Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ከጀሞ 3 አደባባይ ወደ ሀይሌ ጋርመንት በሚወስደው በሃጫሉ ጎዳና ትራኮን ሪል ስቴት አካባቢ በመገንባት ላይ ያለ ህንፃ ላይ የእሳት አደጋ ተከሰተ። አደጋውን ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

@etconp
😢12👍4❤1🙏1
What do you think about these buildings?


@etconp


SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍3👌1
Geotechnical quiz

Capillary force is dependent on
Anonymous Quiz
30%
Pore pressure
14%
Water content
19%
Depth of water
37%
Surface tension of water
😁5👍2
👉በትራኮን ሪል እስቴት ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር አስር ሰዓት ወስዷል

⚡️በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት 1:05 ሰዓት ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሀጫሉ ሁንዴሳ መንገድ ትራኮን ሪል እስቴት እየገነባ ባለዉ አፓርታማ  5ኛና 6ኛ ፎቅ ላይ የተነሳዉ የእሳት አደጋ ለሊት 10 ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋሉን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

⚡️የእሳት አደጋው በሁለት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ሲያደርስ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል ተብሏል።

⚡️አደጋዉ የደረሰባቸዉ ሁለቱም  የእሳት አደጋ ሰራተኞች ሲሆኑ  አንደኛዉ ሰራተኛ እሳቱን በማጥፋት ሂደት ከህንጻዉ ላይ ወድቆ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በአሁን ሰዓት በአለርት ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።

⚡️የእሳት አደጋዉ  በአካባቢዉ ባሉ  መኖሪያ ቤቶች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን  እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር 9 ሰዓት መፍጀቱ ተነግሯል።

Via ዳጉ ጆርናል

@etconp
👍10❤4
Tensile strength of concrete as compared ot its compressive strength is:
Anonymous Quiz
29%
8%
35%
10%
17%
12%
19%
None
🕊5
Maximum spacing of main bars ni slab is:
Anonymous Quiz
29%
3d1
44%
4d1
18%
5d1
9%
6d1
😢3👌3
🏆11❤1
በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት አርክቴክት አረፉ

ዛሬ፤ ማክሰኞ መስከረም 15 2016 ዓ ም በመንበረ ጸባኦት ቅስድስ ሥላሴ ካቴድራል የቀብራቸው ስነ ስርዓት ይፈጸማል።

ወይዘሮ ምንትዋብ አዱኛ ከአባታቸው ከአቶ አዱኛ ካሳ እና ከእናታቸው ሴት አርበኛ ወይዘሮ ሙሉእመቤት ኃይለሥላሴ በወርሃ ታህሳስ በዕለተ ሰንበት፥ በቀን 27, 1928 ዓ ም በኬንያ ናይሮቢ ከተማ ተወለዱ።

ወይዘሮ ምንትዋብ አዱኛ ከወላጆቻቸው እና ከታላቅ ወንድማቸው ጋር በልጅነታቸው ወደ ሐገራቸው ተመልሰው በሐረር ከተማ አደጉ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ሐረር በየሺ እመቤት የአዳሪ ትምህርት ቤት ተከታተሉ። በእሳቸው ትውልድ ለሴት ልጅ የማይታሰብ የሚባለውን የትምህርት ዕድል አግኝተው ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን፥ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውንም በቡልጋሪያ ሐገር በሶፊያ ከተማ ተማሩ።

በሪጅናል ፕላኒንግ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሠሩትና የሰማንያ ስምንት አመት የዕድሜ ባለጸጋዋ ወይዘሮ ምንትዋብ፥ ለሐገራችን ኢትዮጵያ ምናልባትም ለአፍሪካ ብሎም ለመላም የጥቁር ሴቶች የመጀመሪያዋ ፋና ወጊ ሴት የስነ ሕንጻ ንድፍ ባለሙያ ናቸው። አርክቴክት ምንትዋብ አዱኛ በአውሮፓ በተለይም በጀርመን ሐገር ወደ ሐገራቸዉ ተመልሰው ከማገልገላቸው በፊት ለአመታት በሙያቸው ሠርተዋል።
በወቅቱ ምዕራብ ጀርመን በሚባለው በተለይም በሙኒክ ከተማ ከሌሎች የሙያ አጋሮቻቸው ጋር በቡድን እንዲሁም በግላቸው አፓርትመንቶችን፤ ልዩ ልዩ መኖሪያዎችን፥ የሕጻናት መዋያዎችን፥ ሌሎች የተለያዩ አገልግሎት ያላቸውን ግንባታ ንድፎችን
ሠርተዋል። ከነዚህም ውስጥ የጀርመን ሙኒክ ኦሎምፒክ የተካሔደበት ስታዲየም ንድፍ ስራ የነበራቸው ተሳትፎ ተጠቃሽ ነው።

አርክቴክት ምንትዋብ አዱኛ በትምህርትና በልምድ ያካበቱትን እውቀት ወደሐገራቸው ይዘው በመምጣት ከሐይለ ስላሴ ዘመን እስከ ኢህአዴግ ዘመን ድረስ በውጭ ድርጅቶች፥ በመንግሥት መስሪያ ቤቶችና በግላቸው በበጎ ፈቃደኝነትና በቅጥር በልዩ ልዩ የሓላፊነት ደረጃ ለአስርት አመታት አገልግለዋል። ከሚጠቀሱት ሥራዎች መካከል

የቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዩኒቨርሲቲ የአሁኑ የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ንድፍ ስራ ቡድን አባልነት

በዩኒቨርሲቲው የሚገኘው የኬኔዲ ቤተመጻሕፍት የማንበቢያ ቦታዎች ነዳፊነት

በከተማና ቤቶች ልማት ሚኒስትር መስሪያ ቤት የኪራይ ቤቶች አስተዳደር የአርክቴክቸር ባለሞያነት

ለ German Relief Operation እና Norwegian Save the Children በበጎ ፈቃደኝነት

ለ Pan African Housing Group ለመቀሌ የልጆች መንደር ንድፍ ስራ የቡድን ተሳትፎ

በዘመነ ደርግ የሕጻናት አምባ ንድፍ ስራ እና አማካሪነት

በገጠር ግብርና ቦታ ልማት ሚኒሰቴር መስሪያ ቤት የአረዳይታ ተቋም ግቢ መልክዓ ምድር ዲዛይነር እና የግንባታ ሱፐርቫይዘር

በብሔራዊ መሐንዲሶች እና ኮንትራክተሮች ድርጅት በፕሮግራም እና ቴክኒክ ክፍል ልዩ ልዮ የሀላፊነት ስራዎች

በዋናነት የሚጠቀሱ ስራዎቻቸው ናቸው።

አርክቴክት ምንትዋብ የአንዲት ሴትና የአንድ ወንድ ልጆች እናት፥ የአራት ወንድ ልጆች አያት ነበሩ።

የመጀመራያዋ ሴት አርክቴክት ምንትዋብ አዱኛ ካደጉበት ሐገርና ከተማሩበት ከሰሩበት የተለያየ ሐገር የተነሣ የአማርኛ የኦሮምኛ የሶማሊኛ ቋንቋዎችን ከሐገር ውስጥ ከውጭ ደግሞ የእንግሊዝኛ የጀርመንኛ እና የቡልጋሪያ ቋንቋን አቀላጥፈው መናገር የሚችሉ የስድስት ቋንቋ አዋቂ ነበሩ።

አርክቴክት ምንትዋብ አዱኛ ከሴት ልጃቸው ጋር አብረው በጡረታ ዕድሜያቸው ኖረው በትላንትናው ዕለት በክብር በተወለዱ በሰማንያ ስምንት አመታቸው በዕለተ ሰኞ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ ም አርፈዋል።

ዛሬ፤ ማክሰኞ መስከረም 15 2016 ዓ ም በመንበረ ጸባኦት ቅስድስ ሥላሴ ካቴድራል የቀብራቸው ስነ ስርዓት ይፈጸማል።

Via ጌጡ ተመስገን

@etconp
😢16👍12
👉የቻይና ሳይንቲስቶች በጨረቃ ላይ መጠለያ መገንባት ይቻል እንደሆነ ለማወቅ ምርምር ጀመሩ
*******
🌟ተመራማሪዎቹ በጨረቃ ላቫ ቱቦዎች ውስጥ አስተማማኝ፣ የተረጋጋ እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ መጠለያ የማዘጋጀት እድል መኖሩን ለማወቅ ነው ምርምሩን የጀመሩት።

የሻንጋይ የጠፈር በረራ ቴክኖሎጂ አካዳሚ ተመራማሪ የሆኑት ዣንግ ቾንግፌንግ እንዳሉት በሺዎች በሚቆጠሩ ዓመታት የጂኦሎጂካል እንቅስቃሴዎች ተፅዕኖ እና የጨረቃ እንቅስቃሴዎች ጥልቅ ቱቦዎች መፈጠራቸው የጨረቃን አካላት ለማሰስ በር ከፍቷል።

የቻይናው የሼንዙ የጠፈር መንኮራኩር እና የጨረቃ ተጓዦች ምክትል ዋና ዲዛይነር ዣንግ በቅርቡ በሻንጋይ በተካሄደው 10ኛው የስፔስ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ኮንፈረንስ (CSA-IAA) ላይ ጥናታቸውን አቅርበዋል።

እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ የላቫ ቱቦዎቹ በጨረቃ ወለል ላይ ካለው አስቸጋሪ እንቅስቃሴዎች የተጠበቁ እንደሆኑ እና ይህም ከከፍተኛ የሙቀት መጠን እና ጨረር እንደሚከላከል ዣንግ በጥናታቸው አመልክተዋል።

እንደ ዣንግ ገለጻ የእሳቸው ቡድን እና የቻይና የፕላኔቶች ጂኦሎጂ ባለሙያዎች ስለ ጨረቃ ላቫ ቱቦዎች ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ በቻይና ውስጥ ባሉ በርካታ የላቫ ዋሻዎች ላይ በጋራ የመስክ ምልከታዎችን አካሂደዋል።

በምልከታውም በምድር እና በጨረቃ ላይ ባሉት የላቫ ቱቦዎች መካከል የተወሰነ መመሳሰል እንዳለ መገንዘባቸውን እና ይህም በቱቦዎቹ ውስጥ መጠለያ ለመገንባት እንደሚያስችል ፍንጭ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

በቱቦዎቹ መግቢያ ላይ የኃይል እና የመገናኛ ማእከልን በመገንባት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የምርምር እና የመኖሪያ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል የምርምር ሀሳባቸውንም አቅርበዋል፡፡

የቻይና ጠፈር ኤጀንሲ ባለፈው ግንቦት ወር እንዳስታወቀው ቻይና እ.ኤ.አ. በ2030 ሰው ሰራሽ የጨረቃ ማረፊያን እውን ለማድረግ እቅድ እንዳላት እና የፕሮግራሙን የመጀመሪያ ደረጃ መጀመሯን አስታውቃለች።

Via EBC

@etconp
👍7👌2
Lap Length In Column, Beam And Slab Reinforcement :
What is Overlapping or Lap Length in RCC?
Due to the limited length of the bar, lapping of bars are required in a member of more than 12m in length or where the length of bar required is more than 12m.
Lap Length:- Overlapping Length or Lap Length is provided to maintaining the continuity of bars in order to safely transfer the load from one bar to another bar. It depends on the Grade of Concrete, the grade of steel and dia. of the bar.
How Much Lap Length is Provided in Column?
As per IS Code 456-2000 overlapping length should not be less than 75mm. Lapping should be avoided in the tensile zone of construction members. In case of column generally, we take 24d – 40d where ‘d’ is dia of the bar.
Important Point Should be Remember for Column Lap Length:
1- Lapping should be provided at the centre of the column because bending moment at the midpoint is zero so try to lap at the midpoint.
2- Lapping of bars should be provided alternately. Lap should not be given at same point because buckling may occur.
3- Lateral ties should be provided closely spaced in Lapping zone.
4- Due to maximum stress, we can’t lap at the column/beam/slab joint. Lapping should not be given at L/4 distance from top and bottom of the slab.
How Much Lap Length is Provided in Beam?
In case of the beam we generally use 24d for compression zone and 45d for tensile/tension zone.
Important Point Should be Remember for Beam Lap Length:
1- Lapping (24d) in top bars avoided L/3 distance from both ends. For top bar, lapping should be at mid-span.
2- Lapping (45d) in bottom bars lap should be provided at column junction or L/4 distance from column face but should not be in mid-span of the beam.
3- Stirrups should be closely spaced near the columns and lose/normal at mid-span.
4- Lapping of bars should be alternately provided.
How Much Lap Length is Provided in Slab?
In the case of the slab, we use lap length 50d where ‘d’ is dia of the bar.
Important Point Should be Remember for Slab Lap Length:
1- RCC slabs function is similar to beams if the slab is designed as one way. It is ideal to lap bars at point of the least bending moment or at points of contra flexure.
2- Practically laps are provided beyond L/5 to L/3 ( L being the effective span) from support for bars at bottom of the slab. The top bars are generally short and no laps are necessary. However, at no point, the lapped bars shall exceed one-third of the total bars.
3- Bars will be considered staggered if an end to end distance b/w laps is at least (lap length +75mm)



@etconp


SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC

📞 +251 971 71 71 71
  📞 +251 994 69 69 69

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍17❤2😢1🙏1
. 人 ★* 。 • ˚* ˚ 🌙
. ( _ _) * ኢድ * ★
. ┃口┃ * ሙባረክ *
. ┃口┃★ * ***. . *˛•
. ┃口┃★ * •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛* 人 •˛˚ *
. ┃口┃ .-:'''"''''"''.-.
. ┃口┃ (_(_(_()_)_)_)
. ┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. ┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. ||三||_||三三三三三||
👉የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ለሆናችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እንኳን ለተከበረው ለ መውሊድ በዐል በሰላም አደረሳችሁ።
. ‌‌‌‌ ╔═════ ❁✿❁ ═════╗
. ★ ★ ★ ☆ ☆ ☆
@etconp
🙏7👍4
Types of foundation in one picture

No strip footing in this picture ….
What’s strip footing ?


@etconp


SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍4❤1
👉የአፓርተመንት ኪራይ እና ሽያጭ በአዲስ አበባ በጣም አትራፊው ንግድ እየሆነ መጥቷል።

🚧ከቅርብ አመት በኋላ በተለይ ባለሀብቶች በግል ወይም በህብረት በስፋት የአፓርትመንት ግንባታ ላይ እየገቡ ሲሆን እንደ ቤቶቹ ስፋት የአፓርተመንቶቹ ዋጋ ከ 20 ሚልየን እስከ 40 ሚልየን ብር ዋጋቸው ይጠራል።

🚧ባለፉት ሶስት አመታት ቢያንስ የአንድ አፓርተምንት ዋጋ በአማካኝ አንድ አንድ ነጥብ አምስት ሚልየን ብር እየጨመረ መጥቷል።

🚧ኪራያቸው የማይቀመሰው እነዚህ አፖርትመንቶች በወር ከ 70 ሺ እስከ 150 ሺ ብር ድረስ እየተከራዩ ሲሆን አብዛኞቹ ተከራዮች ሀብታም ነጋዴዎች ፣ ዲያስፖራዎች እና የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው።

🌟በዚህ ቢዝነስ የሀገሪቱ ታዋቂ አስመጪና ላኪዎች እንዲሁም ኢንቨስተሮች እየተሳተፉ መሆኑን ፊደል ፖስት መረዳት ችሏል።

@etconp
👍11❤1
👉ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ ደመራ በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

🚩በዓሉ የሠላም ፣ የጤና ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የብልፅግና እንዲሆን ፈጣሪ አምላክ ፍቃዱ ይሁን!"

@etconp
👍7🙏4
👉በግንባታ እንቅስቃሴዎች ሳቢያ በመንገድ ሀብት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢ ሆኗል

🚧አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የመንገድ ሽፋን ለማሳደግና የትራፊክ ፍሰቱን ይበልጥ ምቹ ለማድረግ በየዓመቱ በከፍተኛ በጀት የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎችን በማከናወን የከተማችንን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ ይገኛል።

ይሁን እንጂ በመንገድ ሀብት አጠቃቀም ጉድለትና ኃላፊነት በጎደለው ህገ-ወጥ ተግባራት ሳቢያ በመንገድ ሀብት ላይ በየጊዜው እየደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ለአብነትም በጀሞ አካባቢ እየተከናወነ በሚገኘው የጤና ተቋም ግንባታ ምክንያት፣ በአካባቢው የሚገኘው የወንዝ ውሃ መውረጃ መስመር በመዝጋቱና ወደ መንገድ እየፈሰሰ ባለው ውሃ የአካባቢው የአስፋልት እና የኮብል መንገድ ለጉዳት ከመጋለጡም ባሻገር የትራፊክ እንቅስቃሴው እየተስተጓጎለ ይገኛል፡፡

የደቡብ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር ቡድን መሪ ኢንጂነር ኃይሉ ደመቀ እንደገለፁት ችግሩን ለመፍታትና የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በማሳወቀ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የከተማዋ የመንገድ አውታሮች ለረጅም ጊዜያት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ፣ በልዩ ልዩ የግንባታ ሥራዎች ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ አካላት በመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ከሚያደረሱ ህገ-ወጥ ድርጊቶች በመቆጠብ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያሳስባል፡፡

@etconp
👍11❤1
👉የድልድዮች ጽዳትና ጥገና ስራ እየተከናወነ ነው

🚧የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠትና በተለያዩ ምክንያቶች ለከባድ ብልሽት የተዳረጉ ድልድዮችን እየጠገነ ነው፡፡

የወንዞችን ተፈጥሯዊ ፍሰት በማስተጓጎል ለድልድዮች ብልሽት ምክንያት እየሆኑ የሚገኙ የቆሻሻና የግንባታ ተረፈ-ምርት ክምችቶችን በማፅዳት እያስተካከለም ይገኛል፡፡

ባለስልጣኑ በዕቅድ ከያዛቸው ዘርፈ ብዙ የመንገድ መሰረተ ልማት ጥገና ስራዎች መካከል የድልድዮች ጥገና እና የጽዳት ስራ ይገኝበታል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የድልድይ ፅዳትና ጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የአባ ጃሌ ድልድይ አንዱ ሲሆን፣ ድልድዩ ለረጅም ጊዜያት አገልግሎት ሲሰጥ በመቆየቱ ምክንያት እና በድልድዩ አካባቢ በሚጣል ቆሻሻና የግንባታ ተረፈ ምርት ሳቢያ የድልድዩ ምሰሶ ለጉዳት ተጋልጧል፡፡

አሁን ላይ በድልድዩ ሥር የተከማቸውና የወንዙን ፍሰት ያስተጓጎለውን ቆሻሻ በማንሳትና የድልድይ ጥገና ሥራ በማከናወን የነበረውን ችግር መፍታት ተችሏል፡፡

በተመሳሳይም በቦሌ ክፍለ ከተማ፣ በተለምዶ ፍየል ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ድልድይ ከፍተኛ መጠን ባለው ደለል እና ቆሻሻ በመደፈኑ ምክንያት የወንዙ ውሃ ወደ አፋልት በመፍሰስ ለእግረኛ እና ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኖ ከመቆየቱም በተጨማሪ በንብረት ላይም ጉዳት አድርሷል፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወንዙ መስመሩን ጠብቆ እንዲፈስ ለማስቻል በድልድዩ ስር የተከማቸውን ከፍተኛ መጠን ያለው ቆሻሻና ደለል የማንሳት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ሕብረተሰቡም የዝናብ ወቅት የጐርፍ አደጋ ምክንያት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለማስቀረትን እና በመንገድ ሀብት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል፣ በየአካባቢው በመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች እና ወንዞች ውስጥ ቆሻሻና የግንባታ ተረፈ ምርት የሚደፉ አካላትን በመከላከል በኩል የድርሻውን እንዲወጣ ባለሥልጣኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

@etconp
👍4😁2❤1