Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ስለ Road structure components

🌟Super Elevation = የመንገድ Curve ላይ መኪናን ከመንገዱ
ውጪ የሚጎትትን Centrifugal Force ለመቋቋም የአስፓልቱ
ከርቭ ዙሪያውን ከፍ ተደርጎ ይሰራል - ለሹፌሩም ምቾትን ይሰጣል እንዲሁም በሚታጠፍበት ግዜ ኣደጋን ይቀንሳል፡፡

🌟Pavement Crown = ለፍሳሽ ተብሎ የአስፓልቱ መሃል ከዳርኞቹ ይልቅ ከፍ ተደርጎ ይሰራል የሚሰራ ኮምፐነንት ነው።

⏺ሌሎችም components ከላይ በ ፒክቸሩ እንደምታዩት ዲፋይን ተደርገዋል

⚡️ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍6👏5🕊2
የግንባታ_ሥራ_ተቋራጮች_የፕሮጀክት_አፈፃፀም_ምዘና_መመሪያ.pdf
38.3 MB
👉የግንባታ ሥራ ተቋራጮች የፕሮጀክት አፈፃፀም ምዘና መመሪያ

🌟ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን  SHARE  አድርጉልን።

@etconp
🙏6🕊5❤4
🌟🌟🌟 SNS ፈርኒቸር 🌟🌟🌟

💫ህንፃዎ ገንብተው ጨርሰው ውብ የ እንጨት ውጤት ስራ ቀርቶታል?

🚧እጅግ ዘመናዊ ቅንጡ አዳዲስ የ እንጨት ፈርኒቸር ውጤቶች ማለትም በር፣ኪችን ካቢኔት እና ዳይኒንግ ቴብሎች በአጠቃላይ ጥራታቸውን የጠበቁ ማራኪ የፈርኒቸር ውጤቶች እኛ ዘንድ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረባችንን ስንገልጽ በደስታ ነው።

📩መግዛት ለምትፈልጉ እና ዝርዝር መረጃ በ @Philemona7 ያግኙን።

👌በጥራት ፣ በውበት ፣ በምቾት እና በጥንካሬ አምነውብን ስለመረጡን እናመሰግናለን!
👍16
👉እስቲ ኣሁን ደሞ ስለ lap length , Development length,Anchorage length ትንሽ እንንገራቹ

🌟ላፕ ሌንግዝ (lap length) - ተፈላጊ የብረት (ፌሮ) ርዝመት ውጥረትን (stresses) ከአንድ ብረት ወደሌላ የሚተላለፍበት

🌟ደቨሎፕመንት ሌንግዝ (Development length) -ተፈላጊ
የብረት ርዝመት ውጥረትን (stresses) ከብረቱ ወደ ኮንክሪቱ የሚተላለፍበት

🌟አንኮሬጅ ሌንግዝ (Anchorage length) - ይህ ርዝመት አይነት በቂ የሆነ ደቨሎፕመንት ሌንግዝ (development
length ) በሌለባቸው በ Support/fixed ends ላይ provide የምናረገው ርዝመት ነው::

⚡️ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን  SHARE  አድርጉልን።

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍12❤2
👉ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚፈስበት የመንገድ ሃብት የሚጠበቅበትን አገልግሎት እንዲሰጥ ተገቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ያስፈልገዋል፡፡

⚡️መንገዶችን ለብልሽት ከሚዳርጉ ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው ከተፈቀደው ክብደት በላይ በመጫን መጓዝ (Axels load) ነው።

🚧በዚህም ረገድ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ከባድ ጭነትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ  ሚዛን ጣቢያዎችን በማቋቋም እንደሚሰራ ይታወቃል።
የተሽከርካሪዎችን ክብደት የመቆጣጠር ዋና አላማ በመንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ከተፈቀደላቸዉ የአክስል ክብደት መጠን በላይ ጭነዉ በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የመንገድ አዉታሮች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ የመከላከል እንዲሁም መንገዶች እና ድልድዮች ሳይበላሹ ለረዥም ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማድረግ ነዉ፡፡

🚧በሀገራችን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የሚዛን ጣቢያዎች እና መገኛ ቦታቸው

⏺እስካሁንም 14 ሚዛን ጣቢያዎቸን በተለያዩ ቦታዎቸ ተቋቁመው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን ፣ መገኛ አካባቢያቸውም፡- ሞጆ ፣ ሆሎታ ፣ ሱሉልታ ፣ ሠንዳፋ ፣ ዲማ (ሰበታ) ፣ ጂማ ፣ ሻሸመኔ አዋሽ ፣ ሠመራ ፣ደንገጎ ፣ ኮምቦልቻ ፣ ጢቅ (ደጅን) ፣ወረታ ፣ ኵሓ (መቐለ) ናቸው።

🌟የተሽከርካሪዎች ክብደት መቆጣጠር ዋና ዋና ዓላማዎች በትንሹ የሚከተሉት ናቸው

•  መንገዶች እና ድልድዮች ከልክ በላይ በሆነ ክብደት ምክንያት ማገልገል የሚገባቸውን ጊዜ ሳያገለግሉ ለብልሽት እንዳይዳረጉ ለመከላከል

•  ከልክ ያለፈ ክብደት መንገዶች እና ድልድዮችን ስለሚጎዳ የጥገና  እና የመልሶ ግንባታ ወጪዎችን ለመቀነስ

•  በትርፍ ጭነት ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ

•  የእቃዎች ዝውውር ወይም መነሻና መድርሻ ለመቆጣጠር ፣

Via ERA

@etconp
👏5👍1
👉ለላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት አዲስ መጠለያ ለመስራት ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ፡፡

🌟አዲስ የሚሰራው መጠለያ ውቅር አቢያተ ክርስቲያኒቱ ላይ ጉዳት በማያደርስ እና ረጅም ዓመት እንዲቆይ ታስቦ ይሰራል ተብሏል፡፡

Via - Sheger FM

@etconp
👍7❤3
የአለም ከተሞች ባብላጮቹ መንሀተን ኒውዮርክን መምሰል እንደሚመኙ ከተማና ኪነህንጻቸው ያሳብቅባቸዋል።

ለመምሰል ከሞከሩ በአገራችን በቅርበት ከሚገኙ ከተሞች መካከልም የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቷ ዱባይም ግንባር ቀደም ሆና ትጠቀሳለች።

የአምሳያነት አበይት  መገለጫውም ጥግግቱና አለሁ ባይ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎቹ ናቸው። ለዚህ ክስተት መኖር  ከመዋቅራዊው የምህንድስና ጥበብ ባሻገር ግን ሰማይ ድረስ የሚገፋ  ውሀ መገኘት እና በቂ የፍሳሽ መስመር መኖር የማናስተውላቸው አስቻይ ምክንያቶች ናቸው። ዱባይም ቢሆን ከባህር ውሀ ጨውን በማስወገድ ጥበብ ለህንጻዎቿ ውሀ ማቅረብ ትችላለች። 

እኛስ ሰማይ ጠቀስ መኖርያና መስርያ ስንገነባ ውሀ አቅርቦቱን አብረን እያሰብን ይሆን? ። ውሀ ፍላጎት ማሟያስ አንድን ትልቅ ወንዝ መጥለፍ ይኖርብን ይሆን? ወይስ  የሚቀጥለው ትውልድ የሚሰቃይባቸው ቀውላላ ቀውላላ ፎቅ ደርድረን እያለፍን ነው? 

በአዲስ አበባ ከአንዳንዶቹ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች የሚወጣው የፍሳሽ ትቦ ስፋትም  ከተማው ከዘረጋው የትቦ መስመር ይበልጣል እየተባለ ነው።

የተያያዘው ምስል ለረጅም ዘመን በቁመት ተወዳዳሪ ያልነበረው በመንሀተን የሚገኘው እውቁ የ "ኢምፓየር ስቴት"  ህንጻ ነው።

Via ዳዊት በንቲ

@etconp
👍7👏1
👉What are two advantages of T-beam?

🌟Flanges are more effective in resisting bending stresses while the Web is more resistive in shear stresses.

🌟The T-beam has separate parts for resisting both bending and shear forces as a result very good in resisting stresses in buildings.

Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Twitter:- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👏4
በበጀት ዓመቱ ከ7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ደርሷል

በ 2015 በጀት ዓመት በተሸከርካሪዎች ግጭት ምክንያት 7ከ ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ባለው የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

በበጀት ዓመቱ በቀለበት መንገድ ላይ 135፣ ከቀለበት መንገድ ውጪ ደግሞ 199፣ በድምሩ 334 የግጭት አደጋዎች ደርሰዋል፡፡

በተሽከርካሪዎች ግጭት በአብዛኛው ጉዳት እየደረሰባቸው የሚገኙት የመንገድ መብራት ምሶሶዎች፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የአቅጣጫና ርቀት አመላካች ሰሌዳዎች፣ የእግረኛ መከላከያ አጥሮች፣ የመንገድ አካፋይ ከርቭስቶን እና የማንሆል ክዳኖች ናቸው፡፡

በተሽከርካሪ ግጭት ሳቢያ እየደረሰ ላለው የመንገድ ሀብት ጉዳት መንስኤ ከሆኑት መካከል ጠጥቶ ማሽከርከር፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ መንዳት እና ያለ መንጃ ፈቃድ ማሽከርከር ተጠቃሽ ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ካደረሱ አሸከርካሪዎች ተገቢውን የካሣ ክፍያ ከመሰብሰብ ጎን ለጎን ጉዳት የደረሰባቸውን የመንገድ ሀብቶች በመጠገን ላይ ይገኛል፡፡

Via የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች

@etconp
👍9
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
LAS LAJAS SANCTUARY

ይህ የምትመለከቱት መቅደስ ስሙ Las Lajas ይባላል።
መገኛውም ኮሎምቢያ ሲሆን ለሀገሪቱ የቱሪስት መስዕብ የሚኖረውም ድርሻ የላቀ ነው።
ይህ ቤተመቅደስ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ነው።

በተለምዶ “በሸለቆ ውስጥ የእግዚአብሔር ተዓምር “ ወይም "miracle of GOD in the abyss.” በመባል ይታወቃል።

አሁን ያለው ቤተክርስቲያን የተገነባው በ 1916 እና በ 1949 መካከል ባለው የጎቲክ style መነቃቂያ ጊዜ ነው።

This sanctuary is one of the most fascinating religious structures in all of Colombia .

The present church ⛪️ was built in Gothic revival between 1916 and 1949.

Nariño, Colombia 🇨🇴

Source:- Wikipedia

ውብ ምሽት ተመኘን

我們希望有一個美麗的夜晚

‎كنا نتمنى أمسية جميلة

हमने एक खूबसूरत शाम की कामना की

We wished a beautiful evening

Мы пожелали прекрасного вечера

Waarii gaarii sifan haawaa

@ETCONp
👍6❤5💯1
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በአዲስ መዋቅር አሰራሩን በማዘመን በቁጥጥር ስራ የሚገኙ ግድፈቶች ላይ በተጠናከረ መልኩ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በአዋጅ 1263/2014 በወጣ ደንብ መሰረት አዲስ አደረጃጀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህንኑ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የ2016 በጀት አመት እቅድ መታቀዱ ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረትም ለዕቅድ ዘመኑ ዘጠና አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር በጀት የተመደበለት ሲሆን፣ በበጀት አመቱ 39 ዋና ዋና ግቦች እና 176 ግብ ተኮር ተግባራትን ለማሳካት አቅዷል፡፡

በአዲሱ አወቃቀር ከተጨመሩት መካከል አማራጭ የግጭት አፈታት (ADR) ፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን፣ የመረጃ መጠመርና ለመተንተን የሚያስችሉ መተግበሪያዎች ማልማት፣ የቁጥጥር ስራው በኤሌክትሮኒክስ አሰራር እንዲዘምን መተግበሪያዎችን የማልማት እና ቀድሞ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር በአዲስ መልኩ ወደሀገር ውስጥ የሚገቡ የኮንስትራክሽን እቃዎች ላይ ከወደብ ሳይገቡ ቁጥጥር በማድረግ ጥራት የሌላቸው ምርቶች እንዳይገቡ የማድረግ ተግባራትን የሚያከናውኑ የስራ ክፍሎች በአዲሱ መዋቅር በመኖራቸው እቅዱ እነዚህን ታሳቢ በማድረግ ታቅዷል፡፡

በ2015 ዓ.ም. እቅድ አፈጻጸም ሲገመገም የታዩ ክፍተቶች ውስጥ እቅዶች የድርጊት መርሃ ግብር ጠብቀው አለመፈጸማቸው ሲሆን፣በዕቅድ ክለሳ ለማስተካከልና ለማሳካት ተችሏል፡፡

ነገር ግን በ2016 ሁሉም ተግባራት በድርጊት መርሃ ግብራቸው መሰረት ሊከወኑ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

ከተጠናቀቀው የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት መነሻነት በ2016 ዓ.ም በጉልህ መስተካከል ያለባቸው የእቅድ ተግባራት በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መፈጸም የሚለው መሆኑ ተገልጿል፡፡

የድርጊት መርሃ ግብሩን አስጠብቆ ለማስኬድ እንዲሁም ዋና ዋና ግቦችን የበላይ አመራሮች በዋና ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ የሚያስችል የእቅድ ትግበራ ስምምነት ሰነድ (team charter) ተዘጋጅቷል፡፡

ይሄንንም በመከተል እያንዳንዱን ተግባር ክንውን ለመከታተል አመቺ ለማድረግ ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በ2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ተብሎ ከታቀዱ ተግባራት መካከል የቁጥጥር ስርዓትን በማዘመን የቁጥጥር የግብረ መልስ ስርዓትን ማጠናቀር እና ወጥ በሆነ ቅርጽ ማካሄድ ዋንኛው ነው፡፡

ተቋሙ ቀድሞ ሲሰራበት ከነበረው የቁጥጥርና የግብረ መልስ ስርዓት በተጠናከረ መልኩ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚደረጉ የቁጥጥር ተግባራት ትኩረት ተሰቶባቸውና በቁጥጥር በሚገኙ ጉድለቶች ላይ የተጠናከረ የእርምት እርምጃ በመውሰድ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በ2016 ዓ.ም እንደተቋም የተያዘውን ዓላማ ለማሳካት በቅድሚያ እቅድን መረዳት፣ በእቅድ ላይ ተግባቦት መፍጠርና የድርጊት መርሃ ግብር ሰሌዳ በተቀመጠበት ጊዜ ማከናወን ያስፈልጋል፡፡ በማለት የእቅድና የበጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ለገሰ ገልጸዋል፡፡

የ2016 ዓ.ም የእቅድ ትግበራ ስምምነት ሰነድ (team charter) የመጨረሻው ረቂቅ ለተቋሙ የማኔጅመንት አባላትና የስራ ሃላፊዎች ቀርቦ አስተያየት ተሰቶበታል።

@etconp
👍5
Dream house 🎸 🎹 ….. how fascinating is that designing a house inspired by musical 🎤 🎵 instruments

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=MzRlODBiNWFlZA==

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

Twitter:- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432
❤5👍1
👉የህንጻ ግንባታ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሰዎች ተገልጋይነት ታሳቢ ማድረግ ይኖርበታል

▶በኢትዮጵያ የህንጻ አዋጅ አንቀጽ 36 ላይ "ማንኛውም የህዝብ መገልገያ ህንጻ ውስጥ በተሸከርካሪ ወንበር ለመንቀሳቀስ የሚገደዱትን እና መራመድ የሚችሉ ሆኖ ደረጃ መውጣት የሚሳናቸውን ጨምሮ የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች የሚመች መዳረሻ መዘጋጀት አለበት" በሚል በግልጽ ተደንግጓል፡፡

▶️ድንጋጌው በአስገዳጅ/obligatory/ ሁኔታ የተቀመጠ ነው፡፡

▶️በተጨማሪም በህንጻ ግንባታ ወቅት የሚሰሩ መጸዳጃ ቤቶች የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች የሚመቹ እና ሊደርሱባቸው የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚሁ መጸዳጃ ቤቶችም በበቂ መጠን/ቁጥር መኖር ይገባቸዋል፡፡

▶️ሌላው ከመሬት ወለል በላይ/above the ground floor/ ከ20(ሀያ) ሜትር
በላይ ከፍታ የሚኖራቸው የህንጻ ግንባታዎች ልዩ ግዴታ አለባቸው፡፡

▶️ይሄውም ህንጻው አሳንሰር ወይንም ተመሳሳይ አገልግሎት ሊኖረው እንደሚገባ እና አሳንሰሩም ያለማቋረጥ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባው የህንጻ አዋጁ አንቀጽ 33(4) እና(5) ይደነግጋል፡፡

▶️ስለዚህ አሳንሰር ከግራውንድ ፍሎር ጀምሮ ወደላይ ከሀያ ሜትር በላይ ከፍታ ላላቸው ህንጻዎች የቅንጦት ሳይሆን በህግ የተቀመጠ ግዴታ ነው ማለት ነው፡፡

▶️ይህን የህንጻ ግንባታ ህግ መጣስ ደግሞ ከህንጻ አዋጁ አንቀጽ 47 ጀምሮ በተደነገገው አግባብ የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡

▶️ስለሆነም የህንጻ አዋጁ በሚያስቀምጠው አግባብ የህንጻ ግንባታዎችን እንዲከናወኑ ማድረግ ከተጠያቂነት የሚያድን ከመሆኑም ባሻገር የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች በህግ የተሰጣቸውን መብት እንዲገለገሉ ምቹ ሁኔታ መፍጠርም መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👏6👍1