Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የወንጪ - ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር ዛሬ ይመረቃል

🌟በ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" መርሃ ግብር ከተገነቡት መዳረሻዎች ሶስተኛው የወንጪ - ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር ዛሬ እንደሚመረቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

@etconp
❤12👍4
👉የፎርምወርክ ማፍረሻ ቀነ ገደብ

🚧በቀድሞው የሀገራችን የሕንጻ እና መንገድ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ባለሥልጣን (Building and Transport Construction Design Aucthority – BaTCoDA Specification) ላይ በቁጥር 03244  ላይ እንደተመለከተው  ፎርምወርክ የሚነሳበት (የሚነቀልበት/የሚፈርስበት) ቀንን (Formwork Removal) በተመለተ እንደሚከተለው አስቀምጧል።

⏺አቀባዊ የአርማታ ግድግዳዎች ( shear wall)፣ አምዶች (columns) እና aግዳሚ ጋንዴላዎች ወይም ምሰሶዎች (beams) = ከ16 ሰዓታት በኋላ

⏺የወለል አርማታ ሙሌት የታችኛው አልጋ (slab soffit) = በ21 ቀናት ውስጥ

⏺የወለል አርማታ የጎንዮሽ ማፈኛ (props of slab) = በ14 ቀናት

⏺የአግዳሚ ጋንዴላ/ምሰሶ የታችኛው አልጋ (soffit of beam) = 21 ቀናት

⏺የአግዳሚ ጋንዴላ/ምሰሶ የጎንዮሽ ማፈኛ (Props of beam) = 14 ቀናት

🖱ማሳሰቢያ፦ ለተዘረዘሩት የአርማታ ስትራክቸር ክፍሎች (Concrete skeletons) የተጠቀሱት ቀናት "ቢያንስ ቢያንስ" ተብሎ የተቀመጠ ዝቅተኛው የጊዜ ገደብ ነው።

@etconp
👍15❤9
👉በ600 ሚሊየን ብር የተገነባው የሰንጋተራ ህንፃ ተመረቀ

🚧የሰንጋተራ ነጋዴዎች ህብረት አክሲዮን ያስገነባው ህንፃ በዛሬው እለት የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት አካላትና እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

🌟የሰንጋተራ ነጋዴዎች ህብረት አክሲዮን ማህበር በ1995 ዓ.ም በ71 አባላት የተመሰረተ ሲሆን ማህበሩም አዲስ አበባ ሰንጋተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ በ600 ሚሊየን ብር ያስገነባውን ባለ 23 ወለል ትልቅ የገበያ ማዕከል ገንብቶ ስራ በማስጀመር በዛሬው እለትም የህንፃውን ምረቃ መርሃግብር አካሄዷል።

🖱አጠቃላይ ለህንፃው የተሰጠው ቦታ 3 ሺ 500 ካሬ ሜትር ሲሆን ህንፃው ያረፈበት 2 ሺ 800 ካሬ ላይ መሆኑ ተገልጿል

🖱ህንፃው 5 ባንኮችን ፣ የብሄራዊ ቲያትር ጽ/ቤት ፣ ፐርፐዝ ብላክ ከፍተኛ ቢሮዎች ፣ የህንፃ መሳሪያዎች ፣ የኤኬክትሪክ እቃዎች መሸጫ ፣ የጥርስ ህክምና ፣ የእርዳታ ድርጅቶች ፣ የግል ሰራተኞች ጽ/ቤት ፣ የምግብ አዳራሽ ካፌ አገልግሎትና የመሰብሰቢያ አዳራሾችን በውስጡ ይዟል።

⏺በቅርቡም የጂም አገልግሎት በቅርብ የሚከፈት ሲሆን ከ3000 በላይ ለሆኑ ሰራተኞች የስራ እድል መፍጠሩም ተገልጿል።

⏺እንዲሁም ህንፃው 2 ቤዝመንት የፓርኪንግ አገልግሎት እንደሚሰጥም ተነግሯል።

Via ድሬቲዩብ

@etconp
👍16❤2
👉ጥናት

🌟በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ጥራታቸው ተጠብቆ ባለመገንባታቸው፣ በዕጣ የቤት ባለቤት የሆኑ ዕድለኞች ለከፍተኛ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን የአፍሪካ ከተሞች የምርምር ጥምረት (ACRC) እና ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) በጋራ ባደረጉት ጥናት ማረጋገጥ መቻላቸውን አስታውቀዋል።

ሁለቱ ተቋማት ጥናቱን ለአንድ ዓመት ያህል ነው ያደረጉት።

በጥናቱ ከ6 በላይ ከፍተኛ ተመራማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በኢኮኖሚ፣ በመዋቅራዊ ሽግግርና በወጣቶች አቅም ግንባታና በመኖሪያ ቤቶች ላይ የተደረገ ነው።

ጥናቱ ምን ይላል ?

- በአዲስ አበባ ከተማ ከመነሻውም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ አይደሉም፡፡

- መንግሥት 40/60 ወይም የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በዕጣ ለደረሳቸው ሲያቀርብ ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ስለማይገነቡ፣ ዕድለኞች መልሰው አፍርሶ ለመሥራት ይገደዳሉ ለከፍተኛ ወጪ ይዳረጋሉ።

- የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸው ዕድለኞች

* ለኤሌክትሪክ ኃይል ዝርጋታ፣
* የሲራሚክ ንጣፍ፣
* ለመፀዳጃ ቤት መስመር፣
* ግድግዳ እንደገና ለመሥራትና ሌሎች የጎደሉ ነገሮች ለማሟላት ለከፍተኛ ወጪ ይዳረጋሉ።

- እነዚህ ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልጉ በመሆናቸው፣ መንግሥት ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከግብዓት ጀምሮ እስከ ባለሙያ ድረስ ጥራታቸውን በመጠበቅ ማቅረብ ይኖርበታል።

በተጨማሪ ...

* በአዲስ አበባ ከተማ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ለሥራ ተስማሚ የሆኑ ነገሮች እንደሌላቸው ታይቷል። ወጣቶች በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ፣ በኢመደበኛ ዘርፍና በጤና ላይ ያላቸውን በጎ ተግባራትና ያሉባቸው ችግሮች ተለይተው በጥናቱ ተካተዋል።

* በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት አብዛኛውን የቤት አቅርቦት ተፈጻሚ የሚሆነው በመንግሥት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ቤት አልሚ ድርጅቶች ተቋቁመው የማኅበረሰቡን የቤት ጥያቄ እየመለሱ መሆናቸው የሚበረታታ ነው።

* በቤት አቅርቦት ላይ ለውጦች እየመጡ ቢሆንም አሁንም የመሬት አቅርቦት፣ እንዲሁም በዝቅተኛና በመካከለኛ ገቢ ላይ የሚገኙ ሰዎች ቤት ለመሥራት ቢፈልጉ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር እየገጠማቸው ነው።

በአጠቃላይ ጥናት የተደረገባቸው ጉዳዮች ላይ ያሉትን ችግሮች ለመፍታትና በጥናቱ የቀረቡ ግኝቶች መሬት ወርደው ተግባራዊ እንዲሆኑ፣ ለፖሊሲ አውጪዎች የሚቀርቡ ይቀርባሉ ተብሏል።

Via ሪፖርተር

@etconp
👍11
👉 NEW VACANCY

🖱ሲቪል መሐንዲስ

☄ከ 0 - 6 ዓመት የ ስራ ልምድ

🌟የ መከላከያ መሐንዲስ ዋና መምርያ

@ETCONpWORK‌‌
👍5🙏3❤1
👉Scholarship Web site Tip

🔺Mastercard Foundation Scholars Program at the University of Oxford

🌟The University of Oxford and the Mastercard Foundation have an innovative and ambitious partnership under the Mastercard Foundation Scholars Program and the Africa Oxford Initiative (AfOx). The partnership is set to provide 400 young African scholars with a fully-funded opportunity to pursue taught Masters degrees in programmes related to pandemic preparedness and recovery at the University of Oxford.  

Official Link: https://www.afox.ox.ac.uk/mastercard-foundation-scholars-program-university-oxford

@etconp
👍7
👉የለገሃር ፕሮጀክት አካል የሆነዉና በ30 ሺህ ካሬሜትር ላይ እየተገነባ የሚገኘዉ ግዙፉ ህንፃ በ2026 ይጠናቀቃል

🌟የለገሃር ፕሮጀክት የሆነዉና በ 30,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈዉ የአፓርትመንትና የሾፒንግ ሞል ኮምፕሌክስ በ 2026 ተጠናቆ ለባለቤቶቹ እንደሚረከብ ኤግል ሂልስ አስታወቀ ።

የኢትዮጵያ መንግስት 27 በመቶ ድርሻ ኃብት እንደሚኖረውና በአዲስ አበባ ለገሃር አከባቢ በሚገነባው የተቀናጀ የመኖሪያ ቤት ግንባታ በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተነግሯል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እኤአ በ 2018 የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት ከ 5 እስከ 7 ዓመት ድረስ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ መግለፃቸው ይታወቃል።

መቀመጫውን አቡዳቢ ያደረገው ኤግል ሂልስ ኩባንያ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከል በሽርክና እየተሰራ የሚገኘዉ ልማቱ 50 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

በሪል ስቴት ልማት ግንባር ቀደም እንደሆነ የሚነገረዉ ኤግል ሂልስ የለገሃር ሞል መኖሪያ ቤቶች ሽያጭ መጀመሩን አሳዉቋል። ከቻይና ኮሙዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ ሊሚትድ (ሲሲሲሲ) ጋር ለአራቱም ህንፃዎች ግንባታ መያዙ ካፒታል ሰምቷል።

Via ካፒታል

@etconp
👍10👌2
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በማመከር ስራ አብሮ ለመስራት ተስማሙ
ጥር፡2016 ዓ̇.ም
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር የማማከር ስራዎችን ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ ።
ስምምነቱ የሚያተኩረው በግንባታ እና በህንፃ ኢንደስትሪ ውስጥ የሚታዩ የስንጥቅ ችግሮችን መፍትሄ የሚሰጡ ባዮ-ፊለር እና ባዮግሮውትን ምርቶችን በማምረት ላይ ነው። የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንደስትሪውን ለማሳደግ በተደረገው የቴክኖሎጂ ፕሮፖዛል ጥሪ መሰረት በማድረግ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በዋና ተመራማሪ በዶ/ር መስፍን ታፈሰ መሪነት የተሳካ ፕሮፖዛል በማቅረብ የማማከር ስራውን ለመስራት አሸናፊ ሆኗል፡፡
በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ሽግግር የማማከር ውልን በ2,647,875 የኢትዮጵያ ብር በመዋዋል ስምምነቱን የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሀም ደበበ እና የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ ተፈራርመዋል።
ዶ/ር አብርሀም ደበበ ስምምነቱ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ያሉ ወሳኝ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል ትልቅ ስራ እንደሚሆን ገልፀዋልፀዋል። ይህ ትብብር የዩኒቨርሲቲውን አቅም ከከማሳየት ባለፈ የሁለቱም ተቋማት በኮንስትራክሽን ዘርፍ አወንታዊ ለውጦችን ለማምጣት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ ነው።
👍7😁2
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን

፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን

፦ankerbolt

፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

አድራሻችን
ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706 ወይም @heavenic1 ፃፉልን

ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።
👍4
👉አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በማመከር ስራ አብሮ ለመስራት ተስማሙ

🌟የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር የማማከር ስራዎችን ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ የሚያተኩረው በግንባታ እና በህንፃ ኢንደስትሪ ውስጥ የሚታዩ የስንጥቅ ችግሮችን መፍትሄ የሚሰጡ ባዮ-ፊለር እና ባዮግሮውትን ምርቶችን በማምረት ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንደስትሪውን ለማሳደግ በተደረገው የቴክኖሎጂ ፕሮፖዛል ጥሪ መሰረት በማድረግ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በዋና ተመራማሪ በዶ/ር መስፍን ታፈሰ መሪነት የተሳካ ፕሮፖዛል በማቅረብ የማማከር ስራውን ለመስራት አሸናፊ ሆኗል፡፡

በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ሽግግር የማማከር ውልን በ2,647,875 የኢትዮጵያ ብር በመዋዋል ስምምነቱን የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሀም ደበበ እና የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ ተፈራርመዋል።

ዶ/ር አብርሀም ደበበ ስምምነቱ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ያሉ ወሳኝ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል ትልቅ ስራ እንደሚሆን ገልፀዋልፀዋል።

ይህ ትብብር የዩኒቨርሲቲውን አቅም ከከማሳየት ባለፈ የሁለቱም ተቋማት በኮንስትራክሽን ዘርፍ አወንታዊ ለውጦችን ለማምጣት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ ነው።

@etconp
👍15🙏1
👉ከኮንስትራክሽን ዋስትና አፈጻጸም ወቅት በተግባር የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች

✳️በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዲስትሪ ገና ዳዴ እያለ ያለ የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው፡፡ ሆኖም ግን ዘርፋ ከጠቅላላው የአገር ውስጥ ምርት (Gross Domestic Product) ያለው ድርሻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው፡፡

✳️ዳሩ ግን በዘርፋ የሚታዩ በርካታ ተግዳሮቶች አሉ፡፡ ከእነዚህ ችግሮችም ከኮንስትራክሽን ዋስትና ጋር የተያያዙም ይገኙበታል፡፡ ለምሳሌ፡-በመንግስት የጋራ ቤቶች ግንባታ የዋናው ገንዘብ መያዣ (retention) የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቆ የጊዜያዊ እና የመጨረሻ ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ የተያዘው 5(አምስት) ፐርሰንት ገንዘብ አብዛኛውን ጊዜ ተመላሽ አይሆንም፡፡

✳️ሌላው በኢትዮጵያ አብዛኛው የግንባታ ውሎች የመንግስት ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች ከግዥ እና ውል አስተዳደር ያለው ከፍተኛ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ከላይ የተባሉትን የዋስትና መንገዶች በአግባቡ እንዳይተገብሩ የሚያደርግበት ሁኔታ አለ፡፡

✳️ሌላው ድግሞ በፍ/ቤቶች ዘንድ የሚታዩ የአተረጓጎም ክፍተቶች ናቸው፡፡ ወሰኑ ያለየለት የኮንስትራክሽን ዋስትና በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው፡፡ ለምሳሌ፡-በአንድ የኮንስትራክሽን ፕሮጅክት አፈጻጸም የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትናን በተመለከተ በንግድ ሕግ ወይስ በፍትሐብሔር ሕግ ይገዛ የሚለው ነጥብ ነው፡፡ በተለይም የመድን ድርጅቶች ከሚሰጧቸው ዋስትናዎች ጋር ተያይዞ የሚነሳ ክርክር ነው፡፡ ይህም የሚሆነው በመድን ድርጅት የወጣ ቦንድን እንደ የመድን ሥራ አድርጎ የመቁጠር አዝማሚያ አለ፡፡

✳️በእርግጥ በአሁኑ ጊዜ የመድን ድርጅቶች ያለቅድመ ሁኔታ ዋስትናዎችን ጨምሮ የገንዘብ እዳ ማስከበሪያ ቦንድ ከማውጣት ቢከለከሉም በቅድመ ሁኔታ የተመሰረቱ ቦንዶች ማውጣት ይችላሉ፡፡ ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ የሰው ዋስትናም ሆነ የመድን ውል ሁለቱም የካሳ ውሎች (contract of indemnity) ናቸው፡፡ እንዲሁም ምንጫቸው ከተለየ ልዩነታቸውን ማቋቋም የሚከብድ አይደልም::

🖱የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና አብዛኛውን ጊዜ በችሮታ (gratuitous) ሊቋቋም ይችላል፡፡ በፋይናንስ ተቋማት በሚዘጋጅበት ጊዜ ድግሞ በክፍያ (consideration) ይሆናል፡፡ በዚህ ሳቢያ ለተባለው የፍይናንስ ተቋም ኮሚሽን ሊከፍል ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ተፈጻሚ ሊሆን የሚችለው የሕግ ማዕቀፍ የፍትሐብሔር ሕግ ከአንቀጽ 1920-1951 ያለው ነው፡፡ በእርግጥ የፍትሐብሔር ሕጉ ድንጋጌዎች በፍይናንስ ተቋማት በሚሰጡ ዋስትናዎች ላይ ሙሉ በሙሉ ባይፈጸምም የግዴታውን ሁኔታ ይገዛል፡፡

✳️በአንጻሩ ግን የመድን ግዴታ ቀዳማዊ እንጂ ደባል አይደለም፡፡ ተራ የውል ጥሰትም የመድን ውል ተፈጻሚ ሊያደርግ አይችልም ለምን ቢባል በቅን ልቡና መግባትን ጨምሮ የመድን የሚገባበት ጥቅም መኖር (insurable interest) ግድ ይላል፡፡ ስለሆነም ተገቢውን የሕግ ማዕቀፋ ከጉዳዩ አላማ ጋር ታይቶ ትርጉም ቢሰጠበት መልካም ነው፡፡

✳️ሌላው ደግሞ #የመልካም ሥራአፈፃፀም ዋስትና በመድን ድርጅቶች በሚሠጥበት ወቅት እስከ -------- ብር ተብሎ የሚገለፅ ሲሆን፣ በአሠሪዎች በኩል ያለው ሃሣብ ግን ሙሉ ክፍያው ስለተሠራው ስራም ሆነ ስለደረሠው ጉዳት መጠን ከግምት ሣይገባ እንዲከፈል የሚጠየቅበት ሁኔታ እና የቅድሚያ ክፍያ ለሥራ ተቋራጩ በሚሠጥበት ጊዜ ስለተጨማሪ እሴት ታክስ መታከል ወይም ያለመታክል ወጥ አሠራር ያለመኖርን በተግባር ማየት ይቻላል፡፡

✳️በመጨረሻም በአገራችን የዋስትና ገበያ የመንግስት ክትትል አናሳ መሆን ነው፡፡

🌟ለምሳሌ፡- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ሥራ ተቋራጩ በርካታ ሠራተኞችን በሥሩ ቀጥሮ ሊያሰራ ይችላል፡፡ ዳሩ ግን በሠራተኞች የማጭበርበር ወይም ብልሹ አሰራር ምክንያት ለሚደርስበት ጉዳት ማካካሻ የሚሆን የመተማመን ዋስትና (Fidelity bond) አለመኖር ተጠቃሽ ነው፡፡ ⚠️በዚህ ሳቢያ ብዙ ሥራ ተቋራጮች የመክስር አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡⚠️

🫵ማጠቃለያ

⏺ዋስትና በውል አፈጻጸም ወቅት እንደ ተጨማሪ(ደባል) የሚቆጠር ግዴታ ነው፡፡ ባለዕዳው በውሉ መሰረት ላለበት ግዴታ ማስከበሪያ የሚሆን ዋስ ጠርቶ የባለገንዘቡን ስጋት የሚቀንስበት መንገድ ነው፡፡ #ዋስትና ዓይነቱና መልኩ ይለያይ እንጂ ሁሉም ዓይነት ዋስትና ቀዳማዊው ግዴታ ባለመፈጸሙ የሚከተል ግዴታ ነው፡፡ #ዋስትና ከሚሰጠው ፈርጀ ብዙ ጥቅም አንጻር የሰው፣ የንብረት፣ የፍይናንስ እንዲሁም #የኮንስትራክሽን ብለን መፈረጅ እንችላለን፡፡ በእርግጥ #የኮንስትራክሽን\ዋስትና በአተገባበሩ በአንድ በኩል የሰው ዋስትና የሚመስል ይዘት ያለው ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኛውን #የኮንስትራክሽን_ዋስትና የሚሰጠው በፋይናንስ ተቋማት በመሆኑ ወሰኑን በወል መለየት አዳጋች ያደርገዋል፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የታወቁ የዋስትና ዓይነቶች የሚባሉት #የውል ማስከበሪያ፣ #የጨረታ_ማስከበሪያ፣ #የቅድሚያ_ክፍያ፣ #የዋናው_ገንዘብ_መያዣ እና #የጥገና_ብልሽት ዋስትናዎች ናቸው፡፡ ዳሩ ግን በተግባር አብዛኛውን ጊዜ የመንግስት ፕሮጀክቶች ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ውልን በሚያስተዳድሩና ጨረታን በሚመሩ ሰዎች ከሕግ የወጡ ሥራዎች ሲሰሩ ይስተዋላል፡፡ በተለይም የዋና ገንዘብ ዋስትና(retention) በጊዜዉ አለመመለስ አንዳንዴም የውሃ ሽታ ሆኖ መቅረት ተጠቃሽ ነው፡፡ ሌላው ጉልህ ችግር በሥራ ተቋራጮች ለሚደርሱ ከሠራተኛ ጋር የተያያዙ ጥፋቶችን ለመቀነስ #የመተማመኛ_ዋስትና(fidelity bond) ቢጀመር መልካም ነው፡፡ በመጨረሻም መንግስት የዋስትናን ገበያ ከፍተኛ ድጋፋ ቢያደርግ እና የግሉን ዘርፍ ቢያጠናክር አሁን ያለውን የዋስትና ሽፋን ያጠናክራል የሚል እምነት አለኝ፡፡

#ConstructionLaw

@etconp
👍21🙏5🕊1
ETCONp For Foreigner Contractors .pdf
346.8 KB
👉በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለሚሰማሩ ለውጭ ኣገር ዜጎች ስራፈቃድ ለማውጣት የድጋፍ ደብዳቤ የሚሰጥበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመርያ ቁጥር 29/2012

🖱የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር


@etconp
👍10
📢SAFETY FIRST

👉10 simple construction site safety rules

#ConstructionSafety

@etconp
👍10👌3
👉ውድ የ ቻናላችን ቤተሰቦች

⚡ለ ኮንስትራክሽን እቃ አቅራቢዎች እና ተያያዥ ስራ ወይም ድርጅት ያላቹ

⭐️ዛሬ አንድ የምስራች ይዘን መጥተናል ይህም ለ ሁሉም የግንባታ ግብዓት ዕቃ ማቴሪያል አቅራቢዎች እና ተያያዥ ስራ ያላቹ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ነፃ የ ማስታወቂያ አገልግሎት ለመስጠት አስበናል ስለዚህ ይህን ሀሳብ የምትስማሙ በ @Philemona7 ልታገኙን ትችላላቹ።

🙏እናመሰግናለን🙏

@etconp
❤5👍3