Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ኮንክሪት እና የኮንክሪት ግሬዶች
.
ኮንክሪት (concrete) ስሙን ያገኘው ከጥንት ሮማኖች ሲሆን ቃሉም የመጣው ኮንክሪተስ (Concretus) ከሚለው የሮማኖች ቃል ነው የቃል በቃል ትርጉሙ ተያይዞ ማደግ / አንድ ላይ ማደግ የሚለውን ይወክላል።
.
ኮንክሪት በአለም ላይ በብዛት የምንጠቀመው የግንባታ ቁስ ነው። ኮንክሪት የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠሮች ውህድ ነው ። የኮንክሪት የእመቃ ጥንካሬ (compressive strength) ሚለካው በግሬዱ ነው (Grade)። የተለያዩ የኮንክሪት ግሬዶች አሉ C-5 ፣ C-15 C-25 C-30 ወዘተ የኮንክሪት ግሬድ ማለት ኮንክሪቱ ከሃያ ስምንት ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ (compressive strength ) ማለት ነው ለምሳላ C-25 የሆነ ኮንክሪት ግሬድ ከ28 ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ 25N/mm^2 ይሆናል ማለት ነው የC-30 ግሬድ ደግሞ ጥንካሬው 30N/mm^2 ነው
.
ለውሃ ስራዎች ብዙን ግዜ ተመራጩ የኮንክሪት ግሬድ ከ C-30 በላይ ነው
.
አንዳንድ ግዜ የኮንክሪት ግሬዶች በተለያዩ መፅሃፎች በተለያየ መልክ ይጠቀሳሉ ለምሳሌ አንዳንድ መፅሃፎች C-30 C-15 የሚለውን አጠቃቀስ ሲጠቀሙ አንዳንዶቹ ደግሞ M-30 M-15 የሚለውን ይጠቀማሉ (ከታች በምስሉ እንደተጠቀሰው) ....በ «C»የሚጠቀሱ የኮንክሪት ግሬዶች በC መጠቀሳቸው የእመቃ ጥንካሬያቸው የተለካው በሲሊንደሪካል ፍተሻ (CYLINDRICAL test ) ስለሆነ ነው በM የሚጠቀሱት ደግሞ ፍተሻው (test) የተደረገው በኪውቢክ ፍተሻ (cubic test) ስለሆነ ነው። በሁለቱ የፍተሻ አይነቶች የሚደረጉ የኮንክሪት ግሬዶች የእመቃ ጥንካሬአቸው ይለያያል። ሲሊንደሪካል ፍተሻ በአንፃራዊነት የኮንክሪትን ትክክለኛ እምቅ ጥንካሬ ይገልፃል ስለዚህ ከኪውቢክ ፍተሻው የተሻለ ነው ማለት ነው።
.
ከታች በምስሉ በኪውቢክ ፍተሻ የተደረገ የተለያዩ የኮንክሪት ግሬዶች ፣ ያላቸው የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠር ምጣኔ (ratio) እና ከ28 ቀን በኋላ የሚያገኙት ጥንካሬ ተገልጿል።

@etconp
👍30👌12👏4
Ethio Construction Engineering
ስራ ይፈልጋሉ ? አርኪቴክት ኖት ወይስ ሲቪል እንጂኔሪንግ ነው ያጠኑት መልካም እንግዲያውስ አውቶካድ(AUTOCAD) በደምብ ይችላሉ ? Drawing መስራት ይችላሉ ? ከናንተ ሚጠበቀው laptop ይኑሮ ፣ smart phone ይኑሮ ባሉበት ቦታ ሆነው online መስራት ይችላሉ ይደውሉ :- +251973267834 ጆርዳኖ/JORDANO/جوردانو
የተመዘገባችሁ በሙሉ complete your information

Insert your email /ኢሜላችሁን አስገቡ
Insert phone number/ስልክ ቁጥራችሁን አስገቡ

ሌሎች ጥያቄዎችንም ሙሉ

የተሟላ profile እንዲሆን አርጉ

ከተቻለም የሰራችሁት ስራ ካላ ፎቶ load አርጉ የሰራችሁትን ስራ 3D sample display ላይ አስቀምጡ client ያገኛችኋል ደግሞ የሰራችሁትን ስራ ሌላ ሰው እንዳይወስደው ስም እና ስልክ ቁጥር የምትለጥፉበት ፎቶ ላይ አድርጉ
👍8❤1
ወጋገን ባንክ በመቀሌ ከተማ ከ 1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባለ 25 ፎቅ ሕንጸ ሊገነባ ነው

ወጋገን ባንክ በመቀሌ ከተማ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው ባለ 25 ፎቅ ሕንጻ በዛሬው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

ሕንፃው የሚገነባው በትግራይ ክልል ዋና ከተማ በመቀሌ የሚገኘው ብሔራዊ ስታዲየም አቅራቢያ በ3,500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ መሆኑን ትግራይ ቲቪ ዘግቧል።

ለባንኩ ሕንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡት ትግራይ ክልላዊ መንግሥት ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፤ "ወጋገን ባንክ ለትግራይ መልሶ ግንባታ ትልቅ ሚና ሊጫወት ይገባል" ሲሉ ማሳሰባቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።

@etconp
👍10
የቦሌ ሚካኤል ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት የሚያሻሽሉ 6 የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድዮችን በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ ይገኛል ከነዚህም የቦሌ ሚካኤል የመንገድ መጋጠሚያ አንዱ ነው፡፡

የቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ከተገነቡ አዳዲስ መንገዶች ጋር ተሳስሮ ከሳሪስ አቦ ወደ ቦሌ አቅጣጫ ከሚወስደው የቀለበት መንገድ ጋር በተለያዩ መጋጠሚያዎች የሚያገናኙ የመቃረቢያ መንገዶችን ጨምሮ የቦሌ ሚካኤል የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ግንባታ እውን እንዲሆን ምክንያት ሆኗል፡፡

ፕሮጅክቱ ከ720 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ አሰር ኮንስትራክሽን የተባለ የሀገር ውስጥ የሥራ ተቋራጭ እየገነባው የሚገኝ ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ በሀይ ዌይ ኢንጂነርስ አማካሪ ኩባንያ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ቀደም ሲል 600 ሜትር ርዝመት ያለው የቦሌ ሚካኤል ትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን፣ ከአጠቃላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ ክፍል 3.8 ኪሎ ሜትሩ የመጀመርያ አስፋልት ደረጃ ለብሷል።

በተጨማሪ በቀሪው 200 ሜትር በሚሆነው የመንገዱ ክፍል የአስፋልት ንጣፍ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ምንጭ ኢፕድ

@etconp
👍3👏2
📌የ ምስራች ዜና ለ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በ ሙሉ

🏗በ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በ ተቋራጭነት፣በ መንገድ ስራ፣በ ኢንተርየር ዲዛይን፣በ ሰብ ኮንትራክት፣በ ብረታ ብረት፣በ እንጨት ስራ እና የ ህንፃ ግንባታ ተያያዥ ስራዎች ያላቹ በ ሙሉ

🗞አዳዲስ ጨረታዎች ሲወጡ፣ ዕለታዊ የማተርያል ና ማሽነሪ Cost ለማወቅ በቀላሉ በ Private ቴሌግራም ቻናል አመቱን ሙሉ በ ማይታመን ዋጋ áŠĽáŠ•á‹˛á‹°áˆ­áˆłá‰š ለምትፈልጉ ከታች ባሉት አደራሻዎች አናግሩን።

👊እስካሁን ከ ደረጃ 1 እስከ 10 በዛ ያሉ
በየቀኑ አዳዲስ ጨረታዎች እየለጠፍን እንገኛለን::

🌟(ማረጋገጫ አሁናዊ የ ቻናሉ ገፅታ በ ምስል አያይዘንላቹዋል)

🚧ለመመዝገብ @Philemona7 ወይም @etconpworks ያናግሩን።

☎️ለ በለጠ መረጃ በ +251925446661 ወይም 0707444849 ይደውሉ

🙏እናመሰግናለን🙏

@etconp
👍9❤1
👉ትንሽ ስለ ጊቤ 3 ሃይድሮኤሌትሪክ ግድብ ፕሮጀክት

▶️የፕሮጀክቱ ስም፦ ጊቤ 3 ሃይድሮኤሌትሪክ ግድብ
▶️የብሮጀክቱ ባለቤት (Client) ፦ የኢትዮጵያ ማብራት ሃይል
▶️የፈጀው ወጪ በ ዩሮ€ 1,470 million

➡MAIN TECHNICAL DATA

⏺የግድቡ ቁመት (Dam Height) ፦ 250m
⏺የግድቡ የቁንዲ ርዝመት (Crest length)፦ 630m
⏺ግድቡ በሚያርፍበት ቦታ ላይ የተደረገ ቁፋሮ መጠን (Excavation)፦ 4,000,000m^3
⏺የተሞላው የኮንክሪት መጠን (Roller compacted concrete) ፦ 6,114,000m^3
⏺የ Power house መጠን፦ 234×37×43
⏺የተርባይን አይነቶች እና ብዛት ፦10ፍራንሲስ ተርባይን እያንዳንዳቸው 187MW የማመንጨት አቅም ያላቸው
.
➡POWER & ENERGY
.
⏺የማመንጨት አቅም (Installed capacity) ፦ 1870 MW
⏺በአንድ አመት የሚያመነጨው የሃይል መጠን ፦ 6500GWH/yr

⏺የውሃ ማቆርያው(Reservoir)
ስፋት (Surface area)፦ 200 km²
⏺ውሃ የማቆር አቅም (Storage capacity)፦ 14,000 x 160 m³
.
➡የወንዝ ቅልበሳ ክንውን (River diversion)

⏹ሁለት ኮፈር ግድቦችን ተጠቅሟል (እነዚህ ግድቦች አፈርን ከድንጋይ ጋር በመጠቅጠቅ የተሰሩ ናቸው Embankment dam የሚባለው)

⏺የነዚህ ግድቦች የላይኛው አካል ቁመት (Upstream height ) ፦ 55 m 
የታችኛው አካል ቁመት (Down stream height) ፦ 19m

📍ሶስት ወሃ ቀልባሽ ዋሻዎች ተቆፍረዋል ባጠቃላይ 3218 m ይረዝማሉ

#Hydraulics

@etconp
👍19❤5
👉እስኪ አሁን ደግሞ አለማችን ትልቁ የንፁህ መጠጥ ውሃ ማጠራቀሚያ ስለሆነው የሳውዲ አረቢያው ብሪማን የውሃ አቅርቦት ፋሲሊቲ እናውራ

⭕▶ይህ የውሃ ማጠራቀሚያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2014 በአለም የድንቃድንቅ መዝገብ (World gunnies  book of records) ላይ የአለማችን ትልቁ Water supply Reservoir (የውሃ ጋን) በመባል ተመዝግቧል
.
⭕▶የ ብሪማን የውሃ አቅርቦት ፋሲሊቲ 11 ትላልቅ  ሪዘርቮየሮች ሲኖሩት አንዱ ሪዞርቮየር 120m ዲያሜትር እና 18m ቁመት አለው እንዲሁም 187,500m^3 በላይ መጠን ያለው ውሃን ማቆር ይችላል
.
⭕▶ፕሮጀክቱ 200M ዶላር የፈጀ ሲሆን ከአስራአንዱም የውሃ ታንከሮች 2,062,500m^3 ውሃ የማቅረብ ብቃት አለው
.
⭕▶ እነዚህ የውሃ ጋኖች ከተለመደው የውሃ ጋን አሰራር ወጣ ያለ አሰራርን የተጠቀሙ ሲሆን ከግዝፈታቸው አንፃር በድልልድዮች የምናያቸውን post-tensiond ኮንክሪት ግድግዳዎችን በመጠቀም ታንፀዋል የውሃ አቅርቦቱንም ለማቀላጠፍ እርስ በእርሳቸው በሃይድራውሊክ የተያያዙ ናቸው። (ስለ ፖስት ቴንዥንድ ከታች ያለውን ፁፍ ይመልከቱ)
.
⭕▶ከአስራ አንድ ጋኖች የምናገኘው የውሃ መጠን 800 ኦሎንፒክ ስታንዳርድ የመዋኛ ገንዳዎችን ይሞላልናል ለአንዱ ስናሰላው ደግሞ 73 ያህል ገንዳዎችን ይሞላልናል
.
⭕▶ ለአንድ አመት እንኳ ውሃ ከናካቴው ቢጠፋ እነዚህ ሪዘርቨየሮች የጅዳ ከተማን የውሃ አቅርቦት የማሟላት አቅም አላቸው።

#Hydraulics

@etconp
👍11❤1
Ethio Construction Engineering
ስራ ይፈልጋሉ ? አርኪቴክት ኖት ወይስ ሲቪል እንጂኔሪንግ ነው ያጠኑት መልካም እንግዲያውስ አውቶካድ(AUTOCAD) በደምብ ይችላሉ ? Drawing መስራት ይችላሉ ? ከናንተ ሚጠበቀው laptop ይኑሮ ፣ smart phone ይኑሮ ባሉበት ቦታ ሆነው online መስራት ይችላሉ ይደውሉ :- +251973267834 ጆርዳኖ/JORDANO/جوردانو
መመዝገብ የምትፈልጉ ቀጥታ ከታች በተቀመጠው link ገብታችው ተመዝገቡ

ሊንክ:- https://www.buildmost.com/bm_promote.html?pcode=U3WB0Y

አደራ personal information ሞልታችሁ ጨርሱ ኢሜል አስገቡ ከቻላችሁ የስራችሁን sample display ላይ አስቀምጡ in that way you can make exposure to clients ስራ ወደናንተ አይመጣም እናንተ ወደስራ ሂዱ effort ያስፈልጋል
👍11
Ethio Construction Engineering
ኮንክሪት እና የኮንክሪት ግሬዶች . ኮንክሪት (concrete) ስሙን ያገኘው ከጥንት ሮማኖች ሲሆን ቃሉም የመጣው ኮንክሪተስ (Concretus) ከሚለው የሮማኖች ቃል ነው የቃል በቃል ትርጉሙ ተያይዞ ማደግ / አንድ ላይ ማደግ የሚለውን ይወክላል። . ኮንክሪት በአለም ላይ በብዛት የምንጠቀመው የግንባታ ቁስ ነው። ኮንክሪት የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠሮች ውህድ ነው ። የኮንክሪት የእመቃ ጥንካሬ (compressive…
~ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት~

የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በሳይት የሚተገበር የፍተሻ አይነት ሲሆን የኮንክሪትን የመስራት አቅም (Workability) እና ፅኑእነት (Consistency) ለመለካት ይጠቅማል
.
ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በየእያንዳንዱ የኮንክሪት ሙሌት ስራውስጥ መተግበር አለበት ። ስላምፕ ቴስት በትንሽ ወጪ ምንተገብረው የኮንክሪትን Workability ምንመዝንበት ተመራጭ መፈተሻ ነው በዚህ ምክንያት ከ1922 G.c ጀምሮ እስካሁን  አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።
.
➡የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፉ ነገሮች (Factors which influence the concrete slump test)
.
1- ለ ኮንክሪቱ እንደግብአት የተጠቀምናቸው እቃዎች ባህርይ...ለምሳሌ ስነውህድ (ኬሚስትሪ) ቅጥነት ፣ የቁሱ መጠን እና ስርጭት (particle size and distribution) ፣ እርጥበት ፣ የሲሚንቶ ግብአት እና እርጥበት የመያዝ አቅም.
.
2- የኬሚካል አድሚክስቸር መጠን አይነት መስተጋብር...
.
3- የኮንክሪቱ አየር የመያዝ አቅም
.
4- ኮንክሪት ማቀላቀያ ማጓጓዣ ቁስ እና ዘዴ
.
5- የኮንክሪቱ temperature
.
6- በኮንክሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውሃ መጠን
.
7- ኮንክሪቱ ለፍተሻ የተወሰደበት ግዜ
.
.
➡Slump test ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች
.
⚫Slump ለመስራት የሚያገለግል መሃሉ ክፍት የሆነ ኮን (cone) መሰል ቅርፅ ማውጫ ይህ ቅርፅ ማውጫ 30cm ርዝመት 20 cm የታችኛው ዲያሜትር  10cm የላይኛው ዲያሜትር ያለው ነው (mold)
⚫መለኪያ ማስመሪያ
⚫ከብረት የተሰራ 16 mm dia. እና 60 cm ርዝመት ያለው መጠቅጠቂያ ብረት
.
➡ስላምፕ ቴስትን የመከወኛ ቅደም ተከተል
.
✅step-1▶ መጀመርያ የቅርፅ ማውጫ ኮን (mold ) ንፁ መሆን አረጋግጥ ኮንክሪቱ በቀላሉ ከሞልድ እንዲላቀቅ ቅርፅ ማውጫውን ዘይት መቀባት አለበት
.
✅step-2 ▶ቅርፅ ማውጫውን  (mold ) ትልቅ ዲያሜትር ባለው ጫፍ በኩል ወንፊት ባልሆነ ስሃን ላይ አቁመው
.
✅Step 3-▶ የቅርፅ ማውጫ (mold) በእኩል 4 layer በኮንክሪት ሙሉት
.
✅Step 4- ▶እያንዳንዱን የኮንክሪት ላየር 25 ግዜ በመጠቅጠቂያ ብረት ምቱት (ጠቅጥቁት) የአጠቃጠቅ ጉልበታችሁ እኩል መሆን አለበት
.
✅Step 5- ▶ኮኑ (mold) ከሞላ በኋላ ትንሽ ዲያ ባለው ጫፍ ላይ ያል ትርፍ ኮንክሪትን አስወግዱት ጫፉንም ለስኑት
.
✅Step 6-▶ ቅስ በማለት የኮንክሪት ቅርፅ ማውጫውን (mold) ከኮንክሪቱ አለያዩት
.
✅Step 7- ▶ቀጥሎም ኮንክሪቱ ከቅርፅ ማውጫ (mold) ያለውን የርዝመት ልዩነት ለኩት
.
.
⏩⏩Note - እዚጋ ማሳሰብ ምፈልገው ነገር ይህን ቴስት ስታደርጉ ቦታው ከእርግብግቢት (Vibration) የፀዳ መሆን አለበት ያልተረጋጋ ቦታ ላይ ማድረግ የቴስቱን ውጤት ያበላሸዋል...ሳምፕሉ ከተወሰደ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ቴስቱን መከወን አለብን
.
.
➡ከኮንክሪት ስላምፕ ቴስት የምናገኛቸው የውጤት አይነቶች
.
▶True Slump- ይህ ከፍተሻው ምናገኘው ብቸኛው ልኬት ነው ቅርፅ ማውጫው ከኮንክሪቱ ከተለያየ በኋላ ያለው የኮንክሪቱ ቁመት ከቅርፅ ማውጫው በንፃሬ የምናገኘው ልዩነት (ምስሉን ይመልከቱ)
.
▶Zero Slump - ዜሮ ስላምፕ ኮንክሪቱ አነስተኛ የውሃ-ሲሚንቶ ratio ያለው መሆኑን ያሳያል ዜሮ ስላምፕ ያለው ኮንክሪት ለመንገድ ግንባታ አገልግቶት ላይ ይውላል...
.
▶Collapsed Slump- ይህ ደግሞ ከዜሮ ስላምፕ በተለየ የኮንክሪቱን የውሃ ሲሚንቶ ውህድ Ratio ትልቅ መሆን ያሳያል ይህ ማለት የኮንክሪቱ የእርጥበት መጠን ከፍተኛ መሆኑን እና High workability mix ያሳየናል።
.
▶Shear Slump- ይህ ደግሞ የፍተሻው ውጤት ሙሉ እንዳልሆነ ይነግረናል።

@etconp
👍16❤1🏆1
Ethio Construction Engineering
👉ትንሽ ስለ ጊቤ 3 ሃይድሮኤሌትሪክ ግድብ ፕሮጀክት ▶️የፕሮጀክቱ ስም፦ ጊቤ 3 ሃይድሮኤሌትሪክ ግድብ ▶️የብሮጀክቱ ባለቤት (Client) ፦ የኢትዮጵያ ማብራት ሃይል ▶️የፈጀው ወጪ በ ዩሮ€ 1,470 million ➡MAIN TECHNICAL DATA ⏺የግድቡ ቁመት (Dam Height) ፦ 250m ⏺የግድቡ የቁንዲ ርዝመት (Crest length)፦ 630m ⏺ግድቡ በሚያርፍበት ቦታ ላይ የተደረገ ቁፋሮ…
👉የውሃ ተርባይን አይነቶች

▶️የውሃ ተርባይን ተሽከርካሪ (በራሱ ዛቢያ የሚዞር ወይም Rotary ) ማሽን ሲሆን ውሃ በፍጥነቱ አማካኝነት የሚፈጥረውን ሃይል (Kinetic Energy ) እና በሚወረወርበት ርዝመት አማካኝነት የሚፈጥረውን ሃይል (potential Energy) ወደ ሚካኒካል ስራ (መዞር መሽከርከር) የሚቀርልን ማሽን ነው።

▶️የውሃ ተርባይኖች የተፈጠሩት በ19ኛው ክፍለዘመን ሲሆን ይህም ማለት የኢንደስትሪው አብዮትበፈነዳበት ወቅት ነው። ስራቸው በወቅቱ ለነበሩ ኢንደስትሪዎች ሜካኒካል ሃይልን ማመንጨት ነው።

▶️በዚህ ዘመን ግን ትልቁ ስራቸው ከውሃ የሚመጣን ሃይል (kinetic and potential energy) ወደ ሚካኒካል ኢነርጂ መቀየር ነው።

▶️ውሃን ዘውረን ለምናገኘው ሃይል (hydro power ) የምንጠቀመው የተርባይን አይነት የሚወሰነው ውሃው (ሃይል የሚያመነጭልን ውሃ) ተርባይኑን ተንደርድሮ የሚመታበት ርዝመት (ከፍታ ) በእንግሊዘኛው Head በምንለው እና የውሃው መጠን (Volume) ወይም የፍሰት አቅም (Discharge) ላይ በመመስረት ነው።

⏺ከዚህ አንፃር የውሃ ተርባይኖች በአጠቃላይ ለ ሁለት ይከፈላሉ፦

▶️1- Reaction Turbine
▶️2- Impulse Turbine

⭕1-Reaction turbine፦ ይህ የተርባይን አይነት የአሰራር መርሁ በኒውተን 3ተኛ ህግ (law of action and reaction ) ላይ የተመሰረተ ነው።
መካከለኛ (30-300m) እና አነስተኛ (< 30m)  የውሃ የመስፈንጠሪያ ርዝመት (Head) ላላቸው ሃይል ማመንጫዎች ተመራጭ ነው።

⏺የሪአክሽን ተርባይን አይነቶች፦
✅Francis turbine
✅Kaplan turbine
✅Tyson turbine
✅Gorlov helical turbine ....ወዘተ
.
⭕2-Impulse turbine፦ በዚህ የተርባይን አይነት በተሽከርካሪው የተርባይን አካል ምላጮች ላይ የሚያርፈው የውሃ ግፊት ተመሳሳይ ሲሆን እና ለመሽከርከሩም ምክንያት ውሃው የሚፈጥረው የኬኔቲክ ኢነርጂ ልዩነት ነው። የውሃው ኬኔቲክ ኢነርጂ ወደ ፖቴንሻል ኢነርጂ የሚቀየረው ኖዝል በሚባለው የተርባይኑ ክፍል ነው። በተርባይኑ ምላጭ ላይ ምንም አይነት የኢነርጂ ለውጥ አይከሰትም።
የዚህ የተርባይን አይነት መንቀሳቀሻ መርሁ የኒውተን 2ተኛ ህግ ነው። ትላልቅ Head (>300m) ላላቸው ሃይል ማመንጫዎች ተመራጭ ነው።
የኢምፐልስ ተርባይን አይነቶች፦

▶️Peltone turbine አይነቶች

✅Turgo turbine
✅Cross flow turbine
✅Jonval turbine
✅Screw turbine.....ወዘተ

🚧በዚህ አጭር ፅሁፍ ከኢምፐልስ ተርባይን ስለ ፔልቶን ተርባይን ከሪአክሽን ተርባይን ስለፍራንሲስ እና ካፕላን ተርባይን እናነሳለን
.
.
▶Pelton Turbine
.
ይህ የተርባይን አይነት ከኢምፐልስ ተርባይን አይነቶች አንዱ ሲሆን አገልግሎቱም ትልቅ Head ላላቸው የሃይድሮ ኤሌትሪክ ስራዎች ነው። በዚህ የተርባይን አይነት የውሃው ጉልበት ወደ ኬኔቲክ ኢነርጂ የሚቀየረው ኖዝል (nozzel) በሚባለው የተርባይኑ ክፍል ነው። ከዚ ክፍል የሚፈነጠረው የውሃ ሃይል ትይዩ በሆነ አቅጣጫ የሚገኘውን የተርባይኑን ምላጭ (buckets or blades) ይመታና ገፊ ሃይል (impulsive force ) እንዲፈጠር ያደርጋል ። ይህ ሃይል የተርባይኑ ተሽከርካሪ አካል (rotor part) እንዲሽከረከር ይዳርገዋል። የዚህ አካል መሽከርከር ጀነሬተሩን የኤሌትሪክ ሃይል እንዲያመነጭ ይረዳዋል።
.
ፔልቶን ተርባይን የሚከተሉት ክፍሎች አሉት
.
✅Nozzel
✅Runner and bucket
✔Casing
✔Breaking Jet
.
▶Nozzel- ዋና ጥቅሙ ውሃን ወደ ተፈለገው አቅጣጫ መምራት ነው በተጨማሪም የውሃውን ፍሰት ይቆጣጠራል
(ከታች ምስሉን ይመልከቱ)
.
▶Runner እና Bucket- Runner ማለት ክብ ሰሃን የመሰለ አካል ሲሆን ጫፍ ጫፉ ላይም የኩባያ አይነት ቅርፅ ያላቸው Bucket የሚባለውን አካል ይዟል። ይህ የተርባይን አካል ከፍተኛ ጉልበት ላለው ተወንጫፊ ውሃ ስለተጋለጠ ከጠንካራ የብረት አይነቶች (ብዙን ግዜ stillness
steel ተመራጭ ነው) በጥንቃቄ ይሰራል። የውሃው ተወንጫፊ ሃይል ካቪቴን ለሚባለው እንከን ብዙ ግዜ እንዲጋለጥ ያደርገዋል። (ከታች ምስሉን ይመልከቱ)
.
▶Casing- ይህ ከብረት የተሰራ ቁስ ሲሆን የፔልተን ተርባይኑ Runner ለመሸፈን ይጠቅመናል ። ተጨማሪ ጥቅሞቹ
- Runner 'ሩን ከአደጋ ይከላከልልናል
- በንፋስ አማካኝነት ሊፈጠር የሚችልን loss ይከላከላል
- የውሃን መፈናጠር፤ መረጨት ይከላከላል
- ባኬቱን የመታ ውሃ ወደ tail race እንዲሄድ ይመራልናል
.
▶Breaking Jet- ይህ አካል የውሃውን ተወንጫፊ ጉልበት በመገደብ ራነሩ ፍጥነት እንዲቀንስ ያደርጋል (ብዙን ግዜ ብልሽቶች ሲኖሩ አገልግሎት ላይ ይውላል)
፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨

➡Application
.
ፔልተን ተርባይን አገልግሎት ላይ የሚውለው  የሃይድሮ ኤሌትሪክ ማመንጫው ትልቅ የውሃ መፈንጠሪያ ከፍታ (Head) ኖሮት ነገር ግን የፍሰቱ መጠን (discharge) ዝቅተኛ ሲሆን ነው። ፔልተን ተርባይን ከ44.9-1799.8m ድረስ ባለው Head effective የሆነ ግልጋሎት ይሰጠናል።

ይቀጥላል......

#Hydraulics

@etconp
👍12🏆5❤1
👉TYPES OF PIPES COMMONLY USED IN WATER SUPPLY SYSTEM

▶TYPES OF PIPES:

⏺The types of pipes commonly used in water distribution system are described below.
.
⭕1. CAST IRON PIPES:
.
Cast iron pipes or CI pipes are broadly utilized for distribution of water because they are less
expensive, corrosion resistant, and long lasting.
CI pipes are mainly produced by following four techniques.
.
1. Horizontally cast ( MC ware pipes)
2. Vertically cast ( Pit cast in sand molds)
3. Centrifugally cast in sand lines molds spun
type.
4. Centrifugally cast in water cooled molds.

Uses of horizontally cast CI pipes are presently pretty much outdated, that’s why they are infrequently produced these days. Centrifugally cast pipes are most widely used because they have more grained dense structure and uniform thickness. Generally, CI pipes are 3-6 m long, so much heavy, and require extra care to avoid from damaging while transporting and creating connections.
.
⭕2. STEEL PIPES:
.
Steel pipes are utilized in water mains circumstances where the pipes are going through very high pressure ( More than 7 kg/cm2)  and required large diameter pipes. These pipes have greater strength and less weight than CI pipes. Satisfactory treatments should be given to maintain antagonistic climatic conditions.
.
⭕3. GALVANIZED IRON PIPES:
.
Galvanized pipes are also known as GI pipes are fashioned steel pipes with zinc coating. GI pipes are mostly utilized for water supply and service connections.
.
⭕4. COPPER PIPES:
.
Copper pipes are most commonly utilized in hot water supply establishment. Some features of
this pipes are as following:
1. They possess high tensile strength.
2. They can be bent easily.
3. Copper pipes can be used in thin wall. Copper pipes are sometimes chromium plated to enhance their appearance and to match with the chromium plated water supply fittings.
.
⭕5. POLYTHENE PIPES:
.
Polythene and PVC pipes are being utilized progressively nowadays for cold water supply inside and outside works. These pipes are lightweight, cheaper, corrosion resistant, and require no threading for making any connections.

Besides these, there are other pipes commonly used for water distribution such as :

asbestos cement (AC) pipes,

reinforced concrete (RCC) pipes,

prestressed reinforced concrete (PSC) pipes etc.
.
The selection of the types of pipe for utilizing any purposes is adopted according to the design criteria, material availability, cost, and other comparative variables.

@etconp
👍9❤2
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
መመዝገብ የምትፈልጉ ቀጥታ ከታች በተቀመጠው link ገብታችው ተመዝገቡ

ሊንክ:- https://www.buildmost.com/bm_promote.html?pcode=U3WB0Y

አደራ personal information ሞልታችሁ ጨርሱ ኢሜል አስገቡ ከቻላችሁ የስራችሁን sample display ላይ አስቀምጡ in that way you can make exposure to clients ስራ ወደናንተ አይመጣም እናንተ ወደስራ ሂዱ effort ያስፈልጋል
👍8❤1
👉በ 3 ነዋሪዎች ተቃውሞ ከመፍረስ የተረፈው አፓርትመንት መስህብ ሆኗል

🚧በቻይና ጉዋንዙ ግዛት ሃይዙ በተባለው አካባቢ የሚገኘው ባለስምንት ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ በፈረንጆቹ 2008 ለመንገድ ግንባታ በሚል ሊፈርስ ነበር።

🚧በአፓርትመንቱ የሚኖሩ አብዛኞቹ ሰዎችም ከአልሚው ጋር ስምምነት ፈጽመዋል። ይሁን እንጂ ሶስት ሰዎች ያስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ ካልተሟላ ቤታችን አይፈርስም በሚለው አቋማቸው ጸኑ።

🚧ጉዋ ዢሚንግ እና ወንድሞቹ ለ30 ካሬሜትር ቤታቸው 400 ሺህ የቻይና ዩዋን ካሳ ቢሰጣቸውም አልተቀበሉም።

🚧መንገዱን የሚገነባው አካል በተደጋጋሚ ለማግባባትና ተጨማሪ ገንዘብ ለመክፈል ቃል ቢገባም ግለሰቦቹ “ቤታችን ለቀን አንወጣም” አሉ።

🌟የሶስቱን ዜጎች አቋም ያከበረው አልሚ መፍትሄን አበጀ፤ ቤቱ ሳይፈርስ መንገድ የሚገነባበትን ዲዛይንም አቅርቦ ወደ ስራ ገባ።

🚧እናም ሊፈርስ ቀናት ቀርተውት የነበረው ባለስምንት ፎቅ ቢጫ ህንጻ ሳይፈርስ ዙሪያውን ተሽከርካሪዎች የሚርመሰመሱበት የቀለበት መንገድ ተሰራ።

🚧በሶስቱ ነዋሪዎች ከመፍረስ የተረፈውና በመንገድ የተከበበው ብቸኛ ህንጻ አሁን የጎብኝዎችን ቀልብ የሚስብ ሆኗል።

🚧በተለያዩ ሀገራት መንግስትም ሆነ ሌሎች አልሚዎች ዜጎችን ለልማት በሚል ከቀደመ መኖሪያቸው ሲያስነሱ ተገቢውን ምትክ ቦታ እና ካሳ አይሰጡም የሚለው ቅሬታ ተደጋግሞ ይሰማል።

🚧በጉዋንዙ እንደሆነው አይነት ለመነሳት ፈቃደኛ ላልሆኑ ዜጎች ሁሉንም የሚያስማማ መፍትሄን የሚፈልጉት ጥቂቶች ናቸው።

Via Alain

@etconp
👍17❤6
👉ከአምቦ እስከ ጉደር ከተማ የሚዘልቀው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት በጥሩ አፈፃፀም ላይ ይገኛል።

የአምቦ-ጉደር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 19 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በመንግሥት በተመደበ 1,038,722,506.06 (አንድ ቢሊዮን ሰላሳ ስምንት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ስድስት ብር ከዜሮ ስድስት ሳንቲም) በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ነው።

የአምቦ-ጉደር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመካሄድ ላይ የሚገኘው በኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ነው።

የመንገድ ግንባታውን ጥራት በመቆጣጠር ረገድ ደግሞ ፕሮሚነንት ኢንጅነሪንግ ሶሉሽንስ በአማካሪነት በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡

መንገዱ 14 ሜትር ስፋት አንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፣ በሁለቱም አቅጣጫ 2.5 ሜትር የዕግረኛ መንገድ እና 2.5 ሜትር አካፋይ እንዲኖረው ተደርጎ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው፡፡

መንገዱ ከዚህ ቀደም በአስፋልት ደረጃ ተገንብቶ የነበረ ቢሆንም ፣ ነባሩ መንገድ እጅግ የተጎዳ በመሆኑ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከግምት ውስጥ ገብቶ በአሁኑ ወቅት በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ የአፈር ቆረጣ ፣ የስትራክቸር፣ የአስፋልት ንጣፍ  ፣ የአራት ድልድዮች ግንባታ ፣ የሰቤዝ እና የቤዝ ኮርስ ስራዎችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ግንባታዎችን (የመንገድ ምልክቶችን መትከል፣መንገድ ቀለም መቀባት) ባካተተ መልኩ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው፡፡

ከፕሮጀክቱ ጅማሮ አንስቶ አስካሁን የድልድይ እና የፍሳሽ ውሃ ማስወገጃ ፣ አፈር ቆረጣ፣የሰቤዝ እና የቤዝ ኮርስ እንዲሁም አስፋልት የማንጠፍ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በዚህም መሰረት የፕሮጀክቱ የእስካሁን አፈፃፀም 46 በመቶ ወይም 9 ኪሎ ሜትር  ስራው ተጠናቋል፡፡

ግንባታው በመጪው 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይታመናል፡፡ የስራ ተቋራጩ በአሁኑ ወቅት ቀሪ የቁፋሮ ስራ ፣ የአስፋልት ንጣፍ ፣ የሰቤዝ እና የቤዝ ኮርስ ንጣፍ ፣ የስትራክቸር ፣ የትራፊክ ምልክቶችን የመትከል እንዲሁም መንገዱን ቀለም የመቀባት ስራ ለማከናወን አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡

ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ ግንባታው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

መንገዱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ አምቦ እና ጉደር ከተሞችን ከማገናኘት ባሻገር ሀገር አቋራጭ መንገድ በመሆኑ ለሀገሪቱ ትልቅ ፋይዳ ያስገኛል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው የተፈጥሮ ፍል ውሃ እና በፕሮጀክቱ አቅራቢያ የሚገኝ የወንጪ ሃይቅ የሚገኝ በመሆኑ ፤ የመንገዱ መገንባት ለቱሪስት መዳረሻነትም ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

Via ERA

@etconp
👍7
Ethio Construction Engineering
መመዝገብ የምትፈልጉ ቀጥታ ከታች በተቀመጠው link ገብታችው ተመዝገቡ ሊንክ:- https://www.buildmost.com/bm_promote.html?pcode=U3WB0Y አደራ personal information ሞልታችሁ ጨርሱ ኢሜል አስገቡ ከቻላችሁ የስራችሁን sample display ላይ አስቀምጡ in that way you can make exposure to clients ስራ ወደናንተ አይመጣም እናንተ ወደስራ…
የ AUTOCAD ክህሎት ኖሯችሁ online ስራ መስራት ምትፈልጉ

ሊንክ:- https://www.buildmost.com/bm_promote.html?pcode=U3WB0Y

ገብታችሁ ተመዝገቡ personal information ሞልታችሁ አጠናቁ

ሁለት አይነት ስራ ይኖራችኋል outsource የተደረገ ስራ ወይም የራሳችሁን project sample በማስቀመጥ ከ client ጋር ምትገናኙበት
❤4👍3🏆2🙏1