Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የኮንስትራክሽን ዋስትና (Construction security)]

🌟ክፍል ሶስት

▶️በኮንስትራክሽን ውል አፈጻጸም ወቅት በርካታ የዋስትና ዓይነቶች ሲተገበሩ ይታያል፡፡ ከቅድመ ግንባታ ጀምሮ በግንባታ ወቅት አንዳንዴም ከግንባታ በኋላ ለሚከሰቱ ችግሮች ዋስትና ጥቅም ላይ ሲውል ይሰተዋላል፡፡

በተለይም የህንጻ አሰሪዎች (Clients) ግንባታው በፈለጉት ጊዜና ዕቅድ መሰረት እንዲካናወንላቸው ካላቸው ጽኑ ፍላጎት የተነሳ ውሉ እንዲፈጸምላቸው አሰፈላጊ ከለላ እንዲኖራቸው ይሻሉ፡፡

በኢትዮጵያም አብዛኛው የኮንስትራክሽን ውሎች መንግስት አሰሪ በመሆን የሚቀርብባቸው ናቸው፡፡

ለማሳያ ያህል የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ፣ የኢንዲስትሪ ፓርኮች ግንባታ፣ የባቡር ዝርጋታ፣ የመንገድ ግንባታዎች ወዘተ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በተለምዶው የመንግስት ኪስ እርጥብ (solvent) ነው ቢባልም በውል አስተዳደር ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች የክፍያ መዘግየት ይስተዋላል በዚህ ጊዜም ሥራ ተቋራጩ ልክ እንደ አሰሪው ሁሉ ግዴታ አለተፈጸመልኝም ብሎ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል፡፡

በመርህ ደረጃ አሰሪ ሆኖ የቀረበው የመንግስት መስሪያ ቤት ውል ባለመፈጸሙ ምክንያት ሼል ተቋራጩ ውል አልተፈጸም በሚል መከራከሪያ ሊያቀርብ እንደማይችል ከፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 3177 ድንጋጌ እና ከተለመደው የላቲን አባባል፡- ‘Exceptio non adimpleti contractus’ (ግዴታ አለተፈጸመልኝምን እንደ መከራከሪያ አለማቅረብ) áˆ˜áˆ¨á‹łá‰ľ ይቻላል፡፡

ታዲያ ከላይ ያሉት ስጋቶች የሚከሰቱ ከሆነ፣ አሰሪውም ሆነ ሥራ ተቋራጮች ሁነኛ የሚሉትን የኮንስትራክሽን ዋስትና ሊጠቀሙ ይገባል፡፡
በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የታወቁ የዋስትና ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነዚህም የዉል ማስከበሪያ፣ የጨረታ ማስከበሪያ፣ የቅድሚያ ክፍያ፣ የዋናው ገንዘብ መያዣ እና የጥገና/ብልሽት ዋስትናዎች ናቸው፡፡ 

🌟የውል ማስከበሪያ ዋስትና (Contract security/ Performance Bond) 

⏺የውል ማስከበሪያ ዋስትና (contract security) ወይም የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና (performance security bond) የሚባለው አንድም ግራ ቀኙ ለገቡት ውል መልካም አፈጻጸም ሲባል በአንድ ሦስተኛ ወገን የሚሰጥ ዋስትና ነው፡፡
አብዛኛውን ጊዜም ሥራ ተቋራጮች ለፕሮጀክት ባለቤቶች ወይም ንዑስ ተቋራጮች ለዋናው ሥራ ተቋራጭ ውል ለመፈጸም ብለው ከአንድ የፋይናንስ ተቋም ወይም ሌላ ሦስተኛ ወገን አማካኝነት የሚቀርብ ዋስትና ነው፡፡
ሆኖም ግን ቀደም ሲል እንደተገለጸው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ተፈጻሚ የሚሆነው ዋናው ባለዕዳ(ለምሳሌ፡-ሥራ ተቋራጭ) ግዴታውን ባይወጣ ነው::

“ከመንግስት አስተዳደር መ/ቤት ጋር የሥራ ውል ያደረገ ወገን እንደውሉ መፈጸም ባልቻለ ጊዜ የአስተዳደር መ/ቤቱ ተዋዋዩ የውል ማስከበሪያ (contract security) በሚል ካስያዘው ገንዘብ ላይ ውል ባለመፈጸሙ የደረሰበትን የጉዳት ኪሣራ መቀነስ ይችላል፡፡ ”

በፌደራል የመንግስት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁ.649/2001 አንቀጽ 47 ላይ በግልጽ እንደተመለከው በተለይም የመንግስት ግንባታ ውሎች ላይ አቅራቢ (ውል ተቀባይ) ሆኖ የሚቀርብ ወገን ግዴታውን ባለመፈጸሙ ምክንያት በውል ሰጪው መንግስት መ/ቤት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ማካካሻ የሚሆን የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

መጠኑን በተመለከተም የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡ እኤአ በ ሰኔ ወር 2010 የወጣው የገ/ኢ/ል/ሚ መመሪያ አንቀጽ 16.25 ላይ እንደተመለከው አሸናፊው ሥራ ተቋራጭ ጨረታውን አሸንፎ ውል በተዋዋለ በ 15 ቀናት ውስጥ ቢያንስ የውሉን 10በመቶ እንደ ውል ማስከበሪያ(Performance security) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

የዋስትናው መክፈያ መንገድም በመመሪያው አንቀጽ 16.16.4 በተመለከተው መሰረት በተጫራቹ ምርጫ በጥሬ ገንዘብ ፣ በቼክ፣ የባንክ ዋስትና ሰነድ ፣ ክሬዲ ወይም በቅድመ ሁኔታ በሚዘገጅ የመድን ቦንድ ሊሆን ይችላል፡፡

በተጨማሪም መመሪያው በአንቀጽ 16.25.3 ላይ ውል ሰጪው የመንግስት መ/ቤት አቅራቢው (ሥራ ተቋራጩ) በውሉ በተቀመጠው መሰረት ግዴታውን መወጣት ካልቻለ የያዘውን ውል ማስከበሪያ ገንዘብ እንደነገሩ ሁኔታ መጠቀም ወይም መውረስ ይችላል፡፡

እንዲሁም ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር ሥራ ተቋራጩ ውሉን በተወጣ ጊዜ ያስያዘው ገንዘብ ይመለስለታል፡፡ /የመመሪያው አንቀጽ 16.25.7 ይመለከተዋል፡፡ /

ሲጠቃለልም የውል ማስከበሪያ ዋስትና ስለፕሮጀክቱ መልካም አፈጻጸም ውል ተቀባዩ ከአንድ ከሌላ ሦስተኛ ወገን ጋር በሚደርገው ግንኙነት ሊቋቋም ይችላል፡፡

🌟በቀጣይ ክፍል

💫ስለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond)

https://youtube.com/@Etconp432
👍12👏7❤3🎉1
👉የግንባታ ሥራዎች ሂደት ደረጃዎች/Stages in Construction/

🌟የግንባታ ሥራዎች የሂደት ደረጃዎች በዋናነት በሶስት የሚከፈሉ ሲሆን እነዚህም:

⏺i. የቅድመ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/Preconstruction Stages/

⏺ii. የግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/construction Stages/

⏺iii. የድህረ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ//Postconstruction Stages/

▶️i. የቅድመ ግንባታ ክንዋኔዎች ደረጃ/Preconstruction Stages/

🚧1.የፕሮጀክት ተፈጻሚነትና አዋጭነት ጥናት/Inception and Physibility study/

✨ይህ ደረጃ አሰሪው ወይም ኢንቬስተሩ ያለመውን ነገር ወይም ፍላጎቱን ወደእውነታ ለማምጣት የመጀመሪያ ሥራው የታሰበውን ፕሮጀክት የተፈጻሚነትና አዋጭነት ጥናት ውጤት ማወቅ ነው፡፡

✨በዚህ ጊዜ የተላያዩ ባለሞያዎችን የሚይዝ ቡድን፡-

⏺የታሰበውን ስራ እውን ሊሆን የሚችል መሆኑንና አለመሆኑን በማስረጃ ያረጋግጣል ለፕሮጀክቱ አዋጭነት ወሳኝ የቦታ መረጣ ያካሂዳል ፕሮጀክቱ በታሰበበት አካባቢ ከገንዘብ ሃብት ውጭ ያሉ የፕሮጀክት ሃብቶች አቅርቦት ሁኔታ፣ የዋጋ ሁኔታና እንደታሰበው ፕሮጀክቶች ዓይነት ሌሎች ሁኔታዎችን ያጠናል፡፡
የፕሮጀክቱን አዋጭነት ስሌት ዘገባ ይዘጋጃል፣ የሥራውን አጠቃላይ ሁኔታ ሊያሳይ የሚችል ሀሳባዊ ረቂቅ ንድፍ ያዘጋጃል፡፡ 

🚧2.የአፈር አካላት ሳይንስ ጥናት /Geotechnical Investigations/

⏺የአፈር አካላት ሳይንስ ጥናት፡-

▶️አጠቃላይ የግንባታ ሥራው የሚከናወንበትን ወይም ግንባታው የሚያርፍበትንና በዙሪያው ያለውን አካባቢ ሊያካልል የሚችል ፤የመሬቱ የመሸከም አቅም፣ ችግርሮችና የመፍትሄ ሃሳቦች የሚጠናበት ነው፡፡

🚧3.የመሬት አቀማመጥ አጠቃላይ ሁኔታ የሰርቬይንግ መረጃ ይሰበሰባል፡፡

🚧4.የዕቅድና የንድፍ ሥራ /Planning and Design stage/

⏺የአፈር ሳይንስ ጥናት መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ቀጣዩ ሥራ የሚሆነው የዕቅድና የዲዛይን ማጠቃለያ ሥራዎች የሚከናወኑበት ነው፡፡በዚህም፡
እንደፕሮጀክቱ ሁኔታ የአርክቴክቸራል፣ስትራክቸራል፣ ኤሌክትሪካል፣የኤሌክሮ ሜካኒካልና የሳኒተሪ የመሳሰሉት የዲዛይንና የንድፍ ሥራዎች ይሰራሉ፡፡

🚧5.የፕሮጀክት ሥራ አመራር መዋቅር ዝግጅትና ዕቅድ

🚧6.የገንዘብ ሀብት ዝግጅት ዕቅድ

🚧7.የታሰበው ፕሮጀክት እንደፕሮጀክቱ ግዝፈትና ሊሰራ ለታሰበበት ደረጃ የሚመጥን፤ ለሥራው ጥራት ደረጃ ዕቅድ
የግንባታ ዕቃዎች ዓይነት ምርጫና የጥራት ልክ ዕቅድየሥራ ተቋራጭ ብቃት ደረጃ ዕቅድና የመሳሰሉት ይሰራሉ፡፡

🚧8.የጨረታ ሥራዎች /Tendering stage/

💫በዚህ ደረጃ የሚከተሉት ስራዎች ይከናወናሉ

▶️የጨረታ ሰነድ የማዘጋጃት ሥራ/Bidding Document Preparation/፡-

⏺በጨረታ ሰነድ ዝግጅት የጨረታ ሼል ባለሞያዎች በጨረታ ሰነዱ ሊያካትቷቸው  የሚገቡ ጉዳዮች እንደሚከተለው ይሆናሉ፡፡

⏹የጨረታ ጥሪ/Bid Invitation /
በቂ ለሆነ ጊዜና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች የጨረታ ጥሪ ይፋ መደረጉ የሚረጋገጥበት ሲሆን የጨረታ ጥሪ አድራጊውን አካል ስምና አድራሻ፣የግነባታ ሥራው ዓይነትና የሚከናወንበትን ቦታ፣ሥራውን ለመስራት የሚፈለገው ተቋራጭ የመወዳደር ችሎታ ዝርዝር መመዘኛዎች፣ሥራው ስለሚፈጀው ጠቅላላ ጊዜ፣የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት አኳሆንና የሚገኝበት ቦታ፣ሰነዱን ለማግኘት ስለሚያስፈልግ ክፍያ መጠን፣የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ሰለሚያበቃበት ቀን፣ የተጫራቾች ዜግነት፣ በጨረታው ለመሳተፍ ቅድሚያ ሊከፈል ወይም ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid security) የሚያዝ ገንዘብ ካለ መጠኑና፣ እነደአስፈላጊነቱ ሌሎች ዝዝር መረጃዎችን የሚይዝ ይሆናል፡፡

⏹የተጫራቾች መመሪያ/instraction to bidders/

በተጫራቾች መመሪያ ዝርዝር፡-
_የጨረታ መገምገሚያ ዘዴዎችና የመገምገሚያ መስፈርቾች/Evaluation Methods and Criteria/
_ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ምን ምን ሊያካትት እንደሚገባው የሚገልጽ ዝርዝር
_ የአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚገባቸው መሆኑን
_ ለዘመኑ የታደሱ የተለያዩ ለመጫረት ብቁ የሚያደርጉ ምዝገባዎች ማቅረብ አስፈላጊ ስለመሆኑ
_ ለመንግስት የሚገባውን ግብር ከፍሎ ማረጋገጫ ያለው ስለመሆኑ (Tax Clearance)
_ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈር እንደሚገባቸው
_ ጨረታው ተከፍቶ ካለቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል እንደማይችሉ የሚያመለክት መግለጫ
_ ጨረታውን ለማዛባት ስለመሞከርና በተጫራቹ ላይ ስለሚያስከትለው ጉዳት
_ ስለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና ሰለየመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና
_ ስለጨረታው ማቅረያ ጊዜ፣የሚያበቃበትንና የሚከፈትበትን ጊዜና ሰዓት እንዲሁም የአቀራረብ ሁኔታና
_ ተጫራቹ ስለማጭበርበርና ሙስና/ጉቦ መስጠትንና መቀበልነ ጭምር በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆኑን በማረጋገጥ ግዴታ በመግባት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘወን ቅጽ መፈረም እንዳለበትና
እንደግዢው ዓይነት ሌሎች ሁኔታዎችን የሚያካትት ይሆናል

-የአገልግሎት ዝርዝር/Survice Description/

-የጨረታ ሃሳብ ማቅረቢያና የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ/BOQ/

-የውል ቃሎችና ሁኔታዎች/Contract terms and Conditions/

በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሌላው ሊካተት የሚገባውና በሰነዱ ውስጥ አንድ ክፍል ሆኖ መቅረብ ያለበት ነገር የውል ቃላትና የውል ሁኔታዎች ዝርዝር ነው፡፡ ይኽውም የስራውን ስፋት፣ መሰጠት የሚገባቸው አገልግሎቶችን፣ የአሰሪውና የሥራ ተቋራጩን መብትና ግዴታዎች ዝርዝር፣ የሥራ ተቆጣጣሪው/አማካሪው መሃንዲስ የስራ ድርሻዎች፣ ባለሞያዎች አሟልቶ ስለመስራት፣ የፕሮጀክት መሪ ባለሞያ  ተግባርና ሃላፊነቶችና የመሳሰሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች የሚይዝ ሲሆን ከውሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች በተጨማሪ ከሚሰጠው አገልግሎት የተለየ ባህሪ ጋር የሚሄዱ ልዩ ሁኔታዎችን እና ሥራው የሚከናወንበትን ቦታ የሚያመለክቱ ዝርዝር መረጃችን መያዝ አለበት፡፡
የውል ቃላት የተለያዩ በሰነዱ ውስጥ አገልግሎት ላይ የዋሉ ቃላትን በውል ሰነዱ አተረጓጎም ወቅት ሊኖራቸው

-ጨረታ ይፋ የማድረግ ፣ የመገምገም ፣ አሸናፊውን የመለየት ሥራዎች

-የጨረታ አሸናፊ ጥሪ ስለማድረግና ውል  ስለመዋዋል /Award of Contract and contracing/

ii. የግንባታ ሥራ ክንዋኔዎች ደረጃ ከጅማሬ እስከ ፍጻሜ/construction Stages/

በዚህ ክፍል ዋና ዋና የክንውን ጊዜያት ሶስት ናቸው።

* የዝግጅት ጊዜ/Period of Mobilization/

* የግንባታ ዋና ሂደት ጊዜ/Period of Main Construction Activities/

* የጥገናና የዕድሳት /Defects liability Period/

iii. የግንባታ ሥራ ፍጻሜና ርክክብ /Commissioning and Acceptance/
---------------------------------------------------
ለወደፊት እያንዳንዱን በዝርዝር የምናይ ይሆናል።
---------------------------------------------------
በ FaceBook መረጃ እንዲደርሶ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ ለጓደኛዎም ያጋሩ።

https://www.facebook.com/etconp/
👍21❤2
👉የኮንስትራክሽን ዋስትና

🌟ክፍል አራት

💫የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond)

⏺የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለት ጨረታ ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ለምሳሌ ሥራ ተቋራጩ በአሸነፈው መሰረት ውሉ ቢሰጠው ግዴታውን ስለመፈጸሙ የሚያቀርበው ዋስትና ነው፡፡

⏺በሌላ አባባል ይህ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ ለአሰሪው ጨረታውን በማሸነፉ ወደ ውሉ እገባለሁ ሲል የሚገባው የዋስትና ግዴታ ነው፡፡

⏺ይህም ጉዳይ በመንግስት ግዥ አዋጅ ላይ በአንቀጽ 40 በስፋት ተመልክቷል፡፡ የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያሰሩት ግንባታ በሚያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡

⏺ይህም መያዣ ተጫራቹ ጨረታው አየር ላይ እያለ ከውድድሩ ከወጣ ወይም ከአሸነፈ በኋላ ውሉን ለመፈጸም ፈቃደኛ ካልሆነ የጨረታ መያዣ ገንዘቡ ሊወረስ ይችላል፡፡

⏺በሌላ አባባል የጨረታ ማስከበሪያ በሚል የሚያዝ ገንዘብ ጨረታውን ባዘጋጀው አካል ሊወሰድ የሚችለው ተወዳዳሪው ጨረታውን ባሸነፈው መጠን ሆኖ በጨረታው መሠረት  መፈጸም ካልቻለ ወይም አስቀድሞ ከወጣ ነው::

⏺የጨረታ ዋስትና መጠኑን በተመለከተም እኤአ በ2010ዓ.ም በወጣው የገ/ኢ/ል/ሚ የግዥ መመሪያ አንቀጽ 16.16.2 ላይ እንደተገለጸው የጨረታ ዋስትና የውሉን አጠቃላይ ግምት ወስጥ 0.5 (ግማሽ) እሰከ 2(ሁለት) ፐርሰንት ሊደርስ ይችላል፡፡

⏺ነገር ግን የተባለው የመንግስት መ/ቤት የጨረታ ዋስትናውን መጠን በሚወስንበት ጊዜ ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺ) ብር መብለጥ የለበትም፡፡

⏺የጨረታው አካሄድ ሚዛናዊ እንዲሆን መመሪያው እንደሚለው የመንግስት የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ለማከናወን የሚወጣ ጨረታ ቢያንስ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡

▶️1ኛ በግዥ የሚሰራው ሥራ የዋጋ አስተማማኝነት ግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል፡፡

▶️2ኛ በጨረታው በቂ ቁጥር ያላቸው ተጫራቾች እንዲኖሩ ግድ ይላል፡፡

⏺የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘቡ ተጫራቾችን እንዳይሳተፋ አስቀድሞ የሚከለክል መሆን የለበትም፡፡

▶️3ኛ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘቡ አጫራቹ የመንግስት መ/ቤት በጨረታው አሸናፊ የሆነው ተጫራች ጨረታውን ባለመፈጸሙ ምክንያት ሊደርስበት የሚችልን ጉዳት መሸፈን ይኖርበታል፡፡

🙏ለወዳጆ ያጋሩ❤️

https://youtube.com/@Etconp432
👍13
👉የኮንስትራክሽን ዋስትና

🌟ክፍል አምስት

🚧የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና (Advance Payment Guarantee) 

⏺የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሲባል ሥራ ተቋራጩ ጨረታውን አሸንፎ ውል ተፈርሞ ወደ ሥራው ሊገባ ሲል የፕሮጀክቱ ባለቤት ለሥራ ተቋራጩ የተወሰነ የቅድሚያ ገንዘብ በመስጠቱ ምክንያት ሥራ ተቋራጩ በአንጻሩ ለወሰደው ገንዝብ የሚያቀርበው ዋስትና ነው፡፡

⏺በመሰረቱ በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ጅማሮ የቅድሚያ ክፍያ መኖር በአንድ በኩል ሥራ ተቋራጩ ያለምንም የገንዘብ ችግር ለሥራው የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች መግዣ ይሆነዋል፡፡ ወይም ደግሞ ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ከፍሎ ለንዑስ ተቋራጮች በሚሰጥበት ጊዜ እንደ ሥራ ማስጀመሪያ (mobilization commission) ይሆናቸዋል፡፡

⏺ስለ ቅድሚያ ክፍያ አስፈላጊነት ታዋቂው የኮንስትራክሽን ክሌም ጸሀፊ ጆን ስካይስ እ.ኤ.አ 1999 በወጣው መጽሀፋቸው እንዳብራሩት ቅድሚያ ክፍያ መኖር ለሥራ ተቋራጮች ከመጥቀሙ ባሻገር የጨረታ ወጥ መለኪያ (tender standardization) ተድርጎ ስለሚወሰድ ጭምር ነው፡፡

⏺የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና መኖረን አስመልክቶ የመንግስት ግዥ አዋጅ ቁ.649/2001 በአንቀጽ 48 እንደተመለከተው የቅድመ ክፍያ ሊፈጸም የሚችለው ሥራ ተቋራጩ በቅድሚያ ክፍያ መልክ ከሚወስደው ገንዘብ መጠን ጋር እኩል የሆነ ዋስትና ሲያቀርብ እንደሆነ ይናገራል፡፡

⏺የመንግስት የኮንስትራክሽን ውሎችን የቅድሚያ ክፍያ መጠንን በተመለከተ እኤአ በ2010 የወጣው የገ/ኢ/ል/ሚ የግዥ መመሪያ አንቀጽ 16.26 ላይ የቅድመ ክፍያ መጠን የውሉን 30(ሰላሣ) ፐርሰንት መብለጥ የለበትም፡፡

⏺ሆኖም ግን በአገር በቀል የሥራ ተቋራጮች የሚሰራ የመንገድ ግንባታ ሲሆን ግን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ እስከ 50(ሃምሳ) ፐርሰንት ይደርሳል፡፡ ዝርዝር ሁኔታው በእያንዳንዱ ጨረታ ይገለጻል፡፡

⏺በሥራ ተቋራጩ የሚቀርበው የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናው መጠን የተከፈለውን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ጋር እኩል መሆን አለበት፡፡

⏺የዋትናው አቀራረብም በቼክ፣ ያል ቅደመ ሁኔታ የሚቀርብ የባንክ ዋስትና ወይም በቅድመ ሁኔታ የሚዘጋጅ የመድን ዋስትና ሊሆን ይችላል፡፡

⏺ሌላው የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ ለምን ዓላማ መዋል እንደለበትና በምን አግባብ ሊሰጥ እንደሚችል መመሪያው በአንቀጽ 16.26.7 ተመልክቶታል፡፡

▶️በተለይም የመንገድ እና ህንጻ ግንባታ የሚሰሩ ሥራ ተቋራጮች በቅድሚያ ክፍያው ገንዘብ ስለሚገዙት የማሽነሪ ዝርዝር በመመሪያው አባሪ 4 መሰረት በተዘረዘረው ብቻ ይሆናል::

🙏ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ❤️

https://www.facebook.com/etconp/
👍14👏1
👉A new 12-story, 54-room hotel scheduled to open in Cape Town, South Africa, is being hailed as the world’s tallest building made with industrial hemp. As such, it promises views of Cape Town’s massive Table Mountain and a “minimal ecological footprint,” according to a report by Agence France-Presse (AFP) published in May.

🚧The appropriately named Hemp Hotel consists of “hempcrete” blocks made from woody parts of hemp plants and supported by a cement-and-concrete structure. The hempcrete lends insulating and fireproof properties to the building.

🌟According to the National Ready Mixed Concrete Association, each pound of concrete releases 0.93 pounds of carbon dioxide. In addition, building materials are responsible for 11 percent of global carbon emissions.

@etconp
👍3💯1
2023 -07-05 Trainees Selection Criteria.docx
16.7 KB
ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት!

ጂ.አይ.ዜድ. ኢትዮጵያ ኢንተግሬሽን በሚባል ኩባንያ በኩል ከፍ ያለ ደረጃ ያለውና ለ 10 ቀናት የሚሰጥ የአመራር (Leadership) ሥልጠና ለመስጠት አቅዶ በዚህ ሥልጠና ላይ ለመካፈል ፍላጎቱ ያላቸውን በፆታቸው ሴት የሆኑና በአመራርነት እየሠሩ የሚገኙ ሠልጣኞችን መርጠን እንድልክለት ጠይቆናል፡፡

ለሥልጠናው ብቁ የሚሆኑ ሠልጣኞችን ለመምረጥ የሚስችል መሥፈርትም አዘጋጅቶ የላከልን በመሆኑ ይኽው መሥፈርት ከዚህ ማስታወሻ ጋር ተያይዞ እንዲደርሳችሁ ተደርጓል፡፡ ሥልጠናው የሚጀምረው እ.ኤ.አ. በኦገስት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ ሥልጠና ላይ ለመካፈል ፍላጎቱ ያላቸውና መሥፈርቱን የሚያሟሉ ሠልጣኞችን እስከ መጪው ረቡዕ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በዚሁ ገፅ ላይ እንድታሳውቁን እንጠይቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር

@etconp
👍5🙏2
👉የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ እና በኮንስትራክሽን ውል የስራ መጀመሪያ ቀን/Commencement date/.

በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ የስራ መጀመሪያ ቀን እና ውል የተደረገበት ቀን የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ይሄውም የሆነበት ውሉ በተደረገበት እለት የግንባታ ስራ ይጀመራል ተብሎ ስለማይታሰብ ነው፡፡

*በኮንስትራክሽን ውል የስራ መጀመሪያ ቀን/Commencement date/

በመርህ ደረጃ የውል የግንባታ ስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ነው፡፡ ስለዚህ የውሉ የግንባታ ጊዜ ተብሎ የሚጠቀሰውን ቀን ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ መቁጠር ስህተት ነው፡፡ ETCONp

ምክንያቱም የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ መካከል ከተፈረመ በኋላ የግንባታው ተጨባጭ ስራ በተለያየ ምክንያት ሊዘገይ ይችላል፡፡ለምሳሌ ግንባታው የሚከናወንበት ቦታ የይገባኛል ጭቅጭቅ ቢነሳበት ጭቅጭቁ እስኪፈታ ድረስ አሰሪው የግንባታውን ሳይት ለተቋራጩ ማስረከብ ያልቻለ እንደሆነ ግንባታው ችግሩ እስከሚፈታ ድረስ ሳይጀመር መቆየቱ የማይቀር ይሆናል፡፡

*ለተቋራጩ የሳይት ርክክብ/site handover/

ለግንባታ የተወሰነው ቦታ ከጥያቄ ነጻ ከሆነና አሰሪው ሙሉ ባለይዞታ ለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ፤ ውል ላዋዋለው ሥራ ተቋራጭ የሥራ ቦታውን ያስረክባል ወይም የሳይት ርክክብ ያደርጋሉ ማለት ነው፡፡ ETCONp

ይህ ከሆነ በኋላ አሰሪው ሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራውን የሚጀምርበትን ቀን
- በርክክብ ወቅት በቃለ ጉባዔ ይወስናል፡፡
- ወይም አስቀድሞ በውሉ ልዩ ሁኔታዎች(Special condition of contract) ላይ በተቀመጠው ቀን እንደሆነ ታውቆ በተባለው ቀን ሥራ ይጀመራለረ ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ሥራ ተቋራጩ ሳይት ሳይረከብ የግንባታው ጅማሬ ቀን ሊቆጠር አይችልም ማለት ነው፡፡
ሳይት ርክክብ ከተደረገ በኋላ እንደፕሮጀክቱ ዓይነት ወይም መጠን ስፋት የሞቢላይዜሽን ቀን ተጨምሮ ዋና የግንባታ ሥራ ማስጀመሪያው ቀን ይወሰናል፡፡ ስለዚህ ተቋራጩ የግንባታ ቁሳቁስ እና የሰው ሀይል ሞቢላይዝ እስከሚያደርግበት ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ የስራ መጀመሪያ ቀን ሊጀምርበት አይገባም፡፡

በዚህ ረገድ በተግባር አልፎ አልፎ ስህተት ሲሰራ ይስተዋላል፡፡ይሄውም አሰሪዎች አንዳንዴ የግንባታውን ጊዜ ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምረው በመቁጠር እና ተቋራጩን በቂ ምክንያት ካለህ የጊዜ ማራዘሚያ/Time extension/ ጠይቅ የሚሉበት የተሳሳተ ሁኔታና አጋጣሚ አለ፡፡

በዚህ ረገድ በሀገራችን እና በአለም ሀገራት እየተሰራባቸው ያሉ የዳበሩ የፊዲክ ጀኔራል ኮንዲሽኖች እና በሀገራችን ተጣጥመው የተቀረጹ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ምን ይዘት አላቸው የሚለውን እና የፍትሀብሄር ህግ ድንጋጌዎችን ደግሞ ቀጥለን እንዳስሳለን፡፡

1. FIDIC RED BOOK 1999

በፊዲክ ሬድ ቡክ 1999 ቨርሽን ክሎስ 8.1 ላይ ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ስራ እንዲጀምር ማስታወቅ እንዳለበት እና ከ7 ቀን ያላነሰ ጊዜ መስጠት እንደሚገባው ይጠቅሳል፡፡ ETCONp

እንደዚሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በልዩ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር የስራ መጀመሪያው ቀን/ Commencement date/ ተቋራጩ በጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ42 ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበት ተቀምጧል፡፡

በተጨማሪም ተቋራጩ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ወዲያውኑ እና ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡ተቋራጩ/contractor/ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ይቅርታ ሊያሰጥ የሚችል ምክንያት ሳይኖረው ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት በክሎስ ላይ የተቀመጠውን ግዴታውን ያልተወጣ እንደሆነ ደግሞ አሰሪው/client/ውሉን ለማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 15.2(c) ላይ ተቀምጧል ETCONp

2. FIDIC 1987

በኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ፎር ወርክስ ኦፍ ሲቪል ኢንጅነረንግ ኮንስትራክሽን ፊዲክ 1987 ቨርሽን ክሎስ 41.1 ላይ ስለ ኮመንስመንት ዴት/የስራ መጀመሪያ ቀን ተቀምጧል፡፡ይዘቱም መሀንዲሱ የስራ መጀመሪያውን ቀን በጨረታ ሰነዱ አፔንዴክስ ላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት የሚገልጽ ነው፡፡ተቋራጩም የስራ መጀመሪያው ቀን በመሀንዲሱ ከተገለጸለት በኋላ ያለመዘግየት እና በተቻለ ፍጥነት የግንባታ ስራውን መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡

የግንባታ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቆጠር የሚጀምረውም ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ስለመሆኑ ክሎስ 43.1 ላይ ተቀምጧል፡፡

እንግዲህ ተቋራጩ በቂ ምክንያት ሳይኖረው በክሎስ 41.1 ላይ በተመለከተው አግባብ የግንባታ ስራውን ሳይጀምር የቀረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ለማቋረጥ እና ተቋራጩን ከሳይት ለማስወጣት መብት/expel right/ እንዳለው ክሎስ 63.1 ያስቀምጣል፡፡

3. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር  አቋም/MoWUD 1994

ይህ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ1994 ስራ ላይ አውሎት የነበረው የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/MoWUD 1994 በተለይ ከፊዲክ/FIDIC 1987 ቨርሽን የተወሰደ ሲሆን ስለኮመንስመንት ዴት በሁለቱም ጀኔራል ኮንዲሽኖች ላይ ተመሳሳይ ይዘት ባለው ሁኔታ ያስቀምጣሉ፡፡
ስለዚህ ማብራሪያውን መድገም አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም፡፡

4. የመንግስት ግዢዎች ኤጀንሲ/PPA 2011

በፒፒኤ 2011 ቨርሽን ክሎስ 71 ላይ የስራ መጀመሪያ ቀን በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ላይ ሊቀመጥ እንደሚችል ወይም ደግሞ በአስተዳደራዊ መንገድ በኢንጅኒየሩ በሚሰጥ ትእዛዝ ሊታወቅ እንደሚችል ይጠቅሳል፡፡ ETCONp

እንዲሁም በሌላ ሁኔታ በውሉ ላይ ካልተገለጸ በስተቀር ለተቋራጩ የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለጸ ቀን ጀምሮ ታስቦ ከ120 ቀናት ለማለፍ አይችልም፡፡

5-የፍትሀብሄር ህግ

የስራ ማከናወኛ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610 - 2637) በሚመለከት በውሉ ላይ የጊዜ ጉዳይ በግልጽ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ተቋራጩ ወዲያውኑ ስራ መጀመር እንደሚኖርበት በአንቀጽ 2619 ላይ ተደንግጓል፡፡የግንባታ ጊዜ በተገለጸባቸው ውሎች ደግሞ ስራ ተቋራጩ ስራውን ወዲያው ያልጀመረ እንደሆነ እና በጊዜ ገደቡ የግንባታ ስራውን ለመፈጸም የማይችል መሆኑ የታወቀ እንደሆነ አሰሪው ለተቋራጩ ስራውን የሚጀምርበትን ጊዜ ሊወስንለት እንደሚችል በአንቀጽ 2618 ላይ ተቀምጧል፡፡ ETCONp

ሌላው እነዚህ ደንቦች ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ስራ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3019-3040) በሚመለከተው የግል የስራ ተቋራጭነት ውል ላይ ጭምር ተፈጻሚነት እንደሚኖራቸው ከአንቀጽ 3019(2) ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡

የአስተዳደር መስሪያ ቤት የኮንስትራክሽን ውል ማለትም የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3244 እና ተከታዮቹ) በሚመለከት እያንዳንዱ ተዋዋይ ወገን ግዴታዎቹን በውሉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡

በውሉ ላይ ግልጽ የጊዜ ስምምነት የሌለ እንደሆነ ደግሞ ግዴታው በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ መፈጸም እንደሚኖርበት በአንቀጽ 3174 ላይ ተቀምጧል፡፡

ይህ ድንጋጌ ስለአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጠቅላላው የተደነገገ ሲሆን የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውልን በሚመለከተው ልዩ ክፍል ላይም በግልጽ ስለስራ ጊዜ ተደንግጓል፡፡

https://youtube.com/@Etconp432
👍10❤2👏2
ይሄውም በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የግንባታ ስራዎቹ በሙሉ የሚከናወኑበት ጠቅላላው ጊዜ ብቻ ተጠቅሶ እንደሆነ አሰሪው መስሪያ ቤት/client/ የግንባታ ስራው የሚጀመርበትን ጊዜ/ Commencement date/ ዘርዝሮ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3253(2) ላይ ተደንግጓል፡፡

#ConstructionLaw

@etconp

https://youtube.com/@Etconp432
👍1🏆1
👉የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/

🌟የኮንስትራክሽን ውል ስምምነት/contract agreement በአሰሪ/client እና በተቋራጭ/contractor መካከል የሚፈረምበት ቀን የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

🚧እዚህ ላይ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020 ድንጋጌ እና አንድ ውል ተቋቋመ ሊባል የሚችለው መቸ ነው? የሚለው ማለትም የውል አቀራረብ/offer እና አቀባበል/acceptance በሚመለከት በፍትሀብሄር ህጉ 1681 እና ተከታዮቹ የተደነገገው እና የውል ፎርም ጉዳይ ከግምት ውስጥ መግባት ጭምር አለበት፡፡ ETCONp

🚧የግል የኮንስትራክሽን ውል ጉዳዮችን በሚመለከተው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ አሰሪና ተቋራጭ ስለሚሰራው ስራ እና ስለዋጋው ካልተስማሙ በስተቀር የተቋራጭነት ውል አለ እንደማይባል ተደንግጓል፡፡

🌟ሌላው ከአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎችን በሚመለከት ስለውሎች በጠቅላላው የተደነገገው ጭምር ተፈጸሚነት እንዳለው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3131(1) ይደነግጋል፡፡ ETCONp

🚧የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጽሁፍ መደረግ እንዳለባቸው በፍትሀብሄር ህግ ስለውሎች በጠቅላላው በሚደነግገው ክፍል በአንቀጽ 1724 ላይ ተደንግጓል፡፡

🚧የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2005(1) ላይ እንደተደነገገው ደግሞ የጽሁፍ ሰነድ በላዩ ላይ የተጻፈውን ቀን በሚመለከት በተፈራራሚዎች መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ነው ይላል፡፡

🌟እንግዲህ ውል የተደረገበት ቀን በአሰሪና ተቋራጭ መካከል የውል ግንኙነት መቋቋሙን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡

🚧ውል ደግሞ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ በተዋዋዮች መካከል እንደህግ እንደሚቆጠር የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731(1) ይደነግጋል፡፡

🌟ሆኖም ግን ውሉ የተደረገበት ቀን የውሉ የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን ተደርጐ ሊወሰድ አይገባም፡፡

❤️ከወደዱት ከታች ያለውን ሊንክ ለሌሎች ያጋሩ🙏

https://www.facebook.com/etconp/
👏8👍2
👉ለባከነ የግንባታ ጊዜ ''የጊዜ የጉዳት መቀጫ''/Liquidated damage/

🌟በኮንስትራክሽን ውል ላይ የውሉ የግንባታ ስራ ተብሎ የተቀመጠውን በዲዛይኑ እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽኑ መሰረት በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሰርቶ ማጠናቀቅ የተቋራጩ ሀላፊነት ነው፡፡

🌟ተቋራጩ የውሉን የግናባታ ስራ በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በወቅቱ ሰርቶ ያላጠናቀቀ እንደሆነ ከውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ/completion date/ በኋላ ግንባታው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ለእያንዳንዱ ቀን ተቋራጩ የግንባታ መዘግየት ምክንያት ለአሰሪው የጊዜ የጉዳት መቀጫ/Liquidated damage/ የመክፈል ሀላፊነት ይኖርበታል፡፡

🚧በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሲባል ምን ማለት ነው?

▶️አንዳንድ አሰሪዎች/client/ በግንዛቤ እጥረት በውሉ ላይ የተቀመጠው ተቋራጩና አሰሪው ለግናባታው ማጠናቀቂያ የተስማሙበትን የቀን ብዛት/የጊዜ እርዝማኔ/ መቆጠር የሚጀምረው ውሉ በግራ ቀኙ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ ይረዱታል፡፡ይሄ አረዳድ ስህተት ነው፡፡

🚧በኮንስትራክሽን ውል ስለ ጊዜ አቆጣጠር በተለይ

⏺የግንባታ ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ፣
⏺ሞቢላይዜሽን ፔሬድ/mobilization period/፣
⏺የሳይት መረከቢያ ቀን/site handover/፣
⏺የስራ መጀመሪያ ቀን/commencement date/ እና
⏺የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ የሚሉትን መረዳት የግንባታ የጊዜ የጉዳት መቀጫ/Liquidated damage/ የሚለውን በአግባቡ ለማወቅ ይጠቅማል፡፡

🚧በመሰረቱ በውሉ የተቀመጠው የስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ተቋራጩ የግናባታውን ሳይት ከአሰሪው ከተረከበ በኋላ ነው፡፡ይሄውም ከሳይት ርክክብ በኋላ የስራ መጀመሪያ ቀን /commencement date/ በመሀንዲሱ የሚወሰን እና ለተቋራጩ የሚገለጽለት ይሆናል፡፡

🚧እንግዲህ  በመሀንዲሱ ከሚወሰነው የስራ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ በውሉ ላይ የተቀመጠው ቀን ይቆጠርና የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቼ እንደሆነ ለማወቅ ያስችላል ማለት ነው፡፡ ETCONp

🚧እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነገር በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ ውል ሊደረግ የሚችልበት እድልም አለ፡፡/Partial completion/ ማለት ነው፡፡የቀን አቆጣጠሩ ከላይ እንደተብራራው የሚሰላ ይሆናል፡፡

🚧ስለሆነም የግንባታ መዘግየት ቅጣት የሚለው ጉዳይ የሚመጣው ተቋራጩ የውሉን የግንባታ ስራ በውሉ ስራ የማጠናቀቂያ ጊዜ /completion date/ ሳያጠናቅቅ የቀረ እንደሆነ ነው፡፡የገንዘብ ቅጣቱ የሚጣለው በተቋራጩ ላይ ነው፡፡ተቋራጩ ግንባታውን ላዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን በውሉ የተቀመጠውን የጊዜ ኪሳራ መቀጫየሚከፍል ይሆናል፡፡

🚧በነገራችን ላይ እየተቀጡ መስራት ለተቋራጩ መብትም ጭምር ነው፡፡ይህ ማለት አሰሪው የውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ ስላለቀ ውል አቋርጣለሁ ማለት አይችልም፡፡ ETCONp

🚧በውሉ ላይ የተቀመጠው የመዘግየት ቅጣት ጣሪያ መጠን ከሞላ በኋላ ግን አሰሪው ውል ማቋረጥ ይችላል ውል ከተቋረጠ በኋላ የመዘግየት ቅጣት የሚባል ነገርም የለም፡፡

🚧ሌላው ተቋራጩ ወደ መዘግየት ቅጣት እንዲገባ ከመደረጉ አስቀድሞ በአግባቡ መረጋገጥ ያለበት ነገር መሀንዲሱ ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ/Extension of Time / ፈቅዷል ወይስ አልፈቀደም የሚለው ነጥብ ነው፡፡ምክንያቱም ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ ተፈቅዶለት ከሆነ የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜውም አብሮ ስለሚራዘምና ቀኑ ስለሚቀየር ነው፡፡

🚧የሀገራችንን የህግ ማእቀፍ በዚህ ረገድ ምን ይላል? የሚለውን ለመመለስ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1887 እስከ 1895 ድረስ የተደነገጉትን መዳሰስ ይጠይቃል፡፡

🚧በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1889 ላይ ተዋዋዮች በውላቸው ምናልባት አንደኛው ወገን እንደውሉ ግዴታውን ያልፈጸመ እንደሆነ ወይም አጓድሎ የፈጸመ እንደሆነ ወይም አዘግይቶ የፈጸመ እንደሆነ የሚከፍለውን የመቀጮ መጠን አስቀድመው በውላቸው ለመወሰን እንደሚችሉ በሚፈቅድ መልኩ ተደንግጓል፡፡

🌟እዚህ ላይ የውል ግዴታን አዘግይቶ መፈጸም ስለሚያስከትለው ቅጣት የሚዋዋሉት በተለይ የግንባታ ጊዜ የጉዳት መቀጫ/liquidated damage/ የሚመለከት ይሆናል፡፡

✨የመዘግየት ቅጣት ስምምነት ባለ ጊዜ አሰሪው የውሉ ስራ እንዲፈጸምና የቅጣት ገንዘቡንም ለመቀበል መብት እንደሚኖረው የፍ/ህ/ቁ 1890(2) ይደነግጋል፡፡ ETCONp

🚧እንደዚሁም አሰሪው ኪሳራ ባይደርስበት እንኳ የመዘግየት ቅጣት ገንዘቡ ሊከፈለው እንደሚገባ የፍ/ህ/ቁ 1892(1) ይደነግጋል፡፡

🚧እንግዲህ ተቋራጩ ግንባታውን በወቅቱ ያላጠናቀቀው አሰሪውን ሆነ ብሎ ለመጉዳት አስቦ ጉልህ በሆነ ቸልተኝነት ወይም በከባድ ጥፋት መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ አሰሪው በውሉ ከተቀመጠው የቅጣት ገንዘብ በላይ በደረሰበት ትክክለኛ ጉዳት መጠን ልክ ከተቋራጩ ላይ ኪሳራ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 1892(2) ይደነግጋል፡፡

🚧ሌላው የመዘግየት ቅጣት መጠን በዳኞች ሊቀነስ የሚችልበት እድል ስለመኖሩ የፍ/ህ/ቁ 1893 ይደነግጋል ይሄውም ተቋራጩ ግዴታውን በከፊል የፈጸመ ሆኖ ሲገኝ ነው ይህ ማለት ተቋራጩ ባከናወነው ስራ ሁሉ ቅጣት የሚጣልበት አይሆንም ማለት ነው፡፡

🚧በዚህ ረገድ በሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ አንቀጽ 47(1) ላይ ተቋራጩ ስራውን በውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ ካላጠናቀቀ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን የውሉን ዋጋ 1/1000 እንደሚከፍል እና ይሄውም አጠቃላይ መጠኑ ከውሉ ዋጋ ከ (10-20%)መብለጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡

🚧ሆኖም ግን በከፊል ለተከናወነው ስራ መሀንዲሱ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በሰጠ ጊዜ የቅጣቱ መጠን የሚሰላው ባልተከናወነው ስራ መጠን ዋጋ ላይ በመመስረት ይሆናል ማለት ነው፡፡

🌟በመጨረሻም የመዘግየት ቅጣት በኛ ሀገር ከላይ እንዳየነው እንደቅጣት የሚቆጠርና በህጉ ቅጣቱ እውቅና የሚሰጠው ሲሆን በኮመን ሎው የህግ ስርአት ግን ቅጣት አይደለም፡፡በኮመን ሎው የጊዜ የጉዳት መቀጫ በአሰሪው ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን የሚኖርበት ሲሆን የቅጣት አይነት ተመሳሳይ ባህሪ ካለው ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

❤️ከወደዱት ሊንኩን ለሌሎች ያጋሩ🙏

https://youtube.com/@Etconp432
👍22❤5
ክፍያ ምሥክር ወረቀት/payment certificate/

1. ቅድመ ክፍያ(Advance Payment Certificate)

• ከ 20% እስከ 30% ባለው ወሰን ውስጥ እንደ አሠሪው ፍላጎት ለሥራ ማስጀመሪያ የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡

• ለዚህ ክፍያ ተቋራጭ ተመጣጣኝ በሁኔታ ላይ ያልመሠረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል፡፡

• አንዳንድ አሠሪዎች ተቋራጫቸው የባንክ ዋስትናውን መስያዝ የሚሳነው ሆኖ ከተገኘ፤ ዋስትናውን በሁኔታ ላይ የተመሠረተ ዋስትና ተአማኒነት ካለው ኢንሹራንስ ድርጅት እንዲያሲዝ ፈቅደው፤ ገንዘቡ በጋራ በተከፈተ ሂሣብ(አሠሪና ተቋራጭ) እንዲቀመሥ ተደርጎ በጋራ ፊርማ እንዲወጣ ያደርጋሉ፡፡

• የቅድሚያ ክፍያው ለሚሠራ ሥራ ከሚዘጋጅ ተከታታይ ክፍያዎች በሂደት ተቀንሶ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

2. ጊዜያዊ ክፍያ (Interim Payment Certificate)

• ለተሠራ ሥራ በየወቅቱ የሚዘጋጅና በአማካሪው ተረጋግጦ የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡

• ይህ ክፍያ ስሙም እንደሚያመለክተው ጊዜአዊና ወደፊት የሚወራረድ ሂሣብ ነው፡፡

• አንድ ክፍያ ሲፈጸም የሂሣብ ስህተት ቢያጋጥም የሚቀጥለው ላይ ለማስተካክል የሚያስችል መንገድ አለው፡፡

3. የመጨረሻ ክፍያ (Final Payment)

• በሕጉ የአንድ ፕሮጀክት ክፍያ የሚባለው የመጨረሻ ክፍያ ነው፡፡

• በዚህ ግዜ አማካሪው ከመጀመሪያ ጀምሮ በተከታታይ የተፈጸመውን ጊዜአዊ ክፍያ ከመስክ በሚወስደው ስፍረ መሠረት አገናዝቦና መርምሮ የሚያጸድቀው ክፍያ ነው፡፡

• ክፍያው ከጸደቀ በኋላ ለመያዣ ከተያዘው ግማሹን ጨምሮ ለተቋራጩ እንዲከፈል ያዛል፡፡

• ግማሹ የመያዣ ገንዘብ ከአንድ ዓመት የዋስትና እና የጥገና ግዜ በኋላ የመጨረሻ ክፍያ ሲፈጸም ይለቀቃል፡፡ በዚህ ግዜ የፕሮጀክቱም ሂሣብ ይዘጋል ማለት ነው፡፡

• የመያዣ ገንዘብ ሚባለው በመንግስት ሥራ ግዢ ደንብ መሠረት የተሠራው ሥራ 5% ሲሆን ጊዜአዊ ርክክብ ከተፈተመ በኋላ እስከ መጨረሻ ርክክብ የሚቆየው እና በመጨረሻ የሚለቀቀው ግማሹ 2.5% ነው፡፡

በክፍያ አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ችግሮች

1. ወጥነት የሌለው የክፍያ መፈጸሚያ ምስክር ወረቀት ቅጽ
• ይህ ቅጽ በሐገር አቀፍ ደረጃ አንድ አይነት ቢሆን ተቋራጮች በሠሩበት ሁሉ አንድ አይነት ግንዛቤ ስለሚኖራቸው መደናገር አይኖርም፤ የሂሣብ ምርመራ ሥራንም ቢሆን ያቀላል፡፡
2. በባለቤት እና/ወይም አማካሪ ምክንያት የሚዘገይ ክፍያ
• የተቋራጩን የግዢ ዑደት ስለሚያሰናክል የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ይታወካል
• በጀት አጠቃቀም ላይ ችግር ይፈጥራል
• የሥራ ጥራት ያበላሻል
• ዋጋ ያንራል
➗➗➗➗➗➗➗➗
@etconp @etconp @etconp
👍12❤5
Construction_Projects_Delay_and_Their_Antidotes_The_Case_study_of.pdf
519.1 KB
🔖journal: Construction Projects Delay and Their Antidotes: The Case of Ethiopian Construction Sector

📝Zinabu Tebeje Zewdu, 2016Gc
@etconp
❤3👍2
👉በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው  ድልድዮች ተጠግነው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ፡፡

በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የሚገኙና በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ ሶስት ድልድዮች ተገቢው ጥገና ተደርጎላቸው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡ እነዚህ ሶስት ድልድዮች በአስተዳደር መስሪያ ቤቱ የድልድይ እና ስትራክቸር ሥራዎች ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት ጥገና ተደርጎላቸው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል፡፡
ከመቀሌ በ122 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው እና ከመቀሌ ወደ ሀውዜን ለመጓዝ የሚያስችለው የ አደሀ  ድልድይ በብረት ድልድይ ደረጃ ተሰርተው አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ድልድዮች መካከል አንዱ ነው፡፡ አጠቃላይ የድልድዩ ርዝመት 36.6 ሜትር ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት ጥገናው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
ከዚህም ባሻገር ከአላማጣ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው እና አላማጣን ከመሆኒ ጋር ለማገናኘት የሚያስችለው የአደገረብ ድልድይ በብረት ድልድይ ደረጃ ተሰርቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ አጠቃላይ የድልድዩ ርዝመትም 36.6 ሜትር ነው፡፡
በተጨማሪም ከሰቆጣ ከተማ በ33 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው እና የሰቆጣ ፣ ፃዳ እና ማይጨው አካባቢዎችን የሚያገናኘው 48 ሜትር ድልድይ በብረት ድልድይ ደረጃ ተጠግኖ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
ከዚህ ቀደም በአፋር ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ስድስት ድልድዮች ጥገና ተደርጎላቸው  አገልግሎት መስጠት ስለመጀመራቸው መዘገባችን ይታወሳል።
እነዚህ ድልድዮችም ከወልዲያ ወደ ቆቦ የሚያሻግረው 109.73 ሜትር የአልወሃ ድልድይ ፣ ከሚሌ-ጭፍራ-ወልዲያ የሚያሻግረው  48 ነጥብ 86 የሚረዝመው የጨረቲ ድልድይ  ፣  ሁመል እና ሽሬን የሚያገናኘው  27. 43 ሜትር  የተከዜ 3 ድልድይ ፣ ከቆቦ የገጠር አካባቢዎችጋር የሚያገናኘው 48 ነጥብ 86 የጎቡ ድልድይ ፣  ከአምደወርቅ ወደ እብናት በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘው  48 ነጥብ 86  የተከዜ ድልድይ እና  ከኮረም ወደ ሰቆጣ የሚወስደው  42 ነጥብ 67 ሜትር  የጽላሬ ድልድይ ናቸው፡፡

@etconp
👍6👏4
Common window types: Which is your favourite?
via: 07sketches
@etconp
❤2
Good News : ሁለተኛ ዙር የሠራተኞች የመኖሪያ መንደር ግንባታ ፕሮጀክትን ለማስጀመር ከኮንትራክተር ጋር የፊርማ ስነስርዓት ተደረገ፡፡

ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች ቁጥር 2 የመኖሪያ መንደር ግንባታ ፕሮጀክት (2nd Phase Housing Project) የሚዉል የመሬት ይዞታ በህጋዊ መንገድ ርክክብ ተደርጎ ይዞታዉን አጥር ከማጠር ጀምሮ ቅድመ ሁኔታዎች ተጠናቅቀዉ ግንባታ ለማስጀመር  በዝግጅት ላይ መሆኑን በቅርቡ ያሳወቅናችሁ መሆኑ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሰረት 5000 ሠራተኞችን የመኖሪያ እድል ተጠቃሚ የሚያደርገዉ ሁለተኛዉ ዙር የሠራተኞች የመኖሪያ መንደር ግንባታ ፕሮጀክትን ለማስጀመር በዛሬዉ እለት በቀን ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድርጅታችን የኢትየጵያ አየር መንገድ ግሩፕ   ከ C.C.C.C.እና ከሰንሻይን ቢዝነስ ግሩፕ  ጋር የፊርማ ስነስርዓት ተፈራረመ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ይህ የሠራተኞች ቁጥር 2 የመኖሪያ መንደር ግንባታ ፕሮጀክት እንዲጀመር ከሁለተኛ ዙር መኖሪያ ቤቶች ሱፐርቫይዘሪ ቦርዱ (2nd Phase Housing Supervisory board) ጋር በመሆን የበኩሉን ሚና የተጫወተ ሲሆን አሁንም ፕሮጀክቱ በፍጥነት ተጠናቅቆ የሠራተኛዉን የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲፈታ ለማስቻል የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ እየገለጽን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለዚህ ፕሮጀክት ስኬታማነት የሚጠበቅበትን ሃላፊነቶች ሁሉ እንዲወጣ በድጋሚ እንጠይቃለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር የዚህ ፕሮጀክት ጅማሮ እዉን እንዲሆን ያለሰለሰ ጥረት ላደረጉ የድርጅታችን ከፍተኛ አመራር አካላት እና የሱፐርቫይዘሪ ቦርዱ አባላት ምስጋናዉን ያቀርባል፡፡


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር!!!
👍9❤1
🌟የ ፕሮግራም ጥቆማ

👉ዛሬ ቅዳሜ በ 01/11/2015ዓ.ም ከ ምሽቱ 2:00 እስከ 3:00 ድረስ በህንፃ አዋጅ ደንብና መመሪያ በተለይ ሰለ ግንባታ ፈቃድ፣የፕላን ስምምነት፣የመጠቀም ፈቃድ፣ግንባታ ስለ ማስቆም፣ስለጎረቤት ህንፃ እና ተያያዥ ጉዳዮች በአማራ ቴሌቪዥን ምክረ ህግ ፕሮግራም የህግ ባለሙያዎች: ፍስሀ ሲሳይነው፣ጉባዔ አሰፋ እና በቃሉ ሞላ ይጠብቋቹዋል ተከታተሉት።

#ConstructionLaw

@etconp
🙏6👍4❤2
ዛሬ ዘለግ ያለ ፅሁፍ ይዘን ተከስተናል

ለትውልድ የሚተላለፉ የግንባታ ተቋራጮችን የማፍራት ግብ

በአንተነህ ቸሬ

የሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዘርፍ ችግሮች ጠቅለል ተደርገው ሲገለፁ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና ዋጋና እንዲሁም በሚፈለገው ጥራት አለማጠናቀቅ በሚለው ክፍተት ላይ የሚያርፉ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልፃሉ። በተለይ የሀገር ውስጥ ተቋራጮች ከዚህ አኳያ ከፍተኛ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አስተዳደር (ማነጅመንት) ችግር እንዳለባቸው ይጠቆማል። የሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የአቅም ክፍተቶች ይስተዋሉበታል፤ ዓለም አቀፍ የገበያ ተለዋዋጭነት፤ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች መማር አለመቻል፣ ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡

የዘርፉን ችግሮች በጥናትና ምርምር በመታገዝ የመፍታትና የግንባታ አስተዳደር የማሳደግ ኃላፊነት የተሰጠው የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩትም Construction Management Institute) ይህን ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚኝ ከ<<አዲስ ዘመን>> ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬከተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ ያስረዳሉ፡፡

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ምንነት
<<ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት>> ማለት አንድን ግንባታ በጊዜ፣ በዋጋ እና በጥራት መመራት፣ ወይም ግንባታን ጊዜውንና ጥራቱን ጠብቆ በተያዘለት ጊዜና የውል ዋጋ ማጠናቀቅ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ግብ ፕሮጀክቶችን በዋጋ፣ በጊዜና በጥራት ማጠናቀቅ ነው፡፡

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ተግባራትና ኃላፊነቶች
የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በደንብ ቁጥር 289/2005 የተቋቋመ ተቋም ነው። የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትን ማሳደግን ግብ ካደረጉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዋና ኃላፊነቶችና ተግባራት መካከል የፖሊሲ ግብዓቶችን በማመንጨት እንዲተገበሩ ማድረግ፣ ተግባር ተኮር የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ሥልጠናዎችን መስጠት፣ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ዓለም አቀፋዊ ብቃት ያላቸው እንዲሆኑ የሚያደርግ የምዘናና የብቃት ማረጋገጫ (ሰርቲፊኬሽን) እንዲኖር ማመቻቸት፣ ለኮንስትራክሽን ማኔጅመንት እድነት የሚረዱ ቴክኖሎጂዎች እንዲስፋፋና እንዲሰርፁ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል።

ተቋራጭ፤ አሰሪ እና አማካሪ በተደራጀ መልኩ የሚሠሩበትን የአሠራር ሥርዓት እያጠኑ አንዲተገበር ማድረግ በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ዘርፍ የማማከር አገልግሎት መስጠት፣ በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ዘርፍ ጥናትና ምርምር ማድረግ፤ ለኮንስትራክሽን እድገት አስተዋፅዎ የሚያደርጉ መረጃዎችን እያሰባሰቡና እየመዘኑ ለዘርፉ ግብዓት እንዲሆኑ ማድረግ፤ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚስተዋውቁና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያተኮሩ ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን መስጠት፣ ተመሳሳይ ተግባር ካላቸው የግልና የመንግሥት ተቋማት በትብብር መሥራት፣ ምርጥ ተሞክሮዎች እንዲቀምሩ ማድረግ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ለኮንስትራክሽን ማኔጅመንት እድገት አስፈላጊ የሆኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን የማከናወንና ተቋማቱ የጥናትና ምርምር ማዕከላት እንዲሆኑ ማገዝ የሚሉትም የኢንስቲትዩቱ ሌሎች ኃላፊነቶቹና ተግባሮቹ ናቸው። ETCONp

ኢንስቲትዩቱ በሰንዳፋ ከተማ የልህቀት ማዕከል እያስነባ ነው:: ማዕከሉ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ትልቅ ተቋም ስለሚሆን ማዕከሉን ማስተዳደር በተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት ውስጥ ይካተታል። የልኀቀት ማዕከሉ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የሰው ኃይል ማበልፀጊያ ተቋም ነው። ማዕከሉ ግንባታዎች ሳይፈርሱ የግንባታ ጥራትን ለመፈተሽና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ አሠራሮችና መሣሪያዎች (Non Destructive Testing Methods) እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ ተግባራት የሚከናወኑባቸው የቤተ-ሙከራ ማዕከላት ይኖሩታል።

የማዕከሉ ግንባታ በሁለት ምዕራፎች የሚከናወን ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በሦስት ዓመታት፣ ቀሪውን ደግሞ በሁለት ዓመታት በማከናወን ማዕከሉ ከአምስት ዓመታት በኋላ በሙሉ አቅም ሥራ እንዲጀምር ይደረጋል፡፡ የግንባታው 17 በመቶ ሥራ በ2016 ዓ.ም ይጠናቃል ተብሎ ታቅዷል። ከዚህ በተጨማሪም፣ ተዘጋጅቶ ለመንግሥት የቀረበው የተቋሙ የደንብ ማሻሻያ፣ ኢንስቲትዩቱ የምዘናና የብቃት ማረጋገጫ ሥራውን ከማመቻቸት ባለፈ በራሱ የምዘናና የብቃት ማረጋገጫ ሥራ እንዲያከናውን ይጠይቃል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የበጀት ዓመቱ ዋና ዋና ተግባራት
ኢንስቲትዩቱ በዘንድሮው የበጀት ዓመት በኢንዱስትሪው ውስጥ በሥራ ላይ ለሚገኙ 2442 ተቋራጮች፣ አማካሪ መሐንዲሶች ሌሎች የዘርፉ ተቋማት ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ይህ ሥልጠና የፕሮጀከት ማኔጅመንት አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ የሚያግዝ ነው። ETCONp

የምንመድባቸው አሠልጣኞች በዘርፉ በቂ ልምድና ዝግጅት ያላቸው ናቸው፡፡ ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከ20ሺ በላይ ለሚሆኑ ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን ሰጥቷል፡፡

ለ180 ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ (Project Management Professionals) እንዲሆኑ የሚያስችላቸውንና ዓለም አቀፍ ሰርተፊኬት እንዲያገኙ ዕድል የሚፈጥርላቸውን ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ባለፈው ዓመት ይህ ሥልጠና ለ120 ባለሙያዎች ተሰጥቶ ነበር፡፡

ኢንስቲትዩቱ በ2015 የበጀት ዓመት ያከናወነው ሌላ ተግባር የ<ቢም> (Building information Modeling) ቴክኖሎጂ ስልጠና ነው፡፡ ይህ ቴከኖሎጂ የዲዛይን ሥራዎችን በማስተባበር የጊዜና የገንዘብ ብክነት እንዳይኖር የሚያደርግ ነው፡፡ በተለያዩ ባለሙያዎች የሚሠሩ የዲዛይን ዝግጅት ሥራዎች የተናበቡ እንዲሆኑ ለማድረግ ቁልፍ ሚና ያለው ቴከኖሎጂ ነው፡፡ ዘንድሮ 243 ባለሙያዎች ሥልጠናውን ወስደዋል፤ ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከ4ዐዐ በላይ ባለሙያዎችን በ<ቢም> ቴክኖሎጂ አሰልጥኗል፡፡ አማካሪ መሐንዲሶችን ጨምሮ የዘርፉ መንግሥታዊ ተቋማት ባለሙያዎችና የዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ሥልጠናውን ወስደዋል፡፡ ቴክኖሎጂው የተበላሸውን የኢንዱስትሪውን ገፅታ ለመገንባት እና ሥራን በእውቀት ለመምራት ከፍተኛ ጥቅም አለው፡፡

የኮንስትራክሽን ዘርፉ እየተመራ ያለው ባለሙያዎች ተመዝነው ብቃታቸው በምዘና ተረጋግጦ ስላልሆነ የብቃት ምዘና መመሪያ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ መመሪያው ሲጸድቅ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ባለሙያዎች በጥንቃቄ በሚዘጋጅ የፈተና ሥርዓት አማካኝነት ብቃታቸው ይመዘናል ለፈተናው የሚያግዙ ግብዓቶችም እየተዘጋጁ ነው፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለማዘመን የሚያግዙ የአሠራር ሥርዓቶችንም ያስተዋውቃል። ለአብነት ያህል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና ሃሳቦችን ይዘው የሚቀቡ ተወዳዳሪዎችን የሚያበረታቱ እንዲሁም የሥራ ቅብብሎሽ እንዲኖር የሚያስችሉ አሠራሮች የሚመሩባቸውን መመሪያዎችን አዘጋጅቷል።

ኢንስቲትዩቱ ከሰባት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር አንድ ባለሙያ ከረዳቶቹ ጋር ሆኖ በቀን ምን ያህል ሥራ መሥራት እንደሚቻል የሚያመለክት የምርታማነት መለኪያ (Productivity Norm) እያዘጋጀ ነው። ኢንስቲትዩቱ የምክር አገልግሎቶችንም ይሰጣል፡፡ በቂ ባለሙያ ለሌላቸው ተቋማት የሙያ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ለብዙ ተቋማት ሥራዎች ሙሉ የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎችን አከናውኗል።
👍5
የተቋማት ፐሮጀክት የመምራት ደረጃን (Organizational Project Maturity) የማሳደግ ሥራ በዚህ ዓመት የተከናወነ ሌላው ተግባር ነው፡፡ ይህ አሠራር በዓለም አቀፍ መመዘኛ አምሰት ደረጃዎች አሉት። ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ (በተቋማት ፕሮጀክት የመምራት ደረጃ) የምትናኘው ከአንድ እስከ ሁለት ባለው ወሰን ውስጥ ነው፤ ይህም አነሰተኛ የሚባል ነው:: ይህን ደረጃ በ10 ዓመት ውስጥ ወደ አምስት/ አራት ለማድረስ የታቀደ ሲሆን፤ በአምስት ዓመታት ውስጥ ወደ ሦስት ለማድረስ እየተሠራ ነው። ለዚህ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ተዘጋጅተው የአሠልጣኞች ሥልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡ ከተቋማት ኃላፊዎች ጋር ምክከር ተደርጓል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የመሠረተ ልማት ቅንጅት እጦት እያስከተለ ያለውን ችግር በማጥናት በመሠረት ልማት ዝርጋታ ላይ ከተማሩ ተቋማት ጋር ውይይት አድርጓል ለዚህ ችግር መፍትሄ የሚሆን ቴክኖሎጂንና አማራጭ የግንባታ ግብዓቶችን (ለምሳሌ ከአፈር የሚሠሩ ብሎኬቶችን) አስተዋውቋል፡፡ ተቀባይነት ያገኙት ቴክኖሎጂዎችና አሠራሮች ደግሞ ብሔራዊ ደረጃ (National Standard) እንዲወጣላቸው እየሠራ ነው፡፡ የ<ቢም> ቴክኖሎጂ አስገዳጅ ብሔራዊ ደረጃ እንዲኖረው የሚያስችሉ ግብዓቶች ተሟልተው ደረጃው ለሚኒስትሮች ኮሚቴ ቀርቧል በቅርቡ ይፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

የሀገር በቀል ተቋራጮች አቅምና ችግሮች ETCONp

የሀገር በቀል ተቋራጮች ከዚህ ቀደም በጥሩ እድግት እየተጓዙ የነበረ ቢሆንም መልሰው ተዳከመዋል፡፡ የእውቀትና የአደረጃጀት ችግሮት አሉባቸው። በአሁኑ ሰዓት ተወዳዳሪ መሆን አልቻሉም። ለዚህ ችግር ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል አንዱ ተቋማቱ በኮርፖሬት ደረጃ የተደራጁ አለመሆናቸው ነው። ለምሳሌ አንድ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት በአንድ ግለሰብ ስም ተሰይሞ፣ ግለሰቡ ሁሉንም ኃላፊነት ይዞ ሥራ ይጀምራል፡፡ ግለሰቡ በሆነ ምክንያት ሥራውን ሲያቆም ድርጅቱም አብሮ ይከስማል፡፡ ተቋማቱ የአንድ ሰው ተቋማት ሳይሆኑ የኮርፖሬት አሠራር ሊኖራቸው ይገባል። ሰውየው ኖረም አልኖረም ተቋማቱ እንዲቀጥሉ የእውቀት ሥራ መሥራት ይገባል፡፡

የኮርፖሬት አሠራር ስልት (Corporate Culture) አንድ ተቋም በአንድ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን ሥርዓት ባለው አሠራር (System) ሥራውን እንዲያከናውን የሚያስችል ነው፡፡ ይህ ስልት ዝርዝር የአሠራር ሥርዓቶችን በመዘርጋትና ውሳኔዎች በተገቢው ጊዜ እንዲወሰኑ በማስቻል፤ የፕሮጀክት አፈፃፀም ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆን ያደርጋል።

ክፍያዎች በተገቢው ጊዜ አለመከፈላቸው ተቋራጮቹን አዳክሟቸዋል፡፡ ሥራ ለማግኘት ሲባል ብቻ አዋጭ ያልሆነ (በጣም ዝቅተኛ) ዋጋ ያቀርባሉ። ገበያን በሚገባ አጥንቶ ለፐሮጀክት የሚመጥን ዋጋ ያለማቅረብ ችግር አለ፡፡ ይህ ደግሞ ሥራው እንዳይሠራና ሀገርም ኪሳራ እንዲገጥማት ያደርጋል፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ጎድቶታል።

ስለሆነም <<ተቋራጮቹ ለሥራው የሚመጥን ዋጋ አስገብተዋል ወይ?>> የሚለውን ጉዳይ በጥንቃቄ መመልከት ይገባል፡፡ የግዥ ሥርዓቱ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ እንዲያሸንፍ ዕድል የሚሰጥ (Least Evaluated Bid) ነው፡፡ ይህ የግዥ ሥርዓት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለብዙ ዓመታት የቆዩና ልምድ ያላቸው ተቋራጮች ከሥራ እንዲወጡ አድርጓቸዋል። ስለሆነም ተቋራጮቹ ለሥራው የሚመጥን ዋጋ አስገብተዋል ወይ? የሚለውን ጉዳይ በጥንቃቄ መመልከት እና የግዥ ሥርዓቱን ማስተካከል ያስፈልጋል።

የውጭ ሀገራት የሥራ ተቋራጮች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሥራ በሚጀምሩበት ጊዜ የሀገር ውስጥ ተቋራጮች ወሳኝ በሆኑ ሥራዎች ላይ እንዲያሳተፉ የሚያስችል አሠራር (Joint Venture System) ተዘጋጅቷል፡፡ በ10 ዓመት ውስጥ በሀገር ውስጥ ከሚወጡ ዓለም አቀፍ ጨረታዎች መካከል 75 በመቶው የሀገር ውስጥ ተቋራጮች የነበያ ድርሻ እንዲኖራቸው ታቅዷል።

ኢንጂነር ታምራት <የሀገር ውስጥ ተቋራጮች የአቅም ክፍተት አለባቸው፡፡ ክፍተቶቻቸውን ለማስተካከልም የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ለሥራ ተጽራጮች በብዙ ዘርፎች ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል። የኛ ሀገር የሥራ ተቋራጮቹ የ10 ዓመት ብቻ ታሪክ ባለቤት እየሆኑ ነው:: ለውልድ የሚተላለፉ ተቋራጮችን ማፍራት አለብን ብለን እየሠራን ነው ይላሉ፡፡

ከዚህ ቀደም የሥራ ተቋራጮችን አቅም ለመወሰን ተቋራጮቹ ያላቸውን ማሽኖችና ሌሎች መሳሪያዎችን ከግምት ውስጥ የማስገባት አሰራር ይተገበር ነበር። ነገር ግን አንድ ተቋራጭ እውቀቱ ካለው ማሽኖችን ተከራይቶ እንዲሠራ በማድረግ ተቋራጩ ያለውን አቅም ለሀገር ልማት መጠቀም ይቻላል። ብዙ አቅም ያላቸው ባለሙያዎች ማሽኖች ስላሌሏቸው ብቻ ለብዙ ዓመታት ተቀጣሪ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ስለሆነም እያንዳንዱ ተቋራጭ የሁሉም ማሽኖች ባለቤት ሊሆን እንደሚገባ የሚያስገድደው መስፈርት አስገዳጅ መሆን እንደሌለበት ስምምነት ላይ ተደርሷል። ያለውን ሀብት በአግባቡ የሚያስተዳድር የአሠራር ሥርዓት መፍጠርም አስፈላጊ ነው፡፡ ተቋራጮችን አቀናጅቶ ማሠራት በጣም ይጠቅማል። ትልቅ የአመለካከት ችግር አለ፡፡ የጥቅም ግጭትና ቅሬታ እንዳይፈጠርም የሚገኘውን ትርፍ ተቋራጮቹ በሥራው ላይ ባላቸው አበርክቶ መሠረት በማስላት መከፋፈል ይገባል።

<በባለሙያ እየተመሩ ያሉ ተቋማት አሉ፣ በባለሙያ የማይመሩ ተቋማትም አሉ፡፡ በአመዛኙ ግን የኮንስትራክሽን ዘርፉ በባለሙያ እየተመራ አይደለም> የሚሉት ኢንጂነር ታምራት፤ <አሠራራችንን ፐሮፌሽናሊዝምን የሚጋብዝ ከሆነ፣ አሳማኝ ያልሆነና ዘርፉን የሚጎዳ ዋጋ ይዘው የሚቀርቡ ተቋራጮችን ከጨዋታው ውጪ የምናደርግበት አሠራር ከተፈጠረ፣ የሚጠየቁት የምዘና መስፈርቶች የተቋማትን ብቃት መመዘን የሚያስችሉ ከሆኑ፣ ልምድ ያላቸው፤ በኢንዱስትሪው ላይ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ፣ ሀገርን ሊገነቡ የሚችሉ ከዝያ የወጡ ተቋራጮች ወደ ገበያው ሊመሰሱ ይችላሉ> በማለት ያስረዳሉ።

ቀጣይ እቅጾች
የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዘርፉን ለማሳደግ በቀጣዩ በጀት ዓመት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውንና ዓለም አቀፍ ሰርተፊኬት እንዲያገኙ ዕድል የሚፈጥርላቸውን ሥልጠና አጠናክሮ መቀጠል አንዱ ነው፡፡ በዚህም 180 ለሚሆኑ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ለሚመሩ ተቋማት ባለሙያዎች ይህ ሥልጠና ይሰጣል፡፡ ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ 200 ባለሙያዎች የ<ቢም> እና ለሦስት ሺ 8oo የዘርፉ ባለሙዎች የፕሮጀክት ማኔጅመነት ሥልጠናዎች የሚሰጥ ይሆናል። ለአንድ ሺ ባለሙያዎች የብቃት ምዘናና ማረጋገጥ ሥራ ለመሥራት አቅዷል፡፡ የልኅቀት ማዕከሉን 17 በመቶ ግንባታውን ማጠናቀቅም የኢንስቲትዩቱ የቀጣዩ ዓመት እቅድ ነው።

ምንጭ፡ አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 24 ቀን 2015

@etconp
👍14❤1🙏1
👍6❤2