Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዲሱ ህንጻ በየካቲት ወር 2017 ለማጠናቀቅ እየተሠራ ይገኛል ተባለ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ከኹለት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እየተከናወነ መሆኑን የፌደራል መንግሥት ሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ግንባታው ሲጠናቀቅ ኹለት ሺሕ 400 መቶ ሰዎችን ማስተናገድ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሃራ አብዱልሃዲ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የብሔራዊ ቴአትሩ አዲስ ሕንጻ ግንባታ ዘጠኝ በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ በየካቲት ወር 2017 ለማጠናቀቅ እየተሠራ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ፕሮጀክቱን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ የግንባታው ሂደት በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ግንባታው ሲጠናቀቅ ኹለት ሺሕ አራት መቶ ሰዎችን ማስተናገድ ያስችላል ብለዋል፡፡

በፕሮጀክቱ ሦስት የመሰብሰቢያና አንድ ኹለገብ ክፍሎች እንደሚገነቡ ያስታወቁት ሥራ አስኪያጇ፤ ለተለያዩ የሥነ-ጥበብ ነክ ክንውኖች የሚውሉና የተለያዩ ኹነቶችን የሚያስተናግዱ የመሰብሰቢያ ቦታዎች መካተታቸውን ገልጸዋል።

በግንባታው ሂደት ለመድረክ ሥራውና ከመድረኩ ጋር ተያይዞ ለሚያስፈልጉ ቴክኖሎጂዎች ሲባል የዲዛይን ክለሳ መደረጉን ገልጸው፤ በአገር ውስጥና የውጭ አገር ባለሙያዎች ጥረት ግንባታው እየተከናወነ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በአዲሱ ዘመናዊ ሕንጻ ዓለም አቀፍ የቴአትር ቤት መስፈርቶችን ማሟላት የሚያስች የመብራት፣ የድምፅና፣ የመድረክ ግንባታ እንደሚካሄድ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ ቴክኖሎጂን ማዕከል በማድረግ በጥንቃቄ ግንባታው እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ ለአርቲስቶች የተሻለ የመድረክ አጠቃቀምን ተግባራዊ የሚያደርጉበት ምቹ ኹኔታ እንደሚፈጥርም አመላክተዋል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ ቴአትር ቤቱ ኦፔራን ጨምሮ የተለያዩ ትርዒቶችን ማዘጋጀት የሚችል ትልቅ መድረክ እንደሚኖረው ጠቁመው፤ የቴአትር ቤቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የቱሪስት መስህብ የሚሆን ድንቅ ፕሮጀክት እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር አዲስ ዘመናዊ የሕንጻ ግንባታ በስድስት ሺሕ 200 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መሆኑን አስታውቀዋል። ግንባታው ከምድር በታች ኹለት ወለል ያለውና ባለ 11 ወለል ከፍታ እንዲኖረውና ተደርጎ በጥራት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ግንባታው እየተከናወነ ያለው አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዘመናዊ ሕንፃ ከነባሩ ቴአትር ቤት ጎን እየተገነባ ይገኛል።

@etconp
🏆3
በከተሞች ህጋዊ የካዳስተር ስርአት እና የሪል ፕሮፐርቲን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ ሁሉም የህግ ማዕቀፎች በአግባቡ ሊተገበሩ እንደሚገባ ተገለጸ

ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ በከተማ መሬት ዘርፍ ለሚሰሩ ከ200 በላይ አመራሮችና ባለሙያዎች በተዘጋጁ ሰነዶችና የሀግ ማዕቀፎች ዙሪያ ከጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ኢየተሰጠ ነው፡፡

ማንኛውም የሥርዓት ግንባታ መነሻው የሕግ ማዕቀፍ፣ ስታንዳርድ እና እንዲመጣ የሚፈለገው የአገልግሎት አይነት ጥናት ከመሆኑ አንፃር የሚገነባው ፍላጎት ጥናቱ ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም የሕግ ማዕቀፉ ሀገራዊ ተፈጥሮ እና አተገባበር ይዞ፤ ይህን ማስተግበሪያ አቅም እንዲኖረው በማድረግ በዘመናዊ የመረጃ ስርዓት መደገፉ አስፈላጊ ነው፡፡

የመሬት ይዞታ ምዝገባ (ካዳስቴር) ዓላማዎች ከተሞች ያላቸውን መሬት ቆጥረው ማወቅ እንዲችሉ በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተናባቢ የሆነ የመሬት ይዞታ መረጃ እንዲኖ በማስቻል አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባቱን ሂደት ማገዝ፤ ይዞታ መብትን በምዝገባ በማረጋገጥ፣ የባለይዞታውን የመሬት ይዞታ ተጠቃሚነት ዋስትና እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት መብትን እውቅና በመስጠት የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊ እና አካባቢያዊ ልማትን ማፋጠን፤ ከተሞች ያላቸውን መሬት ቆጥረው ማወቅ እንዲች በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተናባቢ የሆነ የመሬት ይዞታ መረጃ እንዲኖር በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒሰቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን በስልጠናው መድረክ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት በከተሞች መሬትና መሬት ነክ ሀብት በሀገራችን ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው እጅግ የጎላ ነው፡፡

በከተሞች ፈጣን የህዝብ እድገት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ ለዜጎች አስፈላጊውን ሁሉ የመሠረተ-ልማት ለማሟላት መሬትን በዘመናዊ የመረጃ ስርአት(ካዳስቴር) መዝግቦ በመያዝ ለተሻለ የኢንዱስትሪ ልማት ዝግጁ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም በከተሞች የዜጎችን ቅሬታና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ መሬትን ህጋዊ የካዳስተር ስርአትን እውን በማድረግ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖርና የዜጎችን የሀብት ባለቤትነት ማረጋገጥ እንደሚቻል ጠቅሰው ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የሚወጡ አጠቃላይ የህግ ማእቀፎች፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚገኙ ተሞክሮዎችን ሁሉም ክልሎች ተግባራዊ ሊያደርጓቸው እንደሚገባ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

በስልጠናውም ከመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የሊዝ አዋጅ፣ የመሬት ምዝገባና ማረጋገጫ አዋጅ፣ የቅየሳ ስታንዳርድ ጋይድ ላይን፣ የከተማ መሬት ባንክ አሰራር ማንዋል፣ የአድራሻ ሥርዓት ስታንዳርድ፣ የካሳ አዋጅና ደንብ ፣ የመልሦ ማልማት ኦፖሬሽናል ማንዋል፣ የሪል ፕሮፖርቲ ግብይት ግመታና ፈቃድ አሰጣጥ ፅንሰ ሀሳብ፣ የሪል ፕሮፐርቲ ልማት ግብይትና ግመታ አዋጅ፣ የቦታ ደረጃ ሰነድ እና የእሴት እርከን መወሰኛ መስፈርትና ሌሎች የክልሎች ተሞክሮዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት በተለያዩ ባለሙያዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ከመርሃ ግብሩ ማወቅ ችለናል፡፡

Via ሞገስ ዓሊ

@etconp
👍5❤2
ኮስሞፖሊታን ሪል እስቴት ዘመናዊ አፓርታማ አስመረቀ

ኮስሞፖሊታን ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አቅራቢያ ተሰርቶ የተጠናቀቀውን ጂ+11 የሆነ በ700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ ባለ ምቾት አፓርታማ የቤት ገዢዎችን ፍላጎት ያሟላ ዛሬ ጥቅምት 3/2016 ዓ.ም የክብር እንግዶች በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል።

ህንፃው የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም፣ ሳውናና ስቲም የተሟላለት የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክ የተመቻቸላቸው በሙያው የላቀ ልምድ ባካበቱ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሙያዎች የተገነቡ ሲሆን የቤቶቹ የአሠራር ጥራት ደረጃውን የጠበቀ እና ዋጋቸውም ተመጣጣኝ  ናቸው ተብሏል።

ኮስሞፖሊታን ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአሁኑ ሰዓት በአገራችን በቤቶች ግንባታ እና በሌሎች ዘርፎችም ላይ ተሠማርቶ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ኦሎምፒያ ጂ+17 ህንጻ እንዲሁም በፒያሳ ካቴድራል አካባቢ ለሱቅና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የገበያ ማዕከል ግንባታ የሚጀምር ሲሆን ይህም ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን የስራ ዕድል ይፈጥራል ከዚህ ፊት በሶስቱ ፕሮጀክቶች ለ25ዐ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።

በይፋ ከተመሠረተ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረው ኮስሞፖሊታን በአስመጪና ላኪነት፣ በቤት እና በቢሮ እቃዎች፣ በወረቀት ማምረት እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ ለደንበኞቹ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለ ድርጀት ነው እንደሆነ ተገልፇል።

@etconp
👍6❤1
👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባቸው 9 የመንገድ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

በዛሬው ዕለት የተመረቁት የመንገድ ፕሮጀክቶች 2 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል ተብሏል።

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ የቦሌ ሚካኤል ተሻጋሪ ድልድይን ጨምሮ ከአራራት ሆቴል - ኮተቤ ኮሌጅ፣ ከኮተቤ ኮሌጅ - ካራ (ሎት2)፣ ከቄራ ከብት በረት - ጎፋ መብራት ኃይል፣ ከቀጨኔ - ቁስቋም፣ ከየካ አማኑኤል ሆስፒታል - ኮተቤ እንዲሁም ሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ አያት 2 ኮንዶሚኒየም፣ አያት መሪ ሳይት 4 ናቸው።

ዛሬ የተመረቁት መንገድ ፕሮጀክቶች በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ በማቃለል የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ያስችላል ተብሏል።

በምረቃ መርኃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ ጨምሮ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

@etconp
👍6
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦የአገልግሎታችንን አድማስ በማስፋት የክቡራን ደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማርካት በታማኝነት እንተጋለን

፦ፕሌት 1mm-30mm any size

፦jbolt 12mm-32mm

፦ankerbolt

፦stafa

፦any modefic wor

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706
👍1🏆1
DEBUB GLOBAL BANK HEADQUARTER DESIGN

DESIGNED BY :- AHAA DESIGN

@etconp

SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍5❤1
👉ዓባይን የደፈረውን አላታ ድልድይ በጨረፍታ!

🚧የዓባይ ወንዝ የማይደፈር የማይሞከር ኾኖ በታየበት በዛ ዘመን ይህን ወንዝ ተሻግሮ ለመሄድ መላ መዘየድ ግድ ይል ነበር፡፡

🌟በወቅቱ ወንዙን ለመሻገር የሚሞክሩ ሰዎች በውኃ የመወሰድ እድላቸው ከፍተኛ ስለነበር በዚህ ወንዝ ላይ መሻገሪያ መሥራት ያስፈልግ ነበር፡፡

🌟በዓባይ ወንዝ ላይ ድልድይ ለመሥራት ሲታሰብ እንዴት ኾኖ ያሉ ባይጠፉም ተግባሩን የዘመኑ ድንቅ ሥራ ሲሉም ያሞካሹት የትየለሌ ናቸው፡፡

🌟አይደፈሬውን የዓባይ ወንዝን ደፍሮ ከጢስ ዓባይ ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኝ የወንዙ ክፍል ላይ የአላታ ድልድይ ተሠራ፡፡

🌟ይህም በዓባይ ወንዝ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራ ድልድይ ነው፡፡

🚧ድልድዩ 45 ሜትር ርዝመት እና 3 ሜትር አማካኝ ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነበር የተገነባው፡፡

⏺በወቅቱ በነበረው ጥበብ ጥርብ ድንጋዮች በሥርዓት ተደርድረው በኖራ ተጣብቀው እንዲቀመጡ ማድረግም ችለዋል።

⏺የአላታ ድልድይ በአጼ ፋሲል ዘመን ነበር የተሠራው፡፡ አጼ ፋሲል ሀገር ለማዘመን እና የማይደፈረውን ወንዝ ደፍሮ ለሕዝባቸው እፎይታ ለመስጠት በማሰብ ካሠሯቸው ሥራዎች መካከልም ይህ ድልድይ ተጠቃሹ እንደኾነም የአማራ ክልል ባሕል ቱሪዝም ቢሮ ገልጿል፡፡

▶️እንደ ቢሮው ማብራሪያ ድልድዩ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ አግራሞትን በመፍጠሩም እንዲህ ተብሎ ተገጥሟል፡-

❤️“ርብና ዓባይ፣ ሸፍተው ሲኖሩ
አላፊ አግዳሚውን፣ ከጎራ እያሠሩ
በትልልቅ ድንጋይ፣ ተደብድበው ቀሩ፡፡" ሲል የአካባቢው ሕዝብ ተቀኝቷል፡፡

Via አሚኮ

@etconp
👍9❤6
👉ከ ብሔራዊ ትያትር አዲሱ ህንጻ ነዳፊ ከ አዲስ መብራቱ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

🚧እየተገነባ ያለው አዲሱ ቴአትር ቤት ምን ይመስላል?

🌟በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በየአመቱ ከሚታተመው "ከሞያችን" መጽሄት 2015 ዕትም የተወሰደ

@etconp
👍9❤1