Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
መመዝገብ የምትፈልጉ ቀጥታ ከታች በተቀመጠው link ገብታችው ተመዝገቡ

ሊንክ:- https://www.buildmost.com/bm_promote.html?pcode=U3WB0Y

አደራ personal information ሞልታችሁ ጨርሱ ኢሜል አስገቡ ከቻላችሁ የስራችሁን sample display ላይ አስቀምጡ in that way you can make exposure to clients ስራ ወደናንተ አይመጣም እናንተ ወደስራ ሂዱ effort ያስፈልጋል
👍8❤1
👉በ 3 ነዋሪዎች ተቃውሞ ከመፍረስ የተረፈው አፓርትመንት መስህብ ሆኗል

🚧በቻይና ጉዋንዙ ግዛት ሃይዙ በተባለው አካባቢ የሚገኘው ባለስምንት ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ በፈረንጆቹ 2008 ለመንገድ ግንባታ በሚል ሊፈርስ ነበር።

🚧በአፓርትመንቱ የሚኖሩ አብዛኞቹ ሰዎችም ከአልሚው ጋር ስምምነት ፈጽመዋል። ይሁን እንጂ ሶስት ሰዎች ያስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ ካልተሟላ ቤታችን አይፈርስም በሚለው አቋማቸው ጸኑ።

🚧ጉዋ ዢሚንግ እና ወንድሞቹ ለ30 ካሬሜትር ቤታቸው 400 ሺህ የቻይና ዩዋን ካሳ ቢሰጣቸውም አልተቀበሉም።

🚧መንገዱን የሚገነባው አካል በተደጋጋሚ ለማግባባትና ተጨማሪ ገንዘብ ለመክፈል ቃል ቢገባም ግለሰቦቹ “ቤታችን ለቀን አንወጣም” አሉ።

🌟የሶስቱን ዜጎች አቋም ያከበረው አልሚ መፍትሄን አበጀ፤ ቤቱ ሳይፈርስ መንገድ የሚገነባበትን ዲዛይንም አቅርቦ ወደ ስራ ገባ።

🚧እናም ሊፈርስ ቀናት ቀርተውት የነበረው ባለስምንት ፎቅ ቢጫ ህንጻ ሳይፈርስ ዙሪያውን ተሽከርካሪዎች የሚርመሰመሱበት የቀለበት መንገድ ተሰራ።

🚧በሶስቱ ነዋሪዎች ከመፍረስ የተረፈውና በመንገድ የተከበበው ብቸኛ ህንጻ አሁን የጎብኝዎችን ቀልብ የሚስብ ሆኗል።

🚧በተለያዩ ሀገራት መንግስትም ሆነ ሌሎች አልሚዎች ዜጎችን ለልማት በሚል ከቀደመ መኖሪያቸው ሲያስነሱ ተገቢውን ምትክ ቦታ እና ካሳ አይሰጡም የሚለው ቅሬታ ተደጋግሞ ይሰማል።

🚧በጉዋንዙ እንደሆነው አይነት ለመነሳት ፈቃደኛ ላልሆኑ ዜጎች ሁሉንም የሚያስማማ መፍትሄን የሚፈልጉት ጥቂቶች ናቸው።

Via Alain

@etconp
👍17❤6
👉ከአምቦ እስከ ጉደር ከተማ የሚዘልቀው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት በጥሩ አፈፃፀም ላይ ይገኛል።

የአምቦ-ጉደር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 19 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በመንግሥት በተመደበ 1,038,722,506.06 (አንድ ቢሊዮን ሰላሳ ስምንት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ስድስት ብር ከዜሮ ስድስት ሳንቲም) በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ነው።

የአምቦ-ጉደር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመካሄድ ላይ የሚገኘው በኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ነው።

የመንገድ ግንባታውን ጥራት በመቆጣጠር ረገድ ደግሞ ፕሮሚነንት ኢንጅነሪንግ ሶሉሽንስ በአማካሪነት በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡

መንገዱ 14 ሜትር ስፋት አንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፣ በሁለቱም አቅጣጫ 2.5 ሜትር የዕግረኛ መንገድ እና 2.5 ሜትር አካፋይ እንዲኖረው ተደርጎ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው፡፡

መንገዱ ከዚህ ቀደም በአስፋልት ደረጃ ተገንብቶ የነበረ ቢሆንም ፣ ነባሩ መንገድ እጅግ የተጎዳ በመሆኑ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከግምት ውስጥ ገብቶ በአሁኑ ወቅት በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ የአፈር ቆረጣ ፣ የስትራክቸር፣ የአስፋልት ንጣፍ  ፣ የአራት ድልድዮች ግንባታ ፣ የሰቤዝ እና የቤዝ ኮርስ ስራዎችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ግንባታዎችን (የመንገድ ምልክቶችን መትከል፣መንገድ ቀለም መቀባት) ባካተተ መልኩ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው፡፡

ከፕሮጀክቱ ጅማሮ አንስቶ አስካሁን የድልድይ እና የፍሳሽ ውሃ ማስወገጃ ፣ አፈር ቆረጣ፣የሰቤዝ እና የቤዝ ኮርስ እንዲሁም አስፋልት የማንጠፍ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በዚህም መሰረት የፕሮጀክቱ የእስካሁን አፈፃፀም 46 በመቶ ወይም 9 ኪሎ ሜትር  ስራው ተጠናቋል፡፡

ግንባታው በመጪው 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይታመናል፡፡ የስራ ተቋራጩ በአሁኑ ወቅት ቀሪ የቁፋሮ ስራ ፣ የአስፋልት ንጣፍ ፣ የሰቤዝ እና የቤዝ ኮርስ ንጣፍ ፣ የስትራክቸር ፣ የትራፊክ ምልክቶችን የመትከል እንዲሁም መንገዱን ቀለም የመቀባት ስራ ለማከናወን አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡

ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ ግንባታው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

መንገዱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ አምቦ እና ጉደር ከተሞችን ከማገናኘት ባሻገር ሀገር አቋራጭ መንገድ በመሆኑ ለሀገሪቱ ትልቅ ፋይዳ ያስገኛል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው የተፈጥሮ ፍል ውሃ እና በፕሮጀክቱ አቅራቢያ የሚገኝ የወንጪ ሃይቅ የሚገኝ በመሆኑ ፤ የመንገዱ መገንባት ለቱሪስት መዳረሻነትም ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

Via ERA

@etconp
👍7
Ethio Construction Engineering
መመዝገብ የምትፈልጉ ቀጥታ ከታች በተቀመጠው link ገብታችው ተመዝገቡ ሊንክ:- https://www.buildmost.com/bm_promote.html?pcode=U3WB0Y አደራ personal information ሞልታችሁ ጨርሱ ኢሜል አስገቡ ከቻላችሁ የስራችሁን sample display ላይ አስቀምጡ in that way you can make exposure to clients ስራ ወደናንተ አይመጣም እናንተ ወደስራ…
የ AUTOCAD ክህሎት ኖሯችሁ online ስራ መስራት ምትፈልጉ

ሊንክ:- https://www.buildmost.com/bm_promote.html?pcode=U3WB0Y

ገብታችሁ ተመዝገቡ personal information ሞልታችሁ አጠናቁ

ሁለት አይነት ስራ ይኖራችኋል outsource የተደረገ ስራ ወይም የራሳችሁን project sample በማስቀመጥ ከ client ጋር ምትገናኙበት
❤4👍3🏆2🙏1
👉አንዳንዴ እንዲ ያሉ ጥቃቅን ነገር ግን ትልቅ ጉዳት የሚያደርሱ ስህተቶች ይሰራሉ።

🚧Fence (አጥር) መስራት አንድን የውሃ ጋን (reservoir )  እኩል ቦታ ተሰጥቶት ዲዛይን ይደረጋል ፤ ይሰራልም።

ለምን ቢባል ምክንያት ደሞ..

- የውሃ ጋኑን (reservoir) ከሰዎችም ሆነ ከእንስሳት ንክኪ ለመጠበቅ
- የውሃ ጋኑን እድሜ ለማራዘም

እንደውም ጥበቃ ተመድቦላቸው ሊጠበቁ ሲገባ እንዲ ያለአጥር ቀርተው በየቦታው እናስተውላቸዋለን - አስቡት አንድ ክፉ አድራጊ በዚህ ጋን ውስጥ ያለን ውሃ ቢበክል ማህበረ ሰብን ሊያወድም አይችልም??

#Hydraulics

@etconp
👍15🏆1
🚧Picture Of The Day

🌟Different beam name at the different positions

@etconp
👍3👏1
👉የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም

🌟ሰሜን ሸዋ ልዩ ቦታው የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም

⏺ወጪ:- 320 ሚሊዮን ብር
⏺አማካሪው:- SAY Consult
⏺ዋና ህንጻውን የነደፈው:- ሳሙኤል አፈወርቅ ለማ

▶️ነዳፊው የቤቷክርስትያኗን  ኪነህንጻ ከሀያኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ከውጭ ማለትም ከህንድ፣ ከአርመን፣ ከጣልያን፣ ከግሪክ ወዘተ  በቀጥታ ተቀድተው የመጡትን የንድፍ ትእምርቶች፣ ቅርጽና ደርዞች ሳይመረኮዝ በመስራቱ ሊደነቅ ይገባል።

🚧በ20ኛው ክፍለዘመን መጀመርያ ላይ  የኒዮክላሲካል (አራዳ ጊዮርጊስ)፣ የኒዮ ባሮክ (ቅድስት ስላሴ) እንዲሁም የአርመን እና የህንድ ንድፍ ዘይቤዎች  (አብዛኞቹ  በ1900 መጀመርያ በአዲስ አበባ የተገነቡት አብያተክርስትያናት) የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ህንጻ ንድፎች ላይ ተጽእኖአቸውን ያሳረፉ ሲሆን በዘመናችን ደግሞ ፔዲመንትና አእማዶችን  ጭምር ከግሪኮ ሮማን ኪነህንጻ ቋንቋ በብዛት ተውሶ የመስራት ዝንባሌ ይታያል።

🚧የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. እጅግ ብዛት ያለው የእይታ  ጥበብና የቤተክርስትያን ንድፍ ሀብት ስላላት ያንን ሀብት በዘመናችን ተርጉመው የሚነድፉ ነዳፊዎች ያስፈልጓታል።

ምስል ምንጭ በይነ መረብ

@etconp
❤16👍7😢1
የውሃ ጋኖች (water supply Reservoir)
.
የውሃ ጋኖች ከጥቅማቸው አንፃር ለ ሶስት ይከፈላሉ
.
1-Collector reservoir
2-Service reservoir
3-Supply reservoir
.
እያንዳንዱ ጥቅማቸው ምንድነው……
.
[Collector reservoir ]
.
ይህ የጋን አይነት ዋና ስራው ውሃው ከሚመነጭበት (የገጸ ምድር ወይም የከርሰ ምድር ውሃ) ቦታ ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚቀመጥበት ጋን ነው፡፡ ጥቅሙ የተሰበሰበውን ውሃ ወደተለያዩ ጋኖች እስኪሰራጭ በጊዜያዊነት እንዲቀመጥና ውሃው ለጋኖቹ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጉልበት እንዲያገኝ ይረዳዋል፡፡ ብዙን ጊዜ ውሃው ከሚመነጭበት ቦታ አቅራቢያ ይተከላል፡፡ ውሃ ፈሳሽ እንደመሆኑ ብዙን ግዜ ሚፈልቀው ከፍታቸው ካነሱ ቦታዎች ስለሆነ ከሌሎች ጋኖች ይልቅ የዚህ ጋን ከፍታ (elevation) ያንሳል፡፡
.
[Service reservoir]
.
ይህ የጋን አይነት በቋሚነት ከcollecter reservoir የተቀበለውን ውሃ የሚያርፍበት ነው፡፡ አሰራሩም ከሌሎቹ ጋኖች ለየት ይላል ፡፡ ውሃው የሚያደርስበትን ግፊት ለመቋቋም የሚያስቸለውን መካች ጉልበት(reaction force) በበቂ ሁኔታ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ በቁመትም በመጠንም ትልቅ ነው፡፡ ወጪ ለመቀነስ ከፍ ካለ ቦታ ይተከላል (ውሃ በ3 አይነት መንገድ ይከፋፈላል
.
1-የሞተር ሀይልን በመጠቀም

2-የመሬት የመሳብ ሃይልን (gravity force) በመጠቀም።

3-የሞተር ሃይልንና የመሬት የስበት ሃይልን በማጣመር በመጠቀም እንዲሰራጭ ይደረጋል ፡፡

በአሁን ጊዜ ሶስተኛው አማራጭ በስፋታ አገልግሎት ላይ ይውላል ይህ አማራጭ ከወጪም አንፃር በጣም ተመራጭ ነው ለዚህ ዘዴ ተመራጩ ደግሞ የservice reservoir ከፍ ካለ ቦታላይ መተከል ወሳኝነት አለው፡፡)
ከዚህ ጋን ቀጥታ ለስርጭት ቧንቧ አይገጠምም ምክንያቱም ከጋኑ የሚወጣው ውሃ ከፍተኛ ጉልበት ስላለው የማሰራጫ ቱቦዎችን ሊያፈነዳ ይችላል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ቀጣዩን የጋን አይነት መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡
.
[Supply  reservoir]
.

የዚህ ጋን ዋና ጥቅም ውሃውን ለስርጭት ወደ ስርጭት ቱቦዎች እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ከሰርቪስ ጋን ቀጥታ ወደ ስርጭት ቧንቧ ውሃ አይገባም ምክንያቱም ከፍተኛ ሀይል ስላለው የቧንቧዎቹን የመቆየት አቅም ያሳጥራል ብሎም እስከ ማፈንዳት ያደርሳል፡፡ ይህ እንዳይከሰት የሳፕላይ ጋኖች ይገነባሉ፡፡ ይህ ጋን በቱቦዎቹ የሚያልፈውን ውሃ ግፊት በመቀነስና ፈጥነቱን (velocity) ከ 0.5-2 m/s በማድረግ እና ወደ ቱቦዎቹ የሚገባን ሃይል በመቀነስ (Energy dissipate ) ቱቦዎቹ  ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ያስወግዳል፡፡ ይህ ጋን ከፍ ባለ ቦታ ይተከላል ነገር ግን ከፍታው ከService reservoir ያነሰ ነው።
.
Like | Share | Comment

#Hydraulics

@etconp
👍22
👊Picture Of The Day

✍Put The Reason @COTMp

@etconp
❤2
ግድብ (Dam) ማለት ገዝፈ አካል ሲሆን የውንዝን ሸለቆ ላይ ተገንብቶ የውሃን ተፋሰስ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚገታ ነው።

ይህ መግታት (blockage) በውሃ ተፋሰስ ላይ መታቆርን (reservoir) ይፍጥራል ይህም ወሃውን ለተፈለገው አገልግሎት እንዲውል ቀሊል ያደርገዋል ። ይህ አጋጅ ገዝፈ አካል ወይም ግድብ ከተለያዩ ቁሶች ይሰራል ፦ ኮንክሪት፣ የድንጋይና አፈር መደምደም (compaction) ወዘተ...
.
ግድም በዋነኛነት ለነዚህ አገልግሎቶች ይገነባል፦
1- ጎርፍን ለመቆጣጠር - for flood control
2- ለውሃ አቅርቦት እና የመስኖ ስራ - for water supply and irrigation
3- የኤሌትሪክ ሃይልን ለማመንጨት - for electric power generation
4- የአንድን ወንዝ ፍሰት ለመመጠን እና ለመቆጣጠር - for regulation or balancing of a river flow

#Hydraulics

@etconp
👍17
📌የ ምስራች ዜና ለ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በ ሙሉ

🏗በ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በ ተቋራጭነት፣በ መንገድ ስራ፣በ ኢንተርየር ዲዛይን፣በ ሰብ ኮንትራክት፣በ ብረታ ብረት፣በ እንጨት ስራ እና የ ህንፃ ግንባታ ተያያዥ ስራዎች ያላቹ በ ሙሉ

🗞አዳዲስ ጨረታዎች ሲወጡ፣ ዕለታዊ የማተርያል ና ማሽነሪ Cost ለማወቅ በቀላሉ በ Private ቴሌግራም ቻናል አመቱን ሙሉ በ ማይታመን ዋጋ እንዲደርሳቹ ለምትፈልጉ ከታች ባሉት አደራሻዎች አናግሩን።

👊እስካሁን ከ ደረጃ 1 እስከ 10 በዛ ያሉ
በየቀኑ አዳዲስ ጨረታዎች እየለጠፍን እንገኛለን (ማረጋገጫ አሁናዊ የ ቻናሉ ገፅታ በ ምስል አያይዘንላቹዋል)

🚧ለመመዝገብ @Philemona7 ወይም @etconpworks ያናግሩን።

☎️ለ በለጠ መረጃ በ +251925446661 ወይም 0707444849 ይደውሉ

🙏እናመሰግናለን🙏

@etconp
👍4