Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ከቃሊቲ እስከ ቱሉ ዲምቱ በወፍ በረር ቅኝት

በአዲስ አበባ ከተማ በመገንባት ላይ ከሚገኙ ግዙፍ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል ከቃሊቲ አደባባይ - ቱሉ ዲምቱ ድረስ የሚዘልቀውና 11 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የመንገድ ፕሮጀክት ቀዳሚውን ቦታ የሚይዝ ነው፡፡
የቃሊቲ -ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን ግዙፍነት አጉልተው ከሚያሳዩ የመንገዱ ገፅታዎች መካከል በመንገድ ፕሮጀክቱ 3 ቦታዎች ላይ የተገነቡት የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድዮች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በተለያዩ ዋና ዋና የመንገድ መጋጠሚያ ሥፍራዎች ላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ አካል ሆነው የተገነቡት እነዚህ የትራፊክ ማሳለጫ ድልድዮች ለመንገድ ፕሮጀክቱ ተጨማሪ ድምቀትን ያጎናፀፉ ናቸው፡፡
የፕሮጀክቱ መነሻ በሆነው የቃሊቲ ማሰልጠኛ ቀለበት መንገድ መጋጠሚያ ላይ ተገንብቶ፣ አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ግንባታ ሥራ እየተከናወነበት የሚገኘው የመጀመሪያው ማሳለጫ ድልድይ 240 ሜትር ርዝመት አለው፡፡
የማሳለጫ ድልድዩ የቀድሞውን የቀለበት መንገድ አደባባይ ሳይነካ በቁመት ከፍ ብሎ የተገነባ በመሆኑ የትራፊክ እንቅስቃሴውን ከማሳለጡ ባሻገር ለአካባቢው ገፅታም ልዩ ውበት የሚያላብስ ነው፡፡
በቀለበት መንገዱ ላይ የተገነባው ይህ የማሳለጫ ድልድይ፣ ከሳሪስ አቦ የሚመጣውን ትራፊክ ተቀብሎ ወደ ቃሊቲ የሚያሸጋግር ሲሆን ከስር ያለው ነባሩ አደባባይ ደግሞ ወደ ሳሪስ አቦ እና ወደ ኃይሌ ጋርመንት አደባባይ ለሚተላለፉ ተሽከርካሪዎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
የዚሁ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አካል የሆነው ሁለተኛው የማሳለጫ ድልድይ ደግሞ፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፣ ከሥር ወደ አቃቂ ከተማ ለመግባትና ለመውጣት የሚያገለግል፤ ከላይ ደግሞ በቀጥታ ወደ ቱሉ ድምቱ እና ቃሊቲ አደባባይ በግራና ቀኝ የሚተላለፈውን የትራፊክ ፍሰት በሚገባ የሚያሳልጥ ነው፡፡
ይህ የማሳለጫ ድልድይ 90 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን አሁን ላይ የግንባታ ስራው በመገባደዱ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
ሦስተኛውና የመጨረሻው የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ደግሞ፣ ቀደም ሲል ጋሪ ድልድይ እየተባለ በሚጠራው ሥፍራ የተገነባውና 50 ሜትር ርዝመት እና 20 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በአዲስ መልክ የተገነባው ተሸጋጋሪ ደልድይ ነዉ፡፡
የቃሊቲ አደባባይ- ቱሉ ድምቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 11 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን ሲሆን በ2.4 ቢሊዮን ብር የግንባታ ዋጋ በቻይናው ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (CCCC) እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን, ኢንጂነር ዘውዴ አማካሪ ድርጅት ደግሞ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን እየተከታተለው ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች

@etconp
👍7
ከደጃች ውቤ ወደ ሶር አምባ ሆቴል የሚያቋርጠው መንገድ የጥገና ስራ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ

ባለስልጣን ከደጃች ውቤ ወደ ሶር አምባ ሆቴል አቅጣጫ የሚወስደውን አቋራጭ የአስፋልት መንገድ በመጠገን ለትራፊክ ክፍት አደርጓል፡፡

በተለያየ ምክንያት የተጎዳውን የአስፋልት ክፍል ለይቶ በማንሳት 264 ሜትር ርዝመት በ7 ሜትር የጎን ስፋት የአስፋልት ጥገና የተከናወነለት ይህ የመንገድ ክፍል በአካባቢው ያለውን የትራፊክ ፍሰት በማሻሻል የተቀላጠፈ የትራፊፈክ ፍሰት እንዲኖር ያግዛል፡፡

በዚህ ዓመት ከበልግ ወቅት ጀምሮ እስከ አሁን የዘለቀው የዝናብ ሁኔታ በባለሥልጣኑ አጠቃላይ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ቢሆንም የአየር ሁኔታ አመቺነትን በመጠቀም በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የተያዙ ሥራዎችን ለማሳካት በትጋት እየተሰራ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች

@etconp
👍7
The Fédération Internationale Des Ingénieurs-Conseils (FIDIC) is an international organization that produces various standard construction contracts, known as FIDIC contract books. They are often referred to by the color of their cover:

1. Red Book (Conditions of Contract for Construction): This book is specifically for construction contracts and focuses on works designed by the Employer. The Red Book is most suitable for projects where design is completed before construction begins.

2. Yellow Book (Conditions of Contract for Plant & Design-Build): This book is for projects where the contractor designs and builds the project. It is particularly relevant for plant and design-build works, such as mechanical, electrical, and process plants.

3. Silver Book (Conditions of Contract for EPC/Turnkey Projects): The Silver Book is aimed at EPC (Engineering, Procurement, and Construction) and turnkey projects. Here, the contractor assumes most of the design and construction risks.

4. Green Book (Short Form of Contract): This book covers smaller projects, like repairs and renovations, with simple and straightforward contract agreements.

5. Gold Book (Conditions of Contract for Design, Build and Operate Projects): This book is specifically for Design, Build, and Operate (DBO) projects. It includes provisions for the design, construction, and long-term operation of the works.

6. Blue Book (Dredgers Contract): This book, produced in association with the International Association of Dredging Companies (IADC), is exclusively for dredging and reclamation works.

7. White Book (Client/Consultant Model Services Agreement): This book guides agreements between clients and consultants for the provision of professional services. It mainly involves consultancy assignments, where consultants are engaged to provide expert advice.
✦ ━━━━━━━ ✦
   @etconp
✦ ━━━━━━━ ✦
👍10❤1
ለሕዳሴ ግድብ ባለፉት 10 ወራት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለፉት አስር ወራት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

በዚህም ከሃምሌ 01/2014 እስከ መጋቢት 30/2015 ድረስ ከአገር ዉስጥ ቦንድና ስጦታ 897 ሚሊዮን በላይ መሰብሰብ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ከዲያስፖራ ቦንድና ስጦታ ከ13 ሚሊዮን በላይ እንዲሁም ከአጭር የሞባይል መልእክት አገልግሎት ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ እና በኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል የስጦታ አካውንት ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ እንደተሰበሰብ ተጠቁሟል።

በሚያዚያ ወር እንዲሁ ከአገር ውስጥ ቦንድና ስጦታ፣ ከአጭር የሞባይል መልእክት አገልግሎት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል የስጦታ አካውንት በአጠቃላይ ከ67 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡም ነው የተመላከተው።

ሆኖም በዘንድሮው በጀት ዓመት ባሉት አስር ወራት ለህዳሴ ግድቡ የተሰበሰበው ጠቅላላ ገንዘብ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በተወሰነ መጠን መቀነሱን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሀይሉ አብርሃም ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

የህዳሴ ግድቡ ከተጀመረበት መጋቢት 2003 ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 30/2015 ደረስ ከአገር ውስጥና በውጭ አገር ካሉ ኢትዮጵያዊያን የተሰበሰበ ገንዘብ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑ ተገልጿል።

ከተጀመረ አስራ ኹለት ዓመታትን ያስቆጠረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጠቅላላ ስራው 91 በመቶ መጠናቁ የተጠቆመ ሲሆን፤ ቀሪ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ከኹለት እስከ ሦስት ዓመታትን እንደሚወስድ ተመላክቷል።

ግድቡ ሙሉ ለሙሉ ተገንብቶ ሲጠናቀቅም 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የውሃ መጠን በመያዝ እና ከ5 ሺሕ ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ  ኃይል በማመንጨት በአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ግድብ እንደሚሆን ይጠቀሳል።

Via አዲስ ማለዳ

@etconp
👍6❤3
👉ስለ ኦፒሲ እና ፒፒሲ የ ሲሚንቶ ኣይነቶች ትንሽ እንንገራቹ
.
⏩OPC— Ordinary Portland cement

⏩PPC —Portland pozzollana cement

➡በሀገራችን ኢትዮጲያ በስፋት ህንፃ እና መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ በስፋት እየተጠቀምንባቸው የምንገኝባቸው የሲሚንቶ አይነቶች ናቸው።

የሁለቱንም የሲሚንቶ አይነቶች ጥቅም አንድነት እና ልዩነት ከዚህ በታች አጠር አድርገን እናቀርባለን።

▶ኦፒሲ/OPC/ በምጣነ ስርገት( Permeability) ከ ፒፒሲ/ PPC/ ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ ነው።
ውሃ ዘልነት /Heat of Hydration/ የኦፐሲ ከፍተኛ በመሆኑ ከፒፒሲ በተሻለ መልኩ ቶሎ የሚፈለገውን ጥረንካሬ ቀድሞ ያገኛል።

በተቃራኒው ደግሞ ፒፒሲ heat of hydration ቀርፋፋ በመሆኑ ለመርጋት/curing period/ ተጨማሪ ቀናት ይወስዳል
ማለት ነው።

👉በጥንካሬ ደረጃ /Grade of Strength / ኦፒሲ 42.5R grade cement ሲሆን ፒፒሲ ደግሞ 32.5R Grade Cement ነው።

➡Note: Number represent compressive strength of
cement in MPa.

@etconp
👍12
La Sagrada Familia, located in Barcelona, Spain, is indeed one of the most remarkable and splendid architectural constructions in the world. The construction started on 1882 and still under construction meaning it one the worlds construction which takes about 139 years till now.
Official sources estimate that La Sagrada Familia will be completed by 2026.
What do you think about it
✦ ━━━━━━━ ✦
   @etconp
✦ ━━━━━━━ ✦
❤1👌1