damage/ የመክፈል ሀላፊነት ይኖርበታል፡፡

# በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሲባል ምን ማለት ነው? አንዳንድ አሰሪዎች/client/ በግንዛቤ እጥረት በውሉ ላይ የተቀመጠው ተቋራጩና አሰሪው ለግናባታው ማጠናቀቂያ የተስማሙበትን የቀን ብዛት/የጊዜ እርዝማኔ/ መቆጠር የሚጀምረው ውሉ በግራ ቀኙ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ ይረዱታል፡፡ይሄ አረዳድ ስህተት ነው፡፡

#በኮንስትራክሽን ውል ስለ ጊዜ አቆጣጠር በተለይ የግንባታ ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ፣ሞቢላይዜሽን ፔሬድ/mobilization period/፣የሳይት ርክክብ/site handover/፣ የስራ መጀመሪያ ቀን/commencement date/ እና የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ የሚሉትን መረዳት የግንባታ መዘግየት ቅጣት/Liquidated damage/ የሚለውን በአግባቡ ለማወቅ ይጠቅማል፡፡

#በመሰረቱ በውሉ የተቀመጠው የስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ተቋራጩ የግናባታውን ሳይት ከአሰሪው ከተረከበ በኋላ ነው፡፡ይሄውም ከሳይት ርክክብ በኋላ የስራ መጀመሪያ ቀን /commencement date/ በመሀንዲሱ የሚወሰን እና ለተቋራጩ የሚገለጽለት ይሆናል፡፡
#እንግዲህ ከዚሁ በመሀንዲሱ ከሚወሰነው የስራ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ በውሉ ላይ የተቀመጠው ቀን ይቆጠርና የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቸ እንደሆነ ለማወቅ ያስችላል ማለት ነው፡፡

#እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነገር በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ ውል ሊደረግ የሚችልበት እድልም አለ፡፡/part work completion/ ማለት ነው፡፡የቀን አቆጣጠሩ ከላይ እንደተብራራው የሚሰላ ይሆናል፡፡

#ስለሆነም የግንባታ መዘግየት ቅጣት የሚለው ጉዳይ የሚመጣው ተቋራጩ የውሉን የግንባታ ስራ በውሉ ስራ የማጠናቀቂያ ጊዜ /completion date/ ሳያጠናቅቅ የቀረ እንደሆነ ነው፡፡የገንዘብ ቅጣቱ የሚጣለው በተቋራጩ ላይ ነው፡፡ተቋራጩ ግንባታውን ላዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን በውሉ የተቀመጠውን የግንባታ መዘግየት ቅጣት የሚከፍል ይሆናል፡፡በነገራችን ላይ እየተቀጡ መስራት ለተቋራጩ መብትም ጭምር ነው፡፡ይህ ማለት አሰሪው የውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ ስላለቀ ውል አቋርጣለሁ ማለት አይችልም፡፡በውሉ ላይ የተቀመጠው የመዘግየት ቅጣት ጣሪያ መጠን ከሞላ በኋላ ግን አሰሪው ውል ማቋረጥ ይችላል፡፡ውል ከተቋረጠ በኋላ የመዘግየት ቅጣት የሚባል ነገርም የለም፡፡

# ሌላው ተቋራጩ ወደ መዘግየት ቅጣት እንዲገባ ከመደረጉ አስቀድሞ በአግባቡ መረጋገጥ ያለበት ነገር መሀንዲሱ ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ/time extension/ ፈቅዷል ወይስ አልፈቀደም የሚለው ነጥብ ነው፡፡ምክንያቱም ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ ተፈቅዶለት ከሆነ የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜውም አብሮ ስለሚራዘምና ቀኑ ስለሚቀየር ነው፡፡

# የሀገራችንን የህግ ማእቀፍ በዚህ ረገድ ምን ይላል? የሚለውን ለመመለስ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1887 እስከ 1895 ድረስ የተደነገጉትን መዳሰስ ይጠይቃል፡፡
*በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1889 ላይ ተዋዋዮች በውላቸው ምናልባት አንደኛው ወገን እንደውሉ ግዴታውን ያልፈጸመ እንደሆነ ወይም አጓድሎ የፈጸመ እንደሆነ ወይም አዘግይቶ የፈጸመ እንደሆነ የሚከፍለውን የመቀጮ መጠን አስቀድመው በውላቸው ለመወሰን እንደሚችሉ በሚፈቅድ መልኩ ተደንግጓል፡፡እዚህ ላይ የውል ግዴታን አዘግይቶ መፈጸም ስለሚያስከትለው ቅጣት የሚዋዋሉት በተለይ የግንባታ መዘግየት ቅጣት/liquidated damage/ የሚመለከት ይሆናል፡፡
*የመዘግየት ቅጣት ስምምነት ባለ ጊዜ አሰሪው የውሉ ስራ እንዲፈጸምና የቅጣት ገንዘቡንም ለመቀበል መብት እንደሚኖረው የፍ/ህ/ቁ 1890(2) ይደነግጋል፡፡እንደዚሁም አሰሪው ኪሳራ ባይደርስበት እንኳ የመዘግየት ቅጣት ገንዘቡ ሊከፈለው እንደሚገባ የፍ/ህ/ቁ 1892(1) ይደነግጋል፡፡እንግዲህ ተቋራጩ ግንባታውን በወቅቱ ያላጠናቀቀው አሰሪውን ሆነ ብሎ ለመጉዳት አስቦ ጉልህ በሆነ ቸልተኝነት ወይም በከባድ ጥፋት መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ አሰሪው በውሉ ከተቀመጠው የቅጣት ገንዘብ በላይ በደረሰበት ትክክለኛ ጉዳት መጠን ልክ ከተቋራጩ ላይ ኪሳራ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 1892(2) ይደነግጋል፡፡
*ሌላው የመዘግየት ቅጣት መጠን በዳኞች ሊቀነስ የሚችልበት እድል ስለመኖሩ የፍ/ህ/ቁ 1893 ይደነግጋል፡፡ይሄውም ተቋራጩ ግዴታውን በከፊል የፈጸመ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ይህ ማለት ተቋራጩ ባከናወነው ስራ ሁሉ ቅጣት የሚጣልበት አይሆንም ማለት ነው፡፡
*በዚህ ረገድ በሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ አንቀጽ 47(1) ላይ ተቋራጩ ስራውን በውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ ካላጠናቀቀ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን የውሉን ዋጋ 1/1000 እንደሚከፍል እና ይሄውም አጠቃላይ መጠኑ ከውሉ ዋጋ ከ20% መብለጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ሆኖም ግን በከፊል ለተከናወነው ስራ መሀንዲሱ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በሰጠ ጊዜ የቅጣቱ መጠን የሚሰላው ባልተከናወነው ስራ መጠን ዋጋ ላይ በመመስረት ይሆናል ማለት ነው፡፡

#በመጨረሻም የመዘግየት ቅጣት በኛ ሀገር ከላይ እንዳየነው እንደቅጣት የሚቆጠርና በህጉ ቅጣቱ እውቅና የሚሰጠው ሲሆን በኮመን ሎው የህግ ስርአት ግን ቅጣት አይደለም፡፡በኮመን ሎው ሊኩዴትድ ዳሜጅ በአሰሪው ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን የሚኖርበት ሲሆን የቅጣት አይነት ባህሪ ካለው ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

Via ጉባዔ አሰፋ

@etconp
👍25👏1
✌️ማሳሰብያ

👉የምትፖስቱት ፅሁፎች እና ፋይሎች ሴቭ እና ሼር ማረግ አልቻልንም ላላቹ

🚧የምትፈልጉት ፋይል ወይም ፅሁፍ... ላይ አንዴ ንኩት ከዛ ከሚመጣላቹ ዝርዝር ኮፒ ሊንክ ብላቹ...ሊንኩ ለምታጋሩት ሰው ወይ ግሩፕ ካልሆነ Saved message (ክላውድ) ላይ ፔስት አርጋቹ መላክ ትችላላቹ።

🙏እናመሰግናለን🙏

@etconp
👏9👍1🕊1💯1
The Great Pyramid of Giza:

The Great Pyramid of Giza, also known as the Pyramid of Khufu, was an incredible architectural achievement of the time and is a part of the three-pyramid structures of the Giza Pyramid Complex. The construction of the pyramid started in 2680 BC and was completed in 2560 BC during the 4th dynasty rule of Egyptian pharaoh Khufu.

The Khufu Pyramid was built using limestone blocks, and at present, there are more than 2.5 million pieces of limestone blocks keeping the structure intact. The weight of these blocks is believed to be more than 6.5 million tons.

With a height of 147 m, the Great Pyramid of Giza remained the tallest structure in the world for more than 3800 years till the time Lincoln Cathedral's spire soared 160 m into the air.


👉 Can We Build the Great Pyramid Today?

@etconp
👍2💯1
Keys to Operating a Successful Construction Business

In order to run a successful construction business, it is suggested to work with the below guidelines.

✨Embrace Technology
✨Have a Revolutionary Strategy
✨Keep Detailed Records
✨Delight Clients
✨Invest in a Committed Team
✨Have a Unique Marketing Plan

Beginning and operating a successful construction business is both rewarding and challenging.

For you to succeed, you must remain focused, disciplined and persevere.

#Share

@etconp
👍3🙏1
📌የ ምስራች ዜና ለ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በ ሙሉ

🏗በ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በ ተቋራጭነት፣በ ኢንተርየር ዲዛይን፣በ ሰብ ኮንትራክት፣በ ብረታ ብረት፣በ እንጨት ስራ እና የ ህንፃ ግንባታ ተያያዥ ስራዎች ያላቹ በ ሙሉ

🗞አዳዲስ ጨረታዎች ሲወጡ፣ ዕለታዊ የማተርያል ና ማሽነሪ Cost ለማወቅ በቀላሉ በ Private ቴሌግራም ቻናል አመቱን ሙሉ በ ማይታመን ዋጋ áŠĽáŠ•á‹˛á‹°áˆ­áˆłá‰š ለምትፈልጉ ከታች ባሉት አደራሻዎች አናግሩን።

👊እስካሁን ከ ደረጃ 1 እስከ 10 በዛ ያሉ
በየቀኑ አዳዲስ ጨረታዎች እየለጠፍን እንገኛለን

🚧ለመመዝገብ @Philemona7 ወይም @etconpworks ያናግሩን።

☎️ለ በለጠ መረጃ በ +251925446661 ወይም 0707444849 ይደውሉ

🙏እናመሰግናለን🙏

@etconp
👏6👍2👌2❤1
በአገራችን ያሉ ግንባታዎችና የርዕደ መሬት  አደጋዎችን የመቋቋም አቅማቸው።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በኢትዮጵያ የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ የሚገኙ ግንባታዎች ለመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የተጋላጭነታቸው መጠን እና የምህንድስና ሙያተኞች የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ አካሂዷል፡፡

በመድረኩ መክፈቻ ስነስርዓት ላይ የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ ባስተላለፉት መልዕክት ሰው  እና ግንባታ  ረዘም ያሉ ዘመናትን የተሻገረ ታሪክ እንዳላቸው የድርሳናትን እማኝነት  አውስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊከሰትባቸው የሚችሉ አካባቢዎች ስለመኖራቸው ሳይንሳዊ ማረጋገጫዎች እንዳሉም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ በቅርቡ በቱርክና በሶሪያ አገሮች  ላይ በርዕደ መሬት መከሰት ምክንያት የደረሱ አደጋዎችን መጠን ያወሱት ኢንጅነር መስፍን ኮድና ስታንዳርድ በአግባቡ ተጠብቆ የተከናወኑ ግንባታዎች የተከሰተውን አደጋ ተቋቁመው  ሰለባ ከመሆን እንደዳኑ፣ በተቃራኒው ደህንነታቸው ተጠብቆ ያልተገነቡ ደግሞ የደረሰባቸው የአደጋው መጠን ምንያህል እንደሆነ እማኝነቱን አውስተዋል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ በዘርፉ የተሰማሩ ሙያተኞች፣ ተዋናዮች  እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በዚህ ረገድ  ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ፣  በጥልቀት ማሰብ እና በስፋት መመልመር እንደሚገባ በሀገራቱ ላይ የደረሰው አደጋ  ማሳያ  ነው ብለዋል፡፡

መድረኩም በዚህ ረገድ ሳይንሳዊ የእይታ መጠንን ለማስፋት፣  በሀገር ደረጃ ቀደም ሲል የተከናወኑ  ግንባታዎች በመሬት ውስጣዊ ኃይል ሊከሰት የሚችል የመሬት መንቀጥቀጥን ምን ያህል ሊቋቋሙ ይችላሉ ብሎ ለማሰብ አንዱ የትኩረት አላማ ነው ብለዋል፡፡  በሁለተኛ ደረጃ አሁን እየተካሄዱ ያሉ ግንባታዎች ረገድ የኢትዮጵያ የግንባታ ኮዶችና ስታንዳርዶች   እንዲሁም ወደፊት የሚከናወኑ ግንባታዎችን በጥብቅ ሙያዊ ስነምግባር ማስተግበር እንደሚገባ ማንቃትና ማስገንዘብ ሌላው ዓላማ ነው ብለዋል፡፡ 

የግንባታ ኮዶችና ስታንዳርዶች  ብቃትንና የመሬት መንቀጥቀጥ ሊያስከትላቸው የሚችሉ አደጋዎችን በመቋቋምና በማስጠበቅ  ረገድ ያሉባቸውን   ክፍተቶች በመለየት ቀጣይ ተግባራትን በትኩረት ለማከናወን የሚያስችል የጋራ ቅንጅትን ለማጠናከር  መድረኩ ቁልፍ ሚና እንዳለውም ገልፀዋል፡፡በመድረኩ ላይ የዘርፉ የፌዴራል ተቋማት ባለድርሻዎች፣  የክልሎች የኮንስትራክሽ ቢሮ የስራ ኃላፊዎች፣ ከ70 ከተሞች የተውጣጡ የህንፃ ሹሞች፣ የዘርፉ ሙያ ማህበራት ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡  

Via ኢኮባ

@etconp
👍4❤1
This bamboo-inspired supertall skyscraper is coming to Singapore. Designed by SOM (the same design firm which designed Burj khalifa) , the 305-metre structure will become the city's new tallest building

በቀርቀሀ 305 ሜትር ከፍታ ያለው ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ንድፍ ተነደፈለት ይህን ንድፍ ያዘጋጀው አማካሪ ድርጅት በርጅ ካሊፋን የነደፈው (design ያረገው) አሁን ደግሞ በ አዲስ ሀሳብ ብቅ ብሏል

@etconp

Twitter:- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
❤4👍2
ተቋራጭን ከሳይት ስለማባረር/Expel right/
------------- --------------- --------
በዚህ ጽሁፍ ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብት ለማን የተሰጠ ነው?በየትኛው ህግ?በምን ሁኔታ?በየትኛው የውል አይነት?በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት?የሚሉትን በአጭሩ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡

#ይህ መብት ያለው የትኛው አካል ነው? የሚለውን በተመለከተ ተቋራጭን ከግንባታ ሳይት/ከግንባታ ስፍራ ለማባረር መብት ያለው አሰሪው ነው፡፡ስለዚህ መብቱ የግንባታው ባለቤት ወይም የአሰሪው ነው፡፡ስለዚህ ይህን መብት ተቋራጮች ሆኑ አሰሪ ያልሆነ ሌላ አካል ተግባራዊ ሊያደርገው አይችልም ማለት ነው፡፡

#በየትኛው ህግ? ለሚለው ምላሹ በፍትሀብሄር ህጉ እና በጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት ነው፡፡በዝርዝር ሲታይ፡-
-በግንባታ ውሎች በተለይ ጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት መጠቀም የተለመደ ነው፡፡እነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች በራሳቸው ህግ አይደሉም፡፡እዚህ ላይ አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች እንደ መመሪያ እና ህግ ስለሚቆጥሩት ይህ የግንዛቤ ክፍተት መታረም ይኖርበታል፡፡የግንባታ ውል ተዋዋዮች በስምምነታቸው እነዚህን ጀኔራል ኮንዲሽኖች የውሉ አካል ሲያደርጓቸው በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731 መሰረት በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ፡፡እዚህ ላይ ሌላው ጉዳይ ስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ተብለው የሚቀመጡት ከጀኔራል ኮንዲሽኑ ድንጋጌዎች የተፈጻሚነት ቅድሚያ ይኖራቸዋል፡፡ለምሳሌ ከነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ውስጥ የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/Standard condition of contract for the construction of civil work projects/ አንዱ ነው፡፡ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን በከተማ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀ ሲሆን ይዘቱ በዋናነት ከFIDIC 1987 version የተወሰደ ነው፡፡በአብዛኛው MoWUD 1994 ተብሎ ይጠራል፡፡ሆኖም ዋናው ነጥብ ተዋዋዮች ጥቅም ላይ ያዋሉትና የውላቸው አካል ያደረጉት የትኛውን ጀኔራል ኮንዲሽን እንደሆነ መለየትና ማወቅ የግድ ይላል፡፡
-ከዚህ አንጻር MoWUD 1994 ክሎዝ 63 ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብትን አስመልክቶ በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት በዋናነት አማካሪ መሀንዲሱ ለአሰሪው የተቋራጩን እንደውሉ ያለመፈጸም ሲያሳውቅ በተለይም ተቋራጩ ስራውን እንደተወው አማካሪው ሲያስታውቅ፣ተቋራጩ በአማካሪ መሀንዲሱ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ለ28ቀናት ስራውን ሳይጀምር ሲቀር፣በመሀንዲሱ ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ የግንባታ ቁሳቁሶችን በ28 ቀናት ውስጥ ከሳይት ያላስወጣ እንደሆነ፣በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ስራውን በውሉ አግባብ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ፣አማካሪ መሀንዲሱ እየከለከለው የስራውን ክፍል ለሌላ ተቋራጭ አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ወይም ተቋራጩ የከሰረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት ማባረር የሚችል ይሆናል፡፡በዚህ ጊዜ ውሉ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡/Termination of contract/
-በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3288 አና ተከታዮቹ ላይ የተደነገገውም ተቋራጩ የውል ግዴታውን ባልፈጸመ ጊዜ የግንባታ ባለቤት ለሆነው ለአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ስራውን ከተቋራጩ ለመንጠቅ እና ውሉ ሳይቋረጥ ስራው በስራ መሪ ስር ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ መብት ይሰጠዋል፡፡እንዲሁም ውሉ ሊሰረዝ የሚችልበት ፈቃጅ የውል ቃል በግንባታ ውሉ ላይ ያለ እንደሆነ አሰሪው ቀሪውን ስራ ለሌላ ተቋራጭ በጨረታ ወይም በስምምነት በማሰራት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ይችላል፡፡/የፍ/ህ/ቁ 3291(1) በዚህም ምክንያት አሰሪው ለተጨማሪ ወጭ/Additional cost/ የተዳረገ እንደሆነ ከተቋራጩ ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 3291(2) በግልጽ መብት ይሰጠዋል፡፡ሆኖም በውል ህግ ላይ አሰሪው የተቋራጩን ግዴታ በሚያከብድ ሁኔታ ቀሪውን ስራ ማከናወን እንደሌለበት የሚያስገነዝበውን ግዴታውንም ማክበር አለበት፡፡
#በየትኛው የውል አይነት? ለሚለው በዋናነት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውሎችን በሚመለከት ሊተገበር የሚችል ነው፡፡ በግል የግንባታ ውሎች/private construction contract/ በተለይ ከፍ/ህ/ቁ 2610 እና ተከታዮቹ እንዲሁም ከፍ/ህ/ቁ 3019 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ውስጥ ተቋራጭን ስለማባበር አስመልክቶ ግልጽ ድንጋጌ አለመኖሩ ይህ መብት ለግለሰቦች ለመተግበር አስቸጋሪ የመሆኑን ሁኔታ ታሳቢ ተደርጐ በህግ አውጭው በማወቅ/ፐርፐዝሊ/ የተተወ ይመስላል፡፡ተዋዋዮች የግንባታ ውል ሲዋዋሉ ጀኔራል ኮንዲሽን ቢጠቀሙና በዚህም ስለተቋራጭ የማባረር መብት ድንጋጌ ቢኖረውስ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል?ይሄን እንዴት ይተገብረዋል የሚለው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ውሉ ግን ለተዋዋዮች ህግ ስለሚሆን በተቻለ መጠን ሊተገበር ይገባዋል የሚል እሳቤ አለኝ፡፡
#በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት? ለሚለው በዋናነት በ MoWUD 1994 ክሎዝ 63(2) ላይ እንደተቀመጠው በግንባታ ሳይት ላይ የተገኘ ቁሳቁስ በሙሉ በዝርዝር መመዝገብና ዋጋ ወጥቶለት መጠኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡በተቋራጩ የተሰራው ስራ መጠን/level of work done/ በትክክል መታወቅና በዝርዝር መመዝገብ አለበት፡፡ተቋራጩ ያለበት እዳ/ከወሰደው የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ ያልመለሰው ማለት ነው/ መታወቅ አለበት፡፡ለተቋራጩ የተከፈለው የስራ ክፍያ ሊታወቅ ይገባል፡፡እነዚህን የሂሳብ ሁኔታዎች አመዛዝኖ እና ዋጋ አስቀምጦ ተቋራጩ የሚከፈለው ገንዘብ ካለ እንዲከፈለው ለአሰሪው የሚመልሰው ገንዘብ ካለም እንዲመልስ ሂሳብ የማስተሳሰብና ሪፖርት የማቅረብ ሀላፊነቱ የአማካሪ መሀንዲሱ ነው፡፡በዚህ ረገድ አማካሪ መሀንዲሶች ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሪፖርት ስለማያቀርቡ የግንባታ ክርክሮች ያልተሸከፉ ይሆኑና ለፍርድ ቤቶች ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስቸገሪ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡
#አሰሪው ይህን መብቱን ለመጠቀም ሀይል መጠቀም የሚችልበት ግልጽ ፈቃጅ ህግ ግን የለም፡፡
#በመጨረሻም አሰሪና ተቋራጮች ለግንባታ ጥራት በመስራትና ለትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር በመተባበር የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እድገት እንዲያሳይ ማገዝና አለመግባባቶችን በስምምነት መፍታት ቢችሉ ጠቀሜታው ለሀገርም ለራሳቸውም ነው፡፡በአሰሪና ተቋራጭ ክርክር ብዙ ትምህርት ቤት እና የጤና ተቋም እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታቸው ተቋርጦ ማህበረሰቡን ከተጠቃሚነት የሚያዘገይበት ሁኔታ ወደፊት ተቀርፎና ተቃልሎ ማየት የዘወትር ምኞታችን ነው፡፡

Via Gubaie Asefa

#ConstructionLaw

@etconp
👍20👏5❤1
ቢሾፍቱ ከተማን ወደ ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ ጌታቸዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት ከተማዋን ወደ ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማ የማሳደግ ስራ እየተሳራ ሲሆን አወቃቀሯንም በመቀየር እንደ አዳማ እና ሻሸመኔ ሁሉ ቢሾፍቱም በክፍለ ከተማ እና ወረዳ እንድትደራጅ መደረጉን አንስተዋል።

ቢሾፍቱ ከበፊት ስፋቷን በመጨመር አምስት ትናንሽ ከተሟችን ወደራሷ በመቀላቀል 1ሺ 52 ሄክታር ስፋት እንዲኖራት መደረጉንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የቢሾፍቱ ከተማን በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የቢሾፍቱ ማዘጋጃ ቤት ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

ለዚህም ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹና ደረጃዋን የጠበቀች ለማድረግ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 46 አዲስ ፕሮጀክቶች እና 26 ነባር በድምሩ 72 ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሚገኙ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት አስታውቆ፣ ከፕሮጀክቶቹ መካከልም የመንገድ፣ የኮብል ስቶን ንጣፍ ፣የጋር መኖሪያ ቤቶች፣ቤተ መጻሕፍት እንዲሁም የውሀ ፕሮጀክቶች እንደሚገኙባቸው ጠቅሶ ነበር፡፡

@etconp
👍10❤3
Self weight (dead load = volume of the space they occupy x unit weight) + live load (applied load that varies)

From the roof truss to TOP TIE BEAM then to columns then to foundation footing (we need good soil to bear the load)

What are the variables G,M,F & NGL ?

Next time I’ll post section(AR), foundation layout and reaction in each footing (excel file) then we will see how we design footing given the bearing capacity of the soil

በቀጣይ ሴክሽን፣ ጠቅላላ የ ፊቲንግ አቀማመጥ እና በ ኤግዜል ፋይል ከየ ኮለኑ የሚመጣውን ክብደት አርጌ ለቅላችኋለው ከዛም እንዴት ንድፍ እንደሚወጣለት እናያለን የ አፈሩ የመሸከም አቅምም ይሰጣችኋል።

@etconp

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍5❤3💯1
👉ስለ ብርሃን የሚያሳልፍ ኮንክሪት ያውቃሉ?

ብርሃንን የሚያሳልፍ ኮንክሪት ( Transparent concrete ) የኮንክሪት አይነት ሆኖ ከምናውቀው ከኮንክሪት የሚለየው በውስጡ ብርሃንን ማሳለፉ ነው።

ይህ የኮንክሪት አይነት ከተለመደው የኮንክሪት አይነት በተለየ የተለየ አግሪጌትን ይጠቀማል (Aggregate ~gravel+add mixtures) ማለትም ብርሃን አሳላፊ የአግሪጌት አይነቶችን ይጠቀማል።

በዚህ የኮንክሪት አይነት እንደዋና የአግሪጌት ግብአት ምንጠቀመው ፋይበር ኦፕቲክስ ነው (fiber optics) እና Glass fiber ነው

ብርሃን አሳላፊ ኮንክሪት ለመጀመሪያ ግዜ የተዋወቀው በ2001 G.C በኃንጋሪያዊው አርክቴክት Aronlosonzi ነው

ብርሃን አሳላፊ ኮንክሪት አሰራሩ ከ4-5% (by volume) የፋይበር ኦፕአቲክስን ከደቃቅ ኮንክሪት (ደቃቅ ኮንክሪት በጣም ከደቀቀ የአሸዋና የሲሚንቶ ውህድ ነው) ጋር በማቀላቀል ነው ይህ ኮንክሪት ከተለመደው የኮንክሪት አይነት የወረደ ጥንካሬ አለው።

የምንጠቀመው የግብአት አይነት

ሲሚንቶ - ኦርድናሪ ፖርትላንድ ሰመንት ተመራጭ ነው

አሸዋ - 1.18mm seive ያነሰ መጠን ያለው በጥራቱም ላቅ ያለ መሆን አለበት

ውሃ- ለመጠጥ አገልግሎት የምንጠቀመው ውሃ ተመራጭ ነው ምክንያቱ turbid የሆነ ውሃ የብርሃን የማስተላለፍ አቅሙን ይቀንስብናል

Optical fiber- ኮንተንቱ ከ4-5% በvolume መሆን አለበት ቅጥነቱ (thickness) ደግሞ እንደየብርሃን የማስተላለፍ ልኩ ከ 2 µm እስከ 2 mm ሊሆን ይችላል::

የዚህ ኮንክሪት compressive strength በትክክል ከተሰራ እስከ 70Mpa ሊደርስ ይችላል

#ConcreteTechnology

@etconp
👍20❤1👌1