Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ተቋራጭን ከሳይት ስለማባረር/Expel right/
------------- --------------- --------
በዚህ ጽሁፍ ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብት ለማን የተሰጠ ነው?በየትኛው ህግ?በምን ሁኔታ?በየትኛው የውል አይነት?በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት?የሚሉትን በአጭሩ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡

#ይህ መብት ያለው የትኛው አካል ነው? የሚለውን በተመለከተ ተቋራጭን ከግንባታ ሳይት/ከግንባታ ስፍራ ለማባረር መብት ያለው አሰሪው ነው፡፡ስለዚህ መብቱ የግንባታው ባለቤት ወይም የአሰሪው ነው፡፡ስለዚህ ይህን መብት ተቋራጮች ሆኑ አሰሪ ያልሆነ ሌላ አካል ተግባራዊ ሊያደርገው አይችልም ማለት ነው፡፡

#በየትኛው ህግ? ለሚለው ምላሹ በፍትሀብሄር ህጉ እና በጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት ነው፡፡በዝርዝር ሲታይ፡-
-በግንባታ ውሎች በተለይ ጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት መጠቀም የተለመደ ነው፡፡እነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች በራሳቸው ህግ አይደሉም፡፡እዚህ ላይ አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች እንደ መመሪያ እና ህግ ስለሚቆጥሩት ይህ የግንዛቤ ክፍተት መታረም ይኖርበታል፡፡የግንባታ ውል ተዋዋዮች በስምምነታቸው እነዚህን ጀኔራል ኮንዲሽኖች የውሉ አካል ሲያደርጓቸው በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731 መሰረት በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ፡፡እዚህ ላይ ሌላው ጉዳይ ስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ተብለው የሚቀመጡት ከጀኔራል ኮንዲሽኑ ድንጋጌዎች የተፈጻሚነት ቅድሚያ ይኖራቸዋል፡፡ለምሳሌ ከነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ውስጥ የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/Standard condition of contract for the construction of civil work projects/ አንዱ ነው፡፡ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን በከተማ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀ ሲሆን ይዘቱ በዋናነት ከFIDIC 1987 version የተወሰደ ነው፡፡በአብዛኛው MoWUD 1994 ተብሎ ይጠራል፡፡ሆኖም ዋናው ነጥብ ተዋዋዮች ጥቅም ላይ ያዋሉትና የውላቸው አካል ያደረጉት የትኛውን ጀኔራል ኮንዲሽን እንደሆነ መለየትና ማወቅ የግድ ይላል፡፡
-ከዚህ አንጻር MoWUD 1994 ክሎዝ 63 ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብትን አስመልክቶ በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት በዋናነት አማካሪ መሀንዲሱ ለአሰሪው የተቋራጩን እንደውሉ ያለመፈጸም ሲያሳውቅ በተለይም ተቋራጩ ስራውን እንደተወው አማካሪው ሲያስታውቅ፣ተቋራጩ በአማካሪ መሀንዲሱ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ለ28ቀናት ስራውን ሳይጀምር ሲቀር፣በመሀንዲሱ ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ የግንባታ ቁሳቁሶችን በ28 ቀናት ውስጥ ከሳይት ያላስወጣ እንደሆነ፣በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ስራውን በውሉ አግባብ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ፣አማካሪ መሀንዲሱ እየከለከለው የስራውን ክፍል ለሌላ ተቋራጭ አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ወይም ተቋራጩ የከሰረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት ማባረር የሚችል ይሆናል፡፡በዚህ ጊዜ ውሉ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡/Termination of contract/
-በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3288 አና ተከታዮቹ ላይ የተደነገገውም ተቋራጩ የውል ግዴታውን ባልፈጸመ ጊዜ የግንባታ ባለቤት ለሆነው ለአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ስራውን ከተቋራጩ ለመንጠቅ እና ውሉ ሳይቋረጥ ስራው በስራ መሪ ስር ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ መብት ይሰጠዋል፡፡እንዲሁም ውሉ ሊሰረዝ የሚችልበት ፈቃጅ የውል ቃል በግንባታ ውሉ ላይ ያለ እንደሆነ አሰሪው ቀሪውን ስራ ለሌላ ተቋራጭ በጨረታ ወይም በስምምነት በማሰራት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ይችላል፡፡/የፍ/ህ/ቁ 3291(1) በዚህም ምክንያት አሰሪው ለተጨማሪ ወጭ/Additional cost/ የተዳረገ እንደሆነ ከተቋራጩ ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 3291(2) በግልጽ መብት ይሰጠዋል፡፡ሆኖም በውል ህግ ላይ አሰሪው የተቋራጩን ግዴታ በሚያከብድ ሁኔታ ቀሪውን ስራ ማከናወን እንደሌለበት የሚያስገነዝበውን ግዴታውንም ማክበር አለበት፡፡
#በየትኛው የውል አይነት? ለሚለው በዋናነት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውሎችን በሚመለከት ሊተገበር የሚችል ነው፡፡ በግል የግንባታ ውሎች/private construction contract/ በተለይ ከፍ/ህ/ቁ 2610 እና ተከታዮቹ እንዲሁም ከፍ/ህ/ቁ 3019 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ውስጥ ተቋራጭን ስለማባበር አስመልክቶ ግልጽ ድንጋጌ አለመኖሩ ይህ መብት ለግለሰቦች ለመተግበር አስቸጋሪ የመሆኑን ሁኔታ ታሳቢ ተደርጐ በህግ አውጭው በማወቅ/ፐርፐዝሊ/ የተተወ ይመስላል፡፡ተዋዋዮች የግንባታ ውል ሲዋዋሉ ጀኔራል ኮንዲሽን ቢጠቀሙና በዚህም ስለተቋራጭ የማባረር መብት ድንጋጌ ቢኖረውስ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል?ይሄን እንዴት ይተገብረዋል የሚለው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ውሉ ግን ለተዋዋዮች ህግ ስለሚሆን በተቻለ መጠን ሊተገበር ይገባዋል የሚል እሳቤ አለኝ፡፡
#በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት? ለሚለው በዋናነት በ MoWUD 1994 ክሎዝ 63(2) ላይ እንደተቀመጠው በግንባታ ሳይት ላይ የተገኘ ቁሳቁስ በሙሉ በዝርዝር መመዝገብና ዋጋ ወጥቶለት መጠኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡በተቋራጩ የተሰራው ስራ መጠን/level of work done/ በትክክል መታወቅና በዝርዝር መመዝገብ አለበት፡፡ተቋራጩ ያለበት እዳ/ከወሰደው የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ ያልመለሰው ማለት ነው/ መታወቅ አለበት፡፡ለተቋራጩ የተከፈለው የስራ ክፍያ ሊታወቅ ይገባል፡፡እነዚህን የሂሳብ ሁኔታዎች አመዛዝኖ እና ዋጋ አስቀምጦ ተቋራጩ የሚከፈለው ገንዘብ ካለ እንዲከፈለው ለአሰሪው የሚመልሰው ገንዘብ ካለም እንዲመልስ ሂሳብ የማስተሳሰብና ሪፖርት የማቅረብ ሀላፊነቱ የአማካሪ መሀንዲሱ ነው፡፡በዚህ ረገድ አማካሪ መሀንዲሶች ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሪፖርት ስለማያቀርቡ የግንባታ ክርክሮች ያልተሸከፉ ይሆኑና ለፍርድ ቤቶች ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስቸገሪ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡
#አሰሪው ይህን መብቱን ለመጠቀም ሀይል መጠቀም የሚችልበት ግልጽ ፈቃጅ ህግ ግን የለም፡፡
#በመጨረሻም አሰሪና ተቋራጮች ለግንባታ ጥራት በመስራትና ለትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር በመተባበር የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እድገት እንዲያሳይ ማገዝና አለመግባባቶችን በስምምነት መፍታት ቢችሉ ጠቀሜታው ለሀገርም ለራሳቸውም ነው፡፡በአሰሪና ተቋራጭ ክርክር ብዙ ትምህርት ቤት እና የጤና ተቋም እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታቸው ተቋርጦ ማህበረሰቡን ከተጠቃሚነት የሚያዘገይበት ሁኔታ ወደፊት ተቀርፎና ተቃልሎ ማየት የዘወትር ምኞታችን ነው፡፡

Via Gubaie Asefa

#ConstructionLaw

@etconp
👍20👏5❤1
ቢሾፍቱ ከተማን ወደ ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ ጌታቸዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት ከተማዋን ወደ ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማ የማሳደግ ስራ እየተሳራ ሲሆን አወቃቀሯንም በመቀየር እንደ አዳማ እና ሻሸመኔ ሁሉ ቢሾፍቱም በክፍለ ከተማ እና ወረዳ እንድትደራጅ መደረጉን አንስተዋል።

ቢሾፍቱ ከበፊት ስፋቷን በመጨመር አምስት ትናንሽ ከተሟችን ወደራሷ በመቀላቀል 1ሺ 52 ሄክታር ስፋት እንዲኖራት መደረጉንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የቢሾፍቱ ከተማን በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የቢሾፍቱ ማዘጋጃ ቤት ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

ለዚህም ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹና ደረጃዋን የጠበቀች ለማድረግ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 46 አዲስ ፕሮጀክቶች እና 26 ነባር በድምሩ 72 ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሚገኙ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት አስታውቆ፣ ከፕሮጀክቶቹ መካከልም የመንገድ፣ የኮብል ስቶን ንጣፍ ፣የጋር መኖሪያ ቤቶች፣ቤተ መጻሕፍት እንዲሁም የውሀ ፕሮጀክቶች እንደሚገኙባቸው ጠቅሶ ነበር፡፡

@etconp
👍10❤3
Self weight (dead load = volume of the space they occupy x unit weight) + live load (applied load that varies)

From the roof truss to TOP TIE BEAM then to columns then to foundation footing (we need good soil to bear the load)

What are the variables G,M,F & NGL ?

Next time I’ll post section(AR), foundation layout and reaction in each footing (excel file) then we will see how we design footing given the bearing capacity of the soil

በቀጣይ ሴክሽን፣ ጠቅላላ የ ፊቲንግ አቀማመጥ እና በ ኤግዜል ፋይል ከየ ኮለኑ የሚመጣውን ክብደት አርጌ ለቅላችኋለው ከዛም እንዴት ንድፍ እንደሚወጣለት እናያለን የ አፈሩ የመሸከም አቅምም ይሰጣችኋል።

@etconp

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍5❤3💯1
👉ስለ ብርሃን የሚያሳልፍ ኮንክሪት ያውቃሉ?

ብርሃንን የሚያሳልፍ ኮንክሪት ( Transparent concrete ) የኮንክሪት አይነት ሆኖ ከምናውቀው ከኮንክሪት የሚለየው በውስጡ ብርሃንን ማሳለፉ ነው።

ይህ የኮንክሪት አይነት ከተለመደው የኮንክሪት አይነት በተለየ የተለየ አግሪጌትን ይጠቀማል (Aggregate ~gravel+add mixtures) ማለትም ብርሃን አሳላፊ የአግሪጌት አይነቶችን ይጠቀማል።

በዚህ የኮንክሪት አይነት እንደዋና የአግሪጌት ግብአት ምንጠቀመው ፋይበር ኦፕቲክስ ነው (fiber optics) እና Glass fiber ነው

ብርሃን አሳላፊ ኮንክሪት ለመጀመሪያ ግዜ የተዋወቀው በ2001 G.C በኃንጋሪያዊው አርክቴክት Aronlosonzi ነው

ብርሃን አሳላፊ ኮንክሪት አሰራሩ ከ4-5% (by volume) የፋይበር ኦፕአቲክስን ከደቃቅ ኮንክሪት (ደቃቅ ኮንክሪት በጣም ከደቀቀ የአሸዋና የሲሚንቶ ውህድ ነው) ጋር በማቀላቀል ነው ይህ ኮንክሪት ከተለመደው የኮንክሪት አይነት የወረደ ጥንካሬ አለው።

የምንጠቀመው የግብአት አይነት

ሲሚንቶ - ኦርድናሪ ፖርትላንድ ሰመንት ተመራጭ ነው

አሸዋ - 1.18mm seive ያነሰ መጠን ያለው በጥራቱም ላቅ ያለ መሆን አለበት

ውሃ- ለመጠጥ አገልግሎት የምንጠቀመው ውሃ ተመራጭ ነው ምክንያቱ turbid የሆነ ውሃ የብርሃን የማስተላለፍ አቅሙን ይቀንስብናል

Optical fiber- ኮንተንቱ ከ4-5% በvolume መሆን አለበት ቅጥነቱ (thickness) ደግሞ እንደየብርሃን የማስተላለፍ ልኩ ከ 2 µm እስከ 2 mm ሊሆን ይችላል::

የዚህ ኮንክሪት compressive strength በትክክል ከተሰራ እስከ 70Mpa ሊደርስ ይችላል

#ConcreteTechnology

@etconp
👍20❤1👌1
G+8 Office Building +Meeting Hall
Consulting firm:LIHIKET DESIGN CONSTRUCTION AND SUPERVISION
Structural design: Edoniyas. B
Architectural design: Hanamariam

Structural Analysis and Design:
Seismic Zone: 1
Structural Type: Dual shear wall+Frame
Software: Csi ETABS and Csi Safe+SAP.
✔BUILDING CODES: ES EN1991: "Minimum Design Loads for Buildings
✓ SEISMIC DESIGN:
Seismic Provisions for Structural Design based on ES EN 1998:2015
✔Structural framing checks is performed through CSI ETABS software undertaking both static and non-static seismic force calculations. Stiffness coefficients applied to slab, beam, column and wall sectional properties adopt cracked concrete sections for both service and ultimate state.

@etconp
❤8👍5
You are given foundation layout (you can get foundation ID from) you are given the section you can see how many stories there are and you are given the reaction (excel file)

Design F1, F2 and F3 type footings

@etconp
👍5❤4
CV እንዴት ይጻፋል

CV ማለት የአንድ ሰው የትምህርትና ሌሎች professional ታሪኮቹን በአጭር መልኩ የሚገለፅበት መንገድ ነው፡፡

ብዙ ግዜ ለስራ ማመልከቻነት እንጠቀምበታለን የራሳችንንም ማንነት በጥሩና ቀለል ባለ መልኩ ለማቅረብ ያስችለናል፡፡

ታዲያ በዚህ ወቅት እንዲቀጥሩን ለምንፈልጋቸው ቀጣሪዎች አሰልቺ ያልሆነና ሳቢ የሆነ CV መፃፍ ትልቅ ትኩረት ለማግኘት ያስችለናል፡፡

ታዲያ እንዴት እንዲህ ያለውን CV መፃፍ እንችላለን እና ምን ምን መካተት አለበት የሚለውን እንመልከት፡፡

፩ ከቀድሞ ስራ ጋር የተያያዙ የስራ ልምዶች፡፡
.
፪ የትምህርት ሁኔታ እና ሌሎች ተዛማጅ ችሎታዎች
.
፫ አፃፃፋችሁን ለማንበብ እና ለመረዳት ቀለል ባለመልኩ ይሁን
.
፬ የስራ ልምድ ካላችሁ በቀደመው ስራችሁ ያሳካችኋቸውን ነገሮች ጥቀሱ፡፡

ጀማሪ ከሆናችሁ ደግሞ በነፃ አገልግሎት
እንዲሁም በተማራችሁበት የትምህርት ተቋም ስታደርጉ የነበረውን መልካም እንቅስቃሴ ጥቀሱ፡፡
.
፭ ፊደላት እና ቃላት አጠቃቀም ትኩረት ማድረግ ፡፡
.
፮ እናንተ በመስሪያ ቤቱ ብትቀጠሩ ልታበረክቱ
የምትፈልጉትንና እናንተ በመቀጠራችሁ በመስሪያ ቤቱ ስኬት ላይ
ልትጨምሩ የምትፈልጉትን ጥቀሱ
.
፯ አድራሻችሁን ስትጠቅሱ የተለያዩ አማራጮችን
አስቀምጡ፡ ስልክ ኢሜይል፡፡
.
፰ ሪፈረንስ ስትጠቅሱ ስለእናንተ በደንብ ሊገልፅ የሚችል
ሰው ይሁን፡፡
.
፱ ከሁለት ገፅ ባይበልጥ መልካም ነው አሰለቺ እንዳይሆን
.
.
ተጠንቀቁ

~ማድረግ የሌለባችሁ

1 የቃላትና ፊደላት ግድፈት እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡
.
2 የማይሰራና የማትገኙበትን አድራሻ አትጠቀሙ፡፡
.
3 ራሳችሁን ስትገልፁ ግልፅ ያልሆነና የሚያሻማ እንዳይሆን
.
4 ውሸት!!! ውሸት ወንዝ አያሻግርም በፍፁም አትዋሹ፡፡
.
እውነተኛው ማንነታችሁን ብቻ ግለፁ፡፡

እስኪ እነዚህን ነገሮች በ CVዎቻችሁ ላይ አካቷቸው ጥሩ ነገር እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

እናንተ ያወቃችሁትን ሌሎች ወዳጆቻችሁ እንዲደርሳቸው ሼር ያድርጉ፡፡

@etconp
👍26❤1