🌟አዲስ ዐመት ሲመጣ አደይ አበባ ትዝ ይላል፣ በዛውም ግንባታው 900 ቀን ብቻ ይፈጃል ተብሎ ተነግሮለት አሁን 8 አመት ሊሞላው ትንሽ ወራት የቀረው አደይ አበባ ስታዲየምም ሊታወስ ይችላል።
🚧የግንባታውን የአመታት ሂደት ከሳተላይት ምስሎች ያስቀረሁበትን ይህን ምስል ላጋራችሁ።
Via Elias
@etconp

👏5👍2
🌟የሚፈጀው 1 ትሪሊየን ብርም ሆነ አሁን ላይ አስፈላጊነቱ የብዙዎች መወያያ ርዕስ የሆነው "ጫካ ፕሮጀክት" ከሳተላይት ይህንን ይመስላል።
የሳተላይት ምስሉ እንደሚያሳየው የግንባታ ስፍራው 276,000 ገደማ ካሬ ላይ ያርፋል። በደረሰኝ መረጃ መሰረት ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ለሚደረጉ ድርጅቶች ተጨማሪ ቦታ ይሰጣል፣ እንዲሁም የሁለተኛ ዙር ማስፋፍያ ፕሮጀክት እንዲኖረው ጥናት በቅርቡ ይጀመራል።
ይህ ፕሮጀክት በተለይ በአሁን ወቅት አስፈላጊ ነው ብለው ያምናሉ?
ተወያዩበት!

🕊9👍4😢2
👉Managing dust and debris during house remodeling or renovations time
የሕንፃ ግንባታዎችን ዲዛይን መለወጥ እና እድሳት ማካሄድ ቀላል ሥራ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፡፡
የንግድ ሱቆችን እንዲሁም መኖሪያዎችን ለማደስ እና የዲዛይን ለውጥ ለማድረግ የሚካሄዱ ግንባታዎች እጅግም በጣም አድካሚ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡
በተለይ በሥራው ሂደት የሚፈጠሩ ፍርስራሾችን ቀደም ብሎ ለማስወገድ የሚያስችሉ ዝግጅቶች ካልተደረጉ ድካሙን የጎላ ከማድረጉም በላይ ብክነትንም ይጨምራል፣ ብክለትም እንዲፈጠር ያደርጋል፣ ለጤናም አደገኛ ነው፡፡
የግንባታ ባለሙያዎች እና ባለቤቶች በነባር ግንባታዎች ላይ እድሳት ወይም የዲዛይን ለውጥ ሲያደርጉ ከሚዘነጓቸው ጉዳዮች ዋነኛው በሥራው ወቅት የሚፈጠረውን የአቧራ እና ፍርስራሽ ክምርን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለጤና ጠንቅ በሆኑ አቧራዎች፣ የሊድ እና የአስፔስቶስ ብናኞች እንዲጠቁ ያደርጋቸዋል፡፡
ከዚህ የከፋ ውጣ ውረድ ለመዳን ከሚያስችሉ ዘዴዎች "Managing dust and debris during house remodeling or renovations time" በሚል ርዕስ ከሰፈሩ የባለሙያ ምክሮች ውስጥ የሚከተሉት አምስቱ በቀዳሚነት ይቀመጣሉ፡፡
1. የአቧራ እና የፍርስራሽ ጎጂነትን መረዳት
የአቧራ እና የፍርስራሽ ጎጂነትን በቀላሉ መረዳት ዋናው አንገብጋቢ ጉዳይ ከመሆን ባለፈ፣ የማፅጃ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት እና ቆሻሻን ቀብሮ ማስወገድን ማንም አይዘነጋውም፡፡ ችግሩ በቤት ቁሳቁሶች፣ ወለል እና ግድግዳዎች ላይ የሚያርፉ ቆሻሻዎች ሙሉ በሙሉ ማፅዳት አለመቻሉ እና በሂደት ወይም ውሎ አድሮ የጤና ጠንቅ መሆናቸው ነው፡፡
ለእንዲህ ዓይነት ችግር መፍትሄው በአየር ውስጥ የሚገኙ እና የሚተኑ እንደ ሊድ ብናኝ ዋናው ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም የአሸዋ፣ የድንጋይ እና የማዕድን ብናኝ በመተንፈሻ አካላችን ገብተው እንደ ሲልኮሲስ ያሉ የጤና ጉዳቶችን እንዳያስከትሉብን፣ በሥራው ሂደት የመተንፈሻ አካላችንን ከጥቃት የሚከላከሉ እንደ ኦክሲጅን ማስክ የመሳሰሉ የፊት ጭምብሎችን ማጥለቅ እንዲሁም አፍ፣ አፍንጫችንን እና አይናችንን ከብናኞቹ የሚከላከሉ መሣሪያዎች መጠቀም ተገቢ ርምጃ ነው፡፡
2. አስፈላጊ የብክለት መከላከያ በጀት መመደብ
እድሳት ወይም የዲዛይን ለውጥ ሲደረግ እንደ ግንባታው ወጪ ከላይ የተጠቀሱ ብክለቶችን ለማስወገድ የሚያስችሉ የቁሳቁስ መሸፈኛ የማፅጃ እና የሰውነት ብክለት መከላከያ መሣሪያዎችን ለመግዛት የሚያስፈልግ በጀት መድቦ ቀደም ብሎ ማዘጋጀት ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ የግንባታ ወጪ ሲታሰብ በተጨማሪ ቢያንስ 1ዐ በመቶ ተጨማሪ በጀት መመደብ ይገባል፡፡
3. ቁሳቁሶኝ ከቤት ማውጣት
ፍርስራሽ ብናኞች እንዳይፈጠሩ መከላከል ባይቻልም፣ ከቤት ውስጥ የሚገኙ መገልገያ መሣሪያዎችን እና ቀደም ብሎ ቁሳቁሶቹን ከቤት ውስጥ አውጥቶ ንጽሕናውን በተጠበቀ መጋዘን ወይም ክፍል ውስጥ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ ምን አልባት አንዳንድ ቁሳቁስን ከቤት ለማውጣት አስቸጋሪ ወይም ከፍተኛ የማጓጓዣ ወጪን ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ለዚሁ አማራጭ መፍትሔ ተብሎ የተቀመጠው ቁሶቹ ላይ ብናኝ እንዳያርፍ የሚያስችሉ መሸፈኛዎችን በመጠቀም በሚያስተማምን መንገድ መሸፈን ነው፡፡
4. ወለሉን እና ቋሚ ቁሶችን መከላከል
ወለሎችን እና የማይንቀሳቀሱ ቁሶችን በአቧራ እና ብናኝ እንዳይበከሉ፣ እንዳይጫጫሩ እንዲሁም እንዳይጐዱ ለመከላከል በሚያስችሉ እንደ ታርባዩሊን ባሉ አስተማማኝ መከላከያዎች መሸፈን ይገባል፡፡
5.ሥራዎች በተቻለ መጠን ወጪ መሥራት
በመጨረሻም፣ በእድሳት ወቅት የሚበየዱ ብረቶችን፣ የሚቆረጡ እንጨቶችን የሚቦካ ኮንክሪት እና ሲሚንቶን ከግንባታው ራቅ ባለ ገላጣ ሜዳ ላይ የማይዘጋጅበት ምንም በቂ ምክንያት አይኖርም፡፡ እንደተጠቀሱት ያሉ ሥራዎችን ከግንባታ ራቅ ባለ ሜዳ ላይ ማከናወን ከዘላቂ ብክለት ከመጠበቅ ባለፈ፣ በቀጣይ በቀላሉ ንጹህ የመኖሪያ ወይም የመስሪያ ከባቢን ለመፍጠር ያስለችናል፡፡

👍4😁1
🌟የአለማችን ትልቁ ጌት ቫልቭ (የውኃ መስመር መክፈቻና መዝጊያ) በአሜሪካ ቴክሳስ ውስጥ ተገጥሞ በሥራ ላይ ውሏል።
🚧ይህ ግዙፍ ቫልቭ 40 ቶን ክብደትና 40 ጫማ (12.2 ሜትር) ርዝመት አለው።
@etconp
🚧ይህ ግዙፍ ቫልቭ 40 ቶን ክብደትና 40 ጫማ (12.2 ሜትር) ርዝመት አለው።
@etconp
👍8
👉ለአዲስ አበባ ከተማ የጠጠር መንገዶች ይመጥኗታል?
🚧
እስከ አሁን ድረስ የከተማው መንገዶች ባለስልጣን በርካታ የአስፋልት መንገዶች ግንባታ እያካሄደ መሆኑን የሚታወቅ ነው። ከዚያም አለፍ ሲል በስፋት የኮብልስቶን ግንባታ ሲካሃድ ቆይቷል።
በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች በከተማ ውስጥ መገንባት አዋጪነቱ የሚያጠያይቅ ነው። ከአቅም ማነስና ከበጀት እጥረት ጋር የተያያዙ ጉዳይች እንኳን ካሉ ከጠጠር መንገድ ይልቅ የኮብልስትን መንገዶችን መገንባት አዋጪ ነው።
ይሁን እንጂ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ መሰረተ-ልማት ተደራሽነትን ለማሳደግ በአዳዲስ የመኖሪያ አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች በመገንባት ላይ ናቸው።
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በመረጃው፦ የከተማዋን የመንገድ ኔትወርክ ይበልጥ በማስተሳሰር ደህንነቱ የተጠበቀ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ለማስቻል ከሚያካሂደው መጠነ ሰፊ የመንገድ መሰረተ-ልማት ግንባታና ጥገና ሥራ ጎን ለጎን፤ የመንገድ መሠረተ ልማትን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ አዳዲስ መንደሮች በተገነቡባቸው አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች በመገንባት ላይ መሆኑን ይገልፃል።
አሁን ላይ በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገድ እየተገነባባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ከናሆም አደባባይ - ገልማ አባገዳ ፣ ከናሆም አደባባይ - ሃና ማርያም መውጫ፣ ላምበረት አካባቢ እንዲሁም ከሲ.ኤም.ሲ - የተባበሩት አካባቢ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
@etconp
🚧
ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የተገኘው መረጃ፦ "በአዳዲስ የመኖሪያ አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች እየተገነቡ ነው" ይላል። እስከ አሁን ድረስ የከተማው መንገዶች ባለስልጣን በርካታ የአስፋልት መንገዶች ግንባታ እያካሄደ መሆኑን የሚታወቅ ነው። ከዚያም አለፍ ሲል በስፋት የኮብልስቶን ግንባታ ሲካሃድ ቆይቷል።
በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች በከተማ ውስጥ መገንባት አዋጪነቱ የሚያጠያይቅ ነው። ከአቅም ማነስና ከበጀት እጥረት ጋር የተያያዙ ጉዳይች እንኳን ካሉ ከጠጠር መንገድ ይልቅ የኮብልስትን መንገዶችን መገንባት አዋጪ ነው።
ይሁን እንጂ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ መሰረተ-ልማት ተደራሽነትን ለማሳደግ በአዳዲስ የመኖሪያ አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች በመገንባት ላይ ናቸው።
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በመረጃው፦ የከተማዋን የመንገድ ኔትወርክ ይበልጥ በማስተሳሰር ደህንነቱ የተጠበቀ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ለማስቻል ከሚያካሂደው መጠነ ሰፊ የመንገድ መሰረተ-ልማት ግንባታና ጥገና ሥራ ጎን ለጎን፤ የመንገድ መሠረተ ልማትን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ አዳዲስ መንደሮች በተገነቡባቸው አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች በመገንባት ላይ መሆኑን ይገልፃል።
አሁን ላይ በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገድ እየተገነባባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ከናሆም አደባባይ - ገልማ አባገዳ ፣ ከናሆም አደባባይ - ሃና ማርያም መውጫ፣ ላምበረት አካባቢ እንዲሁም ከሲ.ኤም.ሲ - የተባበሩት አካባቢ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
@etconp
👏7👍3❤1
👉በህዳሴ ግድብ ሌላኛ ትልቅ ሙሌት በዚህ አመት ተከናውኗል፣ ትልቅ ስኬት ነው!
አንዳንዶቻችሁ "ዜናውን ሳትዘግበው" የሚል መልዕክት አድርሳችሁኛል፣ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ብቻ ሁለት ግዜ ሙሌቱ እየተጠናቀቀ እንደሆነ መረጃ ስላቀረብኩ ቢያንስ ለሶሻል ሚድያ ገፆቼ ተከታታዮች ብዙም አዲስ አይደለም በሚል ነው።
በነገራችን ላይ፣ አራተኛ ሙሌቱ መከናወኑን ተከትሎ ጠ/ሚር አብይ አህመድ "የመጨረሻ ሙሌት" ብለው ጠቅሰውት ነበር። ቲክቫህ እንዳስነበበን ይህንን በተመለከተ ቃላቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ የሰጡት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ "አራተኛና የመጨረሻው የውሃ ሙሌት የተባለው አራቱ ዙሮች ከፍተኛ የውሃ መጠን የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ነው፣ በእነዚህ አራት ዙሮች ግድቡ መያዝ ያለበትን የውሃ መጠን መያዝ ችሏል። አራተኛና የመጨረሻው ሲባልም ከዚህ በኋላ የውሃ ሙሌት አይደረግም ማለት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት። ይልቁንም ግድቡ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ከፍተኛ የውሃ መጠን ሳያስፈልግ ይከናወናል" ብለዋል።

👍7❤5
👉ከተማ እየገነባ ያለው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፤ ቀለም እየቀቡ ኪራይ ከመሰብሰብ ሪል ስቴትን ወደ መገዳደር ያመራ ተቋም፤
ዛሬ ጸሐይ ስለሞቀው ሀቅ እነግራችኋለሁ፡፡
ወደ 2016 በስኬት ከሚጓዙ የሀገራችን መንግስታዊ ተቋማት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አንዱ ነው፡፡ ይህ ተቋም ለዓመታት የደርግ አዋጅ ያጎረሰውን አፉ ላይ ይዞ ያንን እያመነዠገ ከሚኖርበት ድንዛዜ ወጥቷል፡፡
በተለይም አሁን ተቋሙን እየመሩ ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ረሻድ ከማል ልታይ ልታይ ያለማለት ድምጻቸውን አጥፍተው የሚመሩትን መስሪያ ቤት ሌላ ተአምር ውስጥ አስገብተውታል፡፡ ሚዲያዎች ወደ እሳቸው ሄዱ እንጂ ወደ ሚዲያ አልመጡም ነበር፡፡ የተቋሙ ስራ አፍጦ መነጋገሪያ ሲሆን አሁን መገናኛ ብዙሃንም ስለ ፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ማውራት ጀምረዋል፡፡
ያ አከራይቶ ኪራይ እየሰበሰበ እጁ ላይ ቤት የሚወድቅበት ተቋም አሁን አዲስ አበባ ዓይን ውስጥ የሚገቡ ህንጻዎችን በአጭር ጊዜ እውን አድርጓል፡፡ በርካታ ቤቶችን ሰርቷል፡፡ ነባር ቤቶችን በዘመናዊ መልክ ለመያዝ ጥረቶች እያደረገ ነው፡፡
ኮርፖሬሽኑ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚስተዋለውን የግብዓት አቅርቦት እጥረትን የሚያቀሉ የኮንክሪት ውህድ እና ብሎኬት ማምረቻ ማሽን ተከላ ለማከናወን የግንባታ ፕሮጀክት ሥራ መጀመሩ ተበስሯል፡፡ በቀን ከ60 ሺህ በላይ ብሎኬቶችን የሚያመርተው ይህ ፕሮጀክት ለኮርፕሬሽኑ በዓመት ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ያስገኛል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ስኬት ሪፖርት አይደለም፡፡ መካኒሳ፣ አዋሬ፣ ተዘንዓ፣ ቀበና፣ ሱማሌ ተራ በመሳሰሉት አካባቢዎችመሬት ላይ የቆሙ ሕንጻዎች ትናንት ያልነበሩ ዛሬ የሚታዩ ናቸው፡፡ በ2010 ዓ.ም. 300 ሚሊዮን ብር ገቢ የነበረው ተቋም 2015 ዓ.ም. ላይ ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል የሚለው ዜና ቁጥር ብቻ ተብሎ የሚታለፍም አይመስለኝም፡፡
ተቋም እዚህ እዚያም ግሩም ግንባታዎችን እያነጸ ቤት ገንብቶ ከተማ እያነጸ እንደሆነ እንደ ገርጂ ያሉ ሳይቶች ማሳያ ናቸው፡፡ እናም በእኔም እምነት ያለ ግርግር ትልቅ ስራ ሰርቶ ዓመቱን በስኬት ያጠናቀቀ ተቋም ብባል የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እላለሁ፡፡
ቀለም ከመቀባት እና ቧንቧ ከመጠገን ውጪ እዚህ ግባ የማይባል ስኬት ሳያስመዘግብ እጅና እግሩ ታስሮ የኖረውን ይሄንን ተቋም ከድንዛዜ በማውጣት አሁን ሪል ስቴት የሚገዳደር ሆኗል፡፡
የተቋሙ ሥራ አስፈጻሚ የሚመሩት የልዑካን ቡድን ሰሞኑን በሀገረ እንግሊዝ ለንደን የስራ ጉብኝት አድርጎ ነበር፤ በእንግሊዝ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን ጋር በዳያስፖራ የመኖሪያ ቤት ፕሮግራም ላይ ተወያይቷል፡፡ ለዲያስፖራው የሚሆኑ ጥራት ያላቸውን ቤቶች ገንብቶ ለማቅረብ ወጥኗል፡፡ ልዩ የሚያደርገው ግን የፕሮጀክት ፍጥነቱ ከጥራት ጋር ሳይነጣጠል በአጭር ጊዜ የሚሳካ መሆኑ ነው፡፡
እንደ እኔ ደግሜ እላለሁ ይህንን ያሳለፍነውን ዓመት በስኬት ተሻገርነው ማለት ከሚችሉ ጥቂት የመንግስት ተቋማት አንዱ ይሄ መስሪያ ቤት ነው፡፡ በዚህ ፍጥነት እና ስኬት ከቀጠለ በቀጣዮቹ አስርና አስራ አምስት አመታት በእርግጠኝነት ተአምር ሰርቶ እንደ አህጉር ምሳሌ የሚሆን ተቋም ይሆናል፡፡
Via አስቻለው እውነቱ

❤9👍6
👉
1,ፕሪ እስትረስድ ኮንክሪት👇
▶️ኮንክሪቱ ላይ ሎድ ከመጫኑ በፊት Axial Compressive Stress አፕላይ ይደረግባቸል።
⏺ለምሳሌ አንድን ቢም ከጎንና ከጎን Compressive ፎርስ ስናደርግበት የ ‹‹ በ ›› ፊደል አይነት ቅርፅ ይኖረዋል (ሲጋነን) ኢሄ የታጠፈው ቢም እላዩ ላይ ሎድ ሲጫንበት ቢሙ ወደ ነበረበት ቦታው ይመለሳል።
🚩እንደዛ ነው pre-stressed ኮንክሪቶች act የሚያደርጉት
🚧PSC Vs RC
➡️1 RC beam ላይ ለዲዛይን assume ስናደርግ ኮንክሪቱ ምንም አይነት tensile stress አይሸከምም - tensile እስትረሱን የሚሸከመው ፌሮው ነው ብለን ነው ሌላው assumption ፌሮው ቴንሽኑን ይሸከማል ብንልም የፌሮውን አቅም fully utilize አናደርገውም ወይም ደሞ ሙሉ ለሙሉ አንጠቀምበትም የዚህም ምክንያቱ ኮንክሪቱ ቴንሽን ዞን ውስጥ የሚከሰተውን Crack width ለመገደብ ወይም limit ለማድረግ ነው።
⏹ከላይ በተገለፁት ሁለት ምክንያቶች ማለትም የኮንክሪቱንም የፌሮውንም አቅም ሙሉ ለሙሉ ባለመጠቀማችን የተነሳ ለትልልቅ ሎዶች RC ከ PSC አንፃር ኢኮኖሚካል አይደለም።
⏹የዚህም ምክንያቱ የ RCን አቅም ሙሉ ለሙሉ ስለማንጠቀምበት ነው በተጨማሪም RC ላይ ትልልቅ Grade ያላቸው ኮንክሪትና ፌሮ መጠቀማችን ብዙም ዋጋ የለውም ከ RC ድክመት ለመዳን Pre-Stressed ኮንክሪቶች ተፈጠሩ ከRC በተሻለ መልኩ የኮንክሪቱንና የብረቱን እስትሬንግዝ ይጠቀማሉና።
🚧Methods of Prestressing
➡️1) Pre tensioning👇
⏺ቢሙን ካስት ማድረጊያ mold እናዘጋጃለን።
⏺ሞልድ ውስጥም PSC ኬብሎች ወይም tendon
እናስቀምጣለን
⏺እነዚህ ኬብሎችም ላይ Tensile ፎርስ apply እናደርጋለን
⏺አፕላይ እንደተደረገ ኮንክሪቱን ሞልድ ውስጥ አስገብተን ኮንክሪቱን ካስት እናደርጋለን
⏺ኮንክሪቱ ሲደርቅ ፎርሶቹን remove እናደርጋለን ቢሙም ዝግጁ ሆነ ማለት ነው::
➡️2) Post tensioning👇
⏺እዚህ ላይ ኮንክሪቱ ከደረቀ በኋላ ነው Compressive force አፕላይ የምናደርገው
⏺Apply የሚደረጉት ፎርሶች ኮንክሪቱ ላይ compressive stress ሲፈጥሩ ብረቱ ላይ ደሞ tensile stress ይፈጥራሉ ማለት ነው::
#Concretetechnology
@etcpnp
PRE-STRESSED CONCRETE (PSC) VS REINFORCED CONCRETE (RC)1,ፕሪ እስትረስድ ኮንክሪት👇

👍17
የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 እስከ 23 /2016 ዓ/ም ይሰጣል ተብሏል።
ፈተናው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ይሰጣል።
ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ ፦
የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 21-23/2016 ዓ.ም በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በበየነ-መረብ የሚሰጥ መሆኑን፤ እና ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው Graduate Admission Testing (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ከመስከረም 11 - 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በበየነ መረብ ማመልከት እንደሚገባቸው ፤
ተፈታኞች ለፈተና ሲያመለክቱ ፈተናውን ለመውሰድ የሚከፈለውን ክፍያ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በቴሌ ብር እንዲከፍሉ ከወዲሁ የቴሌ ብር አካውንት መክፈት እንደሚገባቸው መረጃው በትክክል እንዲያውቁ እንዲደረግ ፤
- ተቋማት ለመማር ያመለከቱና የሚያመለክቱ አመልካቾችን በበየነ መረብ እንዲያመለክቱ እንዲሁም የፈተና ፕሮግራምና ተያያዥ መረጃዎችን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድረ ገጽና ፖርታል፤ www.aau.edu.et እና https://portal.aau.et ብሎም ኦፊሺያል ቴሌግራም ቻናል፤ Testing_Center IER AAU እንዲያገኙ መረጃውን በትክክል እንዲደረሳቸው ፤
- በየትኛውም የመፈተኛ ማዕከላት ለፈተና ለመቀመጥና ፈተናውን ለመውሰድ ተፈታኞች ፎቷቸው ያለበት Test Admission Ticket (TAT) ይዘው መገኘት እንዳለባቸው፤ https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestTaker)
- የመግቢያ ፈተናው በመላ ሀገሪቱ ባሉ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ በበየነ መረብ የሚሰጥ በመሆኑ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ ኮምፒዩተር ያላቸው የመፈተኛ ማዕከላት Safe Exam Browser (SEB) ሶፍትዌር ተጭኖባቸው Corrective and Preventive Maintenance ተደርጎላቸው እንዲሁም Power Backup እንዲኖራቸው ተደርጎ አስፈላጊው ዝግጅት እንዲደረግ፤
- ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች ኔትወርክ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ ይህንኑ የየዩኒቨርሲቲው አይሲቲ ዳይሬክተር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር እንዲያስፈጽም መመሪያ እንዲሰጥ፤
- የመግቢያ ፈተናውን የትምህርት ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የሚያስተዳድሩት እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚሰጥ መሆኑ እንዲታወቅ፤
- የፈተናውን ውጤት ተፈታኞች ፈተናቸውን ሲጨርሱና በመጨረሻ መልሳቸውን ሲያስገቡ ወዲያውኑ ማየት የሚችሉ መሆኑን፤
- ተፈታኞች የፈተናውን ውጤት የሚያሳይ ሰርተፊኬት በወረቀት (Hard Copy) አትመው መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ለመማር በሚያመለክቱበት ተቋም ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን፤
- የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና የማለፊያ ነጥብ በትምህርት ሚኒስቴር የሚወሰን መሆኑን አሳውቋል።

👍14🙏3
Forwarded from Ethiopian Construction Vacancy & Tender (Itoophiyaa❤️)
🌼🌼 እንኳን አደረሳችሁ🌼🌼
➡️ውድ ቤተሰቦቻችን አዲሱ አመት የሰላም፤ የፍቅር፤ የአንድነት፤ የብልፅግናና የደስታ ይሆንላቹ ዘንድ ልባዊ ምኞታችን ነው!
🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት 🌼🌼
@ETCONpWORK

❤8👍4
👉የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አምና በ2015 አዲስ ዓመት የመሠረት ድንጋዩ የተጣለው ግዙፉ መሐመዲያ ቪሌጅ ግንባታ እየተፋጠነ ነው።
🌟ሁዳ ሪል እስቴት፣ ዚያስ ዲዛይን ኢንተርናሽናል አማካሪ ድርጅት፣ ሜፖ ኮንትራክቲንግ እና ማኔጅመንት ሰርቪስስ ኃ/የተ/የግ/ማ እና ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ ይኸንኑ በሀገራችን ትልቁ የሪል ስቴት ግንባታ እያከናወኑ መኾኑ ታውቋል።
✨ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ👌

👍7❤3
👉Why don't we use sea sand in construction.
1- Sea sand tends to be very fine and rounded, Smooth rounded particles would offer less resistance to rearrangement than angular or elongated particles with rough surfaces.
2- In sea water, chloride is present which will cause corrosion of steel and iron which ultimately leads to reducing the carrying capacity of steel and iron, so that the structure built using this may not be sustainable.
3- Sea sand contains a large number of salt particles and also dirt particles like macro microscopic And It is very expensive to remove them and it’s a tedious process.
4- Sea sand does not have high compressive strength, high tensile strength, so it cannot be used in construction activities.
5- Sea sand contains salts which deteriorate the plastered surface and the slab surface and in the long run cause seepage in the building.
6- The salt in sea sand tends to absorb moisture from the atmosphere, bringing dampness.
Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK
YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432
💫Comment @ETCONpBot
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
╔═════
🌐 join 👇
@ETCONp
@COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════

👍7🙏2🏆1
👉በሀረሪ ክልል በ3.3 ቢሊየን ብር የመንግስት አገልግሎት ሰጪ የአንድ ማእከል ህንፃ ግንባታ ሊካሄድ መሆኑን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
በተያዘው 2016 በጀት አመት በሐረሪ ክልል በ3.3 ቢሊየን ብር የመንግስት አገልግሎት ሰጪ የአንድ ማእከል ህንፃ ግንባታ እንደሚካሄድ የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታውቋል።
ህንፃው የሚያርፍበት 7ሺ ካሬ ሜትር በላይ መሬት መዘጋጀቱን የገለፁት የቢሮው ሀላፊ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም ለግንባታውም በክልሉ የመጀመሪያ የሆነ አለም አቀፍ ጨረታ መካሄዱን ገልፀዋል፡፡
ለህንፃው ግንባታ አለም አቀፍ ጨረታ ማካሄድ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት የፕሮጀክት በጀት ትልቅ መሆኑን ሀላፊዋ ገልፀዋል፡፡
ጨረታው ላይ የሀገር ውስጥ እና የቻይና ግንባታ ድርጅቶች መሳተፋቸውን የገለፁት ወይዘሮ አሚና ለፕሮጀክቱ በዚህ ልክ ትኩረት የተሰጠው በተያዘለት ግዜ ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ነው ብለዋል፡፡
የሚገነባው ህንፃ 18 ወለል ያለው መሆኑን የገለፁት ሀላፊዋ ዲዛይኑ የክልሉን ህዝብ ባህላዊ እሴቶችን ባካተተ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ህንፃው ተገንብቶ ለአገልግሎት ብቁ ሲሆን ቢሮ ተከራይተው ለሚሰሩ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ትልቅ እፎይታ የሚፈጠር መሆኑን ገልፀው የክልሉ ህዝብም ጉዳይ ለማስፈፀም ከቦታ ቦታ መሄድ ሳያስፈልገው በአንድ ቦታ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል፡፡
የሚካሄደው ጨረታ ሁለት ደረጃ ያለው መሆኑን የገለፁት ሀላፊዋ በዛሬው እለት የተከፈተው ጨረታ የመጀመሪያው ዙር ቴክኒካል ኢቫሉዌት(ግምገማ) መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የፕሮጀክቱ በጀት በክልሉ መንግስት አቅም መሸፈን ስለማይችል ከሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በረጅም ጊዜ ክፍያ የሚፈፀም ብድር ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በሁለት አመት እንዲጠናቀቅ ግዜ ገደብ የተቀመጠ ሲሆን ለፕሮጀክቱ ከ3.3 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተይዞለታል፡፡

👍5🙏2❤1
👉አንዳንድ እውነታዎች ስለ ታላቁ የ ህዳሴ ግድብ
.
🚧ግንባታው የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበት እለት - መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም::
.
🚧የግንባታው ስፍራ፡-በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጉባ ወረዳ::
.
🚧የዋናው ግድብ ከፍታ - 145 ሜትር
.
🚧የዋናው ግድብ ርዝመት - 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር
.
🚧የዋናው ግድብ ውፍረት - የግድቡ ግርጌ 130 ሜትር ሲሆን የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው
ክፍል 11 ሜትር
.
🚧ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን - 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር
.
🚧ግድቡ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት 1 ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር
.
🚧ሲጠናቀቅ ውሃ የሚተኛበት መሬት ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር
.
🚧የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ከፍታ- 50 ሜትር
🚧የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ርዝመት 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር
.
🚧ግድቡ16 የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች አሉት እያንዳንዱ ዩኒት የሚያመነጨው የኃይል መጠን ከ375 እስከ 400 ሜጋ ዋት::
.
🚧ጠቅላላ ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚያመነጨው ኃይል መጠን 6 ሽህ 450 ሜጋ ዋት
.
🚧ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ማልማት ያስችላል::
🚧ከ10 ቶን በላይ ዓሳን ማምረት ያስችላል::
🚧74 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም አለው::
🚧ከ40 በላይ ደሴቶች ይኖሩታል።
🚧ከግድቡ የውሃ ላይ የትራንስፖርት፣ የአሳ ልማትና ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ አገልግሎት ይውላል።
🚧ታዳሽ ኃይል በመሆን የከባቢ ብክለትን ይከላከላል።
🚧የከተሞችን ተሞክሮ በመቀመር በአዲሱ የህዳሴ ሐይቅ ዙሪያ ዘመናዊ ከተማ ለመመስረት
ያስችላል።
🚧አጠቃላይ ግንባታው የደረሰበት ደረጃ- 93%
🚧ግድቡ በትልቅነቱ በአፍሪካ አንደኛ ደረጃን ይዟል።
🌟ይቀጥላል.....
ምንጭ፡-ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት

👍26❤6