Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👍5❤2
👉ከ 90 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሐዋሳ ከተማ መግቢያ ሚሊኒየም ፓርክ በነገው ዕለት እንደሚመረቅ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው ምክትል ኃላፊ ታሪኩ ታመነ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በከተማው በ2014 የተጀመሩትን አብዛኛዎቹን ፕሮጀክቶች በዚህ ዓመት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ ነው፡፡

በከተማ በተለይም በUIIDP የሚደገፉ 29 ፕሮጀክቶች መኖራቸው ጠቁመው፤ ከአስፋልት መንገድ ግንባታ ውጪ ያሉት ሌሎች ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቁ ገልጸዋል፡፡

ከኹሉም ለየት የሚለውና ጥቁር ውሃ መግቢያ በር ላይ እየተገነባ የሚገኘው ሚሊኒየም ፓርክ ሪስቶሬሽን ፕሮጀክት ለከተማውና ለክልሉ እንዲሁም እንደ አገርም ትልቅ ትርጉም ያለው ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡

ሰኔ 2014 የአንድ ዓመት የግንባታ ውል የተገባለት ፕሮጀክት ከ90 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበትም ገልጸው፤ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታ የሲዳማን ባህላዊ ዕሴቶችን ማሳየት የሚችልና በአሁኑ ወቅት ዓለም የደረሰበትን ሙሉ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተገነባ እንደሆነም ያስረዱ ሲሆን፤ ወደ ሐዋሳ ከተማ መግቢያ በር የሆነው ፕሮጀክት በአገሪቱ ካሉት መሰል ፕሮጀክቶች የመጀመሪያው ይሆናል ብለዋል።

በጥቁር ዉሃ ዳቶ ሐዋሳ መግብያ በር ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ተክኖሎጂ የተገጠመለት በመሆኑ ወጪና ገቢ የትራፊክ ፍሰት ከመቆጣጠሩም በላይ የከተማዉን ብሎም የህብረተሰቡን ደህንነት ለተጠበቀ ያግዛል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የመግቢያ በሩ በነገው ዕለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።

@etconp
👍7❤1
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
Personal Information (ግላዊ መረጃ) ጨርሳችሁ ከዛም personal ability proof (የግል ብቃት ማረጋገጫ) ጨርሳችሁ ከሞላችሁ በኋላ ከዛም sample ካስቀመጣችሁ በኋላ ስራ ሲመጣላችሁ እንዲ ነው።

አሁንም አልረፈደም ተመዝገቡ አስፈላጊውን መረጃ አሟሉ ተጠቀሙ እራሳችሁን ገበያ ውስጥ ክተቱ

መመዝገብ ማለት ስም እና ስልክ አስቀምጦ መውጣት አይደለም ይሄ አቴንዳስ አይደለም ስራ ነው ስለዚህ እያነበባችሁ የተጠየቃችሁትን ግላዊ መረጃ እና የብቃት ማረጋገጫ በሙሉ አስገቡ አለበለዚያ incomplete ይሆናል እሱ ደግሞ ብዙ ተፎካካሪዎች ባሉበት መስክ ተመራጭ አያደርጋችሁም

ሊንክ:-https://m.buildmost.com/#/main_Promotion_page?code=U3WB0Y

ከዛም free register
👍2
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
እንደምትመለከቱት ነው ሁሉም unsubmitted ነው ሚለው ….. እንዲህ አይነት ውዥንብሮችን ለማጥራት ቪዲዮ ያስፈልጋል ችግር የለውም እንሰራለን

እስከዛ ተመዝገቡ ከዚህ ሊንክ:- https://m.buildmost.com/#/main_Promotion_page?code=U3WB0Y
👉በግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ስለሚነሱ ቅሬታዎች /Claim/

🌟ክፍል አንድ

▶️ማንኛውም ሰው በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ በሚገጥመው መስተጋብር የተለያዩ ጥያቄዎች ወይም መብቶች ሊኖረው ይችላል፡፡

ከዚህ ንድፈ ሃሳብ በመነሳት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውም በርካታ ቅሬታዎች ወይም የመብት ጥያቄዎች መነሳታቸው  የማይቀር ክስተት ነው፡፡

እንደሚታወቀው የግንባታው ዘርፍ ብዙ ባለድርሻ አካላትን ማሳተፋ ብቻ ሳይሆን በተለያየ ሙያ ዘርፍ ውስጥ ያሉ ሰዎችንም  ጭምር የሚያሳትፍ ነው፡፡

ይህም በመሆኑም ከየባለድርሻ  አካላት በርካታ ቅሬታዎች መነሳታቸው የታወቀ ነው፡፡ ከዚህ ብሂል በመነሳት አንዳንዶች ከውል በመነጨ ጉዳይ የውል ቅሬታዎችን የሚያነሱ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ሕጉ አስቀድሞ ባስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መሠረት ውል ሳይኖር አላፊነት በመኖሩ ምክንያት መብታቸውን ከውል ውጭ ሲጠይቁ ይስታዋላል፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚነሱ አለመግባባቶች እና ቁርሾዎች እንደ ምክንያትነት የሚነሣው የቅሬታዎች ወይም መብቶች ጥያቄ ጉዳይ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ቅድሚያውንም የሚወስዱት የቅሬታ መነሻዎች በተለይም ከሥራ ርክክብ መዘግይት እንዲሁም ከውል መለወጥ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው፡፡

በሃገራችንም ምንም እንኳን ልማዱ በዓለም አቀፍ ሥራ ተቋራጮች በርከት ቢልም ቅሉ፤ የሃገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮችም ቢሆን አሁን አሁን የተለያዩ የኮንስትራክሽን የመብት ጥያቄዎች ሲያስተጋቡ ይስተዋላል፡፡

በዋናነትም ለነዚህ የኮንስትራክሽን ሥራ ቅሬታዎች ወይም የመብት ጥያቄዎች መበራከት እንደ መነሻነት የሚቆጠሩት አንድም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ውስብስብነት፣ ከፍተኛ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት መሆን እንዲሁም አሁን አሁን ሥራ ተቋራጮችም ሆነ ባለቤቶች ወደ ክስ እና ሙግት ሥነ ሥርዓት ልማድ ማድረግ እንደ ምክንያትነት ይወሰዳሉ፡፡

ከዚህ በመቀጠል የግንባታ ሥራዎች ላይ ስለሚነሱ ቅሬታዎች ምንነት ብሎም ፍረጃ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ልማድ በሚከተሉት ክፍሎች በአጭሩ የምንዳስስ ይሆናል፡፡

🚧ትርጉም

⏺የግንባታ ስራ ላይ ቅሬታዎች ከተለያየ ምንጮች ሊመጡ ይችላሉ፡፡ ከውል፣ ከውል ውጪ እንዲሁም ከሕግ ሊመነጩ ይችላሉ፡፡

▶️ቅሬታ ማለት ምን ማለት ነው?     
  
Black’s law dictionary 9th edition የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቶት እናገኛለን፡፡ â€œclaim is the aggregate of operative facts giving rise to a right enforceable by a court.” á‰…áˆŹá‰ł ማለት በፍርድ ቤት ሊፈጸም የሚችል በፍሬ ነገሮች የተደገፈ የመብት ጥያቄ ነው፡፡

ቪሰንት ስሚዝ የተባሉ ምሁር (civil Engineering Claims,1989) በሚለው መጽሐፋቸው የመብት ጥያቄ (Claim) የሚለውን ቃል እንደሚከተለው አብራርተውታል፡-

[C]laims are a general term for the assertion of a right to money, property or a remedy… [Sic] In relation to construction industry, claims means, a demand by a contractor for extension of time or for an extra payment of an item of work carried out by him on behalf of the employer for which a readily identifiable amount cannot be ascertained under the term of contract.”

እንደ ስሚዝ ገለጻ ከሆነ ቅሬታ ባጠቃላይ የገንዘብ፣ የንብረት እንዲሁም የካሳ ጥያቄ የሚስተናገድበት ሥርዓት መሆኑን ከገለጸ በኋላ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውም ሥራ ተቋራጩ አሰሪውን ለተጨማሪ ሥራው ተጨማሪ ገንዘብ እንዲሁም ጊዜ እንዲጨመርለት የሚጠይቅበት መንገድ እንደሆነ ያብራራሉ፡፡

ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው የመብት ጥያቄ የሚባለው አንድ ሕጋዊ የሆነን ነገር የምንጠይቅበት ሥርዓት መሆኑን አይተናል፡፡

እንደ ሲርስ ክላፍ (2008) እይታ ከሆነ አብዛኛውን ጊዜ የግንባታ ሥራ ቅሬታዎች የሚነሱት ከመጠን በላይ ያልተጠበቀ ወጪ ሲያጋጥም፣ ሥራው ያለአግባብ ሲሰራ፣ የሕጉ መወሳሰብ (legal entanglement) እንዲሁም የተለያዩ ሥራ ተቋራጮች አሉታዊ እንቅስቃሴዎችን እንደ ምክንያትነት ያስቀምጣል፡፡

የሚገርመው ነገር አልፎ አልፎ የመብት ጥያቄዎች በባለሃብቶች እና ማህንዲሶች ዘንድ በአይነ ቁራኛነት ሲስተዋል እናያለን ለምን ቢባል ይህ መንገድ አብዛኛውን ጊዜ የሥራ ተቋራጮች በመብት ጥያቄ ሽፋን አስቀድመው ያላነሷቸውን መብቶች ወይም ስህተቶች መሸፈኛ ስትራቴጂ ስለሆነ ጭምር ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የግንዛቤ እጥረት እንጅ እንደ ትክክለኛ አመክንዮ አይወሰድም ለምን ቢባል እንደሚታወቀው የመብት ጥያቄ የኮንስትራክሽን ሂደት አንኳር አካል ከመሆኑ በላይ ጥሩ የሚባል የመብት ጥያቄ እና የግጭት አፈታት ሥርዓት መኖር ለጥሩ ምህንድስና ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው ንግድም ሰናይ ነው፡፡

በቀጣይ ክፍል...

በግንባታ ፕሮጀክቶች፣ ቅሬታ ሊያስነሱ ስለሚችሉ ዋና ዋና ምክንያቶች

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👍15
👉በግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ስለሚነሱ ቅሬታዎች/Claim/

🌟ክፍል ሁለት

▶️በግንባታ ፕሮጀክቶች የቅሬታ መነሻ ምክንያቶች

⏺በግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ቅሬታዎች የተለያየ መነሻ ምክንያት ይኖራቸዋል፡፡

የቅሬታ መነሻ ምክንያቶችን ጠንቅቆ ማወቅ፣ ቅሬታዎችን ለማስቆም ወይም ለመቅረፍ በምናደርገው ሂደት ውስጥ የመጀመሪያውን ደረጃ እንደመጓዝ
ይቆጠራል።

በግንባታ ፕሮጀክቶች፣ ቅሬታ ሊያስነሱ የሚችሉ ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

*በግንባታ ወይም በግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ መዘግየት ምክንያት/Delays in construction and completion of the contract/

*በግንባታ ግብዓቶች አቅርቦት መዘግየት ምክንያት/Delays in the delivery and supply of materials/

*የስራ ሂደት ሊያስተጓጉል የሚችል የአየር ንብረት ለውጥ ሲያጋጥም /Weather which slows down or prevents construction from proceeding/

*የአሰሪ የለውጥ ስራ ፍላጎት /Owner requested changes/

*ከአሰሪ ፍላጎት ውጪ የሚፈጠር አስገዳጅ የለውጥ ስራ/Changes which occur not at the request of the owner/

*ደካማ የሥራ አመራርና አስተዳደር/Poor management and administration of the construction site/

*የግንባታ ሥፍራው ሁኔታዎች/ Site conditions/ከተጠበቀው የተለየ ሁኔታ ሲያጋጥም ስራው ፈፅሞ ለመስራት አዳጋች ወይም ከባድ ሆኖ ሲገኝ/ The work becomes impossible to perform/

*የዕቅዶች እና መመዘኛዎች በበቂ ሁኔታ አለመቅረብ/Insufficient plans and specifications/

*ከባለድርሻ አካለት አንዱ ፣ለስራው አስፈላጊ ወይም ወሳኝ የሆነን መረጃ በጊዜው ሳያሳውቅ  መዘግየት ሲፈጠር
የግንባታ ፕሮጀክቱን ለማከናወን ማናቸውም ባለድርሻ አካላት ወይም ተሳታፊዎች መካከል በሚፈጠሩ ቅጭቶች ምክንያት/Conflicts between those involved in the construction of a project/

*በአሰሪው ወይም በሥራ ተቋራጭ በኩል ውል ለማቋረጥ መጠየቅ  /Termination of the contract by the owner or the contractor/

*ከውል መርሃ ግብር ውጪ በተፋጠነ የስራ ክንዋኔ ምክንያት/Acceleration of the work/

*በበቂ ሁኔታ አለማቀድና ሥራን አስተባብሮ መምራት አለመቻል ሲፈጠር/Failure to adequately schedule and coordinate the work/ እና

*የባለድርሻ አካላት መካከል ተናቦ ያለመስራት ወይም ያለመናበብ ችግር ሲፈጠር/Failure of parties to cooperate with each other in the performance of the work.

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👏9👍7
👉ከግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር ተያይዞ ስለሚሰጡ የዋስትና ዓይነቶች መጠነኛ ገለጻ [Construction Security]

🌟ክፍል አንድ

▶️በውል አፈጻጸም ወቅት የተለያዩ ዋስትናዎች ሲተገበሩ ይስተዋላል፡፡

⏺ለምሳሌ፡-
-የግምጃ ቤት ሰነድ (treasury bill)

-ማገቻ(bond)

-በቅድመ ሁኔታ የሚሰጡ ዋስትናዎች (conditional guarantees)

-ያለቅድመ ሁኔታ የሚሰጡ ዋስትናዎች (on demand/Unconditional guarantees)

- የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና (Bid security)

-የቅድመ ክፍያ ዋስትና((Advance security bond)

-የሰው ዋስትና (surety ship)

-የንብረት ዋስትና (pledge or mortgage)

-ራሳቸውን የቻሉ የብድር ሰነዶች ወይም ክሬዲት (Standby letters of credit) ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

አብዛኛውን ከላይ የተባሉት የዋስትና ሰነዶች በገንዘብ አበዳሪ ተቋማት እና ኢንሹራንስ ድርጅቶች ይዘጋጃሉ፡፡

ነገር ግን የሰው እና የንብረት ዋስትና ግን በግራ ቀኝ ተዋዋይ ወገኖች በራሳቸው አሊያም በሌላ ሦስተኛ ወገን አላፊነት ሊከናወኑ ይችላል፡፡

በውል አፈጻጸም ወቅት የዋስትና መኖር በተዋዋዮች ዘንድ ከፍተኛ መተማመን እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ሌላው የውሉን አፈጻጸም ተጠባቂ (predictable) እንዲሆን ያደርጋል፡፡

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪም አንድ የፕሮጀክት ባለቤት ሥራው በተያዘለት ጊዜ እንዲያልቅ በማሰብ የፕሮጀክት አፈጻጸም ዋስትና አስፈላጊነት ትዝ ካለው፤ ለፕሮጅቱ የሚመቸውን የዋስትና ዓይነት ማለትም የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና፣ በገንዘብ አበዳሪ ተቋማት የሚዘጋጅ ዋስትና ወይም ክሬዲ አንዳንዴ ደግሞ የፕሮጀክቱን ክፍያ ገንዘብ በፐርሰንት መያዝ (retention) እንዲኖር ሊያስብ ይችላል፡፡

የሆነው ሆኖ እነዚህ የዋስትና መንገዶች ተመሳሳይ ዓላማ አላቸው፡፡ ይህም በተዋዋዮች መካከል መተማመን እና ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎች (risk) በመቀነስ ግብይትን ማፋጠን ነው፡፡ ዳሩ ግን እያንዳንዳቸው የራሳቸው ባህሪይ አላቸው ብሎም በአፈጻጸም እና አተገባበር የተለያዩ ናቸው፡፡ ስለሆነም አሰፈላጊነታቸው መታየት ያለበት እንደየ ፕሮጀክቱ አካሄድ፣ መጠን እና ጊዜ ሊሆን ይቻላል፡፡

በዓለምአቀፍ ደረጃ ባሉ ግብይቶችም የዋስትና ሰነዶች በጣም የተለመዱ ናቸው፡፡ በተለይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) የዋስትና ወረቀቶች እና ክሬዲ ሥምምነት (UN Convention on Independent Guarantees and Standby Letter of Cedit) በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው፡፡

ይህ ዓለምአቀፍ ሥምምነት እኤአ በ1995 በአሜሪካዋ የኒዮርክ ከተማ ለሥምምነት ክፍት የሆነ ሲሆን 8 (ስምንት) አገራት በመፈረምና በማጽደቅ ተቀብለውታል፡፡ ኢትዮጵያ ግን የዚህ ሕግ ፈራሚ አገር አይደለችም፡፡

ሆኖም ግን ይህ ሥምምነት በዓለምአቀፉ የንግድ ሕግ ኮሚሽን (United Nations Commission on International Trade Law/UNCTRAL) እንደመዘጋጀቱ መጠን ዋስትናን በተመለከተ በቀጣይ ሌሎች የዓለም ሀገራት ለሚያዘጋጇቸው ዝርዝር ህጎች በሞዴልነት እንደመነሻ ሊያገለግል ይችላል፡፡ በተለይ ስምምነቱን የፈረሙ አገራት በዓለምአቀፍ ደረጃ ለሚያከናውኗቸው የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ላይ ዋስትናን በተመለከተ ይህ ሕግ ተፈጻሚ ነው፡፡

ሌላው ዋስትና ሲነሳ ምንጊዜም ቢሆን አብሮ የሚነሳው የመድን ውል (insurance) ነው፡፡ ዋስትናም (security/guarantee) ሆነ መድን አንድ የሚያደርጋቸው ነገር አለ፡፡ ይህም ሁለቱም ባለመብቱን ሊደርስ ከሚችል የአደጋ ስጋት መጠበቃቸው ነው፡፡

ሆኖም ግን በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ሁለቱም የተለያየ የሕግ ውጤት ያላቸው ተግባራት ናቸው፡፡

ዋስትና:
በዋስትና ተግባር ዋስ የሚሆነው ግለሰብ የሚጠበቅበት ግዴታ ቢኖር ባለእዳው ለባለገንዘቡ በውል መሰረት ካልከፈለ ወይም መክፋል ካልፈለገ በሕግ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ጠብቆ በባለእዳው እግር ተተክቶ ዕዳውን ሊወጣ የሚችልበት ሁኔታ ነው፡፡

መድን: 
መድን የገባ ሰው  መደበኛ የሆነ አረቦን (premium) መክፈል እንደተጠበቀ ሆኖ መድን በተገባለት ጉዳይ ሊደርሱ የሚችሉ  አደጋዎችን ይፋ ማድረግን ጨምሮ የመድን ጥቅም (insurable interest) ሊኖረው ግድ ይላል፡፡

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪም ከላይ የጠቀስናቸው የዋስትና ዓይነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስፈላጊነታቸው እየታመነበት ስለመጣ በፕሮጀክት አፈጻጸም ወቅት ሲተገበሩ ይታያል፡፡

📌በ ክፍል ሁለት የዋስትና ምንነት ትርጉም እናያለን።

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👍15
👉ከግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር ተያይዞ ስለሚሰጡ የዋስትና ዓይነቶች መጠነኛ ገለጻ [Construction Security]

🌟ክፍል ሁለት

✨የዋስትና ምንነት

🚧ዋስትና በይዘትም ሆነ በዓይነት መለያየቱን ተከትሎ የተለያዩ ትርጓሜዎችን ሊይዝ ይችላል፡፡

ዋስትና (Security) የሚለው ቃል የመጣው ‘securitat ‘ከሚለው የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም ለዕዳ ማስከበሪያ የሚጠየቅ ገንዘብ እንደሆነ ያሳያል፡፡በጽንሰሃሳብ ደረጃ ዋስትና ሰፋ ያለ ትርጉም ሊይዝ ይችላል፡፡ ለአብነት ያህልም የተለያዩ መዝገበ ቃላቶች የተለያየ ትርጉም ሲሰጡት ይታያል፡፡

* ሜሪያም ዌብስተር መዝገበ-ቃላት (Merriam Webster dictionary)
[S]ecurity as something given, deposited or pledged to make certain the fulfillment of an obligation.” ዋስትና የሚለውን ቃል ግዴታን ለመወጣት ተብሎ የሚሰጥ፣ የሚቀመጥ ወይም የሚያዝ ነገር በማለት ይተረጉመዋል፡፡

* ኦክስፎርድ ኮንሳይስ መዝገበ ቃላት (Oxford Concise Dictionary) 10ኛ ዕትም
ዋስትና የሚለውን ቃል ለብድር ማስከበሪያ ወይም ለግዴታ መወጫ ሊሆን የሚችል መያዣ ወይም ዋቢነት ሲሆን የገንዘብ ብድር መኖርን የሚያሳይ ወረቀት፣ አክሲዮን (stock)፣ የግምጃ ቤት ሰነድ እና ሌሎች ባለቤትነትን ሊያረጋገጡ የሚችሉ ተላላፊ ሰነዶች ናቸው፡፡

* የብላክስ ሎ መዝገበ ቃላት (Black’s Law dictionary) 9ኛ ዕትም
[S]ecurity means collateral given or pledged to guarantee the fulfillment of an obligation...[sic]...especially the assurance that a creditor will be repaid any money or credit extended to a debtor.” ዋስትናን ከብድር ጋር የተያያዘ ግዴታን ለመፈጸም የሚያገልግል መያዣ በማለት ያስቀምጠዋል፡፡

* የተ.መ.ድ የዋስትና ሥምምነት ሕግ
ዋስትና የሚለውን በእንግሊዘኛው ‘Security’ ከማለት ይልቅ ‘undertaking’ በማለት በአንቀጽ 2 ላይ ሰፋ ያለ ትርጉም ሲሰጠው እናያለን፡- â€œan undertaking is an independent commitment, known in international practice as an independent guarantee or as a stand-by letter of credit, given by a bank or other institution or person (“guarantor/issuer”) to pay to the beneficiary a certain or determinable amount upon simple demand or upon demand accompanied by other documents, in conformity with the terms and any documentary conditions of the undertaking, indicating, or from which it is to be inferred, that payment is due because of a default in the performance of an obligation, or because of another contingency, or for money borrowed or advanced, or on account of any mature indebtedness undertaken by the principal/applicant or another person.”በዚህም ዓለምአቀፍ ሕግም ዋስትና ማለት ራሱን የቻለ ግዴታ ሲሆን ይህም በባንክ፣ በገንዘብ ነክ ተቋማት ወይም በግለሰቦች ሊሰጥ የሚችል በተለይም እንደነገሩ ሁኔታ በቅድመ-ሁኔታ አሊያም ያለቅድመ ሁኔታ ተበዳሪው እዳውን መወጣት ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ አሊያም ሌሎች ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን ታሳቢ በማድረግ የሚከናወን የዋስትና ወረቀት ወይም ራሱን የቻለ ክሬዲ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህ የተ.መ.ድ ሕግ በአንቀጽ 1 እንደተመለከተው የተፈጻሚነት ወሰኑ አንድም በዓለም አቀፍ ግብይቶች ላይ ሲሆን ሁለትም በፈራሚ አገራት ብቻ ነው፡፡

* በኢትዮጵያ ህግ ስለዋስትና የተሰጠው ትርጉም

በኢትዮጵያ ሕግጋት ውስጥም ስለ ዋስትና የተመለከቱ አንዳንድ የተበታተኑ ድንጋጌዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ፡-በ2001ዓ.ም የወጣው የፌዴራል መንግስት የፋይናንስ አስተዳድር አዋጅ ቁ.648/2001 ዋስትና የሚለውን ቃል የዋስትና ሰነድ በሚል በአንቀጽ 2 (20) ላይ እንደሚከተለው ይተርጉመዋል፡-

“የዋስትና ሰነድ ማለት የፋይናንስ ቃልኪዳን ወይም የፋይናንስ ግዴታን ለመፈጸም የሚሰጥ ወይም የሚያዝ ማነኛውም ሰነድ ሲሆን፣ የግምጃ ቤት ሰነድን፣ የተስፋ ሰነድን እና ቦንድን ይጨምራል፡፡ ”

ዳሩ ግን የአዋጁ ትርጓሜ የዋስትና ዓይነቶችን ከመዘርዘር ውጪ ዋስትና በምን ሁኔታ ሊሰጥ ይችላል የሚለውን ጉዳይ ግልጽ አላደረገም፡፡

በተጨማሪ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 654(1):
“የመድን ዋስትና ውል ፖሊሲ ማለት የመድን ዋስትና ሰጪ የሚባለው በአንድ ወይም በብዙ የተመደበውን የመድን መግቢያ ዋጋ (ፕርምየም) ተቀብሎ በውሉ የተመለከተው አደጋ በደረሰ ጊዜ ኢንሹራንስ ለገባው ሰው የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ግዴታ የሚገባበት ነው፡፡” በማለት ያስቀምጣል፡፡

ከላይ ከተመለከቱት ለዋስትና ከተሰጡ ትርጓሜዎች የምንረዳው ነገር ቢኖር ዋስትና ቀዳማዊ ግዴታ ሳይሆን የእዳ ማስከበሪያ ተለጣፊ ግዴታ ነው፡፡ በሌላ አባባል የዋስትና ውል ደባል ውል (accessory contract) ነው፡፡ ይህም ሲሆን ዋሱ ባለዕዳው ለገባው ግዴታ ማለትም ባለእዳው ካልከፈል በደባልነት የሚጠየቅበት ሥርዓት ነው፡፡

ከአደጉት አገራት የሕግ ፍልስፋና (developed countries jurisprudence) እና ንጽጽራዊ ጥናት (comparative study) አንጻር ዋስትና የሚለው ቃል በጣም ሰፋ ያለ እና በይዘትም በርካታ ነገሮችን በውስጡ አቅፎ የሚይዝ ነው፡፡ ለምሳሌ፡-

የፋይናንስ ወረቀቶች እንደ አክሲዮን፣ የግምጃ ቤት ሰነድ፣ ቦንድ፣ የንግድ ማህበራት የሚያወጧቸው የብድር ወረቀቶች (debentures) ፣ ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች፣ የኢንቨስትመንት ውሎች፣ ከማዕድን ማውጣት ጋር የተያያዙ ያለተከፋፈለ የወለድ መብት ወዘተ ሊያጠቃልል ይችላል፡፡

በመጨረሻም ዋስትና፣ áˆŠá‹°áˆ­áˆľ ይችላል ተብሎ የሚገመተውን የአደጋ ስጋት የሚያስቀር ሳይሆን ሊገመት የሚችለው አደጋ የደረሰ ወይም የተከሰተ እንደሆነ ፤ጉዳቱን ለመካስ/ በካሳ መልከ ክፍያ መስጠትን የሚያመላክት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

በሌላ ቀጣይ ፅሁፎች

የኮንስትራክሽን ዋስትና ዓይነቶችን ተራ በተራ እናያለን

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👍10👏2🕊1
Autodesk AutoCAD 2024
@etconp
👍7🙏1
🙏9❤3👍3👏3
ETABS 20.3 @etconp
👍5
CSI ETABS Ultimate 21.0.1.3178 (x64) @etconp (1).zip
987.3 MB
ETABS 20.3! 🏗️
🔒zip password: @etconp
📥 Follow the installation notes
@etconp
🙏11👍5❤4
የወልመል መስኖ ልማት ፕሮጀክት በ3.6 ቢሊዮን ብር አጠቃለይ ወጪ  ግንባታው እየተከናወነ ነው

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ባለቤትነት በታህሳስ 2012 በጀት አመት የወልመል መስኖ ልማት ፕሮጀክት ግንባታው  በ3.6 ቢሊዮን ብር አጠቃለይ ወጪ  የተጀመረ  ሲሆን   ፕሮጀክቱ  ሲጠናቀቅ ከ22 ሺህ በላይ አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ነው፡፡

ይህ ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ባሌ ዞን ደሎመና እና ሃረና ቡሉቅ ወረዳዎች  ውስጥ የሚተገበር  ነው ፡፡

ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲደረግ 3 ሜትር ከፍታ እና 50 ሜትር ርዝመት ያለው የወንዝ መቀልበሻ እና 30 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መጋቢ የውሃ ቦይ ግንባታ የሚካሄድ ሲሆን 11,040 ሄክታር ማልማት የሚችል የመስኖ አውታር ግንባታም የሚከናወን ይሆናል፡፡

የወልመል መስኖ ልማት ፕሮጀክት በሁለት ሎቶች ተከፍሎ የሚሰራ ሲሆን የሎት-አንድ  76.68 %  እንዲሁም ሎት-ሁለት  60.07% እስከ  ሰኔ ወር  2015 ዓ/ም ድረስ  ተከናውነዋል፡፡

በፕሮጀክቱም ተጠቃሚ የሚሆኑ አርሶአደሮች በቆሎ፣ ሰሊጥ፣ ማሽላ፣ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በማልማትና በማምረት በዓመት ውስጥ ከ2-3 ጊዜ ምርት ማምረት የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡
የፕሮጀክቱ ተግዳሮቶች የሲምንቶ እጥረት፣  የነዳጅ  አልፎ አልፎ መቆራረጥ፣በስራ ለይ ያሉ የንዑስ ተቋራጮች አቅም ውስንነት ፣የተቋራጩ የአቅም ውስንነት ናቸው፡፡

የተወሰደ የመፍትሄ እርምጃ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በቂ ሲሚንቶ ለተቋራጭ ድርጅቶቹ እያቀረቡ ባለመሆኑ ተቋራጭ ድርጅቶች ሚ/ር መ/ቤቱ ከዚህ በፊት ካደረገው ድጋፍ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ሲሚንቶ እንዲያቀርቡ ግፊት ተደርጓል፡፡

በመስክና በሚኒስቴር መ/ቤት ውይይት  በኩል ተደጋጋሚ የሶስትዮሽ ስብሰባዎችን በማካሄድ  ተግዳሮቶቹ እንዲቀረፉ ጥረት ተደርገዋል፡፡

ተቋራጭ ድርጅቱ የተሻሉ የግንባታ መሽኖችን እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ተሰጥቶት ማስተካከያ አድርጓል፡፡

በፕሮጀክቱ ግንባታ ሁለት አገር በቀል ተቋራጭ ድርጅቶች የሚሳተፉ ሲሆን ሎት-አንድ(የወንዝ መቀልበሻ እና መጋቢ የውሃ ቦይ ግንባታ ሥራውን )  ዓለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ሼል ተቋራጭ  ድርጅት ሲያከናውን ሎት-ሁለት(የመስኖ  መሰረተ ልማት ግንባታን) ኦሮሚያ ኮንስትራክሽን  ኮርፖሬሽን  ተቋራጭ ድርጅት  እያከናወነ ይገኛል፡፡

የፕሮጀክቱ አማካሪ ድርጅት  የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ኮርፖሬሽን  ነው፡፡

@etconp
👍6
Architectural Styles in African Architecture (8 major styles).

1. Nubian architecture - characterized by the use of mud brick and stone architecture, Nubian architecture is found primarily in the Nile Valley region of modern-day Sudan and Egypt.

2. Mud brick architecture
- mud brick architecture is a common style found throughout Africa, and is characterized by the use of mud bricks (dried in the sun) for both residential and public buildings.

3. Swahili architecture - found along the eastern coast of Africa, Swahili architecture is a fusion of African, Indian, and Islamic architectural styles.

4. Sahelian architecture - characterized by the use of adobe brick, Sahelian architecture includes the Great Mosque of DjennĂŠ and other distinctive structures found throughout the Sahel region of Africa.

5. Ethiopian architecture - Ethiopian architecture is known for its use of rock-cut churches, as well as its distinctive house styles characterized by their sloping roofs and whitewashed exteriors.

6. Zulu architecture - characterized by beehive-shaped huts made from woven grass, Zulu architecture is found primarily in South Africa and Lesotho.

7. Moroccan architecture - Moroccan architecture combines Arab and Berber architectural styles, often featuring intricate tiles and mosaics.

8. Berber architecture
- found primarily in North Africa, Berber architecture is known for its distinctive use of earthen materials and the inclusion of courtyards.
@etconp
❤3👏3
👉Construction equipment

▶️are the most crucial and critical resource for a construction company. Construction equipment are a prerequisite for timely completion of all construction projects. As a matter of fact the equipment are one of the most capital intensive long terms investments that a construction company makes. Expenses related to construction equipment have a major impact on wether the company’s balance sheet shows profits or losses and in what quantity. Keeping the economic viability of the company in mind managing the construction equipment and the related expenses becomes top priority at construction equipment companies.

🌟Construction equipment management refers to continuous evaluation of the construction equipment fleet and its cost while at the same time considering the projects at hand.

🚧The process of balancing the expense and use of the construction equipment against the timelines and income from the projects can be called construction equipment management.

🌟A construction equipment manager needs to be able to take practical decisions with regards to management of the construction equipment to ensure maximum benefits with minimal expenses for the company.

🌟Construction equipment should ideally pay for themselves by helping the owner earn more than it costs to own, operate, maintain, store and use the machine. Operation costs are a recurring expense based on frequency of use while idle sitting machines are a drain to the income.

▶️Construction fleets should be evaluated continuously to determine wether

⏺New equipment need to be added to the fleet.

⏺ Equipment or any of its parts need to be replaced.

⏺ If and when under utilised or damaged machines need to be discarded and at what cost.

🌟The choice of construction equipment  for a job site is a key factor to be considered for timely completion of the project within the stipulated budget.It is crucial that the construction equipment managers thoroughly understand the tasks that need to be completed, the machines that need to be used, the budget and time constraints for the same for flawless execution of the construction project.

⏺Construction equipment management can either be taken up project wise or for the company as a whole. Cost-effectiveness is a major criteria of construction equipment management.

🌟Following are the things to be considered for effective construction equipment management

👉The choice of construction equipment and the number in which each of the equipments is required for a certain project or projects.

👉Wether it makes more sense to own, lease or rent the equipment and its effect on the bottom line of the balance sheet.

👉Planning which equipment will be working on which job site at what time and for how long.

👉Considering the transportation and operating costs when dealing with multiple projects and their time lines.

👉How to make the most of the construction equipment at hand.

👉Another major aspect of effective construction equipment management is preventive maintenance of the construction equipment which can help save a lot of down time, money and reduce delays in the project.

▶️All in all effective construction equipment is the answer to making construction projects more cost effective while ensuring timely completion of projects.

@etconp
👍11💯1
👉የኮንስትራክሽን ዋስትና (Construction security)]

🌟ክፍል ሶስት

▶️በኮንስትራክሽን ውል አፈጻጸም ወቅት በርካታ የዋስትና ዓይነቶች ሲተገበሩ ይታያል፡፡ ከቅድመ ግንባታ ጀምሮ በግንባታ ወቅት አንዳንዴም ከግንባታ በኋላ ለሚከሰቱ ችግሮች ዋስትና ጥቅም ላይ ሲውል ይሰተዋላል፡፡

በተለይም የህንጻ አሰሪዎች (Clients) ግንባታው በፈለጉት ጊዜና ዕቅድ መሰረት እንዲካናወንላቸው ካላቸው ጽኑ ፍላጎት የተነሳ ውሉ እንዲፈጸምላቸው አሰፈላጊ ከለላ እንዲኖራቸው ይሻሉ፡፡

በኢትዮጵያም አብዛኛው የኮንስትራክሽን ውሎች መንግስት አሰሪ በመሆን የሚቀርብባቸው ናቸው፡፡

ለማሳያ ያህል የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ፣ የኢንዲስትሪ ፓርኮች ግንባታ፣ የባቡር ዝርጋታ፣ የመንገድ ግንባታዎች ወዘተ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በተለምዶው የመንግስት ኪስ እርጥብ (solvent) ነው ቢባልም በውል አስተዳደር ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች የክፍያ መዘግየት ይስተዋላል በዚህ ጊዜም ሥራ ተቋራጩ ልክ እንደ አሰሪው ሁሉ ግዴታ አለተፈጸመልኝም ብሎ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል፡፡

በመርህ ደረጃ አሰሪ ሆኖ የቀረበው የመንግስት መስሪያ ቤት ውል ባለመፈጸሙ ምክንያት ሼል ተቋራጩ ውል አልተፈጸም በሚል መከራከሪያ ሊያቀርብ እንደማይችል ከፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 3177 ድንጋጌ እና ከተለመደው የላቲን አባባል፡- ‘Exceptio non adimpleti contractus’ (ግዴታ አለተፈጸመልኝምን እንደ መከራከሪያ አለማቅረብ) áˆ˜áˆ¨á‹łá‰ľ ይቻላል፡፡

ታዲያ ከላይ ያሉት ስጋቶች የሚከሰቱ ከሆነ፣ አሰሪውም ሆነ ሥራ ተቋራጮች ሁነኛ የሚሉትን የኮንስትራክሽን ዋስትና ሊጠቀሙ ይገባል፡፡
በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የታወቁ የዋስትና ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነዚህም የዉል ማስከበሪያ፣ የጨረታ ማስከበሪያ፣ የቅድሚያ ክፍያ፣ የዋናው ገንዘብ መያዣ እና የጥገና/ብልሽት ዋስትናዎች ናቸው፡፡ 

🌟የውል ማስከበሪያ ዋስትና (Contract security/ Performance Bond) 

⏺የውል ማስከበሪያ ዋስትና (contract security) ወይም የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና (performance security bond) የሚባለው አንድም ግራ ቀኙ ለገቡት ውል መልካም አፈጻጸም ሲባል በአንድ ሦስተኛ ወገን የሚሰጥ ዋስትና ነው፡፡
አብዛኛውን ጊዜም ሥራ ተቋራጮች ለፕሮጀክት ባለቤቶች ወይም ንዑስ ተቋራጮች ለዋናው ሥራ ተቋራጭ ውል ለመፈጸም ብለው ከአንድ የፋይናንስ ተቋም ወይም ሌላ ሦስተኛ ወገን አማካኝነት የሚቀርብ ዋስትና ነው፡፡
ሆኖም ግን ቀደም ሲል እንደተገለጸው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ተፈጻሚ የሚሆነው ዋናው ባለዕዳ(ለምሳሌ፡-ሥራ ተቋራጭ) ግዴታውን ባይወጣ ነው::

“ከመንግስት አስተዳደር መ/ቤት ጋር የሥራ ውል ያደረገ ወገን እንደውሉ መፈጸም ባልቻለ ጊዜ የአስተዳደር መ/ቤቱ ተዋዋዩ የውል ማስከበሪያ (contract security) በሚል ካስያዘው ገንዘብ ላይ ውል ባለመፈጸሙ የደረሰበትን የጉዳት ኪሣራ መቀነስ ይችላል፡፡ ”

በፌደራል የመንግስት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁ.649/2001 አንቀጽ 47 ላይ በግልጽ እንደተመለከው በተለይም የመንግስት ግንባታ ውሎች ላይ አቅራቢ (ውል ተቀባይ) ሆኖ የሚቀርብ ወገን ግዴታውን ባለመፈጸሙ ምክንያት በውል ሰጪው መንግስት መ/ቤት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ማካካሻ የሚሆን የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

መጠኑን በተመለከተም የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡ እኤአ በ ሰኔ ወር 2010 የወጣው የገ/ኢ/ል/ሚ መመሪያ አንቀጽ 16.25 ላይ እንደተመለከው አሸናፊው ሥራ ተቋራጭ ጨረታውን አሸንፎ ውል በተዋዋለ በ 15 ቀናት ውስጥ ቢያንስ የውሉን 10በመቶ እንደ ውል ማስከበሪያ(Performance security) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

የዋስትናው መክፈያ መንገድም በመመሪያው አንቀጽ 16.16.4 በተመለከተው መሰረት በተጫራቹ ምርጫ በጥሬ ገንዘብ ፣ በቼክ፣ የባንክ ዋስትና ሰነድ ፣ ክሬዲ ወይም በቅድመ ሁኔታ በሚዘገጅ የመድን ቦንድ ሊሆን ይችላል፡፡

በተጨማሪም መመሪያው በአንቀጽ 16.25.3 ላይ ውል ሰጪው የመንግስት መ/ቤት አቅራቢው (ሥራ ተቋራጩ) በውሉ በተቀመጠው መሰረት ግዴታውን መወጣት ካልቻለ የያዘውን ውል ማስከበሪያ ገንዘብ እንደነገሩ ሁኔታ መጠቀም ወይም መውረስ ይችላል፡፡

እንዲሁም ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር ሥራ ተቋራጩ ውሉን በተወጣ ጊዜ ያስያዘው ገንዘብ ይመለስለታል፡፡ /የመመሪያው አንቀጽ 16.25.7 ይመለከተዋል፡፡ /

ሲጠቃለልም የውል ማስከበሪያ ዋስትና ስለፕሮጀክቱ መልካም አፈጻጸም ውል ተቀባዩ ከአንድ ከሌላ ሦስተኛ ወገን ጋር በሚደርገው ግንኙነት ሊቋቋም ይችላል፡፡

🌟በቀጣይ ክፍል

💫ስለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond)

https://youtube.com/@Etconp432
👍12👏7❤3🎉1
👉የግንባታ ሥራዎች ሂደት ደረጃዎች/Stages in Construction/

🌟የግንባታ ሥራዎች የሂደት ደረጃዎች በዋናነት በሶስት የሚከፈሉ ሲሆን እነዚህም:

⏺i. የቅድመ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/Preconstruction Stages/

⏺ii. የግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/construction Stages/

⏺iii. የድህረ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ//Postconstruction Stages/

▶️i. የቅድመ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/Preconstruction Stages/

🚧1.የፕሮጀክት ተፈጻሚነትና አዋጭነት ጥናት/Inception and Physibility study/

✨ይህ ደረጃ አሰሪው ወይም ኢንቬስተሩ ያለመውን ነገር ወይም ፍላጎቱን ወደእውነታ ለማምጣት የመጀመሪያ ሥራው የታሰበውን ፕሮጀክት የተፈጻሚነትና አዋጭነት ጥናት ውጤት ማወቅ ነው፡፡

✨በዚህ ጊዜ የተላያዩ ባለሞያዎችን የሚይዝ ቡድን፡-

⏺የታሰበውን ስራ እውን ሊሆን የሚችል መሆኑንና አለመሆኑን በማስረጃ ያረጋግጣል ለፕሮጀክቱ አዋጭነት ወሳኝ የቦታ መረጣ ያካሂዳል ፕሮጀክቱ በታሰበበት አካባቢ ከገንዘብ ሃብት ውጭ ያሉ የፕሮጀክት ሃብቶች አቅርቦት ሁኔታ፣ የዋጋ ሁኔታና እንደታሰበው ፕሮጀክቶች ዓይነት ሌሎች ሁኔታዎችን ያጠናል፡፡
የፕሮጀክቱን አዋጭነት ስሌት ዘገባ ይዘጋጃል፣ የሥራውን አጠቃላይ ሁኔታ ሊያሳይ የሚችል ሀሳባዊ ረቂቅ ንድፍ ያዘጋጃል፡፡ 

🚧2.የአፈር አካላት ሳይንስ ጥናት /Geotechnical Investigations/

⏺የአፈር አካላት ሳይንስ ጥናት፡-

▶️አጠቃላይ የግንባታ ሥራው የሚከናወንበትን ወይም ግንባታው የሚያርፍበትንና በዙሪያው ያለውን አካባቢ ሊያካልል የሚችል ፤የመሬቱ የመሸከም አቅም፣ ችግርሮችና የመፍትሄ ሃሳቦች የሚጠናበት ነው፡፡

🚧3.የመሬት አቀማመጥ አጠቃላይ ሁኔታ የሰርቬይንግ መረጃ ይሰበሰባል፡፡

🚧4.የዕቅድና የንድፍ ሥራ /Planning and Design stage/

⏺የአፈር ሳይንስ ጥናት መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ቀጣዩ ሥራ የሚሆነው የዕቅድና የዲዛይን ማጠቃለያ ሥራዎች የሚከናወኑበት ነው፡፡በዚህም፡
እንደፕሮጀክቱ ሁኔታ የአርክቴክቸራል፣ስትራክቸራል፣ ኤሌክትሪካል፣የኤሌክሮ ሜካኒካልና የሳኒተሪ የመሳሰሉት የዲዛይንና የንድፍ ሥራዎች ይሰራሉ፡፡

🚧5.የፕሮጀክት ሥራ አመራር መዋቅር ዝግጅትና ዕቅድ

🚧6.የገንዘብ ሀብት ዝግጅት ዕቅድ

🚧7.የታሰበው ፕሮጀክት እንደፕሮጀክቱ ግዝፈትና ሊሰራ ለታሰበበት ደረጃ የሚመጥን፤ ለሥራው ጥራት ደረጃ ዕቅድ
የግንባታ ዕቃዎች ዓይነት ምርጫና የጥራት ልክ ዕቅድየሥራ ተቋራጭ ብቃት ደረጃ ዕቅድና የመሳሰሉት ይሰራሉ፡፡

🚧8.የጨረታ ሥራዎች /Tendering stage/

💫በዚህ ደረጃ የሚከተሉት ስራዎች ይከናወናሉ

▶️የጨረታ ሰነድ የማዘጋጃት ሥራ/Bidding Document Preparation/፡-

⏺በጨረታ ሰነድ ዝግጅት የጨረታ ሼል ባለሞያዎች በጨረታ ሰነዱ ሊያካትቷቸው  የሚገቡ ጉዳዮች እንደሚከተለው ይሆናሉ፡፡

⏹የጨረታ ጥሪ/Bid Invitation /
በቂ ለሆነ ጊዜና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች የጨረታ ጥሪ ይፋ መደረጉ የሚረጋገጥበት ሲሆን የጨረታ ጥሪ አድራጊውን አካል ስምና አድራሻ፣የግነባታ ሥራው ዓይነትና የሚከናወንበትን ቦታ፣ሥራውን ለመስራት የሚፈለገው ተቋራጭ የመወዳደር ችሎታ ዝርዝር መመዘኛዎች፣ሥራው ስለሚፈጀው ጠቅላላ ጊዜ፣የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት አኳሆንና የሚገኝበት ቦታ፣ሰነዱን ለማግኘት ስለሚያስፈልግ ክፍያ መጠን፣የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ሰለሚያበቃበት ቀን፣ የተጫራቾች ዜግነት፣ በጨረታው ለመሳተፍ ቅድሚያ ሊከፈል ወይም ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid security) የሚያዝ ገንዘብ ካለ መጠኑና፣ እነደአስፈላጊነቱ ሌሎች ዝዝር መረጃዎችን የሚይዝ ይሆናል፡፡

⏹የተጫራቾች መመሪያ/instraction to bidders/

በተጫራቾች መመሪያ ዝርዝር፡-
_የጨረታ መገምገሚያ ዘዴዎችና የመገምገሚያ መስፈርቾች/Evaluation Methods and Criteria/
_ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ምን ምን ሊያካትት እንደሚገባው የሚገልጽ ዝርዝር
_ የአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚገባቸው መሆኑን
_ ለዘመኑ የታደሱ የተለያዩ ለመጫረት ብቁ የሚያደርጉ ምዝገባዎች ማቅረብ አስፈላጊ ስለመሆኑ
_ ለመንግስት የሚገባውን ግብር ከፍሎ ማረጋገጫ ያለው ስለመሆኑ (Tax Clearance)
_ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈር እንደሚገባቸው
_ ጨረታው ተከፍቶ ካለቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል እንደማይችሉ የሚያመለክት መግለጫ
_ ጨረታውን ለማዛባት ስለመሞከርና በተጫራቹ ላይ ስለሚያስከትለው ጉዳት
_ ስለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና ሰለየመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና
_ ስለጨረታው ማቅረያ ጊዜ፣የሚያበቃበትንና የሚከፈትበትን ጊዜና ሰዓት እንዲሁም የአቀራረብ ሁኔታና
_ ተጫራቹ ስለማጭበርበርና ሙስና/ጉቦ መስጠትንና መቀበልነ ጭምር በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆኑን በማረጋገጥ ግዴታ በመግባት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘወን ቅጽ መፈረም እንዳለበትና
እንደግዢው ዓይነት ሌሎች ሁኔታዎችን የሚያካትት ይሆናል

-የአገልግሎት ዝርዝር/Survice Description/

-የጨረታ ሃሳብ ማቅረቢያና የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ/BOQ/

-የውል ቃሎችና ሁኔታዎች/Contract terms and Conditions/

በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሌላው ሊካተት የሚገባውና በሰነዱ ውስጥ አንድ ክፍል ሆኖ መቅረብ ያለበት ነገር የውል ቃላትና የውል ሁኔታዎች ዝርዝር ነው፡፡ ይኽውም የስራውን ስፋት፣ መሰጠት የሚገባቸው አገልግሎቶችን፣ የአሰሪውና የሥራ ተቋራጩን መብትና ግዴታዎች ዝርዝር፣ የሥራ ተቆጣጣሪው/አማካሪው መሃንዲስ የስራ ድርሻዎች፣ ባለሞያዎች አሟልቶ ስለመስራት፣ የፕሮጀክት መሪ ባለሞያ  ተግባርና ሃላፊነቶችና የመሳሰሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች የሚይዝ ሲሆን ከውሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች በተጨማሪ ከሚሰጠው አገልግሎት የተለየ ባህሪ ጋር የሚሄዱ ልዩ ሁኔታዎችን እና ሥራው የሚከናወንበትን ቦታ የሚያመለክቱ ዝርዝር መረጃችን መያዝ አለበት፡፡
የውል ቃላት የተለያዩ በሰነዱ ውስጥ አገልግሎት ላይ የዋሉ ቃላትን በውል ሰነዱ አተረጓጎም ወቅት ሊኖራቸው

-ጨረታ ይፋ የማድረግ ፣ የመገምገም ፣ አሸናፊውን የመለየት ሥራዎች

-የጨረታ አሸናፊ ጥሪ ስለማድረግና ውል  ስለመዋዋል /Award of Contract and contracing/

ii. የግንባታ ሥራ ክንዋኔዎች ደረጃ ከጅማሬ እስከ ፍጻሜ/construction Stages/

በዚህ ክፍል ዋና ዋና የክንውን ጊዜያት ሶስት ናቸው።

* የዝግጅት ጊዜ/Period of Mobilization/

* የግንባታ ዋና ሂደት ጊዜ/Period of Main Construction Activities/

* የጥገናና የዕድሳት /Defects liability Period/

iii. የግንባታ ሥራ ፍጻሜና ርክክብ /Commissioning and Acceptance/
---------------------------------------------------
ለወደፊት እያንዳንዱን በዝርዝር የምናይ ይሆናል።
---------------------------------------------------
በ FaceBook መረጃ እንዲደርሶ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ ለጓደኛዎም ያጋሩ።

https://www.facebook.com/etconp/
👍21❤2