Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ለሚመለከታቹ በ ሙሉ

@etconp
👍10😁3🕊1
#ADVERTISEMENTS

👉ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ

0904040477
0911016833 ደውለው ያግኙን

📩ወይም @heavenic1 ፃፉልን

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ ኮርቻ ተራ
                ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
                 ቁ.3 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት
                 ቁ.4 ቄራ ላይ በቅርቡ ይጠብቁን

🌟ከቃላችን ይልቅ ስራችን ይናገራል

🚧ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤1
👉የአርማታ ሙሌታ (Concrete Compaction) ቁጥጥር

🌟1. የግብአት ጥራትን (Materials Quality)፦ በአርማታ ሙሌት ሥራ ሂደት ውስጥ የሚጠቀማቸውን የማምረቻ ግብአቶች ጥራት በተገለጸው መስፈርት መሰረት የሚያሟሉ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። ይህ ማለት የቀረበው ሲሚንቶ (Cement) አይነትና የምርጥ ጥራት፣ የአሸዋ (sand or Fine aggregate) እና ጠጠር (Coarse Aggregate) ሳይንሳዊ ምዘናን ማሟላቱን፣ የማቅጠኛ ውሀ (Water) የኮንክሬት ስትራክቸሩን ሊጎዳ የሚችል ኬሚካልና ቆሻሻ የሌለው የጠራ ውሃ መሆኑን እና ሌሎች ተጨማሪ ኬሚካል (Admixture) መለያ አይነት የተሟላ መሆኑን ሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ ተደግፎ የማረጋገጥ ሂደትን መተግበር ማለት ነው። በዚህ ረገድ የግብአት መሐንዲሱ (Materials Engineer) ለሳይቱ በቀረበው የቤተሙከራ ክፍል ውስጥ በመስራት የማረጋገጥ አልያም በቅርቡ በሚገኝ የቤተሙከራ አገልግሎት ሰጪ ተቋማ በማሰራት የግብአቶችን ጸባይ የመለየትና ማረጋገጫ የመስጠት ግዴታ ይኖርበታል።

🌟2. የግብአቶችን ልኬት (Batching of materials):- በተለይ በሀገራችን የግንባታ ልምድ ኮንክሬት በሚመረትበት ሰዓት ያለው የአሸዋ፣ የጠጠር እና የውሃ ልኬት ለችግር የተጋለጠ ነው። አንድ 1፡2፡3 ምጥጥንን መሰረት አድርጎ ዲዛይን የተሰራ አርማታ አንድ እጅ ሲሚንቶ፣ ሁለት እጅ አሸዋ፣ ሦስት እጅ ጠጠር መጠቀም አለበት ማለት ቢሆንም የመቀላቀያ ማሽኑ ተቆጣጣሪ (Mixer Operator) ይህንን ምጥጥን ጠብቆ አምራታ የማምረት ልምድ ቸልተኝነት የተሞላበት እንደሆነ ይስተዋላል። ተቆጣጣሪ መሐንዲስ በምጥጥን (Proportion) መሰረት እየተመረት መሆኑን መቆጣጠር የግድ ነው።

🌟3. የማሽን እና መሳሪያ ደህንነት (Equipments Security):- የኮንክሬት ድብልቅ ማምረቻ ማሽኖች (mixers) ደህንነታቸው የተረጋገጠ ወይም በአግባቡ የሚሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ የኮንክሬት ግብአቶችን መለኪያ ሳጥኖችን (box) ርዝመት ወርድ እና ቀመት (L, W, H) አግባብነት ያለው መሆኑን (ለምሳሌ፦ 18*40*50)፣ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ብሎም የካሳ ሙግትና የሥራ ማቆም መሰናክል እንዳይፈጠር የሰራተኞች ደህንነት መጠበቂያ አልባሳት የተሟሉ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

🌟4. በአግባቡ መጠቅጠቁን፦ የሚሞላው አርማታ በተለይ ምሰሶ (column) እና የምሰሶ ጫማ (Footing Pad) በክፍልፋይ ላየሮች  ከፋፍሎ እያንዳንዱ የላየር ክፍል ጫፍ ላይ ሲደርስ በኤሌክትሪክ መንዘሪያ (Vibrator) በደንብ መጠቅጠቅ መቻል አለበት። የአርማታ መጠቅጠቅ እያንዳንዱ የግንባታ ግብአት በአግባቡ የተሰራጨ እንዲሆን እና የቀጠነው አርማታ ወደታች ወርዶ ጠጠራማው ወደላይ እንዳይቀር በማድረግ የትኛውም የስትራክቸር ክፍል ተመሳሳይ አይነት ጥንካሬ እንዲኖረው ያደርጋል።

🌟5. የአርማታ ድርቀት እንዳይኖር መቆጣጠር፦ የአርማታ ሙሌት ሂደት ላይ አዲስ የተመረተ አርማታ አላስፈላጊ ደቂቃዎችን ሳይሞላ መቆየት የለበትም። አርማታ ሳይሞላ ከሚክሰር እንደተገለበጠ የሚቆይ ከሆነ በፎርምወርክ ውስጥ ሆኖ መያዝ ያለበትን የመጀመሪያ ጥንካሬ (Initial Setting) መያዝ ስለሚጀምር ከዚያ በኋላ ሙሌትን ለማከናወን አዳጋች ከመሆኑም በላይ የሚፈለገውን የኮንክሬት ስትራክቸር ጥንካሬ ለማግኘት አዳጋች ይሆናል።

🌟6. የድኅረ ሙሌት ቁጥጥር፦ አርማታ ከተሞላ በኋላ በሳይንስ የተቀመጡ የፎርምወርቅ ማስወገጃ ቀናቶችን (Formwork Removal time) ጠብቆ እንዲፈርስ ማድረግ (በተለይ በቀዝቃዛማ እና ዝናባማ አካባቢዎች)፣ የተሞላው አርማታ በአግባቡ ውሃ እየጠጣ (curing) መሆኑን መከታተል እና የሚቀጥሉ የኮንክሬት ስትራክቸሮች ካሉ የተሞላው አርማታ በቂ ጥንካሬ ካገኘ በኋላ ሥራቸው የሚጀምር መሆኑን መከታተል አለበት።

🫵የ ኮንስትራክሽን ስራ እና ጨረታ በ ትኩሱ እንዲደርስዎ ከታች ባለው የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇

t.me/ETCONpWORK

📩ሊያወሩን ካሰቡ በቴሌግራም @ETCONpBot ይጻፉልን።

@etconp
❤9👍8🙏1
👉አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) የዓባይ ግድብ ዋና ተደራዳሪ ሰለህዳሴ ግድብ ትላንት ከተናገሩት መካከል

🚧ሰኔ ላይ የኮንክሪት ስራዉ ሙሉ ለሙሉ ያልቃል፤

🚧በያዝነው አመት አምስት ተርባይኖች ወደ ስራ ይገባሉ፤

🚧ከ94 በመቶ በላይ ደርሷል፤

🚧ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት እየሄዱ ነው፤ በ2016 ውስጥ ይጠናቀቃሉ >>ብለዋል።

@etconp
❤14👍1😢1
👉ኮልፌ አጠቃላይ ሆስፒታል ግንባታ

🌟በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) የሥራ ተቋራጭነት ከ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ የኮንትራት ዋጋ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ቤተል መንዲዳ አካባቢ እየተገነባ ያለው የኮልፌ አጠቃላይ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት 64 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን  የስትራክቸራል ሥራው አልቋል ።

⏺አሁን ላይ የማጠናቀቂያ፣ የመንገድ፣ የአጥር፣ የግቢ ማስዋብ እና ሌሎች የሳይት ሥራዎች እየተሰሩ ነው። ፕሮጀክቱን እስከ በጀት ዓመቱ ሰኔ 30 ቀን 2016ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ታቅዷል፡፡

▶️የዕቃዎች የዋጋ መናር እና በገበያ ላይ አለመገኘት፣ የዲዛይንና የክፍያ ችግሮች በግንባታ ሂደት ውስጥ ያጋጠሙ ችግሮች ነበሩ።

⏺በ24 ሺህ 500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈው ይህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 500 አልጋዎችን የሚይዙ የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችን የሚሰጡ 14፣ 2B+G+1-4 ብሎኮችን፣ ሌሎች 4፣ G+0 ህንፃዎችን እና የሳይት ሥራዎችን ያጠቃልላል፡፡

▶️ፕሮጀክቱ ንዑስ ሥራ ተቋራጮችን ጨምሮ ለ550 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

🚧ፕሮጀክቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እንደ ሥራ ተቋራጭ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ እንደ ባለቤት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ኮርፖሬሽን እንደ አማካሪ ድርጅት ይከታተሉታል፡፡

Via ጌጡ ተመስገን

@etconp
❤8👍3🏆2😢1
👉የወጪ እና ተጨማሪ ክፍያ ውል (Cost Plus Fee Contract)

🌟ይህ የውል አይነት ለግንባታው የወጣውን ዋጋ እና ለተቋራጩ የሚከፈለውን የጉልበት ዋጋ ወይም ትርፍ የሚከፈልበት ሲሆን በሦስት አይነት መንገድ ሊገለጽ የሚችል ነው።

(1). ወጪ እና ቁርጥ ክፍያ (Cost plus fixed fee):- አንድን ሕንጻ ለመገንባት የሚዋዋለው ተቋራጭ ለሕንጻው ግንባታ ያወጣው  የሚያስአጋ ምንምም ይሁን ምን ለሰራበት ለብቻው ተለይቶ የሚከፈለው ሲሆን ነው። ለምሳሌ አንድ ሕንጻን ከሚፈጀው ዋጋ የተለያየ (የሚቀያየር) ቢሆንም ተቋራጩ ግን ለገነባበት የተስማማው ገንዘብ 1,000,000 ብር ያ ብር ብቻ የሚከፈለው ሲሆን ነው።

(2). ወጪ እና አንጻራው ፐርሰንት ክፍያ (Cost Plus Percentage fee)፦ በዚህ አይነት ውል ላይ ተቋራጩ የሰራውን ሥራ ያህል በተቆረጠ ፐርሰንት የሚከፈለው ሲሆን ነው። ለምሳሌ፦ ተቋራጩ አንድን ፕሮጀክት በ100,000,000 ብር ቢያጠናቅቅ ግንባታውን ላከናወነበት ክፍያ 10% የተዋዋለ ቢሆን 10,000,000 ብር የሚቀበል ሲሆን ነው።

▶️ነገር ግን የግንባታ ዋጋው ቢጨምር ወይም ቢቀንስ ለተቋራጩ የሚከፈለውም በዚያው ልክ (በፐርሰንት ስለሚባዛ) ይለያያል ማለት ነው።

(3) ወጪ እና የተለያየ ክፍያ (Cost Plus Variable Fee)፦ በዚህ ውል አይነት ተቋራጩ በተለያዩ የሥራ አይነቶች የተለያየ ክፍያ የሚያገኝበት ሲሆን ነውል። ለምሳሌ፦ የመሬት ሥራዎችን ሲያጠናቅቅ 10% ክፍያ ለሰራበት የሚፈጸመበት፣ ከመሬት በላይ ላሉ ዋና ዋና ስትራክቸራ ሥራዎች ሲያጠናቅቅ 15% ክፍያ ለሰራበት የሚፈጸመበት፣ ፣ ማጠቃለያ ሥራዎች (Finishing works) ሲያጠናቅቅ 8% ክፍያ ለሰራበት የሚፈጸመበት ሲሆን ወይም በሌላ መንገድ በየደረጃው የተለያየ ክፍያ ከተዋዋለ ነው።

Via ኢ/ር ስዩም መሸሻ

📩ሊያወሩን ካሰቡ በቴሌግራም @ETCONpBOT ይጻፉልን።

🫵የመወያያ ቴሌግራም ግሩፕ ለመቀላቀል ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ይግቡ👇

t.me/COTMp
👍16❤4🙏3🕊1
👉የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ግንባታዉ 62 በመቶ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ

🚧በ2013 ዓመተ ምህረት ግንባታዉ የተጀመረዉ የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ግንባታዉ 62 በመቶ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።

▶️ጠ/ሚኒስትሩ ለ12ኛ ጊዜ ባካሄዱት የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግምገማ በተካሄደዉ የፕሮጀክት አስተዳደር እና ክትትል ስርዓት የተነሳ የአጠቃላይ ግንባታው ሂደት 62% ላይ መድረሱን ተናግረዋል።

⏺በአፍሪካ ደረጃ በግዙፍነታቸው አንደኛ እና  ሶስተኛ የሆኑትን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ እና የኮይሻ ግድቦች ባለቤት በመሆናችን የንፁህ የኃይል ማመንጨት ስራችንን እና ጥረታችንን አቻ የሌለው ያደርገዋል ያሉም ሲሆን በቅርብ ርቀት በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘውን የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅን በምንመርቅበት በአሁኑ ወቅት የኮይሻ ግድብ ለአካባቢው የቱሪዝም ዕድል ተጨማሪ አስተዋፅኦ ያደርጋል ሲሉ ጨምረዉ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

@etconp
👍5❤2👏2🥰1
👉ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

🫵የአገልግሎታችንን አድማስ በማስፋት የክቡራን ደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማርካት በታማኝነት እንተጋለን

🖱ፕሌት 1mm-30mm any size

🖱jbolt 12mm-32mm

🖱anker bolt

🖱stafa

🖱any modefic work

🚧ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

📩 @heavenic1 ፃፉልን

ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ

0904040477
0911016833
0994941706  ይደውሉ።
👍9😢1👌1🏆1
👉የግንባታ ሕግ (Construction Law)

🌟ኢትዮጵያ የምትጠቅምባቸው የኮንስትራከሽን ሕጎች" - ሀገራችን ኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ለማስተዳደር የምትጠቀምባቸው አዋጆች (Decree)፣ ደንቦች (regulations)፣ መመሪያዎች (Directives)፣ ስታንዳርዶች (Manuals)፣ የውል ሰነዶች (Contract Conditions)፣ ህጎች (Laws and codes)፣ ጋዜጦች
(Negarit) አሏት።

▶️እነዚህን ማእቀፎች በሁለት ምድብ መመደብ (ዓለም አቀፋዊ እና ሀገር አቀፋዊ) ማለት እንችላለን።

🖱1.በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የኮንስትራክሽን ውል ማህቀፎች

⏺(Federation Internationale Des Ingenieurs Conseils): EU
condition of contract፣ NEC- new
contract, UK (በተለይ ለውኃ ቁፋሮ ውል የሚውል) ናቸው።

✨ከዚህ ባሻገር · ማኑዋሎችን እንደ መሪ ልኬት (በተለይ የግንባታ ግብአቶችን ጥራት በቤተሙከራ ለመለካት) እንጠቀማለን።

📍ከእነዚህም ውስጥ:- American Society Testing Materials (ASTM), and AASHTO (American Association of State Officials) ሲሆኑ Indian Standards (IS) እና እልፎ ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው።

🖱2. የሀገር ውስጥ ማሕቀፎች: Building and Transport Construction Design Authority (BaTCoDA - የግንባታ ሥራዎችንና ግብአቶችን መጠን ለማስላት)፣ Public Procurement Agency (PPA - ለጨራታ እና የስምምነት ውል ሰነድ
አስተዳደር)፣ Civil Code, Civil Procedural codes, Ministry of Works and Urban Development Standard Conditions of Contract (MOWUD Directives), FDRE constitution, ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ (Negarit Gazieta), በየጊዜው የሚሻሻሉ የሕንጻ መመሪያዎች እና ስታንዳርዶች፣ የሙያ እና የሥራ ፍቃድ አዋጆች የመሳሰሉት ይገኙበታል።

🚧በእርግጥ በኮንስትራhሽን ዘርፉ ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ አይችሉም የሚባሉ የሀገሪቱ ህጎች አይኖሩም ማለት
ይከብዳል፣ ምክንያቱም ሁሉም ህጎች ከቦታ፣ ከሥራ፣ ከሰው ኃይል፣ ከመብትና
ግዴታ፣ ከንብረት፣ ከወንጀልና ፍትሕ ጋር የተያያዙ ስለሆነ እና የኮንስትራክሽ
ሴክተሩም እነዚህ ሁሉ የሚገኙበት ኢንዱስትሪ ስለሆነ ነው።

#ConstructionLaw

🫵የ ኮንስትራክሽን ስራ እና ጨረታ በ ትኩሱ እንዲደርስዎ ከታች ባለው የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇

t.me/ETCONpWORK

📩ሊያወሩን ካሰቡ በቴሌግራም @ETCONpBot ይጻፉልን።

@etconp
👍13❤5👌1