Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Forwarded from Ethiopian Construction Vacancy & Tender (Itoophiyaa‍❤️)
🌼🌼 እንኳን አደረሳችሁ🌼🌼

➡️ውድ ቤተሰቦቻችን አዲሱ አመት የሰላም፤ የፍቅር፤ የአንድነት፤ የብልፅግናና የደስታ ይሆንላቹ ዘንድ ልባዊ ምኞታችን ነው!

🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት 🌼🌼

@ETCONpWORK
❤8👍4
👉የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አምና በ2015 አዲስ ዓመት የመሠረት ድንጋዩ የተጣለው ግዙፉ መሐመዲያ ቪሌጅ ግንባታ እየተፋጠነ ነው።

🌟ሁዳ ሪል እስቴት፣ ዚያስ ዲዛይን ኢንተርናሽናል አማካሪ ድርጅት፣ ሜፖ ኮንትራክቲንግ እና ማኔጅመንት ሰርቪስስ ኃ/የተ/የግ/ማ እና ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ ይኸንኑ በሀገራችን ትልቁ የሪል ስቴት ግንባታ እያከናወኑ መኾኑ ታውቋል።

✨ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ👌

@etconp
👍7❤3
👉Why don't we use sea sand in construction.

1- Sea sand tends to be very fine and rounded, Smooth rounded particles would offer less resistance to rearrangement than angular or elongated particles with rough surfaces.

2- In sea water, chloride is present which will cause corrosion of steel and iron which ultimately leads to reducing the carrying capacity of steel and iron, so that the structure built using this may not be sustainable.

3- Sea sand contains a large number of salt particles and also dirt particles like macro microscopic And It is very expensive to remove them and it’s a tedious process.

4- Sea sand does not have high compressive strength, high tensile strength, so it cannot be used in construction activities.

5- Sea sand contains salts which deteriorate the plastered surface and the slab surface and in the long run cause seepage in the building.

6- The salt in sea sand tends to absorb moisture from the atmosphere, bringing dampness.

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

💫Comment @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍7🙏2🏆1
👉በሀረሪ ክልል በ3.3 ቢሊየን ብር የመንግስት አገልግሎት ሰጪ የአንድ ማእከል ህንፃ ግንባታ ሊካሄድ መሆኑን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡

በተያዘው 2016 በጀት አመት በሐረሪ ክልል በ3.3 ቢሊየን ብር የመንግስት አገልግሎት ሰጪ የአንድ ማእከል ህንፃ ግንባታ እንደሚካሄድ የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታውቋል።

ህንፃው የሚያርፍበት 7ሺ ካሬ ሜትር በላይ መሬት  መዘጋጀቱን የገለፁት የቢሮው ሀላፊ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም ለግንባታውም በክልሉ የመጀመሪያ የሆነ አለም አቀፍ ጨረታ መካሄዱን ገልፀዋል፡፡

ለህንፃው ግንባታ አለም አቀፍ ጨረታ ማካሄድ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት የፕሮጀክት በጀት ትልቅ መሆኑን ሀላፊዋ ገልፀዋል፡፡

ጨረታው ላይ የሀገር ውስጥ እና  የቻይና ግንባታ ድርጅቶች መሳተፋቸውን የገለፁት ወይዘሮ አሚና ለፕሮጀክቱ በዚህ ልክ ትኩረት የተሰጠው በተያዘለት ግዜ ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ነው ብለዋል፡፡

የሚገነባው ህንፃ 18 ወለል ያለው መሆኑን የገለፁት ሀላፊዋ ዲዛይኑ የክልሉን ህዝብ ባህላዊ እሴቶችን ባካተተ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ህንፃው ተገንብቶ ለአገልግሎት ብቁ ሲሆን ቢሮ ተከራይተው ለሚሰሩ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ትልቅ እፎይታ የሚፈጠር መሆኑን ገልፀው የክልሉ ህዝብም ጉዳይ ለማስፈፀም  ከቦታ ቦታ መሄድ ሳያስፈልገው በአንድ ቦታ  ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል፡፡

የሚካሄደው ጨረታ ሁለት ደረጃ ያለው መሆኑን የገለፁት ሀላፊዋ በዛሬው እለት የተከፈተው ጨረታ የመጀመሪያው ዙር ቴክኒካል ኢቫሉዌት(ግምገማ) መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ በጀት በክልሉ መንግስት አቅም መሸፈን ስለማይችል ከሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ጋር  በረጅም ጊዜ ክፍያ የሚፈፀም ብድር ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በሁለት አመት እንዲጠናቀቅ ግዜ ገደብ የተቀመጠ ሲሆን ለፕሮጀክቱ ከ3.3 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተይዞለታል፡፡

@etconp
👍5🙏2❤1
👉አንዳንድ እውነታዎች ስለ ታላቁ የ ህዳሴ ግድብ
.
🚧ግንባታው የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበት እለት - መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም::
.
🚧የግንባታው ስፍራ፡-በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጉባ ወረዳ::
.
🚧የዋናው ግድብ ከፍታ - 145 ሜትር
.
🚧የዋናው ግድብ ርዝመት - 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር
.
🚧የዋናው ግድብ ውፍረት - የግድቡ ግርጌ 130 ሜትር ሲሆን የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው
ክፍል 11 ሜትር
.
🚧ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን - 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር
.
🚧ግድቡ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት 1 ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር
.
🚧ሲጠናቀቅ ውሃ የሚተኛበት መሬት ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር
.
🚧የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ከፍታ- 50 ሜትር

🚧የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ርዝመት 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር
.
🚧ግድቡ16 የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች አሉት እያንዳንዱ ዩኒት የሚያመነጨው የኃይል መጠን ከ375 እስከ 400 ሜጋ ዋት::
.
🚧ጠቅላላ ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚያመነጨው ኃይል መጠን 6 ሽህ 450 ሜጋ ዋት
.
🚧ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ማልማት ያስችላል::

🚧ከ10 ቶን በላይ ዓሳን ማምረት ያስችላል::

🚧74 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም አለው::

🚧ከ40 በላይ ደሴቶች ይኖሩታል።

🚧ከግድቡ የውሃ ላይ የትራንስፖርት፣ የአሳ ልማትና ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ አገልግሎት ይውላል።

🚧ታዳሽ ኃይል በመሆን የከባቢ ብክለትን ይከላከላል።

🚧የከተሞችን ተሞክሮ በመቀመር በአዲሱ የህዳሴ ሐይቅ ዙሪያ ዘመናዊ ከተማ ለመመስረት
ያስችላል።

🚧አጠቃላይ ግንባታው የደረሰበት ደረጃ- 93%

🚧ግድቡ በትልቅነቱ በአፍሪካ አንደኛ ደረጃን ይዟል።

🌟ይቀጥላል.....

ምንጭ፡-ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት

@etconp
👍26❤6
🌟በሐረሪ ክልል በ3.3 ቢሊየን ብር ባለ18 ወለል ያለው የመንግሥት ተቋማት ሕንፃ ለመገንባት አስፈላጊ ሂደቶች መጠናቀቃቸው ታውቋል።

ለሕንፃ ግንባታው የተወዳደሩ አለም አቀፍ ተጫራቾች እና ታዛቢዎች በተገኙበት የጨረታ ሰነድ ተከፍቷል።

በክልሉ የመጀመሪያው እና ግዙፉ ህንፃ 7ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ G+18 ከ200 በላይ የመኪና ማቆሚያ ያለው እና የከተማውን ውበት የሚያጎላ እንዲሁም የክልሉን በኪነ ህንፃው የሚያስተዋውቅ ዘመናዊ እንደሚሆን ታውቋል።

በዛሬው እለትም ለህንፃ ግንባታ የሚሆን አለም አቀፍ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲወዳደሩ በማድረግ ባለድርሻ ተቋማት በተገኙበት ተከፍቷል።

ኮሚቴው በጨረታው የተወዳደሩ አሸናፊ ድርጅትን በቅርቡ የሚያሳውቅ ሲሆን፣ ይህ የሕንፃ ግንባታ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


@etconp
❤5👍2
በአዲስ አበባ በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው የአረጋውያን መጠለያ ተመረቀ

የአረጋውያን የመጠለያ እና የመጦሪያ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ በዛሬው ቀን ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል።

ማዕከሉ 730 አረጋዊያንን የመቀበል አቅም ያለው ሲሆን በውስጡም የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ክሊኒኮችና መድሃኒት ቤት፣ ዘመናዊ ላውንደሪ፣ ማብሰያና መመገቢያ ስፍራዎች፣ የእደ ጥበብ መስሪያ ክፍል ይዟል። ማዕከሉን በቋሚነት በገቢ እንዲደግፍ ባለ ሶስት ወለል ህንፃም ይዟል ፤ከህንፃው የሚገኘው ገቢ ሙሉ በሙሉ ማዕከሉን የሚደግፍ ይሆናል።

ማዕከሉ ለ730 አረጋውያን እንክብካቤ የማድረግ አቅም አለው መባሉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ማዕከሉ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ክሊኒኮች፣ ፋርማሲ፣ ምግብ ማብሰያ፣ መመገቢያ አዳራሽ፣ መኝታ ቤት፣ የልብስና የአረጋውያን ንፅህና መጠበቂያ፣ የዕደ- ጥበብ መስሪያ እና የመዝናኛ ቦታዎችን ያከተተ መሆኑም ተጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃ ሥነ - ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ዛሬ የተመረቀው ማዕከልም በ630 ሚሊየን ብር የሰንሻይን ፊላንት ሮፒ ፋውንዴሽን ግንባታውን በጥራት በማጠናቀቅ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ስለተወጣ እናመሰግናለንም ብለዋል።

@etconp
❤9👍1
👉በ2016 በጀት ዓመት 902 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች ለማከናወን ታቅዷል

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባስልጣን በ2016 በጀት ዓመት 902 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎችን ለማከናወን በዕቅድ ይዟል፡፡

በበጀት ዓመቱ 31.62 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 22.39 ኪ.ሜ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንገድ፣ 49.19 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 48.36 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገዶች መልሶ ግንባታ ለማከናወን ታቅዷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ 95 ኪ.ሜ የኮብል ንጣፍ መንገዶች ግንባታ እና 1.88 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ግንባታ የሚከናወን ሲሆን፣ በጠቃላይ በበጀት ዓመቱ 248.44 ኪ.ሜ የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ ሥራዎች ለማከናወን ታቅዷል፡፡

በሌላም በኩል ባለስልጣኑ በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ 102 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 35 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 80 ኪ.ሜ የኮብል መንገዶች ጥገና ለማካሄድ ታቅዷል፡፡

ከአጠቃቀም ጉድለት በተደጋጋሚ ጉዳት እያጋጠማቸው የሚገኙትን የመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች በመፈተሸ 349.36 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና እንዲሁም 13.5 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገና ይከናወናል፡፡

የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ አኳያ 65.92 ኪ.ሜ የሚሸፍን የነባርና የአዳዲስ መንገዶች የትራፊክ ቀለም ቅብ ስራ እና 8 ኪ.ሜ የእግረኛ መከላከያ አጥር ስራ፤ በድምሩ 654 ኪ.ሜ ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራ በበጀት ዓመቱ ለማከናወን ታቅዷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በቁጥር 22 ድልድዮች እና 16 ሺህ የመንገድ ዳር መብራቶች ጥገና በዕቅዱ ከተካተቱ ዋና ዋና ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

@etconp
👍5❤1
👉ETCONp TIP

🌟12 ways to get everything you want.

▪️1. Those who succeed in life are those who are not afraid to dream big and then take risks to fulfill their visions.

▪️2. When you are ready to give up, you are closer to the goal than you think.

▪️3. Why put off your greatness until later? Why wait for a better time to fulfill your dreams and those wonderful opportunities that life opens up for you? Why not take the first step today?

▪️4. Everything you think about comes true.

▪️5. Follow your dreams and the universe will open doors for you where there were only walls...

▪️6. Twenty years will pass, and you will regret more what you didn't do than what you did wrong. So put aside hesitation. Set sail and run away from safe harbor. Catch a fair wind. Explore. Dream. Make discoveries.

▪️7. It is much better to burn out in flight and crash down, pursuing a high goal, than to spend the best days of your life in front of the TV somewhere in the back of life. (Actual for 95% of the population).

▪️8. Everything that exists in the world was once just a dream...

▪️9. The one who does expects success. The one who “tryes” expects something to interfere with him.

▪️10. Take it and do it. If you don't know what to do, take a step forward.

▪️11. Having a goal is more important than having an opportunity.

▪️12. Bold and brightly drawn dreams come true at least 110%. You will always receive + 10% in the form of additional bonuses from Life at the exit of your dreams.

@etconp
👍12❤3
👉እንድታውቁት

🌟በድሬዳዋ አስተዳደር ኢንዱስትሪ መንደር የተገነቡ 253 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ ለእድለኞች ሊተላለፉ መሆኑን የኮንስትራክሽንና ቤቶች ቢሮ አስታውቋል።

🚧በዚህም መስፈርቱን ላሟሉ ቅድመ ቆጣቢዎች ዕጣ የሚተላለፈው መስከረም 20 / 2016 በኢትዮ ጣሊያን ኮሌጅ አዳራሽ ሲሆን የእጣ አወጣጥ ሥርዓቱን መከታተል እንደሚቻል ቢሮው አስታውቋል።

@etconp
👍5❤1🙏1
👉በዓባይ ግድብ ሃይል የሚያመነጩ ተርባይኖችን ቁጥር 7 ለማድረስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
*****
በዓባይ ግድብ ሃይል የሚያመነጩ ተርባይኖችን ቁጥር 7 ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

በ2014 ዓ.ም ሃይል ማመንጨት ከጀመሩት ሁለት ተርባይኖች በተጨማሪ በያዝነው 2016 በጀት ዓመት 5 ተርባይኖችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነው፡፡ 5ቱ ተርባይኖች ወደ ስራ ሲገቡ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያላትን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የሃይል አቅርቦት መጠን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል ፡፡

ወደ ስራ ከገቡት ሁለት ተርባይኖች አንጻር ዘንድሮ ወደ ስራ የሚገቡት 5ቱ ተርባይኖች ሃይል መጠን የበለስ ፣የግልገል ጊቤ አንድና ሁለት እንዲሁም የተከዜ የሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ከሚሰጧቸው አማካይ 1 ሺህ 180 ሜጋ ዋት ተመጣጣኝ ወይም የሚበልጥ ሃይልን ያመነጫሉ ብለዋል።

ይሁንና ከአቀማመጡና ከውሃ ፍሰቱ አኳያ የእነዚህን አምስቱ የሃይል ማመንጫ ተርባይኖች ሃይል የማመንጨት አቅም አሁን ላይ ይህን ያህል ነው ብሎ መናገር እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡

እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ በ13ቱ ተርባይኖች 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይልን ወደ ብሄራዊ የሃይል ቋት እንደሚቀላቀልም ነው ሚኒስተሩ የገለጹት፡፡ በዚህም እያንዳንዳቸው ተርባይኖች በአማካይ ከ375 በላይ ሜጋ ዋት ሃይልን ያመነጫሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@etconp
👍12
👉የጨረታ ማስከበሪያ/bid bond/
 ለምን አስፈልገ?


🚧የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና አይነት ነው፡፡

➢ ለግንባታ ጉዳይ ጨረታ ተሳታፊ የሚሆን ተጫራች ተቋራጭ የሚያቀርበውና ተጫራቹ እንደፈለገ ጨረታውን አቋርጦ እንዳይቀር ለማድረግ እና ምናልባት ተቋራጩ በጨረታው ቢያሸንፍ ውል እንዲገባ ማስገደጃና ዋስትና እንዲሆን ጨረታውን ባወጣው አካል የሚያዝ ዋስትና ነው፡፡

☞ይህንኑ በሚደግፍ ሁኔታ በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጓል፡፡

➢የዚህ ድንጋጌ ይዘትም ተጫራቹ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም እንዲያቀርብ የተጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ካላቀረበ ወይም የጨረታ ማስከበሪያው ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ተጫራቹ ራሱን ከውድድሩ ያገለለ እንደሆነ የጨረታ ማስከበሪያው ጨረታውን ባወጣው የመንግስት መስሪያ ቤት የሚወረስ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው፡፡

☞ጨረታ የሚያወጡ መስሪያ ቤቶችም በሚያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ላይ ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ አብረው ማቅረብ እንዳለባቸው ሊገለጽ ይገባል፡፡የጨረታ ማስከበሪያው መጠንም ጤነኛ ባልሆነ እና ቅንነት በጎደለው ሁኔታ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስቡትን ተጫራቾች ወደጨረታው እንዳይገቡ ከወዲሁ ለማስቀረት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፡፡

☞ለአሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በምን ሁኔታ መገለጽ አለበት?በህጉ አግባብ ያለመገለጽ ውጤቱስ?(Announcing the successful bidder)

☞ለአሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ መገለጽ ያለበት እና ሊደርሰው የሚገባ በጽሁፍ በደብዳቤ መልክ ነው፡

➢የደብዳቤውም ይዘት የመንግስት መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተቀበለው ስለመሆኑ፣የአሸነፈበትን ዋጋ፣አሸናፊው ተጫራች ማቅረብ ያበትን የውል ማስከበሪያ መጠን(Amount of performance security) የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡(Federal public procurement directive:አንቀጽ 16.24 እና አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 46) ስለዚህ በህጉ አግባብ አሸናፊነቱ ያልተገለጸለትን አሸናፊ ተጫራች ውል አልተዋዋለም በማለት የጨረታ ማስከበሪያ መውረስ የሚቻል አይሆንም ማለት ነው፡፡

#ConstructionLaw

@etconp
👍8🙏4❤2
🌟ሐላላ ኬላ ሪዞርት - ዳውሮ

ከአአ 450 ኪሜ በደቡብ ምዕራብ ክልል በዳውሮ ዞን በጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ አመካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ዳርቻ የሚገኘው የሀላላ ኬላ ቅንጡ ሪዞርት።

ይህ ሪዞርት የተገነባው ቦታ - ታላቁ የዳዉሮ ግንብ ካቲ ሃላላ፣ አስደናቂው ግልገል ግቤ ሶስት የሃይል ማመንጫ፣ ልብ የሚሰዉረዉ ጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ እንዲሁም በባህል የበለፀገው ፃራ ማህበረሰብ በአከባቢው የሚገኙ መስህቦች ናቸው።

ይህ ሪዞርት 12 ሄክታር ላይ ያረፈ የንጉስ ሃላላ ግንብና ለምለም ኮረብታዎች  ያጀቡት ጥንታዊ ቦታ ላይ የታነፀ ውብ ማረፊያ ነው።

ሪዞርቱ የአከባቢዉን ባህላዊ ስነ ህንፃ ከዘመናዊዉ ጋር ያማከለ የቤቱ ውስጣዊ ክፍል አየር በደምብ እንዲያገኝ ጣራው ከፍ ብሎ የተሰራ 2 ፕሬዚዳንሻል፣ 10 ፋሚሊ፣  2 የጥንዶች ማረፊያ እና 2 የዋና ገንዳ ስቲም ሳውና ማሳጅ ክፍሎች፣ ዘመናዊ ስብሰባ አዳራሽ፣ ሙዚየም ከሪዞርቱ በስተደቡብ ሳተላይት የእንግዳ መቀበያ በስተደቡብ ሳንሴት መዝናኛ ያሉት ድንቅ ሪዞርት ነው።

መልካም ቀን

@etconp
❤8👍7👏1