Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
3. 📌የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ምንነት

✳️በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ኢንሹራንስ አንዱ የአደጋዎች (risks) ማስተላለፊያ መንገድ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ዋና ዓላማ አደጋን በሚያጋጥምበት ጊዜአሰሪዎች፣ተቋራጮች፣ንዑስ-ተቋራጮች እንዲሁም በግንባታ ወቅት ድርሻ ያላቸው ሌሎች አካላት አደጋንወደ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚያስተላልፉበት መንገድ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ኢንሹራንስ የአደጋ መከላከያ መንገድ እንጂ ምትክ አይደለም፡፡ ለምን ቢባል ኢንሹራንስ በአብዛኛው ጊዜየሚሸፍነውየታወቁ እና ሊካሱ የሚችሉ አደጋወችን ነው፡፡

✳️በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ሲባል በፕሮጀክት ግንባታ ወቅት ለሚደርሱ ጉዳቶች የሚደረጉ የመድን ውሎች ሲሆን ኢንሹራንስም የአደጋ ማስተላለፊያ መንገድ ተብሎ ሲመረጥ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡
(C)onstruction insurance means all contracts of indemnity within the activities of the construction industry where insurance is chosen as the medium through which liabilities are shifted.”

✳️ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የንግድ ህግ ስለ ኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ በግልጽ ባይደነግግም ከአንቀጽ 676 ምንባብ መረዳት እንደሚቻለው በኮንስትራክሽን ፕሮጀክቱ አፈጻጸም ወቅት ለሚደርሱ ጉዳቶች ሽፋን ሊያገኙ እንደሚችሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ነገር ግን በኢንሹራንስ ፖሊሲው በግልጽ ለእነዚህ አደጋዎች ተብሎ መገለጽ ይኖርበታል፡፡ ሌላው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በጣም ውስብስብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስን በተመለከተ ከመደበኛው የንግድ ሕግ ለየት ያሉ ሕግጋት ያስፈልጋል፡፡

✳️ አንድ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት በሚከተሉት ጉዳዮች ኢንሹራንስ ሽፋን ሊያገኝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡-ለንብረት ጉዳት፣ለሦስተኛ ወገን ጉዳት፣በጉዞ ላይ ላሉ ዕቃዎች/goods in transit/፣በሚገነባው ህንጻ ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች/damage to constructional plant/፣ታስቦ ለሚፈጸሙ አደጋዎች…ወዘተ መሰል ጉዳዮችን ያጠቃልላል፡፡

✔️ለማጠቃለል ያህል የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ሲባል አደጋን ለመቀነስ በማሰብ ወይ በሥራ ተቋራጮች አሊያም በአሠሪወች ሥራው ከመጀመሩ በፊት የሚገባ የመድን ዓይነት ነው፡፡

4. 📌የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ጠቀሜታ

✳️በ አንድ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ህንፃ ተደርምሶ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ሰምተናል በተለይም አብዛኛው የከተማዋ ህንጻዎች ግንባታቸው ሳይጠናቀቁ ወደ ስራ መግባታቸው የችግሩ ምንጭ መሆኑ እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡

✳🇪🇹️የኢትየጵያ 📕የሕንጻ አዋጅ ቁ.624/2001 በአንቀጽ 31 እንዲሁም አንቀጽ 32 ላይ በግንባታ ወቅት መወሰድ ስላለባቸው ጥንቃቄወች ይደነግጋል፡፡ በዚህም መሰረት ማነኛውም ግንባታ በግንባታው አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን፣የሚሰሩ ሠራተኞችን ወይም የሌሎችን ግንባታ እና ንብረቶችን ደህንነት በማያሰጋ መልኩ ዲዛይን መደረግ እና መገንባት ይኖርበታል፡፡ በተለይም ደግም የሕንጻ ደንብ ቁ.243/2003 አንቀጽ 29 ላይ የጥንቃቄ እርምጃዋችን በስፋት ይዘረዝራል፡፡ ህጉም እንዚህን የጥንቃቄ እርምጃወች አለመከተል ከፍትሃብሄር እና ከወንጀል ተጠያቂነት በተጨማሪ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚያስወስድ በደንቡ አንቀጽ 44 ላይ ይናገራል፡፡

✳️በዋናነት የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ጠቀሚታው አንድም በግንባታ ወቅት የሚደርሱ አደጋወችን ለመቀነስ (proactive solution) በማሰብ ሥራ ተቋራጩ ወይም ባለቤቱ አስቀድመው ከመድን ድረጅቶች ጋር በሚገቡት ውል አማካኝነት ነው፡፡ ✳️ለምሳሌ፡-ስራ ተቋራጩ የኮንስትራክሽን መድን ውል ግዴታ ቢገባ በየጊዜው የሚከፍለው አረቦን በመኖሩ ምክንያት የሚገነባውን ህንጻ በጥንቃቄ ሊሰራ ይችላል፡፡ ሁለትም ጉዳት ከደረሰ በኋላ (reactive solution) ጉዳት የደረሰባቸውን አካላት ለይቶ በመድን ውሉ መሰረት መካስን ይጨምራል፡፡

✳️የኮንስትራክሽን አደጋን ምንግዜም ማስወገድ ባይቻልም መቀነስ እና ቅድመ-መከላከል ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህም ሊሆን ከሚችልባቸውመንገዶች ውስጥ አንዱ የኢንሹራንስ ሥርዓት ነው፡፡
የህንጻ መደርመስ በሚደርስበት ጊዜ ተቋራጩ ኢንሽራንሽ የገባ ከሆነ መልካም ነው አለበለዚያ ግን የሚደርሰው ጉዳት የከፋ ያደረገዋል፡፡

5. 📌የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ የሕግ ማዕቀፍ

✳️በ2001ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ ሕንጻ አዋጅ ቁ.624/2001 አንቀጽ 26 እና 27 የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ በአስገዳጅነት በይፋ መጀመሩን ያወጀ ህግ ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ የወጣው የሕንጻ ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ.243/2003 አንቀጽ 19 እና 20 ላይ ዝርዝር ጉዳዮችን በመያዝ መውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡

✳️ታዲያ እነዚህን ህግጋተ መሰረት አድርገው የግንባታ ውል ውስጥ የሚገቡ አካላት ዝርዝር ውሎችን ሊዋዋሉ ይችላሉ፡፡ በተለይም አገር-በቀል ኩባንያዎች እንዲሁም ዓለምአቀፍ ይዘት ያላቸውን ውሉች የሚገዛው የዓለምአቀፋ አማካሪ መሀንዲሶች ማህበር ወጥ ውል (FIDIC Red book 1999) የኮንስትራክሽን አደጋዎችን ለመቀነስ ከተቀመጡ መንገዶች አንዱ የሆነውን ማለትም ኢንሹራንስን በተመለከተ በአንቀጽ 18 በዝርዝር ያሰቀመጠበትን ሁኔታ እናገኛለን፡፡

✳️በተለይ በመጀመሪያው አንቀጽ መግቢያ ላይ የመድን ሽፋን ገቢ(“insuring party”) ማን ሊሆን እንደሚችል አስቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት የመድን ሽፋን ገቢው ሥራ-ተቋራጩ፣ ባለቤቱ(አሰሪው) ወይም በጣምራ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በፊዲክ ወጥ ውልም የተባለው መድን በተለይ በአንቀጽ 17(3) ላይ የአሰሪው አደጋዎች ተብለው ከተለዩት ለምሳሌ የጦርነት፣ሽብር ጥቃት፣ብጥብጥ፣የባለቤቱ ሰራተኞች የተባለሸ ስራ ወዘተ ዉጭ ሁሉንም ዓይነት ጥፋቶች እና አደጋዎች ሊሸፍን ይችላል፡፡

✳️በተለይ ፊዲክ በአንቀጽ 18(2)(ረ)ላይ የመደን ሽፋን ላያገኙ የሚችሉ ሁኔታዎችን በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡ ለምሳሌ፡-የተበላሹ የዲዛይን ሥራዎች ወይም የፕሮጀክት ግብዓቶች ላይ ሺፋን አያገኙም፡፡
እርግጥ ነው የFIDIC ወጥ ውል ልክ እንደ ሌሎች ውሎች ወደውና ፈቅደው በታዋዋሉ ወገኖች ላይ አስገዳጅነቱ የታወቀ ነው፡፡

✳️በ1994 ዓ.ም የወጣው የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ወጥ ውል የኮንስተራክሽን ኢንሹራንስን በተመለከተ ለሥራ ተቋራጮች ብቻ በሚመስል መልኩ የተቀረጸ ይመስላል፡፡

በተለይ በአንቀጽ 21 ላይ እንደተመለከተው ሥራ ተቋራጩ በራሱ እና በአሰሪው ስም ለፕሮጀክቱ አፈጻጸም ሲባል እንዲሁም ለሚደርሱ ጉዳቶች የመድን ሽፋን የመግባት ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም ግን በወጥ ውሉአንቀጽ 20 ላይ በተዘረዘሩ ልዩ አደጋዎች ማለትም እንደ ጦርነት፣ብጥብጥ ወዘተ የመድን ሽፍን መግባት አይልም::

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስን በተመለከተ በአስገዳጅነት የተደነገገው ህግ በ2001 ዓ.ም የወጣው የሕንጻ አዋጅ ነው፡፡

#ConstructionLaw

@etconp
👍8🙏1
👉የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ አሁናዊ ገጽታ‼️

🌟የኦሞ ወንዝን ተንተርሶ እየተገነባ ያለው የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ 1 ሺህ 800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን ፕሮጀክቱ በ2.4 ቢሊዮን ዩሮ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል።

⏺መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም

@etconp
❤9👍3💯1
Behaviour of strap beam in combined footing


@etconp


SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍6
👉የድልድዮች ጽዳትና ጥገና ስራ እየተከናወነ ነው

🚧 የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠትና በተለያዩ ምክንያቶች ለከባድ ብልሽት የተዳረጉ ድልድዮችን እየጠገነ ነው፡፡

የወንዞችን ተፈጥሯዊ ፍሰት በማስተጓጎል ለድልድዮች ብልሽት ምክንያት እየሆኑ የሚገኙ የቆሻሻና የግንባታ ተረፈ-ምርት ክምችቶችን በማፅዳት እያስተካከለም ይገኛል፡፡

ባለስልጣኑ በዕቅድ ከያዛቸው ዘርፈ ብዙ የመንገድ መሰረተ ልማት ጥገና ስራዎች መካከል የድልድዮች ጥገና እና የጽዳት ስራ ይገኝበታል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የድልድይ ፅዳትና ጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የአባ ጃሌ ድልድይ አንዱ ሲሆን፣ ድልድዩ ለረጅም ጊዜያት አገልግሎት ሲሰጥ በመቆየቱ ምክንያት እና በድልድዩ አካባቢ በሚጣል ቆሻሻና የግንባታ ተረፈ ምርት ሳቢያ የድልድዩ ምሰሶ ለጉዳት ተጋልጧል፡፡

አሁን ላይ በድልድዩ ሥር የተከማቸውና የወንዙን ፍሰት ያስተጓጎለውን ቆሻሻ በማንሳትና የድልድይ ጥገና ሥራ በማከናወን የነበረውን ችግር መፍታት ተችሏል፡፡

በተመሳሳይም በቦሌ ክፍለ ከተማ፣ በተለምዶ ፍየል ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ድልድይ ከፍተኛ መጠን ባለው ደለል እና ቆሻሻ በመደፈኑ ምክንያት የወንዙ ውሃ ወደ አፋልት በመፍሰስ ለእግረኛ እና ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኖ ከመቆየቱም በተጨማሪ በንብረት ላይም ጉዳት አድርሷል፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወንዙ መስመሩን ጠብቆ እንዲፈስ ለማስቻል በድልድዩ ስር የተከማቸውን ከፍተኛ መጠን ያለው ቆሻሻና ደለል የማንሳት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ሕብረተሰቡም የዝናብ ወቅት የጐርፍ አደጋ ምክንያት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለማስቀረትን እና በመንገድ ሀብት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል፣ በየአካባቢው በመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች እና ወንዞች ውስጥ ቆሻሻና የግንባታ ተረፈ ምርት የሚደፉ አካላትን በመከላከል በኩል የድርሻውን እንዲወጣ ባለሥልጣኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

@etconp
👍6❤1
👉የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ 61% ደረሰ

🌟የኦሞ ወንዝን ተንተርሶ እየተገነባ ያለው የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ 1 ሺህ 800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጭ 2.4 ቢሊዮን ዩሮ መሆኑ ተጠቅሷል።

▶️ግድቡ 6 ዩኒቲቶች እንደሚኖሩት እና እያንዳንዳቸው 300 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም እንደሚኖራቸው የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዓባይነህ ጌትነት ጠቅሰዋል።

▶️የማመንጫ ቤቱ ግንባታ 52% መድረሱም ተጠቅሷል።

🚧ግድቡ  201 ሜትር ቁመት  እንደሚኖረው የፕሮጀክቱ  ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዓባይነህ አብራርተዋል።

🚧130 ኪሎ ሜትር መሬት ላይ የሚንጣለል ሰው ሠራሽ ሐይቅ የሚኖረው ግድቡ 6.5 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ይይዛል ብለዋል።

🚧ጠቅላላ ሰው ሠራሽ ሐይቁ 200 ስኩዌር ኪሎ ሜትር  እንደሚሸፍን ነው የገለጹት።

🌟የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብም ወደፊት የሚኖረው ሰው ሠራሽ ሐይቅ  አካባቢው ካለው የቱሪዝም ፀጋ ጋር ተዳምሮ ለዘርፉ ተጨማሪ መዳረሻ እና መስህብ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።

🚧ግድቡ ዊ ቢዩልድ (በቀድሞ ስሙ ሳሊኒ) ተቋራጭነት እየተሠራ ነው። የዊ ቢዩልድ ፕሮጀክት ማናጀር ኢንጂነር ዞፒስ፣ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች  አቅም በግድቦች ግንባታ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።

🌟በማሳያነትም በኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት ከጉልበት ሥራ እስከ ከፍተኛ ባለሙያ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በኢትዮጵያዊያን እየተገነባ ነው ብለዋል።

Via EBC

@etconp
❤7👍5
👉በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የ ኣኽሱም ኣውሮፕላን ማረፍያ መጠገን የሚችሉ የ ስራ ተቋራጮች የመምረጥ ሂደት ላይ እንደሆነ የኢትዪጵያ ኣየር መንገድ ጉሩፕ ኣስታወቀ።

✈️ኣየር መንገዱ መስከረም 2 / 2016 ዓ/ም በድጋሜ ያወጣው የጨረታ ማስታወቅያ ደረጃ ሁለት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጠቅላላ ስራ ተቋራጮች በመጋበዝ የ ኣኽሱም ኣውሮፕላን ማረፍያ መጠገን እንደሚፈልግ ይገልፃል።

📌ጨረታው እስከ መስከረም 28 / 2016 ዓ/ም እንደሚቆይም ይገልፃል።

@etconp
👍5❤4💔2
የኮንስትራክሽን_አማካሪዎች_የአሰራር_መመሪያ_1_1_1.pdf
10.1 MB
👉የ ኮንስትራክሽ ኣማካሪዎች ለሆናቹ በሙሉ ስለ አሰራር እና መምርያ ጋ የተያያዙ ፅሁፎች ታገኙበታላቹ አውርዳቹ ተጠቀሙበት❤

🔊እንዲሁም ለወዳጆቻቹ በማጋራት አግዙን🙏

@etconp
👍5🙏5
Matt foundation layout

@etconp


SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍6
👉በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለሠራዊቱ እና ለቋሚ ሲቪል ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ

▶️የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ እና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሠራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ መሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

⏺የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ለሠራዊቱ አባላት እና ቋሚ ሲቪል ሠራተኞች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በ26,673 ካሬ ሜትር ላይ ለ1000 አባወራ የሚተላለፍ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የሚገነባ መሆኑ ተገልጿል።

▶️የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጀኔራል ደረጄ መገርሳ እንደገለፁት ለሀገር ህልውና አስጠባቂ ለሆነው መከላከያ ሠራዊት ደረጃውን የጠበቀ የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የዲዛይን ስራው ተጠናቆ ግንባታውም በያዝነው አመት ይጀመራል።

🚧የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ምክትል ስራ አስፈፃሚ ኮሎኔል ታደሠ ጌታቸው በበኩላቸው የጋራ መኖሪያ ቡሎኮቹ ከ16 እስከ 18 እንደሚደርሱ ገልፀው አንዱ ብሎክ እስከ G+12 የሚደርስ ባለ 1፣ ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ ቤቶችን አጠቃሎ እንደሚይዝ ተናግረዋል።

🚧የሠራዊቱ አመራሮች በቃሊቲ ክፍለ ከተማ በቁጥር 1 እና 2 ሳይቶች የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችንም ጎብኝተዋል።

Via EBC

@etconp
👍10
👉የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች እምቅ የቱሪዝም ሀብቶች ጎልተው እንዲወጡና እንዲለሙ እድል ፈጥሯል

🌟የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ቀደም ሲል ትኩረት ሳይሰጣቸው ለነበሩ እምቅ የቱሪዝም ሀብት የሚገኝባቸው ስፍራዎች ጎልተው እንዲወጡና እንዲለሙ እድል ፈጥሯል ሲሉ የመንግስት ኮኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ገለጹ።

በዚህም ለርካታ ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የሥራ ዕድል ፈጥሯልም ብለዋል።

የጨበራ ጩርጩራ ፓርክና በስፍራው የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችና የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በጋዜጠኖች ቡድን ተጎብኝቷል።

በጨበራ ጩርጬራ ፓርክ በግልና በመንግስት እየተገነቡ ያሉ የቱሪዝም መሰረተ ልማቶች ለዘርፉ እድገት ትልቅ አስተዋጵኦ ይኖራቸዋልም ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታዋ።

የኮንታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ነጋ አበራ በበኩላቸው፣ ዞኑ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርስ ባለቤት ቢሆንም ባለፉት ዓመታት ትኩረት ተነፍጎት በመቆየቱ ከዘርፉ ጥቅም ማግኘት አልተቻለም ብለዋል። ከዚህ በፊት ምንም አይነት የቱሪስት ፋሰት ያልነበረ ሲሆን አሁን ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታቀደው ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካባቢው በመታቀፉ ህብረተሰቡ ትልቅ ተስፋ ሰንቋል ነው።

ቀደም ሲል አካባቢው በሚዲያ ባለሙያዎች የመጎብኘት እድል እንዳላገኘ የገለፁት ሃላፊው ጉብኝቱ አካባቢው በዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም በማሳየት የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ለማነቃቃት ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ዞኑ የተለያዩ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ባለቤት መሆኑን ገልጸው፤ ከገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች አንዱ በሆነው ይህ ስፋራ ያሉንን የተፈጥሮ ሀብቶች ወደ ልማት መቀየር እንደሚቻል ማሳያ እ ንደሆነ ጠቁመዋል።

እስካሁን በተደረገ ጥናት በፓርኩ ከ40 በላይ ትላልቅና መካከለኛ አጥቢ የዱር እንሰሳት ከአውራሪስ በቀር የአፍሪካ ዝሆኖች፣ጎሾች፣ጉማሬዎች፣አንበሳ እንዲሁም ብርቅዬ የአዕዋፍና የዓሣ ዝርያዎች፣ ፍል ውሃዎች፣ፏፏቴዎች፣ዋሻዎችና ሌሎችም የተፈጥሮ ሀብቶች እንደሚገኙ አብራርተዋል።

የጨበራ ጩርጩራ ብ/ፓርክ በኮንታና ዳውሮ ህዝቦች ፍላጎትና ጥያቄ በ1997 ዓም የተመሰረተ ሲሆን 1410 ኪ.ሜ የሚሸፍን የቆዳ ስፋት አለው::

ፓርኩ ከአመያ ከተማ በ13 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ስለሚገኝ ለቱሪስቶች ምቹ ነው እንዲሁም ከአ.አ 454 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል::

Via ኢ ፕ ድ

@etconp
👍8😁5
👉የመኖርያ ቤት ውድነት በአዲስአበባ

🌟ኑምቢዎ (Numbeo) በተጠቃሚዎች በሚመነጭ መረጃ መሰረት የከተሞችን የኑሮ ውድነትና ጥራት እንዲሁም ያላቸውን የመሬትላይ ሀብት (Real estate) የሚያነጻጽር በሰርቢያ የሚገኝ ድረገጽ ነው።

⚡️ይህ ድረገጽ በየግዜው ትችት ቢቀርብበትም መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንደሚያቀርብ ደግሞ ይታመናል።

▶️እንደዚህ ድረገጽ መረጃ ከሆነ አዲስአበባ ውስጥ ከገቢ አንጻር ሲታይ የመኖርያ ቤት ዋጋ በአፍሪካ ሁለተኛው ውድ ሲሆን በአለም ላይ ደግሞ በ 13ኛነት ውድ ነው።

🚧የተያያዙት ምስሎች የአዲስ አበባን የመኖርያ ቤት ውድነት ደረጃ የሚያሳዩ ሲሆኑ እንደ የቤት የመግዣና የኪራይ ዋጋ የመሳሰሉ ተያያዥ መረጃዎች ምስልም ቀርቧል።

🫵ለበለጠ መረጃ የተያያዘውን የኑምቢዎ ድረገጽ መጎብኘት ይቻላል።

https://www.numbeo.com/property-investment/in/Addis-Ababa

@etconp
👍12🙏3❤1