Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ክፍያ ምሥክር ወረቀት/payment certificate/

1. ቅድመ ክፍያ(Advance Payment Certificate)

• ከ 20% እስከ 30% ባለው ወሰን ውስጥ እንደ አሠሪው ፍላጎት ለሥራ ማስጀመሪያ የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡

• ለዚህ ክፍያ ተቋራጭ ተመጣጣኝ በሁኔታ ላይ ያልመሠረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል፡፡

• አንዳንድ አሠሪዎች ተቋራጫቸው የባንክ ዋስትናውን መስያዝ የሚሳነው ሆኖ ከተገኘ፤ ዋስትናውን በሁኔታ ላይ የተመሠረተ ዋስትና ተአማኒነት ካለው ኢንሹራንስ ድርጅት እንዲያሲዝ ፈቅደው፤ ገንዘቡ በጋራ በተከፈተ ሂሣብ(አሠሪና ተቋራጭ) እንዲቀመሥ ተደርጎ በጋራ ፊርማ እንዲወጣ ያደርጋሉ፡፡

• የቅድሚያ ክፍያው ለሚሠራ ሥራ ከሚዘጋጅ ተከታታይ ክፍያዎች በሂደት ተቀንሶ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

2. ጊዜያዊ ክፍያ (Interim Payment Certificate)

• ለተሠራ ሥራ በየወቅቱ የሚዘጋጅና በአማካሪው ተረጋግጦ የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡

• ይህ ክፍያ ስሙም እንደሚያመለክተው ጊዜአዊና ወደፊት የሚወራረድ ሂሣብ ነው፡፡

• አንድ ክፍያ ሲፈጸም የሂሣብ ስህተት ቢያጋጥም የሚቀጥለው ላይ ለማስተካክል የሚያስችል መንገድ አለው፡፡

3. የመጨረሻ ክፍያ (Final Payment)

• በሕጉ የአንድ ፕሮጀክት ክፍያ የሚባለው የመጨረሻ ክፍያ ነው፡፡

• በዚህ ግዜ አማካሪው ከመጀመሪያ ጀምሮ በተከታታይ የተፈጸመውን ጊዜአዊ ክፍያ ከመስክ በሚወስደው ስፍረ መሠረት አገናዝቦና መርምሮ የሚያጸድቀው ክፍያ ነው፡፡

• ክፍያው ከጸደቀ በኋላ ለመያዣ ከተያዘው ግማሹን ጨምሮ ለተቋራጩ እንዲከፈል ያዛል፡፡

• ግማሹ የመያዣ ገንዘብ ከአንድ ዓመት የዋስትና እና የጥገና ግዜ በኋላ የመጨረሻ ክፍያ ሲፈጸም ይለቀቃል፡፡ በዚህ ግዜ የፕሮጀክቱም ሂሣብ ይዘጋል ማለት ነው፡፡

• የመያዣ ገንዘብ ሚባለው በመንግስት ሥራ ግዢ ደንብ መሠረት የተሠራው ሥራ 5% ሲሆን ጊዜአዊ ርክክብ ከተፈተመ በኋላ እስከ መጨረሻ ርክክብ የሚቆየው እና በመጨረሻ የሚለቀቀው ግማሹ 2.5% ነው፡፡

በክፍያ አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ችግሮች

1. ወጥነት የሌለው የክፍያ መፈጸሚያ ምስክር ወረቀት ቅጽ
• ይህ ቅጽ በሐገር አቀፍ ደረጃ አንድ አይነት ቢሆን ተቋራጮች በሠሩበት ሁሉ አንድ አይነት ግንዛቤ ስለሚኖራቸው መደናገር አይኖርም፤ የሂሣብ ምርመራ ሥራንም ቢሆን ያቀላል፡፡
2. በባለቤት እና/ወይም አማካሪ ምክንያት የሚዘገይ ክፍያ
• የተቋራጩን የግዢ ዑደት ስለሚያሰናክል የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ይታወካል
• በጀት አጠቃቀም ላይ ችግር ይፈጥራል
• የሥራ ጥራት ያበላሻል
• ዋጋ ያንራል
➗➗➗➗➗➗➗➗
@etconp @etconp @etconp
👍12❤5
Construction_Projects_Delay_and_Their_Antidotes_The_Case_study_of.pdf
519.1 KB
🔖journal: Construction Projects Delay and Their Antidotes: The Case of Ethiopian Construction Sector

📝Zinabu Tebeje Zewdu, 2016Gc
@etconp
❤3👍2
👉በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው  ድልድዮች ተጠግነው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ፡፡

በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የሚገኙና በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ ሶስት ድልድዮች ተገቢው ጥገና ተደርጎላቸው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡ እነዚህ ሶስት ድልድዮች በአስተዳደር መስሪያ ቤቱ የድልድይ እና ስትራክቸር ሥራዎች ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት ጥገና ተደርጎላቸው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል፡፡
ከመቀሌ በ122 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው እና ከመቀሌ ወደ ሀውዜን ለመጓዝ የሚያስችለው የ አደሀ  ድልድይ በብረት ድልድይ ደረጃ ተሰርተው አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ድልድዮች መካከል አንዱ ነው፡፡ አጠቃላይ የድልድዩ ርዝመት 36.6 ሜትር ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት ጥገናው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
ከዚህም ባሻገር ከአላማጣ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው እና አላማጣን ከመሆኒ ጋር ለማገናኘት የሚያስችለው የአደገረብ ድልድይ በብረት ድልድይ ደረጃ ተሰርቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ አጠቃላይ የድልድዩ ርዝመትም 36.6 ሜትር ነው፡፡
በተጨማሪም ከሰቆጣ ከተማ በ33 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው እና የሰቆጣ ፣ ፃዳ እና ማይጨው አካባቢዎችን የሚያገናኘው 48 ሜትር ድልድይ በብረት ድልድይ ደረጃ ተጠግኖ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
ከዚህ ቀደም በአፋር ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ስድስት ድልድዮች ጥገና ተደርጎላቸው  አገልግሎት መስጠት ስለመጀመራቸው መዘገባችን ይታወሳል።
እነዚህ ድልድዮችም ከወልዲያ ወደ ቆቦ የሚያሻግረው 109.73 ሜትር የአልወሃ ድልድይ ፣ ከሚሌ-ጭፍራ-ወልዲያ የሚያሻግረው  48 ነጥብ 86 የሚረዝመው የጨረቲ ድልድይ  ፣  ሁመል እና ሽሬን የሚያገናኘው  27. 43 ሜትር  የተከዜ 3 ድልድይ ፣ ከቆቦ የገጠር አካባቢዎችጋር የሚያገናኘው 48 ነጥብ 86 የጎቡ ድልድይ ፣  ከአምደወርቅ ወደ እብናት በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘው  48 ነጥብ 86  የተከዜ ድልድይ እና  ከኮረም ወደ ሰቆጣ የሚወስደው  42 ነጥብ 67 ሜትር  የጽላሬ ድልድይ ናቸው፡፡

@etconp
👍6👏4
Common window types: Which is your favourite?
via: 07sketches
@etconp
❤2
Good News : ሁለተኛ ዙር የሠራተኞች የመኖሪያ መንደር ግንባታ ፕሮጀክትን ለማስጀመር ከኮንትራክተር ጋር የፊርማ ስነስርዓት ተደረገ፡፡

ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች ቁጥር 2 የመኖሪያ መንደር ግንባታ ፕሮጀክት (2nd Phase Housing Project) የሚዉል የመሬት ይዞታ በህጋዊ መንገድ ርክክብ ተደርጎ ይዞታዉን አጥር ከማጠር ጀምሮ ቅድመ ሁኔታዎች ተጠናቅቀዉ ግንባታ ለማስጀመር  በዝግጅት ላይ መሆኑን በቅርቡ ያሳወቅናችሁ መሆኑ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሰረት 5000 ሠራተኞችን የመኖሪያ እድል ተጠቃሚ የሚያደርገዉ ሁለተኛዉ ዙር የሠራተኞች የመኖሪያ መንደር ግንባታ ፕሮጀክትን ለማስጀመር በዛሬዉ እለት በቀን ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድርጅታችን የኢትየጵያ አየር መንገድ ግሩፕ   ከ C.C.C.C.እና ከሰንሻይን ቢዝነስ ግሩፕ  ጋር የፊርማ ስነስርዓት ተፈራረመ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ይህ የሠራተኞች ቁጥር 2 የመኖሪያ መንደር ግንባታ ፕሮጀክት እንዲጀመር ከሁለተኛ ዙር መኖሪያ ቤቶች ሱፐርቫይዘሪ ቦርዱ (2nd Phase Housing Supervisory board) ጋር በመሆን የበኩሉን ሚና የተጫወተ ሲሆን አሁንም ፕሮጀክቱ በፍጥነት ተጠናቅቆ የሠራተኛዉን የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲፈታ ለማስቻል የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ እየገለጽን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለዚህ ፕሮጀክት ስኬታማነት የሚጠበቅበትን ሃላፊነቶች ሁሉ እንዲወጣ በድጋሚ እንጠይቃለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር የዚህ ፕሮጀክት ጅማሮ እዉን እንዲሆን ያለሰለሰ ጥረት ላደረጉ የድርጅታችን ከፍተኛ አመራር አካላት እና የሱፐርቫይዘሪ ቦርዱ አባላት ምስጋናዉን ያቀርባል፡፡


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር!!!
👍9❤1
🌟የ ፕሮግራም ጥቆማ

👉ዛሬ ቅዳሜ በ 01/11/2015ዓ.ም ከ ምሽቱ 2:00 እስከ 3:00 ድረስ በህንፃ አዋጅ ደንብና መመሪያ በተለይ ሰለ ግንባታ ፈቃድ፣የፕላን ስምምነት፣የመጠቀም ፈቃድ፣ግንባታ ስለ ማስቆም፣ስለጎረቤት ህንፃ እና ተያያዥ ጉዳዮች በአማራ ቴሌቪዥን ምክረ ህግ ፕሮግራም የህግ ባለሙያዎች: ፍስሀ ሲሳይነው፣ጉባዔ አሰፋ እና በቃሉ ሞላ ይጠብቋቹዋል ተከታተሉት።

#ConstructionLaw

@etconp
🙏6👍4❤2
ዛሬ ዘለግ ያለ ፅሁፍ ይዘን ተከስተናል

ለትውልድ የሚተላለፉ የግንባታ ተቋራጮችን የማፍራት ግብ

በአንተነህ ቸሬ

የሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዘርፍ ችግሮች ጠቅለል ተደርገው ሲገለፁ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና ዋጋና እንዲሁም በሚፈለገው ጥራት አለማጠናቀቅ በሚለው ክፍተት ላይ የሚያርፉ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልፃሉ። በተለይ የሀገር ውስጥ ተቋራጮች ከዚህ አኳያ ከፍተኛ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አስተዳደር (ማነጅመንት) ችግር እንዳለባቸው ይጠቆማል። የሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የአቅም ክፍተቶች ይስተዋሉበታል፤ ዓለም አቀፍ የገበያ ተለዋዋጭነት፤ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች መማር አለመቻል፣ ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡

የዘርፉን ችግሮች በጥናትና ምርምር በመታገዝ የመፍታትና የግንባታ አስተዳደር የማሳደግ ኃላፊነት የተሰጠው የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩትም Construction Management Institute) ይህን ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚኝ ከ<<አዲስ ዘመን>> ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬከተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ ያስረዳሉ፡፡

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ምንነት
<<ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት>> ማለት አንድን ግንባታ በጊዜ፣ በዋጋ እና በጥራት መመራት፣ ወይም ግንባታን ጊዜውንና ጥራቱን ጠብቆ በተያዘለት ጊዜና የውል ዋጋ ማጠናቀቅ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ግብ ፕሮጀክቶችን በዋጋ፣ በጊዜና በጥራት ማጠናቀቅ ነው፡፡

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ተግባራትና ኃላፊነቶች
የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በደንብ ቁጥር 289/2005 የተቋቋመ ተቋም ነው። የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትን ማሳደግን ግብ ካደረጉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዋና ኃላፊነቶችና ተግባራት መካከል የፖሊሲ ግብዓቶችን በማመንጨት እንዲተገበሩ ማድረግ፣ ተግባር ተኮር የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ሥልጠናዎችን መስጠት፣ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ዓለም አቀፋዊ ብቃት ያላቸው እንዲሆኑ የሚያደርግ የምዘናና የብቃት ማረጋገጫ (ሰርቲፊኬሽን) እንዲኖር ማመቻቸት፣ ለኮንስትራክሽን ማኔጅመንት እድነት የሚረዱ ቴክኖሎጂዎች እንዲስፋፋና እንዲሰርፁ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል።

ተቋራጭ፤ አሰሪ እና አማካሪ በተደራጀ መልኩ የሚሠሩበትን የአሠራር ሥርዓት እያጠኑ አንዲተገበር ማድረግ በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ዘርፍ የማማከር አገልግሎት መስጠት፣ በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ዘርፍ ጥናትና ምርምር ማድረግ፤ ለኮንስትራክሽን እድገት አስተዋፅዎ የሚያደርጉ መረጃዎችን እያሰባሰቡና እየመዘኑ ለዘርፉ ግብዓት እንዲሆኑ ማድረግ፤ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚስተዋውቁና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያተኮሩ ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን መስጠት፣ ተመሳሳይ ተግባር ካላቸው የግልና የመንግሥት ተቋማት በትብብር መሥራት፣ ምርጥ ተሞክሮዎች እንዲቀምሩ ማድረግ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ለኮንስትራክሽን ማኔጅመንት እድገት አስፈላጊ የሆኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን የማከናወንና ተቋማቱ የጥናትና ምርምር ማዕከላት እንዲሆኑ ማገዝ የሚሉትም የኢንስቲትዩቱ ሌሎች ኃላፊነቶቹና ተግባሮቹ ናቸው። ETCONp

ኢንስቲትዩቱ በሰንዳፋ ከተማ የልህቀት ማዕከል እያስነባ ነው:: ማዕከሉ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ትልቅ ተቋም ስለሚሆን ማዕከሉን ማስተዳደር በተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት ውስጥ ይካተታል። የልኀቀት ማዕከሉ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የሰው ኃይል ማበልፀጊያ ተቋም ነው። ማዕከሉ ግንባታዎች ሳይፈርሱ የግንባታ ጥራትን ለመፈተሽና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ አሠራሮችና መሣሪያዎች (Non Destructive Testing Methods) እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ ተግባራት የሚከናወኑባቸው የቤተ-ሙከራ ማዕከላት ይኖሩታል።

የማዕከሉ ግንባታ በሁለት ምዕራፎች የሚከናወን ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በሦስት ዓመታት፣ ቀሪውን ደግሞ በሁለት ዓመታት በማከናወን ማዕከሉ ከአምስት ዓመታት በኋላ በሙሉ አቅም ሥራ እንዲጀምር ይደረጋል፡፡ የግንባታው 17 በመቶ ሥራ በ2016 ዓ.ም ይጠናቃል ተብሎ ታቅዷል። ከዚህ በተጨማሪም፣ ተዘጋጅቶ ለመንግሥት የቀረበው የተቋሙ የደንብ ማሻሻያ፣ ኢንስቲትዩቱ የምዘናና የብቃት ማረጋገጫ ሥራውን ከማመቻቸት ባለፈ በራሱ የምዘናና የብቃት ማረጋገጫ ሥራ እንዲያከናውን ይጠይቃል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የበጀት ዓመቱ ዋና ዋና ተግባራት
ኢንስቲትዩቱ በዘንድሮው የበጀት ዓመት በኢንዱስትሪው ውስጥ በሥራ ላይ ለሚገኙ 2442 ተቋራጮች፣ አማካሪ መሐንዲሶች ሌሎች የዘርፉ ተቋማት ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ይህ ሥልጠና የፕሮጀከት ማኔጅመንት አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ የሚያግዝ ነው። ETCONp

የምንመድባቸው አሠልጣኞች በዘርፉ በቂ ልምድና ዝግጅት ያላቸው ናቸው፡፡ ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከ20ሺ በላይ ለሚሆኑ ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን ሰጥቷል፡፡

ለ180 ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ (Project Management Professionals) እንዲሆኑ የሚያስችላቸውንና ዓለም አቀፍ ሰርተፊኬት እንዲያገኙ ዕድል የሚፈጥርላቸውን ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ባለፈው ዓመት ይህ ሥልጠና ለ120 ባለሙያዎች ተሰጥቶ ነበር፡፡

ኢንስቲትዩቱ በ2015 የበጀት ዓመት ያከናወነው ሌላ ተግባር የ<ቢም> (Building information Modeling) ቴክኖሎጂ ስልጠና ነው፡፡ ይህ ቴከኖሎጂ የዲዛይን ሥራዎችን በማስተባበር የጊዜና የገንዘብ ብክነት እንዳይኖር የሚያደርግ ነው፡፡ በተለያዩ ባለሙያዎች የሚሠሩ የዲዛይን ዝግጅት ሥራዎች የተናበቡ እንዲሆኑ ለማድረግ ቁልፍ ሚና ያለው ቴከኖሎጂ ነው፡፡ ዘንድሮ 243 ባለሙያዎች ሥልጠናውን ወስደዋል፤ ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከ4ዐዐ በላይ ባለሙያዎችን በ<ቢም> ቴክኖሎጂ አሰልጥኗል፡፡ አማካሪ መሐንዲሶችን ጨምሮ የዘርፉ መንግሥታዊ ተቋማት ባለሙያዎችና የዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ሥልጠናውን ወስደዋል፡፡ ቴክኖሎጂው የተበላሸውን የኢንዱስትሪውን ገፅታ ለመገንባት እና ሥራን በእውቀት ለመምራት ከፍተኛ ጥቅም አለው፡፡

የኮንስትራክሽን ዘርፉ እየተመራ ያለው ባለሙያዎች ተመዝነው ብቃታቸው በምዘና ተረጋግጦ ስላልሆነ የብቃት ምዘና መመሪያ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ መመሪያው ሲጸድቅ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ባለሙያዎች በጥንቃቄ በሚዘጋጅ የፈተና ሥርዓት አማካኝነት ብቃታቸው ይመዘናል ለፈተናው የሚያግዙ ግብዓቶችም እየተዘጋጁ ነው፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለማዘመን የሚያግዙ የአሠራር ሥርዓቶችንም ያስተዋውቃል። ለአብነት ያህል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና ሃሳቦችን ይዘው የሚቀቡ ተወዳዳሪዎችን የሚያበረታቱ እንዲሁም የሥራ ቅብብሎሽ እንዲኖር የሚያስችሉ አሠራሮች የሚመሩባቸውን መመሪያዎችን አዘጋጅቷል።

ኢንስቲትዩቱ ከሰባት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር አንድ ባለሙያ ከረዳቶቹ ጋር ሆኖ በቀን ምን ያህል ሥራ መሥራት እንደሚቻል የሚያመለክት የምርታማነት መለኪያ (Productivity Norm) እያዘጋጀ ነው። ኢንስቲትዩቱ የምክር አገልግሎቶችንም ይሰጣል፡፡ በቂ ባለሙያ ለሌላቸው ተቋማት የሙያ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ለብዙ ተቋማት ሥራዎች ሙሉ የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎችን አከናውኗል።
👍5
የተቋማት ፐሮጀክት የመምራት ደረጃን (Organizational Project Maturity) የማሳደግ ሥራ በዚህ ዓመት የተከናወነ ሌላው ተግባር ነው፡፡ ይህ አሠራር በዓለም አቀፍ መመዘኛ አምሰት ደረጃዎች አሉት። ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ (በተቋማት ፕሮጀክት የመምራት ደረጃ) የምትናኘው ከአንድ እስከ ሁለት ባለው ወሰን ውስጥ ነው፤ ይህም አነሰተኛ የሚባል ነው:: ይህን ደረጃ በ10 ዓመት ውስጥ ወደ አምስት/ አራት ለማድረስ የታቀደ ሲሆን፤ በአምስት ዓመታት ውስጥ ወደ ሦስት ለማድረስ እየተሠራ ነው። ለዚህ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ተዘጋጅተው የአሠልጣኞች ሥልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡ ከተቋማት ኃላፊዎች ጋር ምክከር ተደርጓል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የመሠረተ ልማት ቅንጅት እጦት እያስከተለ ያለውን ችግር በማጥናት በመሠረት ልማት ዝርጋታ ላይ ከተማሩ ተቋማት ጋር ውይይት አድርጓል ለዚህ ችግር መፍትሄ የሚሆን ቴክኖሎጂንና አማራጭ የግንባታ ግብዓቶችን (ለምሳሌ ከአፈር የሚሠሩ ብሎኬቶችን) አስተዋውቋል፡፡ ተቀባይነት ያገኙት ቴክኖሎጂዎችና አሠራሮች ደግሞ ብሔራዊ ደረጃ (National Standard) እንዲወጣላቸው እየሠራ ነው፡፡ የ<ቢም> ቴክኖሎጂ አስገዳጅ ብሔራዊ ደረጃ እንዲኖረው የሚያስችሉ ግብዓቶች ተሟልተው ደረጃው ለሚኒስትሮች ኮሚቴ ቀርቧል በቅርቡ ይፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

የሀገር በቀል ተቋራጮች አቅምና ችግሮች ETCONp

የሀገር በቀል ተቋራጮች ከዚህ ቀደም በጥሩ እድግት እየተጓዙ የነበረ ቢሆንም መልሰው ተዳከመዋል፡፡ የእውቀትና የአደረጃጀት ችግሮት አሉባቸው። በአሁኑ ሰዓት ተወዳዳሪ መሆን አልቻሉም። ለዚህ ችግር ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል አንዱ ተቋማቱ በኮርፖሬት ደረጃ የተደራጁ አለመሆናቸው ነው። ለምሳሌ አንድ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት በአንድ ግለሰብ ስም ተሰይሞ፣ ግለሰቡ ሁሉንም ኃላፊነት ይዞ ሥራ ይጀምራል፡፡ ግለሰቡ በሆነ ምክንያት ሥራውን ሲያቆም ድርጅቱም አብሮ ይከስማል፡፡ ተቋማቱ የአንድ ሰው ተቋማት ሳይሆኑ የኮርፖሬት አሠራር ሊኖራቸው ይገባል። ሰውየው ኖረም አልኖረም ተቋማቱ እንዲቀጥሉ የእውቀት ሥራ መሥራት ይገባል፡፡

የኮርፖሬት አሠራር ስልት (Corporate Culture) አንድ ተቋም በአንድ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን ሥርዓት ባለው አሠራር (System) ሥራውን እንዲያከናውን የሚያስችል ነው፡፡ ይህ ስልት ዝርዝር የአሠራር ሥርዓቶችን በመዘርጋትና ውሳኔዎች በተገቢው ጊዜ እንዲወሰኑ በማስቻል፤ የፕሮጀክት አፈፃፀም ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆን ያደርጋል።

ክፍያዎች በተገቢው ጊዜ አለመከፈላቸው ተቋራጮቹን አዳክሟቸዋል፡፡ ሥራ ለማግኘት ሲባል ብቻ አዋጭ ያልሆነ (በጣም ዝቅተኛ) ዋጋ ያቀርባሉ። ገበያን በሚገባ አጥንቶ ለፐሮጀክት የሚመጥን ዋጋ ያለማቅረብ ችግር አለ፡፡ ይህ ደግሞ ሥራው እንዳይሠራና ሀገርም ኪሳራ እንዲገጥማት ያደርጋል፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ጎድቶታል።

ስለሆነም <<ተቋራጮቹ ለሥራው የሚመጥን ዋጋ አስገብተዋል ወይ?>> የሚለውን ጉዳይ በጥንቃቄ መመልከት ይገባል፡፡ የግዥ ሥርዓቱ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ እንዲያሸንፍ ዕድል የሚሰጥ (Least Evaluated Bid) ነው፡፡ ይህ የግዥ ሥርዓት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለብዙ ዓመታት የቆዩና ልምድ ያላቸው ተቋራጮች ከሥራ እንዲወጡ አድርጓቸዋል። ስለሆነም ተቋራጮቹ ለሥራው የሚመጥን ዋጋ አስገብተዋል ወይ? የሚለውን ጉዳይ በጥንቃቄ መመልከት እና የግዥ ሥርዓቱን ማስተካከል ያስፈልጋል።

የውጭ ሀገራት የሥራ ተቋራጮች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሥራ በሚጀምሩበት ጊዜ የሀገር ውስጥ ተቋራጮች ወሳኝ በሆኑ ሥራዎች ላይ እንዲያሳተፉ የሚያስችል አሠራር (Joint Venture System) ተዘጋጅቷል፡፡ በ10 ዓመት ውስጥ በሀገር ውስጥ ከሚወጡ ዓለም አቀፍ ጨረታዎች መካከል 75 በመቶው የሀገር ውስጥ ተቋራጮች የነበያ ድርሻ እንዲኖራቸው ታቅዷል።

ኢንጂነር ታምራት <የሀገር ውስጥ ተቋራጮች የአቅም ክፍተት አለባቸው፡፡ ክፍተቶቻቸውን ለማስተካከልም የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ለሥራ ተጽራጮች በብዙ ዘርፎች ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል። የኛ ሀገር የሥራ ተቋራጮቹ የ10 ዓመት ብቻ ታሪክ ባለቤት እየሆኑ ነው:: ለውልድ የሚተላለፉ ተቋራጮችን ማፍራት አለብን ብለን እየሠራን ነው ይላሉ፡፡

ከዚህ ቀደም የሥራ ተቋራጮችን አቅም ለመወሰን ተቋራጮቹ ያላቸውን ማሽኖችና ሌሎች መሳሪያዎችን ከግምት ውስጥ የማስገባት አሰራር ይተገበር ነበር። ነገር ግን አንድ ተቋራጭ እውቀቱ ካለው ማሽኖችን ተከራይቶ እንዲሠራ በማድረግ ተቋራጩ ያለውን አቅም ለሀገር ልማት መጠቀም ይቻላል። ብዙ አቅም ያላቸው ባለሙያዎች ማሽኖች ስላሌሏቸው ብቻ ለብዙ ዓመታት ተቀጣሪ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ስለሆነም እያንዳንዱ ተቋራጭ የሁሉም ማሽኖች ባለቤት ሊሆን እንደሚገባ የሚያስገድደው መስፈርት አስገዳጅ መሆን እንደሌለበት ስምምነት ላይ ተደርሷል። ያለውን ሀብት በአግባቡ የሚያስተዳድር የአሠራር ሥርዓት መፍጠርም አስፈላጊ ነው፡፡ ተቋራጮችን አቀናጅቶ ማሠራት በጣም ይጠቅማል። ትልቅ የአመለካከት ችግር አለ፡፡ የጥቅም ግጭትና ቅሬታ እንዳይፈጠርም የሚገኘውን ትርፍ ተቋራጮቹ በሥራው ላይ ባላቸው አበርክቶ መሠረት በማስላት መከፋፈል ይገባል።

<በባለሙያ እየተመሩ ያሉ ተቋማት አሉ፣ በባለሙያ የማይመሩ ተቋማትም አሉ፡፡ በአመዛኙ ግን የኮንስትራክሽን ዘርፉ በባለሙያ እየተመራ አይደለም> የሚሉት ኢንጂነር ታምራት፤ <አሠራራችንን ፐሮፌሽናሊዝምን የሚጋብዝ ከሆነ፣ አሳማኝ ያልሆነና ዘርፉን የሚጎዳ ዋጋ ይዘው የሚቀርቡ ተቋራጮችን ከጨዋታው ውጪ የምናደርግበት አሠራር ከተፈጠረ፣ የሚጠየቁት የምዘና መስፈርቶች የተቋማትን ብቃት መመዘን የሚያስችሉ ከሆኑ፣ ልምድ ያላቸው፤ በኢንዱስትሪው ላይ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ፣ ሀገርን ሊገነቡ የሚችሉ ከዝያ የወጡ ተቋራጮች ወደ ገበያው ሊመሰሱ ይችላሉ> በማለት ያስረዳሉ።

ቀጣይ እቅጾች
የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዘርፉን ለማሳደግ በቀጣዩ በጀት ዓመት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውንና ዓለም አቀፍ ሰርተፊኬት እንዲያገኙ ዕድል የሚፈጥርላቸውን ሥልጠና አጠናክሮ መቀጠል አንዱ ነው፡፡ በዚህም 180 ለሚሆኑ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ለሚመሩ ተቋማት ባለሙያዎች ይህ ሥልጠና ይሰጣል፡፡ ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ 200 ባለሙያዎች የ<ቢም> እና ለሦስት ሺ 8oo የዘርፉ ባለሙዎች የፕሮጀክት ማኔጅመነት ሥልጠናዎች የሚሰጥ ይሆናል። ለአንድ ሺ ባለሙያዎች የብቃት ምዘናና ማረጋገጥ ሥራ ለመሥራት አቅዷል፡፡ የልኅቀት ማዕከሉን 17 በመቶ ግንባታውን ማጠናቀቅም የኢንስቲትዩቱ የቀጣዩ ዓመት እቅድ ነው።

ምንጭ፡ አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 24 ቀን 2015

@etconp
👍14❤1🙏1
👍6❤2
Ethio Construction Engineering
Photo
👉የ ዛሬ ETCONp አርአያ ሰብ እናስተዋውቃቹ

📌ከኳታር ምክትል ገዢ እጅ የወርቅ ሜዳሊያ በመቀበል በዶክትሬት የተመረቀውና ሁለተኛ ዶክትሬቱን በመስራት ላይ የሚገኘውን ይህንን እንቁ የኢትዮጵያ ልጅ ትሁት ወንድሜን እና ወዳጄን ዶ/ር ኢ/ር ታደሰን ላስተዋውቃችሁ
***
1. እ.አ.አ በ2012ዓ.ም በሲቪል ኢንጂነሪንግ የትምህርት መስክ ከአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ  4.0/4.0 በማምጣት  በእጅግ ከፍተኛ ነጥብ ተመርቋል።

2. 3ኛ ዓመት ተማሪ እያለ "ስትራክቸራል ኢንጂነሪንግ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ እየፃፈ ነበር፤

3. በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የድሮ መግቢያ በር ላይ በጩቤ 8 ቦታ ተወግቶ ላፕቶፑ በመሰረቁ ስራዎቹ ጠፍተውበት  የሚያመልከው ጌታ ሕይወቱን ታድጎታል።

4. እ.አ.አ በ2013 ዩኒቨርስቲው ከሳምሰንግ ጋር በመተባበር ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አራት የሲቪል ምህንድስና ተማሪዎች የውጭ አገር የስራ እድል ሲሰጥ አንዱ ይህ ጀግና ወጣት ነበር።

5. ለሦስት ዓመታት በኳታር የዓለም ዋንጫ ፕሮጀክቶችን ሰርቷል።

6. ሁለተኛ ዲግሪውን ለመማር እድል የሰጠው የኳታር ዩኒቨርሲቲ እዛው በመምህርነት ቀጥሮታል።

7. በመምህርት እየሰራ እዛው በሲቪል ምህንድስና 4 ነጥብ በማምጣት፤ ከዶክትሬት ተመራቂዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ እና የዓመቱ ምርጥ ተመራማሪ በመባል ከኳታር ምክትል ገዢ እጅ የወርቅ ሜዳሊያ በመቀበል በዶክትሬት ተመርቋል።

8. ሁለተኛ ዶክትሬት ዲግሪውን በካናዳ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በሌላ የትምህርት ዘርፍ እየሰራ ይገኛል።

9. በኳታር በሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ ላይ ላደረገው የምርምር ስራ እና አስተዋፆ 2 የወርቅ ሜዳሊያ እና 10ሺ ሪያድ ተሸልሟል (ከ2019 እስከ 2022 ብቻ ከ25,000USD ገንዘብ ተበርክቶለታል።)

10. ከሁሉ በላይ  ያኔ ከበላተኛ መንጋጋ ነጥቆ በሕይወት ኑር ያለውን ጌታ የሚወድ እግዚአብሔር የሚፈራ ትሁት ወንድም ነው።

11. ብዙ የምርምር ሽልማቶችን እና የሪሰርች ኤዲተርነት ሽልማቶችን በየጊዜው የሚሸለም የሀገራችን እንቁ ልጅ ነው።

🌟የተሸለማቿውን ሽልማቶች ከታች ባለው ሊንክ መመልከት ትችላላችሁ

https://www.tadessewakjira.com/awards

Via Aklilu Tesfaye

@etconp
👍29👏8❤6
ክፍያ ምሥክር ወረቀት/payment certificate/

1. ቅድመ ክፍያ(Advance Payment Certificate)

• ከ 20% እስከ 30%  ባለው ወሰን ውስጥ እንደ አሠሪው ፍላጎት ለሼል ማስጀመሪያ የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡

• ለዚህ ክፍያ ተቋራጭ ተመጣጣኝ በሁኔታ ላይ ያልመሠረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል፡፡

• አንዳንድ አሠሪዎች ተቋራጫቸው የባንክ ዋስትናውን መስያዝ የሚሳነው ሆኖ ከተገኘ፤ ዋስትናውን በሁኔታ ላይ የተመሠረተ ዋስትና ተአማኒነት ካለው ኢንሹራንስ ድርጅት እንዲያሲዝ ፈቅደው፤ ገንዘቡ በጋራ በተከፈተ ሂሣብ(አሠሪና ተቋራጭ) እንዲቀመሥ ተደርጎ በጋራ ፊርማ እንዲወጣ ያደርጋሉ፡፡

• የቅድሚያ ክፍያው ለሚሠራ ሥራ ከሚዘጋጅ ተከታታይ ክፍያዎች በሂደት ተቀንሶ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

2. ጊዜያዊ ክፍያ (Interim Payment Certificate)

• ለተሠራ ሥራ በየወቅቱ የሚዘጋጅና በአማካሪው ተረጋግጦ የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡

• ይህ ክፍያ ስሙም እንደሚያመለክተው ጊዜአዊና ወደፊት የሚወራረድ ሂሣብ ነው፡፡

• አንድ ክፍያ ሲፈጸም የሂሣብ ስህተት ቢያጋጥም የሚቀጥለው ላይ ለማስተካክል የሚያስችል መንገድ አለው፡፡

3. የመጨረሻ ክፍያ (Final Payment)

• በሕጉ የአንድ ፕሮጀክት ክፍያ የሚባለው የመጨረሻ ክፍያ ነው፡፡

• በዚህ ግዜ አማካሪው ከመጀመሪያ ጀምሮ በተከታታይ የተፈጸመውን ጊዜአዊ ክፍያ ከመስክ በሚወስደው ስፍረ መሠረት አገናዝቦና መርምሮ የሚያጸድቀው ክፍያ ነው፡፡

• ክፍያው ከጸደቀ በኋላ ለመያዣ ከተያዘው ግማሹን ጨምሮ ለተቋራጩ እንዲከፈል ያዛል፡፡

• ግማሹ የመያዣ ገንዘብ ከአንድ ዓመት የዋስትና እና የጥገና ግዜ በኋላ የመጨረሻ ክፍያ ሲፈጸም ይለቀቃል፡፡ በዚህ ግዜ የፕሮጀክቱም ሂሣብ ይዘጋል ማለት ነው፡፡

• የመያዣ ገንዘብ ሚባለው በመንግስት ሥራ ግዢ ደንብ መሠረት የተሠራው ሥራ 5% ሲሆን ጊዜአዊ ርክክብ ከተፈተመ በኋላ እስከ መጨረሻ ርክክብ የሚቆየው እና በመጨረሻ የሚለቀቀው ግማሹ 2.5% ነው፡፡

በክፍያ አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ችግሮች

1. ወጥነት የሌለው የክፍያ መፈጸሚያ ምስክር ወረቀት ቅጽ
• ይህ ቅጽ በሐገር አቀፍ ደረጃ አንድ አይነት ቢሆን ተቋራጮች በሠሩበት ሁሉ አንድ አይነት ግንዛቤ ስለሚኖራቸው መደናገር አይኖርም፤ የሂሣብ ምርመራ ሥራንም ቢሆን ያቀላል፡፡
2. በባለቤት እና/ወይም አማካሪ ምክንያት የሚዘገይ ክፍያ
• የተቋራጩን የግዢ ዑደት ስለሚያሰናክል የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ይታወካል
• በጀት አጠቃቀም ላይ ችግር ይፈጥራል
• የሥራ ጥራት ያበላሻል
• ዋጋ ያንራል


@etconp
👍7❤2👏2
👉የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ

🌟አሁናዊ ገጽታ በፎቶ

@etconp
❤8👍1
💥የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/

🌟የኮንስትራክሽን ውል ስምምነት/contract agreement በአሰሪ/client እና በተቋራጭ/contractor መካከል የሚፈረምበት ቀን የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

⚡️እዚህ ላይ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020 ድንጋጌ እና አንድ ውል ተቋቋመ ሊባል የሚችለው መቸ ነው? የሚለው ማለትም የውል አቀራረብ/offer እና አቀባበል/acceptance በሚመለከት በፍትሀብሄር ህጉ 1681 እና ተከታዮቹ የተደነገገው እና የውል ፎርም ጉዳይ ከግምት ውስጥ መግባት ጭምር አለበት፡፡

⚡️የግል የኮንስትራክሽን ውል ጉዳዮችን በሚመለከተው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ አሰሪና ተቋራጭ ስለሚሰራው ስራ እና ስለዋጋው ካልተስማሙ በስተቀር የተቋራጭነት ውል አለ እንደማይባል ተደንግጓል፡፡

🌟ሌላው ከአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎችን በሚመለከት ስለውሎች በጠቅላላው የተደነገገው ጭምር ተፈጸሚነት እንዳለው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3131(1) ይደነግጋል፡፡

⚡️የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጽሁፍ መደረግ እንዳለባቸው በፍትሀብሄር ህግ ስለውሎች በጠቅላላው በሚደነግገው ክፍል በአንቀጽ 1724 ላይ ተደንግጓል፡፡

⚡️የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2005(1) ላይ እንደተደነገገው ደግሞ የጽሁፍ ሰነድ በላዩ ላይ የተጻፈውን ቀን በሚመለከት በተፈራራሚዎች መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ነው ይላል፡፡

🌟እንግዲህ ውል የተደረገበት ቀን በአሰሪና ተቋራጭ መካከል የውል ግንኙነት መቋቋሙን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡

⚡️ውል ደግሞ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ በተዋዋዮች መካከል እንደህግ እንደሚቆጠር የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731(1) ይደነግጋል፡፡

🌟ሆኖም ግን ውሉ የተደረገበት ቀን የውሉ የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን ተደርጐ ሊወሰድ አይገባም፡፡


@etconp
👍10👏1
🔖ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ይህ ቻናላቹ የ ኮንስትራክሽን ዲጅታል ቤተ መፅሃፍት እንዳለው ያውቃሉ?
.
📚ይህም ዲጂታል ቤተመፃህፍት በውስጡ የ SOFTWARE SETUP, የ ARCH, COTM  እና CIVIL መፅሀፍቶችን በ ሙሉ የያዘ ነው።

🚧ይህ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ሲሆን ለቀጣይ በአስተያየታችው መሰረት ብዙ ነገር ምናስተካክል ይሆናል።

👉ይህን link በመጫን ወደ ቤተመፃህፍቱ ልትሄዱ ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇👇
👉🏿 https://t.me/ETCONpDigitalLibrary_Bot
❤9👍1
👉በነገራችን ላይ የመወያያ ግሩፓችን @COTMp በቀን ብዙ ጥያቄዎች ይስተናገዱበታል።

🚧ከ 8500 በላይ ቋሚ አባላት አለው።

🚧ብዙዎቻችን እንደ ቤተሰብ ሆነንበታል ምክንያቱም ሁሉም ጥያቄዎ ለመመለስ በደስታ የሚጠብቅበት ግሩፕ ነው።

🔖ጥያቄ? ካለዎት፣ ሌሎችን ማገዝ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉን።👇

https://t.me/COTMp
🏆4