Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
Pile foundation depending on their their function divided into two
A. Bearing pile
B. Friction pile


@etconp

@etconp

ማሳሰቢያ/ Announcement 📢

10 days left / 10ቀን ቀረው አሁንም አልረፈደም ተወዳደሩ

500 birr give away question is posted on our Facebook page

የሽልማት ጥያቄው አሸናፊውን የምንለየው November 20- 2023 ሲሆን ሽልማቱ 500 ብር ነው።

ጥያቄው የተለቀቀው በፌስቡክ ገፃችን እና በ ኢኒስታግራም ገፃችን ነው።

አሸናፊው የሚለየው ለመልሶቹ ብዙ ላይክ ያገኘ ነው። በትንሹ 30 ላይክ ሊኖረው ይገባል

አሁንም አልረፈደም

ጓደኞቻችሁን የለጠፋችሁትን ፎቶ ላይክ አስደርጉ

የ ኢንስታግራሙ ጥያቄ ሊንክ:- https://www.instagram.com/p/Cy72qOlsKm0/?igshid=MzRlODBiNWFlZA==

የፌስቡኩ ጥያቄ ሊንክ:- https://www.facebook.com/100064135238834/posts/pfbid033h5xCMU2QNC1taixH6W25gPnUFakMD5RMX4dcEnd3E6M1HCjmhL1UqHYMkEMMiNEl/?app=fbl

SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍2❤1
👉ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ አንድ ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ልትገነባ ነው ተባለ

🚧ኢትዮጵያ በ23 ከተሞች የውሃ አያያዝና አቅርቦትን ለማሻሻል የ523 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት መጀመሯ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ፕሮጀክት በመላ አገሪቱ 1 ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች መገንባትን እንደሚያካትት ተነግሯል፡፡

🚧ለዚሁ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያም የዓለም ባንክ የ460 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ቀሪውን 63 ሚሊየን ዶላር ደግሞ በሌሎች ለጋሽ ተቋማት ይሸፈናል ተብሏል።

🚧ፕሮጀክቱ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባትን የመቀሌ ከተማ የሚያካትት መሆኑን አዲስ ማለዳ ከአለም አቀፍ ኮንስትራክሽን ሪቪዉ ያገኘችዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

🚧ኢትዮጵያ በከተማዋ የውሃ መሰረተ ልማቶችን ለማዳረስ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ፓምፖች ለመግዛት 1 ሚሊየን ዶላር ወጪ ማድረጓም ተነግሯል፡፡

🚧በፈረንጆቹ 2018 ግሎባል ዋተር ኢንተለጀንስ የተሰኘው ተቋም አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት፤ በአገሪቱ ዘመናዊ መጸዳጃ የሚጠቀሙ የከተማ ነዋሪዎች 12 በመቶ ብቻ መሆናቸውን አመላክቷል።

@etconp
👍5
👉የሲሚንቶና የብረት ዋጋ ቅናሽ አሳየ

🌟በሲሚንቶ፣ በብረትና ሌሎች የግንባታ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ መታየቱን በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾችና ነጋዴዎች ገልጸዋል፡፡

🚧በከተማዋ የ1 ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋ ከ800 ብር እስከ 500 ብር ቅናሽ እንዲሁም 1 ቤርጋ ፌሮ በኪሎ የ15 ብር ቅናሽ ማሳየቱ ተሰምቷል፡፡

🚧ቀደም ሲል ግብይቱ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተመን ወጥቶለት ሲሸጥ የቆየ ቢሆንም ከታህሳስ ወር 2015 ዓ.ም ወዲህ  ግን በነጻ ገበያ መርህ ፋብሪካዎች ባቀረቡት ዋጋ  ግብይትት መካሄድ መቀጠሉን በቅኝቱ ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡

🚧ከዚህ ቀደም ሲሚንቶ ከ1 ሺህ 800 እስከ 2 ሺህ ሲሸጥ የቆየ ቢሆንም  አሁን ላይ ግን ኢትዮ ሲሚንቶ ከ1 ሺህ 250 እስከ 1 ሺህ 270፣ ሀበሻ ሲሚንቶ በ1 ሺህ 300 ብር እና ሙገር ሲሚንቶ በ1 ሺህ 350 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

🚧በተመሳሳይ የብረት ገበያም ቅናሽ የታየበት ሲሆን ለአብነትም 10 ቤርጋ ብረት 1 ሺህ 332 ሲሸጥ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ 1 ሺህ 36 ብር፣ 14 ቤርጋ ፌሮ ብረት 3 ሺህ 412 ብር ይሸጥ የነበረ ሲሆን  አሁን 2 ሺህ 654 ብር  በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

🚧በዘርፉ ላይ የተሰማሩት አምራቾችና ነጋዴዎች ሲሚንቶ፣ ብረትና ሌሎችም የግንባታ እቃዎች ሸማቾች ቁጥር መቀነሱንም አመላክተዋል።

Via FBC

@etconp
👍12❤2
👉የቻይና መንግስት  ለባቡር ሀዲድ መጠገኛ የሚሆን ሶስት ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ መስጠቱ ተገለጸ

🌟በ2015 ዓ.ም የማክሮ ፋይናንስ  እና የቻይና መንግስት ከተፈራረሙት አንደኛዉ የመለዋወጫ እቃ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ የመጀመሪያዉ ምዕራፍ ሶስት ኮንቴነር የእቃ መለዋወጫ መግባቱ ነዉ የተገለጸዉ።

🚧የገባዉ የገንዘብ መጠንም በዚህ ምዕራፍ ከታሰበዉ ሀያ ሁለት ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሶስት ሚሊየን የሚሆነው  መግባቱን  የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፓርት አገልግሎት ዋና ሾል አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን  አሰፋ ተናግረዋል።

🚧ከገቡት ሶስት ኮንቴነር የእቃ መለዋወጫ በተጨማሪ ከሶስት ወር በኃላም ተጨማሪ  የባቡር መለዋወጫዎች እንደሚገቡ የገለጹልን ኃላፊዉ አጠቃላይ የባቡር መለዋወጫ ችግርን ለመፍታት በዚህ እርዳታ ብቻ የሚፈታ አለመሆኑን በመግለጽ ለዚህም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥልቅ የሆነ ጥናት በቀላል ባቡር ባለሙያዎች መጠናቱን አስታውቀዋል፡፡

Via መናኸሪያ ሬዲዮ

@etconp
👍9❤2
👉በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ረቂቅ የህግ ማዕቀፎች ላይ የሚመክር የግብኣት ማሰባሰቢያ መድረክ በመካሄድ ላይ ነው

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ማሻሻያ ረቂቅ ሠነድ፣ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ረቂቅ አዋጅ፣ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ረቂቅ የስነ-ምግባር ደንብ እና የግንባታ ቦታ ደህንነት፣ ጤና እና አካባቢ ጥበቃ ደንብ ረቂቅ ሠነዶች ላይ ግብአታ ለማግኘት የሚያስችል የግብኣት ማሰባሰቢያ የጋራ የውይይት መድረክ በሚኒስቴር መ/ቤቱ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት በከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር፣ የኮንስትራክሽንና መሠረተ-ልማት መሪ ሾል አስፈጻሚ፣ ወ/ሎ መዲና መሀመድ እንደተናገሩት የኮንስትራክሽን ዘርፉን  በስነ ምግባርና በአሠራር ስርዓት እንዲደገፍ ለማድረግ የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነና በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትና ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች ሙያዊ አተያይ የማይተካ ሚና እንዳለው በማስታወስ ከተሳታፊዎች በርካታ ሀሳብና አስተያየት እንደሚገኝ ሙሉ እምነት እንዳላቸው በመግለጽ ተሣታፊዎች ጥሪውን አክብረው ስለተገኙ ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና ገልጸዋል፡፡

የእርሳቸውን ንግግር ተከታትሎ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሾል ተቋራጮች ማህበር ዓባላት ላይ በሚያቀርቡት የሠነድ ማዳበር ውይይት ላይ የጋራ አረዳድ ይዞ ለመውጣት እንዲያስችል  በአማካሪነት የሙያ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ የማህበሩ ዓባል፣ ተስፋዬ ያለው (ኢንጅነር)  ባቀረቡት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ረቂቅ አዋጅ ማስተካከያ ላይ ገለጻ ተደርጎ የጋራ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀሪዎቹ ረቂቅ ሠነዶች ላይም በሌሎች የማህበሩ ዓባላት የታዩ የማሻሻያ ሀሳቦች ቀርበው የጋራ ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡

ከማህበር የተወከሉ ኢንጂነሮች ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የተላከላቸውን ረቂቅ ሠነድ ሙያዊ አተያይን በተከተለ መንገድ የዓለም አቀፉን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በሙያው ውስጥ የገጠሟቸውን የአሠራር ችግሮች በማሳያነት በመጥቀስ ግብኣት የሚሆኑ በርካታ ሀሳብና አስተያየቶችን አቅርበው በተሰጡት የማስተካከያና የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ የጋራ አረዳድ ለመያዝ የሚያስችሉ የጋራ ውይይቶች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ዓባላት ፣ የህግ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ፣ የፖሊሲ፣ ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የስራ ክፍሉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከመንግስት አካሉና ከግሉ ዘርፍ ማህበራት የተወከሉ ተሳታፊዎች የሰጧቸው ግብአቶች የተዘጋጁትን የህግ ማዕቀፎች ለማሻሻልና ጸድቀው ተግባር ላይ እንዲውሉ በማድረግ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት እንዲችሉ ይህ የግንኙነት አግባብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ይጠበቃል፡፡

@etconp
👍5❤1🙏1
👉የኢትዮ-ጅቡቲ ትራንስፖርት ኮሪደር ፕሮጀክት አካል የሆነው የአዳማ - አዋሽ ምዕራፍ አንድ አዳማ ኪሎ ሜትር 60 የፍጥነት መንገድ የአስፋልት የማንጠፍ ሥራ ተጀመረ።

🚧የአዳማ-አዋሽ ምዕራፍ አንድ አዳማ ኪሎ ሜትር 60 የፍጥነት መንገድ 61.5 ኪሎ ሜትር  እርዝማኔ  ያለው  ሲሆን ፣ ግንባታው ከአፍሪካ ልማት  ባንክ  እና  ከኢትዮጵያ  መንግሥት  በተገኘ በ 6.6 ቢሊየን  ብር ወጪ  እየተከናወነ ነው። 

🚧ግንባታውን  የሚያከናውኑት  ጂ. ኤም.ሲ  እና  ኤል.አር .ቢ.ሲ.ኤል  የሚባሉ  አለም አቀፍ  ተቋራጮች  በጋራ  ሲሆን የማማከሩን ሼል የሚያከናውኑት  ደግሞ  ኤል.ኤ.ኤስ.ኤ  እና  ዩ.ኒ.ኮን ናቸው።

🚧ይህ 61 ኪ.ሜ የሚሸፍነው የፍጥነት መንገድ አገናኝ መንገዶችን ፣ ማሳለጫ መንገዶችን ፣ የክፍያ ጣቢያዎችን ፣ የመኪና እና የእግረኛ መሸጋገሪያ ድልድዮችን ያካትታል።

🌟የፕሮጀክቱ አሁናዊ አፈጻጸም 12.5 በመቶ ሲሆን፣ በዚህም የአፈር ጠረጋ፣ የቆረጣ ሥራ፣ የአፈር ሙሌት፣ የሰብ ቤዝ እና ቤዝ ኮርስ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን በእስካሁኑ 1.6 ኪሎ ሜትር የአስፋልት  ማንጠፍ ሾል ተከናውኗል። ከአፈጻጸም ጋር በተያያዘ የሚታዮ መስተጓጉሎችን በመቅረፍ በቀጣይ በተሻለ ፍጥነት እንዲከናወን ከፍተኛ ክትትል እና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል።

🚧መንገዱ ትልልቅ የድልድይ ግንባታ ፣ ማሳለጫዎችና ማቋረጫዎች ፣ የአቃፊ ግንብ ፣ የመንገድ ዳር የትራፊክ ምልክቶች ፣ የደህንነት ካሜራዎችን ፣ ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችን አካቶ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

🌟ከአዲስ አበባ እስከ አዳማ የሚዘልቀው 80 ኪሎ ሜትር የአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል ፤  የዚህ መንገድ ቀጣይ ምዕራፍ የሆነው የአዳማ-አዋሽ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የመስመሩን የትራፊክ ፍሰት ለማቀላጠፍ ብሉም የተሽከርካሪዎች የጉዞ ጊዜና ዋጋ በመቀነስ አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ይሆናል፡፡

🚧ከዚህም ባሻገር የዚሁ የፍጥነት መንገድ አካል ለሆነው የአዋሽ - ሜኦሶ - ድሬዳዋ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአለም ባንክ የ730 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ማጽደቁ ይታወቃል፡፡

🚧ይኸው የአዳማ-አዋሽ-ሜኦሶ-ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ከድሬደዋ-ደወሌ የክፍያ መንገድ ጋር በመተሳሰር ለአዲስ አበባ-ሰመራ-ጋላፊ መንገድ አማራጭ ሆኖ በማገልገል የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ወጪና ገቢ ንግድ ይበልጥ እንዲጠናከር ያስችላል።

@etconp
👍11❤1
👉ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

🫵የአገልግሎታችንን አድማስ በማስፋት የክቡራን ደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማርካት በታማኝነት እንተጋለን

🖱ፕሌት 1mm-30mm any size

🖱jbolt 12mm-32mm

🖱anker bolt

🖱stafa

🖱any modefic work

🚧ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

📩 @heavenic1 ፃፉልን

ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ

0904040477
0911016833
0994941706 ይደውሉ።
👍4🏆2❤1
👉የመቐለ የውሃ ፕሮጀክትን እንደገና ለማስጀመር የአንድ ሚሊዮን ዶላር ዕቃዎች ግዢ ተፈፀመ!

🚧በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የ መቐለ ከተማን የውሃ ፕሮጀክት እንደገና ለማስጀመር የአንድ ሚሊዮን ዶላር ዕቃዎች ግዢ መፈፀሙን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

🌟በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሳኒቴሽን መሠረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኑረዲን መሐመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በክልሉ በተለይ በመቐለ እና ዓዲግራት አካባቢዎች በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጠው የቆዩ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አሉ፡፡ ፕሮጀክቶቹን ለማስጀመር መንግሥት በትኩረት እየሠራ ነው፡፡

🌟ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከያዛቸው ሁለት ትላልቅ ፕሮግራሞች መካከል በከተሞች ላይ የንፁህ ውሃ እና ሳኒቴሽን ግንባታ እንደሆነ የጠቀሱት ኃላፊው፤ የተቋረጡ የመቐለ እና ዓዲግራት የውሃ ፕሮጀክቶችን ማስቀጠል የዚህ ፕሮግራም አካል ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

🌟በከተሞቹ ላይ የሚደረገው ግንባታ እስከ አሁን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች የተቃጠሉ ፓምፖች ለመተካት የግዢ ኮንትራት ተፈርሞ በአስቸኳይ ወደ ግዢ መገባቱን አመላክተዋል፡፡በዚህም የመቐለ ከተማን የውሃ ፕሮጀክት ለማስቀጠል የአንድ ሚሊዮን ዶላር ዕቃዎች ግዢ መፈፀሙን አመላክተው፤ ዓዲግራት የውሃ ፕሮጀክትን የማስቀጠል ሥራም የግዢ ሂደት ላይ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡

🌟እነዚህ ፕሮጀክቶች የውሃ ችግር ቁልፍ መፍትሄ እንደሚያመጡ የጠቆሙት ኃላፊው፤ ሌላ በወረዳ እና አነስተኛ ከተሞች ትኩረት በማድረግ የሚሠራ ፕሮጀክት እንዳለ በመጥቀስ፤ ሥራውን ለመቀጠል የተወሰነ ሲሆን፤ ተግባራዊ የሚደረገውም በራሱ በክልሉ እንደሆነና ገንዘብ ተመድቦ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

🌟ፕሮጀክቱ የጋራ መፀዳጃ ቤቶች ግንባታም የሚያጠቃልሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ፕሮጀክቱ በአፋጣኝ የውሃና ሳኒቴሽን ችግሮችን እንዲቀርፉ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው፤ ቀደም ሲል በክልሉ ላይ ተበላሽተው የነበሩት ትላልቅ የውሃ ፓምፖች እና ጄኔሬተሮች ግዢ ተደርጎ ሥራ እንዲጀምሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡

🌟በተመሳሳይ ፕሮጀክቱ በድርቅ እና በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች በተለይ ቦረና፣ አፋር እና አማራ ክልል ላይም ትኩረት በመስጠት በመንግሥትና በአፍሪካ ልማት ባንክ ፋይናንስ ተደርጎላቸው ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Via EPA

@etconp
👏5❤2👍2😢1
❤5👍3👏1
👆👆👆👆👆👆👆
👉የአይዛሂ ድልድይ ታሪክ እና ግንባታ

🌟የአይዛሂ ድልድይ በቻይና የተገነባ ድንቅ ተንጠልጣይ ድልድይ ሲሆን፣ ሁለት ግዛቶችን ማለትም ሁናንን እና ጉይዙን የሚያገናኝ ዘመን አመጣሽ ድልድይ ነው። ድልድዩ እ.ኤ.አ. በ2012 ለትራፊክ ክፍት ሲሆን በዚያን ጊዜ በዓለም ላይ ረጅሙ እና በከፍታውም የመጨረሻ ልዩ ተንጠልጣይ ድልድይ ነበር።

🚧የድልድዩ ግንባታ በጥቅምት ወር 2007 ተጀምሮ በ5 ዓመታት ውስጥ በአንድ ቢሊየን ዶላር ተጠናቀቀ። ድልድዩ 1,146 ሜትር ርዝመትና 355 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን፣ ይህም ድልድይ ከዓለማችን ረጃጅም ድልድዮች አንዱ ያደርገዋል።

🚧የድልድዩ ዲዛይን የተነደፈው በሜጀር ብሪጅ ሪኮንናይሰንስ እና ዲዛይን ኢንስቲትዩት (MBRDI) እና ኮንትራክተሩ ደግሞ የቻይና መንገድ እና ድልድይ ኮርፖሬሽን ነው።

🚧በድልድዩ ግንባታ ወቅት በጣም ግርምትን ከፈጠሩ  ነገሮች አንዱ በሸለቆው ላይ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ ጊዜያዊ የኬብል ዌይ ሲስተም መጠቀሙ ነበር። በዚህ ዘዴ ለድልድዩ ግንባታ የሚውሉ 10 ሺህ ቶን ብረት እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ አስችሏል።

🚧አሁን አሁን የአይዝሃይ ድልድይ በቻይና ተወዳጅ የቱሪስት መስህብ ሆኗል፣ ጎብኚዎች ከመላው አለም በመምጣት የድልድዩን የምህንድስና እና የስነ-ህንፃ አሰራሩን ያደንቃሉ። በተጨማሪም በሁናን እና በጊዙ መካከል ያለውን የመሄጃ ጊዜን በበርካታ ሰዓታት በመቀነስ በክልሉ ያለውን የትራንስፖርት እና ግንኙነት ለማሻሻል ረድቷል።

🚧የአይዝሃይ ድልድይ በመላው ቻይና የመሠረተ ልማት ግንባታና ስርጭት እንዲሁም አቅምን በሚገባ የገለፀና ያሳየ ነው።  ድልድዩ በመላው ቻይና የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን በተለያዩ መንገዶች ገልጿል።

🚧በመጀመሪያ ደረጃ፣ ቻይና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን የመገንባት አቅም እንዳላት አሳይታለች፣ ይህንንም በማድረግ ቻይናን በመሠረተ ልማት ዝርጋታ ዓለም አቀፍ መሪ አድርጓታል።

🚧በሁለተኛ ደረጃ፣ የአይዛሂ ድልድይ የቻይና የመጓጓዣ መሠረተ ልማት ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ምልክት ሆኗል። ድልድዩ በሁናን እና በጊዙ አውራጃዎች መካከል ከዚህ በፊት የሌለውን የትራንስፖርት ግንኙነት በመፍጠር፣ ጊዜን በመቀነስ እና በክልሉ ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማሳደግ ረድቷል።

🚧በሦስተኛ ደረጃ፣ የአይዝሃይ ድልድይ ለድልድይ ግንባታ እና ዲዛይን አዲስ ደረጃዎችን አውጥቷል። በሸለቆው ላይ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ ያገለገለው ጊዜያዊ የኬብል ዌይ ሲስተም ድልድዩ በተቀላጠፈ እና በዝቅተኛ ወጪ እንዲገነባ የሚያስችል ልዩ የምህንድስና መፍትሄ ሆኖ ቀርቧል።

🖱በመጨረሻም የአይዝሃይ ድልድይ የኢንጂነሪንግ እና የስነ-ህንፃ አሰራርን በማድነቅ ከመላው አለም የሚመጡ ጎብኚዎችን በመሳብ ተወዳጅ የቱሪስት መስህብ ሆኗል። ይህም በክልሉ ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ፣ የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማሳደግ እና አዳዲስ የስራ እድሎችን ለመፍጠር ረድቷል።

🌟በአጠቃላይ የአይዛሂ ድልድይ በቻይና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ አዲስ መመዘኛ ያስቀመጠ ሲሆን ስኬቱም በመላ አገሪቱ ያሉ ሌሎች የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን አነሳስቷል።

🚧በኢንቨስትመንት፣ በፈጠራ እና በቁርጠኝነት ቻይና ዜጎቿን የሚጠቅሙ እና የኢኮኖሚ እድገትን የሚያበረታቱ መሠረተ ልማቶችን በመገንባት መቀጠል እንደምትችልም አሳይቷል።

https://t.me/ETCONpWORK
❤7👍7
What type of slab do you think we will have ? As you can see the slab is RC structure and the column is steel structure.

@etconp

ማሳሰቢያ/ Announcement 📢

8 days left / 8 ቀን ቀረው አሁንም አልረፈደም ተወዳደሩ



የሽልማት ጥያቄው አሸናፊውን የምንለየው November 20- 2023 ሲሆን ሽልማቱ 500 ብር ነው።

ጥያቄው የተለቀቀው በፌስቡክ ገፃችን እና በ ኢኒስታግራም ገፃችን ነው።

አሸናፊው የሚለየው ለመልሶቹ ብዙ ላይክ ያገኘ ነው። በትንሹ 30 ላይክ ሊኖረው ይገባል

ውድድሩን በፌስቡክ እየመራ ያለው በፌስቡክ ስሙ Firanbon Tesfaye ሲሆን 36 ላይክ አግኝቷል።

በ ኢንስታግራም ደግሞ እየመራች ያለችሁ በ ኢንስታግራም username @fif_raya ስትሆን 40 ላይክ አግኝታለች

አሁንም አልረፈደም

ጓደኞቻችሁን የለጠፋችሁትን ፎቶ ላይክ አስደርጉ

IG link:- https://www.instagram.com/p/Cy72qOlsKm0/?igshid=MzRlODBiNWFlZA==

FB link:- https://www.facebook.com/100064135238834/posts/pfbid033h5xCMU2QNC1taixH6W25gPnUFakMD5RMX4dcEnd3E6M1HCjmhL1UqHYMkEMMiNEl/?app=fbl

SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍7❤5
👉What Is Concrete | Ingredients of Concrete | Concrete Test | Types of Concrete

🌟What Is Concrete?

⏺Concrete is a composite material made by mixing different material like cement, sand, aggregate & water with or without admixture

⏺Concrete is the most widely used and popular construction material, although no construction can be done without the use of concrete.

⏺Concrete is the oldest and most used man-made material on earth. Its most common construction material extensively used for buildings, bridges, roads, and dams. Its uses range from structural applications to sidewalk ways, curbs, pipes, and drains.

🚧ingredients of Concrete

🖱Concrete Materials

1. Cement

Cement is the main binder material used to bind other building concrete materials together. It is used for making mortar and concrete during the construction process.

2. Coarse Aggregate

Coarse Aggregate forms the major body of concrete. The aggregates contribute to the overall strength of the concrete by increasing density.

3. Fine Aggregate (Sand)

fine aggregate such as sand used to fill in the spaces left between the large coarse aggregate and to “lock” the larger pieces together. Sand helps in reducing the quantity of cement paste required and decreases the amount of shrinkage that could occur.

4. Admixture

Admixtures are added to enhance or to modify the properties of fresh & hardened concrete. (Plasticizers, retarders)

5. Water

it is the key ingredient, which when mixed with cement, forms a paste that binds the aggregate together. The water contributes to the hardening of concrete through a process called hydration. Its role is major in concrete because the strength of concrete extensively depends on water to cement ratio and it is the critical factor in the production of “perfect” concrete.

6. Fly Ash

Fly ash use in concrete improves the workability of plastic concrete and the strength and durability of hardened concrete. Fly ash use is also cost-effective. Fly ash added to concrete to reduce the amount of cement required for concrete, which contributes to considerable saving of cement and cost of concrete making.

🌟How to Make Concrete

🚧Steps of making concrete are given below

1) Decide ratio of concrete (1:1.5:3 or 1:2:4,  ....).

2) Take out the material as per ration like,

1 – For cement (take 50 kg)

1.5 – Sand (take 50 x 1.5 = 75 kg)

3 – Aggregate (take 50 x 3 = 150 kg)

3) These two methods of mixing concrete mixing and machine mixing.

4) First, add coarse aggregate on the floor and over it add sand then spread cement over it. Mix this ingredient well at least for 2 minutes.

 5) After that add water according to the water-cement ratio.

6) Mix all materials well until well mix concrete is ready to be used.

https://t.me/ETCONpWORK
👍14🏆1
"በመዲናዋ የተጀመሩት የ5 ሺህ ቤቶች ግንባታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል" - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ ያለውን የቤት እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ የተጀመሩት የ5 ሺህ ቤቶች ግንባታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃሉ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

የአቃቂ ተገጣጣሚ ቤቶችን ውስጥ ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ 400 ቤቶችን መመልከታቸውን ተቁመዋል።

ከንቲባዋ የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች፣ የቤቶችንና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንደገለፁት፣ በከተማችን ያለውን የቤት እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ በከተማው በጀት ግንባታቸው የተጀመሩ የ5 ሺህ ቤቶች ግንባታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃሉ ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ከተገነቡት ሆስፒታሎች ሁሉ የሚልቁት የቤተል-መንዲዳ ሪፈራል ሆስፒታልና የላፍቶ ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታቸው በያዝነው በጀት አመት ሲጠናቀቁ ከሚሰጡት ማህበራዊ ፋይዳ በተጨማሪ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል የሚያደርጉ ይሆናል።

ለከተማዋ 4ኛው የገበያ ማዕከል የሆነው የላፍቶ ምዕራፍ 2 የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከል 144 ሱቆች እና 14 መጋዘኖች የተካተቱበት ሲሆን በቀጣይ 90 ቀናት ውስጥ ግንባታውን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ የገበያ ሰንሰለቱን በማስተካከል አምራችን በቀጥታ ከሸማች ጋር በማገናኘት የአዲስ አበባን ህዝብ የኑሮ ጫና የማቃለል ስራን ውጤታማ የሚያደርግ ይሆናል ብለዋል::

"አዲስ አበባን ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ ማድረግ በቃል ብቻ ሳይሆን የገባነው ቃል በተግባር እውን እየሆነ በመምጣቱ እንኳን ደስ አላችሁ" ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል።

Via ኢፕድ

@etconp
👍11😁4❤1
" በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ላሉ ባለሙያዎች #የብቃት_ምዘና ይጀመራል " -  ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር)

በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ ላሉ ባለሙያዎች #የብቃት_ምዘና እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡

በዘርፉ ብቃት ሳይኖራቸው፣ አቅማቸው ሳይረጋገጥና ማረጋገጫ ሳያገኙ ራሳቸውን #መሐንዲስ እያሉ የሚጠሩበትን አሠራር ያስቀራል የተባለለት እንዲሁም የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት የሚረዳ የማሠልጠኛ ማንዋልና የሚመዘኑበት መመርያ መዘጋጀቱን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሚኒስትር  ደኤታ ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር) ምን አሉ ?

- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ተመርቆ ወደ ሥራ የሚገባ አንድ ባለሙያ በሚሠራበት ተቋም ውስጥ በቆየ ቁጥር የሙያ ደረጃዎች ከመስጠት ባለፈ መመዘኛ ሥርዓት ባለመኖሩ፣ ባለሙያው ለሚጠበቅበት ዕውቀትና ክህሎት ብቁ ነውወይ ሚለው አይታወቅም።

- ከኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየተዘጋጀ ያለው መመርያ በቅርቡ ለፍትሕ ሚኒስቴር ተልኮ ይፀድቅና ወደ ሥራ ይገባል።

- የሚወጣው መመርያ ባለሙያዎች የሚሠለጥኑበት ፣ የሚገመገሙበትና ዕውቅና የሚያገኙበት ከመሆኑም በላይ የሙያ ግድፈት ሲገኝባቸውም የሚቀጡበትን አሠራር አካቷል።

- አገሪቱ አሁን ባለችበት የኮንስትራክሽን ቁመና የግንባታ ጥራት አደጋ ውስጥ ነው። ሥራ ከተጀመረ በኋላም ሆነ ከመጀመሩ በፊት የሚታየው የጥራት መጓደል አሁን ካልተፈታ በቢሊዮን ዶላሮች የሚፈስበት ዘርፍ ተመልሶ የማይወጣበት ችግር ውስጥ ይገባል።

- በኮንስትራክሽን ዘርፉ የባለሙያ አቅምና የሙያ ሥነ ምግባር እየተሻሻለ ከመሄድ ይልቅ እየባሰበት ነው የሄደው ፤ ባለሙያው ከአዳዲስ ዕውቀትና ቴክኖሎጂ ጋር የሚተዋወቅበትና ራሱን የሚያበቃበት ሳይሆን እያጠፋ የሚማርበት ሆኖ ቀጥሏል።

- በዘርፉ በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች የሉም። ባለሙያዎቹ ወደ ሥራ ከገቡ በኋላ ብቃታቸው ሊያድግ የሚችለው በራሳቸው ጥረት እንጂ፣ ከዘርፉ በሚያገኙት ትምህርትና ተቋማዊ ዕውቀት አይደለም።

- በአገር ውስጥ የበቁ የሚባሉት እና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ወደ ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ናቸው። በተለይም በምሥራቅና በደቡብ አፍሪካ አገሮች ተፈላጊ ናቸው። በአገር ውስጥ ያሉ ባለሙያዎችም ባሉበት ተቋም ለረዥም ጊዜ ረግተው አይቆዩም። በበገበያ ውስጥም የዋጋ ጭማሪን በየጊዜው መተንበይ በማይቻልበት ሁኔታ የግንባታ መሣሪያዎች ዋጋ አልቀመስ ብሏል።

- ግዙፍ ፕሮጀክቶች አብዛኞቹ የውጭ ኮንትራክተሮች ብቻ የሚይዟቸው፣ የአገር ውስጥ ባለሙያዎች የውጭ ኮንትራክተሮች በሚይዟቸው ፕሮጀክት ውስጥ ገብተው ዕውቀት እንዲቀስሙ የሚያደርግ አሠራር አልተዘረጋም ይህ የዘርፉ ሌላው ተግዳሮት ነው።

- በኮንስትራክሽን ዘርፍ የግዥ ሥርዓትን ጠንቅቆ የሚያውቅ ባለሙያ አለመኖሩ ፤ ሁሉም ባወቀውና በገባው ልክ እንጂ በትክክል ሥራውን ተገንዝቦ የሚሠራ የለም።

- በኮንትራት አስተዳደር የተሰማሩ ባለሙያዎች በአንድ ጉዳይ ባለመግባባታቸው ምክንያት ክስ ሲመጣ ተመልሶ ውልን ከመቃኘት ውጪ፣ ከጅምሩ የኮንትራት ውል አስተዳደርን ዝርዝር ጉዳይ ተረድቶ የሚያስረዳ ባለሙያ የለም።

- ለኮንስትራክሽን ጥራት መጓደል ፦ በግዥ ሥርዓቱ ላይ ያለው አሠራር፣ የፕሮጀክቶች ዲዛይን የተሟላና የተደራጀ አለመሆን የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው። ወደ አፈጻጸም ሲገባ ባሉት ኮንትራክተሮችና አማካሪዎች የአቅም ውስንነት የተነሳ የሚታሰበውን ጥራት ለማረጋገጥ አዳጋች ሆኗል።

- በኢትዮጵያ የግንባታ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከመሬት ልየታ ጀምሮ ሕንፃው ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ መሟላት ያለባቸው ዓለም አቀፍ መሥፈርቶች፣ አጠቃላይ ይዘትና ቁመናው ምን መምሰል እንዳለበት የተቀመጡ ስታንዳርዶች የሉም። በዚህም በኢትዮጵያ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የመኖሪያ ቤቶች ሲገመገሙ፣ የመኖሪያ ቤት ለመባል የተሟላ ቁመና ያላቸው ከ25 በመቶ የማይበልጡ ናቸው። 75 በመቶ ያህሉ ከደረጃ በታች ናቸው።

- ለቤቶቹ ጥራት መጓደል ምክንያት ከመጀመሪያው የግንባታ ዕቅድ ጀምሮ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፣ መሟላት ባለባቸው ዓለም አቀፍ መሥፈርቶች የተቃኙ አለመሆናቸው ነው።

- ከዚህ በኋላ በሀገሪቱ ሚገነቡ ቤቶች ለሰው መኖሪያ ለመባል የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ መሥፈርቶችን ባሟላ መንገድ እንዲሆን፣ የሕግ ማዕቀፍና ስታንዳርድ ይዘጋጃል። በአሁኑ አሠራር ግን ማንኛውም የሥራ ተቋራጭ ውል ገብቶ ግንባታ ከጀመረ በኋላ ፣ በጥራትና በጊዜው ያጠናቅ ወይም አያጠናቅ መቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት የለም ብለዋል፡፡

ይህ መረጃ ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ ነው።

@etconp
👍26🙏3❤1🕊1
👉በሱዳን መዲና ካርቱም አባይ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ መፍረሱ ተገለጸ።

🚧በጎረቤት ሀገር ሱዳን በ ብሔርራዊ ጦሩ እና ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች መካከል ጦርነት ከተጀመረ ሰባተኛ ወሩ ላይ ይገኛል።

🚧ሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች ካሳለፍነው ሚያዝያ ወር ጀምሮ እየተዋጉ ሲሆን በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ሲገደሉ ከ6 ሚሊዮን በላይ ሱዳናዊያን ደግሞ ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል።

🚧እልባት ባልተገኘለት በዚህ ጦርነት በሀገሪቱ መዲና በአባይ (ናይል) ወንዝ ላይ በተገነባው ድልድይ ላይ በተፈጸመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ምክንያት ድልድዩ መፍረሱ ተገልጿል።

🚧የሀገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱምን ከኦምዱርማን የሚያገናኘው ይህ ድልድይ ሻምባት የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን አገልግሎት መስጠት በማይችልበት ሁኔታ መውደሙን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

🌟ድልድዩን ማን መታው? የሚለው ጉዳይ እስካሁን ግልጽ ያልሆነ ሲሆን አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጣት ከመጠቋቆማቸው ባለፈ ሀላፊነት የወሰደ አካል የለም ተብሏል።

Via Alain

@etconp
👍8❤3
Notice that this staircase doesn’t have waist slab so what do we call such type of staircase ?

@etconp

ማሳሰቢያ/ Announcement 📢

7days left / 7ቀን ቀረው አሁንም

የሽልማት ጥያቄው አሸናፊውን የምንለየው November 20- 2023 ሲሆን ሽልማቱ 500 ብር ነው።

ጥያቄው የተለቀቀው በፌስቡክ ገፃችን እና በ ኢኒስታግራም ገፃችን ነው።

አሸናፊው የሚለየው ለመልሶቹ ብዙ ላይክ ያገኘ ነው። በትንሹ 30 ላይክ ሊኖረው ይገባል

ውድድሩን በፌስቡክ እየመራ ያለው በፌስቡክ ስሙ Fiseha Birhan ሲሆን 36 ላይክ አግኝቷል።

በ ኢንስታግራም ደግሞ እየመራች ያለችሁ በ ኢንስታግራም username @fif_raya ስትሆን 40 ላይክ አግኝታለች

አሁንም አልረፈደም

ጓደኞቻችሁን የለጠፋችሁትን ፎቶ ላይክ አስደርጉ

IG link:- https://www.instagram.com/p/Cy72qOlsKm0/?igshid=MzRlODBiNWFlZA==

FB link:- https://www.facebook.com/100064135238834/posts/pfbid033h5xCMU2QNC1taixH6W25gPnUFakMD5RMX4dcEnd3E6M1HCjmhL1UqHYMkEMMiNEl/?app=fbl

SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍5❤3