👉የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም
🌟ሰሜን ሸዋ ልዩ ቦታው የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም
⏺ወጪ:- 320 ሚሊዮን ብር
⏺አማካሪው:- SAY Consult
⏺ዋና ህንጻውን የነደፈው:- ሳሙኤል አፈወርቅ ለማ
▶️ነዳፊው የቤቷክርስትያኗን ኪነህንጻ ከሀያኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ከውጭ ማለትም ከህንድ፣ ከአርመን፣ ከጣልያን፣ ከግሪክ ወዘተ በቀጥታ ተቀድተው የመጡትን የንድፍ ትእምርቶች፣ ቅርጽና ደርዞች ሳይመረኮዝ በመስራቱ ሊደነቅ ይገባል።
🚧በ20ኛው ክፍለዘመን መጀመርያ ላይ የኒዮክላሲካል (አራዳ ጊዮርጊስ)፣ የኒዮ ባሮክ (ቅድስት ስላሴ) እንዲሁም የአርመን እና የህንድ ንድፍ ዘይቤዎች (አብዛኞቹ በ1900 መጀመርያ በአዲስ አበባ የተገነቡት አብያተክርስትያናት) የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ህንጻ ንድፎች ላይ ተጽእኖአቸውን ያሳረፉ ሲሆን በዘመናችን ደግሞ ፔዲመንትና አእማዶችን ጭምር ከግሪኮ ሮማን ኪነህንጻ ቋንቋ በብዛት ተውሶ የመስራት ዝንባሌ ይታያል።
🚧የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. እጅግ ብዛት ያለው የእይታ ጥበብና የቤተክርስትያን ንድፍ ሀብት ስላላት ያንን ሀብት በዘመናችን ተርጉመው የሚነድፉ ነዳፊዎች ያስፈልጓታል።
ምስል ምንጭ በይነ መረብ
@etconp

❤16👍7😢1
የውሃ ጋኖች (water supply Reservoir)
.
የውሃ ጋኖች ከጥቅማቸው አንፃር ለ ሶስት ይከፈላሉ
.
1-Collector reservoir
2-Service reservoir
3-Supply reservoir
.
እያንዳንዱ ጥቅማቸው ምንድነው……
.
[Collector reservoir ]
.
ይህ የጋን አይነት ዋና ስራው ውሃው ከሚመነጭበት (የገጸ ምድር ወይም የከርሰ ምድር ውሃ) ቦታ ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚቀመጥበት ጋን ነው፡፡ ጥቅሙ የተሰበሰበውን ውሃ ወደተለያዩ ጋኖች እስኪሰራጭ በጊዜያዊነት እንዲቀመጥና ውሃው ለጋኖቹ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጉልበት እንዲያገኝ ይረዳዋል፡፡ ብዙን ጊዜ ውሃው ከሚመነጭበት ቦታ አቅራቢያ ይተከላል፡፡ ውሃ ፈሳሽ እንደመሆኑ ብዙን ግዜ ሚፈልቀው ከፍታቸው ካነሱ ቦታዎች ስለሆነ ከሌሎች ጋኖች ይልቅ የዚህ ጋን ከፍታ (elevation) ያንሳል፡፡
.
[Service reservoir]
.
ይህ የጋን አይነት በቋሚነት ከcollecter reservoir የተቀበለውን ውሃ የሚያርፍበት ነው፡፡ አሰራሩም ከሌሎቹ ጋኖች ለየት ይላል ፡፡ ውሃው የሚያደርስበትን ግፊት ለመቋቋም የሚያስቸለውን መካች ጉልበት(reaction force) በበቂ ሁኔታ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ በቁመትም በመጠንም ትልቅ ነው፡፡ ወጪ ለመቀነስ ከፍ ካለ ቦታ ይተከላል (ውሃ በ3 አይነት መንገድ ይከፋፈላል
.
1-የሞተር ሀይልን በመጠቀም
2-የመሬት የመሳብ ሃይልን (gravity force) በመጠቀም።
3-የሞተር ሃይልንና የመሬት የስበት ሃይልን በማጣመር በመጠቀም እንዲሰራጭ ይደረጋል ፡፡
በአሁን ጊዜ ሶስተኛው አማራጭ በስፋታ አገልግሎት ላይ ይውላል ይህ አማራጭ ከወጪም አንፃር በጣም ተመራጭ ነው ለዚህ ዘዴ ተመራጩ ደግሞ የservice reservoir ከፍ ካለ ቦታላይ መተከል ወሳኝነት አለው፡፡)
ከዚህ ጋን ቀጥታ ለስርጭት ቧንቧ አይገጠምም ምክንያቱም ከጋኑ የሚወጣው ውሃ ከፍተኛ ጉልበት ስላለው የማሰራጫ ቱቦዎችን ሊያፈነዳ ይችላል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ቀጣዩን የጋን አይነት መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡
.
[Supply reservoir]
.
የዚህ ጋን ዋና ጥቅም ውሃውን ለስርጭት ወደ ስርጭት ቱቦዎች እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ከሰርቪስ ጋን ቀጥታ ወደ ስርጭት ቧንቧ ውሃ አይገባም ምክንያቱም ከፍተኛ ሀይል ስላለው የቧንቧዎቹን የመቆየት አቅም ያሳጥራል ብሎም እስከ ማፈንዳት ያደርሳል፡፡ ይህ እንዳይከሰት የሳፕላይ ጋኖች ይገነባሉ፡፡ ይህ ጋን በቱቦዎቹ የሚያልፈውን ውሃ ግፊት በመቀነስና ፈጥነቱን (velocity) ከ 0.5-2 m/s በማድረግ እና ወደ ቱቦዎቹ የሚገባን ሃይል በመቀነስ (Energy dissipate ) ቱቦዎቹ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ያስወግዳል፡፡ ይህ ጋን ከፍ ባለ ቦታ ይተከላል ነገር ግን ከፍታው ከService reservoir ያነሰ ነው።
.
Like | Share | Comment
#Hydraulics

👍22
ግድብ (Dam) ማለት ገዝፈ አካል ሲሆን የውንዝን ሸለቆ ላይ ተገንብቶ የውሃን ተፋሰስ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚገታ ነው።
ይህ መግታት (blockage) በውሃ ተፋሰስ ላይ መታቆርን (reservoir) ይፍጥራል ይህም ወሃውን ለተፈለገው አገልግሎት እንዲውል ቀሊል ያደርገዋል ። ይህ አጋጅ ገዝፈ አካል ወይም ግድብ ከተለያዩ ቁሶች ይሰራል ፦ ኮንክሪት፣ የድንጋይና አፈር መደምደም (compaction) ወዘተ...
.
ግድም በዋነኛነት ለነዚህ አገልግሎቶች ይገነባል፦
1- ጎርፍን ለመቆጣጠር - for flood control
2- ለውሃ አቅርቦት እና የመስኖ ስራ - for water supply and irrigation
3- የኤሌትሪክ ሃይልን ለማመንጨት - for electric power generation
4- የአንድን ወንዝ ፍሰት ለመመጠን እና ለመቆጣጠር - for regulation or balancing of a river flow

👍17
📌የ ምስራች ዜና ለ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በ ሙሉ
🏗በ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በ ተቋራጭነት፣በ መንገድ ስራ፣በ ኢንተርየር ዲዛይን፣በ ሰብ ኮንትራክት፣በ ብረታ ብረት፣በ እንጨት ስራ እና የ ህንፃ ግንባታ ተያያዥ ስራዎች ያላቹ በ ሙሉ
🗞አዳዲስ ጨረታዎች ሲወጡ፣ ዕለታዊ የማተርያል ና ማሽነሪ Cost ለማወቅ በቀላሉ በ Private ቴሌግራም ቻናል አመቱን ሙሉ በ ማይታመን ዋጋ እንዲደርሳቹ ለምትፈልጉ ከታች ባሉት አደራሻዎች አናግሩን።
👊እስካሁን ከ ደረጃ 1 እስከ 10 በዛ ያሉ
በየቀኑ አዳዲስ ጨረታዎች እየለጠፍን እንገኛለን (ማረጋገጫ አሁናዊ የ ቻናሉ ገፅታ በ ምስል አያይዘንላቹዋል)
🚧ለመመዝገብ @Philemona7 ወይም @etconpworks ያናግሩን።
☎️ለ በለጠ መረጃ በ +251925446661 ወይም 0707444849 ይደውሉ
🙏እናመሰግናለን🙏

👍4
Given the structural drawing of column detail and assume there are 13 columns and you are expected to compute the bar quantity from FOUNDATION LEVEL to BASEMENT FLOOR LEVEL
A. the length of the bar (Total length for 13 columns) and the diameter of the bar
B. Quantify the the total weight of the bar for 13 columns in kilogram (KG)
C. Quantify the total length in BERGA
D. Quantify the stirrup (total length, total weight and in berga) for 13 columns
(ENG)
የኮለን ምሶሶ መዋቅራዊ ስእልተሰጥቷችኋል 13 ኮለን ምሶሶዎችን አሉ ብላችሁ አስቡ በዚህ መሰረት ከ መሰረቱ (foundation level) እስከ ቤዝመንት ያላችሁን ኮለን ማለትም ለfoundation ኮለኖቹን ምን ያህል ብረት እንደሚያስፈልግ አስሉ
ሀ. ለ 13ቱ ኮለን ምን ያህል ርዝመት ያለው ብረት ያስፈልጋል ባለ ስንት ውፍረት ብረት ነው ሚያስፈልገን
ለ. በ ኪሎ (በኬጂ) ግለፁ
ሐ. በ ቤርጋ ግለፁ
መ.ለ ስታፋውም በተመሳሳይ እንደ ሀ,ለ,ሐ ግለፁ
@etconp
Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
YouTube :- https://youtube.com/@Etconp432

👍16❤3
በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ለሚታዩ ችግሮች ሳይንሳዊ ጥናቶችን መሰረት ያደረጉ መፍትሔዎችን ማቅረብ እንደሚገባ ተጠቆመ
በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ለሚታዩ መሰረታዊ ችግሮች ሳይንሳዊ የሆኑ ጥናቶችን መሰረት ያደረጉ መፍትሔዎችን ማቅረብ እንደሚገባ የኢፌዴሪ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረተ-ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጠቁሟል።
ቋሚ ኮሚቴ ይህንን የጠቆመው፤ በወጪ ቆጣቢ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ የግብዓት፣ የወጪ አጠቃቀም እና የዲዛይን ሂደት ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችና ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን ለመለየት በሚያስችለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠንቶ በቀረበው ጥናትና ምርምር ዙሪያ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው።
በውይይት መድረኩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአርክቴክቸርና የሕንፃ ኮንስትራክሽን ክፍል እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው በዘርፉ የካበተ ልምድና እውቅና ያላቸው አንጋፋ ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት፤ የመጠለያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል የወጪ ቆጣቢ ቤት በመገንባት ሂደት የሚያስፈልጉ የግብዓት እቃዎች አቅርቦት፣ የፕላንና ዲዛይን ቅየሳ፣ የፋይናንስ አቅርቦት ዙሪያ የሚያጠነጥነው ጥናታዊ ጹሑፍ ቋሚ ኮሚቴው በሚያደርገው የክትትልና የቁጥጥር ስራ በተጨባጭ መረጃ እና እውነታ ላይ የተደገፈ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ እሸቱ ተመስገን (ዶ/ር) በአሁኑ ወቅት እንደ ሀገር ችግር የሆነውን የመጠለያ ቤት እጥረት ከመሰረቱ ለመፍታት የሚያስችሉ በሳይንሳዊ ጥናቶች የተደገፉና የዳበሩ ግብዓቶችን በመጠቀም የሚወጡ አዋጆችና ፖሊሲዎች ያስፈልጉናል ያሉ ሲሆን፤ ከዲዛይን፣ ከግብዓት አቅርቦት እና ከዋጋ አንፃር የሚታዩ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ ለማስቀመጥ ጥናቱ ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ለሕብረተሰቡ ተደራሽ የሚሆኑ ወጪ ቆጣቢ፣ ጥራታቸው እና ዲዛይናቸው ተጠብቆ የሚሰሩ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታ ስራዎች ከምንጊዜውም በላይ ለዜጎቻችን ያስፈልጋሉ ያሉ ሲሆን፤ ይህንንም ከግምት ያስገባ የሁሉንም አቅም ያማከለ የቤት ግንባታዎችን ተደራሽ ከማድረግ እና በግንባታ ሂደት ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን በመለየትና የመፍትሔ ሀሳብ በማስቀመጥ ለሚመለከታቸው የመንግስት እና ባለድርሻ ተቋማት ለማቅረብ ጥናቱ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።
በውይይቱም በከተማ አካባቢ የሚገነቡ ቤቶች ከወጪ፣ ከጥራትና ዲዛይን እንዲሁም የዜጎችን ፍላጎት ያማከለ ከመሆኑ አንጻር በዓለማቀፍ ደረጃ ያሉ ተሞክሮዎችና ልምዶች በምሁራን የቀረቡ ሲሆን፤ ከዚህም ልምድና ተሞክሮ ተነስተው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ የመፍትሔ ሃሳብ ለማምጣት ጥናቱ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም በጥናቱ የተሳተፉ ምሁራን ገልጸዋል።

👍10
👉የዊንዶው ኦፍ አፍሪካ ፓርክ ግምባታ ተጀመረ
🌟በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አጠገብ ቀደም ብሎ ለፓርክነት ተከልሎ በነበረው ስፍራ ላይ የሚገባው ፓርኩ አጠቃላይ 84 ሄክታር መሬት ይሸፍናል።
🌟በመጀመሪያው ምዕራፍ በ14.5 ሄክታር መሬት ላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ፣ የመዝናኛ ፣ የመናፈሻ ፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች ፣ ሰው ሰራሽ ሀይቅ እና መዋኛ ገንዳዎች እንዲሁም መንገዶች እና የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን እና የህጻናት መጫዎቻ ስፍራዎችን በውስጡ የሚይዝ ይሆናል።
🌟በፕሮጀክቱ የእያንዳንዱን የአፍሪካ ሀገር ባህልና ማንነት የሚያንጸባርቁ ቅርሶች እንደሚቀመጡም ነው የተገለጸው።
✨በፓርኩ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና መሆኗን እና የቦሌ አየር መንገድም የአፍሪካ መግቢያ በር መሆኑን የሚያሳይ ታላቅ የዊንዶው ኦፎ አፍሪካ ማማ እና የአፍሪካ ሙዝየም እንዲሁም ሆቴሎችና የንግድ ህንጻዎችን የሚያካተቱ ይሆናል።
✨በአይነቱ እና በግዝፈቱ ታላቅ ነው የተባለለትን ይህንን ፖርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጅነሪንግ ካምፓኒ የተባለ ተቋራጭ የሚገነባው ሲሆን በ18 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎም ይጠበቃል።

👍14👌2
Ethio Construction Engineering
Given the structural drawing of column detail and assume there are 13 columns and you are expected to compute the bar quantity from FOUNDATION LEVEL to BASEMENT FLOOR LEVEL A. the length of the bar (Total length for 13 columns) and the diameter of the bar…
Answer for the rebar question
መልስ ለ ብረት ስራ
Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
YouTube :- https://youtube.com/@Etconp432
መልስ ለ ብረት ስራ
Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
YouTube :- https://youtube.com/@Etconp432
👍6❤2👏1🏆1
በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት ሥልጠና ያጠናቀቁ ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊሠማሩ ነው።
በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት የሚያበቃቸውን ሥልጠና ያጠናቀቁ የመጀመሪያውዙር ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊሠማሩ መሆኑን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሲቭል ኢንጂነሪንግ፣ በኮንስትራክሽን ማናጅሜንት ቴክኖሎጂ፣ በአርክቴክቸር እና መሰል ሙያዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቁ ተማሪዎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ነበር ተብሏል።
ሥልጠናው፥ ከዛሬ ሦሥት ዓመት በፊት በቀድሞው ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የጀርመን ኮንስትራክሽን ማኅበራት ፌዴሬሽን በጋራ እንደተጀመረ ነበር።
‘ጎኤቴ’ በመባል በሚታወቀው የጀርመን ባህል እና ቋንቋ ኢንስቲትዩት ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ከ50 በላይ የሚሆኑ ሠልጣኞች ናቸው።
ከዚህ ውስጥ 11ዱ ሥልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ የጀርመን ኮንስትራክሽን ፌዴሬሽን የሚፈልገውን መስፈርት አሟልተው የመጨረሻውን ፈተና በማለፍ ለጉዞ ዝግጁ ሲሆኑ 6ቱ ጀርመን ከሚገኙ አሠሪዎቻቸው ጋር የሥራ ውል ተፈራርመዋል።
ሥልጠናቸውን አጠናቀው፣ የመጨረሻው ምዘና አልፈው እና አስፈላጊውን የሥራ ትዕዛዝ ተቀብለው ወደ ጀርመን ሀገር ለመጓዝ ዝግጀታቸውን ያጠናቀቁ እንዲሁም በመሠልጠን ላይ የሚገኙትን ምሩቃንን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ማነጋገራቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

👏12👍6❤2
ማስታወቂያ
ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት!
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ከመጪው ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል በመንግሥት የተወሰነውን የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት የተመለከተ የውይይት መርኃ-ግብር አዘጋጅቷል፡፡
በዚሁ መሠረት በመጪው ሰኔ 13 ቀን 2015 ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል በሚዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በዚህ የግዥ ሥርዓት የተመዘገባችሁ አባላትም ሆናችሁ ያልተመዘገባችሁት የማኅበራችን አባላት እንዲሁም መላው የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች በዚሁ የውይይት መርኃ-ግብር ላይ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡
በተለይ በዚህ በአዲሱ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ያልተመዘገባችሁት የማኅበራችን አባላትም ሆናችሁ ያልተመዘገባችሁት መላው ሥራ ተቋራጮች ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በማንኛውም የመንግሥታዊ ግዥ ሥርዓት ውስጥ ተሳታፊ መሆን የሚችሉት በአዲሱ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ውስጥ የታቀፉ ሥራ ተቋራጮች ብቻ መሆናቸውን ከወዲሁ ተገንዝባችሁ በመርኃ-ግብሩ ላይ ተሳታፊ እንድትሆኑ አጥብቀን እንመክራለን፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር

👍2
👉የፒኤችዲ ነጻ የትምህርት እድል
🚧PhD scholarship opportunity at LondonMet - less than a week left to submit an expression of interest by 9 June 2023!
🌟"Afropolitan London" is a research project that brings together a PhD supervision team including Mavernie Cunningham (Art), Harriet McKay (Design), and Matthew Barac (Architecture) at CUBE: Centre for Urban & Built Ecologies, LondonMet. Apply to join as a doctoral scholar by email
✨details as advised on the VC Scholarship webpage
<https://www.londonmet.ac.uk/applying/funding-your-studies/scholarships/the-vice-chancellors-postgraduate-pgr-scholarships/>). Mid-career professionals or emerging academics are equally welcome to submit an expression of interest.
‘What might London’s future learn from the expression and experience of African metropolitan life? The successful candidate will draw upon the curatorial theme of the 2023 Venice Biennale to read Africa as a ‘laboratory of the future’, exploring intercultural cosmopolitanism and subjectivity in relation to creative placemaking in London. Emergent forms of Black and diasporic identity will be examined through the critical lens of Afropolitanism.‘
The call for expressions of interest in the School of Art Architecture & Design is live (see link https://www.londonmet.ac.uk/applying/funding-your-studies/scholarships/the-vice-chancellors-postgraduate-pgr-scholarships/school-of-art-architecture-and-design/).
The call is part of the university's Race Equity Strategic Plan and as such favours candidates from underrepresented or minority groups with an emphasis on fostering POC academic pathways.

www.londonmet.ac.uk
The Vice Chancellor’s Postgraduate (PGR) Scholarships - London Metropolitan University
A scholarship programme to support our race equity agenda.
❤5👍5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስነ ከተማ ቃለመጠይቅ
ፋና ቴሌቪዥን ከህንጻ ነዳፊው ዳዊት በንቲ ጋር የአዲስ አበባ ስነከተማን በተመለከተ ያደረገው የ7 ደቂቃ ቃለመጠይቅ ተንቀሳቃሽ ምስል ተያይዟል፡፡

👍4❤2
🇪🇹 ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት ማምረቻ ጅምላ እና ችርቻሮ መሸጫ
🛠 በበቂ ሁኔታ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች እደ ምርጫቹ ታገኛላቹ ከበቂ ሀሳብ ጋር
1🔩ፕሌት በሚፈልጉት ሳይዝ ቆርጠን ቀዳዳ አበጅተን እንሰጦታለን
2🧲ጄቦልት በሚፈልጉት የጥርስ መጠን እናም የቁመት መጠን ጥርስ አውጥተን አጥፈን እሰጦታለን
3🪚እንዲሁም ላሜራ 1ሚሊም እስከ 12 ሚሊም ለማስቆረጥ ካሰቡ እኛው ቆርጠን እናስረክባለን
4 ⚙ማንኛውም ላሜራ እንዲሁም ሌላ ብረት ቀዳዳ ሚበሳ ካሎት እበሳለን
5🌈ያጡት እቃ እኛ በሚገርም ሁኔታ ሞደፊክ እናረጋለን
🧰እደው ምን አለፋውት ላሜራ መቁረጫ ቶርኖ ምን ለሁሉም ይጠይቁን ከብቁ ባለሞያ ጋር ሁሉም አለ
ሌላው ብቻ ሚፈልጉት ይዘዙን በታማኝነት በተባለው ቀን ያገኛሉ
📦📦📦መልካም ስራ ለራስ ነው 💌
በዚህ ይደውሉ 0913061530
0923764834 ፀግሽ ፕሌት

👍3
ስለ ሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (Retention Money/Bond) እና የጥገና/የብልሽት
አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
========== ===========
#የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (Retention Money/Bond) የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ የሚባለው በኮንስትራክሽን ውል አስተዳደር ወቅት ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ፈጽሞ ክፍያ በሚጠይቅበት ወቅት የፕሮጀክቱ ባለቤት ከግንባታው አማካሪ መሀንዲስ ጋር በመሆን ስለ ሥራው ጥራት ደረጃ በሚል ሊይዘው የሚችለው ዋስትና ነው፡፡
የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ዓላማ የግንባታውን ጥራት ለማስጠበቅ ሲባል ሥራ ተቋራጮች ለአሰሪዎች የሚገቡት ዋስትና ነው፡፡
የግዥ መመሪያውም በአንቀጽ 28.5(ለ) ላይ በግልጽ እንደሚደነግገው በእያንዳንዱ የክፍያ ሰርተፍኬት ላይ
5 (አምስት) ፐርሰንት የክፍያው ገንዘብ የሚያዝ ይሆናል::
በዋናነት ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ 50(ሃምሳ) ፐርሰንት የሚሆነው ገንዘብ ሥራው እንደ ተጠናቀቀ እና ጊዚያዊ የርክክብ ምስክር ወረቀት (provisional acceptance certificate) ከተሰጠ በኋላ ለሥራ ተቋራጩ ይመለስለታል፡፡
የቀረው ገንዘብ ደግሞ እስከ አንድ አመት ድረስ ዋቢ ሆኖ ይቆያል፡፡
ነገር ግን የተቀረው የመያዣ ገንዘብን አስቀድሞ ሥራ ተቋራጩ ለአንድ አመት የሚጸና ዋስትና ማቅረብ ከቻለ የተያዘበትን ቀሪ ገንዘብ ማስለቀቅ ይችላል::
በተመሳሳይ መልኩም የሲቪል ሥራዎችን በተመለከተም እኤአ በ1994 ዓ.ም የወጣው የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ወጥ ውልም ስለ የዋና ገንዘብ መያዣ ዋስትና በአንቀጽ 59(5) እና 60 ላይ ተቀራራቢ ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል፡፡
ግን የሪቴንሽን ገንዘብ (retention) የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቆ የጊዜያዊ እና
የመጨረሻ ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ የተያዘው 5(አምስት) ፐርሰንት ገንዘብ አብዛኛውን ጊዜ ተመላሽ አይሆንም፡፡
በዚህ ሳቢያም ሥራ ተቋራጮች ለሌላ ወጪ የሚዳረጉበት ሁኔታ አለ፡፡
The law stipulates that the retention bond shall be paid
to contractor after provisional acceptance or final acceptance but its applicability is denied by government side most of the time. So, dear contractors, please ask before you bankrupt.
🌟የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡
በተለይም ከላይ ስለ ሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለ ቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡
የጥገና እና ብልሽት አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡ በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡
ለምሳሌ፡- በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ይነበባል፡-“ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለ ሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡
በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡”
በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ 3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል::
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በቅጽ 18 በሰ/መ/ቁ 101378 በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ናሰው ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር መካከል በነበረው ክርክር የጥገና ዋስትና (maintenance bond) ሊኖር እንደሚችል ካተተ በኋላ አንድ ሥራ
ተቋራጭ በሠራው ህንጻ ላይ የተከሠተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በሌለበት ሁኔታ ወደፊት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሊኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከልከል አግባብነት የሌለው መሆኑን እሰገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡
Via Birhanu T.
#ConstructionLaw

👍8❤7👏1
የቆዩ የንድፍ ውድድሮች
ህብረት ኢንሹራንስ ዋና መስርያ ቤት
ቸርችል ጎዳና
የዛሬ 13 አመት ገደማ በተዘጋጀው የህብረት ኢንሹራንስ የንድፍ ውድድር ጌረታ ኮንሳልት ኃ/የተ/የግ/ማ አንደኛ ወጥቶ አሸንፎ ነበር፡፡
የንድፍ ውድድር የሽልማት መጠኑም 70 ሺህ ብር እንደነበር ከተያያዘው የጋዜጣ ምስል እናያለን፡፡
ከዛን ወዲህ በነበሩት 13 አመታት የግንባታ ዋጋ በስንት እጥፍ ጨምሮ ይሆን? የንድፍ ውድድር ሽልማት መጠንስ?
ምስል ምንጭ ፎርቹን ጋዜጣ

👍5❤2
2023_Report_CorruptionInUrbanPlanning_English.pdf
3.1 MB
ከተማ እቅድ እና ሙስና (Corruption in Urban Planning, a guide for professional and trainee planners)
በአፍሪካ ከተሞች እቅድና ልማት ዙርያ ያለውን ሙስና በጥልቅ የሚተነትነው መጽሀፍ በነጻ በበይነ መረብ ላይ በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በ 2023 እኤአ ቀርቧል፡፡
መጽሀፉ የተያያዘ ሲሆን አውርዶ ማንበብ ይቻላል፡፡
መልካም ንባብ
Via African centre for cities

👍6❤1