You are given foundation layout (you can get foundation ID from) you are given the section you can see how many stories there are and you are given the reaction (excel file)
Design F1, F2 and F3 type footings
@etconp
Design F1, F2 and F3 type footings
@etconp
👍5❤4
CV እንዴት ይጻፋል
CV ማለት የአንድ ሰው የትምህርትና ሌሎች professional ታሪኮቹን በአጭር መልኩ የሚገለፅበት መንገድ ነው፡፡
ብዙ ግዜ ለስራ ማመልከቻነት እንጠቀምበታለን የራሳችንንም ማንነት በጥሩና ቀለል ባለ መልኩ ለማቅረብ ያስችለናል፡፡
ታዲያ በዚህ ወቅት እንዲቀጥሩን ለምንፈልጋቸው ቀጣሪዎች አሰልቺ ያልሆነና ሳቢ የሆነ CV መፃፍ ትልቅ ትኩረት ለማግኘት ያስችለናል፡፡
ታዲያ እንዴት እንዲህ ያለውን CV መፃፍ እንችላለን እና ምን ምን መካተት አለበት የሚለውን እንመልከት፡፡
፩ ከቀድሞ ስራ ጋር የተያያዙ የስራ ልምዶች፡፡
.
፪ የትምህርት ሁኔታ እና ሌሎች ተዛማጅ ችሎታዎች
.
፫ አፃፃፋችሁን ለማንበብ እና ለመረዳት ቀለል ባለመልኩ ይሁን
.
፬ የስራ ልምድ ካላችሁ በቀደመው ስራችሁ ያሳካችኋቸውን ነገሮች ጥቀሱ፡፡
ጀማሪ ከሆናችሁ ደግሞ በነፃ አገልግሎት
እንዲሁም በተማራችሁበት የትምህርት ተቋም ስታደርጉ የነበረውን መልካም እንቅስቃሴ ጥቀሱ፡፡
.
፭ ፊደላት እና ቃላት አጠቃቀም ትኩረት ማድረግ ፡፡
.
፮ እናንተ በመስሪያ ቤቱ ብትቀጠሩ ልታበረክቱ
የምትፈልጉትንና እናንተ በመቀጠራችሁ በመስሪያ ቤቱ ስኬት ላይ
ልትጨምሩ የምትፈልጉትን ጥቀሱ
.
፯ አድራሻችሁን ስትጠቅሱ የተለያዩ አማራጮችን
አስቀምጡ፡ ስልክ ኢሜይል፡፡
.
፰ ሪፈረንስ ስትጠቅሱ ስለእናንተ በደንብ ሊገልፅ የሚችል
ሰው ይሁን፡፡
.
፱ ከሁለት ገፅ ባይበልጥ መልካም ነው አሰለቺ እንዳይሆን
.
.
ተጠንቀቁ
~ማድረግ የሌለባችሁ
1 የቃላትና ፊደላት ግድፈት እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡
.
2 የማይሰራና የማትገኙበትን አድራሻ አትጠቀሙ፡፡
.
3 ራሳችሁን ስትገልፁ ግልፅ ያልሆነና የሚያሻማ እንዳይሆን
.
4 ውሸት!!! ውሸት ወንዝ አያሻግርም በፍፁም አትዋሹ፡፡
.
እውነተኛው ማንነታችሁን ብቻ ግለፁ፡፡
እስኪ እነዚህን ነገሮች በ CVዎቻችሁ ላይ አካቷቸው ጥሩ ነገር እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
እናንተ ያወቃችሁትን ሌሎች ወዳጆቻችሁ እንዲደርሳቸው ሼር ያድርጉ፡፡

👍26❤1
Ethio Construction Engineering
CV እንዴት ይጻፋል CV ማለት የአንድ ሰው የትምህርትና ሌሎች professional ታሪኮቹን በአጭር መልኩ የሚገለፅበት መንገድ ነው፡፡ ብዙ ግዜ ለስራ ማመልከቻነት እንጠቀምበታለን የራሳችንንም ማንነት በጥሩና ቀለል ባለ መልኩ ለማቅረብ ያስችለናል፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት እንዲቀጥሩን ለምንፈልጋቸው ቀጣሪዎች አሰልቺ ያልሆነና ሳቢ የሆነ CV መፃፍ ትልቅ ትኩረት ለማግኘት ያስችለናል፡፡ ታዲያ እንዴት…
👉ትላንት ስለ ሲቪ አጠር ያለ ገለፃ ማረጋችን ይታወሳል
📌ዛሬ ደሞ ብዝዎች በጠየቃቹን መሠረት
📜የ CV Sample ይሀው ብለናል
👇👇👇
📌ዛሬ ደሞ ብዝዎች በጠየቃቹን መሠረት
📜የ CV Sample ይሀው ብለናል
👇👇👇
👍4
ስራ ይፈልጋሉ ?
አርኪቴክት ኖት ወይስ ሲቪል እንጂኔሪንግ ነው ያጠኑት መልካም እንግዲያውስ አውቶካድ(AUTOCAD) በደምብ ይችላሉ ? Drawing መስራት ይችላሉ ?
ከናንተ ሚጠበቀው laptop ይኑሮ ፣ smart phone ይኑሮ ባሉበት ቦታ ሆነው online መስራት ይችላሉ
ይደውሉ :- +251973267834
ጆርዳኖ/JORDANO/جوردانو

👍32👌1
The Ethiopian Construction Authority is tasked to monitor 90 public construction projects, which have been paused due to rising steel and cement prices.
Factories are citing substandard quality of inputs as the reason for diminished production.
Via - Fortune

👍10
ኮንክሪት እና የኮንክሪት ግሬዶች
.
ኮንክሪት (concrete) ስሙን ያገኘው ከጥንት ሮማኖች ሲሆን ቃሉም የመጣው ኮንክሪተስ (Concretus) ከሚለው የሮማኖች ቃል ነው የቃል በቃል ትርጉሙ ተያይዞ ማደግ / አንድ ላይ ማደግ የሚለውን ይወክላል።
.
ኮንክሪት በአለም ላይ በብዛት የምንጠቀመው የግንባታ ቁስ ነው። ኮንክሪት የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠሮች ውህድ ነው ። የኮንክሪት የእመቃ ጥንካሬ (compressive strength) ሚለካው በግሬዱ ነው (Grade)። የተለያዩ የኮንክሪት ግሬዶች አሉ C-5 ፣ C-15 C-25 C-30 ወዘተ የኮንክሪት ግሬድ ማለት ኮንክሪቱ ከሃያ ስምንት ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ (compressive strength ) ማለት ነው ለምሳላ C-25 የሆነ ኮንክሪት ግሬድ ከ28 ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ 25N/mm^2 ይሆናል ማለት ነው የC-30 ግሬድ ደግሞ ጥንካሬው 30N/mm^2 ነው
.
ለውሃ ስራዎች ብዙን ግዜ ተመራጩ የኮንክሪት ግሬድ ከ C-30 በላይ ነው
.
አንዳንድ ግዜ የኮንክሪት ግሬዶች በተለያዩ መፅሃፎች በተለያየ መልክ ይጠቀሳሉ ለምሳሌ አንዳንድ መፅሃፎች C-30 C-15 የሚለውን አጠቃቀስ ሲጠቀሙ አንዳንዶቹ ደግሞ M-30 M-15 የሚለውን ይጠቀማሉ (ከታች በምስሉ እንደተጠቀሰው) ....በ «C»የሚጠቀሱ የኮንክሪት ግሬዶች በC መጠቀሳቸው የእመቃ ጥንካሬያቸው የተለካው በሲሊንደሪካል ፍተሻ (CYLINDRICAL test ) ስለሆነ ነው በM የሚጠቀሱት ደግሞ ፍተሻው (test) የተደረገው በኪውቢክ ፍተሻ (cubic test) ስለሆነ ነው። በሁለቱ የፍተሻ አይነቶች የሚደረጉ የኮንክሪት ግሬዶች የእመቃ ጥንካሬአቸው ይለያያል። ሲሊንደሪካል ፍተሻ በአንፃራዊነት የኮንክሪትን ትክክለኛ እምቅ ጥንካሬ ይገልፃል ስለዚህ ከኪውቢክ ፍተሻው የተሻለ ነው ማለት ነው።
.
ከታች በምስሉ በኪውቢክ ፍተሻ የተደረገ የተለያዩ የኮንክሪት ግሬዶች ፣ ያላቸው የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠር ምጣኔ (ratio) እና ከ28 ቀን በኋላ የሚያገኙት ጥንካሬ ተገልጿል።

👍30👌12👏4
Ethio Construction Engineering
ስራ ይፈልጋሉ ? አርኪቴክት ኖት ወይስ ሲቪል እንጂኔሪንግ ነው ያጠኑት መልካም እንግዲያውስ አውቶካድ(AUTOCAD) በደምብ ይችላሉ ? Drawing መስራት ይችላሉ ? ከናንተ ሚጠበቀው laptop ይኑሮ ፣ smart phone ይኑሮ ባሉበት ቦታ ሆነው online መስራት ይችላሉ ይደውሉ :- +251973267834 ጆርዳኖ/JORDANO/جوردانو
የተመዘገባችሁ በሙሉ complete your information
Insert your email /ኢሜላችሁን አስገቡ
Insert phone number/ስልክ ቁጥራችሁን አስገቡ
ሌሎች ጥያቄዎችንም ሙሉ
የተሟላ profile እንዲሆን አርጉ
ከተቻለም የሰራችሁት ስራ ካላ ፎቶ load አርጉ የሰራችሁትን ስራ 3D sample display ላይ አስቀምጡ client ያገኛችኋል ደግሞ የሰራችሁትን ስራ ሌላ ሰው እንዳይወስደው ስም እና ስልክ ቁጥር የምትለጥፉበት ፎቶ ላይ አድርጉ

👍8❤1
ወጋገን ባንክ በመቀሌ ከተማ ከ 1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባለ 25 ፎቅ ሕንጸ ሊገነባ ነው
ወጋገን ባንክ በመቀሌ ከተማ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው ባለ 25 ፎቅ ሕንጻ በዛሬው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
ሕንፃው የሚገነባው በትግራይ ክልል ዋና ከተማ በመቀሌ የሚገኘው ብሔራዊ ስታዲየም አቅራቢያ በ3,500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ መሆኑን ትግራይ ቲቪ ዘግቧል።
ለባንኩ ሕንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡት ትግራይ ክልላዊ መንግሥት ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፤ "ወጋገን ባንክ ለትግራይ መልሶ ግንባታ ትልቅ ሚና ሊጫወት ይገባል" ሲሉ ማሳሰባቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።

የቦሌ ሚካኤል ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት የሚያሻሽሉ 6 የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድዮችን በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ ይገኛል ከነዚህም የቦሌ ሚካኤል የመንገድ መጋጠሚያ አንዱ ነው፡፡
የቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ከተገነቡ አዳዲስ መንገዶች ጋር ተሳስሮ ከሳሪስ አቦ ወደ ቦሌ አቅጣጫ ከሚወስደው የቀለበት መንገድ ጋር በተለያዩ መጋጠሚያዎች የሚያገናኙ የመቃረቢያ መንገዶችን ጨምሮ የቦሌ ሚካኤል የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ግንባታ እውን እንዲሆን ምክንያት ሆኗል፡፡
ፕሮጅክቱ ከ720 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ አሰር ኮንስትራክሽን የተባለ የሀገር ውስጥ የሥራ ተቋራጭ እየገነባው የሚገኝ ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ በሀይ ዌይ ኢንጂነርስ አማካሪ ኩባንያ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ቀደም ሲል 600 ሜትር ርዝመት ያለው የቦሌ ሚካኤል ትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን፣ ከአጠቃላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ ክፍል 3.8 ኪሎ ሜትሩ የመጀመርያ አስፋልት ደረጃ ለብሷል።
በተጨማሪ በቀሪው 200 ሜትር በሚሆነው የመንገዱ ክፍል የአስፋልት ንጣፍ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ምንጭ ኢፕድ

👍3👏2