Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
For the purpose of the design of
reinforced concrete footings, pressure
distribution is assumed to be
Anonymous Quiz
32%
A: Parabolic
46%
B: Linear
14%
C: Hyperbolic
7%
D: None of the above
👏12🕊4❤3👍2
______ failure is a mode of failure in a
very deep footing in loose sand.
Anonymous Quiz
51%
A: Punching shear
14%
B: General shear
15%
C: Local shear
20%
D: Buckling
👍19
The corresponding lateral earth pressure
when the retaining wall moves towards backfill
is known as
Anonymous Quiz
52%
A: Passive Earth Pressure
35%
B: Active Earth Pressure
10%
C: Earth Pressure at rest
3%
D: None of the above
👍24😢4🙏4
👉ስለ “Specification” ሰነድ

☄በ'FIDIC multilateral Development Bank Harmonized edition 2010  ሕግ መሰረት “Specification” የተባለ ሰነድ በግንባታ ውል ውስጥ መካተት እንዳለበት ግልጽ ነው።

▶️ስለ ሰነዱ ምንንነት “Specification” means the document entitled specification, as included in the Contract, and any additions and modifications to the specification in accordance with the Contract. Such document specifies the Works ይላል።

⏺ነገር ግን በሀገራችን አብዛኞቹ የግንባታ ውሎች (contract documents) ውስጥ የሚገኝ አይደለም።

⏺ስለእያንዳንዱ ሥራ ዝርዝር፣ ስለሚጠቀሙት የግንባታ ግብአት ዝርዝር ማብራሪያ (የምርት አይነት፣ ልኬት፣ መጠን፣ ጥራት)፣ ስለሚያስፈልገው የሰው እና የማሺነሪ ዝርዝር የሚያስረዳ የውል ሰነድ አካል ነው።

⏺ይህ ሰነድ በብዙዎቹ ውሎች ውስጥ የተለመደ አለመሆኑ የግብአት (Material) ጥራት ጥያቄ፣ የጊዜ መጓተት ቅሬታ እና የተጨማሪ ዋጋ ክርክር አያስነሳ ይገኛል።

🖱እርስዎ በሚሰሩበት ድርጅት “Specification” የሚባለውን ሰነድ አዘጋጅተው ወይም ተጠቅመው ያውቃሉ?

🌟የ ኮንስትራክሽን ጨረታዎች እን ስራ ቅጥሮቹ በትኩሱ እንዲደርስዎ ከፈለጉ ከታቻ ያለው ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/ETCONpWORK

📩ሊያገኙን ካሰቡ በ @ETCONpBOT ላይ መልእክት ይላኩልን።
👍12🙏3
👉የ ዛሬ ጥያቄ ደሞ...

🌟የ Negative reinforcement bar (ፌሮ ብረት) ጥቅም ምንድነው?

▶️የትኛው የስትራክቸር ክፍል ላይ እንጠቀማለን?

📩መልሶቻቹ Discusion Group ላይ ወይም @COTMp ተጭነው ይፃፉልን!

@etconp
👍7
👉4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበት እየተገነባ ነው የሚገኘው የተባለው የዓድዋ ዜሮዜሮ ፕሮጀክት #ወደመጠናቀቁ መሆኑ ተነግሯል።

ፕሮጀክቱ በውስጡ ፦
- በዓድዋ ጦርነት የተሰዉ ጀግኖችን የሚዘክር ሙዚየም፣
- የመዝናኛ ሥራዎች፣
- ካፍቴሪያዎች፣
- ሲኒማ ቤቶችና ሁለገብ አዳራሾችን
- የህፃናት መጫወቻ
- አንድ ሺህ (1000) መኪና ማቆም የሚያስችል ፖርኪንግ
- የንግድ ቤቶችን  የያዘ ነው ተብሏል።

🌟የዓድዋ ድል የተበሰረበት ነጋሪት በሙዚየሙ ውስጥ የተቀመጠ ሲሆን #የአጼ_ምኒልክ እና #እቴጌ_ጣይቱን የሚዘክር ሃውልትም ይቀመጣል ተብሏል።

🚧በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል የተባለው ይኸው ፕሮጀክት የተወሰኑ ሥራዎች ብቻ እንደቀሩት ተገልጿል። በ45 ቀናት ውስጥም ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል ተብሏል።

Credit - AMC & EPA

@etconp
👍11🏆3😢1
👉ሰኔጋላዊው እግር ኳስ ተጫዋች ሳዲዮ ማኔ በትውልድ ከተማ ባምባሊ አዲስ ስታድየም አስገንብቶ አስመርቋል

🌟ስታዲየሙ 1,000 ተመልካች የሚይዝ ነው ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

🚧የቀድሞ የሊቨርፑል ተጫዋች ከዚህ ቀደም ሆስፒታል እና ት/ ቤት አስገንብቶ ለህዝብ አስረክቧል።

🖱የ 31 አመቱ ማኔ በለጋስነቱ የሚደነቅ በሀገሩ ህዝብ በጣም የሚወደድ ተጫዋች ነው።

Via Fidel Post

@etconp
❤24👍9👏2
👉በሊዝ የተያዘ መሬት ላይ ግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ

🚧ሀ) ግንባታ ማስጀመሪያ

▶️አንድ ግለሰብ/ድርጅጥ በከተማ ቦታ ላይ በሊዝ የተረከበው ቦታ ላይ የሊዝ ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ለቦታው በተቀመጠው ደረጃ መረሰት ግንባታ እንዳለበት የሚደነግግ የጊዜ ጣሪያ ተቀምጧል።

⏺በሊዝ ቦታ ላይ የግንባታ መጀመሪያ የጊዜ ጣሪያ፦ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች = 6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች = 9 ወር፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች = 18 ወር ነው። ሆኖም ግን እስንደአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች በተጠቀሱት የጊዜ ገደቦች ግንባታ ሳይጀመር ቢቀር ለአንድ ዙር ብቻ የሚፈቀድ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች  6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 9 ወር፣ ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች አንድ ዓመት ተጨማሪ የግንባታ ማስጀመሪያ ጊዜ በግንባታ ፍቃድ ሰጪው አካል ከማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጋር ሊሰጣቸው ይችላል።

🚧ለ) ግንባታ ማጠናቀቂያ

▶️በሊዝ ቦታ ላይ ግንባታ የማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ፦ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች 24 ወራት፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 36 ወራት፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች  48 ወራት ነው።

⏺ነገር ግን የአካባቢው የግንባታ ፍቃድ ሰጪ አካል ካመነበት የግንባታውን ውስብስብነት እያየ ሊያራዝምለት ይችላል።

⏺ሆኖም ግን ለግንባታ ማጠናቀቂያ የሚሰጠው ጊዜ በማንኛውም ምክንያት (ሁኔታ) ቢሆን ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች  2 ዓመት 6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 4 ዓምት፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች ከአምስት ዓመት መብለጥ የለበትም።

@etconp
👍10
👉ከግንባታ ህጎች አንጻር እንዴት ያዩታል?
(ቅሬታ የተፈጠረበት እውነተኛ Case )

🚧አንድ የመንግሥት ተቋም ሕንፃ ለማስገንባት ከተቋራጩ ጋር ውል ተፈራረመ።

ተቋራጩ ሥራውን ከጀመረ በኋላ በተሰጠው ዲዛይን (Drawing) መሰረት ልኬት እየፈጸመ የአሠሪው ተቋም አማካሪ መሐንዲስ (Engineer) እያጸደቀለት ቢሠራም በእውነተኛው ሥራው ላይ ያለው የተመዘገበው የሥራ መጠን (Actual Quantity of activities) በውል ሰነዱ ላይ ከተፈራረሙበት የሥራ መጠን (with the quantities specified in the BOQ of contract document) በ49 በመቶ (49%) ጭማሪ ተገኘበት።

በዚህ መካከል ተቋራጩ በእውነተኛው የሥራ መጠን ተባዝቶ ክፍያ እንዲፈጸምለት ጠየቀ። አሰሪው መሥሪያ ቤት ተጨማሪ የመጣበትን ጉዳይ በውል ስምምነቱ ሰነድ ላይ ከተገለጸው በላይ ስለሆነ ክፍያ አልፈጽምም ብሎ የግንባታ ሂደቱ እንዲቆም ትዕዛዝ ሰጠ። ይህ የክፍያ ጉዳይ፦

⏺ #1ኛ ከግንባታ ህግ አንጻር ተገቢነት ያለው ማንኛው ወገን ነው?

⏺#2ኛ ጥፋት ያለበት ባለድርሻ አካል ማነው? ምን አይነት ጥፋት?

📩መልሱን በዚሁ ገጽ እንለቃቀን ከዚያ በፊት ግን ሁላችንም ምላሽ በመስጠት ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪያችን ዕድገት እውቀት እየተጋራን አስተዋጽኦ እንክፈል።

🖱መልሶቻቹ ከታች ባለው Discussion Group ፃፉልን👇

https://t.me/COTMp
👍16❤4
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን

፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን

፦ankerbolt

፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

አድራሻችን
ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706 ወይም @heavenic1 ፃፉልን

ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።
👍2
👉የአሸዋ ደለል መጠን (Silt Content)

☄በአርማታ (concrete)፣ ልስን (plastering)፣ ወለል ጭረሳ (floor screed) እና የአሸዋ ግርፍ (rendering) ሥራዎች በብዛት የምንጠቀምባቸው ሦስት የግንባታ ግብአቶች ሲሚንቶ፣ አሸዋ እና ጠጠር (Cement, Sand/Fine aggregate & Coarse Aggregate) ናቸው።

☄ሲሚንቶ ዋናው ዓላማው የግንባታ ግብአቶች እስር በእርሳቸው ያላቸውን የመጣበቅ/የመጣመር ሂደት ማጠናከር (As binding agent) ሲሆን የአሸዋ ድርሻ የውስጥ ለውስጥ (air voids) መሙላትና ማእከላዊ የሆነ ማጣበቅና ጥንካሬ መስጠትን ማገዝ ነው።

☄የጠጠር ዋናው ድርሻ ደግሞ የኮንክሬት ክፍሎችን ጥንካሬ መስጠት ነው። 

🖱አሸዋ (Fine aggregate) ማእከላዊ ወሳኝ ግብአት ተብሎም ይታወቃል። በትላልቅ አውሮፓውያን እና በሩቅ ምስራቅ ሀገራት በተለይ በህንድ እና በቻይና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው እና እንደሲሚንቶ የአሸዋ ማጣሪያ ፋብሪካ ጭምር የተገነባለት ግብአት (material) ነው። ይህ ሆኖ ሳለ የአሽዋ መሰረታዊ የቤተሙከራ  ማረጋገጫ ምዘናዎች ውስጥ ቀላሉ ነገር ግን ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የደለል ይዘቱ (silt content) ነው። /ደለል ማለት በጣም የላመ ወይም የደቀቀ ዱቂታማ የአፈር አይነት ነው/። አሸዋ በተቻለ መጠን ምንም የደለል ይዘት አንዳይኖረው ይመከራል። ደለላማ የአፈር መጠን በአሸዋ ውስጥ በብዛት ካለበት አሸዋው ጥቅም ላይ ሲውል የአርማታ ባህርይን ወደ ጭቃማ ጸባይ ይቀይራል ማለት ነው። ደለላማ የአፈር ክፍል አሸዋው ማንኛውንም የቤተሙከራ መስፈርት (laboratory tests) በብቃት እንዳያልፍ ያደርገዋል። አርማታ ጥንካሬ እንዳይኖረው እና ልስን በቀላሉ እንዲፈራርስ የሚያደግ ነው።

✨ደቃቅ አፈር/ደለል (silt content) የሚባለው እንደ ፕሮጀክቱ አይነት ልዩ ሀሳቦች የሚነሱበት ቢሆንም በ'ASTM, AASHTO, IS እና በሌሎች መመሪያዎች ላይ እንደተጠቆመው በብዛት ከ75 micro-millimeter sieve በታች የሚወርደውን ክፍል ነው።

✨በመሆኑም አሸዋ በውስጡ ከስድስት በመቶ (6%) በላይ ደለላማ አፈር (silt content) እንዲኖረው አይፈቀድም። በግንባታ ቤተሙከራዊ የግብአት መስፈርቶች (Experimental criterion) መሰረት አሸዋ ከ6% በላይ ደቃቅ አፈር አንዳለበት ከታወቀ ሁለት አይነት ርምጃ ይወሰዳል።

⏺አንደኛው:- አሸዋውን በአሸዋ ወንፊት መንፋት (sieving) ሲሆን (ሁለተኛው) አሸዋውን አስወግዶ (rejection) ሌላ መስፈርቱን የሚያሟላ አሸዋ መጠቀም ነው።

🌟በብዙ የሀገራችን የግንባታ ቦታዎች ላይ አሸዋ በቁም ወይም በአግዳሚ ወንፊት ሲነፋ የሚስተዋለው ይህንን የደለል መጠን ለመቀነስ እና ከአሸዋ ቅርጽ መጠን በላይ (Above determined sieve size of sand) የሆነ ጠጠራማ ክፍልን (aggregated particles) ለመለየት ነው።

📍የ ኮንስትራክሽን ጨረታዎች እና ቅጥር በ ትኩሱ እንዲደርሶ ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል

t.me/ETCONpWORK

🖱ፌስቡክ https://www.facebook.com/etconp/

📩ሊያወሩን ካሰቡ በቴሌግራም @ETCONpBOT ይጻፉልን።

@etconp
👍11❤10👌1
"እነሆ÷ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀን ተወልዶላችኋል፤ ይኸውም ቡሩክ ጌታ ክርስቶስ ነው።" ሉቃ ፪÷፲፩

ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

መልካም በዓል!

@etconp
🙏18👍11❤6👏1