Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ (ASTU) ጋር በመተባበር የBIM ቴክኖሎጂ ስልጠና ለዩኒቨርስቲው መምህራኖች እየሰጠ ነው።

🚧የ BIM ቴክኖሎጂ ለኢትዮጵያ አዲስ ቢሆንም በውጪው አለም በስፋት እየተሰራበት የሚገኝ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪውን በእጅጉ ለማዘመን የሚረዳ ጠቃሚ ቴክኖሎጂ ነው::

🚧ይህን ቴክኖሎጂ ለማስረፅና ለማሸጋገር ኢንስቲትዩቱ ሰፊ ጥረት እያደረገ ይገኛል::

🚧ጎንደር፤ባህርዳር እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቀደም ብለው ስልጠናውን ያገኙ ተቋማት ናቸው::

🚧ዛሬ አዳማ ዩኒቨርሲቲ ስልጠናውን የጀመረ ሲሆን የነዚህን ዩኒቨርስቲ መምህራኖች መሰልጠን BIM ን በስርአተ ትምህርት ውስጥ በማካተት BIM ን ለማሳወቅ ፤ለማሸጋገር እና ለማስረጽ ይረዳል::

🚧ስልጠናው ከ ነሀሴ 15 እስከ ጳጉሜ 6 ለ 20 ቀን የሚቆይ ሲሆን 31 የዩኒቨርስቲው መምህራን እየሰለጠኑ ይገኛሉ::

🚧በስልጠናው መክፈቻ ላይ አሰልጣኝ ህንጻ ነዳፊ ቅድስት ማሞ የኢንስቲትዩቱ የምዘና ስርአት እና የሰርተፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንስቲትዪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዘመናዊ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ አየሰራ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ስራ ለሰልጣኞች ገለፃ በማድረግ አስተዋውቀዋል::

Via Construction Management Institute

@etconp
👍8❤7
👉የ Scolarship ጥቆማ

🌟University of Milan DSU Scholarship in Italy 2023 (Fully Funded)

➖️Host Country: Italy
➖️University Name: University of Milan
➖️Degree Level: Bachelor, Master, Ph.D., Research
➖️Scholarship Name: DSU Scholarship
➖️Deadline: 30th September 2023

⏺Faculties and Study Areas

✔️Engineering
✔️Computer
✔️Faculty of Agricultural and Food Sciences
✔️Faculty of Humanities
✔️Faculty of Law
✔️Faculty of Medicine
✔️Faculty of Political, Economic, and Social Sciences
✔️Faculty of Science and Technology
✔️Faculty of Veterinary Medicine
✔️School of Exercise and Sport Sciences
✔️School of Language Mediation and Intercultural Communication

🚧Apply here
https://www.unimi.it/en/study/financial-support/regional-scholarships

@etconp
👍12🙏3
👉ኬንያ ከአዲሷ ላሙ ወደብ ወደ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የሚዘረጋውን የኤሌክትሪክ ባቡር ሐዲድ ግንባታ በአውሮፓዊያኑ 2025 ዓ፣ም ለመጀመር ማቀዷን ብሉምበርግ ዘግቧል።

🚧ኬንያ የሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ወደብ ከኾነችው ላሙ በኢሴሎ ግዛት በኩል ወደ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የሚዘልቀውን የባቡር ሐዲድ በኹለት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዷን ዘገባው ጠቅሷል።

🚧የባቡር ሐዲዱ፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የታቀፉበት የቀጠናዊው የ"ላፕሴት" የመሠረተ ልማቶች ፕሮጀክት አካል ነው። ኬንያ የባቡር ሐዲዱን ግንባታ እንደምትጀምር የገለጠችው፣ ኢትዮጵያ ላሙ ወደብን ለመጠቀም ዝግጁ መኾኗን ሰሞኑን መግለጧን ተከትሎ ነው።

🚧3 ሺህ ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የባቡር ሐዲድ ግንባታ ከ13 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚፈጅ ሲኾን፣ ኬንያ ለግንባታው የአዋጭነት ጥናት ከአፍሪካ ኅብረት ፈንድ 9 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት አቅዳለች ተብሏል።

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍8
ሃገር ቤት የአንድ ፒዛና የአንድ ሲሚንቶ ዋጋ እኩል ነው አሉ።

ፒዛ ለጋበዝካት ቺክ ቤዝመንቱን እየበላችው እንደሆነ ንገራት 😂😂

Via Yohanis

For Fun

@etconp
😁16👍3
👉የፕሮጀክት ማናጀሮች ስኬታማ እንዴት ሊሆኑ ይችላሉ?

በኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በማናጀርነት በመስራት የሚፈልገውን ውጤት ለማግኘት እና ተገቢውን ሚና ለመጫወት የሚፈልግ በዘርፉ የሰለጠነ ባለሙያ፣ በመጀመሪያ ደረጃ እንደ ማንኛውም የሥራ መሪ ለሥራው ዓይነት የሚያስፈልገውን ሥልጠና እና ትምህርት መውሰድ እንደሚገባ ለመገመት አያዳግትም፡፡

ከዚህ ውስጥ አንድ ፕሮጀክት ማናጀር የተለመዱ አምስት ሂደቶችን ማለትም ለስራው መነሳሳት ወይም ጅማሮ (initiation)፣ እቅድ፣ ውሳኔ፣ ትግበራ፤ ክትትል እና አጨራረስ ከመደበኛ የማኔጅመንት ኃላፊነት በኃላ የሚጋራቸው የሥራ ሂደቶች በቀዳሚነት የሚቀመጡ ናቸው፡፡

ከነዚህ መደበኛ የሥራ ሂደቶች በተናጠለ መንገድ የአንድ የኮንስትራክሽን ማናጀር የሥራ ሂደት በጣም ጥልቅ ዕውቀት የሚጠይቅ እና ውስብስብ የሆነ የሥራ ሂደትን በመጋፈጥ ምላሽ መስጠትን የሚጠይቅ የሥራ ዘርፍ ነው፡፡ በአሜሪካ የኮንስትክሽን ማኔጅመንት ማህበር ያስቀመጠው መሥፈርት፣ አንድ የኮንስትራክሽን ማናጀር በአማካይ ወደ 120 የሚጠጉ ኃላፊነቶች እንዳሉበት የሚያመለክት ነው፡፡

እነዚህ ኃላፊነቶችን ለመወጣት ከሕንፃ ዲዛይን ባለሞያ፣ ከኮንትራክተር፣ ከእቃ አቅራቢዎች፣ ከሂሳብ እና በጀት ባለሞያዎች ጋር በመገኘት አስፈላጊውን ዕውቀት መቅሰም፣ ሥራን በቀላሉ እና በፍጥነት ለመሥራት የሚያስችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና መሳሪያዎችን በተመለከተ የጠለቀ የቴክኒካል ዕውቀት ማዳበር ይጠበቅበታል፡፡ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ከግምት በማስገባት አንድ የኮንስትራክሽን ማናጀርን ስኬታማ ያደርጋሉ ተብለው የተቀመጡ አምስት እቅዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

▪️በየዘርፉ የማያቋርጥ የግንኙነት መረብ መዘርጋት

ለአንድ ኮንስትራክሽን ማናጀር ወሳኝ ከሆኑ መሳሪያዎች አንዱ በእያንዳንዱ የሥራ ሂደት የሚያገኘው ትክክለኛ መረጃ ነው፡፡ በሥራ ሂደት ዕቅዶችን ለመንደፍ እና ለመተግበር ከሁሉም በላይ መሬት ወርዶ ከባለድርሻ አካላት፣ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች፣ ከኮንትራክተሮች ከሂሳብ (በጀት) ኃላፊዎች፣ ከሥራ የቡድን መሪዎች፣ ከተራ ሰራተኞች ጋር በመገናኘት የሚያገኘው መጥፎም ሆነ ጥሩ መረጃ ፈጣን፣ ውሳኔ እና ማስተካከያ ለመስጠት የሚያስችል ከፍተኛ ግብዕት ይለግሱታል፡፡

በሥራው ቦታ እና ከሚመለከታቸው አባላት ጋር የሚገኙ መረጃዎች፣ በኢሜል ወይም በስልክ ከሚገኙ መረጃዎች የበለጠ ችግሮችን በፍጥነት ለመቅረፍ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን ለመንደፍ ያላቸው ጠቀሜታም የጎላ ነው፡፡
የማያቋረጥ ዕቅድ ማውጣትን ልምድ ማድረግ
በማኔጅመንት የሥራ ዘርፍ ዕቅድ (Planning) ከአምስቱ የሥራ ሂደቶች በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ ነው፡፡

በኮንስትራክሽን የፕሮጀክት ማናጀር የሥራ ዘርፍ ደግሞ ዕቅድ የሚወጣው ሥራው ከመጀመሩ እጅግ በጣም ቀደም ብሎ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ያለማቋረጥ እየተከለሰ እና እያዳበረ መሄድ ይኖርበታል፡፡

በኮንስትራክሽን የሥራ ሂደት ዲዛይኖች፣ ቅድመ ግንባታዎች፣ ድህረ ግንባታዎች በየዘርፉ ሂደቱን እየተከተሉ መለወጥ እና መታደስ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ያልተጠበቁ ገጠመኞችን፣ የዲዛይን ለውጦችን የግብዓት እና የበጀት እጥረቶችን ማስተናገዳቸውን እንደማይቀር ቀድሞ በመረዳት፣ በተለይ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው የዘርፉ ኢንጂነሮች እና ባለሞያዎች ጋር በመገናኘት የማያቋርጥ ዕቅድ የማውጣት ልምድን በማዳበር በአቋራጭ ወደተፈለገው ግብ ለመድረስ ያስችላል፡፡

▪️በአካል እየተገኙ መጎብኘትና መጠየቅ

በየትኛውም የኢንደስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ማናጀር ከሚመራው የሥራ ዘርፍ የሥራ ሂደት እና ከበታች አካል ተነጥሎ ቢሮ ውስጥ ተቀምጦ የሚያስተላልፈው ውሳኔ፣ መሬት ወርዶ የሚያስገኘው ውጤት ባይኖርም፣ የማናጀሩ ኃላፊነት በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ከዚህ የበለጠ ትኩረትን የሚሻ ነው፡፡

ምክንያቱም የኮንስትራክሽን ሥራ ያለመቋረጥ ክትትል ካልተደረገበት እና ሥራውን በሚያጓትቱ ብዙ ውስብስብ ሴራዎች እና ጋሬጣዎች የተከበበ በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት አንድ የፕሮጀክት ማናጀር፣ ሥራው የሚካሄድበት ሳይትን እየጎበኘ፣ ከበታች ያሉትን ኃላፊዎች ወይም የሳይት መሪዎች በቦታው ተገኝቶ እያነጋገረ ተጨባጭ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ በየዓመቱ እየተለወጡ እና እያዳበሩ ሥራ ላይ የሚውሉ መሣሪያዎች እና የአሰራር ዘዴዎች መረዳት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በስኬት እንዲወጣ ያደርጉታል፡፡

▪️በጀት እና ወጪን መቆጣጠር

አንድ የፕሮጀክት ማናጀር እቅድ ነደፎ ወደ ተግባር ሲገባ ቀድም ብሎም ሆነ በየሂደቱ ከሚያስባቸው ነገሮች አንዱ፣ ለሥራው የሚያስፈልገው በጀት እና ወጪን በተቀመጠለት ጊዜ ሳይስተጓጎል ማግኘት ወይም ማወራረድ ነው፡፡

ወደ ተግባር ሲመጣ ደግሞ የኮንስትራክሽን ሥራ ቀደም ብሎ ለመገመት የሚያስቸግሩ ቀጥተኛ ያልሆኑ ወጪዎችን ይዞ ከተፍ የሚል የሥራ ዘርፍ ነው፡፡ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚሰማራ የሒሳብ ባለሞያ ደግሞ ሂደቱ ህጋዊነት እየተከተለ እንዲወራረድ ከማድረግ ወጪ፣ ወደፊት የዋጋ ንረት ሲፈጠር፤ ለሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ ሲጓተት ሥራውን እንዲያጓትት የሚያደርግ ተፅእኖ በመፍጠሩ ለዚሁ እልባት የሚያስገኝ ከእቅድ ውጪ የሆነ የገንዘብ ጥያቄ ቢቀርብ ኃላፊነቱን ፕሮጀክት ማናጀሩ ላይ ከመወዘፍ ውጪ የመወሰን ኃላፊነትም የሌለው እና ተጠያቂነት በመፍራት በጥንቃቄ መጓዝን ምርጫው ያደርጋል፡፡

ከዚሁ በመነሳት፣ አንድ የፕሮጀክት ማናጀር የሚቀርብለትን የግዥ ጥያቄ እና የወጪ ሰነድ መፈረም ብቻ ሳይሆን፣ ከመደበኛ ወጪው ከፕሮጀክቱ የሥራ ሂደት እና ዕድገትን እየገመገመ መቆጣጠር እንደ አስፈላጊነቱም መገደብ ይኖርበታል፡፡ ይህን በሚያደርግበት ጊዜ ተጨማሪ የሥራ ጫና እንዳይፈጠርበት የሚያደርጉ እንደ "ዶኩ ሳይን" የመሳሰሉ የወጪ እና የበጀት መቆጣጠሪያ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም በቀላሉ ለመቆጣጠር ይችላል፡፡

▪️የተቀናጀ የሪፖርት ዘዴን መከተል

አንድ የፕሮጀክት ማናጀር በየቀኑ ለሚቀርቡለት የኢሜይል ጥያቄዎች፣ የስልክ ጥሪዎች፣ የበጀት ጥያቄዎች፣ የሥራ ሂደት ሪፖርቶች በሙሉ ምላሽ የሚሰጥበት ጊዜ አይኖረውም፡፡ ለነዚህ ጥያቄዎች የተቻለውን ያህል ምላሽ ለመስጠት ቢሞክር እንኳ፣ ዋና የሥራ ክትትሎችን በማጓተት የሚያስከትልበት ጉዳት እና ጫና እየጨመረ መሄዱ አይቀሬ ነው፡፡

ለዚህ ችግር መፍትሄው ደግሞ አውቶሞቴድ ሪፖርቲንግ ሲስተም የተባለ የሪፖርት ዘዴን በመከታተል ለእያንዳንዱ ጥያቄ የሚፈልገው አካል ምላሽ እንዲሰጥ የሚያደርጉ፣ ሳምንታዊ የሥራ ሂደቶችን፣ ሪፖርቶችን፣ የገንዘብ ጥያቄዎችን በየዘርፉ እየተቀበሉ በተቀላጠፈ ብሎም በአጭር ጊዜ እና አቀራረብ ሪፖርት የሚያደርጉ ሶፍትዌሮችን ወይም የኮምፒዩተር ዘዴዎችን መጠቀም ይኖርበታል፡፡

#ConstructionMangment

@etconp
👍22❤5
👉Types of Construction Contracts

🚧1. Lump sum Contract
In a lump sum contract, the engineer or/and contractor agrees to do the specified project for a fixed price. Also called “fixed fee contracts,” these are often used for engineering ventures.
A lump sum or fixed fee contract is appropriate if the scope and schedule of the project are sufficiently defined to allow the consulting engineer to estimate project costs.

🚧2. Unit price Contract
A unit price contract is a type of construction contract based on estimated quantities of items included in the project and their unit prices as initially estimated (rates may be hourly, the rate per unit work volume, etc.). In general, the contractor’s overhead and profit are included in the rate. The final cost of the work depends on the total quantity of items required to carry it out and complete it.
Unit price contracts are appropriate only for a project which involves well-known resources in quantities which are unknown at the time of the agreement, and will be defined when the design and engineering or construction work is finished.
A unit price agreement is one of the best choices for construction or supplier projects where the contract documents can correctly identify the various kinds of items, but not the numbers that are needed.
It is not uncommon to combine a unit price contract with a lump sum contract or other types of agreement for some parts of the project.

🚧3. Cost Plus Contract
This is a contract agreement wherein the purchaser agrees to pay the cost of all labor and materials, plus an amount for contractor overhead and profit (usually stated as a percentage of the labor and material cost). In construction, a cost-plus contract may be specified as:
Cost-Plus + Fixed Percentage
Cost-Plus + Fixed Fee
Cost-Plus + Fixed Fee With Guaranteed Maximum Price
Cost-Plus + Fixed Fee + Bonus
Cost-Plus + Fixed Fee With Guaranteed Maximum Price and Bonus
Cost-Plus + Fixed Fee With Agreement for Sharing Any Cost Savings
Cost-plus contracts are preferred when the scope of the work is indeterminate or highly uncertain and the kinds of labor, material and equipment needed are also uncertain.
Under this arrangement, complete records must be maintained of all time and materials that the contractor spends on the work.

🚧4. Time Materials Contract
Contracts for time and materials (T&M) are a hybrid of fixed and cost-reimbursing contracts, and are used in cases where there can be no clear scope of work: for example, if the number of hours that the client needs is not clear.
In this case, a set professional hourly rate is used (for instance, fees and costs). With this kind of contract, it’s always a good idea to set a ceiling or a price that cannot be exceeded, to prevent being overrun with heavy costs.

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍11❤9
👉በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ መሾማቸውን አስተዳደሩ አሳውቋል።

በተጨማሪ ለአዲስ ከተማ ፣ ለሚኩራ፣ አራዳ ፣ ጉለሌ ክፍለ ከተሞች አዳዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ተሹመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተሰጠ በለው ሹመት እና ሽግሽግ አቶ ሲሳይ ጌታቸው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል። በዚሁ ቦታ ላይ የነበሩት ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ተነስተዋል።

አቶ አውራሪስ ከበደ ደግሞ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ሆነው ተሹመዋል።

በሌላ በኩል ፤ ወ/ሮ አይዳ አወል የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ አቶ አበበ ተቀባ የአራዳ ክ/ከተማ ፣ አቶ ወልዴ ወገሴ የጉለሌ ክ/ከተማ፣ አቶ ታረቀኝ ገመቹ የለሚኩራ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸው ተነግሯል

@etconp
👍11❤1👏1
👉ኣስደሳች ዜና

🌟በ 0 አመት የ ስራ ልምድ የውጡ እና ሌሎች የ CIVIL,COTM, SURVEYING ባጠቃላይ በ ኮንስትራክሽን ዘርፉ ኣዳዲስ የ ስራ ማስታወቂያዎች ስለደረሱን ከታች ባለው ሊንክ ተቀላቅለው መመልከት ትችላላቹ።

🫵ለወዳጅችዎ ሼር በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ

https://t.me/ETCONpWORK
👍5🙏5❤1
Wuhalek with Architect Rahel Shawel and Dawit Benti 28-05-14.MP3
54.1 MB
👉በ FM 107.8 በውሀ ልክ ኮንስትራክሽን ቶክ ሾው ዳዊት በንቲ ከራሄል ሻውል ጋር ያደረገው ጭውውት እንድታደምጡት ተጋብዛችኋል።

#Architecture

@etconp
❤4👍4👌1
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን የባቡር መስመር ልትዘረጋ መሆኑ ተገለጸ!

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን የባቡር መስመር በ13 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ልትዘረጋ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

ኬንያ የምትዘረጋው ይህ ፈጣን የባቡር መስመር በኤሌክትሪክ የሚሰራ ሲሆን፤ መነሻውን ከህንድ ውቅያኖስ ላሙ ወደብ በማድረግ ኢትዮጵያን እና ደቡብ ሱዳንን እንደሚያገናኝ ብሉምበርግ ዘግቧል።

በዓይነቱ ልዩ ነው የተባለው ይህ የባቡር መስመር በፈረንጆቹ 2025 ሥራ እንደሚጀመር እና 3 ሺሕ ከሎ ሜትር ወይም 1 ሺሕ 864 ማይል እንደሚረዝም ታውቋል፡፡

የባቡር መስመሩ መነሻውን ከህንድ ውቅያኖስ አድርጎ፣ በኬንያዋ ማዕከላዊ ከተማ ኦሲዮሎን በኩል፣ ናይሮቢን እና አዲስ አበባን በማገናኘት የመጨረሻም መዳረሻውን ደቡብ ሱዳን ጁባ እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡

ይህ ፈጣን የባቡር መስመር “ኢትዮጵያ በአሰብ እና ምጽዋ እንዲሁም ጅቡቲ ወደቦች ላይ ያላትን ጥገኝነት የሚቀንስ ነው” የተባለ ሲሆን፤ ሌሎች በርካታ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች እንዳሉትም ተገልጿል፡፡

በዚሁ ፈጣን የባቡር መስመር ዝርጋታ አማካኝነት ደቡብ ሱዳን ኹለተኛ ወደብ እንደሚኖራትም ተመላክቷል።

የባቡር መሾመር ዝርጋታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠጥ በሚጀምርበት ወቅት፣ ከላሞ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ውል የፈጸመው ላፕሴት፣ በዓመት ከ29 ሚሊዮን ቶን በላይ ጭነት እና 700 ሺሕ ተጓዦችን እንደሚያመላልስ አስታውቋል። 

Via Addis Maleda

@etconp
👍9❤2
👉ETCONp CHALLENGE

🌟ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ ኣንድ ቻሌንጅ ይዘን መጥተናል ይህም የ FACEBOOK እና YOUTUBE ቤተሰቦቻችን ለማብዛት እና ይበልጥ ለመማማር በማሰብ ሁለቱም ገፆቻችን SUBSCRIBE እና LIKE ላደረጉ የዚህ ገፅ ቤተሰቦቻችን የፈለጉት ማለትም PDF መፅሀፍ፣ሶፍትዌር ወይም ቲቶርያል ቪድዮ ኣንዱን መርጠው @COTMp ይፃፉልን ወድያውን በግልዎ እንልክሎታለን።

🫵Like እና Subscribe ካረጋቹ በኋላ Screen Shoot @Philemona7 ላኩልን።

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

🙏እናመሰግናለን❤️

⚡️ጀምሩ ጀምሩ ጀምሩ

@etconp
👍3👏3❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉The Three Gorges Dam in China is on the verge of breaching.

🚧It is the world's largest power plant by installed capacity at 22.5 GW

🌟Due to unprecedented heavy rains, the dam is now under threat.

@etconp
❤7👍3💔1
👉"ፏፏቴ" ሕንፃ በቻይና

🚧ቻይና በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ያስመዘገበችው ስኬት በአገሯ ብቻ ሳይሆን አሻራዋን በመላው አለም በማሳረፍ ትታወቃለች።

🌟ስሞኑን ደግሞ ከቻይና የተሰማው ወሬ "ወይ ጉድ ይኸች አገር" ብለን አፋችንን በእጃችን እንድንይዝ የሚያደርግ ነው።

🚧አሁን አሁን የቻይና የግንባታ ባለሙያዎች ከተለመደው የግንባታ ልማድ ወጣ ባለ መልኩ፣ አዳዲስ ፈጠራዎችን በሁሉም የግንባታ ሥራዎቻቸው ውስጥ ለማሳረፍ እየተጉ ይገኛሉ።

🚧በቅርቡም አዲስ የተገነባው ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ወደ ምድር የሚወረወር ፏፏቴ እንዲኖረውም አድርገው ገንብተውታል።

🚧ባለፏፏቴው ሕንፃ ከ350 ማይልስ ወይም ከ106 ሜትር የሚምዘገዘግ ፏፏቴ አለው። ውሃውን ወደ ላይ ለመውሰድ አራት ፓምፖች ተግባራቸውን ይወጣሉ።

🚧ከሁሉም ከላይ የሕንፃው ባለቤት "Guizhou Ludiya Property Management" እንደ ችግር ያስቀመጠው የኤሌክትሪክ ፍጆታውን ነው። ፏፏቴውን በሥራ ላይ ለማቆየት በሰአት 100 ዶላር ክፍያ አለበት።

🚧በዚህ የተነሳ ፏፏቴውን ሁሌም አንዲሰራ ማድረግ አዋጪ አይደለም። በአላትን እና ልዩ ፕሮግራሞችን ታሳቢ እየተደረጉ ፏፏቴው እንዲሰራ ይደረጋል ተብሎል። ሕንፃው የተገነባባት የጉያንግ ከተማ ከወዲሁ የቱሪስቶችን ቀልብ መሳብ ጀምራለች።

@etconp
👍13❤2
👉የኪነህንጻ ተማሪዎች አገር አቀፍ ማህበር

🚧የአሜሪካ ኪነህንጻ ተማሪዎች ማህበር ወይም American Institute of Architecture Students በ1956 እኤአ የተቋቋመ ጠንካራ የተማሪዎች ማህበር ሲሆን በአሜሪካ በኪነህንጻ ትምህርት ዙሪያ ከተቋቋሙ አምስት ጠንካራ ተቋማት አንዱ ነው።

🌟አላማውን ተልእኮውንና ራዕዩን በተመለከተ ከታች የተያያዘውን ድረገጽ ማየት ይቻላል።

🚧በተረፈም በአሜሪካን ግዛቶች ባሉ ሁሉም የኪነህንጻ ትምህርት ቤቶች በተያያዘው ምስል መልክ የአባልነትና የተሳትፎ ጥሪ ያቀርባል።

🫵የአገራችንም የኪነህንጻ ተማሪዎች ከዚህ አንጋፋ ማህበር ትምህርት ቀስመው አገርአቀፍ ማህበር ሊፈጥሩ ይችላሉ።

https://www.aias.org/

@etconp
👍8
የህዳሴው ግድብ የቴክኒክ ባለሙያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ዳግም ተጀመረ

ኢትዮጵያ የግድቡን የዘንድሮ ውሀ ሙሌት ወደ መስከረም አራዝሜያለሁ ማለቷ ይታወሳል

ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪው አባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተለያዩ ምክንያቶች መቋረጡ ይታወሳል።

በሱዳን እና በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት ለሶስትዮሽ ድርድር አለመቀጠል እና የግብጽ ተለዋዋጭ አቋም ማሳየት ለድርድሩ አለመሳካት ዋነኞቹ ምክንያቶች ነበሩ።

ከአንድ ወር በፊት በግብጽ ካይሮ በሱዳን ለተከሰተው ጦርነት እልባት ለመፈለግ በሚል በተካሄደው የጎረቤት ሀገራት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እግረ መንገዳቸውን ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ  አልሲሲ ጋር መክረዋል።

በዚህ ስምምነት መሰረትም የሶስቱ ሀገራት የህዳሴ ግድብ የቴክኒክ ባለሙያዎች በግብጽ መዲና ካይሮ ተገናኝተዋል።

የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን በዛሬው ውይይታቸው በቀጣይ ስለሚደረጉ ድርድሮች፣ የመወያያ አጀንዳዎች፣ እና በሶስቱ ሀገራት ልዩነቶች ዙሪያ እንደሚወያዩ ተገልጿል።

ከ12 ዓመት በፊት የተጀመረው ታላቁ የህዳሴው ግድብ ግንባታ 84 በመቶ ደርሷል የተባለ ሲሆን የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ሀይል በማመንጨት ላይ ናቸው።

በጣልያኑ ሳሊኒ የግንባታ ተቋራጭ ኩባንያ እየተገነባ ያለው የህዳሴው ግድብ አራተኛው የግድቡ ውሀ ሙሌት ከቀናት በኋላ እንደሚጀመር ይጠበቃል።

@etconp
👍14❤1