Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉Post-tension slab

🚧Post-tension slab is a type of concrete slab that is reinforced with high-strength steel cables or tendons, which are tensioned after the concrete has been poured and cured.

🌟This process helps to increase the strength and durability of the slab by applying a compressive force to the concrete, which counteracts any tensile stress that may occur due to external loads or forces. Post-tension slabs are commonly used in large commercial and residential buildings, bridges, parking garages, and other structures that require a high level of strength and stability.

🌟They offer several benefits over traditional reinforced concrete slabs, including reduced cracking, improved load-bearing capacity, and greater flexibility in design and construction.

💫For More Visit Our Youtube👇

https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
👍16🏆1
👉1.3 ቢሊዮን ብር ወጪ የሆነበት ቤስት ዌስተርን ፕሪሜየር ዳይናሲቲ ሆቴል ሊመረቅ ነው

🌟በ 12 የአንድ ቤተሰብ አባላት የተገነባ ቤስት ዌስተርን ፕሪሜየር ዳይናሲቲ ሆቴል ለግንባታ ሰባት አመታትን የፈጀ ሲሆን ጠቅላላ ካፒታሉ 1.3 ቢሊዮን ብር እንደሆነ አና ከአንድ መቶ ሰባ በላይ ለሚሆኑ የሀገራችን ዜጎች የስራ እድል እንደፈጠረ ተገልፇል።

🚧ሆቴሉ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የአገራችን ሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በቁጥርም ሆነ በጥራት ዓለም ዓቀፍ የሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ ከሚፈልገው አቅርቦት ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አካባቢ ኢንሳ ፊት ለፊት የተገነባ ዓለም ዓቀፍ ሆቴል ነው።

Via Fast mereja

@etconp
👏6👍3
👉ከ ኢንጅነር አቤሴሎም መለስ

📜Series 2000: Site Clearance

🌟ሳይቱ ለግንባታ  clear በሚደረግበት ሰአት ክሊር የተደረገውን area አጋኖ ማቅረብ
🌟በ clearing ወቅት መፍረስ ያለበት ማንኛውም structure ካለ ስራውን አጋኖ ማቅረብ

📜Series 3000: Drainage Structure

🌟የፍሳሽ ትቦዎች ሲሰሩ ቁፏሮውን፣ ግንባታውን፣ back fill ኡንም ጭምር quality ማሳነስ ... ክፍያ ላይ ግን quantity አጋኖ ማቅረብ
🌟መንገዱን አቋርጠው የሚሄዱ ትቦዎች ( cross drainage ወይም culvert) በሚሰሩበት ጊዜ ቁፏሮ፣ backfill ፣ ግንባታውን ወዘተ quality ማሳነስና እንደነገሩ መስራት ... ክፍያ ላይ ያው የተዋዋልነው ተሰርቷል ማለት
🌟የድንጋይ ስራዎች stone pitching፣ masonry ፣ riprap ወዘተ ስራዎችን ማጋነን
🌟ለድልድይና ለትቦዎች ደህንነት የሚሰሩ ግንባታዎችን ማጋነን

📜Series 4000: Earthworks and Material Stabilisation

🌟Road bed (( ወይም የመንገዱ የመጀመሪያው ንጣፍ ማለት ይቻላል)) ሲሰራ መጀመሪያ የነበረው ጥሩ ያልሆነ አፈር (unsuitable material) ተነስቶ ሌላ ተተክቷል ይባላል ((እውነት ሊሆንም ላይሆንም ይችላል)) ለዚህም ክፍያ አለው ... ቀጥሎም Road bed ለተሰራበት ይከፈላል ... የተሰራው መጠንና ካሊቲውን ፈጣሪ ያውቃል

🌟ሌላው የመንገዱ ትልቁና ዋናው ወጪ Cut  እና Fill ነው ።
🌟Cut section ሲኖር የተቆረጠውን volume አጋኖ ሪፖርት ማድረግ በተጨማሪም በቀላሉ የሚቆረጥ ወይም soft excavation ሆኖ ሳለ Hard Excavation ነው ብሎ ማስገባት ... ብሩ ይጨምራላ
🌟Fill section ሲሆን ደሞ ያው በጥራትም ይሁን በ volume ብዙ መብላት ይቻላል። በተጨማሪ ደሞ fill ሲደረግ በ Layer ነው የሚሞላው ለምሳሌ በ25 ሳንቲም thickness ትሞላለህ ከዛ ኮምፖክት ታደርጋለህ ከዛ ክፍያ ይሰጥሃል ... ሳይት ላይ ምን ሊደረግ ይችላል መሠለህ?? ... 1 ሜትር ለመሙላት ኮንትራቱ ላይ በ25 እየተሞላ ይጠቅጠቅ ካለ 4 Layer ይኖራል ማለት ነው። 4x25 cm = 1 ሜትር ...ሳይት ላይ ግን በ2 layer ብቻ ሊሞላ ይችላል። በ50 cm ውፍረት ማለት ነው። ኮንትራክተሩ አራቴ ሰርቶ ሊያገኝ የሚገባውን በሁለት ስራ ያገኛል ማለት ነው። በዛ ላይ ከሙሉ ወጪው በግማሽ ይድናል። ለ50 ብር ስራውም 100 ይከፈለዋል።

🌟Borrow area ለማግኘትም የተወሰኑ ንግግሮች ይኖራሉ በመሬቱ ባለ ይዞታዎችና በመንገዱ ባለቤት መሀል

📜Series 5000 : Sub Base, Road Base and Gravel Wearing Course

🌟እዚህም እንደላይኛው volume በማምታታት ወይም layer በመቀሸብ ... Layer ቅሸባ ከሚገመተው በላይ አዋጭ ነው

📜Series 6000 - Bituminous Surfacings and Road Base

🌟እዚህም እንደሌሎቹ volume ና layer ቅሸባ ነው።

📜Series 8000 - Structure

🌟እዚህ ስር ያሉት masonry work , bridges, box and slab culvert, cofferdam, timber structures, structural steelwork ወዘተ ናቸው። እንደሚታወቀው እነዚህን ለመስራት የሚያስፈልጉት ማቴሪያሎች ፌሮ ፣ ሲሚንቶ ፣ aggregate ፣formwork ያስፈልጋል። excavation እና backfill ስራዎች ይኖራሉ .... በሌባ አእምሮ do the maths!

📜Series 9000 - Ancillary Work

🌟በእዚህ ስር ያሉት gabion, mattresses, kilometer የሚያመላክቱ ኮንክሪቶች ( Kilometer Post), አስፖልቱ ላይ የሚቀቡ ቀለሞች ፣ የትራፊክ ምልክቶች ፣ guardrail ፣ ከግንባታ በኋላ አካባቢውንና borrow areaውን ወደ ተፈጥሯዊው ሁኔታ ለመመለስ የሚሰሩ ማስተካከያዎችና የእፅዋት ተከላዎች ፣ አጥሮች ፣ የእግረኛ መንገዶች ፣ ለሴፍቲ ተብለው የሚሰሩ የኮንክሪትና masonry ግድግዳዎች ወዘተ ናቸው።

📌መንገድ ስራ ላይ ማጭበርበርና ውሸት እንደ hobby ወይም ዝንባሌ ነው። ጥዋት ተነስተህ እስፖርት እንደምትሰራው ምናምን በቃ የመንገድ ስራ ሰራተኞች ወደዛ ያዘነብላሉ። በተለይም ከአዲስ አበባ የራቀ ቦታ ላይ ከሆነ ሌቦቹ እንደፈለጉ ይፈነጩብሃል። መንግስት የለም ወይ የሚያስብለኝ ከህዝቦች መሞት ይልቅ መንገድ ስራ ላይ የሚሠራውን ሳይ ነው። ተቆጣጣሪ ሆነህ ኮንትራክተሩ እንደአለቃ ይሆንብሃል። ተቆጣጣሪ ሆነህ ኮንትራክተሩን ብታማ እንዳንተው ተቆጣጣሪ ተብሎ የተሾመው አለቃህ ይገላምጥሀል ፣ ይነዘንዝሃል። ለምን ካልክ ብዙ ሴራዎችን እየሠሩ መሮህ እንድትሄድ ያደርጉሀል። ይሄንን ፅሁፍ የፃፍኩት ስርቆቱ በግልፅ እንዲታወቅና መፍትሄ እንዲሰጠው ነው። ነገሮቹ መዘርዘራቸውም ለእያንዳንዱ ችግር የራሳችሁን መፍትሄ እንድታስቡ ነው።

የተሻለ መፍትሄ ካላችሁ ወዲህ በሉ
...........

💫መፍትሔው ምንድነው??

1. የመንገድ ባለቤቶች የራሳቸውንም ሰራተኛ፣ ኮንሰልታንቱንም ይሁን ኮንትራክተሮችን ማመን የለባቸውም። ከዚህ ሰርክል ወጣ እያሉ ስራዎችን ቼክ ማድረግ።
2. የተለያዩ ምርምሮችን በማሰራት አዳዲስ የአሰራርና የቁጥጥር መንገዶችን መፍጠር
3. የሚያጋልጡ ግለሰቦችን ማበረታታት
4. መንገድ ስራ ላይ በአብዛኛው በሰርተፍኬት/ዲፕሎማ ነው የሚሰሩት። እነዚህም ሰዎች ስራ እናጣለን በሚል ስጋት የተባሉትን አሜን ብለው ነው የሚሰሩት። የተማረውን ማስገባት የተሻለ ነው።
5. የመንገዶች ባለቤቶች የተቆጣጣሪውንና የራሳቸውን ሰራተኞች ደሞዝ ቢጨምሩ ችግሩን በተወሰነ ደረጃ ይቀንሰዋል።

🏷ሀሳብ ስጡበት👇

https://t.me/COTMp
👍29🏆1
❤2
Ethio Construction Engineering
Photo
የላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት የዕድሳት ሥራ እስካሁን አለመጀመሩ ተገለጸ

ከአራት ዓመት በፊት ታቅዶ የነበረው የላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት የዕድሳት ሥራ እሳካሁን አለመጀመሩን የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል፡፡

በጽህፈት ቤቱ የቅርስ ጥበቃ ቡድን መሪ ማንደፍሮ ታደሰ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፤ በ2011 መጨረሻ በፈረንሳይ መንግሥት ዕድሳት ሊደረግለት የተለያዩ ጥናቶች ተደርገው በቅርብ ቀናት ውስጥ የእድሳት ሥራው ይጀመራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ እስካሁን ድረስ የዕድሳት ሥራው ሊጀመር አልቻለም።

2011 ላይ የከተማው ነዋሪ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናቱ የዕድሳት ሥራ ሊደረግላቸው ይገባል ብሎ በሰላማማዊ ሰልፍ ጭምር መጠየቁን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ሥፍራው አቅንተው የጉዳት መጠኑን መመልከታቸውን አስታውሰዋል፡፡

በወቅቱ 24 ባለሙያዎችን ያካተተ የጥናት ቡድን ከፈረንሳይ አገር መምጣታቸውን እና ሰባት የጥናት ዓይነቶችን በውቅር አቢያተ ክርስቲያናቱ ላይ መደረጉን ጠቅሰው፤ የጥናቱ ውጤትም ለኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን መላኩንም ተናግረዋል፡፡   

ሆኖም በመሀል በተከሰተው የሰሜኑ ጦርነት እና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የጥናት ቡድኑ ዳግም ወደ ሥፍራው ማቅናት ባለመቻሉ፤ ጥናቱ ተጠናቆ የዕድሳት ሥራው እንዳይጀመር ምክንያት ሆኗል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

አሁን ላይ የዕድሳት ሥራው እንዲጀመር ጥላው (ሼልተር) ቀድሞ መነሳት ስላለበት በኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን በኩል በዚህ ላይ የሥራ ልምድ ያላቸው ዓለም አቀፍ ብቁ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ሂደት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

ቡድን መሪው አክለውም፤ ካሉት 11 ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት በተለይ ቤተ አማኑኤል የተሰኘው ውቅር ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰው ጉዳት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ አስቸኳይ እድሳት ካልተደረገለት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የላሊበላ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ተስፋሀብቴ አበራ በበኩላቸው ለእድሳት ሥራው አንደኛ ዙር የበጀት ስምምነት መደረጉን ከጠቀሱ በኋላ፤ ከተማ አስተዳደሩ ከቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ጋር ሳይቀር ተደጋጋሚ ውይይቶች ማደረጉን ገልጸዋል።

ከንቲባዋ አክለውም፤ "ለኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን በተደጋጋሚ ለምን የጥገና ሥራው አይጀመርም?" ብለን ጠይቀን የተሰጠን መልስ "የጥናት ሥራው አላለቀም እንዲሁም በአካባቢው እንደልብ ተንቀሳቅሶ ለመስራት የጥናት ቡድኑ የጸጥታ ስጋት አለበት" የሚል መሆኑን ጠቅሰዋል።

@etconp
👍6
👉አንድ የስራ ተቆጣጣሪ ባለሞያ የኮለን ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት ፎርምወርክ ስራው ላይ መሟላታቸውን ማረጋገጥ የሚገባው መሰረታዊ ነጥቦች

🚧[Elements of good Column formwork finish]

⏺1.ጥብቅ መሆኑን/Formwork rigidity/

▶️የተዘጋጀው ፎርምወርክ የራሱን ክብደት/self weight/፣የብረቱን ክብደት፣የርጥብ ኮንክሪቱን ክብደት፣ የኮንክሪት ሰራተኞች፣ የንፋስ ግፊት፣ የስራ መሳሪያዎችና ሌሎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጫናዎችን የሚቋቋም ሆኖ በቂ ጥንካሬ ኖሮት መሰራቱን ማረጋገጥ የመጀመሪያ ስራ ይሆናል።

⏺2.የፎርምወርክ ጥራት/Quality of formwork material/

▶️ለፎርምወርክ ስራ ጥቅም ላይ የዋለው እቃ ያልተጣመመ፣ ያላበጠና ያልጎበጠ ፣ወጥነት ያለው ፣ያልተቀደደና ጥሩ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ሌላ አስፈላጊ ስራ ነው።

⏺3.አቀባዊ ሊኛ/Vertical alignment/

▶️የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ልክ በሚገባ ወደላይ ቀጥ ማለቱን ማረጋገጥ አለበት።

⏺4.አግድም ሊኛ/Horizontal alignment/

▶️የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ከሌሎች ኮለኖች አንጻር ያለው አቀማመጥ፣ ከታወቀ መነሻ በሚገባ ወጥነት ያለው ሆኖ መቀመጡን ማረጋገጥ አለበት።

⏺5.የኮለን ወርድና ስፋት ልክ/Design dimension/

▶️በዲዛይኑ መሰረት የኮለኑን ወርድና ስፋት ከፎርምወርኩ አቀናንሶ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ።

⏺6.ከመነሻው ያለው ርቀት/Distance from reference/center to center/

▶️ከታወቀ መነሻ በመነሳት አንዱ ኮለን ከሌላው ኮለን ርቆ የተቀመጠው በዲዛይኑ መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ።

⏺7.መሃል ገጠምነት/Eccentricity/

▶️ተንጠልጣይ ወለል/Suspended floors/ በሚኖራቸው ግንባታዎች ላይ የላይኛው ወለል ኮለን ከታችኛው ወለል ኮለን ጋር ሴንተራቸው ፍፁም መሃል ገጠም/eccentric/ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

⏺8.ከብረቱ ያለው ተገቢ ርቀት
/Concrete cover/

▶️ለኮንክሪት ሽፋን ዲዛይኑ የሚጠይቀው ተገቢ መጠን፣ በፎርምወርኩና በብረቱ መሃል በልዩ ጡብ/Spacers/ መለየቱን ማረጋገጥ ሌላው በጣም አስፈላጊው ነጥብ ነው።

📌ለተጨማሪ ገፆች ከታች ባሉ ሊንኮች ይቀላቀሉን

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍27❤2👌2
👉ስራን ስለማስተላለፍ (Assignment)

📜የፍ/ህ/ቁ 3201(1)

🚧ሰራን ማስተላለፍ ስንል ምን ማለት ነው?

⏺ከንዑስ ስራተቋራጭነት subcontracting/ ጋር ልዩነቱስ ምንድነው?

▶️ማስተላለፍ/Assignment/ ዋናው የሥራ ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በሙሉ እንዲፈጽምለት ለሶስተኛ ወገን ለሆነ ሲያስተላልፍ ነው፡፡

▶️ከንዑስ ተቋራጭነት ጋር ሁኔታው ተመሳሳይ አይነት ሲሆን ዋና ልዩነቱ ዋና ተቋራጩ ለሌላ ተቋራጭ(ለንዑስ ተቋራጭ) የሚያሰራውን ሙሉውን የግንባታ ስራ መስጠቱ ነው፡፡

🚧በዚህ ውል ውስጥ ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ተቋራጮች ናቸው፡፡

✨ለምሳሌ "a" የተባለ ተቋራጭ "b" ከተባለ አሰሪ ጋር የኮንስትራክሽን ውል ገባ እንበል የግንባታ ስራው ደግሞ ትምህርት ቤት ቢሆን እና ሁለት ብሎክ መማሪያ ህንጻ እና አንድ ሽንት ቤት ግንባታ ቢሆን እንበል እንግዲህ ዋናው ተቋራጭ "ሀ" ከግንባታ ስራው ውስጥ አንዱን ብሎክ መማሪያ ክፍል "c" ለተባለ ተቋራጭ በውል ሰጥቶ ቢያስገነባው በ "a" እና "c" መካከል የሚደረገው ውል የንኡስ ተቋራጭነት ውል ይባላል ማለት ነው፡፡

🚧በሌላ በኩል ምናልባት ዋናው ተቋራጭ "a" ሁሉንም ግንባታ ማለትም ሁለት ብሎክ መማሪያ ህንጻ እና አንድ ሽንት ቤት "d" ለተባለ ተቋራጭ በውል ሰጥቶ ቢያስገነባው በዋናው ተቋራጭ "ሀ" እና "መ" በተባለው ተቋራጭ መካከል የተደረገው ውል በንዑስ ተቋራጭነት ሳይሆን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ ወይም ማስተላለፍ (Assignment) በሚለው የህግ ክፍል የሚጠቃለል ይሆናል ማለት ነወ፡፡

📜የኢትዮጰያ መንግስት ግዢዊች ኤጀንሲ ሰነድ/PPA 2011/ ምን ይላል?

📍PPA 2011 ስለ ንዑስ ተቋራጭነት በአንቀጽ 14 ላይ አስቀምጧል፡፡

⏺በዚህም የንዑስ ተቋራጭነት ውሉ: - በጽሁፍ መሆን እንዳለበት ይገልጻል፡፡

▶️ስለ ንዑስ ተቋራጭነት በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ያልታወቁ (Non nominated) እንደሆነ ዋናው ተቋራጭ ሌሎች ንዑስ ተቋራጮችን የግንባታ ስራ ለማሰራት የአሰሪውን የጽሁፍ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል በሚል ያስቀምጣል፡፡

▶️የንዑስ ተቋራጭነት ውሉም ከዋናው ውል ጋር የተጣጣመ እና በዋናው ውል ጭምር የሚገዛ እንደሚሆን በPPA አንቀጽ 14.3 ላይ ተቀምጧል፡፡

▶️ዋናው ተቋራጭ የአሰሪው መስሪያ ቤት ሳይፈቅድለት የንዑስ ተቋራጭነት ውል የገባ እንደሆነ አሰሪው ፎርማል ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልገው ውልን ማቋረጥ እንደሚችል አንቀጽ 14.8 ላይ ተቀምጧል።

⏺ሌላው ንዑስ ተቋራጩ የግንባታ ስራ ለማከናወን ብቃት የሚያንሰው እንደሆነ አሰሪው መስሪያ ቤት ወይም መሀንዲሱ ዋናውን ተቋራጭ ሌላ ብቃት ያለው ንኡስ ተቋራጭ እንዲያመጣ ወይም ስራውን በራሱ እንዲያከናውን ሊጠይቀው እንደሚችል አንቀጽ 14.9 ይገልጻል፡፡

📜ዓለም አቀፍ የአማካሪ መሃንዲሶች ማህበር ሰነድስ/FIDIC 1999/ ምን ይላል?

📍ፊዲክ ሬድ ቡክ 1999-በዚህ ጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ 4.4 ላይ ዋናው ተቋራጭ ሙሉውን የግንባታ ስራ ለንኡስ ተቋራጭ መስጠት እንደማይችል ተቀምጧል፡፡

⏺እንዲሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ላይ በሌላ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር ንዑስ ተቋራጩ በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ስሙ የተጠቀሰ በሆነ ጊዜ በንኡስ ተቋራጭነት ለማሰራት የመሀንዲሱን ፈቃድ መጠየቅ አይጠበቅበትም፡፡

▶️ሆኖም የታሰበው ንዑስ ተቋራጭ አዲስ እና በዋናው ውል ስሙ ያልተጠቀሰ የሆነ እንደሆነ በቅድሚያ የመሀንዲሱን ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ ይሆናል፡፡

▶️ዋናው ተቋራጭ ለመሀንዲሱ በተለይ ንዑስ ተቋራጩ ለሚሰራው ስራ የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን/ኮመንስመንት ዴት/ ተብሎ የታሰበውን ጊዜ ከ28 ቀን ባላነሰ ጊዜ ማስታወቅ ሲኖርበት ንኡስ ተቋራጩ በትክክል በሳይት ላይ ስራ የጀመረበትንም ቀን ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

📜Nominated subcontractors በሚመለከት በአንቀጽ 5.1 ላይ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡

▶️በዚህም መሰረት ኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተር የሚባለው በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተር መሆኑ የተገለጸ እንደሆነ ወይም ኢንጅነሩ ለተቋራጩ ንዑስ ተቋራጭ መርጦለት እንዲያሰራው ያዘዘው የሆነ እንደሆነ ነው፡፡

⏺ለኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተሩ ክፍያ የሚፈጸምለት በንኡስ ተቋራጭነት ውሉ አግባብ በመሀንዲሱ በሚሰጥ የክፍያ ሰርተፍኬት መሰረት ሲሆን ክፍያውን የሚፈጽመውም ዋናው ተቋራጭ ስለመሆኑ አንቀጽ 5.3 ላይ ተቀምጧል፡፡

#ConstructionLaw

🌟ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ🙏

📌ለተጨማሪ ገፆች ከታች ባሉ ሊንኮች ይቀላቀሉን

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍14❤4👏1
ግንባታው ተቋርጦ የነበረውን የደብረ ብርሃን አጠቃላይ ሆስፒታልን ለማጠናቀቅ በአዲስ ውል ተፈፀመ፡፡

ግንባታው በአማራ ህንፃ ስራዎች ድርጅት በ2009 ዓ.ም የተጀመረውና በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታው ለ6 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የደብረ ብርሃን አጠቃላይ ሆስፒታል በአዲስ ግንባታውን ለማስቀጠል ርክክብ ተደርጓል።

ባለሦስት ወለል የሆነው ሆስፒታሉ አሁን ላይ ቀድሞ ግንባታውን ከያዘው የአማራ ህንፃ ስራዎች ድስጅት ጋር የነበረው ውል ተቋርጦ በአዲስ ለመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ተሰጥቶ ውል መገባቱን በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የሰሜን ሸዋ ዞን ክላስተር አስተባባሪ አቶ አሸናፊ ሙጬ ገልጸዋል።

ለመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውለታ የተሰጠው በ700 ቀናት ውስጥ ግንባተውን አጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ እንዲያደርግ ነው ያሉት አስተባባሪው፤ ከዚህ በኋላ ላለው የግንባታ ሂደትም 988 ሚልየን ብር በጀት ተይዞለትን ርክክብ ተፈፅሞ ወደስራ እንዲገባ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የዚህ ሆስፒታል መጠናቀቅ አሁን ያለውን የመታከሚያ አልጋ ቁጥር ወደ 500 አልጋ እንደሚያሳድገው የደብረ ብርሃን ኮፕፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አስማረ ሳሙኤል ጠቅሰው፤ ሆስፒታሉ እጅግ ዘመናዊ በመሆኑ ብዙ ችግሮቻችንን እንደሚያቃልል ገልጸዋል፡፡

@etconp
👍13❤3💯1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉Look this video

🚧Best concrete bricks building tutorial

📌Put your thoughts advantage and disadvantages of this bricks.


📍Contact me 🗣 @ETCONpBOT

@etconp
👏6❤2
👉የብረት ክብደት ማስያ ፎርሙላ ግኘታ
/Derivation of weight of steel/

m=[D^2*L]/162.2

🚧የሚታወቅ ምን አለን?

- density=mass/volume
-የብረት density=7850kg/m3
-የብረት ይዘት መለኪያ=[πD^2L]/4

⏺እዚህ ጋር ማወቅ ያለብን

D-የብረት ዲያሜትር በሚሊሜትር እና
L-የብረት ርዝመት በሜትር ማለት ስለሆነ፣
L ን-በ1000 ማባዛት ወይም D ን- ለ1000 ማካፈል ይኖርብናል።

⏺በመሆኑም

√ d=m/v

√ 7850kg/m3=m/[πD^2L]/4

📍m=[D^2*L]/162.2 ይሆናል ማለት ነው።

📌ለምሳሌ: አንድ ሜትር ርዝመት ያለው ባለ 20mm ዲያሜትር ብረት ክብደቱ ስንት ነው?

m=[D^2*L]/162.2

=[[20]^2* 1]/162.2

=2.466kg ይሆናል።


🌟ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ🙏

📌ለተጨማሪ ገፆች ከታች ባሉ ሊንኮች ይቀላቀሉን

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍26👏2❤1
📌ትብብርን ስለመጠየቅ ይመለከታል

✋ጤና ይስጥልኝ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች የ ኮንስትራክሽን ተማሪ ነኝ በአሁን ወቅት MSc ለማጠናቀቅ የመመረቂያ ጥናት በመስራት ላይ እገኛለሁ ለዚህም ይረዳኝ ዘንድ የዚህ ቻናል ቤተሰብ ይህ ከታች ያለው ፎርም እንድትሞሉልኝ በአክብሮት እጠይቃለው ፤ በቅድሚያ ለምታደርጉልኝ ትብብር እጅግ በጣም አመሰግናለው።

💫ሊንኩ ከዚህ በታች የተቀመጠው ነው

https://forms.gle/tpPwGxpqTzCy8k5r5
❤6👍3
👉ከውል የማፈንገጥ ሂደት የሚያስከትላቸው ችግሮችና፣ የመፍትሄ ስርዓቶች/Damage, Breach of Contract and Remedies/

1.ከውል ማፈንደጥ ስንል ምን ማለት ነው?

🚧በመካከላቸው ህጋዊ የውል ስምምነት ካደረጉ ተዋዋይ አካላት መካከል አንደኛው ወገን በውሉ የተቀመጡ መሠረታዊ  ግዴታዎችን ሆነ ብሎ በማወቅ ወይም ባለማወቅ ያለምንም የህግ ድጋፍ ወይም ማብራሪያ በሌለው ምክንያት አለመፈጸም ወይም በውል በተቀመጡ የውል ሁኔታዎች መሠረት መስራት አለመቻልን ከውል ማፈንገጥ /breach of contract/ ይባላል፡፡

🚧ይህ ከውል የማፈንገጥ ሁኔታ በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖቸ መካከል ግጭት እንዲነሳ የሚያደርግ ነው፡፡እነዚህን ከውል በማፈንገጥ ምክንያት የሚነሱ ግጭቶች በፍርድ ቤት የመፍታት ሂደት ብዙ ገንዘብ የሚጠይቅና ጊዜ አባካኝ ከመሆኑም ባሻገር ጉዳዩ እስኪቋጭ አዕምሮን ዕረፍት ሊነሳ የሚችልና የሚያስጨንቅ ነው፡፡

2.ከውል በማፈንገጥ የተጎጂው አማራጭ መብቶች

🚧በአንድ ተዋዋይ ወገን ከውል ማፈንገጥ ምክንያት ውል ያልተፈጸመለት ወገን ራሱን ለመጠበቅ የሚከተሉትን አማራጭ መንገዶች ሊጠቀም ይችላል፡፡
(ፍትሐ ብሄር ሕግ ቁጥር 1771)

-ለደረሰበት ጉዳት ተመጣጣኝ የጉዳት መቀጮ (ፍብሕቁ 1771(2)

-ውል አስገድዶ ማስፈጸም (ፍብሕቁ 1771(1)

-ውል እንዲፈርስለት መጠየቅ (ፍብሕቁ 1771(1)

3.የጉዳት መቀጮ (ፍትሐ ብሄር ሕግ ቁጠር 2360)

🚧የጉዳት መቀጮ ተጎጂው በድርጊቱ የደረሰበትን የጥቅም መቅረት ወይም መቀነስ ለማመዛዘንና ለጉዳቱ መነሻ የሆነው ተግባር ባይፈጸም ኖሮ ተጎጂ ያገኝ የነበረውን ኢኮኖሚያዊ አቋም ለመጠበቅ በታቀደ ዓላማ የሚተገበር አሰራር ነው፡፡ከውል ማፍረስ ጋር ተያይዞ የሚታየው የጉዳት መቀጮ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ካለው ተነጻጻሪ ግዴታ አኳያ የአንደኛው ወገን ግዴታውን አለማክበር በሌላው ተዋዋይ ወገን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ከሚያመጣው አሉታዊ ውጤት አንጻር ነው፡፡ይህ ከውል አፈንጋጩ ግዴታውን በተፈለገው ጊዜና በሚፈለገው አኳኆን አለመፈጸም ለተጎጂው ተመጣጣኝ የሆነ የጉዳት መቀጮ የመጠየቅ መብት ያስፈልገዋል፡፡

🚧ምንጊዜም ቢሆን የተጎጂ ኪሳራ ውሉ በተፈለገው ጊዜና አኳኋን ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ተጎጂው ሊያገኝ ይችል የነበረው ጥቅም የሚያሟላና የሚያካክስ ሊሆን ይገባዋል፡፡

⏺ከውል በማፈንገጥ ምክንንት የሚነሱ ግጭቶችን ለማርጋት የሚኬድባቸው የተለያዩ ዓይነት የመፍትሄ ስርዓቶች አሉ፡፡

⏺ከውል በማፈንገጥ ምክንያት የሚነሳ ቅሬታ የህግ ተቀባይነት ሲያገኝ፣ በህግ ኪሳራን የማስመለስ ሂደቱ ለሚደርሰው ጉዳት ካሳ የማስከፈል ሂደቱ ከዚህ ቀጥሎ በተቀመጡ መንገዶች መሠረት ይሆናል፡፡    
                                                                   
🌟እነዚህም ፡- 

i. የተመጣጣኝ ካሳ የኪሳራ መቀጮ/Compensatory Damages/

▶️በተመጣጣኝ ካሳ የኪሳራን መቀጫ፣ ከውል ያፈነገጠው ወገን ለተጎጂው የሚከፍለው መቀጫ የደረሰው ኪሳራ መጠን ተለክቶ ለደረሰው ኪሳራው ልከኛ የሆነ ካሳ በመክፈል የሚደረግ የመቀጫ ዓይነት ነው፡፡

▶️በዚህ ሂደት የሚደረግ የኪሳራ ወይም የጉዳት መቀጮ በተለካው ጉዳት ልክ ስለሚፈጸም ልከኛ መቀጮ/   actual damages/ ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡

ii. በአስተማሪ የቅጣት ርምጃ የሚደረገረግ የጉዳት መቀጮ/Punitive Damages/

▶️ከተመጣጣኝ ካሳ የጉዳት መቀጮ በተለየ ከውል ያፈነገጠው ወገን ጥፋቱን እንዲያርምና እንዳይደግም ማስተማሪያ እንዲሆነው፣ ለሌሎችም ውጫዊ አካላት ጭምር ምሳሌ እንዲሆን ተብሎ የሚሰጠው ወይም የሚጣል  የቅጣት ወይም የጉዳት መቀጮ ዓይነት ነው፡፡

▶️አስተማሪ የቅጣት ርምጃ በተመጣጣን ካሳ የጉዳት መቀጮ ላይ ተጨማሪ ሆኖ ሊሰጥ ይችላል፡፡

▶️ይህ ዓይነቱ የጉዳት መቀጮ አልፎ አልፎ ከተመጣጣኝ ካሳ  ጉዳት መቀጮ ውጪ ለብቻው ሊፈጸም ይችላል፡፡

iii. የጊዜ ጉዳት መቀጮ(Liquidated damages/Damage from late completion)

▶️ይህ ዓይነቱ የጉዳት መቀጮ የሚተገበረው ከተዋዋይ ወገኖች አንደኛው ሥራውን በውሉ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለመፈጸም ሳይችል ሲቀር ወይም ስራውን በማዘግየት ከውል ያፈነገጠ እንደሆነ ነው፡፡

iv. አነስተኛ መጠን የጉዳት መቀጮ (Nominal damages)

▶️ከተዋዋይ ወገኖች በአንዱ የተፈጠረው ከውል የማፈንገጥ ሂደት የደረሰው ጉዳት ለታለፍ የሚችልና ውል በተጣሰበት ወገን ላይ የሚያደርሰው ኪሳራ ይህ ነው የማይባል ወይም የሚታለፍ (insignificant) እና በምክር ወይም በማስጠንቀቀቂያ የሚታለፍ ሲሆን ይህ ዓይነቱ የጉዳት መቀጮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

#ConstructionLAW

❤️ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ🙏

@etconp
👍16👏4🙏2❤1
🌟የዘንድሮ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላቹ❤

💫እስቲ ያሳለፋችሁትን አምስት አመታት አስታውሷቸው...

⏺ለመጀመርያ ጊዜ የዩንቨርስቲን ደጅ ስትረግጡ ምን እንደተሰማችሁ... የመጀመርያ የዶርም አዳራችሁ ...ጓደኞቻችሁን እንዴት እንደተዋወቃችሁ... የመጀመርያ ክላሳችሁን ... ችከላውን መጨናነቁን ... ደሞ ለብሬክ መሄዱን የቤተሰብ ናፍቆት...ከብሬክ ስትመለሱ የሚሰማችሁ "ቀፋፊ" ስሜት ኧህህ...

"እንኳን ደስ አላችሁ" እየተባለ መነሳንሳችሁን ከቀኝ ወደ ግራ ስታዞሩት ይኽ ሁሉ የስሜት እና የኩነት መፈራረቆች ለዝች ቀን ለመድረስ እንደሆነ ትረዱታላችሁ... በእርግጥ ድስ የሚያሰኝ ደግሞም ቅር የሚል ስሜት ይሰማችሁ ይሆናል ከአዳራሽ ወታችሁ የእናት እና አባታችሁን ፍቅር እና ደስታ የሚንጠፈጠፍባቸውን አይኖች እስክታዩ... እንዲሁም ከ ክላስ እና ዶርም ሜቶቻቹ ስትለያዩ😢

😍ዛሬ ቀናችሁ ናት በደስታችሁ ደስ ያላቸውን ስታዩ ምናልባት የእንባ ዘለላዎች ከጉንጫችሁ ሲወርዱ እንዳትደናገጡ የሚወዱትን ሰው ማስደሰት የሚሰጠው የደስታ ምልክት ነው...።

❤️በደስታችሁ ደስ ብሎናል ... በስኬታችሁ ኮርተናል

✨የ ኢትዮጵያውያን ኮንስትራክሽን ስራ ባለሞያዎች - ETCONp አባላት ... ብሩህ ነገን ይመኝላቹዋል🙏

@etconp
❤13👍5
Geological formation of soils and types

አለም 3 layer አላት core, mantel and crust

Crust (የብስ) ሁለት ክፍል አለ አለት እና አፈር

3 አይነት አለት አለ

፩. IGNEOUS 🪨 ROCK - ከ እሳተ ጎመራ ፍንጣቂ መቀዝቀዝ የሚፈጠር አለት ለምሳሌ :- ባልጩት

2. SEDIMENTARY 🪨 ROCK- በ መሟሟት ከዛም በመዝቀጥ የሚፈጠር የ አለት አይነት ለምሳሌ:- ጂፕሰም መስሪያ ላይምስቶን

3. METAMORPHIC 🪨 ROCK - በሙቀት መጠን መጨመርን ተከትሎ ወይም በግፊት ከ አንዱ የ አለት አይነት ወደሌላኛው ሲለወጥ ለምሳሌ :- እምነበረድ

የትኛው የ አለት አይነት ጠንካራ ይመስላችኋል ?


@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432
👍19❤2💯2👏1
What are Gabions?
A Gabion is a box-shaped container made of tough hexagonal steel wire mesh strengthened by selvedges of heavier wire. It has a lid that you open to fill with rocks and is also known as a Gabion basket.

🔸Gabions retain walls, preventing erosion, reducing water pressure, and increasing stability.

🔸Gabions protect against soil erosion on slopes and embankments while enhancing stability.
🔸 Gabions filled with sound-absorbing materials act as noise barriers, reducing noise pollution.
🔸Gabions in flood-prone areas construct durable and permeable levees or embankments for flood control.

🔸Gabions have aesthetic purposes, creating visually appealing features for gardens, parks, or public spaces. They can be arranged in various forms, such as walls, seats, columns, or sculptures.
@etconp
👍17
👋OPC (Ordinary Portland Cement) and PPC (Portland Pozzolana Cement) are two types of cement used in construction.

👉The main differences between OPC and PPC are:

1. Raw materials: OPC is made from limestone, whereas PPC is made from a mixture of limestone and pozzolanic material such as fly ash or volcanic ash.

2. Strength: OPC has higher early strength, whereas PPC has higher long-term strength due to its pozzolanic material content.

3. Setting time: OPC has a shorter setting time than PPC.

4. Durability: PPC has better durability and resistance to chemical attacks than OPC.

5. Cost: PPC is generally cheaper than OPC due to the lower cost of raw materials used in its production.

6. Environmental impact: PPC has a lower carbon footprint than OPC due to the use of pozzolanic material, which reduces the need for clinker production, a major contributor to greenhouse gas emissions.

Overall, the choice between OPC and PPC depends on the specific requirements of the construction project and the availability of raw materials in the region.

@etconp
👍29❤8😢2💯1🏆1
👉Building construction

🌟Masonry

💫Definitions of terms

1. Course : A course is a horizontal layer of bricks stones 

2. Bed : the surface of a stone perpendicular to the line of pressure of (lower surface of bricks or stones in each course)

3. Back : The inner surface of wall not exposed is called back. 
The material forming back is known as backing 

4. Face : The exterior of the wall exposed to weather is known 
as face. The material used in the facing of wall is known as 
facing

5. Hearting : It is the interior portion of a wall between facing 
and backing 

6. Head : It is a brick or stone, which lies with its greatest length  at right angles to the face of the work. 

7. Stretcher : It is a brick or a stone which lies with its congest 
side parallel to the face of the work 

8. Bond : The method of arranging bricks so that the individual  units are tied together
 
9. Spalls : The chips of stones used for filling the interstices in 
stone masonry
 
10. Quoins : The stones used for the corners of walls of structure 

11. Bat : It is a portion of a brick cut across the width. 

12. Closer: It is the portion of a brickcut in such a manner that its  one long face remains uncut 

13. Queen closer: it is the portion of a brick obtained by cutting a  brick length-wise into two portions

14. King closer: It is the portion of brick obtained by cutting off 
the triangular piece between the centre of one end and the 
centre of one side. 

15. Bevelled closer: It is the portion of a brick in which the 
whole length of the brick is bevelled for maintaining half 
width at one end and full width at the other 

16. Frog : It is an indentation or depression on the top face of a 
brick made with the object of forming a key for the mortar. 

17. Sill : It is a horizontal stone, concrete or wood, employed for 
the purpose of shedding off rain water from the face of wall 
immediately below the window opening 

18. Corbel : It is the extension of one or more course of stone or 
brick from the face of a wall to serve as a support for wall 
plates

19. Templates : Pieces of stones placed under the end of a beam 
to distribute load over a greater area. 

20. Coping : It is the course placed upon the exposed top of an  external wall to prevent the seepage of water 

21. Buttress : It is a sloping or stepped masonry projection from a  tall wall intended to strengthen the wall against the thrust of a roof.

@etconp
👍18👏4❤2🕊1
👉የአክሱም ሐውልት አስቸኳይ ጥገና ካልተደረገለት ሊወድቅ ይችላል ተባለ

በትግራይ ክልል የሚገኘው የአክሱም ሐውልት አስቸኳይ ጥገና ካልተደረገለት ሊወድቅ  ይችላል ሲል የአክሱም ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ለአዲስ ማለዳ ገልጿል፡፡

የአክሱም ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ገብረመድኅን ፍፁምብርሃን ሐውልቶቹን የተሸከመዉ ጥንታዊ የመቃብር ሥፍራ በክረምት ዉሃ እና ሌሎች ምክንያቶች መፈራረሱን ጠቅሰው፤ ከጦርነቱ በፊት ከጣልያን በመጡ ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎ በጣሊያን መንግሥት ዕድሳት ይደረግለታል ተብሎ እንደነበር ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ሆኖም የጥገና ሥራውን ይሰራል የተባለው ቡድን ከዚያ በኋላ ወደ ሥፍራው እንዳልተመለሰ ገልጸዋል።

በአክሱም ከተማ ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተሰሩ በርካታ ሐውልቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ኃላፊው፤ ከእነዚህ መካከል በመጠኑ ትልቅ የሆነው እና ቁጥር ሦስት ተብሎ የሚታወቀው ሐውልት በብረት ምሶሶዎች ተደግፎ ተንጋዶ እንደሚታይ ነው የጠቆሙት።

ስለሆነም ሐውልቱ አስቸኳይ ጥገና እና ዕድሳት ካልተደረገለት ሊወድቅ ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

ሐውልቶቹን ተሸከሞ ያለው "ሞዘልየም" የተሰኘው ጥንታዊ መቃብር በጊዜያዊነት ለመጠገን የፌዴራል መንግሥት ከሳምንት በፊት መጠነኛ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው፤ "ሆኖም ግን ቅርሱን ለመታደግ ይህ ዘላቂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም።" ሲሉ ተደምጠዋል።

በተጨማሪም በዓመት እስከ 25 ሺሕ የሚገመቱ የውጭ አገር ቱሪስቶች ይጎበኙት ነበር የተባለው ከአክሱም ሐወልቶች አቅራቢያ የሚገኝ ሙዚየም፤ በጦርነቱ ወቅት በደረሰበት ከፍተኛ ዘረፋ እና ውድመት እስካሁን ምንም ዓይነት ጥገና እንዳልተደረገለት አብራርተዋል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የአክሱም አውሮፕላን ማረፍያ እንዲሁ እስካሁን እድሳት እንዳልተደረገለት እና ወደ አገልገሎት እንዳልተመለሰ ገልጸዋል፡፡

የአክሱም ከተማ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ገቢ የምታገኘው ከቱሪዝሙ ዘርፍ ነው ያሉት ኃላፊው፤ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ አካባቢው ሰላም ቢሆንም ወደ ከተማዋ የሚመጣ ጎብኚ አለመኖሩን ተናግረዋል።

በዋናነት የሐወልቶቹ አስተዳደርና ጥገና ጉዳይ የሚመለከተው የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ልዑካኑን ወደ አክሱም ከተማ በመላክ የሐውልቶችን ሁኔታ መመልከቱንና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የሚላክ የጥናት ውጤት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም ሐውልቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመጠገን ከክልሉ አቅም በላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ የፌደራል መንግሥቱ ጉዳዩን አጽንኦት ሰጥቶ ሊከታተለው እና ቅርሱን ሊታደገው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Via አዲስ ማለዳ

@etconp
👍9💔5❤3
ከሕንፃ ከፍታና ፕላን አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚደረግ ግንባታ እንዲቆም ታዘዘ

⚡️በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ራማዳ ሆቴል አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ ምንም ዓይነት ግንባታ እንዳይፈቀድና የተፈቀዱ ሕንፃዎችም ግንባታ እንዲቆም፣ የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አዟል፡፡

⚡️ተቋሙ ውሳኔውን ለማስተላለፍ የወሰነው ካለፈው ዓመት ጀምሮ የተለያዩ የከተማ ስታንዳርዶችን በከተማዋ ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ኮሚሽን አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከሕንፃ ከፍታና የፕላን አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ጥናት እንዲደረግ አቅጣጫ በመስጠቱ ነው ተብሏል፡፡

⚡️ላልተወሰነ ጊዜ የግንባታ ፈቃድ እንዳይፈቀድ ውሳኔ የተላለፈበት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ራማዳ ሆቴል ግራና ቀኝ የተለያዩ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ዙሪያ ነው፡፡

⚡️የተለያዩ አገሮች ኤምባሲዎችና ዲፕሎማቶች ያሉበት አካባቢ በመሆኑና በነባሩ ፕላንና አሠፋፈር ስታንዳርዳይዝ የሆኑ ቤቶች ስላሉበት፣ ከሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ምንም ዓይነት ግንባታ እንዳይፈቀድ ባለሥልጣኑ ለቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት በጻፈው ደብዳቤ አዟል፡፡

Via - Alain

@etconp
👍9❤4