👉የቅድመ ክፍያ ዋስትና (Advance guarantee bond) እና የመልካም ስራ አፈፃፀም የዋስትና ቦንድ (performance bond) ልዩነት ምንድን ነው❓
🌟ስራ ተቋራጩ ሁለት ዓይነት ዋስትና ማለትም የቅድመ ክፍያ ዋስትና (Advance guarantee bond) እና የመልካም ስራ አፈፃፀም የዋስትና ቦንድ (performance bond) የሰጠ ሲሆን ተቋራጩ በግንባታ ውሉ መሰረት ግዴታውን መወጣት ባለመቻሉ ውሉ በአሰሪው ተቋርጧል።
🚧የግንባታ ስራው በመጓተቱ ምክንያት የግንባታ ስራ ውሉ በስራ ተቋራጩ ጉድለትና ጥፋት የግንባታ ስራ ውሉን አሰሪው ያቋረጠው ቢሆንም የስራ ተቋራጩ በዋስትና የወሰደውን የቅድመ ክፍያ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለህንፃ ግንባታ ስራው ያዋለው መሆኑ ከተረጋገጠ አሰሪው የቅድመ ክፍያ ዋስትናው ሊከፈለው አይገባም።
🖱ሆኖም ከቅድመ ክፍያ ዋስትና በተጨማሪ የመልካም ስራ አፈፃፀም የዋስትና ቦንድ (performance bond) ተሰጥቶ ከሆነ የግንባታ ውሉ በስራ ተቋራጩ ጉድለትና ጥፋት ሲቋረጥ አሰሪው ለመልካም ስራ አፈፃፀም የዋስትና ቦንድ በተሰጠው ዋስትና መሰረት ገንዘቡ ሊከፈለው ይገባል።
Via ሰ/መ/ቁጥር 116714
#ConstructionContract
@etconp

👍11
👉ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ BIM ቴክኖሎጂ ስልጠና ጀምሯል።
🚧ስልጠናውን ያስጀመሩት በኢንስቲትዩቱ የሰርተፊኬሽንና የምዘና ስርአት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አሰልጣኝ ወ/ሮ ቅድስት ማሞ ናቸው::
▶️ወ/ሮ ቅድስት ማሞ እንደተናገሩት ይህ በአርባምንጭ የሚሰጠው ስልጠና ለ24ኛ ዙር ሲሆን ለበጀት አመቱ ደግሞ 6ኛ ዙር ነው።
▶️ስልጠናውን 7 ዩኒቨርሲቲዎች እንዳገኙና አርባምንጭም 8ኛው እንደሆነ አስረድተው በ7 ዩኒቨርሲቲዎች 300 ተማሪዎችን ማሰልጠን ተችሏል ብለዋል::
🌟ስልጠናው ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚሰጥበት ዋናው አላማ በስርአተ ትምህርት ውስጥ ማካተት እንዲቻል እና በቢም ቴክኖሎጂ የሰለጠነና ብቁ ባለሙያ ለማፍራት መሆኑን ተናግረዋል::
🌟ለ18 ቀን የሚሰጠው የቢም ቴክኖሎጂ ስልጠና ዩኒቨርሲቲው ከሚያሰራው የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት እና ከቴክኖሎጂ ፋኩሊቲ የተመለመሉ መምህራን በአጠቃላይ 32 ሰልጣኝ እየተከታተለ ይገኛል::

👍9❤6
The number of cement bag required for 10 cum of PCC 1:2:4 is
Anonymous Quiz
33%
53
36%
63
21%
73
10%
83
❤16💯6👍4
👉WHAT IS QUANTITY SURVEYING
➡️Quantity surveying means generally materials take off preparation and measuring of quantities Such as length,Area,Volumes and Pcs for Construction projects
🏷Quantity Surveying can be cover different tasks like
*⃣preparation of specification.
*⃣Taking measurements of Construction works.
*⃣preparation of approximate cost estimate at the very early stage of the project.
*⃣preparation of detail cost estimate at different stages.
*⃣Valuation of property.
🏷PURPOSE OF QUANTITY SURVEYING
⏺Assist the client to have an accurate estimate of volume of work as well as the required budget.
⏺to assist in the accurate preparation of tenders,by providing uniform Measuring of quantity.
⏺To give an accurate checklist of work accomplished.
⏺To assist in the certification of payments.
⏺To give insight into the required variation work amounts.
#QuantitySurveying

👍22
👉በመዲናዋ የሚገኙ ከ30 ሺህ በላይ ግንባታዎች ላይ የጥራትና ቁጥጥር ሥራ እየተሠራ ነው
🌟በመዲናዋ በሂደት ላይ የሚገኙ ከ30ሺህ በላይ ግንባታዎች ላይ የጥራት ደረጃና የደህንነት ቁጥጥር እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።
🚧በየመንገዱ የተሰቀሉ ከ45ሺህ በላይ ሕገወጥ ማስታወቂያዎች ተነስተው ወደዲጂታል ሥርዓት እንዲገቡ አቅጣጫ ተቀምጧል።
▶️የባለስልጣኑ የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ከማል ጀማል (ኢ/ር) ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ በአጠቃላይ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ማዕከል በተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት አማካኝነት ከ30ሺህ በላይ ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛል።
▶️ግንባታዎቹ ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በተቋም ደረጃ ልዩ እቅድ ተዘጋጅቶ ክትትል እየተደረገ ነው ያሉት ኢንጂነር ከማል፤ የግንባታ ጥራትና ደህንነት ጥንቃቄዎችን ከግምት ውስጥ ባስገባ መንገድ የፍቃድ አሰጣጥና የክትትል ሥርዓቱ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማና በማዕከል ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። የህንጻ ግንባታዎች በተዘጋጀላቸው ዲዛይንና ቦታ ላይ መከናወናቸውን የሚከታተል ክፍል መኖሩንና፤ ማንኛውም አልሚ የግንባታ ደህንነት መሟላቱን አረጋግጦ ህንጻውን ማጠናቀቅ እንዳለበት አመላክተዋል።
⏺ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተሠራ ባለው ሥራ የማስታወቂያ፣ የመሰረተ ልማትና የሌሎችንም ግንባታዎች ለመቆጣጠር በልዩ ሁኔታ ከጥቅምት ወር ጀምሮ እቅድ ወጥቶ ከማዕከል እስከ ወረዳ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል። በዋና ዋና መስመሮች የከተማ ገጽታን የሚያበላሹ የአጥር ግንባታዎች እንዲስተካከሉ፣ የህንጻ ሽፋኖች ደረጃቸውን እንዲጠብቁና በግንባታ ወቅት የሰራተኞች ደህንነት እንዲጠበቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
🖱ኢንጂነር ከማል እንዳመለከቱት፤ የህንጻ ሽፋን፣ የአጥር ደረጃ፣ የግንባታ ግብዓትና ተረፈ ምርት በመንገድ ላይ የሚያስቀምጡና በህንጻ ደህንነት ላይ ችግር የተገኘባቸው አልሚዎች፣ የግንባታ አማካሪዎችና ኮንትራክተሮች ላይ የማስተካከያ ርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።
☄የግንባታ ግብዓቶች በእግረኛ መንገዶች ላይ በሚያስቀምጡ በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ያደረሱ ሦስት ሺህ የሚጠጉ አካላት ላይ ርምጃ በመውሰድ ግብዓቶቹን የማንሳት ሥራ ተከናውኗል ሲሉ አስረድተዋል።
☄በተጨማሪ የከተማዋን ውበት በማበላሸት በየመንገዱ የተሰቀሉ ከ45ሺህ በላይ ማስታወቂያዎች እንዲነሱና በዋና ዋና መንገዶች ላይ በዲጂታል ማስታወቂያዎች እንዲተኩ መደረጉን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
🚧በመንገድ ዳር በተለያዩ ተለጣፊና ተንጠልጣይ መንገዶች የሚሰቀሉ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ማስታወቂያዎች ህጋዊነታቸው ያልተረጋገጡና የመንገድ ደህንነት ህግን ያላከበሩ በመሆናቸው በቀጣይም የማስተካከሉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በከተማዋ ዋና ዋና አካባቢዎች የተሰቀሉ ዲጂታል የማስታወቂያ ቦርዶች ዘመናዊነትን የተላበሱና በውበትም የተመረጡ በመሆናቸው ማንኛውም ማስታወቂያ ያለው አካል ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመነጋገር ወደዘመናዊ ሥርዓቱ መግባት እንደሚችል አስረድተዋል።
Via ኢ ፕ ድ

👍9❤1
👉የአፄ ዮሃንስ 4ኛ ኤርፖርት መልሶ ግንባታ በግንቦት ወር መጨረሻ ተጠናቆ መደበኛ አገልግሎት ይጀምራል ተባለ
🚧በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳው የአክሱም አፄ ዮሃንስ 4ኛ ኤርፖርት ከአራት ወራት በኋላ ጥገናው ተጠናቆ በግንቦት 25 2016 ዓ/ም ይከፈታል ሲልም 104.4 ኤፍ ኤም መቐለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመሰረተ ልማት ኃላፊ አቶ አብይ ዘበነን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
🌟ባለስልጣኑ ይህን ያሉትም አየር ማረፊያውን በጎበኙበት ወቅት ከፕሮጀክቱ ሰራተኞች እና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ሲወያዩ እንደሆነም ተገልፆል።

👍7❤2
The function of king post in king post roof truss is
Anonymous Quiz
52%
To support the framework of the roof
19%
To receive the ends of principal rafter
10%
To prevent the walls from spreading outward
18%
To prevent the tie beam from sagging at this centre
❤12👍5😢1
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ
፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን
፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን
፦ankerbolt
፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን
፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን
፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን
አድራሻችን
ቁ.1 መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706
ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።

👍5❤2👏1🏆1
👉የግንባታ ዲዛይን ለተቋራጭ ይሰጣልን?
🌟አንድ ግንባታ ዲዛይን በአማካሪ ድርጅት ባለሙያዎች ከተሰራ በኋላ ሙሉ የዲዛይን ሰነዱ በወረቀት ቅጅ (hard copy) እና በሶፍት ቅጅ (soft copy) ለባለቤቱ ይሰጣል።
🚧ነገር ግን በ’ ከተማ ልማት እና ሥራዎች ሚኒስቴር አዋጅ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 1 (Ministry Of Works And Urban Development Standard Conditions Of Contract Clause 6
⏺(1) ‘Custody of Drawings’) መሰረት፣ የግንባታ ዲዛይኑ የግንባታ ክትትል ለሚያከናውነው ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (supervision engineer) በሶፍት ቅጅ (soft copy) ሊሰጥ የሚችል ቢሆንም ለግንባታ ተቋራጩ (contractor) መሰጠት ያለበት ሁለት
⏺(2) የወረቀት ቅጂዎችን ሲሆን ያለምንም ክፍያ በባለቤቱ ወጪ መዘጋጀትና ለተቋራጩ መሰጠት አለባቸው።
▶️የግንባታ ተቋራጩ የሚፈልገው ተጨማሪ ቅጂዎች ካሉ በራሱ ወጪ እንዲባዙለትና እንዲሰጡት ማድረግ ይችላል፣ ነገር ግን ያለባለቤቱ ፍቃድ ማባዛትና ለሦስተኛ (ሌላ) ወገን አሳልፎ መስጠት ተቋራጩን ያስጠይቀዋል። ግንባታው ሲጠናቀቅ ተቋራጩ በውሉ መሠረት በቅጂ የቀረቡትንና የተረከባቸውን ሁሉንም ዲዛይኖች ለመሐንዲሱ (Engineer) እንዲመልስ በሕግ ግዴታ አለበት።
#ConstructionLaw

👍15❤2🙏2
👉ማስታወቅያ
🫵ለተከበራችሁ የማኅበራችን አባላት በሙሉ!
መንግሥት በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ አጋርነት (Public Private Partnership) የመኖሪያ ቤት ልማት ፕሮጀክቶችን መከናወን እንደሚፈልግና በዚህ ረገድም እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ሲነገር መቆየቱ ይታወቃል፡፡
አሁንም በዚህ የአጋርነት የልማት ማዕቀፍ ሊሳተፉ የሚችሉ ሥራ ተቋራጮችን በስፋት እንዲሳተፉ ማስፈልጉን በመጥቀስ በነገው ዕለት ማለትም ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በጉዳዩ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡
የውይይቱን የሚካሄድበት ቦታ እና ሰዓት እንደተገለፀልን የምናሳውቅ መሆኑን እየገለፅን በዚህ ዓይነቱ የልማት መርኃ-ግብር ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱ ያላችሁ የማኅበራችን አባላት ግን ፍላጎታችሁን ከወዲሁ በዚሁ ገፅ ላይ ለማኅበራችን ፅ/ቤት እንድታሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር

🙏10👍5❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉ይህ በዚህ ቪድዮ የምታዪት ግንብ የተገነባው ጃፓንን ከሱናሚ አደጋ ለመታደግ ታስቦ ነው።
🚧The great wall of Japan to protect Japan against tsunamis.

❤7👍4👌2😢1
👉በ2024 ሊጎበኙ የሚገባቸው ምርጥ ከተሞች የትኞቹ ናቸው?
🌟በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ቱሪስቶች ሊጎበኟቸው የሚገቡ የዓለማችን 10 ምርጥ ከተሞችን የብሪታንያው ታይም አውት ኩባንያ ይፋ አድርጓል፡፡
🚧በዚሁ መሠረት÷ ኒውዮርክ፣ ኬፕታውን፣ በርሊን፣ ለንደን፣ ሊቨርፑል፣ ማድሪድ፣ ሜክሲኮ፣ ቶኪዮ፣ ሮም እና ፖርቶ በቅደም ተከተላቸው መሠረት በ2024 ሊጎበኙ የሚገባቸው ምርጥ ከተሞች ተብለው ተመርጠዋል፡፡
🖱የምርጥ ከተሞችን ምርጫ ለማከናወንም በተለያዩ የዓለማችን ከተሞች የሚኖሩ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎችን እና ዓለም አቀፍ ፀሐፍትን አነጋግሬያለሁ ብሏል አውት ኩባንያ፡፡
☄የዓለም ምርጥ ከተሞች ምርጫ የተከናወነበት ዋና ዓላማም ቱሪስቶች ከተሞችን አንዲጎኙ ለማነሳሳት ነው ተብሏል፡፡
✨ኩባንያው ይፋ ባደረገው መሰረት ኒውዮርክን ቀዳሚ ከተማ አድርጓታል
✨በተጨማሪም በከተማዋ የሚዘወተሩ ልዩ ልዩ ምግቦች፣ ዕድሜ ጠገብ ሕንጻዎች፣ ታሪካዊ ቦታዎች፣ ዕድሜ ጠገብ ሙዚዬሞች፣ ቴአትር ቤቶች እና ባሕላዊ ትዕይንቶች መኖር ለኒው ዮርክ በግንባር ቀደም ተመራጭነት የራሳቸውን ሚና አበርክተዋል፡፡
🖱በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ልትጎበኝ የሚገባት ከተማ ተብላ በሁለተኛነት ለተመረጠችው ኬፕታውንም÷ በባሕር መከበቧ፣ ተራራማ አካባቢ ላይ መገኘቷ እና ማራኪ የተፈጥሮ ገፅታ መላበሷ ውበት ሆነውላታል፡፡
🚧የኬፕታውን ባሕላዊ ጨዋታዎች፣ አለባበሶች፣ የምሽት ቴአትር ቤቶች፣ ሬስቶራንቶች፣ የወይን እርሻዎችም ለከተማዋ መመረጥ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተገልጿል፡፡
🚧በሌላ በኩል የበርሊን ግንብ፣ የሪችስታግ ሕንጻ፣ የብራንደንበርግ በሮች፣ የአይሁዶች ሙዚዬም እና ሌሎች ታሪካዊ ሥፍራዎች ውበት ያላበሷት የጀርመኗ በርሊን ልትጎበኝ የሚገባት ምርጥ ከተማ ተብላ በሦስተኛ ደረጃ ላይ እንድመረጥ አድርገዋታል፡፡

👍10😁1
✋ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ዛሬ እስቲ ይቺ ከታች ያለችው ጥያቄ እንወያይባት
👉አንዳንድ የግንባታ ስራ ውሎች ላይ የፕሮጀክት የመዘግየት የጉዳት ካሳ (Liquidated Damage) ለማስላት 0.1% x የቀሪ ሰራዎችን (Remaining Works) የሚል ነገር ይካተታል።
🚧ለእንደነዚህ አይነት ውሎች የውል ጊዜያቸው ካለቀ በኋላ Interim payment ቢጠየቅ Liquidated Damage እንዴት ሊሰላ ይችላል?
🚧የውል ጊዜው ካለቀ በኋላ የተስሩ እና በክፍያ ሰነዱ ላይ በተካተቱት ስራዎች ላይ ብቻ ነው ወይስ አጠቃላይ የውል ጊዜው ካለቀ በኋላ በተሰሩትና ባልተሰሩትም (ወደፊት በሚሰሩት) ስራዎች ጭምር በማካተት?
#ConstructionLaw
📩ሀሳብ አስተያየትዎ ከታች ባለው ሊንክ ፃፉልን እና እንወያይበት
.
http://t.me/COTMp

Telegram
ETCONp Discussion
📩ለማነኛውም ሀሳብ እና አስተያየት @Philemona7
✌️ይህ የ @etconp መወያያ ግሩፓቹ ነው።
✋This is discussion group of @ETCONpWORK
.
🔖ማሳሰብያ ...
.
⚡️ግሩፑ ላይ ማነኛውም ከ ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ውጪ መለጠፍ በፍፁም አይፈቀድም!
@ETCONpBOT ፃፉልን እናመሰግናለን🙏

❤6🕊2
👉ስኬል/Scale/
➡️ዛሬ ለ አንድ የህንፃ ፕላን ለማንበብ ከሚጠቅሙን አንዱ የሆነውን ስኬልን እናያለን።
▶️አርክቲክቱ የህንፃው ፕላን ዲዛይን ሲያደርግ ከሚገነበው ቤት እኩል መጠን ያለው አድርጎ መስራት አይችልም።
▶️በዚህም የተነሳ በስኬል አሳንሶ ሶፍትዌር(AutoCAD) ላይ ዲዛይን ያደርገውን በወረቀት ፕሪንት ተደርጎ በተቀመጠው ስኬል መሰረት ህንፃው ይገነባል።
➡️ለተለያየ አላማ የተለያዩ የስኬል አይነቶችን ሊጠቀም ቢችልም ለ ህንፃ እና መንገድ ግንባታ በብዛት የሚጠቅሙ የ ስኬል አይነቶች የሚከተሉት ናቸው:-
🚧1. 1:200 ሲነበብ አንድ ለሁለት መቶ ሲሆን ትርጉሙም 1ሚ.ሜ ፕላን ላይ 200 ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።
🚧2. 1:100 ሲነበብ አንድ ለአንድ መቶ ሲሆን ትርጉሙም 1ሚ.ሜ ፕላን ላይ 100ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።
🚧3. 1:50 (አንድ ለ ሃምሳ) ትርጉሙ 1 ሚ.ሜ ፕላን ላይ 50 ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።
🚧4. 1:20 (አንድ ለ ሃያ) ትርጉሙ 1ሚ.ሜ ፕላን ላይ 20ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።
#Architecture

👍23❤2
Demolition
Building demolition is the process of dismantling structures along with the materials used in the construction of the property. A building is demolished for various reasons such as: it’s past its span of serviceability, the structural integrity is compromised, parts of the establishment will need to be refurbished to improve its quality and value.
Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=OGQ5ZDc2ODk2ZA==
Facebook:- https://www.facebook.com/etconp?mibextid=LQQJ4d

👍13
👉ኦቪድ ቤቶች ባንክ ወደ ስራ ሊገባ ነው ተባለ
ኦቪድ ቤቶች ባንክ አክሲዮን ማህበር ወደስራ ሊያስገባው የሚያስችለውን የአክሲዮን ሽያጭ በስካይላይት ሆቴል ባካሄደው መርሃ ግብር አስጀምሯል።
ባንኩ 20 ቢሊዮን ብር ካፒታል ለማሰባሰብ የሚረዳውን የ20 ሚሊዮን የአክሲዮን ሽያጭ ያቀረበ ሲሆን የአክሲዮን ሽያጩ ሥራ እንዲጀምር የሚያስፈልገውን ካፒታል ለማሰባሰብ የሚረዳው መሆኑ ተገልጿል።
ከአክስዮን ሽያጭ የሚሰበሰበው ገንዘብ ባንኩ በመላው ኢትዮጵያ የቤትና የቤት ብድር አቅርቦትን የማስፋፋት ተልዕኮውን እንዲወጣ ያስችለዋል ተብሏል።
የባንኩ ዝቅተኛ የግለሰብ አክሲዮን ግዥ 200,000 ብር ፣ ከፍተኛው 1 ቢሊዮን ብር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሥራ ለመጀመር 5 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የሚያስፈልገው እንደሆነ ተገልጿል።
ኦቪድ ኮንስትራክሽን በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ 60,000 ቤቶችን ለማልማት ያቀደ ሲሆን ባንኩ እቅዱን ለማሳካት ትልቅ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።
የቤቶቹ ግንባታ 450 ቢሊዮን ብር ይፈጃል የተባለ ሲሆን በኦቪድ ኮንስትራክሽንና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ70፡30 የሽርክና ስምምነት መሰረት የሚገነባ መሆኑ ተጠቁሟል።
የከተማ አስተዳደሩ በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ለልማት የሚውል 460 ሄክታር የሚጠጋ መሬት ማዘጋጀቱም ነው የተገለፀው።

👍16❤2
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ
፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን
፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን
፦ankerbolt
፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን
፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን
፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን
አድራሻችን
ቁ.1 መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706 ወይም @heavenic1 ፃፉልን

👍7❤1
👉የጠቃሚነት ተሳትፎ (Utilization Factor)
🚧የግንባታ ዋጋ በሚወጣበት ጊዜ የጠቃሚነት ተሳትፎ (Utilization Factor) የሚባል ጽንሰ ሀሳብ አለ።
🌟የጠቃሚነት ተሳትፎ (Utilization Factor) ማለት “አንድ ሰው ወይም ማሽን በተመሳሳይ ሰዓት ስንት ሥራዎች ላይ ሊሳተፍ ይችላል?” የሚለውን ጥያቄ መሰረት አድርጎ የሚሰላ የዋጋ ማባዣ መረጃ ሲሆን ብዙ ጊዜ በሰው ኃይል ላይ የሚተገበር ነው።
🖱ለምሳሌ፦ አንድ ፎርማን በአንድ ፕሮጀክት ላይ የሚሰሩ የቁፋሮ፣ የድንጋይ ግንባታ፣ የአፈር ሙሌት፣ የፌሮ ሥራዎችን ሊቆጣጠር ይችላል።
⏺በዚያ ሰዓት ፎርማኑ አራት ሥራዎችን እየተቆጣጠረ ስለሆነ የጠቃሚነት ተሳትፎው (Utilization Factor) ለአራት ሥራዎች ነው ማለት ነው።
▶️ይህ ማለት ለቁፋሮ፣ ለአፈር ሙሌት፣ ለፌሮ ሥራ፣ ለድንጋይ ግንባታ ሥራዎች የፎርማን አስተዋጽኦ ለእያንዳንዳቸው ያላቸው 25%፣ 25%፣ 25%፣ 25% ነው ማለት ነው። በዚህ አግባብ ለአንዱ ሥራ ዋጋ በሚወጣበት ጊዜ የፎርማን አስተዋጽኦ በ25% ይባዛል ማለት ነው።
🖱ለምሳሌ፦ አንድ ፎርማን በሰዓት 75 ብር የሚከፈለው ቢሆን እና የቁፋሮ ሥራን ዋጋ እያሰላን ቢሆን በቁፋሮ ሥራ የዋጋ ስሌት ውስጥ የፎርማኑ በሰዐት ይከፈለው የነበረው 75ብር በ25% (0.25) ይባዛል ማለት ነው።
⏺ቀሪዎቹ 75% ክፍያዎች በሌሎቹ ሦስት ሥራዎች ሂሳብ ስሌት ውስጥ የሚካተቱ ይሆናል።
⏺በተመሳሳይ ሰዓት አንድ ሥራ ላይ ብቻ የመሳተፍ ዕድል የሚኖራቸው ሰራተኞች ላይ ግን የጠቃሚነት ተሳትፎው (Utilization factor) ሁልጊዜ አንድ (1) ነው።
🖱ለምሳሌ፦ የቁፋሮ ሰራተኛ በአንድ ጊዜ ቁፋሮ ብቻ እንጂ እየቆፈረ እያለ ሌላተጨማሪ ሥራ ሊሰራ አይችልም።

👍35❤5