Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ገንዘብ ሚኒስቴር ከ79 ሺሕ በላይ ቤቶችን ለማስገንባት አቅም ላላቸው አልሚዎች ጥሪ አቀረበ

የመጀመሪያዎቹ ቤቶች ለኢቢሲና ለቤቶች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ይተላለፋሉ
በገንዘብ ሚኒስቴር ሥር ያለው የመንግሥትና የግል አጋርነት ዲፓርትመንት 79,800 ቤቶችን ለማስገንባት አቅም ላላቸው አልሚ ድርጅቶች ጥሪ አቀረበ፡፡ ቤቶቹ በአብዛኛው ለመንግሥትና ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሠራተኞች እንደሚገነቡ ታውቋል፡፡

የገንቢዎችን አቅም ለመለካት የወጣው የተወዳዳሪነት መጠየቂያ (Request for Qualification) እንደሚያመለክተው፣ ገንቢዎች በራሳቸው የፋይናንስ አቅም ቤቶቹን ዲዛይን ማድረግ፣ መገንባት፣ መሠረተ ልማትና አገልግሎት ማቅረብ፣ ማስተዳደርና ጥገና ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በመንግሥትና በግል አጋርነት አሠራር መሠረት፣ መንግሥት የአልሚዎቹን ወጪ ከቤቶቹ ተጠቃሚዎች በሚሰበስበው ገንዘብ ይሸፍናል ተብሏል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር በመንግሥት አሠራር መሠረት ቤቶቹን ገንብተው ለማቅረብ ፍላጎት ያሳዩ አልሚዎች መኖራቸውን ማረጋገጡን፣ እስከሚቀጥለው ወር ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዱን የማይመለስ አሥር ሺሕ ብር እየከፈሉ ከራሱ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ ብሏል፡፡ ለዚሁ ሥራ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ አልሚዎች የተጋበዙ ሲሆን፣ ሁለቱ በመጣመር መወዳደር እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ የሚኒስቴሩ ሰነድ እንደሚያሳየው ከሆነ ከፍተኛ የቤት ፍላጎትና የአቅርቦት ክፍተት መኖሩን፣ ይህንን ችግር ለማቃለል ብሔራዊ የመንግሥትና የግል አጋርነት ምክር ቤት በአፋጣኝ የ79,800 ቤቶቹን ግንባታ አፅድቋል፡፡

ከሚገነቡት ቤቶች ውስጥ በቅድሚያ የሚያልቁት 1,600 ቤቶች ለፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች፣ እንዲሁም 2,000 ያህሉ ደግሞ ለኢቢሲ ሠራተኞች ይሰጣሉ ተብሏል፡፡ በተለይ የኢቢሲ ሠራተኞች፣ ‹‹ለረዥም ዓመታት ቤት ይሰጣችኋል ብንባልም ዘግይቷል፤›› ሲሉ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ለመጀመሪያ ጊዜ የመንግሥትና የግል አጋርነት አሠራርና አዋጅ በ2010 ዓ.ም. ያፀደቀ ቢሆንም፣ በዚህ አሠራር እስካሁን የተሳካ ፕሮጀክት የለም፡፡ የአዳማ-አዋሽና የሚኤሶ-ድሬዳዋ የፍጥነት መንገዶችን፣ እንዲሁም የፀሐይና የኃይድሮ የኃይል ማመንጫዎችን ጨምሮ፣ አሥራ ሰባት ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በአጋርነት ለመገንባት ተይዞ የነበረው ዕቅድም ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል፡፡

በተለይ የውጭ ባለሀብቶች በመንግሥትና በግል አጋርነት አሠራር ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት የውጭ ምንዛሪ ዋስትና ሲጠይቁ የቆዩ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የሚቀርበው ዝቅተኛ የታሪፍ ድርድር ዋነኛው የችግሩ መንስዔ ነበር፡፡

እነዚህን ችግሮችና ሌሎች ለመንግሥትና ለግል አጋርነት አተገባበር የሚያስፈልጉ ሕጎችን በማካተት አዋጁ ባለፈው ዓመት ተሻሽሎ በፓርላማው የፀደቀ ሲሆን፣ የ79,800 ቤቶችም ግንባታ በአዲሱ አዋጅ የሚተገበር የመጀመሪያው ፕሮጀክት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቤቶቹ በተለያዩ ኮንትራክተሮች ተከፋፍለው ይገነባሉ ተብሏል፡፡ በቀጣይ ሆስፒታልን ጨምሮ ሌሎች መንግሥት ብቻውን ፋይናንስ ማድረግ ያልቻላቸው ፕሮጀክቶች፣ በመንግሥትና በግል አጋርነት ለመገንባት ዕቅድ የተያዘ ሲሆን፣ በዚህም መንግሥት እያጋጠመው ያለውን ከፍተኛ የበጀት ጉድለት ያቃልላል ተብሎ ተስፋ ተጥሏል፡፡

Via ሪፖርተር

@etconp
👍15😁2🏆2🙏1👌1
Ethio Construction Engineering
ጥያቄ፦ የመንግሥት አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች አንድን ግንባታ ለተቋራጭ ለመስጠት ጨረታ የማውጣት ግዴታ አለባቸው?
👉የ ትላንት ጥያቄ ከነ መልሱ

🖱ጥያቄ፦ የመንግሥት አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች አንድን ግንባታ ለተቋራጭ ለመስጠት ጨረታ የማውጣት ግዴታ አለባቸው?

🌟አንድን ውል ለመመስረት ተዋዋይ አካላት በሦስት አይነት መንገድ የውል ግቢ ጥሪ (Invitation to bid)
ሊቀርብላቸው ይችላል።

⏺እነዚህም መንገዶች ከአንድ ብቁ ተዋዋይ ጋር ድርድር (Negotiation)፣
የተመረጡ ጥቂቶችን የመጋበዝ (Short listed) እና ከፍት ጨረታ የማውጣት (Open Tendering)
መንገድ ናቸው።

▶️ድርድር (Negotiation የተባለው መንገድ ተግባራዊ የሚሆን አንድ ዮፕሮጀክት ባለቤት ግንባታውን ሊያከናውን ይችላል ተብሎ ከሚታመንበት አንድ ተቋራጭ ጋር የብቃት ድርድርን ተመርኩዞ የሚከናወን ውል አልያም ደግሞ ፕሮጀክቱን ተቋራጮች በአካባቢው የማይገኙ ከሆነ የሚመረጥ ነው ይህ መንገድ የሚስተዋል ሲሆን የግንባታው ባለቤት የሚያምንበትን አንድ ተቋራጭ
የተመረጡ ጥቂቶችን የመጋበዝ (Short listed) የሚባለው ደግሞ በተመረጡ ወይም በፕሮጀክቱ አይነት ላይ የቀደመ ልምድ ያላቸው ዝርጋታ፣ ግድብ እና ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ግንባታ ላይ ተግባራዊ

📍(ለምሳሌ፦ ደረጃ 1 እና ደረጃ 2 ጠቅላላ ተቋራጭ)፣ ወይም ላይ ልምድ ያላቸው፣ በባቡር ሐዲድ ሥራ ላይ ልምድ ተለይተው ሊጠሩ የሚችሉ ሲሆን ይህ የመለየት ሥራ የማውጣት (Open Tendering) የሚባለው የሚችል ጨረታ ነው።

✨የሚያደርገው የዋጋ እና ሊያከናውኑ የሚችል ብቁ ብዙ ጊዜ የግል ግንባታ ላይ
የሚደራደር ሲሆን ነው።

⏳አንድ ፕሮጀክት ሊከናወን የሚችለው
ሲሆን ነው። ብዙ ጊዜ የባቡር ሀዲድ
የሚደረግ ሲሆን ተቋራጮቹን በደረጃ
በፕሮጀክት አይነት (በትላላቅ ግድብ ግንባታ ያለው ...) አልያም እገሌ፣ እገሌ እና እገሌ በሚል Short listed መንገድ ይባላል።

⚡️ክፍት ጨረታ ማንኛውው የንግድ ፍቃድ ያለው አካል ሊሳተፍበት ደግሞ
Bount በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 3140 አካላት ውል እንዲዋዋሉ ፍቃድ የተሰጠ የሚገደዱ ናቸው ማለት ግን አይደለም።

✨መመስረት ያለባቸው በጨረታ 3141 ድንጋጌዎች መሰረት የመንግሥትም ይሁኑ የግል እና በጀት እንዲበጀት የተደነገገ ቢሆንም ወደውል እንዲገቡ ቢሆንም ግን የመንግሥት አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች ውል መነሻነት ስለመሆኑ በአዋጅ ዉጥር 649 የተደነገገ ነው።

⏺ይህ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001 ሥር በግልጽ ተመልክቷል ምክንያቱም አንድን
ፕሮጀክት ለማከናወን በቂ አቅም ያላቸው ሀገር በቀል እና ዓለማቀፍ ተቋራጮች
ባሉበት ሁኔታ የመንግሥትን ግንባታ ያለጨረታ መስጠት የማይቻል እና የመንግሥትን በጀት እንቅስቃሴ ኦዲት ለማድረግ ጨረታ ተመራጭ መንገድ ስለሆነ ነው።

▶️ጨረታው ብሔራዊ (National) ወይም ዓለምአቀፋዊ (international) ሊሆን ይችላል እንጂ ጨረታ ግድ ነው።
በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ብቁ ተቋርጮች እንደሌሉ ከተረጋገጠ እና ልዩ ፍላጎትና አቅም የሚጠይቅ ፕሮጀክት ከሆነ ግን እንደ ፕሮጀክቱ ጸባይ ሁሉም የሚመለከታቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ተወያይተው እና ወስነውበት መንግሥት ድርድር (Negotiation) መንገድን ተጠቅሞ በድርድር
ብቻ ውል ሊፈጽም የሚችልበት አግባብ ይኖራል።

📎በእርግጥ ጨረታ መውጣቱ የሂደቱን አግባብነት እንደማረጋገጫ አንድ መንገድ ይሆናል እንጂ በጨረታ ውድድር ተጫራች ስለተመረጠ እና አሸናፊነቱ ስለተገለጸ ብቻውን የግንባታ ውል እንደትፈጸመ አይቆጠርም።

#ConstructionLaw

@etconp
👍13
👉ተቀማጭነቱን በጀርመን ሙኒክ ከተማ ያደረገው የBMW ዋና መስሪያ ቤት ግዙፍ ሕንፃ ማራኪነቱና ቀልብ ሳቢነቱ ሁሉም የሚመሰክርለት ነው።

🚧ይህ የመኪና አምራች ኩባንያ ቢኤም ደብሊውን ብቻ ሳይሆን በቅንጦትነታቸው የሚታወቁትን ሮይልስ ሮይልን ጨምሮ የተለያዩ ብራንድ መኪናዎችን ያመርታል። የ2022 ዓ.ም በድምሩ 2,382,305 አውቶሞቢሎችን ለገበያ አቅርቦ 142 ቢሊዮን 610 ሚሊዮን ዮሮ ገቢ አግኝቶል።

🚧በዘጠኝ አገራት (በጀርመን ፣ ብራዚል፣ ቻይና፣ ሕንድ፣ ሜክሲኮ፣ ኔዘርላንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩናይትድ ስቴትስ) ውስጥ የሠራተኞቹ ብዛት 149,475 ይደርሳል።

🌟ቢኤም ደብሊው የ107 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ኩባንያ ነው።

@etconp
❤13👍3
የአክሱም ሃውልት ህልውናውን የማጣት ስጋት ዉስጥ መግባቱ ተነገረ

በአክሱም ከተማ የሚገኘው ጥንታዊውና ታሪካዊው የአክሱም ሃውልት ህልውናን የማጣት ስጋት ውስጥ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የቅርስ ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡

በባለስልጣኑ የቅርስ ጥበቃና ልማት ስራ አስፈጻሚ ከፍተኛ የቋሚ ቅርስ ባለሙያ አቶ አቶ አርከበ ነጋሽ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን እንደገለጹት  አለም አቀፋዊ  ቅርስ የሆነው የአክሱም ሃውልት በታቀደው ጊዜ ውስጥ ጥገና ሳይደረግለት በመቆየቱ ህልውናውን የማጣት ስጋት ውስጥ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ሀዉልቱን የማቃናት ፕሮግራም ተቀርፃ የነበረ ቢሆንም በትግራይ ክልል በኮቪድ ወረርሽን ምክንያት ለታሪካዊ ሃውልቱ በተገቢው ሰአት አስፈላጊውን ጥገና ማድረግ ባለመቻሉ ቅርሱን ለጉዳት እንዲጋለጥ አድርጎታል ብለዋል፡፡ሀውልቱ  በታቀደው ጊዜ ውስጥ ጥገና ሳይደረግለት በመቆየቱ የዉሀ ተፋስስ ችግር አጋጥሞታል ሲሉ አክለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ዉሀ በማዘሉ ይህ አለምአቀፍ ቅርስ ሙሉ ለሙሉ ሊጎዳ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ የጠቆሙት የቋሚ ቅርስ ባለሙያው ጉዳቱ በዚሁ ከቀጠለ ዘለቄታዊ እሴቱ ገላጭ እንዳይሆን ጭምር  ያደርገዋል  ሲሉ ተናግረዋል።ቅርሱን ለመታደግና ይዘቱን ጠብቆ ለማቆየት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለገንዘብ ሚኒስቴር የላከው ሰነድ መኖሩ ተገልጿል።

የአክሱም ሃውልት በአክሱም ከተማ የሚገኝ የዓለማችን ረጅሙ ትክል ድንጋይ ሃውልት ነው። ይህ ሀውልት 1700 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የ24 ሜትር ወይም 78 ጫማ ርዝመት አለው።

Via ዳጉ ጆርናል

@etconp
👍15😢2
👉አማራ ባንክ 10 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በሊዝ ዉል ተቀበለ

🚧አማራ ባንክ ለሚያስገነባዉ ዋና መስሪ ያቤት ህንፃ መስሪያ የ10,579 ካሬ ሜትር ከአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ተቀብሏል።

🌟ባንኩ በሊዝ ዉል የተፈረመው ይዞታዉ በልደታ ክ/ከተማ ሜክሲኮ አከባቢ ለሚያስገነባዉ ህንፃዉ መሆኑን አሳዉቋል።

@etconp
👍10❤4🏆1
🫵ውድ ቤተሰቦቻችን ይህንን ኬዝ እስቲ እንወያይበት

👉አንድ ፕሮጀክት በ625 የግንባታ ቀናት እና በ6,000,200.00 ብር ውል የታሰረበት ሲሆን  Liquidated damage  (0.1%) በውሉ የተካተተ ሲሆን የፕሮጀክቱን ዋጋ 10% እስኪደርስ ድረስ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ ምክንያታዊ ባልሆነ የተቋራጩ አፈጻጻም ችግር ምክንያት አሁን ባለበት ሁኔታ ከግንባታ መጀመሪያው ቀን ጀምሮ ሲቆጠር መጠናቀቅ ከነበረበት ቀን በላይ 149 ቀናትን ዘግይቷል።

🖱ጥያቄ፦ Liquidated damage ምን ያክል ብር ነው?

⏺የፕሮጀክቱ መዘግየት ግጭት በ 'Liquidated damage ብቻ ይፈታል ወይስ ሌላ መንገድ አለ?

📩መልሶቻቹ እና ሀሳቦቻቹ @COTMp ማለትም ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይፃፉልን👇

https://t.me/COTMp
👍11
#ADVERTISEMENTS

👉ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ

0904040477
0911016833 ደውለው ያግኙን

📩ወይም @heavenic1 ፃፉልን

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ ኮርቻ ተራ
                ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
                 ቁ.3 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት
                 ቁ.4 ቄራ ላይ በቅርቡ ይጠብቁን

🌟ከቃላችን ይልቅ ስራችን ይናገራል

🚧ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
👍2
👉የግንባታ ፕላን ፍቃድ ስለማቅረብ

⏺Submission of Application and Plans

🌟የኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ  ፮፻፳፬/፪ሺ፩ ክፍል ሁለት መሰረት “የግንባታ ሥራ ለማካሄድ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለከተማው አስተዳደር ወይም ለተሰየመው  አካል ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርበታል።

▶️ሕንፃን ለመገንባት የሚቀርብ ማመልከቻ የከተማው አስተዳደር ወይም የተሰየመው አካል ለዚሁ ብሎ ባዘጋጀው ቅፅ መሠረት ሆኖ ይህም  እንደ ሕንፃው ምድብ አይነት ዲዛይንና ሪፖርት የያዘ መሆን አለበት።

▶️ከማመልከቻው ጋር በአዋሳኝ ባሉ ስፍራዎች የሚገኙ ዋና መንገዶችንና የታወቁ ቦታዎችን ስም የሚገልፁ መረጃዎች መቅረብ ይኖርባቸዋል። አመልካቹ ሕንፃ በሚገነባበት ቦታ ወይም በንብረቱ ላይ የይዞታ መብት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል

▶️የሚቀርቡት ሠነዶች በዚህ አዋጅና በሌሎች ሕጐች የተመለከቱት መሟላታቸውን ለማረጋገጥ በበቂ ሁኔታ የተሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል”

🖱According to Proclamation No. 624/2009 “Any person intending to carry out construction shall submit an application to the urban administration or designated organ. The application to carry out construction shall be made on an application form prepared by the urban administration or designated organ and shall consist of a design and report according to the category of building in question.

⏺The application shall be accompanied with a reference to main roads and names of prominent places. The applicant shall submit proof of possession rights to the land or property on which the construction will take place. The documents to be submitted shall be sufficiently complete to determine compliance with this Proclamation and other laws”

#ConstructionLaw

🫵አዳዲስ የ ስራ ቅጥር ማስታወቅያዎች እና የ ኮንስትራክሽን ጨረታዎች በ ትኩሱ እንዲደርስዎ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://t.me/ETCONpWORK
👍15❤3
👉የግንባታ ተቋራጭ ስለመሆን

🚧Procedure for Contractors
———————
🌟በሀገራችን የግንባታ ሥራ ተቋራጭ ምዝገባ ሂደት ውስጥ ሁለት አይነት ምድብ ይሰጣል።

▶️የሀገር ውስጥ (ሀገር በቀል) ተቋራጮች እና የውጪ ሀገር (ከውጪ ሀገራት የመጡ) የግንባታ ተቋራጮች ሲሆኑ በሀገሪቱ የግንባታ ሥራ ተቋራጭነት ለመሳተፍ የሚያስችላቸው የሚከተለው መስፈርት ነው።
.....
🖱A. የሀገር ውስጥ ተቋራጮች – local contractors

⏺የአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮች በመስፈርቱ መሠረት ማሟላት በሚችሉት ደረጃ ለመመዝገብ፦ ለበጀት ዓመቱ የታደሰ የአገልግሎት ንግድ ፈቃድ፣ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት፣ የተሽከርካሪዎችና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር፤ ፎርም መሙላት /ፎርሙ በተቋራጩ ወይም በወኪሉ ሊሞላ ይችላል። ፎርሙ በወኪሉ ከተሞላ የውክልናውን ደብዳቤ አብሮ መያያዝ አለበት/፣ የአገልግሎት ክፍያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። በድርጅታቸው ሠራተኛነት የሚቀጥሯቸው ባለሙያዎቻቸው ደግሞ፦ ከሥራና ከተማ ልማት የተሰጣቸውን የታደሰ የባለሙያ ሠርተፊኬት፣ ባለሙያው ቀድሞ ሲሠራበት ከነበረው ድርጅት የተሰጠው የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ እና በማኀበራዊና ሲቪል ጉዳይ ፎርማት መሠረት የተዘጋጀ ባለሙያ የቅጥር ውል ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተሽከርካሪ እና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን በተመለከተ፦ ለዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር እና ሚክሰርና የእጅ መጠቅጠቂያ መሣሪያዎች የተገዙበት ደረሰኝ ያስፈልጋቸዋል።

📍All local contractors shall be registered in any type of construction befitting their category but must fulfill; Renewed business license for the fiscal year, Value Added Tax (VAT) registration certificate, title certificate for vehicles & construction equipments, the application forms for registration (it shall be filled and signed by the contractor or his agent.  When the application is made by the agent, photocopy of the letter that states his/her power of attorney shall be submitted) and Service charge. In the side of Manpower Requirement; their original and valid professional certificates given by MWUD, a release from their former employer and the employment agreement between the employer (contractor) and employee (professional) in accordance with the Ministry of Labour and Social Affairs format. For the Vehicle & Equipment; Renewed and valid title certificate of vehicles and heavy-duty construction equipment and purchasing receipt for mixer and hand compactor shall to be submit.

🫵አዳዲስ የ ስራ ቅጥር ማስታወቅያዎች እና የ ኮንስትራክሽን ጨረታዎች በ ትኩሱ እንዲደርስዎ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://t.me/ETCONpWORK
👍16❤10
👉Buildings in addis ababa
2023

🌟Have a nice night🙏

@etconp
❤9👌4👍2👏2🔥1😢1
👉Ethiopian Construction Law

🌟A proposal for a new procedural architecture suitable for Ethiopian construction conflicts.

▶️Many legal systems are adopting a new way to facilitate the resolution of construction-related disputes. Adjudication is the name given to this new procedure.

⏺Adjudication in the context of construction contracts refers to the process of settling disputes or disagreements that may emerge between the contract's parties.

⏺It is a type of alternative dispute resolution (ADR) intended exclusively for the construction sector.

⏺Adjudication often entails choosing an adjudicator, who evaluates the disagreement and renders a binding judgement on problems like as payment, modifications, delays, faults, or other contractual difficulties.
The adjudicator's decision is enforceable and temporary, which means that it gives a speedy settlement to the disagreement, allowing the construction project to move forward while the parties work towards a final resolution, such as arbitration or litigation.
This form of conflict settlement has numerous advantages for the construction industry. It ensures, among other things, a quick and efficient conclusion since it is designed to deliver a quick decision, allowing the parties to move forward with the project and minimise delays. It is also more cost effective because the design makes it less formal, which results in fewer legal and administrative costs for the parties involved. It also allows for experts and specialised adjudicators who can make well-informed rulings.

🖱Although adjudication rulings are often interim, providing temporary answers to contentious issues until final resolution through other procedures such as discussion or arbitration, they are legally binding and enforceable.

⏺Adjudication is an effective method of resolving construction conflicts. However, it requires an efficient domestic legislative framework that defines the legal basis and procedures for construction dispute arbitration.

⏺The scope of conflicts that can be adjudicated, the nomination process for adjudicators, timetables for resolution, and the enforcement of adjudication rulings should all be outlined in this legal framework. Without such a foundation, adjudication would be a paper tiger.

⏺Adjudication is frequently discussed as a technique of resolving disputes in Ethiopian building contracts. The legal structure However, Ethiopia lacks the requisite legal support for adjudication. There are no legal rules that assure the enforceability of adjudicator rulings. As a result, unlike arbitral judgements, adjudicator rulings cannot be directly enforced by ordinary courts. Thus, until such legal flaws are addressed, Ethiopia will be unable to reap the full benefits of adjudication.

⏺We must investigate strategies to strengthen Ethiopia's adjudication base by lobbying for a new procedural design fit for building contracts.

#ConstructionLaw

@etconp
👍14❤3