Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የብረት ክብደት ማስያ ፎርሙላ ግኘታ
/Derivation of weight of steel/

m=[D^2*L]/162.2

🚧የሚታወቅ ምን አለን?

- density=mass/volume
-የብረት density=7850kg/m3
-የብረት ይዘት መለኪያ=[πD^2L]/4

⏺እዚህ ጋር ማወቅ ያለብን

D-የብረት ዲያሜትር በሚሊሜትር እና
L-የብረት ርዝመት በሜትር ማለት ስለሆነ፣
L ን-በ1000 ማባዛት ወይም D ን- ለ1000 ማካፈል ይኖርብናል።

⏺በመሆኑም

√ d=m/v

√ 7850kg/m3=m/[πD^2L]/4

📍m=[D^2*L]/162.2 ይሆናል ማለት ነው።

📌ለምሳሌ: አንድ ሜትር ርዝመት ያለው ባለ 20mm ዲያሜትር ብረት ክብደቱ ስንት ነው?

m=[D^2*L]/162.2

=[[20]^2* 1]/162.2

=2.466kg ይሆናል።


🌟ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ🙏

📌ለተጨማሪ ገፆች ከታች ባሉ ሊንኮች ይቀላቀሉን

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍26👏2❤1
📌ትብብርን ስለመጠየቅ ይመለከታል

✋ጤና ይስጥልኝ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች የ ኮንስትራክሽን ተማሪ ነኝ በአሁን ወቅት MSc ለማጠናቀቅ የመመረቂያ ጥናት በመስራት ላይ እገኛለሁ ለዚህም ይረዳኝ ዘንድ የዚህ ቻናል ቤተሰብ ይህ ከታች ያለው ፎርም እንድትሞሉልኝ በአክብሮት እጠይቃለው ፤ በቅድሚያ ለምታደርጉልኝ ትብብር እጅግ በጣም አመሰግናለው።

💫ሊንኩ ከዚህ በታች የተቀመጠው ነው

https://forms.gle/tpPwGxpqTzCy8k5r5
❤6👍3
👉ከውል የማፈንገጥ ሂደት የሚያስከትላቸው ችግሮችና፣ የመፍትሄ ስርዓቶች/Damage, Breach of Contract and Remedies/

1.ከውል ማፈንደጥ ስንል ምን ማለት ነው?

🚧በመካከላቸው ህጋዊ የውል ስምምነት ካደረጉ ተዋዋይ አካላት መካከል አንደኛው ወገን በውሉ የተቀመጡ መሠረታዊ  ግዴታዎችን ሆነ ብሎ በማወቅ ወይም ባለማወቅ ያለምንም የህግ ድጋፍ ወይም ማብራሪያ በሌለው ምክንያት አለመፈጸም ወይም በውል በተቀመጡ የውል ሁኔታዎች መሠረት መስራት አለመቻልን ከውል ማፈንገጥ /breach of contract/ ይባላል፡፡

🚧ይህ ከውል የማፈንገጥ ሁኔታ በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖቸ መካከል ግጭት እንዲነሳ የሚያደርግ ነው፡፡እነዚህን ከውል በማፈንገጥ ምክንያት የሚነሱ ግጭቶች በፍርድ ቤት የመፍታት ሂደት ብዙ ገንዘብ የሚጠይቅና ጊዜ አባካኝ ከመሆኑም ባሻገር ጉዳዩ እስኪቋጭ አዕምሮን ዕረፍት ሊነሳ የሚችልና የሚያስጨንቅ ነው፡፡

2.ከውል በማፈንገጥ የተጎጂው አማራጭ መብቶች

🚧በአንድ ተዋዋይ ወገን ከውል ማፈንገጥ ምክንያት ውል ያልተፈጸመለት ወገን ራሱን ለመጠበቅ የሚከተሉትን አማራጭ መንገዶች ሊጠቀም ይችላል፡፡
(ፍትሐ ብሄር ሕግ ቁጥር 1771)

-ለደረሰበት ጉዳት ተመጣጣኝ የጉዳት መቀጮ (ፍብሕቁ 1771(2)

-ውል አስገድዶ ማስፈጸም (ፍብሕቁ 1771(1)

-ውል እንዲፈርስለት መጠየቅ (ፍብሕቁ 1771(1)

3.የጉዳት መቀጮ (ፍትሐ ብሄር ሕግ ቁጠር 2360)

🚧የጉዳት መቀጮ ተጎጂው በድርጊቱ የደረሰበትን የጥቅም መቅረት ወይም መቀነስ ለማመዛዘንና ለጉዳቱ መነሻ የሆነው ተግባር ባይፈጸም ኖሮ ተጎጂ ያገኝ የነበረውን ኢኮኖሚያዊ አቋም ለመጠበቅ በታቀደ ዓላማ የሚተገበር አሰራር ነው፡፡ከውል ማፍረስ ጋር ተያይዞ የሚታየው የጉዳት መቀጮ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ካለው ተነጻጻሪ ግዴታ አኳያ የአንደኛው ወገን ግዴታውን አለማክበር በሌላው ተዋዋይ ወገን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ከሚያመጣው አሉታዊ ውጤት አንጻር ነው፡፡ይህ ከውል አፈንጋጩ ግዴታውን በተፈለገው ጊዜና በሚፈለገው አኳኆን አለመፈጸም ለተጎጂው ተመጣጣኝ የሆነ የጉዳት መቀጮ የመጠየቅ መብት ያስፈልገዋል፡፡

🚧ምንጊዜም ቢሆን የተጎጂ ኪሳራ ውሉ በተፈለገው ጊዜና አኳኋን ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ተጎጂው ሊያገኝ ይችል የነበረው ጥቅም የሚያሟላና የሚያካክስ ሊሆን ይገባዋል፡፡

⏺ከውል በማፈንገጥ ምክንንት የሚነሱ ግጭቶችን ለማርጋት የሚኬድባቸው የተለያዩ ዓይነት የመፍትሄ ስርዓቶች አሉ፡፡

⏺ከውል በማፈንገጥ ምክንያት የሚነሳ ቅሬታ የህግ ተቀባይነት ሲያገኝ፣ በህግ ኪሳራን የማስመለስ ሂደቱ ለሚደርሰው ጉዳት ካሳ የማስከፈል ሂደቱ ከዚህ ቀጥሎ በተቀመጡ መንገዶች መሠረት ይሆናል፡፡    
                                                                   
🌟እነዚህም ፡- 

i. የተመጣጣኝ ካሳ የኪሳራ መቀጮ/Compensatory Damages/

▶️በተመጣጣኝ ካሳ የኪሳራን መቀጫ፣ ከውል ያፈነገጠው ወገን ለተጎጂው የሚከፍለው መቀጫ የደረሰው ኪሳራ መጠን ተለክቶ ለደረሰው ኪሳራው ልከኛ የሆነ ካሳ በመክፈል የሚደረግ የመቀጫ ዓይነት ነው፡፡

▶️በዚህ ሂደት የሚደረግ የኪሳራ ወይም የጉዳት መቀጮ በተለካው ጉዳት ልክ ስለሚፈጸም ልከኛ መቀጮ/   actual damages/ ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡

ii. በአስተማሪ የቅጣት ርምጃ የሚደረገረግ የጉዳት መቀጮ/Punitive Damages/

▶️ከተመጣጣኝ ካሳ የጉዳት መቀጮ በተለየ ከውል ያፈነገጠው ወገን ጥፋቱን እንዲያርምና እንዳይደግም ማስተማሪያ እንዲሆነው፣ ለሌሎችም ውጫዊ አካላት ጭምር ምሳሌ እንዲሆን ተብሎ የሚሰጠው ወይም የሚጣል  የቅጣት ወይም የጉዳት መቀጮ ዓይነት ነው፡፡

▶️አስተማሪ የቅጣት ርምጃ በተመጣጣን ካሳ የጉዳት መቀጮ ላይ ተጨማሪ ሆኖ ሊሰጥ ይችላል፡፡

▶️ይህ ዓይነቱ የጉዳት መቀጮ አልፎ አልፎ ከተመጣጣኝ ካሳ  ጉዳት መቀጮ ውጪ ለብቻው ሊፈጸም ይችላል፡፡

iii. የጊዜ ጉዳት መቀጮ(Liquidated damages/Damage from late completion)

▶️ይህ ዓይነቱ የጉዳት መቀጮ የሚተገበረው ከተዋዋይ ወገኖች አንደኛው ሥራውን በውሉ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለመፈጸም ሳይችል ሲቀር ወይም ስራውን በማዘግየት ከውል ያፈነገጠ እንደሆነ ነው፡፡

iv. አነስተኛ መጠን የጉዳት መቀጮ (Nominal damages)

▶️ከተዋዋይ ወገኖች በአንዱ የተፈጠረው ከውል የማፈንገጥ ሂደት የደረሰው ጉዳት ለታለፍ የሚችልና ውል በተጣሰበት ወገን ላይ የሚያደርሰው ኪሳራ ይህ ነው የማይባል ወይም የሚታለፍ (insignificant) እና በምክር ወይም በማስጠንቀቀቂያ የሚታለፍ ሲሆን ይህ ዓይነቱ የጉዳት መቀጮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

#ConstructionLAW

❤️ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ🙏

@etconp
👍16👏4🙏2❤1
🌟የዘንድሮ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላቹ❤

💫እስቲ ያሳለፋችሁትን አምስት አመታት አስታውሷቸው...

⏺ለመጀመርያ ጊዜ የዩንቨርስቲን ደጅ ስትረግጡ ምን እንደተሰማችሁ... የመጀመርያ የዶርም አዳራችሁ ...ጓደኞቻችሁን እንዴት እንደተዋወቃችሁ... የመጀመርያ ክላሳችሁን ... ችከላውን መጨናነቁን ... ደሞ ለብሬክ መሄዱን የቤተሰብ ናፍቆት...ከብሬክ ስትመለሱ የሚሰማችሁ "ቀፋፊ" ስሜት ኧህህ...

"እንኳን ደስ አላችሁ" እየተባለ መነሳንሳችሁን ከቀኝ ወደ ግራ ስታዞሩት ይኽ ሁሉ የስሜት እና የኩነት መፈራረቆች ለዝች ቀን ለመድረስ እንደሆነ ትረዱታላችሁ... በእርግጥ ድስ የሚያሰኝ ደግሞም ቅር የሚል ስሜት ይሰማችሁ ይሆናል ከአዳራሽ ወታችሁ የእናት እና አባታችሁን ፍቅር እና ደስታ የሚንጠፈጠፍባቸውን አይኖች እስክታዩ... እንዲሁም ከ ክላስ እና ዶርም ሜቶቻቹ ስትለያዩ😢

😍ዛሬ ቀናችሁ ናት በደስታችሁ ደስ ያላቸውን ስታዩ ምናልባት የእንባ ዘለላዎች ከጉንጫችሁ ሲወርዱ እንዳትደናገጡ የሚወዱትን ሰው ማስደሰት የሚሰጠው የደስታ ምልክት ነው...።

❤️በደስታችሁ ደስ ብሎናል ... በስኬታችሁ ኮርተናል

✨የ ኢትዮጵያውያን ኮንስትራክሽን ስራ ባለሞያዎች - ETCONp አባላት ... ብሩህ ነገን ይመኝላቹዋል🙏

@etconp
❤13👍5
Geological formation of soils and types

አለም 3 layer አላት core, mantel and crust

Crust (የብስ) ሁለት ክፍል አለ አለት እና አፈር

3 አይነት አለት አለ

፩. IGNEOUS 🪨 ROCK - ከ እሳተ ጎመራ ፍንጣቂ መቀዝቀዝ የሚፈጠር አለት ለምሳሌ :- ባልጩት

2. SEDIMENTARY 🪨 ROCK- በ መሟሟት ከዛም በመዝቀጥ የሚፈጠር የ አለት አይነት ለምሳሌ:- ጂፕሰም መስሪያ ላይምስቶን

3. METAMORPHIC 🪨 ROCK - በሙቀት መጠን መጨመርን ተከትሎ ወይም በግፊት ከ አንዱ የ አለት አይነት ወደሌላኛው ሲለወጥ ለምሳሌ :- እምነበረድ

የትኛው የ አለት አይነት ጠንካራ ይመስላችኋል ?


@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432
👍19❤2💯2👏1
What are Gabions?
A Gabion is a box-shaped container made of tough hexagonal steel wire mesh strengthened by selvedges of heavier wire. It has a lid that you open to fill with rocks and is also known as a Gabion basket.

🔸Gabions retain walls, preventing erosion, reducing water pressure, and increasing stability.

🔸Gabions protect against soil erosion on slopes and embankments while enhancing stability.
🔸 Gabions filled with sound-absorbing materials act as noise barriers, reducing noise pollution.
🔸Gabions in flood-prone areas construct durable and permeable levees or embankments for flood control.

🔸Gabions have aesthetic purposes, creating visually appealing features for gardens, parks, or public spaces. They can be arranged in various forms, such as walls, seats, columns, or sculptures.
@etconp
👍17
👋OPC (Ordinary Portland Cement) and PPC (Portland Pozzolana Cement) are two types of cement used in construction.

👉The main differences between OPC and PPC are:

1. Raw materials: OPC is made from limestone, whereas PPC is made from a mixture of limestone and pozzolanic material such as fly ash or volcanic ash.

2. Strength: OPC has higher early strength, whereas PPC has higher long-term strength due to its pozzolanic material content.

3. Setting time: OPC has a shorter setting time than PPC.

4. Durability: PPC has better durability and resistance to chemical attacks than OPC.

5. Cost: PPC is generally cheaper than OPC due to the lower cost of raw materials used in its production.

6. Environmental impact: PPC has a lower carbon footprint than OPC due to the use of pozzolanic material, which reduces the need for clinker production, a major contributor to greenhouse gas emissions.

Overall, the choice between OPC and PPC depends on the specific requirements of the construction project and the availability of raw materials in the region.

@etconp
👍29❤8😢2💯1🏆1
👉Building construction

🌟Masonry

💫Definitions of terms

1. Course : A course is a horizontal layer of bricks stones 

2. Bed : the surface of a stone perpendicular to the line of pressure of (lower surface of bricks or stones in each course)

3. Back : The inner surface of wall not exposed is called back. 
The material forming back is known as backing 

4. Face : The exterior of the wall exposed to weather is known 
as face. The material used in the facing of wall is known as 
facing

5. Hearting : It is the interior portion of a wall between facing 
and backing 

6. Head : It is a brick or stone, which lies with its greatest length  at right angles to the face of the work. 

7. Stretcher : It is a brick or a stone which lies with its congest 
side parallel to the face of the work 

8. Bond : The method of arranging bricks so that the individual  units are tied together
 
9. Spalls : The chips of stones used for filling the interstices in 
stone masonry
 
10. Quoins : The stones used for the corners of walls of structure 

11. Bat : It is a portion of a brick cut across the width. 

12. Closer: It is the portion of a brickcut in such a manner that its  one long face remains uncut 

13. Queen closer: it is the portion of a brick obtained by cutting a  brick length-wise into two portions

14. King closer: It is the portion of brick obtained by cutting off 
the triangular piece between the centre of one end and the 
centre of one side. 

15. Bevelled closer: It is the portion of a brick in which the 
whole length of the brick is bevelled for maintaining half 
width at one end and full width at the other 

16. Frog : It is an indentation or depression on the top face of a 
brick made with the object of forming a key for the mortar. 

17. Sill : It is a horizontal stone, concrete or wood, employed for 
the purpose of shedding off rain water from the face of wall 
immediately below the window opening 

18. Corbel : It is the extension of one or more course of stone or 
brick from the face of a wall to serve as a support for wall 
plates

19. Templates : Pieces of stones placed under the end of a beam 
to distribute load over a greater area. 

20. Coping : It is the course placed upon the exposed top of an  external wall to prevent the seepage of water 

21. Buttress : It is a sloping or stepped masonry projection from a  tall wall intended to strengthen the wall against the thrust of a roof.

@etconp
👍18👏4❤2🕊1
👉የአክሱም ሐውልት አስቸኳይ ጥገና ካልተደረገለት ሊወድቅ ይችላል ተባለ

በትግራይ ክልል የሚገኘው የአክሱም ሐውልት አስቸኳይ ጥገና ካልተደረገለት ሊወድቅ  ይችላል ሲል የአክሱም ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ለአዲስ ማለዳ ገልጿል፡፡

የአክሱም ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ገብረመድኅን ፍፁምብርሃን ሐውልቶቹን የተሸከመዉ ጥንታዊ የመቃብር ሥፍራ በክረምት ዉሃ እና ሌሎች ምክንያቶች መፈራረሱን ጠቅሰው፤ ከጦርነቱ በፊት ከጣልያን በመጡ ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎ በጣሊያን መንግሥት ዕድሳት ይደረግለታል ተብሎ እንደነበር ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ሆኖም የጥገና ሥራውን ይሰራል የተባለው ቡድን ከዚያ በኋላ ወደ ሥፍራው እንዳልተመለሰ ገልጸዋል።

በአክሱም ከተማ ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተሰሩ በርካታ ሐውልቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ኃላፊው፤ ከእነዚህ መካከል በመጠኑ ትልቅ የሆነው እና ቁጥር ሦስት ተብሎ የሚታወቀው ሐውልት በብረት ምሶሶዎች ተደግፎ ተንጋዶ እንደሚታይ ነው የጠቆሙት።

ስለሆነም ሐውልቱ አስቸኳይ ጥገና እና ዕድሳት ካልተደረገለት ሊወድቅ ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

ሐውልቶቹን ተሸከሞ ያለው "ሞዘልየም" የተሰኘው ጥንታዊ መቃብር በጊዜያዊነት ለመጠገን የፌዴራል መንግሥት ከሳምንት በፊት መጠነኛ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው፤ "ሆኖም ግን ቅርሱን ለመታደግ ይህ ዘላቂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም።" ሲሉ ተደምጠዋል።

በተጨማሪም በዓመት እስከ 25 ሺሕ የሚገመቱ የውጭ አገር ቱሪስቶች ይጎበኙት ነበር የተባለው ከአክሱም ሐወልቶች አቅራቢያ የሚገኝ ሙዚየም፤ በጦርነቱ ወቅት በደረሰበት ከፍተኛ ዘረፋ እና ውድመት እስካሁን ምንም ዓይነት ጥገና እንዳልተደረገለት አብራርተዋል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የአክሱም አውሮፕላን ማረፍያ እንዲሁ እስካሁን እድሳት እንዳልተደረገለት እና ወደ አገልገሎት እንዳልተመለሰ ገልጸዋል፡፡

የአክሱም ከተማ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ገቢ የምታገኘው ከቱሪዝሙ ዘርፍ ነው ያሉት ኃላፊው፤ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ አካባቢው ሰላም ቢሆንም ወደ ከተማዋ የሚመጣ ጎብኚ አለመኖሩን ተናግረዋል።

በዋናነት የሐወልቶቹ አስተዳደርና ጥገና ጉዳይ የሚመለከተው የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ልዑካኑን ወደ አክሱም ከተማ በመላክ የሐውልቶችን ሁኔታ መመልከቱንና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የሚላክ የጥናት ውጤት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም ሐውልቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመጠገን ከክልሉ አቅም በላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ የፌደራል መንግሥቱ ጉዳዩን አጽንኦት ሰጥቶ ሊከታተለው እና ቅርሱን ሊታደገው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Via አዲስ ማለዳ

@etconp
👍9💔5❤3
ከሕንፃ ከፍታና ፕላን አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚደረግ ግንባታ እንዲቆም ታዘዘ

⚡️በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ራማዳ ሆቴል አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ ምንም ዓይነት ግንባታ እንዳይፈቀድና የተፈቀዱ ሕንፃዎችም ግንባታ እንዲቆም፣ የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አዟል፡፡

⚡️ተቋሙ ውሳኔውን ለማስተላለፍ የወሰነው ካለፈው ዓመት ጀምሮ የተለያዩ የከተማ ስታንዳርዶችን በከተማዋ ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ኮሚሽን አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከሕንፃ ከፍታና የፕላን አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ጥናት እንዲደረግ አቅጣጫ በመስጠቱ ነው ተብሏል፡፡

⚡️ላልተወሰነ ጊዜ የግንባታ ፈቃድ እንዳይፈቀድ ውሳኔ የተላለፈበት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ራማዳ ሆቴል ግራና ቀኝ የተለያዩ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ዙሪያ ነው፡፡

⚡️የተለያዩ አገሮች ኤምባሲዎችና ዲፕሎማቶች ያሉበት አካባቢ በመሆኑና በነባሩ ፕላንና አሠፋፈር ስታንዳርዳይዝ የሆኑ ቤቶች ስላሉበት፣ ከሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ምንም ዓይነት ግንባታ እንዳይፈቀድ ባለሥልጣኑ ለቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት በጻፈው ደብዳቤ አዟል፡፡

Via - Alain

@etconp
👍9❤4
👉Calculation of Lap length in Reinforced Concrete Structures

🔰Lap length in Reinforced Concrete

Lap length is one of the im
portant term in the reinforcement.

This is usually confused with another important term called development length and anchorage length. In this article, the lap lengths of bars is discussed. During the placement of steel in Reinforced concrete structure, if the required length of single bar may fall short. To get the desired design length, lapping of two bars side by side is done. An alternative to this is to provide mechanical couplers.
__
La
pping can be defined as the overlapping of two bars side by side to upto the design length. Usually, the stock length of steel bars is limited to 12m. This is for easy transportation of steel bars to the construction site. For example, imagine there is a need to build a 100ft tall column. But it’s not practically available. Hence the bars are cut every second story.

__
The
n the tension forces are required to be transferred from one bar to the other bar at the location of discontinuity of the bar. So the second bar is kept closely to the first bar and overlapping is done. This amount of overlapping between two bars is called “lap length”. Lapping is usually done where minimum bending stress is encountered. In general, lap length is 50d which means 50 times the bar diameter, if both bars are of same diameter.

🔰L
ap length in tension:

The lap length including anchorage value of hooks shall be

For fle
xural tension – Ld or 30d whichever is greater is considered. For direct tension – 2Ld or 30d whichever is greater is considered.
__
The
straight length of lapping of bars shall not be less than 15d or 20cm.

🔰L
ap Length in Compression:

The lap length is equal to the development length calculated in compression but not less than 24d.

🔰F
or Different Diameter Bars:

When the bars of different diameters are to be spliced, the lap length is calculated considering the smaller diameter bar.

🔰Lap Splices

Lap splices should
not be catered for the bars which are having diameter greater than 36 mm. In such cases, welding should be considered. But if welding is also not feasible in some conditions, then lapping may be allowed for the bars larger than 36 mm diameter. But along with lapping, additional spirals of 6 mm should be provided around the lapped bars.

@etconp
👍11👏3❤2
Electricians handbook-74.3.apk
14.1 MB
Handbook of an electrician: wiring diagrams, electrical calculators
1. Theory
2. Schemes
3. Tests
4. Calculators
Electrical Engineering Manual
Version 74.3 Mod app
@etconp
👍5👏3
👉በጅማ ከተማ ሁለት ትላልቅ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ነው

🌟በጅማ ከተማ ሁለት ትላልቅ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

የጅማ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዋሴ ግርማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቶቹ የሚገነቡት ከተማዋን አቋርጦ በሚያልፈው አዌቱ ወንዝ ላይ ነው፡፡ አዌቱ ፔይስትሪ ፕሮጀክት ለሦስት ዓመት ያህል እየተገነባ ያለ ሲሆን ፕሮጀክቱ ብዙ ጥቅም እንደሚሰጥ ታስቦ የተጀመረ ነው፡፡

የአዌቱ ወንዝ ከዚህ ቀደም በኅብረተሰቡ ችግር ፈጣሪ ተደርጎ የሚወሰድ የነበረና በክረምት ቆሻሻን ይዞ በመምጣት ሰዎችን ከማፈናቀል አልፎ ለተለያዩ በሽታዎች ሲዳርጋቸው የቆየ ወንዝ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው፤ የኅብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍ እና በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተገነባ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች ሌጋሲን ለማስቀጠል ታስቦ እየለማ ያለ ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡

እንደ ምክትል ከንቲባው ገለጻ፤ የአዌቱ ፔይስትሪ ፕሮጀክት ሁለት ዙር ግንባታው የተጠናቀቀ ሲሆን አጠቃላይ ግንባታው 400 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ይሆናል፡፡ ግንባታው በከተማ አስተዳደሩና በተለያዩ ድርጅቶች ድጋፍ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

Via ኢ ፕ ድ

@etconp
👍6❤4😢1
🌟ስለ አፈር ጥቅጠቃ ስራ /Soil Compaction/ በጥቂቱ

☄Soil Compaction: - በሜካኒካል መንገድ የአፈርን የመሸከም አቅምን የምንጨምርበት መንገድ ነው።

➡️እንዴት?

✨አፈሩን ስንጠቀጥቅ የአፈር ፓርቲክሎች  ጥግግቶሽ ወይም ትፍፍግ/density/ እንዲጨምር እናደርጋለን።ይህም በአየርና ውሃ የተያዙ ቦታዎች /water and air voids/በአፈር እንዲተኩና እየዲቀንሱ ማድረግ ማለት ነው።

➡️ይህም በመሆኑ:

*የአፈሩን የመሸከም አቅም/Load bearing capacity of soil/ ከፍ እናደርጋለን።

*በውስጡ የውሃ ማንሸራሸር አቅሙን/permeability/ እንቀንሳለን።

*ስምጠት እንዳይኖር ያደርጋል/reduce future settlement/

➡️የደረቅ አፈር ከፍተኛ እፍግታ መጠን/Maximum dry density of soil/

⏺የደረቀ አፈር /ከድንግል መሬት/ ከፍተኛ እፍግታ መጠን/density/=1900kg/m3 ነው።

▶️በሰው ሰልሽ ጥቅጠቃ/Artificial Compaction/ በላቦራቶሪ ሙከራ  የምናገኘው እፍግታ /Proctor density/ ደግሞ ቢያንስ 95% እንዲመጣ ይጠበቃል።ከ95% በታች ከመጣ ወዳቂ ሆኖ የጥቅጠቃ ስራው እንደገና መሰራት ይኖርበታል።

🤞ማስታወሻ:- ደረቅ አፈር ስንል በማድረቂያ ማሽን/Oven/ ውስጥ የደረቀ ማለታችን ነው።

➡️የአፈር እፍግታ ማወቂያ መንገዶች/methods of testing soil density/

⚡️በዋናነት በሁለት ይመደባሉ።

-በሳይት ላይ የሚተገበሩ /Field test/: Sand cone test, Rubber balloon method, Nuclear density, Time domain reflectometry, Shelby tube/ባብዛኛው ጥቅም ላይ የማይውል/ናቸው።

-በቤተ ሙከራ የሚተገበሩ/Laboratory tests/: Proctor test, Modified proctor test... 

ለዛሬ በሳይት ላይ የአፈርን እፍግታ ስለምንፈትሽበት መንገድ እናያለን።

➡️Field density of soil/Cone test/Sand replacement test/

ተጠቅጥቆ የተጠናቀቀውን አፈር በሳይት ላይ እፍግታውን የምንፈትሽበት መንግድ ነው።

* *የሚያስፈልጉ እቃዎች/Apparatuses/

-የአሸዋ እቃ/ክብ ጀሪካን መሳይ/Sand pouring cylinder equipment/: ዲያሜትሩ 15cm ቀመቱና 45cm የሆነ ጃር

-መቆፈሪያ፣ማፅጃና ማስተካከያ እቃ/Tools for levelling and excavation/

-ማንኛውም ማጠራቀሚያ ሰሃን ወይም ሳጥን/Container/:

-ንፁህ አሸዋ

-ወንፊት

-ሚዛን/Balance/

-ዳታ መመዝገቢያ ቅጽ

* *የስራ ቅደም ተከተል/Procedure/

1ኛ.የአሸዋ ጃሩንና አፈር ለማውጫ የተዘጋጀውን ሰሃን ባዶውን መመዘንና መመዝገብ።

2ኛ. ጃሩን አሸዋ መሙላትና ከነአሸዋው መመዘንና በመመዝገቢያ ቅጹ ላይ መሙላት።

3ኛ. በ15cm ዲያሜትርና በ20cm ጥልቀት የተጠቀጠቀውን ሙሊት አፈር በጥንቃቄ መቆፈርና ሳይባክን እያወጡ በተዘጋጀው ሰሃን ላይ በማድረግ መመዘንና መመዝገብ።

ማስታወሻ:- የጉድጓዱን ልክ ለመወሰን በልክ የተዘጋጀ ፕሮፋይል ልንጠቀም እንችላለን።ምስል 5 ን ይመልከቱ

4ኛ. የአሸዋ ጃሩን ከታች በምስል 1 ላይ በተቀመጠው መሰረት በማድረግ ወደተቆፈረው ጉድጓድ ላይ በማድረግና መዝገያውን በመክፈት አሸዋው ጉድጓዱን እስኪሞላ ጠብቆ መዝጊያውን በመቆለፍ ጃሩን ማንሳትና ቀሪውን መመዘንና መመዝገብ።

5ኛ. አሸዋውን ደግሞ ለመጠቀም ካስፈለገ ከጉድጓዱ ጠርጎ ማውጣትና በወንፊት እየነፉ በስቀመጫው እቃ ማከማቸት።

6ኛ. የተሰበሰበው ዳታ በመጠቀም. የሳይት ላይ እፍግታውን/Bulk density/ ማወቅ እንችላለን። በቀጣይ ጽሁፍ የሚወጣውን ምሳሌ መመልከት ይቻለል።

7ኛ. ከፍተኛው የደረቅ እፍግታ ልኩን/MDD/ በቤተ ሙከራ ለመስራት ከሰሃኑ ላይ ለናሙና 1/3ኛ ያህሉን በንፁህና ደረቅ ላስቲክ በማድረግ ማዘጋጀት።

ማስታወሻ:-የተወሰደው ናሙና ባእድ ነገር እንዳገባበትና ከሌላ ናሙና ጋር ለመለየት እንዲያስችለረ በጥንቃቄ መታሸግና እላዩ ላይ መለያ ኮድ መጻፍ ይገባል።

እንደስራው ደረጃና የሳይቱ ስፋት መጠን ከላይ የተጠቀሰውን አካሄድ ቢያን ሶስትና ከዚያ በላይ በመሃንዲሱ በተመረጡ ቦታዎች ላይ መስራት ይገባል።

➡️የአፈር ጥቅጠቃ ስራ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

-የአፈሩ ዓይነት/soil type/

ለምሳሌ: ኮረታማ/ጠጠርማ/Gravel/Granular/ አፈር ለመጠቅጠቅ ምቹና በጣም ጥሩ ውጤት የሚያስገኝ ሲሆን፣በተቃራኒ ጥቁርና ብስባሽ ያለው አፈር ደግሞ ለመጠቅጠቅ የማይሆንና የማይች በመሆኑ ለማንኛውም ስትራክቸራል ሙሊት ስራ የማይመረጥ ነው ይሆናል ማለት ነው።ከታች በምስል 4 ላይ የተቀመጠውን ይመልከቱ።

▶️የአፈሩ ውሃ ይዘት/soil water content/:

⏺አፈሩ በጣም ውሃ ያዠ ወይም ከልክ በላይ የደረቀ መሆን የምንፈልገውን እፍግታ ማግኘት እንዳንችል ያደርጋል ማለት ነው።

▶️የጥቅጠቃ ሃይል/Compaction Effort/


Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍20❤1
በትናትናው እለት በካሜሮን ዱዋላ ከተማ በተከሰተው የህንጻ መደርመስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 34 ደርሷል፡፡

የተደረመሰው ህንጻ የግንባታ ፍቃድ ያልተሰጠው እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ህንጻው ፍቃድ ሳይሰጠው የተገነባ መሆኑን የሀገሪቱ የቤቶችና ከተማ ልማት ሚኒስትሩ ኬሌስቲን ኬቻ ኩረቴስ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሩ አደጋው የደረሰበት ስፍራ ተገኝተው ህንጻው ያደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል፡፡

በካሜሮን የህንጻ መደርመስ የተለመደ ነው የሚሉት ታዛቢዎች የአሁኑ አደጋ ግን የከፋ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ባለ 4 ወለሉ ህንጻ በሌላ ህንጻ ላይ በመደርመሱ ምክንያት የማቾቹ ቁጥር ሊያሸቅብ እንደቻለ ተገልጿል፡፡

በደረሰው አደጋ 21 ሰዎች በጽኑ ቆስለው በሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡

የነብስ አድን ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ አሁን ላይ በህንጻው ፍርስራሽ ውስጥ ምንም የቀረ ሰው እንደሌለ ተረጋግጧል፡፡

እንዲህ አይነት አሳዛኝ አደጋ ዳግመኛ እንዳይከሰት የአገሪቱ መንግስት የቤት ግንባታ ላይ የጥራት ቁጥጥር ሊያደረግ እንደሚገባ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ ከ7 አመት በፊት አንድ ትልቅ ህንጻ በተመሳሳይ ሁኔታ መደርመሱ የሚታወስ ነው ሲል ቢቢሲ ጠቅሶ AMN ዘግቧል፡፡

@etconp
👍9❤2😢1
👋የስሚንቶ ሽያጭ በቅርቡ ወደ ዲጂታል ግብይት ስርአት እንደሚቀየር የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ

⚡️የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተለይም ለአራዳ ኤፍ ኤም እንደገለፀው የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እየፈተነው የሚገኘውን የስሚንቶ ግብይት ሙሉ በመሉ ወደ ዲጅታል ለመቀየር እየተሰራ ነው ብሏል፡፡

⚡️የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ በላይነሽ እረጋሳ እንዳሉት ስሚንቶን ወደ ዲጂታል ግብይት ለማስገባት ከቴሌና ከስሚንቶ አምራች ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተደርሷል፡፡

⚡️የዲጂታል ግብይቱ ሲጀመር ጣልቃ የሚገቡ የስሚንቶ ደላሎችን መሉ በሙሉ ማስቀረት እንደሚችል ታምኖበታል ሲሉ የኮሚዩኒኬሽን አስፈፃሚዋ ገልፃዋል፡፡

⚡️የስሚንቶ አምራች ኩባንያዎችም ወኪሎቻቸው ምንያህል መጠን ስሚንቶ ይፈልጋሉ እንዲሁም ሽጠው ጨርሰዋል ወይ የሚሉትን ከዲጂታል መተግበሪያው ላይ ማወቅም መቆጣጠርም ያስችላቸዋል ነው ያሉት፡፡

🫵ይህም በ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የራሱ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

Via - Arada FM

@etconp
👏6💯1
🤜Did you know what the difference between dozer type

Cat D6, Cat D8, and Cat D9?
Cat D6, Cat D8, and Cat D9 are different models of bulldozers manufactured by Caterpillar Inc.

The main differences between these models are their size, power, and capabilities.

Cat D6 is a medium-sized bulldozer that is commonly used for grading, excavation, and leveling work. It has an operating weight of around 17-20 tons and a horsepower range of 130-190.

Cat D8 is a larger bulldozer that is often used for heavy-duty earthmoving projects such as mining, quarrying, and large-scale construction. It has an operating weight of around 37-54 tons and a horsepower range of 300-400.

Cat D9 is the largest bulldozer in the Cat lineup, designed for extreme earthmoving and mining applications. It has an operating weight of around 49-106 tons and a horsepower range of 335-850.

In summary, the main differences between these models are their size, power, and intended use. Cat D6 is a medium-sized bulldozer for general-purpose earthmoving, while Cat D8 and Cat D9 are larger bulldozers for heavy-duty earthmoving and mining applications.

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍13👏1
Ethio Construction Engineering
Photo
የከተማ አስተዳደሩና ሪል ስቴት አልሚዎች ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መኖሪያ ቤቶችን ሊገነቡ ነው ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግሥትና በግል አጋርነት ፕሮጀክት አማካይነት በመረጣቸው ሪል ስቴት አልሚዎች፣ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ወጪ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሊካሄድ ነው ተብሏል።

በዚህ ፕሮግራም ሥር እንዲሳተፉ 68 ሪል ስቴት አልሚዎችን የመረጠ ሲሆን፤ አልሚዎቹም በተቀመጠው 70/30 አጋርነት መሠረት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተጣምረው ግንባታውን ለማካሄድ ውል መግባታቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ከእነዚህም አልሚዎች ውስጥ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ኦቪድ ግሩፕ፣ ፍሊንትስቶን ሆምስ፣ እንይ ኮንስትራክሽን፣ ጊፍት ሪል ስቴትና ሌሎችም ይገኙበታል ነው የተባለው።

የከተማ አስተዳደሩ የቤቶቹን ግንባታ ለማካሄድ የሚያስፈልገውን መሬት ከሊዝ ነፃ ማቅረብና መሠረተ ልማቶችን ማሟላት ኃላፊነት ሲኖርበት፤ አልሚዎቹ ደግሞ ያስገቡትን የመገንባት አቅም መሠረት ተደርጎ በሚቀርብላቸው መሬት ላይ ወጪውን በመሸፈን ቤቶቹን እንደሚገነቡ ተገልጿል።

አልሚዎቹ የቤቶችን ግንባታ አካሂደው ካጠናቀቁ በኋላ፣ 30 በመቶውን ለከተማ አስተዳደሩ ለማስረከብ መስማማታቸው ታውቋል። ይህ ማለት የከተማ አስተዳደሩ በዚህ ጥምረት ከሚገነቡት ቤቶች ውስጥ 30 በመቶ ድርሻ ይኖረዋል።

በዚህም መሠረት የከተማ አስተዳደሩ በ2016 በጀት ዓመት 100 ሺሕ ቤቶችን ለማስገባት ማቀዱ ተጠቁሟል።

ከዚህ ውስጥ አቪድ ግሩፕ ተቋራጭ 60 ሺሕ ቤቶችን፤ ጊፍት ሪል ስቴት 12 ሺሕ ቤቶችን፤ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 10 ሺሕ ቤቶችን ለመግንባት ውል መግባታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለቤቶቹ ግንባታ የተለዩ ሦስት አካባቢዎች የተመደቡ ሲሆን፤ እነሱም በከተማ ውስጥ፣ በከተማ አቅራቢያና ከከተማ ወጣ ያሉ ናቸው። የከተማ አስተዳደሩ በመንግሥትና በግል አጋርነት ለሚካሄደው የቤት ግንባታ ፕሮጀክት፣ በመሀል አዲስ አበባ 350 ሔክታር መሬት ማዘጋጀቱም ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ ፋይናንስ ሙሉ በሙሉ የሚሸፈነው በአልሚው ድርጅት ሲሆን፤ የግብዓት አቅርቦት፣ የመብራትና የውኃ፣ እንዲሁም ለግንባታ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እጥረት ሲፈጠር አልሚ ድርጅቶቹ ቅድሚያ እንዲያገኙ የማድረግ ኃላፊነት የከተማ አስተዳደሩ መሆኑም ታውቋል።

@etconp
👍8👏2❤1
Ethio Construction Engineering
📩በ ውስጥ መስመር ከ አንድ ወዳጃችን የተጠየቅን ጥያቄ 🌧ከ ክረምት ጋር በተያያዘ የውሃ ስርገትና ርጥበትን እንዴት ልከላከል /Damp Prevention/ 💧የውሃ ስርገትና ርጥበትን የመከላከልያ ሌሎች የተለመዱ መንገዶች/Typical Membrane Damp-proofing Agents/ ⭐️1ኛ. የኮንክሪት ግግር መደብ/Application thin Concrete layer(s) / ▶️አነስተኛ ርጥበት የሚፈጥር…
👉የፍሳሽ ስርገትና ርጥበትን መከላከል/Damp Prevention/
☔️☔️☔️☔️☔️☔️☔️☔️☔️☔️☔️

🌟ከ ባለፈው የቀጠለ

⚡️አንድ ህንጻ የታሰበለትን የተሟላ አገልግሎት እንዲያስገኝ ከሚያስፈልጉ ፍላጎቶች አንዱ ህንጻው ከማንኛውም በግድግዳ፣በጣሪያና ከመሬት በላይ ወይም ከመሬት ስር በሚኖረው ወለል ከሚመጣ ፍሳሽ ከሚፈጠር ርጥበት/hygroscopic moisture/ የጸዳና ደረቅ መሆኑ ነው።


💧ለርጥበት መከሰት ምክንያቶች/Sources of Dampness/:

1.ከመሬት ውስጥ ወደላይ የሚወጣ ውሃ/Moisture Rising up the wall from Ground/:

2.ግድግዳን ሰርጎ ውስጥ ለውስጥ ወደታች የሚወርድ የዝናብ ውሃ/Rain Travel from wall Tops/

3.በግድግዳ ሰርጎ ግድግዳውን የሚያለዝብ የዝናብ ውሃ/Rain beating against External wall/

4.ጥዘት/Condensation/

5.ሌሎች ምክንያቶች

-ደካማ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት

-የህንጻ አቀማመጥ አቅጣጫ ልክ ያለመሆን/imperfect orientation/

-በቂ ያልሆነ የጣራ ተዳፋት/imperfect Roof slope/

-የግንባታ ጥራት ችግር........

💧የርጥበት መከሰት የሚያስከትካቸው ችግሮች/Effects of Dampness/

1.ንጽህናው ያልተጠበቀና ጤናን የሚጎዳ ሁኔታን ይፈጥራል፣

2.ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ  ምክንያት ይሆናል።

3.ለተጠቃሚዎች ምቾትን የሚነሳ አካባቢ እንዲፈጠር ያደርጋል።

4.የልስን ስራ ላይ መሳሳትና መፈርፈር ምክንያት ይሆናል።

5.እንደቀለምና የቤት ማስዋቢያ ስራዎች ላይ ብልሽት ያስከትላል።

6.የወለልና ግድግዳ ማጠናቀቂ ስራዎች/Damages on floor & wall coverings/

7.ከብረት የተሰሩ የተለያዩ የግድግዳ፣ወለልና ጣሪያ ስራዎች ላይ ዝገት እንዲፈጠር ያደርጋል።

8.እንደ ኤሌክትሪክ ስራዎችና

⏺በአጠቃላይ የህንጻ ደህንነት ላይ አደገኛ ደረጃ ጉዳት እስከማድረስ ችግር ሊፈጥር ይችላል ማለት ነው።

💧የውሃ ስርገትና ርጥበትን የመከላከልያ መንገዶች/Methods of Dampness prevention and water proofing works/

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍10👏2❤1🕊1