Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ከ80 ሺህ በላይ የሚሆኑ የፍሳሽ ማስወገጃ ጉድጓድ ክዳኖች ስርቆት ተፈጽሟል

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በመዲናዋ ከ80 ሺህ በላይ የሚሆኑ የፍሳሽ ማስወገጃ ጉድጓድ ክዳኖች ስርቆት ተደርጓል ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በመዲናችን አዲስ አበባ ከ80 ሺህ በላይ የፍሳሽ ማስወገጃ ጉድጓድ ክዳኖች መሰረቃቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

ከፍተኛ ወጪ ወቶባቸው የተቀመጡ የፍሳሽ ማስወገጃ ጉድጓድ መሸፈኛ ክዳኖች በስርቆት እየጠፉ ነው ሲሉ የከተማዋ የውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሚኒኬሽ ዳይርክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በከተማዋ ከ1 ሺህ 6 መቶ ኪ.ሜ በላይ የተዘረጋ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር እንዳለ የገለጹት ዳይሬክተሯ ፤ከ80 ሺህ በላይ የሚሆኑ ክዳኖች ተሰርቀው ተነስተዋል ብለዋል፡፡

ከዚህም የተነሳ ለፍሳሽ ማስወገጃ ተብለው በተዘጋጁ ጉድጓዶች ውስጥ ደረቅ ቆሻሻዎች ስለሚጣሉ ጉድጓዶቹ ይደፈናሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህም በክረምት ወቅት ከሚዘንበው ከፍተኛ ዝናብ የተነሳ፣ ከከተማው የተለያዩ አከባቢዎች የሚነሱ ፍሳሾች ከጉድጓዱ ውጭ በመሆን የትራፊክ አደጋን ጨምሮ የተለያዩ አደጋዎችን እንደሚያደርሱ ገልጸዋል፡፡

Via ጌጡ ተመስገ

@etconp
👍6🙏2❤1
👉ሃይንከን ኢትዮጵያ ደራሽ በተሰኘው ፕሮጀክቱ በአቃቂ አካባቢ ከዕድሜ ብዛት ሊፈርሱ የተቃረቡ ከእንጨት፣ ቆርቆሮ እና ጭቃ የተሰሩ ቤቶችን አፍርሶ እያንዳንዱ ክፍል 30 ካሬ ስፋት እንዲኖረዉ አድረጎ በመስራት ባለ አንድ ፎቅ ህንጻ ለነዋሪዎቹ መልሶ ማስረከቡን ገልጿል።

ህንጻው ደረጃችዉን የጠበቁ የመታጠቢያ፣ የመጸዳጃ እና የማብሰያ ከፍሎችን ያካተተ ሲሆን 16 አባወራዎችን ከእነ ቤተሰቦቻቸው የያዘ መሆኑን ገልጿል።

በመጪው ዓመትም ሌሎቸ አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ የሚኖሩ ወገኖችን ለመርዳት ማቀዱን የካምፓኒው የውጭ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፍቃዱ በሻህ ገልጸዋል።

ባለፉት ሶስት ዓመታትም ሃይኒከን ኢትዮጵያ በልደታ ክፍለ ከተማ ከረዩ ሰፈር፣  በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቀጨኔ ላይ እና በጨርቆስ የገነባቸውን 145 ደረጃቸውን የጠበቁ መኖርያ ቤቶች ለነዋሪዎች ማስረከቡንም አስታውሷል።

የደራሽ ፕሮጀክት በኢኮኖሚ ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በመቆም በዋናነት የአገሪቱን ሁለት ዋና ዋና ተግዳሮቶች ለመፍታት ማለትም ለተቸገሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት ለማቅረብ እና የግንባታ ሥራዎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።

@etconp
👍7❤3
🌟የንድፍ ማስተባበር ልምድ እጦት
በአገራችን ካለው ልክ ያልሆነ ልምምድ የተነሳ አርክቴክቶች ለምንነድፋቸውን ህንጻዎች የምንሰራውን የተለያዩ የምህንድስና ንድፎች በአግባቡ አናዋድዳቸውም።

🚧የዙርያ ገብ ንድፉንም መምራትንም ሙያዬ ብለን አንይዘውም።

▶️የኤሌትሪክ ማብርያ ማጥፍያዎችን፣የመብራት አይነቶችን፣ መገናኛ ሳጥኖችን (junction boxes) እንዲሁም ማሰራጫ ሳጥኖችን የአውታር መረብ መደርደርያዎችን (network racks) በተመለከተ የምንለው ሊኖር ይገባል።

⏺የውሀና ፍሳሽንም ዝርዝር በተመለከተ እንዲሁ የግራጫና የጥቁር ውሀ
ቱቦዎችን (Grey and black water pipes) የእያንዳንዱ የዚህ ሙያ
ቁሳቁሶችን ከነ አብሮ መጤያቸው (accessories), ማወቅ ይጠበቅብናል።

⏺በንድፍ ስራ መጨረሻም የሌሎች መሀንዲሶችን ስራ እርስ በርሳቸው እና
ከኪነህንጻ ንድፉ ጋር አጣጥመን ማዋደድ ግዴታችን ነው።

⏺ይሄንን የንድፍ ሂደት በዚህ መስመር ስናስኬደው ሙያችን የበለጠ ትርጉም እያገኘ ይመጣል።

⏺ለሙያችንም ተገቢ ክብር ይመጣል እንዲሁም የተያያዘው ምስል የማዋደድና ማስተባበር ስራ በሌለበት የተነደፈ ንድፍ
ግንባታን ያመለክተናል።

⏺በመዋቅራዊ ንድፍ መሰረት ያልተከለሰና በቦታ አጠቃቀም ብቻ የተነደፈ ክፍል አሳዛኝ እና ዋጋ አስከፋይ መጨረሻውን እናይበታለን።

https://t.me/ETCONpWORK
👍4
🌟 Product Name: PP Plastic Film Face Plywood
Size(mm): 1220*2440
Thickness(mm):18
Color: Green
Grade: First Class
Edges: Sealed with waterproof paint
Reuse Times : >15 times pending glue Type

✨ What is PP plastic Film plywood?Traditional film face plywood uses melamine film on the surface, where as PP(polypropylene) coating plywood uses plastic. Now what makes plastic better? It is non-corrosive, acid and alkaline retardant, and has a very rigid surface compare to melamine film. The biggest advantage is that PP plywood is wear resistant, durable, waterproof, doesn't stick to the concrete when its dry, and can be removed very easily. After dismount, the surface of the PP plywood remains smooth and intact,so it can be used repeatedly several time ,thus greatly increase the efficiency and quality of the form work.

☎️ Contact us: 0960306035
                     0967289643
👍6👌1
👉try  these questions

🚧1. List at least four factors that affect design of concrete mix?

🚧2. Write procedures of laying of rising main pipes in a water supply project.

🚧3. Estimate the quantities of brickwork and plastering required in a wall 4 m long, 3 m high and 30 cm thick.

⏺Calculate also the cost if the rate of brickwork is 320.00birr per cu m and of plastering is 8.50 birr per sq m.

🚧4. Given 10 m3 Concrete C- 20 Mechanical mixes with mix ratio 1:2:4. Assuming that 30% shrinkage and 5% wastage and also take density of cement as 1400kg/m3.

⏺Calculate the amount of cement required to make 10m3 of 1:2:4 concrete in kilograms.
Calculate the volume of sand in cubic meter and Calculate the volume of gravel (crushed stone) in cubic meter.

📩Put Your Answer on The Discussion Group Or Link Below

https://t.me/COTMp
👍14👌1
What type of foundation is used ?

And when do we use this type of foundation?

@etconp

SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
🙏5👍4
👉የ ኮንስትራክሽን ምህንድስና መሰረታዊ እውቀት

🫵የኮንስትራክሽን መሐንዲሶች እንደ የመንገድ ፣ የአውሮፕላን ማረፊያ ፣ ዋሻዎች ፣ ግድቦች እና ድልድዮች ያሉ ወሳኝ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ዲዛይን ያደርጋሉ።

🚧እንዲሁም የፕሮጀክት ግንባታ እና ጥገናን ይቆጣጠራሉ።

🚧ከወጪ ሂሳብ እስከ ጂኦሎጂ ድረስ አጠቃላይ የክህሎት ስብስብ ሊኖራቸው ይገባል።

🌟ብዙ የ ኮንስትራክሽን መሐንዲሶች በግንባታ ውስጥ በጣም የተግባር ሚና የሚጠይቁ ሥራዎች አሏቸው ፣ ሌሎቹ ደግሞ ለተቆጣጣሪ እና ለአስተዳደር ችሎታዎች የበለጠ ክብደት ያላቸው ቦታዎች ሊኖራቸው ይችላል ስለዚህ የኮንስትራክሽን መሐንዲሶች የ ኮንስትራክሽን ምህንድስና መሰረታዊ ነገሮችን ማወቅ አለባቸው።

🌟ኮንስትራክሽን መሐንዲሶች ብዙውን ጊዜ በጣም የተወሳሰቡ ፕሮጄክቶችን ማስተዳደር አለባቸው ፣ ይህም ብዙዎች ከበርካታ አካባቢዎች በአንዱ ውስጥ እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል።

🚧ስኬታማ የኮንስትራክሽን መሐንዲስ ለመሆን ሁሉንም መረጃ እና አስፈላጊ ክህሎቶችን እና ጥራቶችን እና የኮንስትራክሽን ምህንድስና መሰረታዊ ነገሮችን ማግኘት ይችላሉ።

🌟የኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ መሰረታዊ ቴክኒካዊ ችሎታዎች
አንድ ጥሩ ሲቪል መሐንዲስ የምህንድስና ችግሮችን የሚለይ እና የሚፈታ የሂሳብ እና የፊዚክስ ደረጃ ሊኖረው ይገባል።

🌟የ ኮንስትራክሽን መሐንዲሶችም በዲዛይን ቴክኒኮች የተካኑ እና ከካርታዎች ፣ ስዕሎች ፣ ሞዴሎች እና ከ CAD ሶፍትዌሮች ጋር መሥራት አለባቸው።

⏺ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን መተንበይ እና ለእነሱ መፍትሄ መፈለግ መቻል አለባቸው።

▶️እያንዳንዱ የሲቪል መሐንዲስ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን ከፍተኛ የቴክኒክ ክህሎት ሊኖረው ይገባል።
የሚከተሉት ሊያውቋቸው የሚገቡ አንዳንድ ከፍተኛ ቴክኖሎጂዎች ናቸው።

⏺የሂሳብ ችሎታዎች ኮንስትራክሽን መሐንዲሶች በሂሳብ ውስጥ የካልኩለስ ፣ ትሪጎኖሜትሪ እና ሌሎች የላቁ ርዕሶችን ለሥራ ትንተና ፣ ዲዛይን እና መላ መፈለግ መርሆዎችን ይጠቀማሉ።

⏺የግንባታ ቁሳቁሶች ሙከራዎች( Building material test)
ጤናማ የኮንስትራክሽን መሐንዲስ ስለ የግንባታ ዕቃዎች የተለያዩ ፈተናዎች ትክክለኛ ዕውቀት ሊኖረው ይገባል። አንዳንድ ትክክለኛ ሙከራዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።

▶️Concrete Test: Slump test, compression test, split tensile test, soundness, etc.
▶️Soil Test: Core cutter test, compaction test, sand replacement test, triaxial test, consolidation test, etc.
▶️Bitumen Test: Ductility test, softening point test, gravity test, penetration test, etc.

🚧የአፈር ምርመራ(Soil Investigation) ግንባታ ከመጀመሩ በፊት የአፈርን ሰፈራ እና መረጋጋት (settlement and stability) ለመወሰን የተለያዩ የአፈር ምርመራዎች ይካሄዳሉ።

🌟ስለዚህ እንደ ኮንስትራክሽን መሐንዲስ በቦታው የተከናወኑትን የእነዚህ ምርመራዎች በቂ እውቀት ሊኖርዎት ይገባል።

⏺የዳሰሳ ጥናት መሣሪያዎች አጠቃቀም (surveying Instrument)

▶️እንደ አጠቃላይ ጣቢያ (Total Station) ፣ ቴዎዶላይት ፣ ወዘተ የመሳሰሉት የቅየሳ መሣሪያዎች አጠቃቀምም ለእያንዳንዱ የኮንስትራክሽን መሐንዲስ ግዴታ ነው። እነዚህ መሣሪያዎች ምልክት ለማድረግ እና ለመለካት ያገለግላሉ::

@etconp
👍17❤8👏1😢1🏆1
👉በቻይና አረጋውያን ባልና ሚስት ከመንግሥት ለመንገድ ግንባታ ከመኖሪያ ቤታቸው ለቀው እንዲወጡ ተነገራቸው።

🌟የሚከፈለው የካሳ ክፍያ በቂ እንዳልሆነ በመግለጽ ባል እና ሚስቶቹ ለመንቀሳቀስ ፈቃደኛ አልሆኑም።

🖱በምላሹ መንግሥት መንገዱን በዙሪያቸው ሠራ።

@etconp
😁18👍3😢2
High rise mixed use building by Abiy Woreta and Mahlet Nega


@etconp

SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍6
👉በቀን 18 ሺህ ካሬ ሜትር ሴራሚክ የሚያመርት ፋብሪካ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ ተገለጸ

🚧በቀን 18 ሺህ ካሬ ሜትር ሴራሚክ ማምረት የሚችል ፋብሪካ በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገባ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

🌟የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር)÷ ከግንባታ ማጠናቀቂያ ግብዓቶች ውስጥ ስትራቴጂክ ግብዓት የሆነውን ሴራሚክ በሀገር ውስጥ ለመተካት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

🌟በዚህም በቢሾፍቱ ከተማ 2 ቢሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው ሀገር በቀሉ ካም የሴራሚክ ፋብሪካ ተጠቃሽ መሆኑን አንስተዋል፡፡

⏺ፋብሪካው ከ25 ዓመት በላይ ሴራሚክ እና የሴራሚክ ውጤቶችን ከውጪ በማስገባት ሲሸጥ እንደነበርም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

⏺አሁን ላይ በሀገር ውስጥ ያለውን እምቅ አቅም በመገንዝብ ምርቱን በሀገር ውስጥ ለማምረት ፋብሪካ መገንባቱን ገልጸው÷ የፋብሪካው ግንባታ ሲጠናቀቅ በቀን 18 ሺህ ካሬ ሜትር ሴራሚክ ማምረት እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

⏺አሁን ላይ የተወሰኑ መሰረተ ልማቶችን የማሟላትና የኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎች ካሟላ በኋላ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

⏺መንግስት በዘርፉ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች እንዲመጡ ጥረት እያደረገ መሆኑን አንስተው፤ የኮንስትራክሽን ግብዓት የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ሲስፋፉ ከውጪ የሚመጡ ምርቶች ላይ ያለውን የዘርፉ ጥገኝነት ችግር እየተቀረፈለት እንደሚሄድም አስረድተዋል፡፡

⏺አሁን ላይ 40 በመቶ የሚሆነው አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ግብዓት በሀገር ውስጥ አቅም የሚሸፈን ሲሆን÷ በሚቀጥሉት 7 ዓመታት ውስጥ 80 በመቶውን በሀገር ውስጥ ለመሸፈን መታቀዱ ተመላክቷል።

@etconp
👍2🙏1
🌟 Product Name: PP Plastic Film Face Plywood
Size(mm): 1220*2440
Thickness(mm):18
Color: Green
Grade: First Class
Edges: Sealed with waterproof paint
Reuse Times : >15 times pending glue Type

✨ What is PP plastic Film plywood?Traditional film face plywood uses melamine film on the surface, where as PP(polypropylene) coating plywood uses plastic. Now what makes plastic better? It is non-corrosive, acid and alkaline retardant, and has a very rigid surface compare to melamine film. The biggest advantage is that PP plywood is wear resistant, durable, waterproof, doesn't stick to the concrete when its dry, and can be removed very easily. After dismount, the surface of the PP plywood remains smooth and intact,so it can be used repeatedly several time ,thus greatly increase the efficiency and quality of the form work.

☎️ Contact us: 0960306035
                     0967289643
👍3👌2❤1